በመዲናዋ 100 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች አገልግሎት መስጠት ጀመሩ!
በመዲናዋ አዲስ አበባ ከተማ ያለውን የብዙሃን ትራንስፖርት እጥረት እና የነዋሪዎችን እንግልት የሚቀንሱ 100 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን በመግዛት ወደ ስምሪት መግባታቸውን የከተማ መስተዳድሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።
የITS (ኢንተለጀንት የትራንስፖርት ሥርዓት) እና FCS (የታሪፍ ስብስብ ሥርዓት) ቴክኖሎጂን በተቀናጀ መልኩ በሥራ ላይ ያዋሉት እነዚህ አውቶቢሶች ከአየር ብክለት ነፃ፣ ምቹ፣ በአንድ ጊዜ በርካታ የሠው ቁጥር ማጓጓዝ የሚችሉ፣ ዘመናዊና ተደራሽ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ አስተማማኝ፣ ለአውቶቡስ ብቻ በተፈቀደ መስመር ስለሚጓዙ ፈጣን አገልግሎት የሚሰጡ እንዲሁም ለነዳጅ ይወጣ የነበረውን ወጪ የሚቀንሱ መሆናቸውን ከንቲባዋ ተናግረዋል።
አውቶብሶቹ የቅድመ ክፍያ ካርድን ጨምሮ ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥን መያዛቸው ተገልጿል፡፡
ወደ አገልግሎት የገቡት 100 የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች በዛሬው ዕለት በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫዎች ለነዋሪዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጡም አስታውቀዋል።
አክለውም፤ "የሕዝባችንን እንግልት ለመቀነስ የጀመርነውን ራዕይ በመጋራት በመንግሥትና የግል አጋርነት መርሃግብር የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኦፕሬተር በመሆን ዛሬ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ በነዋሪዎቻችን ሥም ላመሰግነው እወዳለሁ" ብለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa

👍35❤13🔥4⚡1😁1
የፌደራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚደነግገው አዋጅ ጸደቀ
ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ የፌደራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ ማሻሻያ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል፡፡
የማሻሻያ አዋጁ ከዚህ ቀደም በነበረው አዋጅ በትግበራ ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም መሠረት አዋጁ እስከ አሁን በሥራ ላይ የነበረውን አዋጅ ቁጥር 359/ 1995 የሚተካ ሲሆን፤ አዋጅ ቁጥር 1373/2017 ሆኖ በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ በአብለጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

👍19😁7👎3🔥3
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት፤ ከዘጠኝ ወር በፊት ከነበረበት ጋር ሲነፃፀር 200 በመቶ መጨመሩ ተናገረ፡፡
የመጠባበቂያ ክምችቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያው እንዲወሰን ከተደረገበት ሀምሌ 22/2016 ዓ.ም ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን፤ በበጀት ዓመቱ ሊጠናቀቅ ሶስት ወራት እየቀሩ እቅዱ መሳካቱን የተናገሩት የብሔራዊ ባንኩ ዋና ገዥ ማሞ እስመለአለም ምህረቱ ናቸው፡፡
ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ወዲህ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ለረጅም ዐኣመታት ስር ሰዶ የቆየውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በሂደት መሰረታዊ በሚባል ደረጃ እየተቃለለና ፍሰቱም እየጨመረ ይገኛል ብለዋል፡፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በትናንትናው እለት ከባንክ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር በአጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደርና አፈፃፀም በተመለከተ ውይይት ማድረጉንም ገዢው አስረድተዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት በአፈፃፀም በኩል የሚታዩ አንዳንድ ችግሮች እንዲስተካከሉ እና የውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች በጥብቅ እንዲፈፀሙ መመሪያ ተሰጥቷል ብለዋል፡፡በተለይም ባንኮች የሚያስከፍሉትን ኮሚሽን እና የአገልግሎት ክፍያ ተመጣጣኝ እንዲያደርጉ መመሪያ ሰጥቷል ተብሏል፡፡በየሁለት ሳምንቱም የውጭ ምንዛሪ ግልፅ ጨረታ ቢያንስ የተያዘው በጀት መጨረሻ ድረስ እንደሚወጣም አቶ ማሞ ጠቅሰዋል፡፡
ውጭ ምንዛሪ ግብይት ከባንክ ሥርዓት ውጪ በሚያካሂዱ፣ ወደ ውጪ በሚያሸሹ፣ በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በሚሳተፉ እና የ ብሔራዊ ባንክ የአሰራር እና የቁጥጥር ሥርዓት በሚጥሱ ላይ ጥብቅ የቁጥጥር እና የክትትል ስራም ይሰራል ብለዋል፡፡በዚህ ሥራ የተሰማሩ ኩባንያዎች እና ፈቃድ የሌላቸው ኩባንያዎችና ግለሰቦች ከኢትዮጵያ የባንክ ስርዓት ጋር ያላቸው ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥ ይደረጋል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የሰጣቸውን የሐዋላ ኩባንያዎች ስም ዝርዝር በባንኩ ድረ ገፁ እንደሚያሳውቅ የተናገሩት ገዥው ማሞ እስመለአለም ምህረቱ፤ ከዚያ ውጭ ያሉት በሙሉ ፈቃድ ያልተሰጣቸው እንደሆኑ መታወቅ አለበት፤ በዚህም ህብረተሰቡ ከስጋት፣ ከስርቆትና መጭበርበር ራሱን መጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው እለት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ጨረታ አውጥቷል፡፡
የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አካሄድ በማዕካላዊ ባንክ እየተከማቸ ካለው የውጭ ምንዛሪ የተወሰነውን መጠን ለግሉ ዘርፍ ለማቅረብና የማዕከላዊ ባንኩን የገንዘብ ፖሊሲ ዓላማ ለማሳካት የሚረዳ ይሆናል ተብሏል፡፡ፍላጎቱ ያላቸው ባንኮች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዛሬ ከ4 ሰዓት አስከ 6 ሰዓት እንዲያስገቡ ባንኩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
Via Sheger

👍21👎8❤4
ብሔራዊ ባንክ፤ባንኮች የአገልግሎት ክፍያን ተመጣጣኝ እንዲያደርጉ መግባባት ላይ መድረሱን አስታወቀ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ገንዘብ ለማስተላለፍና ለሌሎች የባንክ አገልግሎቶች ባንኮች የአገልግሎትና የኮሚሽን ክፍያ አሳማኝ ባልሆነ መልኩ እያስከፈሉ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ድርጊቱም በአብዛኛው ማህበረሰብ ዘንድ ግርታን መፍጠሩ የሚታወስ ነው።
የብሄራዊ ባንክ፤ ከባንክ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር በተደረገው ስብሰባ ባንኮች የአገልግሎት ክፍያቸውን ተመጣጣኝ እንዲያደርጉ መግባባት ላይ መደረሱን የብሄራዊ ባንክ ገዢው ማሞ ምህረቱ ተናግረዋል።በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጪ ምንዛሬ ተመን ስርዓት ሐምሌ 2016 ዓ.ም. ከተደረገ ወዲህ ብሔራዊ ባንክ ሁለት ጊዜ ዶላር ለባንኮች በጨረታ መሸጡ የሚታወስ ነው።
የብሄራዊ ባንክ ገዢው ማሞ ምህረቱ ባስተላለፉት መልዕክት ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በኋላ ለረጅም አመታት ስር ሰዶ የቆየውን የውጪ ምንዛሬ እጥረት መሠረታዊ በሚባል ደረጃ እየተቃለለና የውጪ ምንዛሬ ፍሰቱ እየጨመረ መሆኑን አስረድተዋል፡በዚህም የባንኩ መጠባበቂያ የውጪ ምንዛሬ ክምችት በእጅጉ መሻሻሉን አስቀድመው ብሄራዊ ባንክ ለተከታታይ ወራቶች ይቀጥላል የተባለለትን የውጪ ምንዛሬ ለባንኮች ማጫረት መጀመሩን የብሄራዊ ባንክ መረጃ ያመላክታል፡፡

