YeneTube
Photo
የውጊያ ጄት በትምህርት ቤት ውስጥ ተከስክሶ ቢያንስ 19 ተማሪዎች ሲሞቱ ከ50 በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸው ተገለጸ
📌የብሔራዊ ሃዘን ቀን ታውጇልም ተብሏል
#Ethiopia | በባንግላዲሽ ዋና ከተማ ዳካ በሚገኝ አንድ የኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ የባንግላዲሽ አየር ኃይል ማሰልጠኛ ጄት ተከስክሶ ቢያንስ 19 ሰዎች ሲሞቱ ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል። አብዛኞቹ ተጎጂዎች ወጣት ተማሪዎች እንደሆኑ ተገልጿል። አገሪቱ ብሔራዊ የሐዘን ቀንን እንዳወጀችም ተሰምቷል።
ኤፍ-7 ቢጂአይ (F-7 BGI) የተሰኘው አውሮፕላን በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ 7 ሰአት ላይ ከፍ ካለ በኋላ፣ ከአስራ ሁለት ደቂቃ ገደማ በኋላ በዋና ከተማዋ ሰሜናዊ ክፍል በኡታራ ዲያባሪ አካባቢ በሚገኘው ማይልስቶን ትምህርት ቤት እና ኮሌጅ ካንቲን አቅራቢያ ተከስክሷል ሲል የኢንተር-ሰርቪስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት (ISPR) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የባንግላዲሽ ጋዜጣ ፕሮቶም አሎ እንደዘገበው ወታደራዊው አውሮፕላን አደጋው ሲከሰት በርካታ ወጣት ተማሪዎች በቦታው በነበሩበት ወቅት የምሳ ሰዓት ላይ ከትምህርት ቤቱ ካንቲን አጠገብ ተከስክሷል ብሏል ዘገባው። የመጀመሪያው የሟቾች ቁጥር አንድ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ የእሳት አደጋና ሲቪል መከላከያ ዳይሬክተር ጀኔራል ብሪጋዴር ጀኔራል መሐመድ ዛሂድ ከማል ወደ ስፍራው ከደረሱና ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ከሰጡ በኋላ የሟቾች ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል ነው የተባለው።
ነገ ማክሰኞም የብሔራዊ የሐዘን ቀን ታውጇል ነው የተባለው፡፡
የባንግላዲሽ ኤፍ-7 የቻይና ቼንግዱ ኤፍ-7 ዘመናዊ ስሪት ሲሆን እሱም በሶቪየት ሚግ-21 ላይ የተመሰረተ ነው ተብሏል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ጊዜ ያለፈበት ቢሆንም፣ ወጪ ቆጣቢነቱ እና ለአብራሪ ስልጠናና ለተገደበ የውጊያ ሚናዎች ተስማሚ በመሆኑ አገልግሎት ላይ ይገኛል ነው የተባለው።
ቻይና የመጨረሻዎቹን 16 የኤፍ-7 ቢጂአይ አውሮፕላኖችን ለባንግላዲሽ በ2013 ዓ.ም. ከሰጠች በኋላ ምርቱ ቆሟል ተብሏል ሲል የዘገበው መናኸሪያ ሬዲዮ።
@Yenetube @Fikerassefa

😭14❤12
Forwarded from LinkedIn Ethiopia
@linkedin_ethiop ያግኙን
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤12👍1
🇪🇹 የኢትዮጵያ መንግሥት አይኤምኤፍ ብሔራዊ ባንክ በገለልተኛ ባለሙያዎች እንዲመራ ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ውድቅ አደረገ
የዓለም የገንዘብ ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግሥት የኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም ጋር በተያያዘ የባንኩን ተቋማዊ ነጻነት ለማረጋገጥ ገዥው፣ ምክትላቸው እና የባንኩ የቦርድ አመራሮች ገለልተኛ እንዲሆኑ በ2017 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ሃሳቡን አቅርቦ እንደነብር የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ነው የዘገበው፡፡
ሆኖም የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ሕገ-መንግሥቱን ይቃረናል በማለት እንዳልተቀበሉት አይኤምኤፍ ገልጿል፡፡
አበዳሪው በተሻሻለው አዲሱ የብሔራዊ ባንክ አዋጅ መሠረት በቀጣዮቹ ወራት ሦስት ገለልተኛ የቦርድ አመራሮች ሊመድቡ እንደሚገባ አሳስቧልም ነው የተባለው፡፡

