YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የግድያ ሙከራ በኢብራሂም ትራዎሬ

#አፍሪካ ጀግና መሪ ቢፈጠርም መስዕዋት ሁኖ ለማለፍ እንጅ ለመስራት አይታደልም። ትራዎሬ ስልጣን በያዘ ሁለት ዓመት ጊዜ እንኳ ከ 18 በላይ የግ ድያ ሙከራ ተደርጎበታል።

በባለፈው ሀሙስ ማታ ብቻ ትራዎሬ ላይ ግድያ ለመፈጸም ሲዘጋጁ የተገኙ 113 በላይ ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከኋላ ሴራውን ሸራቢዎች ምዕራባውያን ቢሆኑም ድርጊቱን ፈጻሚዎቹ የገዛ ዜጎቹ ናቸው።ፈረንሳይ የመሆን እድሏም ከፍ ያለ ነው።በአንድ ወቅት ትራዎሬ ከፈረንሳዮ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮኒ ጋር ያደረገው ንግግር ኃያላኑን ያስደነገጠ ነበር።ነገሩ እንዲህ ነው

ኢማኑኤል :- "ፕሬዝዳንት ትራዎሬ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ለማጠንከር በሀገርህ ወታደር የማሰፍርበት ቦታ ስጠኝ" በማለት ይጠይቀዋል።

የትራዎሬ ምላሽ :- "አሜሪካ ፣ ብሪታኒያ ፣ ብራዚል ወዳጆችህ ናቸው።ታዲያ ለምን ወዳጅነትህን ለማጠንከር በነዚህ ሀገሮች ላይ የጦር ሰፈር አልኖረህም?" የሚል ነበር።

Via አዩዘሀበሻ
@Yenetube @Fikerassefa
👍322😁2717😭9🔥3
👍 ተከታዮችን በፍጥነት ማግኘት ይፈልጋሉ?

Boostgram Promo ይጠቀሙ - ተከታዮችዎን በአጭር ጊዜ ይጨምሩ!

ጀማሪ ኢንፍሉዌንሰር ከሆኑ
ተከታዮችን በፍጥነት ማሳደግ ከፈለጉ
ተጽዕኖዎን ለማሳደግ ከፈለጉ


Boostgram Promo መፍትሄው ነው!

👉 ዛሬውኑ ይሞክሩት: https://tttttt.me/boostgramPromoBot/boostgram
ከሌሎች ጀማሪዎች ልዩ ይሁኑ - የማህበራዊ ሚዲያ ተከታታዮችዎን በቀላሉ ያሳድጉ!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍202
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አቶ  በለጠ ሞላን የፓርቲው ሊቀመንበር፣ አቶ መልካሙ ጸጋዬን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ ሰይሟል።


ከሰዓት በአዲስ የተመረጠው ምክር ቤት በበኩሉ አቶ  በለጠ ሞላን ሊቀመንበር፣ አቶ መልካሙ ፀጋዬን ምክትል አድርጎ የሰየመ ሲሆን፤ አጠቃላይ ዘጠኝ አባላት ያሉት የአስፈጻሚ ኮሚቴን አጽድቋል። በዚሁ መሠረት:-
1. አቶ በለጠ ሞላ ጌታሁንን ሊቀመንበር
2. አቶ መልካሙ ፀጋዬን ምክትል ሊቀመንበር
3. አቶ  ዳምጠው ተሰማን የፖለቲካ ጉዳይ
4. አቶ የሱፍ ኢብራሂምን የሕግ ጉዳዮች
5. አቶ ጋሻው መርሻን የህዝብ ግንኙነት
6. አቶ ሀሳቡ ተስፋይን አደረጃጀት
7. አቶ ጥበበ ሰይፈን ጽ/ቤት
8. አቶ ማሩ ጃኔን ስትራቴጂና ስልጠና
9. አቶ አንዷለም አላምረውን የውጭ ግንኙነት አድርጎ መሰየሙን  ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
😁87👍29👎94😭4
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ

WOMEN'S GIFT PACKAGE
Gift sets

#የእጅ ሰዓት Brand Watch
#ቸኮሌት Chocolates FERRERO
#ፅጌረዳ አበባ Roses
#Teddy bear
# post Card
#perfume
#Neckless

