YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
" እስካሁን የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል። የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል " - ፖሊስ

ዛሬ ከቀኑ 7 ሠዓት 30 ከሙከጡሪ ወደ ጂዳ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ አይሱዚ ቅጥቅጥ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከለሚ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው ከባድ የትራፊክ አደጋ መድረሱን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

አደጋው የደረሰው በኦሮሚያ ክልል፤ በሰሜን ሸዋ ዞን ዋጫሌ ወረዳ ሙከጡሪ ከተማ አቅራቢያ መቼላ ቀበሌ ቄሌምቶ ላይ ነው።

እስከ አሁን የ6 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ከሟቾች በተጨማሪ 21 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በሌሎች 17 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ የዞነ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ክፍል ኃላፊ ም/ ኢንስፔክተር ታከለ ቶሌራ ተናግረዋል፡፡

የአደጋ ከባድ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር  አሁን ካለው ሊጨምር እንደሚችል ተጠቁሟል።


Via :- ኤፍኤምሲ
@Yenetube @Fikerassefa
😭17👍161
ከ14 አመት በፊት የሙምባይ የሽብር ጥቃት አቀናባሪ የተባለው የሀፊዝ ሰኢድን ፓኪስታን አስሬዋለው ብትልም የህንድ መገናኛ ብዙሃን ደግሞ  በላሆር እጅግ የቅንጦት እና ጥብቅ ጥበቃ የሚደረግበትን  ቦታ እየኖረ ነው አሉ


ፓኪስታን ሳኢድ ከእስር ቤት ውጭ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ብትገልጽም፣ የህንድ መገናኛ ብዙሃን አገኘነው የሚሉት  አዳዲስ የሳተላይት ምስሎች እና ቪዲዮዎች 24/7 ጥበቃ እየተደረገለት በምቾት እንደሚኖር ያሳያሉ።

ሙምባይ የሽብር ጥቃት ዋና አቀናባሪ እና የላሽካር ኢ ጦይባ  መሪ የሆነውን እና አሁን ደግሞ ሚያዝያ 14 ቀን በፓሃልጋም 26 ንፁሀን ዜጎችን ለሞት ላበቃው የሽብር ጥቃት አቀናባሪ ተብሎ የሚጠረጠረውን የሀፊዝ ሰኢድን አሁን የሚገኝበትን መደበቂያ ቦታ በህንድ መገናኛ ብዙሃን ታይቷል ።

ኢስላማባድ በሽብር ፋይናንስ ወንጀል እስር ቤት ውስጥ ነው ከሚለው ይፋዊ አቋም በተቃራኒ ሳኢድ በፓኪስታን ላሆር በሚገኝ ከፍተኛ ህዝብ በሚኖርበት አካባቢ ጥብቅ ጥበቃ እየተደረገለት ይኖራልም ብለዋል።
👍19
በአዲስ አበባ ከተማ የአርሶ አደር ይዞታ ይገባኛል መብት ያቀረቡ ሰባት ሺህ ገደማ አመልካቾች ጥያቄቸው ውድቅ ተደረገ!

በአዲስ አበባ ከተማ በአርሶ አደርነት እና በአርሶ አደር ልጅነት የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ሰርተፍኬት እንዲሰጣቸው ካመለከቱ 27 ሺህ ያህል አመልካቾች ውስጥ፤ 7 ሺህ የሚጠጉት ያቀረቡት ጥያቄ “ውድቅ መደረጉን” የከተማይቱ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ። የይገባኛል መብት ጥያቄዎቹ ውድቅ የተደረጉት፤ የቀረቡት ጥያቄዎች ማጣራት ከተደረገባቸው በኋላ ትክክለኛ እንዳልሆኑ በመረጋገጡ እንደሆነ ከንቲባዋ ገልጸዋል።

ከንቲባዋ ይህንን ያሉት ዛሬ ረቡዕ ሚያዝያ 22 በተካሄደው የአዲስ አበባ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ ነው። ጥያቄውን ያቀረቡት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የምክር ቤት ተመራጭ የሆኑት እሌኒ አየለ፤ ከአርሶ አደሮች የይዞታ መብት ጋር በተያያዘ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አስንተዋል።

“የአገልግሎት ጥራት እና ፍጥነት በተመለከተ አንዳንድ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዳሉ ከአርሶ አደሮች እየተነሳ ነው” ያሉት እሌኒ፤ ለዚህ ችግር መፍትሔ እንደሚበጅለት ጠይቀዋል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፤ ትክክለኛ አርሶ አደሮች የይዞታ መብታቸው እንዳይነፈግ እና ሌሎችም ያለአግባብ እንዳይጠቀሙ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት ከንቲባ አዳነች፤ እርሳቸው የሚመሩት የከተማይቱ አስተዳደር ለጥያቄዎቹ “የተሟላ ምላሽ” አለመስጠቱን አምነዋል። የእዚህ ምክንያቱ በአርሶ አደር ስም “አላግባብ ለመጠቀም” በሚደረጉ ጥረቶች፤ “ብዙ ጫናዎች የመፍጠር ሂደቶች” ስለነበሩ እንደሆነ አብራርተዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
👍315😁5😭3👀3
በ780,000 ቅድመ ክፍያ  በመሀል ካዛንቺስ  የቤት ባለቤት ይሁኑ ‼️


እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ  80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ  95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ  140  ,160 ካ.ሜ

✍️ ቅድመ ክፍያ 15%
📹 (ከ780,000ብር ቅድመ ክፍያ  ጀምሮ)

➡️ እስከ 20%  የዋጋ ቅናሽ  አድርገናል

❇️  በ 18 ወራት የሚረከቡት ቤት💁

       📍በግቢው ውስጥ

    ➾ ት/ቤት እና የጤና ማዕከል
    ➾ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ መጫወቻ
    ➾መዋኛ ገንዳ
    ➾የሳይክል እና የእግር ሽርሽር ስፍራዎች
    ➾ሰፊ የመኪና መቆሚያ ከ24/7 ጥበቃ ጋር
    ➾የመኪና ቻርጀር ስፍራዎች

       📍በግቢው ዙሪያ

   ➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
    ➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
    ➾የእምነት ተቋማ

       📍የቤቶቹ እይታ

    ➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
    ➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
    ➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
    ➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ

👉 ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል

❇️  ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።

ለምዝገባ 📲 0950123353 ወይም
በ whatsapp :-https://wa.me/251950123353
አሁኑ ይደውሉ
👍91👎1
🌏IAT & IAIC INTERNATIONAL STUDENT FAIR🌎

Ready to study abroad and change your life?

🎓This is your chance to meet top university representatives from:

USA 🇺🇸 Canada 🇨🇦 Sweden 🇸🇪
Germany 🇩🇪 France 🇫🇷 Finland 🇫🇮 Denmark 🇩🇰 and more!

📆 May 3 & 4
🕐 3:00 - 10:00 (LT)
📍Ghion Hotel

Don’t forget to bring:
🪪Passport or Birth certificate
📚Transcripts or Student copy

Entrance Fee: FREE!!

💡Opportunities:
- Study loan options
- Learn about the scholarships offered

🏆Don’t miss this golden opportunity to take your future global!

🆓No entrance fee — just register now!

Click the link below to book your spot: 🔗
https://forms.gle/81ZueGK5d9R9Cg9P6
👍3👎1
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።  ⭐️ ⭐️

የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!

📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን

በካሬ 64,200 ብር ብቻ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ

ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን

ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!

ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍4👎1
😭14👍42😁1
ሰኞ እለት በአርሲ ዞን ስሬ ወረዳ ምን ተከሰተ?

ባሳለፍነው ሰኞ፣ በቀን 20/08/2017 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን፣ ስሬ ወረዳ አንድ አስደንጋጭ ድርጊት ተከስቶ ነበር።

ወደ 'ስሬ' ከተማ ሲጓዙ የነበሩ 50 ገደማ የአካባቢው ነዋሪዎች ከአዳማ ከተማ በ40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ልዩ ቦታው 'ቀለጣ ወንዝ' ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በዚህ እለት ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በታጣቂዎች ሀይል በተቀላቀለበት መንገድ ታግተው ተወስደዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግስት ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው) ድርጊቱን እንደፈፀመው ሲናገሩ በመንግስት አካላት እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

ከታገቱት ሰዎች መካከል ዕድሜው 26 ዓመት የሆነው እና የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በመጪው እሁድ ይፈፅም የነበረው ወጣት ዮሃንስ አበራ (ዋኑ) (በምስል የተያያዘው ልጅ) በአሰቃቂ ሁኔታ በአጋቾቹ ተገድሎ አስከሬኑ በአውሬ እንዲበላ መደረጉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።

"የሟች ቁርጥራጭ አካል ተሰብስቦ በዛሬው ዕለት በስሬ ከተማ የቀብር ስነ ስርዓቱ በትልቅ ሃዘንና ዋይታ ተፈፅሟል" ያሉን ነዋሪዎቹ ከታገቱት ሰዎች መካከል ነጋዴዎች፣ አረጋውያን፣ የኃይማኖት አባት፣ ወጣቶች፣ ተማሪዎችና ህፃናት ጭምር እንደሚገኙበት ጠቅሰው እስከ 2 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ እንደተጠየቁ ጠቁመዋል።

በአካባቢው በግብርና የሚተዳደረው የአርሶ አደር ማህበረሰብና የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ተከባብረው የሚኖሩበት ወረዳ ሲሆን ታጣቂዎቹ በተለያየ ጊዜ የአካባቢውን ማህበረሰብ ለማጥቃት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።

"አካባቢው በትልቅ የፀጥታ ስጋት ስር የወደቀ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ በሰላም ወጥቶ መግባት፣ 40 ኪ.ሜ ወደ አዳማ ከተማ በነፃነት ተጉዞ መመለስ እንኳን አልቻለም" ያሉ አንድ ነዋሪ ከዚህ ቀደም እገታ የተፈፀመበት አካባቢ በደህንነት ኃይሎች ቀን ቀን ጥበቃ ይደረግ ነበረ ብለዋል።

"በቅርብ ጊዜ እገታው እስከተፈፀመበት ድረስ ጥበቃ የሚያደርጉት አካላት ቦታውን ለቀው በመውጣታቸው ምክንያት ይህ አደጋ ተከስቷል፡፡ የታገቱ አካላት በአስቸኳይ እንዲለቀቁ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ በግፍ ለተነጠቀው ወንድማችን ፍትህ እንዲሰጠን እንዲሁም በቀጣይ የአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑና መሰል ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት መንግስት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠውና የአካባቢውን ፀጥታ እንዲያረጋግጥልን ለፌደራል መንግስትና ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አድረሱልን" ብለዋል።

በድርጊቱ ዙርያ የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽንን መረጃ ለመጠየቅ ያደረግነው መኩራ አልተሳካም። የመንግስት እና የክልል ሚድያዎች በታጣቂዎች የሚፈፀሙ እገታዎችን እና ግድያዎችን እንዳይዘግቡ መታዘዛቸውን ተያይዞ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።


ምንጭ:- መሠረት ሚዲያ
@Yenetube @Fikerassefa
👍24😭243👀1
ቲክ ቶክ በኢትዮጵያ ሴቶችን ማሸማቀቅን ጨምሮ በርካታ ችግሮችን እያባባሰ ነው፤ጥናት

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በተለይም ቲክ ቶክ የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እያባባሰ መሆኑን በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት አመልክቷል።በቲክ ቶክ በሚደረግ ማሸማቀቅ ሀገር ጥለው የሚሰደዱ ሴቶች መኖራቸውም ተመልክቷል።የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በአገር ውስጥ ቋንቋዎች የጥላቻ ንግግሮችን መቆጣጠር አለመቻላቸው ደግሞ ጉዳቱን የከፋ አድርጎታል ተብሏል።

ተጨማሪ  ለማንበብ የDW ዘገባ

https://p.dw.com/p/4tnEI?maca=amh-RED-Telegram-dwcom👉🏾
👍17😁92👀1
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች በወሲብ ንግድ መሰማራታቸው ተገለጸ።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ ኑሮን ለማሸነፍ ስላላስቻላቸው ማታ ማታ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ መኖራቸውን በጥናት መለየቱን የጨርቃ ጨርቅ ፌዴሬሽን ገልጿል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ ለኑሮ ስለማይበቃቸው ማታ ማታ ከሆቴሎች ትርፍራፊ ምግቦችን ይዘው ወደ ቤታቸው የሚገቡ እንዳሉም ፌደሬሽኑ ጠቁሟል፡፡

አምራች ስራተኛ፣ ምቹ ስራ ለወጣቶች እና ሴቶች በጨርቃ ጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ መፍጠር በሚል ርዕስ የፖሊሲ አቅጣጫ ጠቋሚ ጥናት ለማድረግ የማህበራት ጥናት መድረክ (Forum For Social Studies) በጠራው የሁለተኛ ዙር የባለድርሻ አካላት ወይይት ላይ የተገኙት የጨርቃ ጨርቅ ፌዴሬሽን ተወካይ አቶ ተስፋዬ አብዲሳ ‘’የሚከፈላቸው ደመወዝ ለኑሮ ስለማይበቃቸው ማታ ማታ ከሆቴሎች ተመላሽ ምግቦችን ይዘው የሚገቡ እንዳሉም በጥናት አረጋግጠናል’’ ማለታቸውን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል፡፡

በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ስራተኞች ገቢ እንዲሻሻል ለማድረግ  ዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ማፅደቅ አንዱ መፍትሄ ነው፤ ያሉት ተወካዩ ‘’በተለይ ሴቶች ክፍያው ዝቅተኛ ስለሆነ በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ መኖራቸውን በጥናት አረጋግጠናል’’ ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ ባካሄደው ጥናት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ አሰሪዎች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን ፈቃደኞች እንዲሆኑ አረጋግጧል ተብሏል፡፡

መንግስት ግን በጉዳዩ ዙሪያ እልባት ለመስጠት የሚዘገይበት ምክንያት ግልፅ አይደለም ተብሏል፡፡

ሌላ የውይይት ተሳታፊ በበኩላቸው በኢንዲስትሪ ፓርኮች በጨርቃ ጨርቅ እና ጋርመንት ላይ ተሰማርተው የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ክፍያ ዝቅተኛ በመሆኑ በትዳር ሕይወታቸው ላይ እንኳን የመወሰን መብት እንዳይኖራቸው አድርጓል ብለዋል፡፡

ትዳር የሚመሰርቱት ስለፈለጉ ሳይሆን ወጪ ለመጋራት በሚል እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ስራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አማካሪ አቶ ዘሪሁን ገዛኸኝ በበኩላቸው ኮንፌዴሬሽኑ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን መጠየቅ ከጀመረ በርካታ ዓመታት ሆኖታል እስካሁን ግን መፍትሄ አላገኘም ብለዋል፡፡

አቶ ዘሪሁን የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሰራተኞች ወርሃዊ ክፍያ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲተያይ እጅግ ዝቅተኛ ነው ብለዋል፡፡

የጥናት ቡድኑ አባል የሆኑት ደግነት አበባው (ዶ/ር) በበኩላቸው ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ጉዳይ አስፈላጊነቱ እንዳማያጠራጥር ተናግረው ነገር ግን እንዴት ይወሰን የሚለውን በደንብ ማየት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ነገ ሀሙስ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ136ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሰራተኞች ቀንን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ የዝቀተኛ ደመወዝ ወለል እንዲወስን የጠየቀው ጥያቄ መልስ እንዳላገኘለት ተናግሯል፡፡

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም በጉዳዩ ላይ ተጠይቆ የዝቀተኛ ደመወዝ ወለል ጉዳይ ከሀገሪቱ ዋና ኢኮኖሚ ጋር የሚገናኝ ስለሆነ በጥንቃቄ ነው መታየት ያለበት የሚል ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
😭31👍202
የቡርኪናፋሶን የሽግግር ፕሬዝደንትን ለመደገፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሰልፍ ወጡ

በቡርኪናፋሶ ዋና ከተማ ኡጋዱጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሽግግሩን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬን በመደገፍ ሰልፍ ወጡ።

ሰልፈኞቹ ፊሽካ እየነፉ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጦር መሪ ጄኔራል ሚካኤል ላንግሌይ በሰጡት አስተያየት ላይ ቁጣቸውን ገልጸዋል፡፡

ከአደባባይ ለድጋፍ የወጡት ሰልፈኞች "ቡርኪናፋሶ በማንም ላይ አትደገፍም ነገር ግን ዘረፋን አንታገስም ብለዋል:: ጄኔራሉ(የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ ጦር መሪ ጄኔራል ሚካኤል ላንግሌይ) ውሸታም ነው:: እኛ እራሳችን በራሳችን ሁሉን መወሰን እንችላለን፡፡ ሀብታችንን በፈለግን ጊዜ እንጠቀማለን፤ ለፈለግነው እንሸጣለን" ብለዋል፡፡

