አምስት መኪኖችን የሰረቁ ግለሰቦች ከነ ኤግዚቢቱ ተይዘው በአቃቤ ህግ ክስ ተመሰረተባቸው!
የመኪና ስርቆት ወንጀሉ የተፈጸመው ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ/ም ሌሊት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አቤም ከሚባል ስፍራ ፋይን ቴክ ኢንቨስትመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የመኪና አስመጪ ድርጅት ግቢ ውስጥ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ ሦስት የድርጅቱ የጥበቃ ሰራተኞች ሲሆኑ አስቀድመው ወንጀል ለመፈጸም የሚያስችሏቸውን ሁኔታ አመቻችተው የግቢውን መብራት በማጥፋት ከሌሎች አምስት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን አምስቱን መኪኖች ይዘው ይሰወራሉ።
የድርጅቱ ባለቤቶች ንብረታቸው እንደተሰረቀ ሲያረጋግጡ ጥቆማ ለፖሊስ መስጠታቸውን እና ፖሊስም የተደራጀ የምርመራ እና የክትትል ቡድን በማሰማራት እንዲሁም ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራ መሰራቱን ፖሊስ ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ የሚሸጡ መኪኖችን ሰርቀው ከወጡ በኋላ አንደኛው ተጠርጣሪ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ለመሸጥ ሲደራደር በክትትል ሲያዝ በተመሳሳይ ሁለተኛውን በዚያው ክፍለ ከተማ እንደተያዘ ተገልጿል።3ተኛው እና 4ኛው ተሽከርካሪ በመርካቶ እና ፒያሳ አካባቢ ጠንካራ ክትትል ተደርጎባቸው ሲደረስባቸው ጥለው ለማምለጥ ቢሞክሩም ከሁለቱም ተጠርጣሪዎች ጋር ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።
በተመሳሳይ በተደረገ የተጠና ፍለጋ አምስተኛውን ተሽከርካሪ ወላይታ ሶዶ ሦስት ተጠርጣሪዎች ይዘውት ሲንቀሳቀሱ ተይዘዋል። በአጠቃላይ የተሰረቁትን አምስት ተሽከርካሪዎች እና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሠባት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ በማጣራት በአቃቤ ህግ ክስ መመስረቱን ፖሊስ ገልጿል።
[አዲስ አበባ ፖሊስ]
@YeneTube @FikerAssefa

❤37😁7
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰባት ቢሊየን ብር በላይ አጭበርብረውኛል ባላቸው በ14 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ፤ ሁለቱ የደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ናቸው!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰባት ቢሊየን 735 ሚሊየን ብር አጭበርብረውኛል ባላቸው በ14 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ፤ ክስ ከተመሰረተባቸው ግለሰቦች መካከል ሁለቱ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች መሆናቸውን አስታውቋል።አድራሻቸው አዲስ አበባ መሆኑ የተገለጹ የደህንነት ተቋሙ ሰራተኞች ንጉሴ እምሩ ጉሪኖ እና መሀመድ ነጋሽ ገሰሰ (ቅፅል ስም ዋለልኝ የተባሉ መሆናቸውም በክሱ ላይ ተጠቅሷል።
አዲስ ስታንዳርድ የተመለከተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ፀረ ሙስና ወንጀል ችሎት የቀረበው የክስ ዝርዝር እንደሚያሳየው ባንኩ ለመሰረተው ክስ 20 የሰው እና 24 የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።ከ14ቱ ተከሳሾች ውስጥ 13 በእስር ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
የክሱ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተካሳሾቹ “በዋና ወንጀል አድራጊነት እና ስልጣንን አለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል” ነው የተመሰረተባቸው።በተያዘው አመት 2017 ዓ.ም ግንቦት ወር ላይ መገናኛ ብዙሃን “በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የውስጥ አካውንት ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ መዘረፉ ተገለፀ” በሚል ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ዘገባ ማቅረባቸው ይታወሳል፤ ይህንንም ተከትሎ ባንኩ ምንም ገንዘብ አልተዘረፍኩም ሲል መግለጫ በማውጣት አስተባብሎ ነበር።
Via AS

