YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም በአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከሆኑት ሴናተር ቴድ ክሩዝ ጋር ተገናኝተው ተነጋገሩ።

አምባሳደሩ ከሴናተሩ ጋር ሲገናኙ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን በዚህ ውይይታቸውም በአፍሪካ ንኡስ ኮሚቴ ሥራ እንዲሁም ንኡስ ኮሚቴው አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ከማሳደግ አንጻር ባለው ሚና ላይ ተወያይተዋል። ሁለቱም ወገኖች በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የበለጠ ተቀራርበው ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ውይይታቸውም በዋና ዋና የጋራ ጉዳዮች እና በተለያዩ ዘርፎች ትብብርን ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነበር።

@YeneTube @Fikerassefa
👍222😁1
ማስታወቂያ

WOMEN'S GIFT PACKAGE
Gift sets

#የእጅ ሰዓት Brand Watch
#ቸኮሌት Chocolates FERRERO
#ፅጌረዳ አበባ Roses
#Teddy bear
# post Card
#perfume
#Neckless

FREE DELIVERY All over Ethiopia

Inbox for price @Fikerassefa
👍4😁1
አኮያ ፕሮፐርቲስ

🔔 ከፒያሳ በቅርብ ርቀት ላይ ሰሜን ማዘገጃ ሳሬም ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ሳይታችን ላይ የኢድ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የሆነ ከ 5%-13% የሚደርስ ቅናሽ ስናደርግ በታላቅ ደስታ ነው ።

🔔 በካሬ 80,000 ብር ሲሸጥ የነበረውን የኢድ በአልን  አስመልክተን ለ 3 ቀን ብቻ በካሬ 76,000 ብር! 10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

🔔 2B+G+18 በሆነው አፓርትመንታች ላይ የእንጦጦ ንፁህ እና ነፋሻማ አየር እየሳቡ የተረጋጋ ህይወት ይኖራሉ!

🔔 ከ ባለ 1 እስከ ባለ 4 መኝት በተለያየ ካሬ አማራጭ

📌 ባለ አንድ መኝታ- 81 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 6,171,390 ብር
       -10% ቅድመ ክፍያ= 617,139 ብር

📌  ባለ ሁለት መኝታ-110 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 8,380,900 ብር
     -10% ቅድመ ክፍያ= 838,090 ብር

📌 ባለ ሶስት መኝታ-130 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 9,904,700 ብር
     -10% ቅድመ ክፍያ= 990,470 ብር

📌 ባለ አራት መኝታ- 211 ካሬ
      -ጠቅላላ ዋጋ=16,076,090 ብር
    -10% ቅድመ ክፍያ=1,607,609 ብር

🔔 በዚህ የመኖሪያ ህንፃ ላይ፡
💥የከርሰ-ምድር ውሀ
💥400 KVA ጄኔሬተር
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥2 ሊፍት
💥በቂ የተሰየመ የመኪና ማቆሚያ
💥መዋኛ ገንዳ
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥 ሬስቶራንት እና ካፌ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ ሰገነት እና ሌሎች መገልገያዎች።

🔔 የመረጡትን ቤት ተመላሽ በሚሆን 200,000 ብር ለ15 ቀን ማስያዝ ይችላሉ።

  ለሳይት ጉብኝት እና ለቢሮ ቀጠሮ፡
  📞 ⁨0923254077⁩  ይደውሉልን!
ቴሌግራም- @E192087
  
       አኮያ ፕሮፐርቲስ
         ከነገ ለተዛመደ!
👍41
የትግራይ ጊዜያዊ ምክር ቤት ልዑክ ከአሜሪካ አምባሳደር አርቪን ማሲንጋ ጋር በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ መምከሩ ተገለጸ!

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት የተመሰረተው የክልሉ ጊዜያዊ ምክር ቤት ልዑክ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ከሆኑት አርቪን ማሲንጋ ጋር መምከራቸው ተገለጸ።

በክልሉ ጊዜያዊ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ሞገስ ታፈረ እና ምክትላቸው ዶ/ር ደጀን መዝገበ የተመራው ልዑኩ ከአምባሳደር ማሲንጋ ጋር በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ቁመና፣ በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም መምከራቸው ተጠቁሟለ።

በተጨማሪም ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው በሚመለሱበት ሁኔታ እና በክልሉ በቀጣይ ምርጫ ማካሄድ ስለሚቻልበት ሁኔታ ልዑኩ ከአምባሳደሩ ጋር መወያየቱንም ከትግራይ ቴሌቪዢን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በተመሳሳይ በአፈጉባኤው የተመራው የክልሉ ጊዜያዊ ምክር ቤት ልዑክ በቀጣይ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከአውሮፓ ሀብረት፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙ የሀገራት ኤምባሲዎች እና አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመገናኘት እንደሚመክር መረጃው አመላክቷል።

በተያዘው አመት 2017 ዓ.ም በትግራይ ወቅታዊ ጉዳይ ለመወያየት የአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ እና የአውሮፓ ህብረት ልዑካን በተደጋጋሚ ወደ መቀለ ማቅናታቸውን የተመለከቱ ዘገባዎች ማቅረባችን ህይታወሳል።

የልዑካን ቡድኑ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አተገባበር፣ በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ እና በክልሉ ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር እንዲሁም ከህወሓቱ ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ጋር መምከራቸውም በዘገባዎቹ ተካተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍15😁42
የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ፍጥነት ከነበረው በመጨመሩ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ!

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የባቡር ፍጥነት በሰዓት ከነበረበት 37 ኪሎ ሜትር ወደ 60 ኪሎ ሜትር ማደጉን አስታውቋል፡፡የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ለፋና ዲጂታል እንደገለጸው÷የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በቅርቡ በቀን የነበረውን የምልልስ መጠን ከሁለት ወደ ስምንት አሳድጓል፡፡፡

የባቡሩ የፍጥነት መጠኑም በፊት ከነበረው በሰዓት 37 ኪሎ ሜትር ወደ በሰዓት 60 ኪሎ ሜትር ማደጉን አመልክቷል፡፡የባቡሩ ፍጥነት መጨመሩን ተከትሎ ሕብረተሰቡ የፍጥነት መሻሻሉን ባለመገንዘብ ለአደጋ እየተጋለጠ መሆኑም ነው የተጠቆመው፡፡

ስለሆነም በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር መስመር አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች የባቡሩ ፍጥነት ከዚህ በፊት ከነበረው መጨመሩን በመገንዝብ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማህበሩ አሳስቧል፡፡የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ከዚህ በፊት ጉዳት ሲደርስ ይሰጥ የነበረውን የካሳ ክፍያ ማቆሙንም አስታውቋል፡፡

Via FBC
@YeneTube @Fikerassefa
👍50😁145🔥2
🚀 ቡስትግራም:ለቲክቶክ 📹 ፣ ኢንስታግራም 📷፣ ፌስቡክ 👍፣ ዩቲዩብ ✈️ እና ቴሌግራም ✈️ በቀላሉ ላይኮች፣ ተመልካቾች እና ፎሎወሮች ያግኙ።


📹 የቲክቶክ እድገት: ቪዲዮዎችዎ ብዙ ቪውስ፣ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ኮመንቶች ያግኙ።

📷 የኢንስታግራም ማሻሻያ: ፎሎወሮች፣ ላይኮች፣ ቪውስ እና ኮመንቶች ያግኙ።

👍 የፌስቡክ አገልግሎት: የፔጅዎ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ፖስቶች ላይ ኢንጌጅመንቶች ይጨምሩ።

📹 የዩቲዩብ አገልግሎት: ሰብስክራይበሮች እና ቪዲዮ ቪውስ በፍጥነት ያግኙ።

✈️ ቴሌግራም: ቻነል መምበሮች፣ ፖስት ቪውስ፣ ላይኮች እና ሪአክሽኖች ይጨምሩ።

ቡስትግራም - የሶሻል ሚዲያ ገፅታዎን መገንባት አሁን በጣም ቀላል ሆኗል!`

OPEN BOOSTGRAM - 🔗 https://tttttt.me/boostgramPromoBot/boostgram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
26🔥14👍9
ቤንያሚን ኔታንያሁ ወደ አሜሪካ ሊጓዙ ነው

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ  በመጪው ሰኞ አሜሪካን እንደሚጎበኙ የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።

የኔታንያሁ ጉብኝት አሜሪካ ከእስራኤል በምታስገባቸው ሸቀጦች ላይ የጫነችውን የ17 በመቶ ቀረጥን በተመለከተ ለመነጋገር ነው ተብሏል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የእስራኤል ባለስልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንዳሉት ኔታንያሁ ከፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የሚያደርጉት ውይይት የተጣለውን ቀረጥ በማስነሳት ላይ ያተኮረ ነው።

ውይይታቸው የኢራን እና የሒዝቦላህ ጉዳይ ያካትት እንደሆን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ማረጋገጫ መስጠት አልቻለም ነው የተባለው።

የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በተለያዩ ሐገራት ላይ እየጣሉት ያለው የገቢ ዕቃዎች ቀረጥ አካል ነው የተባለለት አዲስ የቀረጥ ፖሊሲ መሰረት አሜሪካ ከእስራኤል በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የ17 በመቶ ቀረጥ መጣሏን ታውቋል።

የእስራኤል የፋይናንስ ሚኒስቴር በበኩሉ ይህ አዲስ የተጣለው ቀረጥ እስራኤል ወደ አሜሪካ በምትልካቸው ማሽኖችና የሕክምና መገልገያ ዕቃዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ገልጿል።

እስራኤልና አሜሪካ ከዛሬ 40 ዓመታት በፊት የገቢ ዕቃዎች  ከቀረጽ ነጻ እንዲገቡ መስማማታቸውን ይታወቃል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍25👎75😁1😭1
የተከዜ ዘብ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የተከዜ ዘበ የሆኑ የሰላም አስከባሪ አባላት የምረቃት ስነ ስርዓት ሲከበር ውሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
😁32👍226🔥2👎1
አዋሽ ባንክ ለሌሎች ባንኮች የውጭ ምንዛሪ እገዛ እያደረገ መሆኑን ተናገረ።

በሦስት ወራት ውስጥ ከ498 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለደንበኞቹ ማቅረቡን አስረድቷል።ባንኩ ከ498 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ያቀረበው እ.አ.አ ከ01/01/2025 እስከ 31/03/2025 ባሉ ሦስት ወራት ብቻ መሆኑን አስረድቷል።

ዶላሩ የቀረበውም ከ2,200 በላይ ለሆኑ ደንበኞቹ መሆኑን ጠቅሷል።ለተለያዩ የሀገር ውስጥ ባንኮች ከ100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ እገዛ ማድረጉን ባንኩ ተናግሯል።

አዋሽ ባንክ የደንበኞቹን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማርካት የአቅርቦት ችግር የለብኝም፣ አሁንም በእጄ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ በሰፊው እያቀረብኩ እቀጥላለሁ ሲል ለሸገር በላከው መግለጫ አስረድቷል።

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
👍47😁175👎3👀1
የግድያ ሙከራ በኢብራሂም ትራዎሬ

#አፍሪካ ጀግና መሪ ቢፈጠርም መስዕዋት ሁኖ ለማለፍ እንጅ ለመስራት አይታደልም። ትራዎሬ ስልጣን በያዘ ሁለት ዓመት ጊዜ እንኳ ከ 18 በላይ የግ ድያ ሙከራ ተደርጎበታል።

በባለፈው ሀሙስ ማታ ብቻ ትራዎሬ ላይ ግድያ ለመፈጸም ሲዘጋጁ የተገኙ 113 በላይ ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከኋላ ሴራውን ሸራቢዎች ምዕራባውያን ቢሆኑም ድርጊቱን ፈጻሚዎቹ የገዛ ዜጎቹ ናቸው።ፈረንሳይ የመሆን እድሏም ከፍ ያለ ነው።በአንድ ወቅት ትራዎሬ ከፈረንሳዮ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮኒ ጋር ያደረገው ንግግር ኃያላኑን ያስደነገጠ ነበር።ነገሩ እንዲህ ነው

ኢማኑኤል :- "ፕሬዝዳንት ትራዎሬ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ለማጠንከር በሀገርህ ወታደር የማሰፍርበት ቦታ ስጠኝ" በማለት ይጠይቀዋል።

የትራዎሬ ምላሽ :- "አሜሪካ ፣ ብሪታኒያ ፣ ብራዚል ወዳጆችህ ናቸው።ታዲያ ለምን ወዳጅነትህን ለማጠንከር በነዚህ ሀገሮች ላይ የጦር ሰፈር አልኖረህም?" የሚል ነበር።

Via አዩዘሀበሻ
@Yenetube @Fikerassefa
👍322😁2717😭9🔥3
👍 ተከታዮችን በፍጥነት ማግኘት ይፈልጋሉ?

Boostgram Promo ይጠቀሙ - ተከታዮችዎን በአጭር ጊዜ ይጨምሩ!

ጀማሪ ኢንፍሉዌንሰር ከሆኑ
ተከታዮችን በፍጥነት ማሳደግ ከፈለጉ
ተጽዕኖዎን ለማሳደግ ከፈለጉ


Boostgram Promo መፍትሄው ነው!

👉 ዛሬውኑ ይሞክሩት: https://tttttt.me/boostgramPromoBot/boostgram
ከሌሎች ጀማሪዎች ልዩ ይሁኑ - የማህበራዊ ሚዲያ ተከታታዮችዎን በቀላሉ ያሳድጉ!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍202
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አቶ  በለጠ ሞላን የፓርቲው ሊቀመንበር፣ አቶ መልካሙ ጸጋዬን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ ሰይሟል።


ከሰዓት በአዲስ የተመረጠው ምክር ቤት በበኩሉ አቶ  በለጠ ሞላን ሊቀመንበር፣ አቶ መልካሙ ፀጋዬን ምክትል አድርጎ የሰየመ ሲሆን፤ አጠቃላይ ዘጠኝ አባላት ያሉት የአስፈጻሚ ኮሚቴን አጽድቋል። በዚሁ መሠረት:-
1. አቶ በለጠ ሞላ ጌታሁንን ሊቀመንበር
2. አቶ መልካሙ ፀጋዬን ምክትል ሊቀመንበር
3. አቶ  ዳምጠው ተሰማን የፖለቲካ ጉዳይ
4. አቶ የሱፍ ኢብራሂምን የሕግ ጉዳዮች
5. አቶ ጋሻው መርሻን የህዝብ ግንኙነት
6. አቶ ሀሳቡ ተስፋይን አደረጃጀት
7. አቶ ጥበበ ሰይፈን ጽ/ቤት
8. አቶ ማሩ ጃኔን ስትራቴጂና ስልጠና
9. አቶ አንዷለም አላምረውን የውጭ ግንኙነት አድርጎ መሰየሙን  ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
😁87👍29👎94😭4
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ

WOMEN'S GIFT PACKAGE
Gift sets

#የእጅ ሰዓት Brand Watch
#ቸኮሌት Chocolates FERRERO
#ፅጌረዳ አበባ Roses
#Teddy bear
# post Card
#perfume
#Neckless

FREE DELIVERY All over Ethiopia

Inbox for price @Fikerassefa
👍6
ኢራን ከአሜሪካ ጋር የቀጥተኛ ንግግርን  'ትርጉም የለሽ'  ስትል ውድቅ አደረገች።

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አባስ አራግቺ ከአሜሪካ ጋር የኒውክሌር መርሃ ግብር ላይ የሚደረግ ቀጥተኛ ድርድር “ትርጉም የለሽ” ሲሉ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ገልፀውታል።

ትራምፕ ባለፈው ወር ለኢራን መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ በላኩት ደብዳቤ ቴህራን ኒውክሌር መርሃግብሯ ጋር በተገናኘ ድርድር እንድታደርግ አለበለዚያ ግን ከፍተኛ ወታደራዊ እርምጃ ይጠብቃታል ማለታቸው የሚታወስ ነው እንደ አልጀዚራ ዘገባ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው “ድርድር ከፈለግክ ማስፈራራት ፋይዳው ምንድን ነው?” በማለት የዋሽንግተን የድርድር ጥያቄ ቅንነት የሌለው ሲሉ አጣጥለውታል  ።

ቴህራን ከዚህ ቀደም ከዋሽንግተን ጋር ቀጥተኛ ውይይትን ውድቅ አድርጋለች፡፡ ይሆን እንጂ ተዘዋዋሪ ድርድርን ግን ክፍት እንደሆነ ተናግራለች።

@Yenetube @Fikerassefa
👍272😁1😭1
መንግስት ጫና ያደርግብኛል
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በመንግሥት አስፈጻሚዎች  ጫና እንደሚደረግበት በፓርላማ ተነገረ


የመንግሥትን ጉዳይ እንጂ ሕዝብ የሚፈልገውን እየሠራ አይደለም ተብሏል

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ አካላት ጫና ስለሚደረግበት የመንግሥት አካላት የሚፈልጉትን እንጂ፣ ሕዝብ የሚፈልገው ጉዳይ ላይ አይሠራም የሚል የኦዲት ሪፖርት ትችት ቀረበበት፡፡

ትችቱ የቀረበው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዜናና ወቅታዊ ጉዳዮች አገልግሎት አሰጣጥና አፈጻጸም ውጤታማነት በተመለከተ፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር በተቋሙ የ2015/2016 ዓ.ም. አፈጻጸም ላይ ባደረገው የኦዲት ሪፖርት ላይ፣ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ከተቋቋሙ ኃላፊዎችና ከዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ሲደረግ ነው፡፡ 

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹መንግሥት የሚፈልገውን እንጂ ሕዝብ የሚፈልገው ሚዲያ ላይ አይውልም።

Via:- ሪፖርተር
@Yenetube @Fikerassefa
👍67😁292👎1👀1
ትግራይ ክልል

በትግራይ ክልል የሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ማስተናገድ ከሚችሉት በላይ እየተጨናነቁ እንደሚገኙ አለም አቀፉ ተቋም አስታወቀ

በትግራይ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች በተፈናቃዮች ቁጥር መጨናነቃቸውን አለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አይኦኤም ትላንት መጋቢት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፤ መጠለያዎቹ በተፈናቃዮች ከመጨናነቃቸው ባለፈ እየፈረሱ ነው፣ በዚህም ሳቢያ ለአስከፊ ኑሮ እየተዳረጉ ነው ሲል ገልጿል።

“በየግዜው ተጨማሪ አዳዲስ ተፈናቃዮች ወደ መጠለያ ጣቢያዎቹ በመግባታቸው እየፈረሱ ነው” ብሏል።

መጠለያዎች ለመጨናነቃቸው በዋናነት የተጠቀሰው ምክንያት ደግሞ ቤት ተከራይተው በአከባቢዎቹ ከሚገኙ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ተፈናቃዮች የሚከፍሉት በማጣታቸው ወደ መጠለያዎቹ በመግባታቸው መሆኑን ጠቅሷል።

በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደ መጠለያ ጣቢያዎች ለማዛወር ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የጠቆመው ተቋሙ አስካሁን 21 ትምህርት ቤቶች ላይ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮችን ወደ መጠለያ ጣቢያዎች ማዛወር መቻሉን አመላክቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍173
ቦይንግ ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ከደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ጋር በተያያዘ ዛሬ በፍትሐብሔር ፍርድ ቤት ፊት ይቆማል

ከአደጋው ጋር በተገናኛ ለመጀመሪያ ግዜ ለፍትሐብሔር ፍርድ ቤት የሚቀርብ ጉዳይ ይሆናል፡፡

ሁለት ሳምንታት ይፈጃል ተብሎ የሚጠበቀው የቺካጎው ችሎት፤ በዚሁ አደጋ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ያጡ ሁለት ከሳሾችን ያካትታል ተብሎ ነበር።

ነገር ግን ከከሳሾቹ  አንዱ እሁድ ከፍርድ ቤት ውጭ በተደረገ ስምምነት ጉዳያቸው እንደተፈታ አንድ የፍርድ ቤት ምንጭን ጠቅሶ የምእራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

ሌላ የመጨረሻ ደቂቃ ስምምነት ካልተደረሰ በስተቀር፤ ችሎቱ ዛሬ ስምንት ከሕዝብ የተወጣጡ ዳኞችን (ጁሪ) በመምረጥ ይጀምራል ተብሏል።

ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን መጋቢት 1፣ 2011 ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር ቢሾፍቱ አካባቢ መከስከሱ ይታወቃል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍21😭21
“ውጤት አልደረሰልኝም” ፖሊስ

በቀነኒ አዱኛ ሞት ላይ ዛሬ ቀጠሮ የነበረ ሲሆን በአራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ በነበረው ችሎት የፖሊስ የምርመራ ውጤት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ፖሊስ የምርመራ ውጤቶቹ አሁንም አልደረሱኝም በማለት 14 ቀን ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል።

የአንዱዓለም ጠበቃ በበኩሉ የቀነኒ ዲያሪ እሱ ጋር እንዳለ ጠቅሶ ቀነኒ ሯሷን ለማጥፋት በተደጋጋሚ መድኃኒት ወስዳ እንደነበር ተፅፎ አግኝቻለሁ ብሏል።

ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መፈቀድ የለበትም አንዱዓለም የዋስ መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል ብሎ ተከራክሯል። በተጨማሪም ከእስር ወጥቶ የሙዚቃ ስራውን ለፋሲካ ያቅርብ የሚለው የዩቲዩብ ዘገባ የተሳሳተ ነው ሊታረም ይገባል ብሏል።

ፍርድ ቤት የሁለቱን ክርክር ከሰማ በኋላ የክርክሩን ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ማክሰኞ ጠዋት ቀጥሮ ሰጥቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍30👀85
YeneTube
“ውጤት አልደረሰልኝም” ፖሊስ በቀነኒ አዱኛ ሞት ላይ ዛሬ ቀጠሮ የነበረ ሲሆን በአራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ በነበረው ችሎት የፖሊስ የምርመራ ውጤት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ፖሊስ የምርመራ ውጤቶቹ አሁንም አልደረሱኝም በማለት 14 ቀን ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል። የአንዱዓለም ጠበቃ በበኩሉ የቀነኒ ዲያሪ እሱ ጋር እንዳለ ጠቅሶ ቀነኒ ሯሷን ለማጥፋት በተደጋጋሚ መድኃኒት ወስዳ እንደነበር ተፅፎ አግኝቻለሁ ብሏል።…
የድምጻዊ አንዱአለም ጠበቃ “ቀነኒ በርካታ ጊዜ ራሷን ለማጥፋት መሞከሯን ከማስታወሻዋ ላይ ተገንዝቤያለው” ሲል ተከራከረ

የድምጻዊ አንዱአለም ጠበቃ “ቀነኒ በርካታ ጊዜ ራሷን ለማጥፋት መሞከሯን ከማስታወሻዋ ላይ ተገንዝቤያለው” ሲል በችሎቱ ተከራከረ። በፍቅር አጋሩ ግድያ ቀነኒ አዱኛ ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው የአፋን ኦሮሞ ድምጻዊ አንዱአለም ጎሳ ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ/ም ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበ።

ተጠርጣሪው አንዱአለም ጎሳ ዛሬ ጠዋት አራዳ በሚገኘው የፌደራል ፍርድ ቤት ከጠበቃው ጋር በቀረበበት ወቅት ፖሊስ በተሰጠው 12  የምርመራ ቀናት ውስጥ ያሰባሰበውን ማስረጃ ለችሎቱ አቅርቧል።

ዛሬ በዋለው ችሎት ፖሊስ መጋቢት 17  ቀን 2017 ዓ/ም በተሰጠው 12 ተጫማሪ የምርመራ ቀናት ውስጥ በሞዴል ቀነኒ አዱኛ ሞት ላይ 15 ተጨማሪ የሰዎች በአጠቃላይ የ28 ሰዎች ማስረጃዎችን ማሰባሰቡን ገልጿል። 

እንዲሁም በቀነኒ መኖሪያ ቤት ውስጥ በሚገኝ ምንጣፍ ላይ የተደረገው ምርመራን ጨምሮ የተለያዩ ናሙናዎችን በመውሰድ ለፎረንሲክ ምርመራ ለፌዴራል ፖሊስ መላኩን እና የምርመራው ውጤት ግን እስካዛሬ አለመድረሱን ገልጿል። 
በተጨማሪም በሟቿ እና በተጠርጣሪው የእጅ ስልክ ላይ ምርመራ እንዲደረግ ወደ ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ተልኮ የምርመራው ውጤት እየተጠበቀ እንደሚገኝ ለችሎቱ አስረድቷል። 

