እግድ
የፌደራል መንግስቱ በመቀሌ የሚገኘውን ኤፍ ኤም 104.4 የባንክ አካውንት ማገዱን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ሰዎች ገልፀዋል።
@Yenetube @Fikerassefa

👍8😁2❤1👎1
🌍 የአፍሪካ ሀገራት የጥቁር ባህር የእህል ስምምነት በድጋሚ እንዲጀመር ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው ሲሉ አልጄሪያዊው ባለሙያ ተናገሩ
🗣 "የአፍሪካ አህጉር እርምጃውን በጉጉት እየጠበቀ ነው፤ በተለይም የምግብ እጥረት የገጠማቸው ደቡባዊ የአህጉሪቱ ሀገራት። ይህ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር እና የእህል ፍላጎቶችን ለመሸፈን ጥሩ አጋጣሚ ነው" ሲሉ በአልጄሪያ ፈርሃት አባስ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ፋሬስ ሃባቼ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
በሩሲያ የእህል ምርት ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ማንሳት ሩሲያ የአፍሪካ ቀዳሚ ምግብ አቅራቢ መሆኗን እንደሚያጠናክር ያነሱት ፕሮፌሰሩ፤ እ.አ.አ 2024 ሩሲያ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የለገሰችውን 200 ሺህ ቶን እህል አስታውሰዋል።
የፑቲን እና ትራምፕን ንግግር ተከትሎ ሩሲያ እና አሜሪካ የጥቁር ባህር ስምምነትን በድጋሚ ለመጀመር ተስማምተዋል። ስምምነቱ በሩሲያ የግብርና ባንክ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ጨምሮ የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸው ላይ የተንጠለጠለ ነው።

👍18❤2
አስገራሚ ዜና
ሶማሌላንድ ለአሜሪካ የጦር ሰፈር ለመስጠት እና በምላሹ የሀገርነት እውቅና ለማግኘት ማቀዷን የሰሙት የሶማሊያ መሪዎች እነሱ ደሞ የተሻለ ያሉትን ሀሳብ ለአሜሪካ በደብዳቤ ልከዋል፡፡ አሜሪካ ሁሉንም የሶማሊያ ወደቦች የአየር ማረፊያዎች ለብቻዋ ያለ ምንም ተቀናቃኝ መቆጣጠር እንድትችል ጥያቄ ማቅረባቸውን ሮየተርስ ዘግቧል፡፡
ሶማሊላንድ በበኩሏ "አሜሪካ የሚጠቅማትን ታውቃለች" የሚል አጭር ምላሽ ለሶማሊያ አመራሮች ሰጥታለች።
Via:- አዩዘሀበሻ

😁63👍19❤7😭7
🇿🇦 የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የውጭ የስለላ ተቋም ለማቋቋም የሚያስችል የሕግ ማሻሻያ ፈረሙ
የተሻሻለ ቁጥጥርና የመንግሥት የደህንነት ኤጀንሲን መሻር ጨምሮ የሕግ ማሻሻያው በደቡብ አፍሪካ የስለላ አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል።
የተሻረው ኤጀንሲ በውጭ መረጃ አገልግሎት እና የሀገር ውስጥ መረጃ ኤጀንሲ እንደሚተካም በመግለጫው ተጠቅሷል። ለሀገር ውስጥ እና ውጭ ስለላ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ መረጃ አካዳሚ እና የመረጃ ስልጠና ኢኒስቲትዩት በድጋሚ እንደሚቋቋሙም ጽ/ቤቱ ጨምሮ ገልጿል።

👍14
🇪🇹 ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የባሕረኞች ማሠልጠኛ አካዳሚ ልትከፍት ነው
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የማሰልጠኛ አካዳሚውን ለመክፈት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋር ተፈራርሟል።
አካዳሚው ከባቦጋያ ሎጅስቲክሰ እና ማሪታይም አካዳሚ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ማሪታይም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ቀጥሎ ለሀገሪቱ ሶስተኛው ማሰልጠኛ እንደሚሆን ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ኢትዮጵያ በ2022 በሎጅስቲክስ አፈፃፀም ከአፍሪካ ቀዳሚ እንድትሆን ለማድረግ እንዲሁም ባሕረኞችን አሠልጥኖ ለዓለም ገበያ በማቅረብ ከመጀመሪያዎቹ አምስት የዓለም ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ እየሠራ እንደሚገኝ በማህበራዊ ትሥሥር ገፁ አስታውቋል።

👍43❤5😁5🔥4⚡1
በማይናማር የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ1,600 በላይ ደርሷል ከ3,400 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
😭20👍6
ጨረቃ ዛሬ በመታየቷ የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ ይከበራል
የሸዋል ወር ጨረቃ ዛሬ ቅዳሜ በመታየቷ 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ እሁድ መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚከበር ተገልጿል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ 1 ሺህ 446ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አስተምኅሮቱን በመተግበር ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

👍36😭36😁7
Boostgram Promo ይጠቀሙ - ተከታዮችዎን በአጭር ጊዜ ይጨምሩ!
ጀማሪ ኢንፍሉዌንሰር ከሆኑ
ተከታዮችን በፍጥነት ማሳደግ ከፈለጉ
ተጽዕኖዎን ለማሳደግ ከፈለጉ
Boostgram Promo መፍትሄው ነው!
ከሌሎች ጀማሪዎች ልዩ ይሁኑ - የማህበራዊ ሚዲያ ተከታታዮችዎን በቀላሉ ያሳድጉ!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5❤2
Forwarded from YeneTube
አኮያ ፕሮፐርቲስ
🔔 ከፒያሳ በቅርብ ርቀት ላይ ሰሜን ማዘገጃ ሳሬም ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ሳይታችን ላይ የኢድ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የሆነ ከ 5%-13% የሚደርስ ቅናሽ ስናደርግ በታላቅ ደስታ ነው ።
🔔 በካሬ 80,000 ብር ሲሸጥ የነበረውን የኢድ በአልን አስመልክተን ለ 3 ቀን ብቻ በካሬ 76,000 ብር! ከ 10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
🔔 2B+G+18 በሆነው አፓርትመንታች ላይ የእንጦጦ ንፁህ እና ነፋሻማ አየር እየሳቡ የተረጋጋ ህይወት ይኖራሉ!
🔔 ከ ባለ 1 እስከ ባለ 4 መኝት በተለያየ ካሬ አማራጭ
📌 ባለ አንድ መኝታ- 81 ካሬ
-ጠቅላላ ዋጋ= 6,171,390 ብር
-10% ቅድመ ክፍያ= 617,139 ብር
📌 ባለ ሁለት መኝታ-110 ካሬ
-ጠቅላላ ዋጋ= 8,380,900 ብር
-10% ቅድመ ክፍያ= 838,090 ብር
📌 ባለ ሶስት መኝታ-130 ካሬ
-ጠቅላላ ዋጋ= 9,904,700 ብር
-10% ቅድመ ክፍያ= 990,470 ብር
📌 ባለ አራት መኝታ- 211 ካሬ
-ጠቅላላ ዋጋ=16,076,090 ብር
-10% ቅድመ ክፍያ=1,607,609 ብር
🔔 በዚህ የመኖሪያ ህንፃ ላይ፡
💥የከርሰ-ምድር ውሀ
💥400 KVA ጄኔሬተር
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥2 ሊፍት
💥በቂ የተሰየመ የመኪና ማቆሚያ
💥መዋኛ ገንዳ
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥 