YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
"የተፈናቃዮችን ሙሉ ደኅንነታቸውን ባስጠበቀ መልኩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው" - ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረዳ "የተፈናቃዮችን ሙሉ ደኅንነታቸውን ባስጠበቀ መልኩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው" ሲሉ ገለጹ።

ፕሬዝዳንቱ ይህንንያሉት በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዳይሬክተር አንድሪው ምቦጊሪን ትላንት ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረዳ አንድሪው ምቦጊሪን ጋር በነበራቸው ቆይታ “ያለ ደህና መጠለያ እና ምግብ ተጥለው በከፍተኛ ችግር ላይ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለአምስተኛ የክረምት ወራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ህይወታቸውነ እያሳለፉ ማየት በጣም ከባድ ነው” ሲሉ መናገራቸውን ከጽ/ቤታቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዳይሬክተር አንድሪው ምቦጊሪን በበኩላቸው በክልሉ በተካሄደው አስከፊ ጦርነት ሳቢያ ቤታቸውን ጥለው የተሰደዱ የክልሉ ነዋሪዎችን ተቋማቸው ተቀብሎ መጠለያ እና ምግበ እንዲያገኙ ማድረጉን አስታውሰው በቀጣይ በሚደረገው የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ይሁን በቀያቸው እስኪቋቋሙ ድረስ ተቋማቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል መግባታቸውን መረጃው አካቷል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
34👀3
ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲን ከምዝገባ ከመሰረዙ በፊት እስከ አምስት ዓመት ማገድ የሚያስችል አዋጅ ማሻሻያ በምክር ቤቱ ፀደቀ!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲን ከምዝገባ ከመሰረዙ በፊት እስከ አምስት ዓመት ማገድ የሚያስችል የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅን ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው በ2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው አፀደቀ።

የታገደ የፖለቲካ ፓርቲ እገዳው ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜያት ከማንኛውንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ፣ በየትኛውም ደረጃ በሚደረግ ምርጫ ላይ እንዲሁም በጋራ ምክር ቤቱ ውስጥ መሳተፍ ይከለክላል። ከመንግስት ከሚሰጥ ደጋፍ ተጠቃሚም አይሆንም።

በጸደቀው አዋጅ ዙሪያ አስተያየታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ የሰጡ የወላይታ ዲሞክራሲያዊ ግንባር አመራሩ ጎበዜ ጎኣ “ምርጫ ቦርድ አሻሻሎ ባስጸደቀው ህግ ገዢው ፓርቲ ብቻውን ቢወዳደር እንጂ ሌላው ሰው የሚወዳደርበት ምንም አይነት ሜዳ የለም” ብለዋል። “ፓርቲዎችን ከምርጫ ሜዳ የሚያስወጣ ነው” ሲሉም ተችተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
😁2518👎2
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
👍31
ተቃዋሚው ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው፣ "የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያልያዙ ፖሊሶች" ቢሸፍቱ ከተማ ከሚገኘውና ከአገር ከመውጣታቸው በፊት ለ10 ዓመት ከኖሩበት ቤት በ10 ቀናት ውስጥ እቃቸውን እንዲያወጡ የሚያስጠነቅቅ ደብዳቤ ቤቱ ላይ ለጥፈው እንደሄዱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኀን ባሠራጩት መረጃ አስታውቀዋል።

ደብዳቤው፣ ቤቱ "ለማኅበራዊ ፖሊስ" አገልግሎት እንደሚፈለግ የሚገልጽ መሆኑን ልደቱ ገልጸዋል። ልደቱ፣ በ10 ቀናት ውስጥ ቤቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ካልወጣ፣ ፖሊስ ርምጃ እንደሚወስድ በደብዳቤው ላይ ማስጠንቀቁንም ጠቅሰዋል።

የማስጠንቀቂያ ትዕዛዝ የያዘውን ደብዳቤ የጻፈው፣ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሆራ አርሰዴ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት እንደኾነም ልደቱ ገልጸዋል።

[ዋዜማ]
@YeneTube @FikerAssefa
😁3118👎13😭21
በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የተቋቋመው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) የፓለቲካ ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤቱ በመቐለ ከፈተ።