ሰልፈኞቹ "ካፒቴን ትራኦሬን ለማጥፋት ከፈለጉ መጀመሪያ ህዝቡን ማጥፋት አለባቸው" ብለዋል።

"በ1987 (ግድያ) ያጋጠመን ነገር አይደገምም። በካፒቴን ሳንካራ ላይ የደረሰው በካፒቴን ትራኦሬ ላይ አይደርስም። ፕሬዝዳንታችንን ለመከላከል እስከመጨረሻው እንሄዳለን።" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ የወታደራዊ ባለስልጣናት መንግስትን ለመገልበጥ "ሴራ" ማግኘታቸውን ከገለጹ ከቀናት በኋላ ነው ሲል አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍623
ልብሶችን ለመግዛት እቀያየር ሲለካ  የነበረ ሰው ከበድ ባለ ቆዳ በሽታ ተያዘ።

ልብሶቹን ከገዛ በኋላ  ሳያጥብ ከለበሳቸው በኋላ ቆዳው  በሽፍታዎች እና በእባጮች ተሸፈነ።

የቆዳ ሐኪሞች ሁሉም ልብሶች ከተገዙ በኋላ መታጠብ እንዳለባቸው ያስጠነቅቃሉ።

በፋብሪካ ውስጥ የሚመረቱ  ጨርቆች የቆዳ መቅላት እና ማሳከክ ሊያስከትሉ በሚችሉ የተለያዩ ቆሻሻን እና ውሃን መከላከያ ኬሚካሎች ይታከማሉ።

እንዲሁም ከእርስዎ በፊት ልብሱን ለመግዛት ለክቶት  የነበረው ሰው ብዙ የቆዳ በሽታዎች ሊኖርበት ይችላል - ለምሳሌ በቀላሉ የቆዳ ፈንገስ ሊይዝዎት ይችላል።

Via:- FidelPost
@Yenetube @Fikerassefa
😭19👍181👀1
የውጭ ዜጎች የመሬት እና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅድ አዋጅ ለፓርላማ ተመራ!

የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም የመሬት ባለይዞታ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው የአዋጅ ረቂቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ።አዋጁ የተዘጋጀው “የዜጎችን የመሬት ይዞታ የማግኘትና የመጠቀም መብት በማያጣብብ መልኩ” እንደሆነ ተገልጿል።

የውጭ ዜጎች ካፒታላቸውን “በኢትዮጵያ ስራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታታት” የታለመ ነው የተባለለት ይህን የህግ ረቂቅ ለፓርላማ የመራው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው። ምክር ቤቱ ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 23፤ 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፤ የአዋጅ ረቂቁን ጨምሮ በስድስት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ዜጎች የመሬት እና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ህጋዊ አሰራር እንዲዘረጋ ከተደረገባቸው ምክንያቶች አንዱ፤ ለኢትዮጵያውያን “የስራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ ጠቀሜታ” ያለው በመሆኑ እንደሆነ ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። በኢትዮጵያ የሚታየውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እና አቅርቦት “ሚዛን ለማስጠበቅ” አዋጁ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል።

የአዋጅ ረቂቁ የቤት ልማት እና ተደራሽነትን “ይበልጥ ለማነቃቃት” የሚያስችል መሆኑም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መግለጫ ላይ ተጠቅሷል። ይህ የህግ ረቂቅ የተላለፈለት የተወካዮች ምክር ቤት፤ የውጭ ባለሃብቶች በሪል ስቴት ልማት ዘርፍ በስፋት እንዲሰማሩ የሚያስችል ሌላ አዋጅ ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ማጽደቁ አይዘነጋም። 

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
👎57👍14😁74👀3
🚀 ቡስትግራም: ተመልካቾች እና ፎሎወሮች ያግኙ።

📣🔥👀📹👍


📹የቲክቶክ : ቪዲዮዎችዎ ብዙ ቪውስ፣ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ኮመንቶች ያግኙ።

📷የኢንስታግራም: ፎሎወሮች፣ ላይኮች፣ ቪውስ እና ኮመንቶች ያግኙ።

📹የዩቲዩብ: ሰብስክራይበሮች እና ቪዲዮ ቪውስ በፍጥነት ያግኙ።

✈️ቴሌግራም: ቻነል መምበሮች፣ ፖስት ቪውስ፣ ላይኮች እና ሪአክሽኖች ይጨምሩ።

ቡስትግራም - የሶሻል ሚዲያ ገፅታዎን መገንባት አሁን በጣም ቀላል ሆኗል!`

📹 📷 📹 ✈️

LINK - 🔗 👉 https://tttttt.me/boostgramPromoBot/boostgram 🕯📈
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5
አስተማሪዋ ተይዛለች