❤27👀7😁4
Forwarded from LinkedIn Ethiopia
@linkedin_ethiop ያግኙን
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤10
በጋዛ ውስጥ ያሉ የአጃንስ ፍራንስ ፕረስ ጋዜጠኞች በሞት አፋፍ ላይ ይገኛሉ ተባለ
የአጃንስ ፍራንስ ፕረስ (ኤኤፍፒ) የጋዜጠኞች ማህበር በጋዛ ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞቹ በረሃብ ምክንያት ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ከሚሠሩት 10 ፍሪላንስ ጋዜጠኝች መካከል አንዱ ጁላይ 19 ላይ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ መልእክት ያሰፈረ ሲሆን፣ “ለሚድያ ተቋሙ ለመስራት በቂ አቅም የለኝም ሰውነቴ ከስቶ ጉልበቴ እየከዳኝ ነው" ሲል ተደምጧል።
በሰርጡ ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ ሰራተኞቻቸው ከዚህ በኋላ ስራቸውን ለመስራት የሚያስችል የአካል ብቃት እንደሌላቸው እና ሁኔታው እየተባባሰ መምጣቱንም AFP አስታውቋል። ተቋሙ አክሎም "ሰራተኞቹ በየቀኑ ልብ የሚሰብሩ የእርዳታ ጥሪዎችን" እያደረሱት መሆናቸውን ገልፆል።
ጋዜጠኞቹ ወርሃዊ ደሞዛቸውን ቢያገኙም የሚገዛው ነገር የለም ወይም እቃው ሙሉ በሙሉ በተጋነነ ዋጋ ብቻ እንደሚገኝ ማህበሩ ተናግሯል። በማንኛውም ጊዜ ሞታቸውን ልንሰማ እንደምንችል እናውቃለን ሰራተኞቹ አደጋ ላይ ነው ያሉት ይህ ለእኛ ለመቋቋም የማይቻል ነው ብለዋል።
“ኤኤፍፒ ከተመሰረተበት እ.ኤ.አ. ነሐሴ 1944 ጀምሮ፣ በግጭቶች ጋዜጠኞችን አጥተናል፣ ቁስለኛ እና እስረኞች በቡድናችን ውስጥ አሉ፣ ነገር ግን ማናችንም ብንሆን አንድ ባልደረባችን በረሃብ ሲሞት አይተን አናውቅም" ሲልም ማህበሩ አክሏል።
Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa

😭19❤9😁2
የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በ15 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተለቀቀ!
ከጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የነበረው የንቅናቄው ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በ15 ሺህ ብር ዋስ ዛሬ ከሰዓት በኋላ መለቀቁን የስራ ባልደረቦቹ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈታ ፍርድ ቤቱ መወሰኑንና ከሰዓት በኋላ 9 ሰዓት አካባቢ መለቀቁን ባልደረቦቹ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ዶ/ር ዳንኤል ከእስር መፈታቱን "አዎንታዊ እርምጃ" ሲል ገልፆ፤ "ማንኛውም የጤና ባለሙያ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መብቱን በመጠየቁ ወይም ለጤና ስርዓት ማሻሻያዎች በመሟገቱ ያለ ፍትህ የሚደረግ እስራትን አጥብቀን እናወግዛለን" ብሏል።

❤24👍1
ነዳሁት እንጂ አልገዛሁትም! - አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ
" ... ለባለቤቴ፤ ለፊልም ባለሞያዋ ሮማን አየለ Tesla Cybertruck ስጦታ አላበረከትኩም።
እኔ፣ ባለቤቴ እና ልጆቼ ጋር ለእረፍት ሰሜን አሜሪካ ነው ያለነው። የTesla ኩባንያን የመጎበኘት ዕድል አጋጥሞን ነበር።
እግረመንገድ "Test Drive" አድርጊያለሁ። ለማስታወሻ የተነሳነውን ፎቶግራፍ ሮሚ በፌስቡክ ገጻ ለጠፈች።

❤30😁12👍1
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ጋር ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በስልክ መነጋገራቸውን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ዛሬ ባደረጉት የስልክ ውይይት የመረጋጋት እና የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ እድገት እንዲሁም የአፍሪቃው ቀንድን በተመለከተ ሁለቱ ሃገራት በሚጋሯቸው ግቦች ላይ ማተኮራቸውን
አመልክቷል።በዚህ ውይይትም የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሪቢዮ ውይይት እና አካባቢያዊ መረጋጋት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት መስጠታቸውም ተጠቅሷል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገጹ ባወጣው መረጃ ማርኮ ሩቢዮ የኢትዮጵያን የኤኮኖሚ ማሻሻያዎች ማድነቃቸውን በማመልከት፤ ለአሜሪካ የንግድ እና የመዋዕለንዋይ ፍሰት አማራጭ የመሆን አቅም ለመኖሩ አጽንኦት መስጠታቸውንም አክሎ ገልጿል።
Via DW

😁22❤7👍6
ታዋቂው እንግሊዛዊ ዘፋኝ ኦዚ ኦስቦርን በ76 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።
ኦዚ የሄቪ ሜታል ባንድ የሆነው ብላክ ሳባዝ መሪ ድምጻዊ እንደሆነ ይታወቃል።
@YeneTube @FikerAssefa
ኦዚ የሄቪ ሜታል ባንድ የሆነው ብላክ ሳባዝ መሪ ድምጻዊ እንደሆነ ይታወቃል።
@YeneTube @FikerAssefa
👀17❤7😭5
Forwarded from YeneTube
ታሪክ
በዛሬው ዝግጅታችን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚ ጀርመንን ወረራ ለማስቆም ፈረንሳይ የገነባችውን የማጂኖ መስመር ስለተባለው ግዙፍ ምሽግ የምናይ ሲሆን ይህ ቢሊዮኖች የፈሰሱበት ምሽግ ለምን የናዚ ጀርመንን ወረራ ማስቆም ተሳነው የሚለውን እንመለከታለን፣ መሰል የታሪክ ትንታኔዎች ለመከታተል ቪዲዮውን ላይክ እና ሼር ቻናሉንም ሰብስክራይብ ያድርጉ።
👇👇
https://youtu.be/LAJZeUvxwjs

YouTube
ግዙፉ የፈረንሳይ ምሽግ እንዴት የጀርመንን ወረራ ማስቆም ተሳነው?
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የጀርመንን ወረራ ለማስቆም ፈረንሳይ የገነባችውን "የማጂኖ መስመር" የተባለውን ግዙፍ ምሽግ የምናይ ሲሆን ይህ ቢሊዮኖች የፈሰሱበት ምሽግ ለምን የናዚ ጀርመንን ወረራ ማቆም ተሳነው የሚለውን እንመለከታለን፣ መሰል የታሪክ ትንታኔዎች ለመከታተል ቪዲዮውን ላይክ እና ሼር ቻናሉንም ሰብስክራይብ ያድርጉ።
❤13👍1🔥1
👀👀
"አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ"
ቀን 16/11/17 የወጣ
0997473781/ 0997470384
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ:ነርስ ጂፒ ዶክተር ነርስ,ላብራቶሪ ቴክኒሻን
♦️ት/ት ደረጃ:diploma/degree
♦️ልምድ:0-5
♦️ደሞዝ:በድርጅቱ እስኬል
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ #አካዉንታንት ለ ድርጅቶች እና ሆቴሎች ላይ /ለአስመጭ/ለፍብሪካ
♦️የት/ደረጃ' ዲግሪ/ዲፕሎማ
♦️የስራ ልምድ'0-6ዓመት
♦️ደሞዝ' 6000-15000
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅NGO
♦️የት/ት ደረጃ ኤኒ ዲግሪ /ዲፕሎማ
♦️የስራ ልምድ 0አመት
♦️ደሞወዝ 25000 30000+
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራመደብ: ስልክ ኦፕሬተር በፈረቃ
♦️ት/ት ደረጃ:10/12/ዲፕሎማ
♦️ልምድ: 0አመት
♦️ደሞዝ: 9800 +
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
የስራ መደብ: የሽልማት አስተባባር
♦️የት/ደረጃ' ዲግሪ/ዲፕሎ
♦️የስራ ልምድ '0አመት
♦️ደሞወዝ 13500
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ:# ጥፍር እና አይላሽ
♦️ት/ት ደረጃ: 10
♦️ልምድ: 0አመት
♦️ደሞወዝ 12000 +
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ #አየር መንገድ ውስጥ ሽያጭ
♦️የት/ደረጃ' 10/ ዲፕሎማ/ዲግሪ
♦️የስራ ልምድ' 0 ዓመት
♦️ደሞዝ' 10,000 +
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ #Reception ለሆቴል ,ድርጅቶች እና ለ ገስት ሀውስ/ለክሊኒክ/ሆስፒታል/ለድርጅት
♦️የት/ደረጃ 10/ degree/dip
♦️ፃታ' /ሴ
♦️የስራ ልምድ'0~1 ዓመት
♦️ደሞዝ' 7000+
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ ሆስተስ
♦️የት/ደረጃ' 10+
♦️ፆታ' /ሴ
♦️ደሞዝ' 15000/ 20000
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ:# ሹፌር ህ1/ደረቅ1
♦️ት/ት ደረጃ 8/10
♦️ልምድ:የሰራ
♦️ደሞዝ:11.000
♦️ፆታ:ሴት
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ:#ካሸር ለድርጅት እና ለትለያዩ ተቁአማት##ለሆቴል#ለሱፕርማርኬት
♦️የት/ደረጃ' 10-ዲግሪ
♦️ልምድ:0-1
♦️ፆታ' ሴ
♦️ደሞዝ' 5500-10000+
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ #በያጅ GMF
♦️የት/ደረጃ'/10/ሰርተፉኬት
♦️ልምድ: የሰራ
♦️ደሞዝ' ማራኪ
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
✅የስራ መደብ: ጉዳይ አስፈፃሚ
♦️የት/ደረጃ' 10+
♦️የስራ ልምድ '0አመት
♦️ፆታ' ወ/ሴት
♦️ደሞዝ: 10500
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
⭐️የስራ መደብ:#የእሸጋ ሰራተኛ
✨የት/ት ደረጃ:10/ሰርተፍኬት
✨ልምድ:0አመት
✨ደሞዝ:በስምምነት
✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏✏
☎️ አድራሻ መገናኛ መተባበር
ህንጻ 4 ፎቅ ቢሮ ቁ B421
📞 0997470384
📞 0997473781

❤15👍1
Forwarded from YeneTube
የምስራች 🎉🎉🎉📍አሚስኮ ሪልስቴት(AMISCO RealEstate)
ለቡ ሙዚቃ ሰፈር
☎️09-03-97-85-64
👍👍ለ 5 ቤት ብቻ የተደረገ ልዩ ቅናሽ
🏠🏠 በካሬ 75ሺ ብር ብቻ (በከፊል ማጠናቂያ)
✅ 100% ለሚከፍል በካሬ=65ሺብር
📌ባለ 3መኝታ 183.7ካሬ
👍ጠቅላላ = 13,777,500 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,133,250ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =11.9ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 192.69ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,451,750 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,335,525ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.5ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 194.67ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,600,250ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4.3ሚሊየን ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.6ሚሊየን ብር
ሳይቱ የሚያሟላቸው ነገሮች
👉B+G+12+terrace
👉 90% የተጠናቀቀ
👉 ምቹ መኖሪያ ሰፈር
👉የተሟላ እና በቂ ፓርኪንግ
👉 የጋራ አዳራሽ
👉 የደህንነት መጠበቂያ ካሜራ
👉 የከርሰ ምድር ውሃ
👉 ዋና ገንዳ
👉 ጂም እና እስፓ
👉 የልጆቹ መጫወቻ
👉 ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ መንደር
👉 የቆሻሻ ማስወገጃ
👉እሳት አደጋ ማጥፊያ
👉 ተጠባባቂ ጀነሬተር
👉 ሊፊት
👉ሰፊ ቴራስ
👉6500 ካሬ ላይ ያረፈ ጊቢ
👉ግሪን ጋርደን
👉በ100ሜ ርቀት የእምነት ተቋማት
የሚያስፈልግዎትን ሁሉ በአቅራቢያዎ የሚያገኙበት
ለበለጠ መረጃ ☎️09-03-97-85-64 ይደውሉ
ለቡ ሙዚቃ ሰፈር
☎️09-03-97-85-64
👍👍ለ 5 ቤት ብቻ የተደረገ ልዩ ቅናሽ
🏠🏠 በካሬ 75ሺ ብር ብቻ (በከፊል ማጠናቂያ)
✅ 100% ለሚከፍል በካሬ=65ሺብር
📌ባለ 3መኝታ 183.7ካሬ
👍ጠቅላላ = 13,777,500 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,133,250ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =11.9ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 192.69ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,451,750 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,335,525ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.5ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 194.67ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,600,250ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4.3ሚሊየን ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.6ሚሊየን ብር
ሳይቱ የሚያሟላቸው ነገሮች
👉B+G+12+terrace
👉 90% የተጠናቀቀ
👉 ምቹ መኖሪያ ሰፈር
👉የተሟላ እና በቂ ፓርኪንግ
👉 የጋራ አዳራሽ
👉 የደህንነት መጠበቂያ ካሜራ
👉 የከርሰ ምድር ውሃ
👉 ዋና ገንዳ
👉 ጂም እና እስፓ
👉 የልጆቹ መጫወቻ
👉 ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ መንደር
👉 የቆሻሻ ማስወገጃ
👉እሳት አደጋ ማጥፊያ
👉 ተጠባባቂ ጀነሬተር
👉 ሊፊት
👉ሰፊ ቴራስ
👉6500 ካሬ ላይ ያረፈ ጊቢ
👉ግሪን ጋርደን
👉በ100ሜ ርቀት የእምነት ተቋማት
የሚያስፈልግዎትን ሁሉ በአቅራቢያዎ የሚያገኙበት
ለበለጠ መረጃ ☎️09-03-97-85-64 ይደውሉ
❤9
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
❤3
ሁለት የኢትዮጵያ የስለላ መኮንኖች በ7.7 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ገንዘብ ማጭበርበር ወንጀል ከተከሰሱት 14 ሰዎች መካከል ይገኛሉ ተባለ
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ7.7 ቢሊዮን ብር በላይ ለማዘዋወር በተደረገ ትልቅ የገንዘብ ምዝበራ ሴራ፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሁለት ሰዎችን ጨምሮ 14 ሰዎች በይፋ ክስ ተመስርቶባቸዋል።
ባለፈው ሚያዚያ ከባንኩ ሆሮ ቅርንጫፍ በምዕራብ ኦሮሚያ በተገኙ የውስጥ ሲስተም የመጠቀም ፍቃዶችን በመጠቀም፣ ተጠርጣሪዎቹ – የንግድ ባንክ ሰራተኞች፣ የመንግስት ተወካዮች እና የግል ዜጎችን ጨምሮ – በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከሶስት የባንኩ የውስጥ ሂሳቦች ወደ በርካታ የውሸት እና የግል ሂሳቦች ለማዘዋወር አቅደው እንደነበር ተገልጿል።
በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ የወንጀል ችሎት የቀረቡ የፍርድ ቤት መዛግብት እንደሚያሳዩት፣ ዕቅዱ ህገወጥ የመንግስት ገንዘብ ማውጣትና ማዘዋወር እንዲሁም ማጭበርበርን ለማስቻል የመዳረሻ ፈቃዶችን አላግባብ መጠቀምን ያካትታል። በክሱ መሰረት፣ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ክሱን ያስከተለውን ምርመራ አካሂዷል። ከሳሾቹ መካከል ሦስት የንግድ ባንክ ሰራተኞች፣ የቀድሞ የባንኩ የሆሮ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅን ጨምሮ በሻምቡ፣ ኦሮሚያ፣ እና ሁለት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የኢኮኖሚ መረጃ መኮንኖች ይገኙበታል።
Via:- አዲስ ስታንዳርድ

❤19😁6👍2
ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ከጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት ጥገኝነት እንዲላቀቁ አንክታድ አሳሰበ!
ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግስታት የንግድ እና ልማት ጉባዔ (አንክታድ) ባወጣው አዲስ ሪፖርት መሰረት፣ ከ80% በላይ የሚሆነውን ምርቷን በጥሬ ዕቃ መልክ ወደ ውጭ የምትልከውን ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት፣ ኢኮኖሚያቸውን ከአደጋ ለመከላከል ከጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት ጥገኝነት በመውጣት እሴት የመጨመር (value addition) ስራ ላይ እንዲያተኩሩ አሳስቧል።
የጥሬ ዕቃዎች ንግድ ለዓለም አቀፍ ንግድ ወሳኝ አካል ሲሆን፣ ከአጠቃላይ የንግድ መጠን አንድ ሶስተኛውን ይይዛል።ይሁን እንጂ፣ አንድ ሀገር ከንግድ ኤክስፖርት ገቢዋ ከ60% በላይ ከጥሬ ዕቃዎች የምታገኝ ከሆነ "የጥሬ ዕቃ ጥገኛ" ተብላ ትገለጻለች። እነዚህ ጥሬ ዕቃዎች እንደ ኢነርጂ፣ ማዕድን እና ግብርና ባሉ ምድቦች ይከፈላሉ።
አንክታድ የረዥም ጊዜ ችግር የሆነው በዋና ምርቶች ላይ መቆየት የኢንዱስትሪ ልማትን የሚያደናቅፍ እና የዓለም ዋጋ ሲለዋወጥ የሀገራትን የፋይናንስ መረጋጋት የሚያሰጋ መሆኑን ገልጿል።
ተጨማሪ ያንብቡ

❤18👍2
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የባንክ ሒሳብ እንዲታገድ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳለፈ፣ ውሳኔው የተላለፈው የ17 ወራት ውዝፍ የመምህራን ክፍያ ጋር በተያያዘ ነው!
በትግራይ ክልል ከተካሄደው ጦርነት ጋር በተያያዘ የክልሉ መምህራን የ17 ወራት ደመወዝ እንዲከፈላቸው የመሰረቱትን ክስ የሚመለከተው የትግራይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጊዜያዊ አስተዳደር ባንክን ሒሳብ እንዲታገድ ውሳኔ አሳለፈ፤ ለሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት የተሰየሙት ዳኞችም ክርክሮችን ከሰሙ በኋላ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተከፈቱትን የባንክ ሒሳቦች እንዳይንቀሳቀሱ በማገድ ወጪ የተደረገው የገንዘቡ መጠን መቼ እንደወጣና ወደ የትኛው የባንክ ሒሳብ እንደተላለፈ ማስረጃ እንዲቀርብ ትእዛዝ አስተላልፈዋል።
የከሳሽ የመምህራን ማህበሩ ጠበቆች በእስር እንዲቀርቡልን ሲሉ የጠየቋቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እና የክልሉ የፋይናንሰ ቢሮ ሃላፊ ምሕረት በየነ (ዶ/ር) ማስረጃዎቹ ከቀረቡ በኋላ እንደሚታይ በመግለጽ የዕለቱ ዳኞች ለሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠታቸው ተገልጿል።

❤29👍8😁1👀1