YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የማዕድን እሰጥአገባ፣ የኦሮሚያ ማዕድን ባለስልጣን የሆንግኮንጉ ሺንግሹ ማዕድን እንዲያለማ የተሰጠው ፍቃድ እንዲሰረዝ ጠየቀ!

በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ላይ ሰፊ አንድምታ ባለው አኳኋን የኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለስልጣን (OMDA) የፌደራል መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን ማዕድን እንዲያለማ ሶስት ፈቃዶች የተሰጠው ሆንግኮንግ ዢንግሹ ማዕድን ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት ኩባንያ (Hong Kong Xingxu Mining International Investment Co. Ltd) ፈቃዶቹ እንዲሰረዙ መጠየቁ ተገለጸ።

ባለስልጣኑ ለማዕድን ሚኒስቴር ሐምሌ ቀን 2017 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ሆንግ ኮንግ ሺንግሹ ኩባንያ የፌደራል እና የክልሉን መንግስት አዋጆች ባለማክበር፣ ስራውን ባግባቡ ባለማከናወን እና የአካሄድ ጥሰቶችን በመፈጸም “የገባውን ውል አላከበረምል” ሲል በመግለጽ የተሰጠው የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ እንዲሰረዝ ጠይቋል።

ባለስለጣኑ በተጨማሪም “በሆንግ ኮንግ ሺንግሹ ማዕድን ያገኘውን የታደሰ የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ “እውቅና እንደማይሰጠው” አስታውቋል።አስካሪ ሜታልስ የነጆ ወርቅ ፕሮጀክትን ሙሉ በሙሉ ጠቀለለው በሚል የቀረበውን መረጃ በተመለከተ አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የሆንግኮንጉ ኩባንያ ሺንግሹ ማዕድን የሀገር ውስጥ ስራ አስኪያጅ ሱራፌል ወንድማገኝ የመገናኛ ብዙሃኑ ዘገባዎች ትክክል አይደሉም ሲሉ አስተባብለዋል።

ሙሉውን ለማንበብ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8557

@YeneTube @FikerAssefa
31
በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው የሆነ የፖስ ማሽን መገጣጠሚያ ፋብሪካ በኢትዮጵያ ተመረቀ!

ሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን በኢትዮጵያ እና በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የፖስ ማሽን መገጣጠሚያ ፋብሪካውን እና ዘመናዊ የክፍያ ስዊች ሲስተምን በይፋ ማስጀመሩን አስታውቋል።ይህ ፋብሪካ የሀገሪቱን ጥሬ ገንዘብ አልባ የግብይት ስርዓት ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት ይጠበቃል።

በቀን 3,000 ዘመናዊ የፖስ ማሽኖችን የማምረት አቅም ያለው ይህ ፋብሪካ፣ በኢትዮጵያ ልጆች ተገጣጥመው በአገር ውስጥ በተገነቡ ሶፍትዌሮች የታገዙ ማሽኖችን ለባንኮች እና ለተለያዩ የንግድ ተቋማት ማቅረብ ጀምሯል ተብሏል።

ይህ የሀገር ውስጥ ምርት ከዚህ ቀደም ፖስ ማሽኖችን ከአውሮፓና ከቻይና በመግዛት ለሃርድዌር እና ለሶፍትዌር ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንደሚያድን የኩባንያው መግለጫ ያመለክታል።

ከፋብሪካው ጎን ለጎን የጥገና ማዕከልም የተቋቋመ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ለጥገና ወደ ውጭ አገር ይላኩ የነበሩ የፖስ ማሽኖች በአገር ውስጥ እንዲጠገኑ ያስችላል መባሉን ሳንቲም ፔይ አስታዉቋል።

ይህም አገልግሎት የማይሰጡ ማሽኖችን ወደ ስራ በመመለስ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።በተጨማሪም ሳንቲምፔይ ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ከሚገኘው ሳኑ ፔይ ጋር በመተባበር ዘመናዊ የክፍያ ስዊች ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ለባንኮች እና ለፋይናንሻል ተቋማት ዘመናዊ የክፍያ አገልግሎቶችን ማቅረብ እንደሚጀመር ከመግለጫዉ ለመረዳት ተችሏል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
28😁9👍4😭1
ሕወሓት ፌደራል መንግሥቱን ከሰሰ!