በአዲስ አበባ በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሰላም በር ትምህርት ቤት የ2ኛ ክፍል ተማሪዋን ለምን የቤት ስራ አልሰራሽም ብላ፣ልጅቷን በተማሪዎች እጇን አስይዛ ሽንቷ እስኪያመልጣት ድረስ ከፍተኛ ድብደባ የፈፀመችባት መምህር በቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን ከትምህርት ቤት ትባረራለች ተብሏል።

Via:- አዩዘሀበሻ
@Yenetube @Fikerassefa
😭61👍3532😁3
ከዛሬ ሚያዝያ 23 ቀን አንስቶ ብሄራዊ ባንክ የኤክስፖርት ቡና ፈቃድ መስጠት አቆመ።

አዲስ በሚተገረው አሰራር ባንኮች እና ቡና እና ሻይ ሃላፊነቱን ተረክበዋል።ከ27 አመታት በፊት ስራ ላይ ውሎ በነበረው የብሄራዊ ባንክ መመሪያ ኮንትራት ምዝገባ እና የጭነት ፍቃድ የሚሰጠው ማእከላዊ ባንኩ ብቻ እንደነበር ይታወሳል።

ሆኖም የኢኮኖሚ መከፈቱን ተከትሎ እየተተገበሩ ባሉ ለውጦች መሰረት የቡና ኮንትራት ምዝገባ ወደ ኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስስልጣን ተደርጓል።በተመሳሳይ ከዛሬ ጀምሮ የቡና ጭነት ፈቃድ በንግድ ባንኮች የሚሰራ ይሆናል።

በ1990 ዓም የወጣው የብሄራዊ ባንክ መመሪያ የንግድ ባንኮች እንደ ብሄራዊ ባንክ በመሆን ከቡና በስተቀር ለሁሉም ገቢ/ወጪ ምርቶች ፈቃድ እንዲሰጡ የሚፈቅድ ነው።

[ቅዳሜገበያ]
@YeneTube @FikerAssefa
👍395😁2
በ780,000 ቅድመ ክፍያ  በመሀል ካዛንቺስ  የቤት ባለቤት ይሁኑ ‼️


እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ  80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ  95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ  140  ,160 ካ.ሜ

✍️ ቅድመ ክፍያ 15%
📹 (ከ780,000ብር ቅድመ ክፍያ  ጀምሮ)

➡️ እስከ 20%  የዋጋ ቅናሽ  አድርገናል

❇️  በ 18 ወራት የሚረከቡት ቤት💁

       📍በግቢው ውስጥ

    ➾ ት/ቤት እና የጤና ማዕከል
    ➾ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ መጫወቻ
    ➾መዋኛ ገንዳ
    ➾የሳይክል እና የእግር ሽርሽር ስፍራዎች
    ➾ሰፊ የመኪና መቆሚያ ከ24/7 ጥበቃ ጋር
    ➾የመኪና ቻርጀር ስፍራዎች

       📍በግቢው ዙሪያ

   ➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
    ➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
    ➾የእምነት ተቋማ

       📍የቤቶቹ እይታ

    ➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
    ➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
    ➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
    ➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ

👉 ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል

❇️  ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።

ለምዝገባ 📲 0950123353 ወይም
በ whatsapp :-https://wa.me/251950123353
አሁኑ ይደውሉ
👍82
Forwarded from In Africa Together
🌏IAT & IAIC INTERNATIONAL STUDENT FAIR🌎

Ready to study abroad and change your life?

🎓This is your chance to meet top university representatives from:

USA 🇺🇸 Canada 🇨🇦 Sweden 🇸🇪
Germany 🇩🇪 France 🇫🇷 Finland 🇫🇮 Denmark 🇩🇰 and more!

📆 May 3 & 4
🕐 3:00 - 10:00 (LT)
📍Ghion Hotel

Don’t forget to bring:
🪪Passport or Birth certificate
📚Transcripts or Student copy

Entrance Fee: FREE!!

💡Opportunities:
- Study loan options
- Learn about the scholarships offered

🏆Don’t miss this golden opportunity to take your future global!

🆓No entrance fee — just register now!

Click the link below to book your spot: 🔗
https://forms.gle/81ZueGK5d9R9Cg9P6
👍101
Forwarded from YeneTube
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።  ⭐️ ⭐️

የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!

📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን

በካሬ 64,200 ብር ብቻ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ

ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን

ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!

ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍2