YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በደቡብ አፍሪካ 44 #ኢትዮጵያውያን አንድ ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው መገኘታቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ

በደቡብ አፍሪካ #ጁሃንስበርግ 44 ኢትዮጵያውያን አንድ ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው መገኘታቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ።

በጁሃንስበርግ በአንድ ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ናቸው የተባሉት 44ቱ ኢትዮጵያውያኑ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ደቡብ አፍሪካ የገቡ ሳይሆኑ አልቀሩም ሲል ፖሊስ ገልጿል።

ትላንት ሚያዚያ 23 ቀን 2017 ሰባት ሰአት ተኩል አከባቢ በአንድ ቤት ግቢ ውስጥ አጠራጣሪ ድምጽ በመሰማቱ ፖሊስ ኦፐሬሽኑን ማካሄዱን የሀገሪቱ ጋዜጣ ኒውስ 24 ተመለከትኩት ያለውን የጆሃንስበርግ ፖሊስ ሪፖርት ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።

የከተማዋ ፖሊሶች ወደ ቤቱ ቅጥር ግቡ በመግባት ፍተሻ ሲያደርጉ በሁለት ክፍል ውስጥ 44 ኢትዮጵያውያኑ ተቆልፎባቸው መገኘታቸውን ዘገባው አመላክቷል።

አንዱ ብቻ በተሰባበረ እንግሊዝኝ ከፖሊሶች ጋር ለመነጋገር መሞከሩን የጠቆመው ዘገባው ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ለፖሊስ መግለጹን አስታውቋል።

በግቢው ውስጥ የነበረው ሁኔታ አስከፊ መሆኑን ፖሊስ በሪፖርቱ አመላክቷል ያለው ዘገባው ኢትዮጵያውያኑ በቂ ምግብ እንዳልቀረበላቸው፣ ከተቆለፈባቸው ክፍል እንዳይወጡ መደረጋቸውና የፀሃይ ብርሃን አይተው እንደማያውቁ እንዲሁም ደህና ልብስ እንኳ እንደሌላቸው አስታውቋል።

ባሳለፍነው አመት 2016 ዓ.ም ሐምሌ ወር ላይ የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ “ኢ-ሰብአዊ በሆነ ሁኔታ” ታጋተው የነበሩ ናቸው ያላቸው 90 ኢትዮጵያውያንን አስለቅቂያለሁ ሲል መግለጹን የተመለከተ ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል።
@Yenetube @Fikerassefa
😭30👍245