❤34😁26🔥3👍2👎1
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
❤4
የምስራች 🎉🎉🎉📍አሚስኮ ሪልስቴት(AMISCO RealEstate)
ለቡ ሙዚቃ ሰፈር
☎️09-03-97-85-64
👍👍ለ 5 ቤት ብቻ የተደረገ ልዩ ቅናሽ
🏠🏠 በካሬ 75ሺ ብር ብቻ (በከፊል ማጠናቂያ)
✅ 100% ለሚከፍል በካሬ=65ሺብር
📌ባለ 3መኝታ 183.7ካሬ
👍ጠቅላላ = 13,777,500 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,133,250ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =11.9ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 192.69ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,451,750 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,335,525ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.5ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 194.67ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,600,250ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4.3ሚሊየን ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.6ሚሊየን ብር
ሳይቱ የሚያሟላቸው ነገሮች
👉B+G+12+terrace
👉 90% የተጠናቀቀ
👉 ምቹ መኖሪያ ሰፈር
👉የተሟላ እና በቂ ፓርኪንግ
👉 የጋራ አዳራሽ
👉 የደህንነት መጠበቂያ ካሜራ
👉 የከርሰ ምድር ውሃ
👉 ዋና ገንዳ
👉 ጂም እና እስፓ
👉 የልጆቹ መጫወቻ
👉 ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ መንደር
👉 የቆሻሻ ማስወገጃ
👉እሳት አደጋ ማጥፊያ
👉 ተጠባባቂ ጀነሬተር
👉 ሊፊት
👉ሰፊ ቴራስ
👉6500 ካሬ ላይ ያረፈ ጊቢ
👉ግሪን ጋርደን
👉በ100ሜ ርቀት የእምነት ተቋማት
የሚያስፈልግዎትን ሁሉ በአቅራቢያዎ የሚያገኙበት
ለበለጠ መረጃ ☎️09-03-97-85-64 ይደውሉ
ለቡ ሙዚቃ ሰፈር
☎️09-03-97-85-64
👍👍ለ 5 ቤት ብቻ የተደረገ ልዩ ቅናሽ
🏠🏠 በካሬ 75ሺ ብር ብቻ (በከፊል ማጠናቂያ)
✅ 100% ለሚከፍል በካሬ=65ሺብር
📌ባለ 3መኝታ 183.7ካሬ
👍ጠቅላላ = 13,777,500 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,133,250ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =11.9ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 192.69ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,451,750 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,335,525ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.5ሚሊየን ብር
📌ባለ 3መኝታ 194.67ካሬ
👍ጠቅላላ = 14,600,250ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4.3ሚሊየን ብር
ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
✅100%ለከፈለ =12.6ሚሊየን ብር
ሳይቱ የሚያሟላቸው ነገሮች
👉B+G+12+terrace
👉 90% የተጠናቀቀ
👉 ምቹ መኖሪያ ሰፈር
👉የተሟላ እና በቂ ፓርኪንግ
👉 የጋራ አዳራሽ
👉 የደህንነት መጠበቂያ ካሜራ
👉 የከርሰ ምድር ውሃ
👉 ዋና ገንዳ
👉 ጂም እና እስፓ
👉 የልጆቹ መጫወቻ
👉 ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ መንደር
👉 የቆሻሻ ማስወገጃ
👉እሳት አደጋ ማጥፊያ
👉 ተጠባባቂ ጀነሬተር
👉 ሊፊት
👉ሰፊ ቴራስ
👉6500 ካሬ ላይ ያረፈ ጊቢ
👉ግሪን ጋርደን
👉በ100ሜ ርቀት የእምነት ተቋማት
የሚያስፈልግዎትን ሁሉ በአቅራቢያዎ የሚያገኙበት
ለበለጠ መረጃ ☎️09-03-97-85-64 ይደውሉ
❤10🔥2
የአመራር ለውጥ ነው:-ፕሬዝዳንቱ።
በትግራይ ደቡባዊ ዞን አስተዳደራዊ ለውጥ እየተደረገ መሆኑን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ገለፁ።
ለውጡ ወረዳዎችን አይጨምርም ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ታደሰ በደቡብ ትግራይ ክልል እየታየ ያለው ለውጥ የመንግስት ፕሮግራም በመሆኑ አሳዳጅ እና ተሰዳጅ የሚባል ነገር አይኖርም ብለዋል።
ለቀድሞው የደቡብ ዞን አስተዳዳሪዎች ሙሉ ኃላፊነትና ጥቅማጥቅም ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።
ጉዳዩን ለመፍታት የፖሊስ አባላት መላካቸውን ጠቁመው ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅም የጸጥታ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ታደሰ የትግራይ ህዝብ ሰላምን መርጧል ብለዋል።
የአመራር ለውጡን በአቶ አስመላሽ ረዳ እና በጸጥታ ኃላፊው አቶ ጉሴ አበጀ (ወዲ ራያ) አስተባባሪነት እየተካሄደ ነው። አቶ ካላዩ ግደይ እና ወ/ሮ አለም ሃላፊነት ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።
ያለውን አደጋ ለማስወገድና የትግራይን ችግር ለመፍታት የአመራር ለውጥ ያሰፈልጋል ሲሉ ነው የተደመጡት።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት ህወሃት ከዛሬ ጀምሮ በራያ ወታደራዊ ሀይል ለማሰማራት እና በሀይል ለመቆጣጠር ማቀዱን ትናንት ማሳወቃቸው የሚታወስ ነው።

