የአመራር ለውጥ ነው:-ፕሬዝዳንቱ።
በትግራይ ደቡባዊ ዞን አስተዳደራዊ ለውጥ እየተደረገ መሆኑን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ገለፁ።
ለውጡ ወረዳዎችን አይጨምርም ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ታደሰ በደቡብ ትግራይ ክልል እየታየ ያለው ለውጥ የመንግስት ፕሮግራም በመሆኑ አሳዳጅ እና ተሰዳጅ የሚባል ነገር አይኖርም ብለዋል።
ለቀድሞው የደቡብ ዞን አስተዳዳሪዎች ሙሉ ኃላፊነትና ጥቅማጥቅም ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።
ጉዳዩን ለመፍታት የፖሊስ አባላት መላካቸውን ጠቁመው ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅም የጸጥታ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ታደሰ የትግራይ ህዝብ ሰላምን መርጧል ብለዋል።
የአመራር ለውጡን በአቶ አስመላሽ ረዳ እና በጸጥታ ኃላፊው አቶ ጉሴ አበጀ (ወዲ ራያ) አስተባባሪነት እየተካሄደ ነው። አቶ ካላዩ ግደይ እና ወ/ሮ አለም ሃላፊነት ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።
ያለውን አደጋ ለማስወገድና የትግራይን ችግር ለመፍታት የአመራር ለውጥ ያሰፈልጋል ሲሉ ነው የተደመጡት።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት ህወሃት ከዛሬ ጀምሮ በራያ ወታደራዊ ሀይል ለማሰማራት እና በሀይል ለመቆጣጠር ማቀዱን ትናንት ማሳወቃቸው የሚታወስ ነው።
@Yenetube @Fikerassefa

❤26👎3😁1
YeneTube
Photo
በአለልኝ አዘነ ግድያ የተከሰሱት ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው!
በቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የባህርዳር ከተማ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ግድያ ጥፋተኛ የተባሉ ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል በ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
አለልኝ አዘነ ባሳለፍነው ዓመት መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ከተማ በድንገት ሕይወቱ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን፤ ህልፈቱን ተከትሎም ስለ አሟሟቱ ብዙ መላ ምቶች ሲነገሩ የቆዩ ቢሆንም እራሱን አጠፋ የሚለው ግን ለእውነት የቀረበ ሆኖ ሲነገር ቆይቷል፡፡
ፖሊስም በተጫዋቹ አሟሟት ዙሪያ የተለያዩ መረጃዎችን በማሰባሰብ በወንጀል የጠረጠራቸውን ሚስቱንና የእህቷን ባል በቁጥጥር ሥር በማዋል፤ በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መመስረቱ ይታወሳል፡፡
ይህንንም ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በችሎቱ የፍርድ ሂደታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት 1ኛ ተከሳሽ የአለልኝ አዘነ ባለቤት ወ/ሮ አደይ ጌታቸው እንዲሁም፤ 2ኛ ተከሳሽ የወ/ሮ አደይ ጌታቸው እህት ባል የሆነው ሉንጎ ሉቃስ ላይ፤ ባለፈው ሳምንት የግድያ ወንጀል ፈጽመዋል በማለት የጥፋተኛነት ብይን ሰጥቷል።
በዚህም "ከሌሊቱ 5፡30 እስከ 8 ሰዓት ገደማ ባለው ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ ልማት ሰፈር በተቀነባበረ ሁኔታ የ26 ዓመቱን ወጣት አለልኝ አዘነን በመግደል፤ ራሱን ያጠፋ እንዲመስል በማድረግ የግድያ ወንጀል መፈጸማቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች በመረጋገጡ ጥፋተኛ ናቸው" ሲል ውሳኔ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ በዛሬው ሐምሌ 15 ቀን 2017 በዋለው ችሎት በቀድሞው እግር ኳስ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ግድያ ጥፋተኛ በተባሉት 1ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ አደይ ጌታቸው (የአለልኝ አዘነ ባለቤት) ላይ የ16 ዓመት እንዲሁም፤ 2ኛ ተከሳሽ ሉንጎ ሉቃስ (የወ/ሮ አደይ ጌታቸው እህት ባል) ላይ 15 ዓመት ፅኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።
በ26 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አለልኝ አዘነ የእግር ኳስ ሕይወቱን በአርባ ምንጭ ከተማ፣ በሀዋሳ ከተማ፣ በባህር ዳር ከተማ እንዲሁም በብሔራዊ ቡድን ያሳለፈ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርቲያን ስርዓት ጋብቻ በፈፀመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወልዶ ባደገበትና አርባ ምንጭ ከተማ በድንገት ሕይወቱ ማለፉን ይታወሳል፡፡
Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa

❤31😭26👎5👀2
የትግራይ ክልል ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት እንደገጠመው ተገለጸ!
የትግራይ ክልል ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተኸልሽ ገ/ህይወት፤ ወደ ትግራይ የሚገባዉ ነዳጅ በቀን ከሁለት የጭነት ቦቴ እንዳይበልጥ በመደረጉ ክልሉ ለከፍተኛ ችግር መዳረጉን ገለጹ፡ከኢትዮ ኤፍኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት ዳይሬክተሩ፤ ከጦርነቱ በፊት በቀን ከ8 እስከ 16 ቦቴ ወደ ክልሉ ይገባ እንደነበረ አስታዉሰዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የሚገባው የነዳጅ መጠን ከሁለት ቦቴ እንደማይበልጥ በመግለጽም፤ ይህን ተከትሎም 72 ማደያዎች ስራ ማቆማቸዉን ጠቁመዋል፡፡በትግራይ በተከሰተው የነዳጅ እጥረት ሳቢያም፣ በክልሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ሰፊ ተግዳሮት እንደገጠመው አቶ ተኸልሽ ገ/ህይወት ገልጸዋል፡፡
ወደ ተፈናቃዮች መላክ የነበረባቸዉ ምግብና መድኃኒቶች በነዳጅ እጥረት ምክንያት እየደረሰላቸዉ እንዳልሆነም አመልክተዋል፡፡የነዳጅ ችግር እንዲፈታ ለሚመለከታቸዉ የፌደራል አካላት በደብዳቤም በአካልም በተደጋጋሚ መጠየቁንና እስካሁን ግን ምንም አይነት ምላሽም ሆነ መፍትሄ እንዳልተሰጣቸው ዳይሬክተሩ ለጣቢያው ተናግረዋል፡፡

❤10😭6👍1👎1
ከተወዳጁ የሂል ሳይድ መንደር ውስጥ ለሽያጭ የመጨረሻ በሆነው የዲያስፓራ ብሎክ ቁጥር 3 ላይ ከስቱድዮ እስከ ባለ አራት መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች
🏡በ 8% ቅድመ ክፍያ ብቻ
የቤቱን 60% ደግሞ እየኖሩበት ወይም አከራይተውት በ20 አመት ቀስ ብለው መክፈል የሚችሉት
🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
💎 ባለ 1 መኝታ በ 487,000 ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 825,982 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 854,221 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,157,787 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
🛍️🛒ሱቆች ከ 70 ካሬ ጀምሮ ይምጡ የግሎ ያድርጉ
- ባሉት ውስን ቀናቶች ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 3 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ አቅርበን እየጠበቅኖት ነው
ይደውሉልን
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ!
☎️0900025097
#telegram (@SamuelDMCRealtor)
#whatsapp

❤10
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የህዳሴ ግድቡ ግንባታ በተደጋጋሚ ሲነገር እንደነበረው በመንግስት እና በህዝብ ድጋፍ የተሰራ ፕሮጀክት ነው ሲል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ገለፀ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአንድ ወር ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ አሜሪካ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች ሲሉ መናገራቸውን ተከትሎ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል።
የጽሕፈት ቤቱ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ፍቅርተ ታምር ዛሬ በሰጡት መግለጫ "ማንም አካል ተነስቶ እኔ ነኝ የሰራሁት ቢል ያለምንም ማስረጃ ምንም ማድረግ አይችልም" ብለዋል።
"ምክንያቱም ምንም አይነት፣ ቅንጣት ያክል ገንዘብ ከውጭ ብድርና እርዳታ እንደሌለ ላለፉት 14 ዓመታት መንግስትም ይፋ ሲያደርግ ቆይቷል። እኛም ለሚድያዎች ስንገልጽ ቆይተናል። ሚዲያውም በተለያየ መልኩ ሲገልጹ ቆይተዋል" ሲሉ የትራምፕን ንግግር ወድቅ አድርገዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩት የተባለውን ነገር መንግስት በአርቆ አሳቢነት በጥልቅ ዲፕሎማሲያዊ አሰራር ነው መልስ መሰጠት ያለበት ሲሉም አክለዋል።
ምክንያቱም ማንም ሰው እየተነሳ ስለ ሀገር ጉዳይ የራሱን እና የግሉን አስተያየት መስጠት አይቻልም ያሉት ወ/ሮ ፍቅርተ እንደ መንግስት ግልጽ እና የተብራራ መረጃ ወደፊት ሊሰጥ እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።
"እውነት እና እውነታው በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የተሰራ መሆን መግለጽ ብቻ ነው፤እኛ ይህንን ነው ልናስረዳ የምንችለው ማለትም የሚገባን። የፍራትም አይደለም የማሽቆጥቆጥም አይደለም። ዲፕሎማሲ የመንግስት አሰራር አለው መንግስት በራሱ ጊዜ እና በሚፈልገው አይነት መልስ ይሰጣል" ሲሉ ገልፀዋል።

❤39😁19👍7
አምስት መኪኖችን የሰረቁ ግለሰቦች ከነ ኤግዚቢቱ ተይዘው በአቃቤ ህግ ክስ ተመሰረተባቸው!
የመኪና ስርቆት ወንጀሉ የተፈጸመው ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ/ም ሌሊት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አቤም ከሚባል ስፍራ ፋይን ቴክ ኢንቨስትመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የመኪና አስመጪ ድርጅት ግቢ ውስጥ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ ሦስት የድርጅቱ የጥበቃ ሰራተኞች ሲሆኑ አስቀድመው ወንጀል ለመፈጸም የሚያስችሏቸውን ሁኔታ አመቻችተው የግቢውን መብራት በማጥፋት ከሌሎች አምስት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን አምስቱን መኪኖች ይዘው ይሰወራሉ።
የድርጅቱ ባለቤቶች ንብረታቸው እንደተሰረቀ ሲያረጋግጡ ጥቆማ ለፖሊስ መስጠታቸውን እና ፖሊስም የተደራጀ የምርመራ እና የክትትል ቡድን በማሰማራት እንዲሁም ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራ መሰራቱን ፖሊስ ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ የሚሸጡ መኪኖችን ሰርቀው ከወጡ በኋላ አንደኛው ተጠርጣሪ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ለመሸጥ ሲደራደር በክትትል ሲያዝ በተመሳሳይ ሁለተኛውን በዚያው ክፍለ ከተማ እንደተያዘ ተገልጿል።3ተኛው እና 4ኛው ተሽከርካሪ በመርካቶ እና ፒያሳ አካባቢ ጠንካራ ክትትል ተደርጎባቸው ሲደረስባቸው ጥለው ለማምለጥ ቢሞክሩም ከሁለቱም ተጠርጣሪዎች ጋር ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።
በተመሳሳይ በተደረገ የተጠና ፍለጋ አምስተኛውን ተሽከርካሪ ወላይታ ሶዶ ሦስት ተጠርጣሪዎች ይዘውት ሲንቀሳቀሱ ተይዘዋል። በአጠቃላይ የተሰረቁትን አምስት ተሽከርካሪዎች እና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሠባት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ በማጣራት በአቃቤ ህግ ክስ መመስረቱን ፖሊስ ገልጿል።
[አዲስ አበባ ፖሊስ]