👍26😁2😭1👀1
ብርቱካን ተመስገንን ጨምሮ በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ መፈቀዱ ተሰማ!
ብርቱካን ተመስገንን በተመለከተ በመገናኛ ብዙኃን ከተላለፈው ሐሰተኛ ዘጋቢ ፊልም ጋር በተያያዘ በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ለፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ፡፡
ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ የሰጠባቸው ተጠርጣሪዎች፤ ብርቱካን ተመስገን፣ ነብዩ ጥዑመልሳን የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅ፣ ታሪኩ ኃይሌ የአዲስ ምራፍ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ፣ ደረጀ ሉቃሌ፣ ኅሊና ታረቀኝ፣ ንጥር ደረጀ እና መታገስ ዓለሜ ናቸው፡፡
በተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል ስልጣንን በኃይል ለመያዝ ፣ የጦር መሣርያ በመታጠቅ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ በመደራጀት፣ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሰ ከሚገኘው ጽንፈኛና ፀረ ሰላም ቡድን አመራሮች ጋር በጥቅም በመመሳጠር፣ መንግሥት የሕዝብ ተቀባይነት እንዲያጣና ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ እንዲደረግበት በማሰብ፣ ተዋድደውና ተከባብረው በሚኖሩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መካከል ቅራኔ በመፍጠርና ወደ ግጭት እንዲገቡ ለማድረግ፣ በውጭ ሀገር ከሚገኝ የፀረ ሰላም የቡድኑ አመራሮች ጋር በተለያዩ መገናኛ መንገዶች በመገናኘት እና ተልዕኮ በመቀበል የሥራ ባህሪያቸውን እንደመልካም አጋጣሚ መጠቀም የሚሉ የምርመራ የጥርጣሬ መነሻውን ለችሎቱ አቅርቧል፡፡
ፖሊስም የምርመራ ሥራየን በሰውና በሠነድ ማስረጃ በስፋት ማጣራት እንድችል 14 ተጨማሪ ቀናት ይፈቀድልኝ ሲል ባሳለፍነው ዓርብ መጠየቁን ተከትሎ፤ ፍርድ ቤቱ በዛሬው ዕለት የፖሊስን ጥያቄ በመቀበል 14 የምርመራ ቀን ፈቅዷል
Via FBC

👎82👍35😁9👀4❤3
ብሄራዊ ባንክ ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ በአማካኝ አንድ ዶላር 131 ነጥብ 70 ብር ተሸጠ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት ያካሄደውን የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ አድርጓል።ባንኩ በየሁለት ሳምንት መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ ማካሄድ እንደሚጀምር ማስታወቁን ተከትሎ፤ በዛሬው ዕለት 50 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ለባንኮች በጨረታ አቅርቧል፡፡
በዚህም ጨረታ ላይ 12 ባንኮች የውጭ ምንዛሬውን መከፋፈል መቻላቸውን ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል።በዚህም አማካኝ የምንዛሪ ጨረታ ዋጋ አንድ የአሜሪካን ዶላር 131 ነጥብ 7095 ብር ሆኖ መመዝገቡን ገልጿል።
ባንኩ ከአንድ ወር በፊት 60 ሚሊየን ዶላር ለጨረታ አቅርቦ የነበረ ሲሆን፤ በአማካኝ 135 ነጥብ 6 ብር ለአንድ ዶላር መግዣ ቀርቦ እንደነበር ይታወሳል።በዚህም ዛሬ በወጣው ጨረታ የቀረበው አማካኝ ዋጋ ካለፈው ወር ጋር ሲስተያይ፤ የ3 በመቶ አካባቢ ቅናሽ ታይቶበታል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መሰል ጨረታዎች ለሚቀጥሉት በርካታ ወራት በየሁለት ሳምንቱ እንደሚካሄዱ ያስታወቀ ሲሆን፤ ዓላማውም የማዕከላዊ ባንኩን የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት ግብን ማሳካት ነው ብሏል፡፡
Via Ahadu

👍18👎5❤2
የኢ ቢ ኤስ ቴሌቪዥን "የአዲስ ምዕራፍ" ፕሮግራም ከስርጭት ታግዶ እንዲቆይ ተወሰነ!
በኢ ቢ ኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ የሚተላለፈውና "አዲስ ምዕራፍ" የተሰኘው ፕሮግራም በኤዲቶሪያል አሰራሩ ላይ አስፈላጊውን እርምት በመውሰድ ለባለሥልጣኑ እስኪያሳውቅና ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ፤ ከስርጭት ታግዶ እንዲቆይ የተወሰነ እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አስታውቋል።
ባለሥልጣኑ እሁድ መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ያሰራጨውን ፕሮግራም ከመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና ከዘርፉ ሕጎች አንጻር በመገምገም አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ነው የገለጸው፡፡
- የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የፕሮግራሙን መታገድ አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