FREE DELIVERY All over Ethiopia

Inbox for price @Fikerassefa
👍6
ኢራን ከአሜሪካ ጋር የቀጥተኛ ንግግርን  'ትርጉም የለሽ'  ስትል ውድቅ አደረገች።

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አባስ አራግቺ ከአሜሪካ ጋር የኒውክሌር መርሃ ግብር ላይ የሚደረግ ቀጥተኛ ድርድር “ትርጉም የለሽ” ሲሉ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ገልፀውታል።

ትራምፕ ባለፈው ወር ለኢራን መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ በላኩት ደብዳቤ ቴህራን ኒውክሌር መርሃግብሯ ጋር በተገናኘ ድርድር እንድታደርግ አለበለዚያ ግን ከፍተኛ ወታደራዊ እርምጃ ይጠብቃታል ማለታቸው የሚታወስ ነው እንደ አልጀዚራ ዘገባ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው “ድርድር ከፈለግክ ማስፈራራት ፋይዳው ምንድን ነው?” በማለት የዋሽንግተን የድርድር ጥያቄ ቅንነት የሌለው ሲሉ አጣጥለውታል  ።

ቴህራን ከዚህ ቀደም ከዋሽንግተን ጋር ቀጥተኛ ውይይትን ውድቅ አድርጋለች፡፡ ይሆን እንጂ ተዘዋዋሪ ድርድርን ግን ክፍት እንደሆነ ተናግራለች።

@Yenetube @Fikerassefa
👍272😁1😭1
መንግስት ጫና ያደርግብኛል
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በመንግሥት አስፈጻሚዎች  ጫና እንደሚደረግበት በፓርላማ ተነገረ


የመንግሥትን ጉዳይ እንጂ ሕዝብ የሚፈልገውን እየሠራ አይደለም ተብሏል

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ አካላት ጫና ስለሚደረግበት የመንግሥት አካላት የሚፈልጉትን እንጂ፣ ሕዝብ የሚፈልገው ጉዳይ ላይ አይሠራም የሚል የኦዲት ሪፖርት ትችት ቀረበበት፡፡

ትችቱ የቀረበው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዜናና ወቅታዊ ጉዳዮች አገልግሎት አሰጣጥና አፈጻጸም ውጤታማነት በተመለከተ፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር በተቋሙ የ2015/2016 ዓ.ም. አፈጻጸም ላይ ባደረገው የኦዲት ሪፖርት ላይ፣ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ከተቋቋሙ ኃላፊዎችና ከዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ሲደረግ ነው፡፡ 

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹መንግሥት የሚፈልገውን እንጂ ሕዝብ የሚፈልገው ሚዲያ ላይ አይውልም።

Via:- ሪፖርተር
@Yenetube @Fikerassefa
👍67😁292👎1👀1
ትግራይ ክልል

በትግራይ ክልል የሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ማስተናገድ ከሚችሉት በላይ እየተጨናነቁ እንደሚገኙ አለም አቀፉ ተቋም አስታወቀ

በትግራይ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች በተፈናቃዮች ቁጥር መጨናነቃቸውን አለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አይኦኤም ትላንት መጋቢት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፤ መጠለያዎቹ በተፈናቃዮች ከመጨናነቃቸው ባለፈ እየፈረሱ ነው፣ በዚህም ሳቢያ ለአስከፊ ኑሮ እየተዳረጉ ነው ሲል ገልጿል።

“በየግዜው ተጨማሪ አዳዲስ ተፈናቃዮች ወደ መጠለያ ጣቢያዎቹ በመግባታቸው እየፈረሱ ነው” ብሏል።

መጠለያዎች ለመጨናነቃቸው በዋናነት የተጠቀሰው ምክንያት ደግሞ ቤት ተከራይተው በአከባቢዎቹ ከሚገኙ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ተፈናቃዮች የሚከፍሉት በማጣታቸው ወደ መጠለያዎቹ በመግባታቸው መሆኑን ጠቅሷል።

በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደ መጠለያ ጣቢያዎች ለማዛወር ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የጠቆመው ተቋሙ አስካሁን 21 ትምህርት ቤቶች ላይ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮችን ወደ መጠለያ ጣቢያዎች ማዛወር መቻሉን አመላክቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍173
ቦይንግ ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ከደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ጋር በተያያዘ ዛሬ በፍትሐብሔር ፍርድ ቤት ፊት ይቆማል

ከአደጋው ጋር በተገናኛ ለመጀመሪያ ግዜ ለፍትሐብሔር ፍርድ ቤት የሚቀርብ ጉዳይ ይሆናል፡፡

ሁለት ሳምንታት ይፈጃል ተብሎ የሚጠበቀው የቺካጎው ችሎት፤ በዚሁ አደጋ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ያጡ ሁለት ከሳሾችን ያካትታል ተብሎ ነበር።

ነገር ግን ከከሳሾቹ  አንዱ እሁድ ከፍርድ ቤት ውጭ በተደረገ ስምምነት ጉዳያቸው እንደተፈታ አንድ የፍርድ ቤት ምንጭን ጠቅሶ የምእራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

ሌላ የመጨረሻ ደቂቃ ስምምነት ካልተደረሰ በስተቀር፤ ችሎቱ ዛሬ ስምንት ከሕዝብ የተወጣጡ ዳኞችን (ጁሪ) በመምረጥ ይጀምራል ተብሏል።

ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን መጋቢት 1፣ 2011 ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር ቢሾፍቱ አካባቢ መከስከሱ ይታወቃል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍21😭21
“ውጤት አልደረሰልኝም” ፖሊስ

በቀነኒ አዱኛ ሞት ላይ ዛሬ ቀጠሮ የነበረ ሲሆን በአራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ በነበረው ችሎት የፖሊስ የምርመራ ውጤት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ፖሊስ የምርመራ ውጤቶቹ አሁንም አልደረሱኝም በማለት 14 ቀን ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል።

የአንዱዓለም ጠበቃ በበኩሉ የቀነኒ ዲያሪ እሱ ጋር እንዳለ ጠቅሶ ቀነኒ ሯሷን ለማጥፋት በተደጋጋሚ መድኃኒት ወስዳ እንደነበር ተፅፎ አግኝቻለሁ ብሏል።

ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መፈቀድ የለበትም አንዱዓለም የዋስ መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል ብሎ ተከራክሯል። በተጨማሪም ከእስር ወጥቶ የሙዚቃ ስራውን ለፋሲካ ያቅርብ የሚለው የዩቲዩብ ዘገባ የተሳሳተ ነው ሊታረም ይገባል ብሏል።

ፍርድ ቤት የሁለቱን ክርክር ከሰማ በኋላ የክርክሩን ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ማክሰኞ ጠዋት ቀጥሮ ሰጥቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍30👀85
YeneTube
“ውጤት አልደረሰልኝም” ፖሊስ በቀነኒ አዱኛ ሞት ላይ ዛሬ ቀጠሮ የነበረ ሲሆን በአራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ በነበረው ችሎት የፖሊስ የምርመራ ውጤት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ፖሊስ የምርመራ ውጤቶቹ አሁንም አልደረሱኝም በማለት 14 ቀን ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል። የአንዱዓለም ጠበቃ በበኩሉ የቀነኒ ዲያሪ እሱ ጋር እንዳለ ጠቅሶ ቀነኒ ሯሷን ለማጥፋት በተደጋጋሚ መድኃኒት ወስዳ እንደነበር ተፅፎ አግኝቻለሁ ብሏል።…
የድምጻዊ አንዱአለም ጠበቃ “ቀነኒ በርካታ ጊዜ ራሷን ለማጥፋት መሞከሯን ከማስታወሻዋ ላይ ተገንዝቤያለው” ሲል ተከራከረ

የድምጻዊ አንዱአለም ጠበቃ “ቀነኒ በርካታ ጊዜ ራሷን ለማጥፋት መሞከሯን ከማስታወሻዋ ላይ ተገንዝቤያለው” ሲል በችሎቱ ተከራከረ። በፍቅር አጋሩ ግድያ ቀነኒ አዱኛ ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው የአፋን ኦሮሞ ድምጻዊ አንዱአለም ጎሳ ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ/ም ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበ።

