YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በኢትዮጵያ 43 ጋዜጠኞች ለእገታ እና እስር መዳረጋቸውን ሪፖርት አመለከተ!

የጋዜጠኞች ደህንነት ግምገማ በማካሄድ የሚታወቀው አለም አቀፉ የሚዲያ ድጋፍ ተቋም ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 ብቻ 43 ጋዜጠኞች ለእገታ እና እስር መዳረጋቸውን አስታወቀ። ሪፖርቱ ጋዜጠኞች ከመንግስት እና መንግስትዊ ካልሆኑ አካላት ማስፈራሪያ፣ እስር እና እንግልትን ጨምሮ ለበርካታ ጫናዎች ተጋላጭ መሆናቸውን አመላክቷል።

ከ60 ጋዜጠኞች ጋር በተደረገ ቃለ መጠይቅ እና በሰነድ በተመዘገቡ ጉዳዮች ላይ የተመሠረተው ሪፖርቱ፣ በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች ያሉ ጋዜጠኞች በተለይም በ አማራ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከፍተኛ አደጋ እንደሚገጥሟቸው አረጋግጧል።

በሪፖርቱ መሠረትም “የታጠቁ ቡድኖች ጋዜጠኞችን የቤዛ ክፍያ ለመቀበል ወይም ስለግጭቶች የሚወጡትን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቁሳቁሶቻቸውን ለመወሰድ በማሰብ በዘፈቀደ አስረዋል።በሌላ በኩል የመንግስት ባለሥልጣናት ደግሞ "ብሔራዊ ደህንነት እና ብሔራዊ ጥቅም" በሚል ሰበስ ጋዜጠኞች እንዲታሰሩ ማድረጋቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
👍111
YeneTube
Photo
አዲስ የገቡት የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ከሌሎች አውቶብሶች የዋጋ ልዩነት እንደማይኖራቸው ተገለጸ

የወረቀት ቲኬትን በማስቀረት የክፍያ ስርዓቱን ሙሉ ለሙሉ በቴክኖሎጂ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተብሏል


በተያዘው ሳምንት 100 የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በትናንትናው ዕለት ሥራ መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማስታወቁ ይታወሳል።

ይህም የትራንስፖርት ችግሩን ከመፍታትና ከአየር ብክለት ጋር ተያይዞ ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሄ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

አሐዱም "አሁን ወደ ሥራ የገቡት እነዚህ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ቻርጅ ለማድረግ የሚያችል መሠረተ ልማት እንዲሁም ከክፍያ ጋር ተያይዞ ልዩነት ይኖራቸዋል ወይ?" ሲል ጠይቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አካሉ አሰፋ በሰጡት ምላሽ፤ አውቶብሶቹ በአንድ ጊዜ ቻርጅ ለ3 ቀን መጠቀም እንደሚያስችሉ የተናገሩ ሲሆን፤ ከክፍያ ጋር ተያይዞም ከሌሎች አዉቶብሶች ልዩነት እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

ከመለዋወጫ ጋር ተያይዞም የኤሌትሪክ አውቶብሶች ብዙ የጥገና ሂደት የማያስፈልጋቸው በመሆኑ ከመደበኛ  አውቶብሶች የሚለዩ ናቸው ብለዋል፡፡

"ስለሆነም ከረዥም ዓመት በኋላ ባትሪ ሊጠይቅ ይችላል" ሲሉ ገልፀው፤ የጥገና ሂደቱ አሳሳቢ አለመሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ሌሎች ተሸከርካሪዎችም ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲቀየሩ በእቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የአውቶብስ አገልግሎት ችግር ሆኖበት የቆየውን የፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም ይፈታል ተብሎ እንደታመነበትም ተናግረዋል።

በተያያዘ በከተማዋ የሚገኙ ሁሉንም የአውቶቡስ አገልግሎቶች የክፍያ ስርዓት በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ እየተሰራበት እንደሚገኝ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አካሉ አሰፋ አስታውቀዋል።

የአውቶቡስ አገልግሎቱ የክፍያ ስርዓት የዘመነ ባለመሆኑ ጊዜን ከመጠቀምና ሀብትን በአግባቡ ከመሰብሰብ አኳያ ትልቅ ተፅዕኖ እንደነበረበት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ "አዲስ የገቡትን 100 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ዘመናዊ አውቶቡሶችን ጨምሮ በአጠቃላይ ድርጅቱ የሚጠቀምባቸው የከተማዋ አዉቶብሶች በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓት እንዲያገለግሉ ይደረጋል" ብለዋል።

ወደ ሥራ እንዲሰማሩ የተደረጉት የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ መሆናቸውን የገለጹም ሲሆን፤ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓት እንዲሰሩ ተደርገው የተሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በዚህ ቴክኖሎጂ መሠረትም የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ የሚፈፅም ተሳፋሪ ካርድ መግዛት እንደሚጠበቅበት ጠቁመው፤ "በካርዱ ብቻ ክፍያ የሚፈፅም ይሆናል" ብለዋል።

አክለውም ወደፊት የወረቀት ቲኬቱ እየቀረ እንደሚሄድ የገለጹ ሲሆን፤ ካርዱን መግዛት ለማይችሉ እንዲሁም አሠራሩ በሰዎች ዘንድ በደንብ እስኪለመድ ድረስ ቲኬት በመቁረጥ እንደሚገለገሉ ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍275
በአማራ ክልል ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎች ተናገሩ

በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎችና የህክምና ባለሙያዎች ተናገሩ።

ራስን ለማጥፋት የአዕመሮ ህመምና ቅፅበታዊ አጋጣሚዎች ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጧል። በባሕር ዳር ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ባለፉት ሰባት ወራት ብቻ 156 ከራስ ማጥፋት ጋር በተያያዘ ወደ ህክና የመጡ ሰዎች መኖራቸውን አንድ የህክምና ባለሙያ ለዶይቸቨለ ተናግረዋል።

በፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ጓዴ ተዋበ ከአዲሱ ዓመት መግቢያ ጀምሮ ራስን ከማጥፋት ጋር በተያያዘ ጉዳተኞች ወደ ሆስፒታሉ መምጣታቸውን ገልጸውልናል። ከታካሚዎቹ መካክልም ብዙዎቹ ከተጎዱ በኋላ ወደ ተቋሙ በመድረሳቸው ሕይወታቸው ያለፈ መኖሩን አመልክተዋል።

በወራቤ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአዕምሮ ህክምና ስፔሽያሊስት ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው በበኩላቸው ራስን ለማጥፋት የሚያስችሉ መነሻ ምክንያቶች በርካታ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ዋነኞቹ ድብርትና ቅፅበታዊ ሁኔታዎች የሚፈጥሩት ሁኔታ እንደሆኑ ተናግረዋል።

Via DW Amharic
@Yenetube @Fikerassefa
👍23😭233👎3🔥1
የማዚያ_ወር_2017_ዓ_ም_የሀራጅ_ሽያጭ_ማስታወቂያ_11.PDF
4 MB
የሚያዚያ ወር 2017 የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚሸጡ ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ!

የሀራጅ ሽያጭ የሚከናወንበት ቦታ ልደታ ከተማ የፈዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግቢ ውስት በሚገኘው የፌዴራል ፍርድ

ቤቶች የፍርድ አራግኦም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ
👍13
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የዓለም ዓቀፉን የጦር ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ቸል በማለት ወደ ሃንጋሪ መጓዛቸዉ ተሰምቷል፡፡

እስራኤል በጋዛ እያደረሰች ያለችዉን የጦር ወንጀል ተከትሎ በዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስር ትዕዛዝ የወጣባቸዉ ቤንያሚን ኔታኒያሁ ፤ የአራት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ሃንጋሪ መግባታቸዉ ተሰምቷል፡፡

ሃንጋሪ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት መስራች አባል እንደመሆኗ በፍርድ ቤቱ የእስር ትዕዛዝ የወጣበት ማንኛዉንም ግለሰብ ወደ አገሯ ከገባ አሳልፋ የመስጠት ግዴታ አለባት፡፡

የሃንጋሪዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን በበኩላቸዉ፤ አገራቸዉ ኔታኒያሁን ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን እና የፍርድ ቤት ትዕዛዙንም እንደማታከብር አስታዉቀዋል፡፡

ከኳታር ገንዘብ ተቀብለዋል የተባሉ ረዳቶቻቸዉ መታሰራቸዉን ተከትሎ በአገር ቤት የፖለቲካ አጣብቂኝ ዉስጥ የሚገኙት ኔታኒያሁ፤ ኦርባንን ለማናገር ወደ ሃንጋሪ መግባታቸዉ ተዘግቧል፡፡

ፖሊስ ስማቸውን ይፋ ያላደረጋቸውን ረዳቶቻቸውን እስር "እገታ" ሲሉ የጠሩት ኔታንያሁ፤ አክለውም "ምንም አይነት ኬዝ የለም" ብለዋል።

በሐማስ እና በእስራኤል መካከል በተደረሰው የጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነት ቁልፍ አሸማጋይ የሆነችው ኳታር በበኩሏ በባለስልጣኗ በኩል ጉዳዩን "የስም ማጥፋት ዘመቻ" ስትል አጣጥላዋለች።

@Yenetube @Fikerassefa
👍374👎3😭2😁1👀1
#በምዕራብ_ጎንደር ዞን ቋራ እና #በባሕር _ዳር ዙሪያ ወረዳ በኮሌራ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ኢንስቲትዩቱ አስታወቀ

#አማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ እና በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በኮሌራ ወረርሽኝ በርካታ ሰዎች እየተያዙ መሆኑን የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የበሽታዎች እና የጤና ሁኔታዎች ምላሽ አሰጣጥ ባለሙያ ሲስተር ሰፊ ደርብ እንደገለጹት ወረርሽኙ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ በየቀኑ የሚደርሰው የበሽተኛ ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ በተለይ በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በቀን ውስጥ በርካታ ሰዎች በበሽታው እየተጠቁ ነው ብለዋል።

አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት በማስከተል ለሞት የሚዳርገው በሽታው በክልሉ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ መከሰቱን አስረድተዋል ሲል አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

ሲስተር ሰፊ ደርብ የኮሌራ የተበከለ ውኃ እና ምግብን በመጠቀም የሚከሰት ሲኾን ሰዎች በብዛት በሚሠባሠቡባቸው ቦታዎች በተለይም ንጹህ የመጠጥ ውኃ እና ንጹህ የመጸዳጃ ቦታ በሌለበት አካባቢ በቀላሉ የሚተላለፍ በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል።

በሽታውን ለመከላከል ከበሽተኛ ጋር ንክኪ ከተደረገ በኋላ እጅን በሳሙና መታጠብ፣ ውኃን በኬሚካል አክሞ እና አፍልቶ መጠቀም እንዲሁም የበሽታው ምልክቶች ከታዩ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ያስፈልጋል ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍83😭3😁1
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 7ኛ ዓመት አስመልክቶ የድጋፍ ሰልፍ በሸገር ከተማ ተካሄደ።
😁80👎44👍21😭82
በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ እና በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በኮሌራ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ኢንስቲትዩቱ አስታወቀ!

በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ እና በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በኮሌራ ወረርሽኝ በርካታ ሰዎች እየተያዙ መሆኑን የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የበሽታዎች እና የጤና ሁኔታዎች ምላሽ አሰጣጥ ባለሙያ ሲስተር ሰፊ ደርብ እንደገለጹት ወረርሽኙ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ በየቀኑ የሚደርሰው የበሽተኛ ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ በተለይ በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በቀን ውስጥ በርካታ ሰዎች በበሽታው እየተጠቁ ነው ብለዋል።

አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት በማስከተል ለሞት የሚዳርገው በሽታው በክልሉ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ መከሰቱን አስረድተዋል ሲል አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

ሲስተር ሰፊ ደርብ የኮሌራ የተበከለ ውኃ እና ምግብን በመጠቀም የሚከሰት ሲኾን ሰዎች በብዛት በሚሠባሠቡባቸው ቦታዎች በተለይም ንጹህ የመጠጥ ውኃ እና ንጹህ የመጸዳጃ ቦታ በሌለበት አካባቢ በቀላሉ የሚተላለፍ በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል።

በሽታውን ለመከላከል ከበሽተኛ ጋር ንክኪ ከተደረገ በኋላ እጅን በሳሙና መታጠብ፣ ውኃን በኬሚካል አክሞ እና አፍልቶ መጠቀም እንዲሁም የበሽታው ምልክቶች ከታዩ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ያስፈልጋል ብለዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
👍152😭2
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ ሊገደዱ ነው!

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።

ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ በቀረበ ጥናት ላይ ውይይት ሲደረግ፣ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።

ላለፉት ዓመታት(እሳቸው በኃላፊነት ከተሾሙ ጀምሮ)፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ  እንዲሆን ካደረጉ መንስዔዎች መካከል፣ የመምህራን ብቃትና የተነሳሽነት ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ጠቁመዋል።

ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲቻል የተለያዩ ተግበራት እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

''የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ'' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ "በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል"ሲሉ ተናግረዋል። ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።

ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።

ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።

በቅርቡ በመምህራን ላይ በተደረገ ግምገማ ፣ 100,000 የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩ መታወቁን የተናገሩት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አሰራሩ በከፍተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንዲቀንስ የበኩልን እንደሚወጣ አስረድተዋል።

ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎችን ክፍተት ለማስተካከል ከተያዙ ዘርፈ ብዙ የማትጊያ ሥርዓቶች አንዱ፣ መምህራን በአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸውና የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋሙ ለማድረግ፣ "የመምህራን ባንክ" ማቋቋም አንዱ እቅድ መሆኑን አንስተዋል።

ባንኩ "በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባዋል ብለን እንጠብቃለን" ያሉት ሚኒስትሩ፣ በ2019 ዓ.ም ደግም በእርግጠኝነት ወደ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ አሰራር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
😁79👍50😭8👎75👀3🔥1
ማስታወቂያ

WOMEN'S GIFT PACKAGE
Gift sets

#የእጅ ሰዓት Brand Watch
#ቸኮሌት Chocolates FERRERO
#ፅጌረዳ አበባ Roses
#Teddy bear
# post Card
#perfume
#Neckless

FREE DELIVERY All over Ethiopia

Inbox for price @Fikerassefa
👍62
አኮያ ፕሮፐርቲስ

🔔 ከፒያሳ በቅርብ ርቀት ላይ ሰሜን ማዘገጃ ሳሬም ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ሳይታችን ላይ የኢድ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የሆነ ከ 5%-13% የሚደርስ ቅናሽ ስናደርግ በታላቅ ደስታ ነው ።

🔔 በካሬ 80,000 ብር ሲሸጥ የነበረውን የኢድ በአልን  አስመልክተን ለ 3 ቀን ብቻ በካሬ 76,000 ብር! 10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

🔔 2B+G+18 በሆነው አፓርትመንታች ላይ የእንጦጦ ንፁህ እና ነፋሻማ አየር እየሳቡ የተረጋጋ ህይወት ይኖራሉ!