❤37😁7
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰባት ቢሊየን ብር በላይ አጭበርብረውኛል ባላቸው በ14 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ፤ ሁለቱ የደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ናቸው!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰባት ቢሊየን 735 ሚሊየን ብር አጭበርብረውኛል ባላቸው በ14 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ፤ ክስ ከተመሰረተባቸው ግለሰቦች መካከል ሁለቱ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች መሆናቸውን አስታውቋል።አድራሻቸው አዲስ አበባ መሆኑ የተገለጹ የደህንነት ተቋሙ ሰራተኞች ንጉሴ እምሩ ጉሪኖ እና መሀመድ ነጋሽ ገሰሰ (ቅፅል ስም ዋለልኝ የተባሉ መሆናቸውም በክሱ ላይ ተጠቅሷል።
አዲስ ስታንዳርድ የተመለከተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ፀረ ሙስና ወንጀል ችሎት የቀረበው የክስ ዝርዝር እንደሚያሳየው ባንኩ ለመሰረተው ክስ 20 የሰው እና 24 የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።ከ14ቱ ተከሳሾች ውስጥ 13 በእስር ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
የክሱ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተካሳሾቹ “በዋና ወንጀል አድራጊነት እና ስልጣንን አለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል” ነው የተመሰረተባቸው።በተያዘው አመት 2017 ዓ.ም ግንቦት ወር ላይ መገናኛ ብዙሃን “በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የውስጥ አካውንት ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ መዘረፉ ተገለፀ” በሚል ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ዘገባ ማቅረባቸው ይታወሳል፤ ይህንንም ተከትሎ ባንኩ ምንም ገንዘብ አልተዘረፍኩም ሲል መግለጫ በማውጣት አስተባብሎ ነበር።
Via AS

❤27👀7😁4
Forwarded from LinkedIn Ethiopia
@linkedin_ethiop ያግኙን
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤10
በጋዛ ውስጥ ያሉ የአጃንስ ፍራንስ ፕረስ ጋዜጠኞች በሞት አፋፍ ላይ ይገኛሉ ተባለ
የአጃንስ ፍራንስ ፕረስ (ኤኤፍፒ) የጋዜጠኞች ማህበር በጋዛ ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞቹ በረሃብ ምክንያት ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ከሚሠሩት 10 ፍሪላንስ ጋዜጠኝች መካከል አንዱ ጁላይ 19 ላይ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ መልእክት ያሰፈረ ሲሆን፣ “ለሚድያ ተቋሙ ለመስራት በቂ አቅም የለኝም ሰውነቴ ከስቶ ጉልበቴ እየከዳኝ ነው" ሲል ተደምጧል።
በሰርጡ ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ ሰራተኞቻቸው ከዚህ በኋላ ስራቸውን ለመስራት የሚያስችል የአካል ብቃት እንደሌላቸው እና ሁኔታው እየተባባሰ መምጣቱንም AFP አስታውቋል። ተቋሙ አክሎም "ሰራተኞቹ በየቀኑ ልብ የሚሰብሩ የእርዳታ ጥሪዎችን" እያደረሱት መሆናቸውን ገልፆል።
ጋዜጠኞቹ ወርሃዊ ደሞዛቸውን ቢያገኙም የሚገዛው ነገር የለም ወይም እቃው ሙሉ በሙሉ በተጋነነ ዋጋ ብቻ እንደሚገኝ ማህበሩ ተናግሯል። በማንኛውም ጊዜ ሞታቸውን ልንሰማ እንደምንችል እናውቃለን ሰራተኞቹ አደጋ ላይ ነው ያሉት ይህ ለእኛ ለመቋቋም የማይቻል ነው ብለዋል።
“ኤኤፍፒ ከተመሰረተበት እ.ኤ.አ. ነሐሴ 1944 ጀምሮ፣ በግጭቶች ጋዜጠኞችን አጥተናል፣ ቁስለኛ እና እስረኞች በቡድናችን ውስጥ አሉ፣ ነገር ግን ማናችንም ብንሆን አንድ ባልደረባችን በረሃብ ሲሞት አይተን አናውቅም" ሲልም ማህበሩ አክሏል።
Via:- ዳጉ ጆርናል

😭19❤9😁2
የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በ15 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተለቀቀ!
ከጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የነበረው የንቅናቄው ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በ15 ሺህ ብር ዋስ ዛሬ ከሰዓት በኋላ መለቀቁን የስራ ባልደረቦቹ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈታ ፍርድ ቤቱ መወሰኑንና ከሰዓት በኋላ 9 ሰዓት አካባቢ መለቀቁን ባልደረቦቹ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ዶ/ር ዳንኤል ከእስር መፈታቱን "አዎንታዊ እርምጃ" ሲል ገልፆ፤ "ማንኛውም የጤና ባለሙያ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መብቱን በመጠየቁ ወይም ለጤና ስርዓት ማሻሻያዎች በመሟገቱ ያለ ፍትህ የሚደረግ እስራትን አጥብቀን እናወግዛለን" ብሏል።

❤24👍1