ሕወሓት፣ የትግራይ ሕዝብ ፍትሃዊ ጥያቄ በጦርነት ዛቻ ሊታፈን አይችልም ሲል ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አቋሙን ገልጧል።

ከመሃል አገር ከሄደ የኃይማኖት ልዑካን ቡድን ጋር ሰሞኑን መወያየቱን የገለጠው ሕወሓት፣ የልዑካኑ አባላት በትግራይ ያለው "የሰላም ፍላጎት" እና "ዝግጁነት" ቀደም ሲል ከሠሙት የተለየ መኾኑን ተናግረዋል ብሏል።

ሕወሓት፣ በትግራይ በኩል ለግጭት የሚጋብዝ እንቅስቃሴ በሌለበት ኹኔታ ፌደራል መንግሥቱ የማስፈራራት ዘመቻ እያካሄደ፣ የታጠቁ ሃይሎችን እያደራጀና እያስታጠቀ ይገኛል በማለትም መክሰሱን ዋዜማ ዘግባለች፡፡

መንግሥት በግጭት ማቆም ስምምነቱ መሠረት ግዴታውን እስካልተወጣ ድረስ፣ የትግራይ ሕዝብ ከመሪ ድርጅቱ ጋር ለኅልውናውና ሉዓላዊነቱ ሠላማዊ የፖለቲካ ትግሉን ይቀጥላል ሲል ሕወሓት አቋሙን ገልጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
58😁19👎8👍7
የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 135.3 ሚሊዮን ደረሰ!

የተባበሩት መንግሥታት የስነ-ሕዝብ ፈንድ  (ዩ ኤን ኤፍ ፒ ኤ) በ2025 የዓለም ሕዝብ ቁጥር ሪፖርት ባወጣው መረጃ መሠረት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ወደ 135.3 ሚሊዮን ደርሷል። ይህ አኃዝ የመጣው ኢትዮጵያ በ1985 ዓ.ም. ከጸደቀ ከሶስት አስርት ዓመታት በኋላ አዲስ ብሔራዊ የሕዝብ ቁጥር ፖሊሲ ለማውጣት በዝግጅት ላይ ባለችበት ወሳኝ ወቅት ነው።

የፖሊሲው ማሻሻያ እና የተመዘገቡ ስኬቶች
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የአዲሱ ፖሊሲ ማሻሻያ ሂደት መሪ ሲሆን፣ ፖሊሲው የኢትዮጵያን አሁን ያለውን የሥነ ሕዝብና ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች እንደሚያንፀባርቅ ገልጿል። ይህም የሀገሪቱን የልማት ቁርጠኝነት እና ዓለም አቀፍ የዘላቂ ልማት ግቦችን (SDGs) ለማጣጣም ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

የሚኒስቴሩ የሕዝብና ልማት ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ ጌታቸው፣ የመጀመሪያው ፖሊሲ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ መሻሻሎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

“የሀገሪቱ የድህነት ምጣኔ ከ45.5% ወደ 19% ቀንሷል” ያሉት አቶ ሀብታሙ፣ የጨቅላ ሕፃናት ሞት መቀነስ፣ የወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም መጨመር እና የትምህርት እድገት መታየቱን አብራርተዋል።

ትንበያዎች እንደሚያመለክቱት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በ2035 ከ170 ሚሊዮን በላይ ሊሆን እንደሚችል እና በ2050 ወደ 225 ሚሊዮን ሊጠጋ ይችላል። ይህ እያደገ የመጣው ሕዝብ ዕድሎችንም ሆነ ተግዳሮቶችን የሚያመጣ ሲሆን፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን፣ ትምህርትን፣ ጤናን፣ ሥራ ስምሪትን እና የአካባቢ ጥበቃን የሚደግፉ ፖሊሲዎችን ይጠይቃል።