🔔 ከ ባለ 1 እስከ ባለ 4 መኝት በተለያየ ካሬ አማራጭ

📌 ባለ አንድ መኝታ- 81 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 6,171,390 ብር
       -10% ቅድመ ክፍያ= 617,139 ብር

📌  ባለ ሁለት መኝታ-110 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 8,380,900 ብር
     -10% ቅድመ ክፍያ= 838,090 ብር

📌 ባለ ሶስት መኝታ-130 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 9,904,700 ብር
     -10% ቅድመ ክፍያ= 990,470 ብር

📌 ባለ አራት መኝታ- 211 ካሬ
      -ጠቅላላ ዋጋ=16,076,090 ብር
    -10% ቅድመ ክፍያ=1,607,609 ብር

🔔 በዚህ የመኖሪያ ህንፃ ላይ፡
💥የከርሰ-ምድር ውሀ
💥400 KVA ጄኔሬተር
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥2 ሊፍት
💥በቂ የተሰየመ የመኪና ማቆሚያ
💥መዋኛ ገንዳ
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥 ሬስቶራንት እና ካፌ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ ሰገነት እና ሌሎች መገልገያዎች።

🔔 የመረጡትን ቤት ተመላሽ በሚሆን 200,000 ብር ለ15 ቀን ማስያዝ ይችላሉ።

  ለሳይት ጉብኝት እና ለቢሮ ቀጠሮ፡
  📞 ⁨0923254077⁩  ይደውሉልን!
ቴሌግራም- @E192087
  
       አኮያ ፕሮፐርቲስ
         ከነገ ለተዛመደ!
👍1
አንዳንድ የክልል መንግስታት በጀታቸውን ወደ ግል ባንኮች ማዞር ንግድ ባንክን በሙሉ አቅሙ እንዳይሰራ ተፅዕኖ አሳድሯል ተባለ!

አንዳንድ የክልል መንግስታት በጀታቸውን ወደ ግል ባንኮች የማዞር አዝማሚያ መቀጠሉንና በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚታየው የጸጥታ ችግር የባንኩ ቅርንጫፎች በሙሉ አቅማቸው እንዳይሰሩ ተጽዕኖ እያሳደረባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት እነዚህን ጨምሮ ተግዳሮቶች ምክንያት ላለፉት 8 ወራት በርካታ የባንኩ ቅርንጫፎች አገልግሎቶቻቸው ለረጅምና ለአጭር ጊዜ እንዲያቋርጡ በመደረጉ ከ418ቱ ቅርንጫፎች መካከል 15ቱ አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን አስገንዝበዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ የባንኩን የ2017 ዓ.ም በጀት አመት የ8 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት መገምገሙን ካፒታል ተመልክቷል ።

አቶ አቤ ሳኖ እንደገለጹት የባንክ ኢንዱስትሪው አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ 2.998 ትሪሊዮን ብር ደርሷል፣ ይህም ትልቅ ምዕራፍ ነው። ከዚህ ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 49.3% የገበያ ድርሻ በመያዝ ከፍተኛውን ድርሻ ይዟል።

ባንኩ 367 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ተቀማጭ መሰብሰቡንና ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ሲወዳደር የ344.4% እድገት ማሳየቱን አብራርተዋል።በበጀት ዓመቱ ባንኩ ከሰጣቸው ብድሮች በመጀመሪያው 8 ወራት 149.26 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡንና ካምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ66.8% እድገት ማሳየቱንም አስረድተዋል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍38😁113😭2👎1
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የቀረበላትን አዲሱን የታሪፍ አወቃቀር ተቀበለች!

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የቀረበላትን አዲሱን የታሪፍ አወቃቀር በደስታ እንደምትቀበል አስታወቀች። ይህ አወቃቀር የኢትዮጵያ ምርቶች ወደ አሜሪካ ገበያ ሲገቡ የሚጣልባቸውን ታሪፍ 10% ብቻ በማድረግ ተወዳዳሪነታቸውን ያሳድጋል ብሏል።

መንግስት ይህ ውሳኔ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር እና የኢትዮጵያን ኤክስፖርት ለማሳደግ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ገልጿል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ዉሳኔዉን ተከትሎ እንዳስታወቀዉ ይህ አዲሱ የታሪፍ አወቃቀር ኢትዮጵያ እንደ ቬትናምና ባንግላዴሽ ካሉ ትልልቅ የማምረቻ ማዕከላት ጋር ስትወዳደር የተሻለ እድል እንዲኖራት ያደርጋል።

"የ10% የታሪፍ መጠን ለኢትዮጵያ ላኪዎች ከፍተኛ ማበረታቻ ይሰጣል" ሲል ሚኒስትሩ አስታውቋል ። "ይህ የኢትዮጵያ ምርቶች በአሜሪካ ገበያ ተወዳዳሪ ዋጋ እንዲኖራቸው በማድረግ የፍላጎት እና የኢንቨስትመንት መጨመርን ያመጣል ሲል ተስፋዉን ጥሏል።

ይሁን እንጂ፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚያስጠነቅቁት፣ ይህንን እድል በአግባቡ ለመጠቀም ኢትዮጵያ አሁንም በርካታ ተግዳሮቶችን መወጣት አለባት። የመሠረተ ልማት ውስንነት፣ የምርት ጥራት እና ደረጃዎች፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እና የፖለቲካ አለመረጋጋት ጥቂቶቹ መሆናቸውን አፅንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል።

Via Capital
@YeneTube @Fikerassefa
👍31😁18👎42😭1
🚀 ቡስትግራም:ለቲክቶክ 📹 ፣ ኢንስታግራም 📷፣ ፌስቡክ 👍፣ ዩቲዩብ ✈️ እና ቴሌግራም ✈️ በቀላሉ ላይኮች፣ ተመልካቾች እና ፎሎወሮች ያግኙ።


📹 የቲክቶክ እድገት: ቪዲዮዎችዎ ብዙ ቪውስ፣ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ኮመንቶች ያግኙ።

