YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።  ⭐️ ⭐️

የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!

📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን

በካሬ 64,200 ብር ብቻ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ

ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን

ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!

ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍5
በኢትዮጵያ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት 71 በመቶ ደርሷል ሲል የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ገለፀ።

የተቀረው ህዝብ ንፅህናው ያልተጠበቀ ውሃ እንደሚጠቀምና ሃገሪቱ ንፅህናው የተጠበቀ ውሃን ለዜጎቿ ለማዳረስ በምታደርገው ጥረት፣ በተለይም በገጠራማው ክፍል መሰናክሎች እንዳሉ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ይህ የተገለፀው አክሽን ፎር ዘ ኒዲ የተሰኘው ሃገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት ጄኔቫ ከሚገኘዉ አለም አቀፍ የውሃ፣ አካባቢ እና ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በውሃና በአካባቢ አያያዝ በጋራ ለመስራት ሚያዝያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል በተስማሙበት መድረክ ነው::

በመድረኩ በህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ፤ ተያያዥ ሰብአዊ እና የልማት ድጋፎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነትም ተፈርሟል።

የመግባቢያ ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማዳረስ በምታደርገው ጥረት መሰናክሎች እንዳሉ ገልፀው፣ በተለይም በገጠራማው አካባቢ ችግሩ እንደሚሰፋ ጠቅሰዋል።

መሰረታዊ የንፅህና አጠባበቅን በተመለከተም ከ10 በመቶ በታች ለሆነው የህብረተሰብ ክፍል ብቻ ተደራሽ እንደሚሆን በፈረንጆቹ 2020 የተደረገ ጥናት እንደሚያመላክት የተናገሩት ሚኒስቴር ዴኤታው፣ እንደዚህ ዓይነት ችግሮችን በማቃልለ ረገድ አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ግንባር ቀደም ሚና የሚጫወት ግብረ ሰናይ ድርጅት መሆኑን ገልፀዋል።የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳሊሁ ሱልጣን ሂዉማን ብሪጅ ከአሁን ቀደም ለነጌሌ ሆስፒልና ለገጠራማ አካባቢዎች በ40 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለነጌሌ ሆስፒልና ለገጠራማ አካባቢዎች 80 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ተጨማሪ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱን ተናግረዋል፡፡ በስምምነቱ መሰረት ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመርዳት በታማኝነትና በቁርጠኝነት መስራት ይጠይቃል ተብሏል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
😁62👍9👎2👀1
ለአማራ ክልል ዳኞች የተወሰነው የደመወዝ ጭማሪ በመዘግየቱ “ከፍተኛ ቅሬታ” ማስነሳቱ ተገለጸ

የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር በክልሉ ለሚገኙ ዳኞች እና የጉባኤ ተሿሚዎች የደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ጭማሪ ተፈጻሚ ሳይሆን በመዘግየቱ  “ከፍተኛ ቅሬታ” ማስነሳቱን ገለጸ። ለደመወዝ ጭማሪው የሚያስፈልገውን በጀት የአማራ ክልል መንግስት እንዲመድብ ለማድረግ፤ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት “የቅርብ ክትትል እና ጥረት” እያደረገ መሆኑን ማህበሩ አስታውቋል። 

የዳኞች ማህበሩ ይህን ያስታወቀው ትላንት እሁድ ሚያዝያ 19፤ 2017 ለአባላቱ ባስተላለፈው መልዕክት ነው። ማህበሩ በዚሁ መልዕክቱ፤ ፍርድ ቤቶችን ከማጠናከር እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጀመረውን የለውጥ ስራ የተሟላ ከማድረግ አኳያ የዳኞችን እና የጉባኤ ተሿሚዎችን ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም ማሻሻሉ “የማይተካ ሚና ያለው” “መሰረታዊ ነጥብ” እንደሆነ አስገንዝቧል።

የዳኞች ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄን ለመመለስ፤ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሚቴ አዋቅሮ ጥናት ካደረገ በኋላ በክልሉ ዳኞች አስተዳደር ዐብይ ጉባኤ አማካኝነት ዝርዝር መመሪያ ማጽደቁን ማህበሩ አስታውሷል።

ዐብይ ጉባኤው ካጸደቀው የደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም በተጨማሪ ሀገር አቀፍ የኑሮ ውድነት ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ለሁሉም ሰራተኛ የተደረገ መሆኑን በትላንቱ መልዕክቱ የጠቀሰው ማህበሩ፤ ሁለቱም “እስካሁን ተፈጻሚ ባለመሆናቸው” በዳኞች ዘንድ “ከፍተኛ ቅሬታ” እያስነሳ መሆኑን ገልጿል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
👍131👀1
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዓለም ባንክ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ሊቀበል ነው!

መንግስታዊዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአለም ባንክ ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ ድጋፍ በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ለመቀበል በዝግጅት መሆኑ ተጠቆመ።

ከ650 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከተመደበው ገንዘብ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በዚህ የመጀመሪያ ዙር ዝውውር እንደሚካተት ይጠበቃል።

ይህ በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ የገንዘብ ድጋፍ የአለም ባንክ የፋይናንስ ሴክተርን የማጠናከር ፕሮጀክት አካል ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፋይናንስ አቅሙን እንዲያሳድግና የኢትዮጵያን ሰፋ ያሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን እንዲደግፍ ያለመ ነው።

ባንኩ ይህንን ድጋፍ ለማግኘት መንግስት ቦንድ ማውጣትንና የቦርድ ስብጥርን ማስተካከልን ጨምሮ የተወሰኑ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቷል።

ይህን ተከትሎ በሚቀጥለው ሳምንት ቢያንስ 350 ሚሊዮን ዶላር መቀበል እንደሚችል ይጠበቃል። ይህ የገንዘብ ድጋፍ በተለይም ባንኩ ቀደም ሲል ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በሰጠው ያልተመለሰ ብድር ምክንያት ያጋጠሙትን የፋይናንስ ተግዳሮቶች ለማቃለል ትልቅ እገዛ ያደርጋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት የንግድ ባንኩን ካፒታል ለማጠናከር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተገልጿል። ባለሙያዎች ይህ የዓለም ባንክ ድጋፍ የሀገሪቱን የፋይናንስ ሴክተር ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ይስማማሉ።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍27👎85😭1
ኮሚሽኑ በመጀመሪያ ዙር 75 ሺ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ወደ ህብረተሰቡ ለመመለስ ቢያቅድም እስከ አሁን የተመለሱት 17 ሺህ ብቻ ናቸው ተባለ!

በአማራ ክልል ከ3ሺህ በላይ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ማሕበረሰቡ ተቀላቅለዋል ተብሏል

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን በትግራይ ክልል እስከ ሰኔ ወር ድረስ እንደሚጠናቀቅ በተገለጸው በመጀመሪያ ዙር ለ75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ ቢያቅድም እስከ አሁን የተመለሱት 17 ሺህ ብቻ መሆናቸውን አስታወቀ።

ባለፈው ኅዳር ወር አጋማሽ 2017 ዓ.ም በብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን ተጀምሮ የነበረው እንስቅስቃሴ ብዙ ሳይዘልቅ ለወራት ተቋርጦ መቆየቱን የብሔራዊ ተሃድሶ ኮምሽን ኮምሽነር ተመስገን ጥላሁን ተናግረዋል።

"በትግራይ ክልል በወቅቱ የነበረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ለሥራችን ትልቅ እንቅፋት ሆኖ ነበረ" ያሉት ኮምሽነሩ አክለውም "የቀድሞ ተዋጊዎችን መረጃ ማጥራት፣ ከትጥቅ ርክክብ እና የትጥቅ ሁኔታ ማደራጀት ጋር ተያይዞ ማጥራት ያለብን ጉዳዮች ስለነበሩ በዚሁ ምክንያት ልናቋርጥ ተገደን ነበረ" ብለዋል።

Via AS
@YeneTube @Fikerassefa
👍234😁4
የቀድሞ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳደሪ የአሁኑ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አሊ ከድር ዛሬ በሞጆ የፍጥነት መንገድ ላይ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭34👍10
አዲሱ የጌታቸው ረዳ ፓርቲ ስሙ ታወቀ


በጌታቸው ረዳ ካሕሳይ የሚመራው አዲሱ ፓርቲ የትግራይ ሊበራል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እንደሚባል ተሰምቷል።

ግንቦት አምስት ቀን 2017 ዓ.ም የፓርቲው ምሥረታ ይፋ ይሆናል ያሉት ምንጮች ምርጫ ቦርድ ህወሃት ከፓርቲነት ለመሰረዝ እስከ ግንቦት አምስት ቀነ ገደብ መስጠቱ ይታወሳል።

"የእነ ጌታቸው" የሚባለው ሕወሓት ትናንት ባወጣው መግለጫ አዲስ ፓርቲ ሊያቋቁም እንደሚችል ፍንጭ መስጠቱ ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍33😁62
የሰላም ሚኒስትር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ “ከ18 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማወያየት ችያለሁ” ሲል ገለጸ

የሰላም ሚኒስትር በበጀት አመቱ “25 ሚሊዮን የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማወያየት አቅዶ ከ18 ሚሊዮን የሚልቁትን ማወያየት ችሏል” ሲሉ ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ ኢድሪስ መናገራቸው ተገለጸ።

ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት የተቋማቸውን የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት መሆኑን ከህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሚኒስትሩ “18 ሚሊየን የማህበረሰብ ክፍል” በምን፣ እንዴት እና የት እንዳወያዩ በሪፖርታቸው ስለማካተታቸውም ይሁን አለማካተታቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያለው ነገር የለም።

ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ “የፌዴራልና የክልል መንግስታትን እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር በርካታ ስራዎች ሰርቷል” በሚል ከቋሚ ኮሚቴው አድናቆት ተችሮታል ሲል ምክር ቤቱ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ፌስቡክ ገጹ ባገራው መረጃ አስታውቋል።

መረጃው በተጨማሪም ቋሚ ኮሚቴው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ “ለግጭት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን አስቀድሞ በመለየት የግጭት ምንጮችን ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በትብብር የማጋለጥ ስራዎች ላይ ትኩረት እንዲደረግ አቅጣጫ እንደተቀመጠለት አመላክቷል።

አቶ መሐመድ፣ “በየአካባቢው የሚከሰቱ ጥቃቅን ግጭቶችን ላይ ላዩን የብሄርና የሃይማኖት መልክ ያለው በማስመሰል በተዛባ ግንዛቤ ግጭቱን ከማስፋፋት ይልቅ፣ የግጭቱን እውነተኛ መንስኤ መፈለግና መፍትሄ መስጠት የተሻለ” ነው ሲሉ ጠቁመዋል ብሏል። ሚኒስቴru ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት “ከሃይማኖት ተቋማትና ከሌሎች ተቋማት እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል” ሲሉ አቶ መሐመድ አስረድተዋል ብሏል።

@Yenetube
😁48👍20👎32🔥1
Forwarded from HuluPay Community
በTelegram ላይ የተረጋገጠ ምልክት (Verified Checkmark) ለማግኘት የእርስዎን አካውንት አሁን Premium ያድርጉት
- 4GB እስከሆኑ ፋይሎችን ይጫኑ
- በፍጥነት ያውርዱ
- የእርስዎን online status ከሌሎች ይደብቁ
- እስከ 4 accounts ድረስ ይጠቀሙ
- ልዩ ስቲከሮች እና ኢሞጂዎች
🎭
- የድምፅ መልእክቶችን ጽሁፍ ያድርጉ
- ልዩ badges ያግኙ

- ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ


አሁኑኑ ይቀላቀሉ እና የእርስዎን Telegram ተሞክሮ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግሩ! 🚀

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍7
"የትምህርት ስረአታችን ከቀኝ-ግዛት ተፅእኖ ነፃ ማውጣት አለብን" ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ኮራ ጡሽኔ ተናገሩ

ሚኒስትር ዲኤታው እንደገለፁት አብዛኛው የአፍሪካ የትምህርት ሥርዓት ሙሉ በሙሉ የተወሰደው ከምዕራባውያን ሀገሮች እና ከባህላቸው ነው ፤ በዚህም ምክንያት በተለያየ መንገድ የቅኝ ግዛት ተፅእኖው አሁንም አለ።

ከቀኝ ግዛት ነፃ መውጣት ማለት... ባህላዊ እሴቶቻችንን በትምህርት ስረአታችን ውስጥ በማካተት ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን መፈለግ ነው" በማለት አመለካከታችንም ጭምር ነፃ መውጣት እንዳለበት  ከኢኖቬሽን 2025 የሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።


@Yenetube @Fikerassefa
👍44😁168👎3👀3
Instagram የራሱን የቪድዮ ኢዲት ማድረጊያ መተግበሪያ አስተዋወቀ።

Instagram "Edits" ሲል የሰየመውን የediting መተግበሪያ ከቀናት በፊት አስተዋውቋል። ይህም ከቲክቶኩ የኢዲቲንግ መተግበሪያ Capcut ጋር በርካታ ተመሳሳይ features አሉት።

ይህ መተግበሪያ በAI የተደገፉ tools ስላሉት ለcontent creators ስራ አቅላይ ነውም ተብሏል።

አሁን ላይ ያን ያህል ከሌሎች የኢዲቲንግ መተግበሪያዎች ጋር መፎካከር የሚያስችለው features ባይኖሩትም ወደፊት ጥሩ features/አገልግሎቶች እንደሚያካትትም ተገልጿል።

መተግበሪያውን ከplay store ለማውረድ edits

Via:- Big habesha
@Yenetube @Fikerassefa
👍456😁1
🔒 በHulugram ውስጥ የግል ውይይቶችን እንዴት መደበቅ ይችላሉ? 🔒

📱 ውይይቶችዎን በሚስጥር መጠበቅ ይፈልጋሉ? Hulugram ቀላል ያደርገዋል! 💯

ማንኛውንም ውይይት በጥቂት ቀላል ደረጃዎች እንዴት መደበቅ እንደሚችሉ እነሆ:

1️⃣ የሚፈልጉትን ውይይት ላይ ረጅም ጊዜ ተጭነው ይያዙ 👆

2️⃣ በሚታየው menu ውስጥ "More options" ላይ ይንኩ ⋮ 👉📋

3️⃣ ከአማራጮቹ ውስጥ "Hide" ን ይምረጡ 🙈


🔐 የመጀመሪያ ጊዜ ወይይቶን እየደበቁ ነው? 🔐

ለጥበቃ የይለፍ ቁጥር እንዲያዘጋጁ ይጠየቃሉ! 🔑🛡️

የይለፍ ቁጥርዎን ካዘጋጁ በኋላ:
ግላዊ እንዲሆኑ የሚፈልጓቸውን ማንኛውንም ውይይቶች መደበቅ ይችላሉ! 🤫👀

Download Here 👉 https://play.google.com/store/apps/details?id=plus.ride.huluchat 🔄📥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍91
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵዊያን ሰራተኞች የኑሮ ሁኔታ፤ አሁንም አሳሳቢነቱ ቀጥሏል ሲል የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ተናገረ፡፡

ኮንፌዴሬሽኑ በመጪው ሀሙስ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ136ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሰራተኞች ቀንን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ኢሰማኮ በመግለጫውም የዋጋ ግሽበት የደመወዝ ተከፋዩን የመግዛት አቅም በእጅጉ እንዳዳከመው ነውም ብሏል፡፡

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እስካሁን አለመወሰኑን ያስታወሰው ኮንፌዴሬሽኑ ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ አነስተኛ ሆኖ እያለ ከፍተኛ የገቢ ግብር ስለሚቆረጥባቸው መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እንዳያሟሉ አድርጓቸዋል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ አንዳንድ አሰሪዎች፣ የማህበር መሪዎች ለአባሎቻቸው ስለቆሙ ወይም ለአባሎቻቸው መብት ስለተከራከሩ ብቻ ከስራ ይባረራሉ፣ ይዋከባሉ ወይም ራቅ ወዳለ ቦታ እንዲዘዋወሩ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡

አቶ ካሳሁን ኑሮ የከበዳቸውን ተቀጣሪ ሰራተኞችን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተላኩ ጥያቄዎችን በተመለከተ በተደረገው ውይይት ጥያቄያችን ተቀባይነት አግኝቶ ለሚመለከታቸው ሚኒስትሮች ተላልፎ ተሰጥቷቸዋል፤ ሆኖም የተወሰኑ ጥያቄዎች ምላሽ ያገኙ ቢሆንም መሰረታዊና ቁልፍ የሆኑ የሰራተኛ ጥያቄዎች አልተመለሱም ብለዋል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
👍51😭133
#ትሊዴፓ

" ከብልጽግና ጋር ልክ እንደሌሎቹ በአገር ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ተባብሮ ለመሥራት ይችላል እንጂ የሚያገናኘው ነገር የለም፤ ገለልተኛ እና ነጻ ፓርቲ ነው " - የቀድሞ የህወሓት አመራር


በጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ከህወሓት የተከፈለው ቡድን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም በሂደት ላይ መሆኑን ከአመራሮቹ መካከል አንዱ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ገልጸዋል።

የፖለቲካ ፓርቲው በሊብራል ዴሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብ የሚመራ ሲሆን " ትግራይ ሊብራል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ " በማለት ለመጠራት ውስኗል።

" ስሜ አይጠቀስ " ያሉ አንድ የቀድሞ የህወሓት አመራር ስለ ፓርቲው ምስረታ ምን አሉ ?

- " የፓርቲው ስያሜ የፖለቲካ ፓርቲውን ለመመሥረት በእንቅስቃሴ ላይ ባሉ ሰዎች የተመረጠ እንጂ ከምርጫ ቦርድ እውቅና ስላላገኘ ጉባዔ ሲካሄድ ሊቀየር ወይንም ሊሻሻል ይችላል። "

- " የህወሓት ሕጋዊነት ስለሚያበቃ የህወሓት የፖለቲካ ዓላማዎችን ለማሳካት የሚያስችለን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመሥረት ተገድደናል። "

-  " የፓርቲው ሕገ ደንብ እና ፕሮግራሞቻችን አርቅቀን ጨርሰናል። "

- " አሁን ላይ የደጋፊዎችን ፊርማ በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን። "

- " የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች ገና ስላልተሟሉ እስካሁን ድረስ ለቦርዱ በይፋ የቀረበ ጥያቄ የለም። "

- " የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ቡድኑ ለምዝገባ እየሄደበት ያለውን ሂደት ያውቃል። "

- " ፓርቲው ክልላዊ ፓርቲ ነው። ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በግንቦት የመጀመሪያ ወር ላይ ቅድመ እውቅና እናገኛለን ብለን እንጠብቃለን። "

- " የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአንድ ዓመት ጊዜ ካበቃ በኋላ ክልላዊ መንግሥትን ለመመሥረት በሚደረገው ምርጫ እንሳተፋለን። "

- " ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እውቅና ካገኘን በኋላ ከባለሀብቶች እስከ የቀን ሠራተኞች ድረስ በአባልነት እና በአመራርነት ተቀላቅለው ሊሳተፉበት ይችላሉ። "

- " ትግራይ ሊብራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ከብልጽግና ጋር ልክ እንደሌሎቹ በአገር ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ተባብሮ ለመሥራት ይችላል እንጂ የሚያገናኘው ነገር የለም፤ ገለልተኛ እና ነጻ ፓርቲ ነው።
"

የትግራይ ሊብራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ እየመሠረቱ ካሉተ አንጋፋ ሰዎች መካከል ፦
• የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣
• የህወሓት ፖሊት ቢሮ አባል የነበሩት እና የትዕምት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በየነ መክሩ
• ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት እንደሚገኙበት ታውቋል። (ፕሮፌሰር ክንደያ በቅርቡ በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል)

በሁለት ተከፍሎ እርስ በእርሱ ሲካሰስ የቆየው ህወሓት የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው ቀነ ገደብ ጉባዔ ማካሄድ ባለመቻሉ ከፓርቲነት ሊሰረዝ እንደሚችል ቦርዱ ማስታወቁ ይታወሳል።

የመሰረዝ አደጋ የገጠመው በደብረፂዮን (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተደራድሮ የፕሪቶሪያ ስምምነትን እንደፈረመ ድርጅት እንደ አዲስ በቦርዱ መመዝገቡ ተገቢ አለመሆኑን ሲገልጽ ቆይቷል።

የህወሓት መሰረዝ ስጋት የፈጠረባቸው በአቶ ጌታቸው የሚመራው የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከሳምንታት በፊት ባወጡት መግለጫ በደብረፂዮን (ዶ/ር) ለሚመራው ቡድን በጋራ ጉባዔ ለማካሄድ ጥሪ አቅርበው የነበረ ቢሆንም በጎ ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል።

በመሆኑም " የህወሓት ሕጋዊነት ስለሚያበቃ የህወሓት የፖለቲካ ዓላማዎችን ለማሳካት የሚያስችለን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመሥረት ተገድደናል " ብለዋል።

የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ዜና
👍25😁321👎1
"ስዩም ተሾመ የተባለውን ግለሰብ የፌደራል ፖሊስ ማቅረብ ካልቻለ እና ስማችንን ማጉደፍ የሚቀጥል ከሆነ ስራችንን ልናቆም እንገደዳለን"- የከፍተኛ የፍርድ ቤት ዳኞች

- ፌደራል ፖሊስ ለሶስተኛ ግዜ አክቲቪስቱን ማግኘት አልቻልኩም ብሏል፣ ዳኞች በበከላቸው ለፍትህ ስርዐቱ ያለውን ንቀት ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል

(መሠረት ሚድያ)- ስዩም ተሾመ የተባለው አክቲቪስት የአቶ ዮሐንስ ቧያሌው እና የአቶ ክርስቲያን ታደለን የክስ ሂደት አስመልክቶ በችሎቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረ ነው በሚል ፍርድ ቤቱ ግለሰቡን ሥነ-ሥርዓት እንዲያሲዘው መጠየቃቸውን አስመልክቶ በቅርቡ መዘገባችን ይታወሳል።

ጉዳዩን እየተመለከተው የሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሽብር ወንጀል ችሎት አክቲቪስቱ ቀርቦ መልስ እንዲሰጥ ለፌደራል ፖሊስ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።

ይሁን እንጂ ስዩም ተሾመ የተባለውን ግለሰብ በዛሬው እለትም ለሦስተኛ ጊዜ የፌደራል ፖሊስ ግለሰቡን አላገኘሁትም በሚል ምላሽ ሰጥቷል።

የችሎቱ ዳኞች በበኩላቸው "የፌደራል ፖሊስ ግለሰቡን ለደህንነቱ ሲባል እጀባ እያደረገለት እንደሆነ ይታወቃል።ነገር ግን ፍርድ ቤቱ እንዲያቀርበው ትዕዛዝ ሲደርሰው አላገኘሁትም የሚል ምላሽ መስጠቱ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ያለውን ንቀት የሚያሳይ ነው" ብለዋል።

አክለውም "ግለሰቡ መሀል አዲስ አበባ ተቀምጦ የፍርድ ቤቶችን ዳኞች ስም ሲያጎድፍ እየዋለ ነው። ከችሎቱ አቅም በላይ ሆኗል። ስለዚህ የፍርድ ቤቱ የበላይ አመራሮች ጉዳዩን ለማስቆም አለመሞከራቸው ያሳዝናል" ብለው በዛሬው ችሎት ላይ እንደተናገሩ የመሠረት ሚድያ ምንጮች ጠቁመዋል።

"አሁንም ግለሰቡ በፖሊስ ተይዞ ካልቀረበ እና የዳኞችን ስም የሚያጎድፍ ከሆነ ስራችንን ለማቆም እንገደዳለን" ሲሉ ተናግረዋል።

አቤቱታውን ያቀረቡት አቶ ዮሐንስ ቧያሌው በበኩላቸው "የዓቃቢ ሕግ ምስክሮች ለደኅንነታቸው ሲባል የስም ዝርዝራቸው እንዳይደርሰን ተከልክለን እያለ በዓቃቢ ሕግ አቶ ኢዮሲያድ አበጀ በኩል ለአቶ ስዩም ተሾመ ተሰጥቶት በማሕበራዊ ሚዲያ ማን እንደ ሚመሰክርብን ነግሮናል። ፍርድ ቤቱ የሚቀጣንንም ቅጣት ከወዲሁ ግለሰቡ እየነገረን ነው። እኛ በሕግ ቁጥጥር ስር እያለን ይሄ ሁሉ ዘመቻ ሲፈፀምብን ፍርድ ቤቱ ለምን ማስቆም አልቻለም?" ሲሉ አቤት ብለዋል።

ችሎቱ በበኩሉ "አሁን ጉዳዩ ከእናንተ ወጥቶ የፍርድ ቤቱ ጉዳይ ሆኗል። ከዚህ ችሎትም አልፎ አጠቃላይ የፍትሕ ሥርዓቱን የሚመለከት እየሆነ ነው። ለፌደራል ፖሊስ ደጋግመን መፃፋችንን ታውቃላችሁ። ማቅረብ የሚችለው ፖሊስ ነው። ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ካልፈፀመ የፍትሕ ሥርዓቱ ጥያቄ ውስጥ እንዳለ ይጠቁማል። ለጊዜው ይሄ ችሎት ማለት የሚችለው ይህንን ብቻ ነው" ሲሉ ዳኞች በምሬት ተናግረዋል።

የፌደራል ፖሊስ ለአራተኛ ጊዜ ስዩም ተሾመን አስገድዶ ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ ችሎቱ ለሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍66😁25😭96
Forwarded from YeneTube
🌏IAT & IAIC INTERNATIONAL STUDENT FAIR🌎

Ready to study abroad and change your life?