ዝርዝር ዘገባዉ :

here

@YeneTube @FikerAssefa
42👀10😁3🔥2😭1
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
5👎1😁1
ትራምፕ ለሶስተኛ ጊዜ አሜሪካ ለታላቁ የ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች ሲሉ የተሳሳተ ንግግር አደረጉ!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ዕለት የሪፐብሊካን ሴናተሮችን በዋይት ሀውስ ተቀብለው ባስተናገዱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገለት ሲናገሩ ተደምጠዋል።

“ኢትዮጵያ ግድቡን የገነባችው በአብዛኛው በአሜሪካ ገንዘብ ነው” ሲሉ በአንድ ወር ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ተናግረዋል።

እውነታው ግን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተገነባው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ህዝብ በህዝባዊ መዋጮ እና በአገር ውስጥ ሀብት መሆኑ ነው። በተጨማሪም ግድቡ ለግብፅ የውሃ ደህንነት ምንም አይነት ስጋት አይፈጥርም።

@YeneTube @FikerAssefa
😁3413👎9👀1
YeneTube
Photo
"ኢፈርት በክልሉ የተፈጠረው የፖለቲካ ልዩነት ሰለባ ሁኗል፣ለህዝቡ ጥቅም ሲባል ጊዜያዊ አስተዳደር ጣልቃ ለመግባት ይገደዳል" - ሌ/ጀ ታደሰ ወረደ

የትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኢፈርት) እና ያቀፋቸው ድርጅቶች በትግራይ ክልል የተፈጠረው ልዩነት ሰለባዎች ሁነዋል ሲሉ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለጹ።በዚህም ምክንያት የሶስተኛ ወገን ጣልቃ እንዲገባ የሚያደርግ እና እየሰፋ የሄደ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት ለሁለት ቀናት ሐምሌ 12 እና 13 ቀን 2017 ዓ.ም በመቀለ ከተማ በተካሄደው ትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኢፈርት) አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ተቋሙ ስላጋጠመው አደጋ እና ከተሳታፊዎቹ ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

በኢፈርት የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ ጉዳዩ በህግ እንዲታይ መቅረቡን ጠቁመው ይህም በባሰ ደረጃ ጉዳዮቹን ሊያወሳሰበው ይችላል ብለዋል፤ ተቋሙ ላጋጠመው ችግር ሁሉም መወገኖች በከፍተኛ የህዝብ ሀላፊነት በምክክር እና በትዕግስት እንዲፈቱት አሳስበዋል።

ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ለህዝብ ጥቅም ሲባል የጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለበት ሃላፊነት እጁን በማስገባት ሊፈታው እንደሚገደድ አሳታውቀዋል፤ “ለህዝቡ ጥቅም ሲባል የጊዜያዊ አስተዳደሩ ጣልቃ ለመግባት ይገደዳል” ብለዋል።

በኢፈርት መተዳደሪያ ደንብ መሰረት አንድ ሶስተኛ የምክር ቤቱ አባላት ፒቲሽን በማሰባሰብ ጉባኤ መጥራት እንደሚችሉ መደንገጉን ተከትሎ የተጠራ ጉባኤ መሆኑን ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ህጋዊ የትዕምርት ባላደራ ቦርድ መሆኑን በመግለጽ ላይ የሚገኘው በአቶ ቴዎድሮስ ሀጎስ የሚመራው አካል በበኩሉ የትግራይ ፍትህ ቢሮ ያሳለፈውን ውሳኔ በመጥቀስ በሁለቱ ቀናት የተካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ህግን የጣሰ እና በኢፈርት ስር የሚገኙ ድርጅቶችን በቀጣይ ቀውስ ውስጥ የሚከት አካሄድ ነው ማለታቸውን ዘገባዎቹ ጠቁመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
33
4
YeneTube
Photo
የውጊያ ጄት በትምህርት ቤት ውስጥ ተከስክሶ ቢያንስ 19 ተማሪዎች ሲሞቱ ከ50 በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸው ተገለጸ

