YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኢትዮጵያ በማዕድን ኢንቨስትመንት ማራኪነት በአለም የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀመጠች!

በካናዳው "Fraser Institute" የተዘጋጀው የ2024 ዓመታዊ የማዕድን ኩባንያዎች ጥናት፣ ኢትዮጵያ በማዕድን ኢንቨስትመንት ማራኪነት ደረጃ ከአለም መጨረሻ ላይ መቀመጧን አመላክቷል። ጥናቱ 82 ሀገራትን ገምግሞ ለኢንቨስትመንት ማራኪ የሚያደርጉ የፖሊሲ መረጋጋት እና ግልጽነት ላይ ችግሮች እንዳሉ በመጠቆም ኢትዮጵያን ከሁሉም በታች አስቀምጧታል።

የኢንቨስትመንት ማራኪነት ደረጃው የሀገሪቱን የጂኦሎጂካል አቅም ከመንግስት የፖሊሲ ማዕቀፎች ጋር በማጣመር የሚሰላ ነው።ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በሀብት የበለፀገች ብትሆንም፣ ደካማ የፖሊሲ አሰራር ኢንቨስተሮችን እያራቀ መሆኑን ጥናቱ ያሳያል።

ጥናቱ እንደ የግብር አወሳሰን፣ የህግ ስርዓት እና የፖለቲካ መረጋጋት ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮችን የሚገመግም ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በዚህ ምድብ ውስጥ ካሉ 10 ዝቅተኛ ደረጃ ከተሰጣቸው ሀገራት ውስጥ አንዷ ነች።

የጥናቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹት፣ የማዕድን ሀብት መሠረታዊ ቢሆንም፣ 40% ያህሉ የኢንቨስትመንት ውሳኔዎች የሚወሰኑት በፖሊሲ አሰራር ላይ ነው። ይህም ግልፅ ደንቦች፣ የፖለቲካ መረጋጋት እና ፍትሃዊ የህግ ማዕቀፎች የማዕድን ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆኑ ያመለክታል።ሪፖርቱ ኢትዮጵያ የፖሊሲ ክፍተቶቿን ካልሞላች፣ ኢንቨስትመንቶች ግልጽ እና ባለሀብት ወዳድ ወደሆኑ ሀገራት ሊዞሩ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
😁5131👍4👀4👎3😭1
Forwarded from YeneTube
7 ሳይቶችን በጥራት በታማኝነት አስረክበናል::
ለንግድ ሱቅ ፈላጊዎች በሙሉ

📍 ፒያሳ ከሚኒልክ አደባባይ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር የሚወስደው መንገድ ላይ የንግድ ሱቆችን መሸጥ ጀምረናል።
👉 2 ቤዝመንት ያለው
👉ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
👉በ1 ዓመት ተኩል የምትረከቡት

👉ምድር ቤት
20 ካሬ= 7ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2.8ሚሊዮን ብር
👉1ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 5.5 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2 ሚሊዮን ብር
👉2ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.8 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.5 ሚሊዮን ብር
👉3ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.2 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.2 ሚሊዮን ብር
👉4ኛ እና 5ኛ  ፎቅ
20 ካሬ= 3.9 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 900 ሺ ብር
👉ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፈል።

ለበለጠ መረጃ
09-76-19-58-35

Telegram username
@Ruthtemersales

Whats app
Message Temer properties on WhatsApp. https://wa.me/251976195835
6
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ጀልባ ተገልብጦ 68 ኢትዮጵያዊያን በየመን አቅራቢያ ህይወታቸው አለፈ!