🎓This is your chance to meet top university representatives from:

USA 🇺🇸 Canada 🇨🇦 Sweden 🇸🇪
Germany 🇩🇪 France 🇫🇷 Finland 🇫🇮 Denmark 🇩🇰 and more!

📆 May 3 & 4
🕐 3:00 - 10:00 (LT)
📍Ghion Hotel

Don’t forget to bring:
🪪Passport or Birth certificate
📚Transcripts or Student copy

Entrance Fee: FREE!!

💡Opportunities:
- Study loan options
- Learn about the scholarships offered

🏆Don’t miss this golden opportunity to take your future global!

🆓No entrance fee — just register now!

Click the link below to book your spot: 🔗
https://forms.gle/81ZueGK5d9R9Cg9P6
👍5
Forwarded from YeneTube
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።  ⭐️ ⭐️

የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!

📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን

በካሬ 64,200 ብር ብቻ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ

ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን

ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!

ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍53
🇪🇹በአምናው በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የደረሰው መኪና አደጋ በቁጥር ሲገለፅ;

👉3,111 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አልፏል;

👉በቀን በአማካኝ 9 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል;

👉67, 633 ተሽከርካሪዎች ወደ ሃገር የገቡ ሲሆን 46, 571 ተሽከርካሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል;

👉ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል;

👉68 በመቶ የተከሰቱት አደጋዎች በአሽከርካሪዎች ጥፋት ነው።
😭18👍91👎1
የተባበሩት_አረብ_ኤምሬትስ #ቢትኮይን ኩባንያ በ #ኢትዮጵያ የማይኒንግ አቅሙን በ52 ሜጋ ዋት ኣሳደገ

የተባበሩተ አረብ ኤምሬትስ የቢትኮይን ማይኒንግ ኩባንያ የሆነው ፎኒክስ ግሩፕ፤ በኢትዮጵያ ባለው የማይኒንግ አቅም ላይ 52 ሜጋ ዋት ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።

ኩባንያው ትናንት ሚያዚያ 21 ቀን 2017 እንዳስታወቀው፤ አዲስ ተግባራዊ ካደረገው ጭማሪ ጋር በኢትዮጵያ የፎኒክስ የቢትኮይን ማይኒንግ አቅም 132 ሜጋ ዋት ደርሷል። የኩባንያው አጠቃላይ አቅም አሁን ከ500 ሜጋ ዋት በላይ መሻገሩ ተገልጿል።

የፎኒክስ ተባባሪ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙናፍ አሊ፤ የኩባንያው ስትራቴጂ "የተትረፈረፈ እና ዝቅተኛ ኃይል ወጭ ያላቸውን ዋና ዋና አካባቢዎች ማገኘት ላይ የተመሠረተ ነው" ብለዋል።

"በኢትዮጵያ ያደረግነውን የቅርብ ጊዜ መስፋፋታችን የመሳሰሉ ተነሳሽነቶች ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው፣ ዛሬ ከፍተኛ ዋጋ በመፍጠር ብቻ ሳይሆን አቋማችንን በማጠናከር ላይም ይገኛሉ" ሲሉም መናገራቸውን ኮይንቴሌግራፍ ዘግቧል።

ይህ ማስፋፊያ ዜና የተሰማው የ #አቡ_ዳቢው ክሪፕቶማይኒንግ ኩባንያ ፎኒክስ ግሩፕ የ80 ሜጋ ዋት ኃይል ግዥ ስምምነት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር መፈራረሙን ተከትሎ ነው። በወቅቱ ኩባንያው በ2025 ሁለተኛው ሩብ አመት ስራ እንደሚጀምር ገልጿል።

ፎኒክስ ኩባንያ በአቡዳቢ ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ ኩባንያ (IHC) የሚደገፍ ሲሆን፣ በመላው #ኤምሬትስ#አሜሪካ እና #ካናዳ ውስጥ የክሪፕቶ ማይኒንግ ስራዎችን ያከናውናል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍373👎2😁1