📌የብሔራዊ ሃዘን ቀን ታውጇልም ተብሏል

#Ethiopia | በባንግላዲሽ ዋና ከተማ ዳካ በሚገኝ አንድ የኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ የባንግላዲሽ አየር ኃይል ማሰልጠኛ ጄት ተከስክሶ ቢያንስ 19 ሰዎች ሲሞቱ ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል። አብዛኞቹ ተጎጂዎች ወጣት ተማሪዎች እንደሆኑ ተገልጿል። አገሪቱ ብሔራዊ የሐዘን ቀንን እንዳወጀችም ተሰምቷል።

ኤፍ-7 ቢጂአይ (F-7 BGI) የተሰኘው አውሮፕላን በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ 7 ሰአት ላይ ከፍ ካለ በኋላ፣ ከአስራ ሁለት ደቂቃ ገደማ በኋላ በዋና ከተማዋ ሰሜናዊ ክፍል በኡታራ ዲያባሪ አካባቢ በሚገኘው ማይልስቶን ትምህርት ቤት እና ኮሌጅ ካንቲን አቅራቢያ ተከስክሷል ሲል የኢንተር-ሰርቪስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት (ISPR) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የባንግላዲሽ ጋዜጣ ፕሮቶም አሎ እንደዘገበው ወታደራዊው አውሮፕላን አደጋው ሲከሰት በርካታ ወጣት ተማሪዎች በቦታው በነበሩበት ወቅት የምሳ ሰዓት ላይ ከትምህርት ቤቱ ካንቲን አጠገብ ተከስክሷል ብሏል ዘገባው። የመጀመሪያው የሟቾች ቁጥር አንድ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ የእሳት አደጋና ሲቪል መከላከያ ዳይሬክተር ጀኔራል ብሪጋዴር ጀኔራል መሐመድ ዛሂድ ከማል ወደ ስፍራው ከደረሱና ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ከሰጡ በኋላ የሟቾች ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል ነው የተባለው።

ነገ ማክሰኞም የብሔራዊ የሐዘን ቀን ታውጇል ነው የተባለው፡፡

የባንግላዲሽ ኤፍ-7 የቻይና ቼንግዱ ኤፍ-7 ዘመናዊ ስሪት ሲሆን እሱም በሶቪየት ሚግ-21 ላይ የተመሰረተ ነው ተብሏል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ጊዜ ያለፈበት ቢሆንም፣ ወጪ ቆጣቢነቱ እና ለአብራሪ ስልጠናና ለተገደበ የውጊያ ሚናዎች ተስማሚ በመሆኑ አገልግሎት ላይ ይገኛል ነው የተባለው።

ቻይና የመጨረሻዎቹን 16 የኤፍ-7 ቢጂአይ አውሮፕላኖችን ለባንግላዲሽ በ2013 ዓ.ም. ከሰጠች በኋላ ምርቱ ቆሟል ተብሏል ሲል የዘገበው መናኸሪያ ሬዲዮ።
@Yenetube @Fikerassefa
😭1412
Forwarded from LinkedIn Ethiopia
⚠️ ''ደሞዝተኛ እናድርግዎ''

🚨 በሳምንት ከ1,000 - 4,000 ብር ተከፋይ ይሁኑ

🌐 ከተከፈቱ ከአንድ ዓመት በላይ የሆኑ የLinkedin አካውንቶችን በማከራዬት በሳምንት ጠቀም ያለ ክፍያ ያግኙ !