👎88👍24❤3
ፕሬዚዳንት ፑቲን በዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የተባለለትን የውትድርና ጥሪ አስተላለፉ
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከፈረንጆቹ 2011 ወዲህ ከፍተኛ የተባለለትን ወታደራዊ ጥሪ ለዜጎች አስተላልፈዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ጥሪውን ያደረጉት ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 30 ዓመት ለሚሆኑ 160 ሺህ የሀገሪቱ ወንዶች ሲሆን፣ ይህም የሀገሪቱን መከላከያ ሠራዊት አባላት ቁጥር በእጅጉ እንደሚያሰፋው ተገልጿል፡፡
ጥሪው የተላለፈው ፕሬዚዳንት ፑቲን የሩሲያን መከላከያ ሠራዊት አባላት ብዛት ወደ 2.39 ሚሊየን እንደሚያደርሱ ከተናገሩ ከወራት በኋላ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
ይህም በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ 180 ሺህ ተጨማሪ ኃይል ምልመላ ማለት ነው።
ምክትል አድሚራል ቭላድሚር ሲምልያንስኪ፣ አዲሶቹ ምልምል ወታደሮች በዩክሬን ጦርነት እንደማይሳተፉ አረጋግጠዋል።
ይሁን እንጂ ከዚህ በፊት ሰራዊቱን የተቀላቀሉ ምልምል ወታደሮች በዩክሬን ጦርነት ተሳትፈው ህይወታቸው ያለፈ ስለመኖሩ በዩክሬን በኩል መነገሩ ተነስቷል፡፡
ፕሬዚዳንት ፑቲን ክስተቱን አስመልክተው በሰጡት ማስተባበያ፣ ጅምር ላይ ጥቂት ምልምል ወታደሮችን በስህተት ወደ ግንባር በመላክ የተፈጠረ እንጂ ሁሉንም ያሳተፈ እንዳልነበር መግለፃቸውን የአር ቲ ኢ ዘገባ አመልክቷል፡፡

👍74❤5🔥3👎1
Forwarded from YeneTube
አኮያ ፕሮፐርቲስ
🔔 ከፒያሳ በቅርብ ርቀት ላይ ሰሜን ማዘገጃ ሳሬም ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ሳይታችን ላይ የኢድ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የሆነ ከ 5%-13% የሚደርስ ቅናሽ ስናደርግ በታላቅ ደስታ ነው ።
🔔 በካሬ 80,000 ብር ሲሸጥ የነበረውን የኢድ በአልን አስመልክተን ለ 3 ቀን ብቻ በካሬ 76,000 ብር! ከ 10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
🔔 2B+G+18 በሆነው አፓርትመንታች ላይ የእንጦጦ ንፁህ እና ነፋሻማ አየር እየሳቡ የተረጋጋ ህይወት ይኖራሉ!
🔔 ከ ባለ 1 እስከ ባለ 4 መኝት በተለያየ ካሬ አማራጭ
📌 ባለ አንድ መኝታ- 81 ካሬ
-ጠቅላላ ዋጋ= 6,171,390 ብር
-10% ቅድመ ክፍያ= 617,139 ብር
📌 ባለ ሁለት መኝታ-110 ካሬ
-ጠቅላላ ዋጋ= 8,380,900 ብር
-10% ቅድመ ክፍያ= 838,090 ብር
📌 ባለ ሶስት መኝታ-130 ካሬ
-ጠቅላላ ዋጋ= 9,904,700 ብር
-10% ቅድመ ክፍያ= 990,470 ብር
📌 ባለ አራት መኝታ- 211 ካሬ
-ጠቅላላ ዋጋ=16,076,090 ብር
-10% ቅድመ ክፍያ=1,607,609 ብር
🔔 በዚህ የመኖሪያ ህንፃ ላይ፡
💥የከርሰ-ምድር ውሀ
💥400 KVA ጄኔሬተር
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥2 ሊፍት
💥በቂ የተሰየመ የመኪና ማቆሚያ
💥መዋኛ ገንዳ
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥 ሬስቶራንት እና ካፌ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ ሰገነት እና ሌሎች መገልገያዎች።
🔔 የመረጡትን ቤት ተመላሽ በሚሆን 200,000 ብር ለ15 ቀን ማስያዝ ይችላሉ።
ለሳይት ጉብኝት እና ለቢሮ ቀጠሮ፡
📞 0923254077 ይደውሉልን!
ቴሌግራም- @E192087
አኮያ ፕሮፐርቲስ
ከነገ ለተዛመደ!

