YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለሳምንታት ከሚዲያ የጠፉት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ብቅ ብለዋል። ይህንን በሶሻል ሚዲያቸው አጋርተዋል።

"ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር ቤንጃሚን ቦል ሜል ከወንድሜ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ይዘውት የመጡትን መልእክት ተቀብያለሁ።

ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል። በደቡብ ሱዳን ወቅታዊውን የጸጥታና የፖለቲካ ችግሮች ለመፍታት፣ ሁሉን አቀፍ ቀጣናዊ አካሄድ እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ሰጥቻለሁ።

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ህዝቦች ያላትን የድጋፍ ቁርጠኝነት አጠናክራ ትቀጥላለች።
"

@Yenetube @Fikerassefa
👍52😁31👎94🔥3😭3
በጋምቤላ ክልል በወባ በሽታ እየተያዙ ያሉ ሰዎች ቁጥር ቀንሷል ቢባልም ባለፈው ሳምንት ብቻ ከ1 ሺህ 7 መቶ በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል

በጋምቤላ ክልል እየተሰሩ ካሉ የመከላከል ስራዎች ባለፈ ያለንበት የበጋ ወቅትን ተከትሎ በወባ በሽታ እየተያዙ ያሉ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።በቢሮዉ የወባ ፕሮግራም ባለሙያ አቶ በርሄ ካልአይ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ባለፉት አራት እና አምስት ዓመታት በክልሉ ወባ በወረርሽኝ ደረጃ ተከስቶ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከጥር ወር ወዲህ ግን በክልሉ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን አቶ በርሄ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።በተለይም ያለንበት የበጋ ወቅት እንደመሆኑ ለወባ ትንኝ መራቢያ አመቺ  አለመሆኑን በማንሳት በዚህም ምክንያት በወባ በሽታ እየተያዙ ያሉ ሰዎች ቁጥር ሊቀንስ ችሏል ብለዋል።ከዚህ ቀደም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው እንደሚያዙ የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ  ግን በበሽታው የሚጠቁ ሰዎችን ቁጥር  በከፍተኛ መጠን መቀነስ  እንደተቻለ ተጠቅሷል።

በክልሉ ምንም እንኳን በበሽታው የሚያዙ ዜጎችን ቁጥር መቀነስ ተችሏል ቢባልም ባለፈው ሳምንት ብቻ 1 ሺህ መቶ 7 መቶ 38   ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው በሪፓርት ተመላክቷል።የክረምት መግቢያና መውጪያ ወቅት ለወባ በሽታ  ስርጭት አመቺ እንደመሆኑ የዜጎችን ጤንነት ሙሉ ለሙሉ ለመጠበቅ በጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች አማካኝነት ለማህበረሰቡ ስለ በሽታው ምንነት  የግንዛቤ  ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍304😭2
ነጋዴዎች እና ሱቅ መክፈት የምትፈልጉ ይሄ መልዕክት እንዳታሳልፉት❗️
ምን እየነገዱ ነውምን ዓይነት ሱቅ መክፈት ይፈልጋሉ

* በከተማው ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ቦታ ከተማው ላይ ሱቅ የፈረሰባቸው ነጋዴዎች የከተሙበት

* 4000 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ እስኬሌተር የሚገጠምለት G+5 የሆነ የገበያ ማዕከል

* በ 1 ዓመት ከ 6 ወር የሚያልቅ ከፍለው እስኪጨርሱ በዶላርም ሆነ በግንባታ እቃዎች ግሽበት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አይደረግም

* ⚠️ ከ 900ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

እንዲሁም የመኖሪያ አፓርትመንቶችን

📍 ሊሴ ገብረማርያም  ት/ቤት ጀርባ
ሙሉ ለሙሉ ለመኖሪያ ብቻ

ባለ 1 መኝታ
ባለ 2 መኝታ
ባለ 3 መኝታ

ከ66ካሬ - 142ካሬ ለመኖር  ለኢንቨስትመንት ምቹ

⚠️ቅድመ ክፍያ ከ693ሺ ብር ጀምሮ


ቴምር ሪልስቴት


ለበለጠ መረጃ
+251 950 05 56 55

TG :  @Davehomes

What’s Up : https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1


#temer #temerproperties #TEMERREALESTATE #realestateagent #realestate #RealEstate #investment #investmentopportunity #InvestmentProperty #investing #apartmentliving #apartment #apartmentforsale #apartments
👍384👀3😁1😭1
ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ስልጣን ተረከቡ።

@Yenetube @Fikerassefa
👍20😁122🔥2
YeneTube
Photo
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጀኔራል ታደሰ ወረደን  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አድርገው ሾመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገጻቸው እንዳሉት የአቶ ጌታቸው የሥልጣን ዘመን በሕጉ መሠረት ሲያበቃ  በይፋና በሰላማዊ መንገድ በአዲስ ባህል የሥልጣን ሽግግሩንቅብብሎሹን ለማካሄድ የተዘጋጀ ፕሮግራም አከናውነናል ብለዋል።

በዚህም በጌታቸው ረዳ የስልጣን ዘመን ምክትል ሆነው ያገለገሉትን ጀኔራል ታደሰ ወረደን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አድርገው መሾማቸውን አስታወቀዋል፡፡

ባለፋት ሁለት ዓመታት የአቶ ጌታቸው ምክትል ሆነው ያገለገሉት ጅኔራል ታደሰ ባለፋት ሁለት ዓመታት የነበሩ ድካሞችን እና ጥንካሬዎችን በግልጽ የሚገነዘቡ ሰው ናቸውም ሲሉ ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ::

አሁን ትግራይ ውስጥ ያለውን ክፍተት ሞልተው ወደ ፊት ሊወስዱ ይችላሉ የሚል እምንት በብዙ አካላት የታመነ ነውም ሲሉ አብራርተዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ የጠማውን ሰላም እና ልማት፣ እንደ ሌሎች ወንድሞቹ ወጥቶ የመግባት መሻት ስናሳካ፣ ለኢትዮጵያም ለአፍሪካም እጅግ ጠቃሚ የሆነ ነገር ሠርቶ ለማለፍ ታሪክ የሰጣቸውን ዕድል እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁም ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍3111😁5🔥1
ቃል የተገቡባቸው ነጥቦች።

ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዚያው አስተዳደር ፕሬዚደንት ሆነው ሲሾሙ በስልጣን ቆይታቸው ከላይ የተያያዙትን ነጥቦች ለማስፈጸም ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና አቶ ጌታቸው ረዳ በተገኙበት በፊርማቸው ቃል ገብተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍21😁73
በትግራይ ከአስገድዶ መድፈር እና ግድያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚያዩ ዳኞች ጫና እየበረታባቸው ነው ተባለ

በትግራይ ክልል ከአስገድዶ መድፈር እና ግድያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚያዩ ዳኞች እየደረሰባቸው ያለው ውስጣዊ እና ውጫዊ ጫናዎች እየተበራከቱ መጥተዋል፣ አሳሳቢ ሁነዋል ሲል የትግራይ የዳኞች ማህበር መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

“በአሁኑ ወቅት በተለይም ደግሞ ባለፉት ሁለት አመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በትግራይ በሴቶች ላይ አስገድዶ መድፈር እና ግድያዎች ተበራክተዋል” ሰል ማህበሩ በመግለጫው ጠቁሟል።

“እነዚህን ወንጀሎች በፈጸሙ ተጠርጣሪዎች እና ከሳሾች ዙሪያ ያሉትን ጉዳዮች የሚሰሙ ዳኞች ከፍርድ ሂደቱ በኋላም ሆነ በፍርድ ሂደቱ ላይ በተለያየ መንገድ ጫና እየደረሰባቸው ይገኛል” ሲል አሳስቧል፤ “ለደህንነታቸው በመስጋት አንሰራም ሊሉ ስለሚችሉ የሚመለከተው አካል ከክልሉ ፍርድ ቤቶች ጋር ልዩ ትኩረት በመስጠት በጋራ እንዲሰራ” ጠይቋል።  

Via አዲስ ስታንዳርድ
@Yenetube @Fikerassefa
👍153😁1
ፌደራል ፖሊስ ስዩም ተሾመን ለማግኘት እንዳልቻለ ለፍርድ ቤት ገለፀ!

አቶ ዮሃንስ ቧያሌው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተከሰው ጉዳያቸው በመታየት ላይ እያለ ስዩም ተሾመ መጋቢት 11/ 2017 ዓ/ም ባስተላለፈው ፕሮግራሙ ከተከሰሱበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ የአማራን ወጣት አስፈጅተዋል፣ ድሽቃ መሣሪያ መግዣ ጠይቀዋል ወዘተ በሚል በፍትህ ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተፅኖ የሚያሳድር፣ ሕግን የተላለፈ  ፕሮግራም ስላቀረበ፣ የፌደራል ፖሊስ ለዛሬ መጥሪያ አድርሶት ችሎት እንዲያቀርበው ቢታዘዝም፣  የስዩም ተሾመ አድራሻው ስላልተገለፀልኝ ላቀርበው አልቻልኩም ብሎ ምላሽ ሰጥቷል።

በዚህ ላይ አቶ ዮሃንስ ቧያሌው አስተያየት ሲሰጥ፣ ከአሁን ቀደምም በስም ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤት ከስሼው ተቀጥቷል።  ፖሊስ ቋሚ አድራሻ ቢኖረውም በተደጋጋሚ ሄዶ እያየ ሰላምታ እየሰጠው ነው የሚመለሰው። ትምህርት ሳያገኝ በመቅረቱ ነው አሁንም ተመሳሳይ ድርጊት የፈፀመው። መንግስት ቤት የሰጣቸው፣ ደሞዝ የሚከፍላቸው እና መኪና የተሰጣቸው የመንግስት አክቲቪስት ናቸው። አማራ ሲሆን የትም ይገኛል። ደብል ስታንዳርድ ነው። የፌደራል ፖሊስ የሰጠው መልስ ለእኛ አሳማኝ አይደለም ብለዋል።

አቶ ክርስቲያን ታደለ በበኩሉ ደግሞ ይሄ "ወስፌ ሲለግም ቂቤ አይወጋም" የሚለው አባባል እውነት መሆኑን ያሳየ ነው። ስዩም ማለት የኢትዮጵያ መንግስት ጠባቂ ፖሊስ የመደበለት የመንግስት ተከፋይ ሃሜተኛ ነው። እኔን አጅባችሁ ውሰዱኝና ቤቱን ላሳያችሁ። የመንግስት ሹመኛን የሚጠብቀው የፌደራል ፖሊስ አካል ነው። እኛን የህዝብ እንደራሴዎችን ከቤተሰባችን ፊት ደብድቦና አዋርዶ ለማምጣት ያልተቸገረው ፌዴራል ፖሊስ፣ ላገኛቸው አልቻልኩም ማለቱ ስላቅ ነው። እውነቱን ንገረኝ ካላችሁኝ ስዩም ያልታሰረው አማራ ነኝ ስላላለ ነው ብሎ ለፍርድ ቤቱ ሃሳቡን ገልጿል።

በስተመጨረሻም የተከሳሾች ጠበቆች በደንበኞቻቸው ላይ የተላለፈው ፕሮግራም ሕግን የተላለፈ በመሆኑ ፖሊስ ያለምንም ምክንያት ስዩምን እንዲያቀርብ ይደረግልን ብለዋል። ፍርድ ቤቱም በድጋሚ የፌደራል ፖሊስ ስዩም ተሾመን እንዲያቀርባቸው ለሚያዝያ  7/ 2017 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍45😁245
ለጦርነት ዝግጁ ነን
"ለጦርነቱ በሙሉ ተዘጋጅተናል አሜሪካና አጋሮቿን ለመፋለም በጭራሽ አንፈራም እነርሱን ከመፋለምም አንድት ስንዝር አናፈገፍግም " ይህ የኢራን ኢስላማዊው ዘብ ጦር IRGC ዋና አዛዥ የዛሬ መግለጫ ነው።


በአሜሪካና ኢራን መካከል ያለው የጦርነት ጉሰማ ተካርሮ ሲቀጥል አሜሪካ የቦንብ ጣይ አይሮፕላኖቿን ከኢራን 3.600 ኪሎሜትር በሚርቀው ዲያጎ ጋርሺያ የጦር ሰፈሯ እያጓጓዘች ትገኛለች። በተጨማሪም የጦር ጄት ተሸካሚ መርከቦቿም ወደ ህንድ ውቅያኖስ እና ቀይ ባህር መጓጓዛቸውን ቀጥለዋል።

ኢራን በበኩሏ የጦር ሀይሏ በተጠንቀቅ እንዲቆም አዛለች። ሚሳኤሎቿም ተሰድረው የጠላት አቅጣጫን እንዲያልሙ ተዘጋጅተዋል።በዛሬው እለት የኢራን ኢስላማዊ ዘብ ሰራዊት IRGC አየር ሀይል ለነትኛውም ማጥቃትና መከላከል በተጠንቀቅ እንዲቆም ታዟል።

የ IRGC ዋና አዛዥ በኢድ እለት ባስተላለፈው መልእክት አሜሪካ ማለት መስታወት ላይ ቆሞ ድንጋይ እንደሚወራወር ሰው ነች አሜሪካ ወደኛ ስትወረውር የቆመችበትን መስታወት እንሰባብረዋለን ማለቱ ይታወሳል።
ትራምፕም ዝቷል ኢራንም ዝታለች። ኔታኒያሁ በጉዳዩ ለመምከር ከቀናት በፊት አሜሪካ ገብቷል።።

ኢራን አፀፋዊ ምላሿ አሜሪካና እስራኤልን ብቻ ሳይሆን እንግሊዝንም የሚያካትት መሆኑን ገልፃለች። "በእኛ አይን እንግሊዝ ከአሜሪካ ተነጥላ የምትታይ አይደለችም" ብላለች።

ነውጠኛው ትራምፕ ከሁለተኛው የአለም ጦርነቱን በሖላ ግዙፉን ጦርነት ለመክፈት የቦንብ ምላጩን ስቦ ይገኛል። የጦርነት ነጋሪቱም በሁለቱም በኩል እተደለቀ ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
👍69😁338🔥1
በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት "በኢትዮጵያ መልቀቂያ የብሔራዊ ፈተና ውጤት የቅርብ ጊዜ ተለዋዋጭነት ግምገማ" በሚል ርዕስ ለአንድ ዓመት የቆየ ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል።

ኢንስቲትዩቱ ካቀረባቸው የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦች መካከል፣ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይሰጥ የሚለው ይገኝበታል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የማኅበራዊ ልማትና አካታችነት ማዕከል ኃላፊና ከፍተኛ ተመራማሪ ደሳለኝ አንጭሶ (ዶ/ር)፥ የተማሪዎች ውጤት እንዲቀንስ ካደረጉ ቁልፍ ምክንያቶች መካከል የፈተና አሰጣጥ ስርዓቱ መቀየር በተለይ ከከተሞች ራቅ ካሉ አካባቢዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚመጡ ተማሪዎች ላይ የፈጠረው የስነ-ልቦና ችግር ተጠቃሽ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተፈጠረው የስነ-ልቦና ችግር ምክንያት ጥሩ ውጤት ማምጣት የነበረባቸው ተማሪዎች ውጤት ሳያመጡ መቅረታቸው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

"ተማሪዎች የባዮሜትሪክ መረጃዎች እንዲሞሉ በማድረግ እንዲሁም በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የደኅንነት ካሜራዎችን በመግጠም የቁጥጥር ስራ በመስራት፣ ተማሪዎች ከሚኖሩበት አካባቢ ሳይርቁ ፈተናውን እንዲፈተኑ ትምህርት ሚኒስቴር የረዥም ጊዜ ዕቅድ ይዞ እንዲሠራ" ምክረ ሐሳብ መቅረቡን ገልፀዋል።

የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ማሻሻል እና ከታች ጀምሮ ጥራት ላይ ሊሰራ እንደሚገባ የገለፁት ኃላፊው፤ የትምህርት ቤት አመራሮች ዕውቀትን መሠረት ባደረገ ሁኔታ ሊመደቡ እንደሚገባም ምክረ ሐሳብ መቅረቡን ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍51👎10😁64🔥1
#AddisAbaba

" ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር ለማድረግ የቀረበው ጥናት ፀድቋል " - የአዲስ አበባ ካቢኔ

በዛሬዉ እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ከነዚህም አንዱ  ፥ በፕላንና ልማት ቢሮ እና በት/ት ሚኒስቴር በጋራ ተጠንቶ የቀረበውን ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር የማድረግ ነው።

ካቢኔው " በአካባቢው ያሉትን አገልግሎቶች አካቶ የትምህርት ፣ የምርምር ፣ የእውቀት እና የባህል ልህቀትን በከተማዋ ለማሳደግ በሚያስችል አግባብ የቀረበ በመሆኑ የመንደር ምስረታውን ዉሳኔ ፀድቋል " ሲል አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ ካቢኔው ፦

- የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤትና ፤የአደጋ ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፏል።

- በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቀረበዉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶች፤ የመሬት ምደባ ጥያቄዎች አስመልክቶም ዉሳኔ አስተላልፏል።

- የምግብ ስርዓትና ኒዉትሪሽን ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይም ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል።
👍39😁87😭2
ማይክሮሶፍት የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) ለእስራኤል ጦር ሃይል እንዲቀርብ የተቃወሙ መሐንዲሶችን ከስራ አባረረ

የዩናይትድ ስቴትስ ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት ኩባንያ ለእስራኤል ጦር ሃይል የሚያቀርበውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የተቃወሙትን ሁለት የሶፍትዌር መሃንዲሶችን ከስራ አሰናብቷል። በማይክሮሶፍት የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ክፍል የሶፍትዌር መሐንዲስ ኢብቲሃል አቡሳድ “ሆን ብሎ አልታዘዝም በማለት ወይም ግዴታን በመዘንጋት” ከስራ ተባሯል። ሌላዋ መሐንዲስ ቫኒያ አግራዋል ኤፕሪል 11 ለመልቀቅ አቅዶ የነበረ ቢሆንም ኩባንያው የስራ መልቀቂያዋን አስቀድሞ ተግባራዊ አድርጓል ሲል CNBC ዘግቧል.

የተቃውሞ እንቅስቃሴ አርብ እለት የጀመሩት አቡሳድ የኩባንያው 50ኛ አመት የምስረታ በዓል ሲከበር የ ሰው ሰራሽ አስተውሎት AI ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙስጠፋ ሱለይማን ንግግር በማቋረጥ "የንፁሃን ደም በእጁ ላይ ነው" በማለት ጩኸት አሰምቷል። ማይክሮሶፍት የእስራኤል ወታደራዊ ሃይል የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሳሪያ እንዲጠቀም አድርጓል ሲል በመክሰስ "50,000 ሰዎች ሞተዋል እናም ማይክሮሶፍት ይህንን የዘር ማጥፋት ወንጀል በክልላችን እንዲፈፀም አድርጓል" ሲል ክስ ሰንዝሯል።በኋላ፣ አግራዋል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳቲያ ናዴላ፣ የቀድሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስቲቭ ቦልመር እና መስራቹ ቢል ጌትስ ያሉበትን የተለየ የፓኔል ዉይይት በማቋረጠ፣ “ ከእስራኤል ጋር ያለውን ግንኙነት ቁረጥ ሲል ተደምጧል።

ተቃውሞውን ተከትሎ አቡሳድ ለማይክሮሶፍት ሰራተኞች እና የስራ ኃላፊዎችን በኢሜል መልዕክት ልኳል ፣ ኩባንያው በሰራተኞች መካከል ያለውን አለመግባባት አፍኗል ። ከዚህ ቀደም ኩባንያው ከእስራኤል ጋር ያለውን ግንኙነት የተቃወሙ የማይክሮሶፍት ሰራተኞች ቡድን አቤቱታ ልኳል። ማይክሮሶፍት ለአቡሳድ ኢሜል ምላሽ መስጠቱን “ስነ ምግባሩን” በመኮነን “በአፋጣኝ ከስራው ማሰናበት ብቸኛው ተገቢ ምላሽ ነው” በማለት ተናግሯል። አግራዋል በተመሳሳይ መልኩ ማይክሮሶፍት በወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ውስጥ ያለውን ተሳትፎ በመተቸት በአፓርታይድ እና የዘር ማጥፋት ዘመቻን በመደገፍ ሲል ተችቷል።

የማይክሮሶፍት ቃል አቀባይ አርብ ዕለት እንዳሉት "ሁሉም ድምጽ እንዲሰማ ብዙ መንገዶችን እናቀርባለን። በአስፈላጊ ሁኔታ ይህ የንግድ ስራ መቋረጥ በማይፈጥር መልኩ እንዲደረግ እንጠይቃለን። ያ ከሆነ ተሳታፊዎች ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ እንጠይቃለን" ብለዋል። የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል አጠራጣሪ ባህሪን ለመለየት እና የጠላትን እንቅስቃሴ ለመከታተል ኢንተለጀንስን ለመተንተን፣ ግንኙነቶችን ለመጥለፍ እና የክትትል መረጃዎችን ለማግኘት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ድጋፍ ማድረጉን ማይክሮሶፍት አምኗል። እ.ኤ.አ ከጥቅምት 2023 ጀምሮ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በፈጸመችው አሰቃቂ ጥቃት ከ50,700 በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል፣ አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ህጻናት ናቸው። እስራኤልም ከቀጠናው ባደረገችው ጦርነት በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ቀርቦባታል።

Via :- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
👍375😁5👎2
ኢትዮጵያ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች ሁሉ በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት በየዓመቱ ከበጀቷ 3 በመቶ ያህል ገንዘብ ለመሰብሰብ እያንዳንዱ ነዋሪ የማዋጣት ግዴታ አለባት ተባለ

በዚህም ኢትዮ ኤይድ በሚል ከራሷ አልፋ ለተቸገሩ ጎረቤቶች እርዳታ ታቀርባለች ተብሏል፡፡

የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ረቂቅ አዋጅ ላይ በፓርላማው ውይይት ሲደረግ ነው ይህ የተባለው፡፡

ለአደጋ ጊዜ ምላሽ ይሰጣል የተባለው እና በአዋጁ መሰረት ለሚቋቋመው ፈንድ በአመት ከኢትዮጵያ በጀት 3 በመቶ የሚሆን ገንዘብ ይሰበስባል የተባለ ሲሆን ይህም በዘንድሮው የአንድ ነጥብ አምስት ትሪሊዮን በጀት ስናሰላው 45 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል እንደማለት ነው፡፡

ለዚህም የመንግስት እና የግል ሰራተኛው እንዲሁም የግልና የመንግስት ተቋማት መንግስታዊ ያልሆኑም ድርጅቶች እንዲያዋጡ በረቂቅ አዋጁ በአስገዳጅነት ተደንግጓል፡፡

ከዛም ባለፈ እያንዳንዱ ግለሰብ እንዳቅሙ ማዋጣት ይጠበቅበታል ተብሏል፡፡

ከተቋማት እና ከኢትዮጵያውያን በተሰበሰበው ገንዘብ ጠንካራ የአደጋ ጊዜ ምላሽ የሚሰጥ ተቋም በመመስረትም ኢትዮ ኤይድ በሚል ለጎረቤት አገራትም እንተርፋለን ብሏል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፡፡

Via:- ሸገር ሬዲዮ
👎121😁34👍323
ነጋዴዎች እና ሱቅ መክፈት የምትፈልጉ ይሄ መልዕክት እንዳታሳልፉት❗️
ምን እየነገዱ ነውምን ዓይነት ሱቅ መክፈት ይፈልጋሉ

* በከተማው ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ቦታ ከተማው ላይ ሱቅ የፈረሰባቸው ነጋዴዎች የከተሙበት

* 4000 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ እስኬሌተር የሚገጠምለት G+5 የሆነ የገበያ ማዕከል

* በ 1 ዓመት ከ 6 ወር የሚያልቅ ከፍለው እስኪጨርሱ በዶላርም ሆነ በግንባታ እቃዎች ግሽበት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አይደረግም

* ⚠️ ከ 900ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

እንዲሁም የመኖሪያ አፓርትመንቶችን

📍 ሊሴ ገብረማርያም  ት/ቤት ጀርባ
ሙሉ ለሙሉ ለመኖሪያ ብቻ

ባለ 1 መኝታ
ባለ 2 መኝታ
ባለ 3 መኝታ

ከ66ካሬ - 142ካሬ ለመኖር  ለኢንቨስትመንት ምቹ

⚠️ቅድመ ክፍያ ከ693ሺ ብር ጀምሮ


ቴምር ሪልስቴት


ለበለጠ መረጃ
+251 950 05 56 55

TG :  @Davehomes

What’s Up : https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1


#temer #temerproperties #TEMERREALESTATE #realestateagent #realestate #RealEstate #investment #investmentopportunity #InvestmentProperty #investing #apartmentliving #apartment #apartmentforsale #apartments
👍206👎3
የኦብነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አብዲከሪም ሼክ ሙሴ (ቀልቢ ደጋህ)ን የግንባሩ ተጠባባቂ ሊቀመንበር አድርጎ ሰየመ።

የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር እያካሄደ በሚገኘው 2ኛ መደበኛ ስብሰባው ከሀላፊነታቸው በተነሱት አብዲራህማን ማሃዲ ምትክ የግንባሩ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር የነበሩትን አብዲከሪም ሼክ ሙሴ የግንባሩ ተጠባባቂ ሊቀመንበር አድርጎ ሰይሟል።

አቶ አብዲከሪም ሼክ ሙሴ ኦብነግ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ በነበረበት ወቅት ለ20 አመታት የኦብነግ ወታደራዊ ክንፍ ከፍተኛ የጦር ኮማንድር ሆነ አገልግለዋል።

ድርጅቱ የግንባሩን ሊቀ መንበር በጠቅላላ ጉባኤ እስኪመረጥ ድረስ አብዲከሪም ሼክ ሙሴ (ቀልቢ ደጋህ) የግንባሩ ተጠባባቂ ሊቀመንበር ሆነው ይቀጥላሉ።

የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ማዕከላዊ ኮሚቴ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ከመጋቢት 30/ 2017 እስከ ሚያዚያ 2/2017 ዓ.ም ድረስ በጅግጅጋ እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍275
ነዳጅ በባቡር
ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ ኢትዮ-ጂቡቲ ምድር ባቡር ነዳጅን ሙሉ በሙሉ ሊያጓጉዝ ነዉ

የኢትዮ ጂቡቲ የምድር ባቡር አክሲዮን ማኅበር በመጪው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ነዳጅን ሙሉ በሙሉ በባቡር ለማጓጓዝ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።

በቀን እስከ አስር ጊዜ በመመላለስ በዓመት 4.2 ሚሊዮን ቶን ነዳጅ ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ እቅድ ተይዟል። ይህ የነዳጅ አቅርቦት ችግርን ከመቅረፉም በላይ የነዳጅ ማጓጓዣ ጊዜን በእጅጉ ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ቀደም ሲል አንድ ቦቴ ነዳጅ ከጂቡቲ ለመምጣት እስከ ስምንት ቀናት ይወስድ የነበረ ሲሆን ይህ አዲሱ ስርዓት የነዳጅ ዋጋን ሊያሳንስ ይችላል ተብሏል። የባቡር መስመሩ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ አገልግሎቱ በስፋት እንደሚጀመር ተገልጿል።

Via:- አዩዘሀበሻ
👍88😁1210