ሳይበሰበሰቡ የቀሩ ማስረጃዎች ከዚህ ቀደም በነበረው ችሎት ላይ ከቀረቡት የምርመራ ውጤቶች ጋር እንደ ተጨማሪ ግብዓት እንዲካተትለት የጠየቀው ፖሊስ መሰብሰብ ያለባቸውን ተጨማሪ ማስረጃዎች ለማሰባሰብ ተጨማሪ የምርመራ ቀን እንዲሰጠው ጠይቋል። 
መጋቢት 17  ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ፖሊስ በአስክሬን መርመራ ቀነኒ “ከፍ ካለ ቦታ ላይ ወድቃ ህይወቷ ማለፉን” ጠቁሟል።  “ነገር ግን የአስከሬን ምርመራ ውጤትን በተመለከተ ከህክምና ባለሙያዎች ተጨማሪ ማብራሪያ በመጠየቁ ውጤት እስኪደርሰው ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጠው መጠየቁ ይታወሳል።  

ይሁን እንጂ ፖሊስ በዛሬው ችሎት እንደገለጸው ማስረጃውን ከያዙት የህክምና ባለሙያዎች መካከል የተወሰኑት በአገር ውስጥ እንደሌሉና እነሱን ለማግኘት የተለያዩ ዘዴዎችን እየተጠቀመ መሆኑን በመግለጽ ውጤቱን እስኪቀበል 14 ተጨማሪ ምርመራ ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል።
የአንዱአለም ጎሳ ጠበቃ ሊበን አብዲ በበኩሉ፤ ፖሊስ ተመሳሳይ ምክንያት በማናቅረብ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ያቀረበው ጥያቄ “ተቀባይነት የሌለው” በመሆኑ ተጠርጣሪው የዋስትና መብት ሊጠበቅለት ይገባል ሲል ተከራክሯል።
የተጠርጣሪው ጠበቃ የቀነኒ አዱኛ የማስታወሻ ደብተር በእጁ ላይ እንዳለ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል። በማስታወሻ ደብተሩ ላይ  [ቀነኒ] ብዙ ጊዜ እራሱን ለማጥፋት ከመጠን በላይ መድሃኒት መውሰዷን መረዳቱን ለችሎቱ ተናግሯል። 

የመቷ ምክንያትም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው ሲል ተከራክሯል። አክሎም አንዱአለም ጎሳ በቀነኒ ሞት ውስጥ መሳተፉን የሚያረጋግጥ የሰው ማስረጃ እና የምርመራ ሰነድ መረጃ እንደሌለ በመግለጽ፤ ይህም “ንፁህ መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ” ተጠርጣሪው የዋስ መብቱ ተጠርብቆለት ወደ ቤት ሄዶ ፍቅረኛውን ህልፈተ ሃዘነ እንዲያወጣ ጠይቋል።

ከዚህም በተጨማሪ ‘ኢትዮ ፎረም’ የተሰኘ ዩቲዩብ ሚዲያ ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያዎች በባለፈው ችሎት ተጠርጣሪው አንዱአለም ጎሳ ለመጪው የትንሳኤ በዓል ኮንሰርት ስላለው የዋስትና ጥያቄ እንዳቀረበ አድርገው መዘገባቸው ”በቀነኒ ቤተሰብ እና የሚወደው ማሀበረሰበ እንዲጨክንበት ታስቦ የተደረገ የስም የማጥፋት ዘመቻ ነው” ሲል ገልጾ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን እንዲመለከተው ጠይቋል። 
ፍርድ ቤቱ በበኩሉ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር ካዳመጠ በኋላ ፖሊስ ያቀረበውን የምርመራ ውጤት እና በሁለቱም ወገኖች የተነሱትን ጥያቄዎች መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ መጋቢት 30 ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ቀጠሮ ሰጥቷል።
ሞዴል እና የማስታወቂያ ባለሙያ የሆነችው ቀነኒ አዱኛ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ሌሊት 10 ሰዓት አካባቢ ከእጮኛዋ ጋር ከሚኖሩበት ውዳሴ ከተሰኘው ሕንጻ 5ኛ ፎቅ በረንዳ ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በመውደቋ ህይወቷ ማለፉ ይታወቃል።

- Addis Standard
👍57😭154😁3🔥1