ተጠርጣሪው አንዱአለም ጎሳ ዛሬ ጠዋት አራዳ በሚገኘው የፌደራል ፍርድ ቤት ከጠበቃው ጋር በቀረበበት ወቅት ፖሊስ በተሰጠው 12  የምርመራ ቀናት ውስጥ ያሰባሰበውን ማስረጃ ለችሎቱ አቅርቧል።

ዛሬ በዋለው ችሎት ፖሊስ መጋቢት 17  ቀን 2017 ዓ/ም በተሰጠው 12 ተጫማሪ የምርመራ ቀናት ውስጥ በሞዴል ቀነኒ አዱኛ ሞት ላይ 15 ተጨማሪ የሰዎች በአጠቃላይ የ28 ሰዎች ማስረጃዎችን ማሰባሰቡን ገልጿል። 

እንዲሁም በቀነኒ መኖሪያ ቤት ውስጥ በሚገኝ ምንጣፍ ላይ የተደረገው ምርመራን ጨምሮ የተለያዩ ናሙናዎችን በመውሰድ ለፎረንሲክ ምርመራ ለፌዴራል ፖሊስ መላኩን እና የምርመራው ውጤት ግን እስካዛሬ አለመድረሱን ገልጿል። 
በተጨማሪም በሟቿ እና በተጠርጣሪው የእጅ ስልክ ላይ ምርመራ እንዲደረግ ወደ ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ተልኮ የምርመራው ውጤት እየተጠበቀ እንደሚገኝ ለችሎቱ አስረድቷል። 

ሳይበሰበሰቡ የቀሩ ማስረጃዎች ከዚህ ቀደም በነበረው ችሎት ላይ ከቀረቡት የምርመራ ውጤቶች ጋር እንደ ተጨማሪ ግብዓት እንዲካተትለት የጠየቀው ፖሊስ መሰብሰብ ያለባቸውን ተጨማሪ ማስረጃዎች ለማሰባሰብ ተጨማሪ የምርመራ ቀን እንዲሰጠው ጠይቋል። 
መጋቢት 17  ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ፖሊስ በአስክሬን መርመራ ቀነኒ “ከፍ ካለ ቦታ ላይ ወድቃ ህይወቷ ማለፉን” ጠቁሟል።  “ነገር ግን የአስከሬን ምርመራ ውጤትን በተመለከተ ከህክምና ባለሙያዎች ተጨማሪ ማብራሪያ በመጠየቁ ውጤት እስኪደርሰው ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጠው መጠየቁ ይታወሳል።  

ይሁን እንጂ ፖሊስ በዛሬው ችሎት እንደገለጸው ማስረጃውን ከያዙት የህክምና ባለሙያዎች መካከል የተወሰኑት በአገር ውስጥ እንደሌሉና እነሱን ለማግኘት የተለያዩ ዘዴዎችን እየተጠቀመ መሆኑን በመግለጽ ውጤቱን እስኪቀበል 14 ተጨማሪ ምርመራ ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል።
የአንዱአለም ጎሳ ጠበቃ ሊበን አብዲ በበኩሉ፤ ፖሊስ ተመሳሳይ ምክንያት በማናቅረብ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ያቀረበው ጥያቄ “ተቀባይነት የሌለው” በመሆኑ ተጠርጣሪው የዋስትና መብት ሊጠበቅለት ይገባል ሲል ተከራክሯል።
የተጠርጣሪው ጠበቃ የቀነኒ አዱኛ የማስታወሻ ደብተር በእጁ ላይ እንዳለ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል። በማስታወሻ ደብተሩ ላይ  [ቀነኒ] ብዙ ጊዜ እራሱን ለማጥፋት ከመጠን በላይ መድሃኒት መውሰዷን መረዳቱን ለችሎቱ ተናግሯል። 

የመቷ ምክንያትም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው ሲል ተከራክሯል። አክሎም አንዱአለም ጎሳ በቀነኒ ሞት ውስጥ መሳተፉን የሚያረጋግጥ የሰው ማስረጃ እና የምርመራ ሰነድ መረጃ እንደሌለ በመግለጽ፤ ይህም “ንፁህ መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ” ተጠርጣሪው የዋስ መብቱ ተጠርብቆለት ወደ ቤት ሄዶ ፍቅረኛውን ህልፈተ ሃዘነ እንዲያወጣ ጠይቋል።