📷 የኢንስታግራም ማሻሻያ: ፎሎወሮች፣ ላይኮች፣ ቪውስ እና ኮመንቶች ያግኙ።

👍 የፌስቡክ አገልግሎት: የፔጅዎ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ፖስቶች ላይ ኢንጌጅመንቶች ይጨምሩ።

📹 የዩቲዩብ አገልግሎት: ሰብስክራይበሮች እና ቪዲዮ ቪውስ በፍጥነት ያግኙ።

✈️ ቴሌግራም: ቻነል መምበሮች፣ ፖስት ቪውስ፣ ላይኮች እና ሪአክሽኖች ይጨምሩ።

ቡስትግራም - የሶሻል ሚዲያ ገፅታዎን መገንባት አሁን በጣም ቀላል ሆኗል!`

OPEN BOOSTGRAM - 🔗 https://tttttt.me/boostgramPromoBot/boostgram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥5👍4
የአርኤስኤፍ ምክትል አዛዥ የሰሜን ሱዳን ግዛቶችን ሊወሩ እንደሚችሉ ተናገሩ

የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች (አርኤስኤፍ) ምክትል አዛዥ አብደል ራሂም ሃምዳን ዳግሎ፣ ወታደራዊ ቡድኑ ከፍተኛ የጦር ሜዳ ኪሳራ ካጋጠመው በኋላ ባደረጉት ንግግር ሁለት የሱዳን ሰሜናዊ ክፍል ግዛቶችን ሊወሩ እንደሚችሉ ዝተዋል። የሱዳን ጦር ከሴናር፣ ገዚራ እና ነጭ ናይል ግዛቶች እንዲሁም ከአብዛኛው የዋና ከተማዋ ካርቱም አከባቢዎች አስወጥቶ የሰሜን ኮርዶፋን ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ኤል ኦቤይድ የአርኤስኤፍን ከበባ ሰብረዋል።

በምእራብ ዳርፉር ግዛት ባልታወቀ ቦታ በተቀረፀው ቪዲዮ ላይ ዳግሎ በሰሜናዊ ግዛት ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን የሚጠቁሙ መፈክሮችን በሚያሰሙ ተዋጊዎች ተከበው ታይተዋል። በአርኤስኤፍ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ እንደተገለጸው ከሆነ ደግሞ 20ሺ አዳዲስ ተዋጊዎች በተመረቁበት ወቅት ነው ንግግር ያደረጉዮት ተብሏል። "በሰሜን ግዛት እና በናይል ወንዝ ውስጥ እየመጣን ነው" ሲሉ ዳግሎ የተደመጡ ሲሆን አሁን ግን ጦርነቱ በሰሜን በኩል ነው ሲሉም አክለዋል።

ምክትል አዛዡ ከወንድሙ ከአርኤስኤፍ አዛዥ መሀመድ ሃምዳን ዳግሎ ጎን በመሰለፍ ለመፋለምም ቃል ገብቷል። በቪዲዮው ላይ፣ ዳግሎ ጥለው የሄዱ የRSF መኮንኖች በሰአታት ውስጥ ወደ ጦር ግንባር እንዲያመለክቱ ያዘዙ ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን ከስራ እንዲባረሩ እና እንዲከሰሱ እንደሚያደርጉም ገልፀዋል።  አንዳንድ መኮንኖችን “ከእናቶቻቸው እና ከእህቶቻቸው ጋር” ቤት ይቆያሉ ሲልም ተደምጠዋል።

የዳግሎ ዛቻ በአርኤስኤፍ መስክ አዛዦች በደርዘን የሚቆጠሩ መኮንኖች እና ወታደሮች ከቅርብ ጊዜ ሽንፈት በኋላ ጥለው መውጣታቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
👍174😭1
በሚያንማር ከእገታ ነፃ ወጥተው የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው የሚመልሳቸው አካል በመጥፋቱ ወደ አስፈሪ ካምፖች ሊመለሱ መሆኑን ተናገሩ

(መሠረት ሚድያ)- በሚያንማር በእገታ ተይዘው ከባድ ስራ ካለ ክፍያ ሲሰሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በአንድ የአካባቢው ጦር ሀይል ከሳምንታት በፊት ነፃ ቢወጡም ወደ ሀገራቸው የሚመልሳቸው አካል በመጥፋቱ ወደ አስፈሪ ካምፖች ሊመለሱ መሆኑን ተናግረዋል።

"ወደ ሀገራችን ለመውጣት ዛሬ ነገ እያልን ወደ አስፈሪው ካምፓኒ ተመለሱ ተባልን" ብለው ለመሠረት ሚድያ ቃላቸውን የሰጡት ኢትዮጵያውያኑ አብዛኞቹ ተዳክመው የሞት አፋፍ ጭምር ላይ ያሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

"በሚያንማር ተገደን የማጭበርበር ስራ ላይ የነበርንና በሚሊተሪ ድጋፍ ነጻ የወጣን ከ730 በላይ የምንሆን ኢትዮጵያዊን በሁለት የሚሊተሪ ካምፖች ሆነን የሀገራችን ምላሽና የማጓጓዝ ስራ ከተጠባበቅን ሁለተኛ ወራችን እያገባደድን እንገኛለን" የሚሉት ዜጎች ይህም ከካምፓኒ ለመውጣት ሲጠየቁ ከነበረው 5 ሺህ ዶላር ነጻ ያደረጋቸው እና የኢትዮጵያ መንግስትም ፓርኮቹ ድረስ ገብቶ ዜጎቹን ለማውጣት ተፈጥሮበት የነበረውን ፈተና ያቀለለ ምቹ አጋጣሚ ነበር ይላሉ።