👍3
አሜሪካዊው ተዋናይ ቫል ኪልመር ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
ባትማንን ጨምሮ በአይረሴ ፊልሞች ባሳየው የትወና አቅም የሚታወሰው አሜሪካዊው የፊልም ሠው ቫልኪልመር ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።
የ65 ዓመቱ አዛውንት ከቀደምት ስራዎቹ ‘ቶፕ ገን’ እና ‘ባትማን ፎሬቨር’ የተሰኙት ይጠቀሱለታል።
የተዋናዩ የሞት መንስኤ በሳምባ ምች እንደሆነ ሴት ልጁ የገለፀች ሲሆን ከ11ዓመታት በፊት 2014 በጉሮሮ ካንሰር ህመም ተጠቅቶ እንዳገገመ በተጨማሪነት ገልፃለች።

👍24❤6😭4
🇪🇹ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የውጪ ባንኮች አምስት ቢሊዮን ብር ዝቅተኛ ካፒታል ሟሟላት እንደሚኖርባቸው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣው አዲስ መመሪያ ጥብቅ ቅደመ ሁኔታዎችን ያስቀመጠ ነው ተብሏል።
መመሪያው በባንኩ ዘርፍ የውጭ ሀገራት ተሳትፎን የውጭ ባንክ ተቀጥላ፣ የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ እና የእንደራሴ ቢሮ ብሎ የሚከፍል ሲሆን ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት የወንጀል እና የታክስ ማጣራትን ጨምሮ ጥብቅ ምርምራ ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው አስቀምጧል።
የውጭ ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ ብቻ ለማስቀመጥ እና ለመጠቀም ይገደዳሉ። ክፍያን በተመለከተ ከውጭ የሚገቡ ባንኮች ለምርመራ 200 ሺህ፣ ለፈቃድ 400 ሺህ እና ለእድሳት 400 ሺህ ብር መክፈል አለባቸው።
መመሪያው የሀገር ውስጥ ባንኮች ካፒታላቸውን መጨመር፣ የመረጃ አጠቃቀም ሕጋቸውን ከሀገሪቱ ጋር ማስማማት እና በቦርዶቻቸው ውስጥ የፆታ ብዝሃነትን ማረጋገጥ ጨምሮ ደረጃቻውን ከፍ እንዲያደርጉ ደንግጓል።