ከዚህም በተጨማሪ ‘ኢትዮ ፎረም’ የተሰኘ ዩቲዩብ ሚዲያ ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያዎች በባለፈው ችሎት ተጠርጣሪው አንዱአለም ጎሳ ለመጪው የትንሳኤ በዓል ኮንሰርት ስላለው የዋስትና ጥያቄ እንዳቀረበ አድርገው መዘገባቸው ”በቀነኒ ቤተሰብ እና የሚወደው ማሀበረሰበ እንዲጨክንበት ታስቦ የተደረገ የስም የማጥፋት ዘመቻ ነው” ሲል ገልጾ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን እንዲመለከተው ጠይቋል። 
ፍርድ ቤቱ በበኩሉ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር ካዳመጠ በኋላ ፖሊስ ያቀረበውን የምርመራ ውጤት እና በሁለቱም ወገኖች የተነሱትን ጥያቄዎች መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ መጋቢት 30 ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ቀጠሮ ሰጥቷል።
ሞዴል እና የማስታወቂያ ባለሙያ የሆነችው ቀነኒ አዱኛ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ሌሊት 10 ሰዓት አካባቢ ከእጮኛዋ ጋር ከሚኖሩበት ውዳሴ ከተሰኘው ሕንጻ 5ኛ ፎቅ በረንዳ ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በመውደቋ ህይወቷ ማለፉ ይታወቃል።

- Addis Standard
👍57😭154😁3🔥1
ለሳምንታት ከሚዲያ የጠፉት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ብቅ ብለዋል። ይህንን በሶሻል ሚዲያቸው አጋርተዋል።

"ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር ቤንጃሚን ቦል ሜል ከወንድሜ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ይዘውት የመጡትን መልእክት ተቀብያለሁ።

ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል። በደቡብ ሱዳን ወቅታዊውን የጸጥታና የፖለቲካ ችግሮች ለመፍታት፣ ሁሉን አቀፍ ቀጣናዊ አካሄድ እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ሰጥቻለሁ።

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ህዝቦች ያላትን የድጋፍ ቁርጠኝነት አጠናክራ ትቀጥላለች።
"

@Yenetube @Fikerassefa
👍52😁31👎94🔥3😭3
በጋምቤላ ክልል በወባ በሽታ እየተያዙ ያሉ ሰዎች ቁጥር ቀንሷል ቢባልም ባለፈው ሳምንት ብቻ ከ1 ሺህ 7 መቶ በላይ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል

በጋምቤላ ክልል እየተሰሩ ካሉ የመከላከል ስራዎች ባለፈ ያለንበት የበጋ ወቅትን ተከትሎ በወባ በሽታ እየተያዙ ያሉ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።በቢሮዉ የወባ ፕሮግራም ባለሙያ አቶ በርሄ ካልአይ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ባለፉት አራት እና አምስት ዓመታት በክልሉ ወባ በወረርሽኝ ደረጃ ተከስቶ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከጥር ወር ወዲህ ግን በክልሉ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን አቶ በርሄ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።በተለይም ያለንበት የበጋ ወቅት እንደመሆኑ ለወባ ትንኝ መራቢያ አመቺ  አለመሆኑን በማንሳት በዚህም ምክንያት በወባ በሽታ እየተያዙ ያሉ ሰዎች ቁጥር ሊቀንስ ችሏል ብለዋል።ከዚህ ቀደም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው እንደሚያዙ የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ  ግን በበሽታው የሚጠቁ ሰዎችን ቁጥር  በከፍተኛ መጠን መቀነስ  እንደተቻለ ተጠቅሷል።