"እዚህ ካምፕ በቆየንበት የሁለት ወር ጊዜ ውስጥ በየጊዜው ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የወላጆች ኮሚቴ ሒደቱ እየተሰራበት እንደሆነ በሚደርሱን መረጃዎች እየተጽናናን ቆይተናል፡፡ በመካከላችንም የቀዶ ጥገና የተሰራላቸውና ማገገም ያልቻሉ፣ በተፈጥሮ አደጋው አደጋ የደረሰባቸውና የሚፈሳቸው ደም አሁን ድረስ ያላቆመ፣ በአንጀት እና አንገት ህመም ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ ማይችሉ እና ሌሎችም ጽኑ ህሙማን እንዳሉ እና በቂ ህክምና ማግኘት ማይቻልበት ጠረፍ ላይ መሆናችን ሰው እንዳናጣ እየሰጋን መሆኑን ለሚዲያዎች እና ለመንግስት ተቋማት እያሳወቅን የቆየን መሆናችን ይታወቃል" ብለው አስረድተዋል።

አክለውም "ሚሊተሪው የተያዘውን ምግብ ቢያቀርብም ከሀይማኖታችንና ከሀገራችን የአመጋገብ ባህል ጋር ፈጽሞ የማይሔድ የእስያ ምግብ በመሆኑ በውድ ዋጋ በሽያጭ የሚያቀርቧቸውን ምግቦች እየገዛን እንጠቀም ነበር። አሁን ግን ሁላችንም እጃችን ላይ የነበረንን ገንዘብ ጨርሰን ምግብና መድኃኒት ምንገዛበት የሌለን በመሆኑ ለረሀብ እና ለጤና ችግር ተጋልጠናል፡፡ ይህንን ሁሉ ችግር ያልፋል ብለን በኢትዮጵያ መንግስት እና ኤምባሲዎቹ እየተሰሩ ያሉ እኛን የመመለስ ስራ በተስፋ እየጠበቅን ባለንበት ወቅት ሁላችንንም ያስደነገጠ እና ተስፋችን የቀማን ችግር ተከስቷል፡፡"

"ይህም ከአረመኔያዊ አያያዝ አውጥቶ ካምፕ ውስጥ ያስገባን ሚሊተሪ የእለት ምግብ የሚለውን እያቀረበ የሀገራችን ምላሽ እየተጠባበቀ የነበረ ቢሆንም ከኢትዮጵያ መንግስት እና በኤምባሲዎቻችን በኩል እየተሰራ ያለው እኛን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እጅጉን የተጓተተ በመሆኑ እና ከ29 ሀገራት እኛ ብቻ በመቅረታችን ሚሊተሪው በኢትዮጵያ መንግሥት ተስፋ ቆርጦ ወዷ ካምፓኒዎች እንዲንመለስ ሊጠይቀን ችሏል" በማለት በሀዘን ያሉበትን ሁኔታ ለመሠረት ሚድያ አስረድተዋል።

"ይህም በብዙዎቻችን ላይ ትልቅ ሽብርና መደናገጥ የፈጠረ አደገኛ ክስተት ሆኖ ለጭንቀት የዳረገን ጉዳይ ነው። በመሆኑም ሚዲያዎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ኤምባሲዎች ለዚህ አደገኛ ሒደት ፈጣን ግብረ መልስ በመስጠት ወደ ሀገራችን መመለስ ካልቻሉ መቀልበስ የማንችለው የ735 ወጣት ህይወት አደጋ ውስጥ እየገባ እንደሆነ ማሳወቅ እንፈልጋለን" ብለዋል።

"የኢትዮጵያ መንግስት እኛን የመመለስ አቅም የለውም ወይ? መልሱ አዎ ከሆነ ተመልሰን እዛ ካምፓኒ ከምንገባ እዚሁ እራሳችንን እናጠፋለን፣ የመጨረሻ አማራጭ እሱ ነዉ፣ የመጨረሻ ዛሬ ተስፋ ቆርጠናል፣ ጭንቀታችን በርትቷል ስለዚህ መልስ እንፈልጋለን" በማለት ተናግረዋል።

እስራኤል የተባለ አንድ ኢትዮጵያዊ "አሁን በምንገኝበት ቦታ ላይ ምግብ በቀን አንዴ እና አልፎ አልፎ ሁለቴ ይሰጣሉ፣ የሚጠጣ ውሃ ስለሌላ የመጸዳጃ ውሃ ነው የምንጠጣው። የምንተኛው መሬት ላይ ነው፣ በረሀብ እና በህክምና እጦት እያለቀን ነው፣ እኛ ያለንበትን አካባቢ የሚያስተዳድረው DKBA (Democratic Karna Buddhist Arm) ይባላል። አካባቢው ያልተረጋጋ እና ጦርነት ያለበት ነው ስለዚህ ለእኛ ትልቅ ስጋት ፈጥሮብናል፣ ሌሎች አገራት ወጥተው አለቁ፣ ዛሬ ራሱ ዩጋንዳ አውጥቷል። ኢትዮጵያውያን ብቻ ቀርተዋል። ሌሎች አገራትን ሊያወጡ ሲመጡ ስንጠይቃቸው የኢትዮጵያ መንግሥት መልስ አይሰጥም ይሉናል" ብሏል።