👍28😁12❤6🔥2
ባንኮች እስከ ምሽት 3፡30 ሰዓት ድረስ ክፍት እንዲሆኑ የሚያስገድደዉ ደንብ ከባንኮች አሰራር ጋር የማይጣጣም ነዉ ሲል የባንኮች ማህበር አስታወቀ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣው ባንኮች እስከ ምሽት 3:30 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ ከባንኮች አሠራር ጋር የማይጣጣም መሆኑን ማህበሩ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጿል፡፡
ባንኮች በዘመናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አማካይነት የተለያዩ የባንክ አገልግሎቶችን ለደንበኞቻቸው በቀላሉ ማቅረብ እየቻሉ በመሆኑ፣ የምሽት አገልግሎት አላስፈላጊና አግባብነት የሌለው መሆኑን የባንኮች ማህበር አስታዉቋል።
የባንኮች ማህበር ዋና ጸሀፊ አቶ ደምሰው ሞገስ እንደሚገልጹት፣ደንበኞች በፖስ ወይም ኤቴኤም ማሽኖች፣ በተንቀሳቃሽ ስልክ የባንክ መትግበሪያዎችና በኢንተርኔት ባንኪንግ አማካይነት የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት ስለሚችሉ ባንኮች እስከ ምሽት ክፍት ሆነው መቆየት አለባቸዉ የሚለዉ አስገዳጅ መመሪያ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ማህበሩ በፌዴራል መንግሥት ሥር ያሉ ተቋማትን የከተማ አስተዳደር በመመሪያ እንዲያስተዳድር የተሰጠው ሥልጣን አግባብ እንዳልሆነና ይህ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስተያየት መጠየቅ እንደነበረበት ይገልጻሉ።
በተለይም ይህ መመሪያ የባንኮችን የስራ ባህሪ ያላገናዘበና ለባንኮችም ሆነ ለደንበኞች ደህንነት አስጊ ሊሆን የሚችል መሆኑን የገለጹት ዋና ጸሃፊው አቶ ደምሰው በምሽት የሚሰጥ የባንክ አገልግሎት ለዘረፋና ለሌሎች የደህንነት ስጋቶች ሊያጋልጥ እንደሚችል ተናግረዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ደምብ 185/2017 የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ምሽት 4 ሰዓት ድረስ በመንገድ ዳር የሚገኙ የንግድ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ደግሞ ምሽት 3:30 ሰዓት ድረስ እንዲቆዩ የሚያስገድድ ደምብ ከየካቲት 29 ጀምሮ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወሳል ሲል መነኸሪያ ሬዲዮ ነው የዘገበው።

👍50❤3🔥2😭1
በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በኢትዮጵያ 43 ጋዜጠኞች ለእገታ እና እስር መዳረጋቸውን ሪፖርት አመለከተ!
የጋዜጠኞች ደህንነት ግምገማ በማካሄድ የሚታወቀው አለም አቀፉ የሚዲያ ድጋፍ ተቋም ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 ብቻ 43 ጋዜጠኞች ለእገታ እና እስር መዳረጋቸውን አስታወቀ። ሪፖርቱ ጋዜጠኞች ከመንግስት እና መንግስትዊ ካልሆኑ አካላት ማስፈራሪያ፣ እስር እና እንግልትን ጨምሮ ለበርካታ ጫናዎች ተጋላጭ መሆናቸውን አመላክቷል።
ከ60 ጋዜጠኞች ጋር በተደረገ ቃለ መጠይቅ እና በሰነድ በተመዘገቡ ጉዳዮች ላይ የተመሠረተው ሪፖርቱ፣ በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች ያሉ ጋዜጠኞች በተለይም በ አማራ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከፍተኛ አደጋ እንደሚገጥሟቸው አረጋግጧል።
በሪፖርቱ መሠረትም “የታጠቁ ቡድኖች ጋዜጠኞችን የቤዛ ክፍያ ለመቀበል ወይም ስለግጭቶች የሚወጡትን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቁሳቁሶቻቸውን ለመወሰድ በማሰብ በዘፈቀደ አስረዋል።በሌላ በኩል የመንግስት ባለሥልጣናት ደግሞ "ብሔራዊ ደህንነት እና ብሔራዊ ጥቅም" በሚል ሰበስ ጋዜጠኞች እንዲታሰሩ ማድረጋቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል።
Via AS

👍11❤1
YeneTube
Photo
አዲስ የገቡት የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ከሌሎች አውቶብሶች የዋጋ ልዩነት እንደማይኖራቸው ተገለጸ
የወረቀት ቲኬትን በማስቀረት የክፍያ ስርዓቱን ሙሉ ለሙሉ በቴክኖሎጂ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተብሏል
በተያዘው ሳምንት 100 የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በትናንትናው ዕለት ሥራ መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማስታወቁ ይታወሳል።
ይህም የትራንስፖርት ችግሩን ከመፍታትና ከአየር ብክለት ጋር ተያይዞ ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሄ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡
አሐዱም "አሁን ወደ ሥራ የገቡት እነዚህ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ቻርጅ ለማድረግ የሚያችል መሠረተ ልማት እንዲሁም ከክፍያ ጋር ተያይዞ ልዩነት ይኖራቸዋል ወይ?" ሲል ጠይቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አካሉ አሰፋ በሰጡት ምላሽ፤ አውቶብሶቹ በአንድ ጊዜ ቻርጅ ለ3 ቀን መጠቀም እንደሚያስችሉ የተናገሩ ሲሆን፤ ከክፍያ ጋር ተያይዞም ከሌሎች አዉቶብሶች ልዩነት እንደሌለው ተናግረዋል፡፡
ከመለዋወጫ ጋር ተያይዞም የኤሌትሪክ አውቶብሶች ብዙ የጥገና ሂደት የማያስፈልጋቸው በመሆኑ ከመደበኛ አውቶብሶች የሚለዩ ናቸው ብለዋል፡፡
"ስለሆነም ከረዥም ዓመት በኋላ ባትሪ ሊጠይቅ ይችላል" ሲሉ ገልፀው፤ የጥገና ሂደቱ አሳሳቢ አለመሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ሌሎች ተሸከርካሪዎችም ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲቀየሩ በእቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የአውቶብስ አገልግሎት ችግር ሆኖበት የቆየውን የፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም ይፈታል ተብሎ እንደታመነበትም ተናግረዋል።
በተያያዘ በከተማዋ የሚገኙ ሁሉንም የአውቶቡስ አገልግሎቶች የክፍያ ስርዓት በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ እየተሰራበት እንደሚገኝ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አካሉ አሰፋ አስታውቀዋል።
የአውቶቡስ አገልግሎቱ የክፍያ ስርዓት የዘመነ ባለመሆኑ ጊዜን ከመጠቀምና ሀብትን በአግባቡ ከመሰብሰብ አኳያ ትልቅ ተፅዕኖ እንደነበረበት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ "አዲስ የገቡትን 100 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ዘመናዊ አውቶቡሶችን ጨምሮ በአጠቃላይ ድርጅቱ የሚጠቀምባቸው የከተማዋ አዉቶብሶች በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓት እንዲያገለግሉ ይደረጋል" ብለዋል።
ወደ ሥራ እንዲሰማሩ የተደረጉት የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ መሆናቸውን የገለጹም ሲሆን፤ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓት እንዲሰሩ ተደርገው የተሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በዚህ ቴክኖሎጂ መሠረትም የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ የሚፈፅም ተሳፋሪ ካርድ መግዛት እንደሚጠበቅበት ጠቁመው፤ "በካርዱ ብቻ ክፍያ የሚፈፅም ይሆናል" ብለዋል።
አክለውም ወደፊት የወረቀት ቲኬቱ እየቀረ እንደሚሄድ የገለጹ ሲሆን፤ ካርዱን መግዛት ለማይችሉ እንዲሁም አሠራሩ በሰዎች ዘንድ በደንብ እስኪለመድ ድረስ ቲኬት በመቁረጥ እንደሚገለገሉ ተናግረዋል።

👍27❤5
በአማራ ክልል ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎች ተናገሩ
በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎችና የህክምና ባለሙያዎች ተናገሩ።
ራስን ለማጥፋት የአዕመሮ ህመምና ቅፅበታዊ አጋጣሚዎች ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጧል። በባሕር ዳር ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ባለፉት ሰባት ወራት ብቻ 156 ከራስ ማጥፋት ጋር በተያያዘ ወደ ህክና የመጡ ሰዎች መኖራቸውን አንድ የህክምና ባለሙያ ለዶይቸቨለ ተናግረዋል።
በፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ጓዴ ተዋበ ከአዲሱ ዓመት መግቢያ ጀምሮ ራስን ከማጥፋት ጋር በተያያዘ ጉዳተኞች ወደ ሆስፒታሉ መምጣታቸውን ገልጸውልናል። ከታካሚዎቹ መካክልም ብዙዎቹ ከተጎዱ በኋላ ወደ ተቋሙ በመድረሳቸው ሕይወታቸው ያለፈ መኖሩን አመልክተዋል።
በወራቤ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአዕምሮ ህክምና ስፔሽያሊስት ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው በበኩላቸው ራስን ለማጥፋት የሚያስችሉ መነሻ ምክንያቶች በርካታ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ዋነኞቹ ድብርትና ቅፅበታዊ ሁኔታዎች የሚፈጥሩት ሁኔታ እንደሆኑ ተናግረዋል።
Via DW Amharic

👍23😭23❤3👎3🔥1