154 ሰዎችን ጭና ቀይ ባህርን እያቋረቀጠች የነበረች ጀልባ ተገልብጣ 68ቱ ሲሞቱ የተቀሩትም እስካሁን አልተገኙም። እንደ ዶቸ ቨለ ዘገባ በጀልባዋ ላይ የነበሩት ሁሉም ኢትዮጲያዊያን ዜጎች የነበሩ ሲሆን ፍለጋው አሁንም እንደቀጠለ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
😭909
በሀገራዊ የምክክር ሂደት ውስጥ የተሳታፊዎች ደህንነት ስጋት ላይ ነው ተባለ!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት፣ በሀገራዊ የምክክር ሂደት ውስጥ የተለያዩ ችግሮች መከሰታቸውን ገልጿል። ከእነዚህም መካከል፣ የውይይት ተሳታፊዎች ደህንነትን የሚመለከቱ፣ የአካታችነት ችግሮች እና የግልጽነት ጥያቄዎች በዋናነት ተጠቅሰዋል።

በሪፖርቱ መሠረት፣ በብዙ ክልሎች የተካሄዱ ውይይቶች ላይ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን በነጻነት ሲገልጹ ቢቆዩም፣ ፈቃድ ሳይጠይቁ ምስል እና ቪዲዮ የሚቀርጹ ሚዲያ ነን ባዮች መኖራቸው የብዙዎችን ስጋት ፈጥሯል።

በተለይም በአማራ ክልል አንዳንድ ተሳታፊዎች፣ የታጣቂ ኃይሎች በምክክሩ መሳተፋቸውን በመገናኛ ብዙኃን ካዩ ሊያጠቋቸው እንደሚችሉ በመፍራት ፊታቸውን በመሸፈን እና ሀሳባቸውን ከመግለጽ መቆጠባቸውን አብራርተዋል።

ኢሰመኮ በሪፖርቱ እንደጠቆመዉ አንዳንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኮሚሽኑን ገለልተኝነት በመጠራጠር ከሂደቱ ራሳቸውን አግልለዋል። በተጨማሪም፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ውስጥ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ከሚገኙ አካባቢዎች ተሳታፊዎችን ማካተት ባለመቻሉ፣ የምክክር ሂደቱ ሁሉን አቀፍ እንዳይሆን አድርጎታል ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም በአማራ ክልል ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በዋናው ምክክር ላይ እንደሚሳተፉ ሲነገር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ግን የማይሳተፉበት ምክንያት አለመገለጹ የሂደቱን ግልጽነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥል እንደሆነ ተገልጿል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
20👎2👍1😁1
የአፍሪካ ህብረት ከ50 በላይ አል-ሸባብ ታጣቂዎች በደቡባዊ ሶማሊያ መገደላቸውን አረጋገጠ!

የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ(አውሶም) በሶማሊያ የመንግስት ኃይሎች የሚደገፉት ወታደሮቹ ባሳለፍነው አርብ በደቡባዊ ሶማሊያ በባሪሬ ከተማ በተካሄደ ከባድ ውጊያ ከ50 በላይ የአል-ሸባብ አባላትን መግደላቸውን አስረጋገጠ።

አውሶም ከሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በሰጠው መግለጫ፤ “በባሪሬ በተልዕኮው ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል” የሚሉ የሚዲያ ዘገባዎችን አስተባብሏል።

"አውሶም ኃይሎቹ ከሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ኃይሎች (SNAF) ጋር በመተባበር የባሪሬ ከተማን መልሶ ለመቆጣጠር ሐምሌ 25 ቀን ጥቃት መጀመሩን ግልጽ ማድረግ ይፈልጋል" ሲል የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ(አውሶም) ገልጿል።

አውሶም ይህን ያለው፤ አል-ሸባብ በባሪሬ በተካሄደው ከባድ ውጊያ፤ "የአፍሪካ ህብረት የወታደሮች ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን መውደማቸውን እና የአውሶም ወታደሮች ማፈግፈጋቸውን" መግለጹን አስመልክቶ በገዳዩ ላይ ምላሽ ሲሰጥ ነው።

“የጋራ ወታደራዊ ዘመቻው ለአሸባሪው ቡድን ከፍተኛ ኪሳራ አስከትሏል፣ ከ50 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች ሲገደሉ ሌሎች በርካቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል” ሲል የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) ማስታወቁን ዥንዋ ዘግቧል።ከሞቃዲሾ በስተደቡብ ምዕራብ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ባሪሬ ከተማ፤ በሸበሌ ወንዝ ዳርቻ ከሚገኙ ስትራቴጂካዊ አካባቢዎች አንዷ ነች።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
15
ከፍተኛ የግብር ጫና ዜጎችን ከመደበኛ ሥራ እያራቃቸው ነው ሲል አይኤምኤፍ አስጠነቀቀ!