በተጨማሪም ፓርቲድ የመቐለ እና ደቡባዊ ምስራቕ ዞን ቅርንጫፍ ቢሮዎች ከፍቷል።

ፓርቲው እንዳስታወቀው ዋና ፅህፈት ቤቱ በመቐለ በመክፈት የፓለቲካ ስራውን በግልፅ ጀምሯራ።

ፓርቲው በሁሉም የትግራይ የዞን ፣ የወረዳና ከተሞች ፓለቲካዊ ፅህፈት ቤቶች መክፈት እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የመረጃ ምንጮች እንዳሉት ከአንድ ወር በፊት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ  የምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና ያገኘው ስምረት ፓርቲ ለምስረታ ብቁ የሚያደርጉት አባላት መልምሎ ጨርሷል።

የክልል ፓርቲ ለመመስረት የሚስፈልገው 4 ሺህ በላይ መስራች አባላት መልምሎ ለይፋዊ ምስረታ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የመረጃ ምንጮቹ ተናግረዋል።

ስምረት ፓርቲ በቀጣዩ የነሀሴ ወር 2017 ዓ.ም በትግራይ ይፋዊ ምስረታ በማከናወን ከቅድመ እውቅና ወደ ሙሉ እውቅና እንደሚሸጋገር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@Yenetube
28👍1
ሰበር

የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአለልኝ ባለቤት እና የባሌቤቱ እህት ባልን በተጨዋቹ ሞት ጥፋተኛ ናቸው ብሎ ወስኗል::

ፍርድ ውሳኔውን ለመስማት ለከሰዓት ቀጠሮ ታይዟል::

አለልኝ አዘነ ራሱን አጥፍቶ አልሞተም!

ሸገር ስፖርት
44👍16😭61
ጠ/ሚኒስትሩ ከትግራይ ህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያዩ!

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ህብረተሰብ ተወካዮች ጋር በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን፤ ምክክሩ በተፈናቃዮች፣ በትግራይ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

ጠ/ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግበራ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን መቅረፍ በሚቻልበት መንገድና የትግራይን ማገገምና ወደ መደበኛ ህይወት መመለስ በተመለከት ከተወካዮቹ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍1311👎11🔥2
ለተቀጣሪ ሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲኖር ማድረግ እንደ አንድ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ እየታየ ነው ተባለ።

ከኢትዮጵያ ምርቶችን የሚገዙ የአውሮፓ ሀገራት እና አሜሪካ ጉዳዩን እንደ አንድ ቅድመ ሁኔታ እያቀረቡት እንደሆነ ተጠቅሷል።

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል በኢትዮጵያ በህግ እንዲወሰን ካልተደረገ እነዚህ ሀገራት ምርቶችን ከኢትዮጵያ መግዛት ሊያቆሙ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር ባዘጋጀው አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ሲነገር ሠምተናል።

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር ዛሬ ሲኤምሲ በሚገኘው መስሪያ ቤቱ ማካሄድ የጀመረው አለም አቀፍ ጉባኤ እስከ ነገ ይቆያል።

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዙሪያ የተዘጋጁ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበውም ተሳታፊዎች እየተወያዩባቸው ነው።

ማህበሩ እንዲህ አይነቱን አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ሲያዘጋጅ የዘንድሮው ለ22ኛ ጊዜ እንደሆነ ሠምተናል።

ከ34 ዓመት በፊት የተመሠረተው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር አሁን ከስድስት ሺህ በላይ አባላት አሉኝ ብሏል።

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
53👍1
በአፋር ክልል መነሻ ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት አደጋ ሁለት ሰዎች ሲጎዱ ከ1 ሺህ 800 በላይ ቤቶች ተቃጠሉ!

በአፋር ክልል ዳሎል ወረዳ ትናንት ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት አከባቢ በደረሰ ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት አደጋ ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱንና 1 ሺህ 805 ቤቶች መቃጠላቸውን የዳሎል ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡስማን አሕመድ ገለጹ።

በአደጋው በበዳ-አድሙሩግ ቀበሌ 600 ሱቆች፣ 950 ምግብ ቤቶች እና 255 መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ኃላፊው ለኢቢሲ ተናግረዋል።በተጨማሪም ከ20 በላይ የሚሆኑ የቤት እንስሳት በእሳት አደጋው መሞታቸውን ገልጸው
ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል።

አክለውም በክልበቲ ረሱ ዞን የሚገኘው የአብኣለ እና በራህሌ ሆስፒታል ባለሙያዎች በአከባቢው በመገኘት የሕክምና ድጋፍ እየሰጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል። የተነሣውን እሳቱ እስካሁን ድረስ ማጥፋት አለመቻሉ የተገለጸ ሲሆን በአደጋው ቤት ንብረት የወደመባቸው የቀበሌዋ ነዋሪዎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
17😭16👍1
Spiritual Gift መንፈሳዊ ስጦታ
YAHO💚 WOMEN'S GIFT PACKAGE
- ነጠላ
- ዉዳሴ ማርያም
- የሚያበራ ምስል 
- ሽቶ
FREE DELIVERY

⨳ዋጋ 3500br

For order @Fikerassefa
10😁5
ማስታወቂያ

በZoje Digital slightly Used ማሽን interlock, Overlock, Single needles machine ያላቹ በዚህ @Fikerassefa ያናግሩን።
6
ኤርትራ 10 ኪ.ሜ ወደ ኢትዮጵያ ገብታለች
በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ የጀርመን ዜና ወኪል ከስፍራው አንድ ዘገባ አሰራጭቷል፡፡


በመቀሌ ነዋሪ የሆኑ አንዲት ለዜና አውታሩ ሲናገሩ ‹‹አሁን ላይ ሆነን ምንም ማቀድ አንችልም፡፡ አዲስ ጦርነት ነገ ሊጀመር ይችላል፡፡›› ያሉ ሲሆን ነዋሪው በዚህ የተነሳ ከፍተኛ ፍርሀት ውስጥ መውደቁን አስረድተዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹ኑሮ በጣም እየተወደደ ነው፡፡ እኛ ሰላማዊ መፍትሄ መጥቶ ወደስራችን መመለስና ህይወታችንን መልሰን መገንባት ነው የምንፈልገው›› ብለዋል፡፡

እንደዘገባው በህወሀት ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል ተከትሎ የትግራይ መከላከያ ሀይል(ቲዲኤፍ) ዋና አዛዥ የነበሩት ታደሰ ወረደ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ሆነዋል፡፡፡ እሳቸው በህዝቡ ዘንድ ያለውን ስጋት በማጣጣል ‹‹ጦርነት አይኖርም፡፡

ከትግራይ በኩል ምንም አይነት ቀስቃሽ ሁኔታ የለም›› በማለት እየተናገሩ መሆናቸውንም አስረድቷል፡፡ ዘገባው ሲቀጥል በሌላ በኩል የህወሀት ሊቀመንበር የሆኑት ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ደግሞ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ለተፈጠረው ችግር ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲፈለግ እያሳሰቡ መሆናቸውን ገልጿል፡፡ የፌዴራል መንግስቱና አጋሮቹ ለጦርነት እያደረጉ ካለው ዝግጅት እንዲቆጠብ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና እንዲያደርግበት ጥሪ ማቅረባቸውንም አስረድቷል፡፡

ይሁንና እነዚህ ሁሉ የመቀሌ ነዋሪዎችን ስጋት እንዳልቀረፉ ገልጿል፡፡ አንድ የከተማው ነዋሪ ሲናገሩ ‹‹ህዝቡ አሁን ከባንክ ገንዘብ እያወጣ ነው፡፡ እንደጤፍ የመሳሰሉ እህሎችም ከመጋዘን እያለቁ ነው›› ያሉ ሲሆን ለሁለቱም የህወሀት አንጃዎችም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በመልእክታቸውም ‹‹ሁለቱም የህወሀት አንጃዎች ወይ ስልጣን ይልቀቁ፣ አልያም ተፅእኗቸውን ተጠቅመው ከማእከላዊው መንግስት ጋር ይህንን ቀውስ ለማስወገድና ጦርነትን ለማስቀረት ይስሩ›› ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ድጋሚ ጦርነት ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት እንዳለ የጠቀሰውዘገባው በዚህ ጉዳይ የጀርመን አለም አቀፍና የደህንነት ጉዳዮች ኢኒስቲትዩት የአፍሪካ ጉዳዮች ኤክስፐርት የሆኑትን ጊርት ኩርዝ ማነጋገሩን አስታውቋል፡፡

ኩርዝ ለዜና አውታሩ በሰጡት ማብራሪያ ሁለቱ አገራት ሙሉ ጦርነት ውስጥ ይገባሉ የሚል እምነት እንደሌላቸው ጠቅሰው ይሁንና በውክልና የሚደረግ ግጭት እንደሚኖር አስረድተዋል፡፡

ዘገባው አያይዞም ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት 10 ኪሎሜትር መግባቷንና ጦር እያሰለጠነች መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።

@Yenetube @Fikerassefa
63👍1👀1
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
8
የሞሳድ ኃላፊ የጋዛ ነዋሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ፣ ሊቢያና ኢንዶኔዥያ ለማዘዋወር አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ መጠየቃቸው ተዘግበ!

የእስራኤል የስለላ ድርጅት (ሞሳድ) ኃላፊ ዴቪድ ባርኔያ የጋዛ ነዋሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ፣ ሊቢያ፣ ኢንዶኔዥያ ለማዘዋወር አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ የሀገሪቱን ልዩ መልዕክተኛ መጠየቃቸው ተዘግበ።የሞሳድ ኃላፊው ይህን ጥያቄ ያቀረቡት በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን ባደረጉት ጎብኝት ወቅት መሆኑን አክሲዮስ ዘግቧል።

እስራኤል ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ለማዘዋወር የትራምፕን አስተዳደር እርዳታ እየፈለገች መሆኑን ጉዳዩን የሚያውቁ ሁለት ምንጮችን ጠቅሶ የዜና አውታሩ ዘግቧል፣ ሁለቱ ምንጮች እንደገለፁት፤ የሞሳዱ ኃላፊ ባርኔያ፤ ኢትዮጵያ፣ ኢንዶኔዥያ እና ሊቢያ ከጋዛ የፍልስጤማውያን ስደተኞችን ለመቀበል ፈቃደኝነት አሳይተዋል ሲሉ ለአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ተናግረዋል። እናም ዋሽንግተን እነዚህ ሀገራት ስደተኞችን ለማዛወር እንዲስማሙ “ማበረታቻ” መስጠት አለባት ማለታቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ስቲቭ ዊትኮፍ በጉዳዩ ላይ ቁርጠኛ አልነበረም ሲሉ አንደኛው ምንጭ ገልጿል።የአሜሪካ ባለስልጣናትም ከአረብ ከሀገራት ተቃውሞ የሚያከትል በመሆኑ ዋይት ሀውስ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማስወጣት ፍላጎት እንደሌለው ገልጸዋል ሲል ዘገባው አክሏል።

ከወራት በፊት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ሰርጥ ግንባት ሲጀመር የጋዛ ነዋሪዎች በሙሉ ላልተወሰነ ጊዜ ወደሌላ ቦታ እንዲዘዋወሩ ሀሳብ ማቅረባቸው ይታወቃል። ሀሳቡን የእራኤሉ መሪ ኔታንያሁ እና ጥምረታቸው ሲደግፉ፣ የአረብ ሀገራት እና አብዛኛው የምዕራቡ ዓለም በብርቱ ተቃውመውታል።

Via Axios/AS
@YeneTube @FikerAssefa
33😁23😭6👎4🔥1
በደብቡ ወሎ ዞን ከተለያዮ የኢትዮጱያ አካባቢ ተፈናቅለዉ በመጠለያ ካምፕ ዉስጥ የሚገኙ የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ዝናቡ በመጨመሩ መጠለያ ድንዃኖቻቸዉ እየፈረሱና ዝናብ እያስገቡ መሆኑን ተናገሩ።

ለስድስት ወራት አገልግሎት እንዲሰጡ የመጡ የመጠለያ ድንዃኖች ለሶስት አመት ያገለገሉ ሲህን በፀሀይና ዝናብ ብዛት ተቀዳዶ አገልግሎት የማይሰጥበት ደረጃ ላይ ደርሶል ብለዋል።ነፍሰ ጡር እናቶች ህፃናትና አረጋዉያን በከፍተኛ ችግር ዉስጥ እንዳሉም ተነግሯል።

ከ4 ዓመታት በፊት በሞቀ ጎጃቸው ውስጥ ሆነው የክረምቱን መምጣት በጉጉት የሚጠብቁ የሚያርሱ እና የሚያመርቱ ገበሬዎች ነበሩ፡፡ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ የሰላም መደፍረሶች ቤታቸውን ትተው የተፈናቀሉት እነኝህ በደቡብ ወሎ ዞን ባሉ 11 የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ቁጥራቸው ከ14 ሺ የሚልቅ ተፈናቃዮች ዛሬ ላይ ግን የተጠለሉበት የሸራ ድንኳን እና ላስቲክ ከክረምቱ ዝናብ የሚያስጥል ሆኖ አላገኙትም፡፡ ለበረከት ሲፈልጉት የነበረው ዝናብም ቤታቸውን አፍራሽ ሆኗል ነው የሚሉት፡፡

‹‹ በክረምቱ ብዙ ሰዎች ተቸገሩብን፤ ዝናብ እየጎዳን ነው በጣም ከብዷል፡፡ አሁን ከሞቱት እኛ እንሻላለን የሚል ነው እንጂ ዝናቡ ከባድ ነው፡፡›› ‹‹የዝናቡ ነገር አላህ ይዞት ነው እንጂ ልብስ ደራርበን ነው የምንተኛው በጣም ነው የተቸገርነው››፡፡ ማለታቸውን DW ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
20😭3👍1