"የሌሎች ሀገራት 40 እና 30 ዜጎች እየወጡ ነው፣ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ከ250 በላይ ዜጎች እያሉ ዝምታን መርጧል፣ መንግስት ለምን እንደዚህ ይጨክንብናል? እኛ ኢትዮጵያዊን አይደለንም። የደቡብ አፍሪካ መንግስት እዚህ ያሉ 3ቱንም ዜጎቹን ከትናንት በስትያ ፍለጋ መጥቶ ወስዳል፣ እኛስ?" ብሎ ጠይቋል።

በዚህ ዙርያ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጨማሪ መረጃ ካገኘን እንመለስበታለን።

@Yenetube @Fikerassefa
👍47😭314😁1
ማስታወቂያ

WOMEN'S GIFT PACKAGE
Gift sets

#የእጅ ሰዓት Brand Watch
#ቸኮሌት Chocolates FERRERO
#ፅጌረዳ አበባ Roses
#Teddy bear
# post Card
#perfume
#Neckless

FREE DELIVERY All over Ethiopia

Inbox for price @Fikerassefa
👍71
አኮያ ፕሮፐርቲስ

🔔 ከፒያሳ በቅርብ ርቀት ላይ ሰሜን ማዘገጃ ሳሬም ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ሳይታችን ላይ የኢድ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የሆነ ከ 5%-13% የሚደርስ ቅናሽ ስናደርግ በታላቅ ደስታ ነው ።

🔔 በካሬ 80,000 ብር ሲሸጥ የነበረውን የኢድ በአልን  አስመልክተን ለ 3 ቀን ብቻ በካሬ 76,000 ብር! 10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

🔔 2B+G+18 በሆነው አፓርትመንታች ላይ የእንጦጦ ንፁህ እና ነፋሻማ አየር እየሳቡ የተረጋጋ ህይወት ይኖራሉ!

🔔 ከ ባለ 1 እስከ ባለ 4 መኝት በተለያየ ካሬ አማራጭ

📌 ባለ አንድ መኝታ- 81 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 6,171,390 ብር
       -10% ቅድመ ክፍያ= 617,139 ብር

📌  ባለ ሁለት መኝታ-110 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 8,380,900 ብር
     -10% ቅድመ ክፍያ= 838,090 ብር

📌 ባለ ሶስት መኝታ-130 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 9,904,700 ብር
     -10% ቅድመ ክፍያ= 990,470 ብር

📌 ባለ አራት መኝታ- 211 ካሬ
      -ጠቅላላ ዋጋ=16,076,090 ብር
    -10% ቅድመ ክፍያ=1,607,609 ብር

🔔 በዚህ የመኖሪያ ህንፃ ላይ፡
💥የከርሰ-ምድር ውሀ
💥400 KVA ጄኔሬተር
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥2 ሊፍት
💥በቂ የተሰየመ የመኪና ማቆሚያ
💥መዋኛ ገንዳ
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥 ሬስቶራንት እና ካፌ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ ሰገነት እና ሌሎች መገልገያዎች።

🔔 የመረጡትን ቤት ተመላሽ በሚሆን 200,000 ብር ለ15 ቀን ማስያዝ ይችላሉ።

  ለሳይት ጉብኝት እና ለቢሮ ቀጠሮ፡
  📞 ⁨0923254077⁩  ይደውሉልን!
ቴሌግራም- @E192087
  
       አኮያ ፕሮፐርቲስ
         ከነገ ለተዛመደ!
👍52
ዛምቢያዊያን በአሰቃቂ የህፃናት መደፈር ሪፖርቶች አደባባይ ወጡ!

በዛምቢያ ዋና መዲና ሉሳካ በቅርብ በተሰሙ ተደጋጋሚ የህፃናት መደፈር ሪፖርቶች ምክንያት የአደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።ባለፉት ሁለት ወራት ዛምቢያዊያን ሞትንም ባስከተሉ በበርካታ የህፃናት መደፈር ሪፖርቶች ደንግጠዋል።

በጣም ዘግናኝ ከሆኑ ሪፖርቶች መካከል ለካንሰር ሕክምና ሆስፒታል የተኛችውን የሰባት ዓመት ልጁን የደፈረ አባት ይገኝበታል።የአምስት ዓመት ልጅ በአራት ወንዶች በቡድን መደፈርን ጨምሮ የስድስት ዓመት ልጁን በመድፈር የብልት ኪንታሮት እና የአባላዘር በሽታ ያስያዘ አባት ታስሯል።

የዛምቢያ ፍትሕ ሚኒስትር ፕሬንሰስ ካሱኑ-ዙሉ መድፈርን ለመከላከል እና ህፃናትን ከጥቃት ለመጠበቅ የደፋሪዎች ብልትን መቁረጥ የመሰለ ከመጠን በላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል።

"እንደ አገር ከዚህ በታች መውረድ እንችላለን? እንደ ማኅበረሰብ ከዚህ በታች ምን ያህል ዝቅ እንላለን? እየሆነ ያላው ያሳምማል። አሁን ከሕግ በላይ ነው። ሞራላችን ለምን እንደዘቀጠ ዛምቢያዊያን መመርመር የእናንተ ፋንታ ነው" ብለዋል ለአገሪቱ እንደራሴዎች።

ሪፖርቶቹን ተከትሎ ሐሙስ ዕለት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ ሙዚቀኞች እና ግለሰቦች የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ መንግሥት የህፃናት ደፋሪዎች ላይ ከባድ ቅጣትን የሚጥሉ ሕጎችን እንዲወጣ ጠይቀዋል።ለምክትል ፕሬዝዳንት ሙታላ ናሉማንጎ በደረሰ የፊርማ ስብስብ በህፃናት መድፈር የተጠረጠሩ ሰዎች ዋስትና እንዲከለከሉ የሕግ ለውጥ እንዲደረግም ጠይቀዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጉዳዩ ሁሉንም የዛምቢያ ዜጋ የሚያሳስብ በመሆኑ አቋም መያዝ አለበት ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።በተቃውሞ ሰልፉ የተሳተፈች ሙዚቀኛ "ለልጆቻችን ደኅንነት ያለው ከባቢ ልንፈጥር ይገባል" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች።

ሲስታ ዲ በሚል ስም የምትታወቀው ሙዚቀኛ ህፃናት ደፋሪዎች ብልታቸው ሊቆረጥ ይገባል ያለችም ሲሆን፤ ይህም "ለህፃናት ደኅንነት ሲባል እና ከወንድነት ክብራቸው መግፈፍ ያስፈልጋል። ምክንያቱም አይገባቸውምና" ብላለች።እ.አ.አ በ2024 ሦስት ወራት ብቻ በዛምቢያ ከህፃናት ፆታዊ ጥቃት ጋር የተያያዙ ከ10 ሺህ የሚበልጡ ሪፖርቶች ተመዝግበዋል።የአገሪቱ ብሔራዊ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንደዘገበው አብዛኞቹ ሪፖርቶች በዋና ከተማው ሉሳካ ተመዝግበዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍25😭16👎2
የቤት ሠራተኞችን የጡረታ ተጠቃሚ የሚያደርግ የሥራ ቅጥር ውልና አጠቃላይ ደንብ በ6 ወር ውስጥ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ!

የቤት ሠራተኞች ጡረታን ጨምሮ የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል የሥራ ቅጥር ውልና አጠቃላይ የቤት ሠራተኞች ደንብ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አንድነት የኢትዮጵያ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ማህበራት ሕብረት አስታውቋል።

የሕብረቱ ፕሬዚዳንት ሂሩት አበራ የቤት ሠራተኞችን ሕግ በሚመለከት በዓለም አቀፉ ኮንቬንሽን 189 በተቀመጠው ሕግ መሠረት በቀጥታ ለመተግበር አስቻይ ሁኔታ ባለመኖሩ፤ ከኢትዮጵያ ጋር እንዲስማማ ተደርጎ ደንቡና የሥራ ቅጥር ውሉ እንደሚዘጋጅ ተናግረዋል፡ይኸው ደንብ በረቂቅ ደረጃ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል እየተዘጋጀ እንደሚገኝም ጨምረው አስታውቀዋል።

ለአብነትም በቋሚነት የሚሰሩ ሠራተኞች በሥራ ቦታቸው ላይ የመኖር፣ ተመላላሽ የሆኑት ደግሞ ሰርተው የሚሄዱበትን አግባብ የለየና የሥራ ቅጥር ውሉን ጨምሮ የሚወጣው ደንብ መሠረታዊ የሆኑ መብቶቻቸው ላይ ያተኮረ መሆኑን የሕብረቱ ፕሬዝደንት ገልጸዋል።በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ የሥራ ቅጥር ውሎች መኖራቸውን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቷ፤ ነገር ግን ውሎቹ ሕጋዊ አለመሆናቸውን አስረድተዋል።

ከዚህም በመነሳት ለቀጣሪዎችም ሆነ ለቤት ሠራተኞች የሚጠቅም ወጥ የሆነ የሥራ መቀጠሪያ ውል እንዲኖር ለማስቻል ያሰበ መሆኑን ጠቅሰዋል።ከዚሁጋ ተያይዞም ውሉ መውጣቱ ብቻ ሳይሆን 'ተፈፃሚነቱስ እስከምን ድረስ ነው?' የሚለውን ጉዳይ ማህበረሰቡ በደንብ ማየት ስላለበት የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እየተሰራበት እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የቤት ሠራተኞች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ዘርፈ ብዙ እንደሆኑ የገለጹት ፕሬዚዳንቷ፤ የሥራ ቅጥር ውሉን ጨምሮ አጠቃላይ የቤት ሠራተኞች የሕግ ማዕቀፍ ጸድቆ ተግባራዊ በሚሆንበት ወቅት የሚታዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሁሉ ሊቀርፍ እንደሚችል አንስተዋል።አክለውም "ውሉ ለቤት ሠራተኝነት ሥራ እውቅና የሚሰጥ በመሆኑ የሕክምና አገልግሎት፣ ሰርተው ሲደክማቸው በጡረታ የሚካተቱበት አግባብን ጨምሮ ማህበራዊ ዋስትናቸውን ሊያረጋግጡ የሚችሉበትን መንገድ ይፈጥራል" ብለዋል። በመሆኑም በዚህ 6 ወር ጊዜ ውስጥ የሥራ ቅጥር ውሉና አጠቃላይ የቤት ሠራተኞች ደንብ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
👍486👀3😁2