⚠️መስፈርቶች

💠ከተከፈተ ከ1 ዓመት እና ከዛ በላይ የሆነ
💠ምንም Friend (Connection) ባይኖረውም እንከራያለን

📮 የክፍያው መጠን በተከፈተበት ዓመት ቆይታ ይወሰናል።

☎️+251934848429 ይደውሉልን

⬛️ በውስጥ መስመር ➡️
@linkedin_ethiop ያግኙን

🌐 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ➡️ @linkedin_ethiopiaa
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
12👍1
🇪🇹 የኢትዮጵያ መንግሥት አይኤምኤፍ ብሔራዊ ባንክ በገለልተኛ ባለሙያዎች እንዲመራ ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ ውድቅ አደረገ

የዓለም የገንዘብ ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግሥት የኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም ጋር በተያያዘ የባንኩን ተቋማዊ ነጻነት ለማረጋገጥ ገዥው፣ ምክትላቸው እና የባንኩ የቦርድ አመራሮች ገለልተኛ እንዲሆኑ በ2017 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ሃሳቡን አቅርቦ እንደነብር የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ነው የዘገበው፡፡

ሆኖም የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ሕገ-መንግሥቱን ይቃረናል በማለት እንዳልተቀበሉት አይኤምኤፍ ገልጿል፡፡

አበዳሪው በተሻሻለው አዲሱ የብሔራዊ ባንክ አዋጅ መሠረት በቀጣዮቹ ወራት ሦስት ገለልተኛ የቦርድ አመራሮች ሊመድቡ እንደሚገባ አሳስቧልም ነው የተባለው፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
35😁26🔥3👍2👎1
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
4
የምስራች 🎉🎉🎉📍አሚስኮ ሪልስቴት(AMISCO RealEstate)
ለቡ ሙዚቃ ሰፈር

☎️09-03-97-85-64

👍👍ለ 5 ቤት ብቻ የተደረገ ልዩ ቅናሽ

           🏠🏠 በካሬ 75ሺ ብር ብቻ (በከፊል ማጠናቂያ)
100% ለሚከፍል በካሬ=65ሺብር

        📌ባለ 3መኝታ 183.7ካሬ
👍ጠቅላላ = 13,777,500 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,133,250ብር
      ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
100%ለከፈለ =11.9ሚሊየን ብር

         📌ባለ 3መኝታ 192.69ካሬ

👍ጠቅላላ = 14,451,750 ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4,335,525ብር
      ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
100%ለከፈለ =12.5ሚሊየን ብር


       📌ባለ 3መኝታ 194.67ካሬ

👍ጠቅላላ = 14,600,250ብር
👍30% ቅድመክፍያ = 4.3ሚሊየን ብር
      ቀሪውን በ1&1/2ዓመት የሚከፍሉት
100%ለከፈለ =12.6ሚሊየን ብር

ሳይቱ የሚያሟላቸው ነገሮች
👉B+G+12+terrace
👉 90% የተጠናቀቀ
👉 ምቹ መኖሪያ ሰፈር
👉የተሟላ እና በቂ ፓርኪንግ
👉 የጋራ አዳራሽ
👉 የደህንነት መጠበቂያ ካሜራ
👉 የከርሰ ምድር ውሃ
👉 ዋና ገንዳ
👉 ጂም እና እስፓ
👉 የልጆቹ መጫወቻ
👉 ደህንነቱ የተጠበቀ የመኖሪያ መንደር
👉 የቆሻሻ ማስወገጃ
👉እሳት አደጋ ማጥፊያ
👉 ተጠባባቂ ጀነሬተር
👉 ሊፊት
👉ሰፊ ቴራስ
👉6500 ካሬ ላይ ያረፈ ጊቢ
👉ግሪን ጋርደን
👉በ100ሜ ርቀት የእምነት ተቋማት


   የሚያስፈልግዎትን ሁሉ በአቅራቢያዎ የሚያገኙበት
ለበለጠ መረጃ ☎️09-03-97-85-64 ይደውሉ
10🔥2