በክልሉ ምንም እንኳን በበሽታው የሚያዙ ዜጎችን ቁጥር መቀነስ ተችሏል ቢባልም ባለፈው ሳምንት ብቻ 1 ሺህ መቶ 7 መቶ 38   ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸው በሪፓርት ተመላክቷል።የክረምት መግቢያና መውጪያ ወቅት ለወባ በሽታ  ስርጭት አመቺ እንደመሆኑ የዜጎችን ጤንነት ሙሉ ለሙሉ ለመጠበቅ በጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች አማካኝነት ለማህበረሰቡ ስለ በሽታው ምንነት  የግንዛቤ  ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍304😭2
ነጋዴዎች እና ሱቅ መክፈት የምትፈልጉ ይሄ መልዕክት እንዳታሳልፉት❗️
ምን እየነገዱ ነውምን ዓይነት ሱቅ መክፈት ይፈልጋሉ

* በከተማው ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ቦታ ከተማው ላይ ሱቅ የፈረሰባቸው ነጋዴዎች የከተሙበት

* 4000 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ እስኬሌተር የሚገጠምለት G+5 የሆነ የገበያ ማዕከል

* በ 1 ዓመት ከ 6 ወር የሚያልቅ ከፍለው እስኪጨርሱ በዶላርም ሆነ በግንባታ እቃዎች ግሽበት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አይደረግም

* ⚠️ ከ 900ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

እንዲሁም የመኖሪያ አፓርትመንቶችን

📍 ሊሴ ገብረማርያም  ት/ቤት ጀርባ
ሙሉ ለሙሉ ለመኖሪያ ብቻ

ባለ 1 መኝታ
ባለ 2 መኝታ
ባለ 3 መኝታ

ከ66ካሬ - 142ካሬ ለመኖር  ለኢንቨስትመንት ምቹ

⚠️ቅድመ ክፍያ ከ693ሺ ብር ጀምሮ


ቴምር ሪልስቴት


ለበለጠ መረጃ
+251 950 05 56 55

TG :  @Davehomes

What’s Up : https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1


#temer #temerproperties #TEMERREALESTATE #realestateagent #realestate #RealEstate #investment #investmentopportunity #InvestmentProperty #investing #apartmentliving #apartment #apartmentforsale #apartments
👍384👀3😁1😭1
ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ስልጣን ተረከቡ።

@Yenetube @Fikerassefa
👍20😁122🔥2
YeneTube
Photo
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጀኔራል ታደሰ ወረደን  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አድርገው ሾመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገጻቸው እንዳሉት የአቶ ጌታቸው የሥልጣን ዘመን በሕጉ መሠረት ሲያበቃ  በይፋና በሰላማዊ መንገድ በአዲስ ባህል የሥልጣን ሽግግሩንቅብብሎሹን ለማካሄድ የተዘጋጀ ፕሮግራም አከናውነናል ብለዋል።

በዚህም በጌታቸው ረዳ የስልጣን ዘመን ምክትል ሆነው ያገለገሉትን ጀኔራል ታደሰ ወረደን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አድርገው መሾማቸውን አስታወቀዋል፡፡

ባለፋት ሁለት ዓመታት የአቶ ጌታቸው ምክትል ሆነው ያገለገሉት ጅኔራል ታደሰ ባለፋት ሁለት ዓመታት የነበሩ ድካሞችን እና ጥንካሬዎችን በግልጽ የሚገነዘቡ ሰው ናቸውም ሲሉ ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ::

አሁን ትግራይ ውስጥ ያለውን ክፍተት ሞልተው ወደ ፊት ሊወስዱ ይችላሉ የሚል እምንት በብዙ አካላት የታመነ ነውም ሲሉ አብራርተዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ የጠማውን ሰላም እና ልማት፣ እንደ ሌሎች ወንድሞቹ ወጥቶ የመግባት መሻት ስናሳካ፣ ለኢትዮጵያም ለአፍሪካም እጅግ ጠቃሚ የሆነ ነገር ሠርቶ ለማለፍ ታሪክ የሰጣቸውን ዕድል እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁም ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍3111😁5🔥1
ቃል የተገቡባቸው ነጥቦች።

ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዚያው አስተዳደር ፕሬዚደንት ሆነው ሲሾሙ በስልጣን ቆይታቸው ከላይ የተያያዙትን ነጥቦች ለማስፈጸም ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና አቶ ጌታቸው ረዳ በተገኙበት በፊርማቸው ቃል ገብተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍21😁73