በኢትዮጵያ ያለው የግብር ስርዓት፣ በተለይም በዝቅተኛ ገቢ ላይ ባሉ ግብር ከፋዮች ላይ የሚጣለው ከፍተኛ የግብር ተመን፣ ዜጎች ወደ መደበኛ የስራ ዘርፍ እንዳይገቡ ተስፋ እያስቆረጣቸው መሆኑን የአይኤምኤፍ ሪፖርት አመለከተ።

የአለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ ) ባወጣው የቅርብ ጊዜ የግብር ግምገማ ላይ እንዳመለከተው፣ የኢትዮጵያ የግብር ስርዓት አወቃቀር በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ ላይ ባሉ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የግብር ተመን የሚጥል ሲሆን፣ ይህም ድርጅቶችና ሰራተኞች መደበኛ ባልሆነው የንግድ መስክ ውስጥ እንዲቆዩ ሊያደርግ ይችላል። ይህ ደግሞ ለልማት የሚውለውን የግብር ገቢ እንዲቀንስ ያደርጋል።

ሪፖርቱ አክሎም፣ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት እያሳየች ብትሆንም፣ የግብር አሰባሰቧ ከሰሃራ በታች ካሉ አገሮች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ መሆኑን ጠቅሷል። ከገቢና ትርፍ የሚገኘው የግብር ገቢም ቢሆን ደካማ መሆኑ ተጠቁሟል።

ካፒታል የተመለከተዉ የአይኤምኤፍ ዘገባ እንደሚያሳየው፣ ኢትዮጵያ በብቃት የግብር ስርዓቷን ብታስተካክል ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርቷ (GDP) እስከ 17% የሚደርስ ገቢ ማግኘት ትችል ነበር፤ አሁን የምታገኘው ግን 8% ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በገንዘብ አሰባሰብ እና አጠቃቀም ላይ ትልቅ ክፍተት መኖሩን ያሳያል።

ሪፖርቱ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የግብር አሰባሰብ መሰረትን በማስፋፋት፣ ከአላስፈላጊ የግብር ነጻነቶች በመውጣትና የግብር አክባሪነትን በማሻሻል ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን ማስቀጠል እንደሚቻል አሳስቧል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
27👍24
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን ጀልባ መስጠም አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን የተሰማውን ሃዘን ገለጸ!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ በደረሰው የሞት አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል፡፡ሚኒስቴሩ የደረሰውን አደጋ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እያጣራ መሆኑን ለፋና ዲጂታል አስታውቋል፡፡

በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ ለሕልፈት ለተዳረጉ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝቷል፡፡መንግሥት ዜጎች በተለያዩ ሀገራት በሕጋዊ መንገድ ተንቀሳቅሰው መሥራት እንዲችሉ ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶችን በማከናወን በርካታ ዜጎችን የዕድሉ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ሚኒስቴሩ ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ብቻ የውጭ ሀገራት የሥራ ሥምሪት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና ከሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁም አሳስቧል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
😁1711👎10👍2😭2
የቀድሞው የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በተመድ የአፍሪካ ሕብረት ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው ተሾሙ!

የቀድሞው የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በዓለም የንግድ ድርጅት (ጄኔቫ) የአፍሪካ ሕብረት ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው ተሹመዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ዶ/ር ግርማ አመንቴን ለዚህ ትልቅ ኃላፊነት ለመሾም ያሳለፉትን ውሳኔ በአድናቆት እንደምትመለከተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

ውሳኔው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች አፍሪካን በመወከል ለምትጫወተው ሚና ሕብረቱ ያለውን ትልቅ ግምት የሚያመላክት ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢቢሲ ገልጿል።

ዶ/ር ግርማ አመንቴ የካበተ የአመራር ልምዳቸውን በመጠቀም የተጣለባቸውን ትልቅ ኃላፊነት በላቀ ብቃት እንደሚወጡት ያለውን ሙሉ እምነትም ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
33😁12
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
በ 25% ዲስካውንት ለገበያ አቅርበናል!

📌 ፒያሳ ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት        

👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል  
መገልገያዎች    
👉 ሦስት ሊፍት   
👉 ባለ 3 ፎቅ የመኪና ማቆሚያ ቦታ    
👉 ቴራስ    
👉  ያልተገደበ የውሃ አቅርቦት    
👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር

📌 የካሬ አማራጮች
👉ባለ 1መኝታ - 63 ካሬ
👉ባለ 2 መኝታ - 86  እስከ 103 ካሬ
👉ባለ 3 መኝታ - 132  እስከ 146 ካሬ        

👉1 መኝታ 63ካሬ=      
        10% ቅድመ ክፍያ 693,000 ብር       
                   ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር 
👉2መኝታ 86 ካሬ       
          10%ቅድመ ክፍያ 946,000 ብር       
                  ሙሉ ክፍያ 9,460,000 ብር       
👉3መኝታ 114 ካሬ     
           10%ቅድመ ክፍያ 1,219,800 ብር     
                   ሙሉ ክፍያ 12,198,000 ብር  

ለበለጠ መረጃ 
☎️ +251976195835

Telegram username
@Ruthtemersales

What's app
https://wa.me/251976195835

TEMER PROPERTIES
Create | Construct | Deliver
#TemerProperties #Temerrealestate
6
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘሁ አለ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት በዓመቱ 6 ዓለም አቀፍ ጣቢያዎች መክፈት የቻለው አየር መንገዱ 13 የተለያዩ አውሮፕላኖች ወደ ስራ አስገብቷል።

በ2017 በጀት ዓመት 19 ሚሊየን መንገደኞችን አየር መንገዱ ማጓጓዝ ሲችል በጭነት አገልግሎት ደግሞ 785 ሺህ 323 ቶን በላይ ካርጎ እንዳጓጓዘም ጨምረው አስታውቀዋል።

ከመንገደኞችና ዕቃ ጭነት አገልግሎትም 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱንም አስታውቀዋል።እንደ ኤፍ ኤም ሲ ዘገባ አሁን ላይ የአየር መንገዱ የሀገር ውስጥ በረራ መዳረሻዎች 21 መሆናቸውን እና በቅርቡ የሚጠናቀቁ የ5 መዳረሻዎች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን አቶ ጣሰው ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
19👎6🔥1😁1
በኤርትራ የተያዘብኝን ገንዘብ በፍርድ ቤት ለማስመለስ ያረኩት ጥረት አልተሳካም ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት በኤርትራ አየር ክልል እየበረረ መሆኑን ገልጾ፤ በኤርትራ ያልተከፈለው የተየዘበት ገንዘብ ግን እስከአሁን እንዳልተመለሰ አስታውቋል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2017 በጀት ዓመት ሪፖርቱን አስመልክቶ፤ በዛሬዉ ዕለት ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህ በዛሬው መግለጫ ላይ አየር መንገዱ ያለፈው በጀት ዓመት ከሌሎች ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ለየት ያለ ዓመት መሆኑ ተገልጿል። መግለጫውን የሰጡት የአየር መንገዱ ዋና ስሥ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፤ አየር መንገዱ በተለይም በዓለም ተለዋዋጭ የፀጥታ ስጋት ተፅዕኖ ውስጥ መውደቁን ገልጸዋል።

የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሥመራ እንዳይበር ባገደ ሰሞን፤ አየር መንገዱ 'ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በፊት ያልከፈለኝ ነው' ያለውን 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍለው መጠየቁ ይታወሳል።

ይህንን በሚመለከት አሐዱ ገንዘቡን ለማስመለስ የተሠራ ሥራ ስለመኖሩ የአየር መንዱን ሥራ አስፈፃሚ ጠይቋል።በምላሻቸውም "በፍርድ ቤት ገንዘቡን ለማስመለስ ጥረት የተደረገ ቢሆንም፤ አዲስ የፓለቲካ ውጥረት በመኖሩ ይሆን ምላሽ ሊሰጡን አልፈቀዱም" ብለዋል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
32😁21
የራሺያ ፌደሬሽን ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት የሀዘን መግለጫ ላከ

የራሺያ ፌደሬሽን በአዲስ አበባ በሚገኘው ኢምባሲው በኩል ሰሞኑን በየመን የባህር ዳርቻ በኢትዮጵያውያን ላይ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ አሰመልክቶ ለኢፌዲሪ መንግስት እና ህዝብ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በህወት የተረፉት 32 ሰዎች ወደ ኤደን ወደብ ተዘዋወረወዋል። ሌሎች የጠፉ 74 ሰዎችን የማፈላለጉን ሥራ የሰደተኞቹ መደረሻ የነበረችው አብያን ግዛት ጸጥታ ኃላፊዎች ሰፊ የነብስ አድን ልዑክ አሰማርቶ አሰሳው እንደቀጠለ ተነግሯል።

ይሁን እንጂ የጠፉት 74 ሰዎች በህይወት የመገኘታቸው ዕድል ጠባብ መሆኑን የአለም አቀፍ ስደተኞች ተቋም ያለውን ስጋት ገልጿል።

Via:- ማለዳ ሚዲያ
@Yenetube @Fikerassefa
😭4219👍3
"የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለራሺያ አዉሮፕላኖችን በኪራይ የመስጠት እቅድ የለዉም" -አቶ መስፍን ጣሰዉ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ አየር መንገዱ ለሩሲያ አውሮፕላኖችን በኪራይ ለመስጠት በውይይት ላይ ነው የሚለው መረጃ ፍፁም ሐሰት ነዉ ሲሉ አስተባብለዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ይህን የገለጹት፣ አየር መንገዱ ከሩሲያ ጋር ስለአውሮፕላን ኪራይ እየተነጋገረ ነው በሚል የካፒታል ጋዜጣ ዘገባ ተከትሎ ነው።

ባለፈው ወር በኢትዮጵያ እና በሩሲያ ባለስልጣናት መካከል በተደረገ ስብሰባ ላይ፣ የሁለቱ ሀገራት የአቪዬሽን ትብብር እንዲስፋፋ ፍላጎት መኖሩ ተገልጿል። ከውይይቱ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ለሩሲያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖችን በ"ዌት ሊዝ" (wet-lease) ስምምነት ማከራየት አንዱ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
19😁16👍2
ኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት ገደማ የዲፕሎማሲያዊ መሻከር በኋላ በሶማሊያ አዲስ አምባሳደር ሾመች!

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር የነበራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተቀዛቀዘ ከአስር ወራት በኋላ አዲስ አምባሳደር ሾመች።የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር የሆኑት አብዲሰላም አብዲ አሊ በሞቃዲሾ በሚገኘው የሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ትናንት ሰኞ እለት በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙትን የሱሌይማን ደደፎ የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል።

ሚኒስትሩ አዲስ የተሾሙትን አምባሳደር በመቀበል በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እና ትብብርን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በሶማሊያ አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር የተሾሙት፤ በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ሶማሊያ አንድ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማትን “ከዲፕሎማሲያዊ ሚናቸው ጋር በማይጣጣም መልኩ” ተሰማርተዋል ስትል ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከሻከረ በኋላ ነው።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
22😁9🔥1