❤26👎3😁1
YeneTube
Photo
በአለልኝ አዘነ ግድያ የተከሰሱት ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው!
በቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የባህርዳር ከተማ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ግድያ ጥፋተኛ የተባሉ ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል በ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
አለልኝ አዘነ ባሳለፍነው ዓመት መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ከተማ በድንገት ሕይወቱ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን፤ ህልፈቱን ተከትሎም ስለ አሟሟቱ ብዙ መላ ምቶች ሲነገሩ የቆዩ ቢሆንም እራሱን አጠፋ የሚለው ግን ለእውነት የቀረበ ሆኖ ሲነገር ቆይቷል፡፡
ፖሊስም በተጫዋቹ አሟሟት ዙሪያ የተለያዩ መረጃዎችን በማሰባሰብ በወንጀል የጠረጠራቸውን ሚስቱንና የእህቷን ባል በቁጥጥር ሥር በማዋል፤ በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መመስረቱ ይታወሳል፡፡
ይህንንም ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በችሎቱ የፍርድ ሂደታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት 1ኛ ተከሳሽ የአለልኝ አዘነ ባለቤት ወ/ሮ አደይ ጌታቸው እንዲሁም፤ 2ኛ ተከሳሽ የወ/ሮ አደይ ጌታቸው እህት ባል የሆነው ሉንጎ ሉቃስ ላይ፤ ባለፈው ሳምንት የግድያ ወንጀል ፈጽመዋል በማለት የጥፋተኛነት ብይን ሰጥቷል።
በዚህም "ከሌሊቱ 5፡30 እስከ 8 ሰዓት ገደማ ባለው ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ ልማት ሰፈር በተቀነባበረ ሁኔታ የ26 ዓመቱን ወጣት አለልኝ አዘነን በመግደል፤ ራሱን ያጠፋ እንዲመስል በማድረግ የግድያ ወንጀል መፈጸማቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች በመረጋገጡ ጥፋተኛ ናቸው" ሲል ውሳኔ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ በዛሬው ሐምሌ 15 ቀን 2017 በዋለው ችሎት በቀድሞው እግር ኳስ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ግድያ ጥፋተኛ በተባሉት 1ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ አደይ ጌታቸው (የአለልኝ አዘነ ባለቤት) ላይ የ16 ዓመት እንዲሁም፤ 2ኛ ተከሳሽ ሉንጎ ሉቃስ (የወ/ሮ አደይ ጌታቸው እህት ባል) ላይ 15 ዓመት ፅኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።
በ26 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አለልኝ አዘነ የእግር ኳስ ሕይወቱን በአርባ ምንጭ ከተማ፣ በሀዋሳ ከተማ፣ በባህር ዳር ከተማ እንዲሁም በብሔራዊ ቡድን ያሳለፈ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርቲያን ስርዓት ጋብቻ በፈፀመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወልዶ ባደገበትና አርባ ምንጭ ከተማ በድንገት ሕይወቱ ማለፉን ይታወሳል፡፡
Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa

❤31😭26👎5👀2
የትግራይ ክልል ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት እንደገጠመው ተገለጸ!
የትግራይ ክልል ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተኸልሽ ገ/ህይወት፤ ወደ ትግራይ የሚገባዉ ነዳጅ በቀን ከሁለት የጭነት ቦቴ እንዳይበልጥ በመደረጉ ክልሉ ለከፍተኛ ችግር መዳረጉን ገለጹ፡ከኢትዮ ኤፍኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት ዳይሬክተሩ፤ ከጦርነቱ በፊት በቀን ከ8 እስከ 16 ቦቴ ወደ ክልሉ ይገባ እንደነበረ አስታዉሰዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የሚገባው የነዳጅ መጠን ከሁለት ቦቴ እንደማይበልጥ በመግለጽም፤ ይህን ተከትሎም 72 ማደያዎች ስራ ማቆማቸዉን ጠቁመዋል፡፡በትግራይ በተከሰተው የነዳጅ እጥረት ሳቢያም፣ በክልሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ሰፊ ተግዳሮት እንደገጠመው አቶ ተኸልሽ ገ/ህይወት ገልጸዋል፡፡
ወደ ተፈናቃዮች መላክ የነበረባቸዉ ምግብና መድኃኒቶች በነዳጅ እጥረት ምክንያት እየደረሰላቸዉ እንዳልሆነም አመልክተዋል፡፡የነዳጅ ችግር እንዲፈታ ለሚመለከታቸዉ የፌደራል አካላት በደብዳቤም በአካልም በተደጋጋሚ መጠየቁንና እስካሁን ግን ምንም አይነት ምላሽም ሆነ መፍትሄ እንዳልተሰጣቸው ዳይሬክተሩ ለጣቢያው ተናግረዋል፡፡

❤10😭6👍1👎1
ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከስቱድዮ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች
🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ
የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት
🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
💎 ባለ 1 መኝታ በ 487,000 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
🛍️🛒ሱቆች ከ 70 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ
- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#whatsapp

❤10
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የህዳሴ ግድቡ ግንባታ በተደጋጋሚ ሲነገር እንደነበረው በመንግስት እና በህዝብ ድጋፍ የተሰራ ፕሮጀክት ነው ሲል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ገለፀ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአንድ ወር ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ አሜሪካ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች ሲሉ መናገራቸውን ተከትሎ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል።
የጽሕፈት ቤቱ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ፍቅርተ ታምር ዛሬ በሰጡት መግለጫ "ማንም አካል ተነስቶ እኔ ነኝ የሰራሁት ቢል ያለምንም ማስረጃ ምንም ማድረግ አይችልም" ብለዋል።
"ምክንያቱም ምንም አይነት፣ ቅንጣት ያክል ገንዘብ ከውጭ ብድርና እርዳታ እንደሌለ ላለፉት 14 ዓመታት መንግስትም ይፋ ሲያደርግ ቆይቷል። እኛም ለሚድያዎች ስንገልጽ ቆይተናል። ሚዲያውም በተለያየ መልኩ ሲገልጹ ቆይተዋል" ሲሉ የትራምፕን ንግግር ወድቅ አድርገዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩት የተባለውን ነገር መንግስት በአርቆ አሳቢነት በጥልቅ ዲፕሎማሲያዊ አሰራር ነው መልስ መሰጠት ያለበት ሲሉም አክለዋል።
ምክንያቱም ማንም ሰው እየተነሳ ስለ ሀገር ጉዳይ የራሱን እና የግሉን አስተያየት መስጠት አይቻልም ያሉት ወ/ሮ ፍቅርተ እንደ መንግስት ግልጽ እና የተብራራ መረጃ ወደፊት ሊሰጥ እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።
"እውነት እና እውነታው በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የተሰራ መሆን መግለጽ ብቻ ነው፤እኛ ይህንን ነው ልናስረዳ የምንችለው ማለትም የሚገባን። የፍራትም አይደለም የማሽቆጥቆጥም አይደለም። ዲፕሎማሲ የመንግስት አሰራር አለው መንግስት በራሱ ጊዜ እና በሚፈልገው አይነት መልስ ይሰጣል" ሲሉ ገልፀዋል።

❤39😁19👍7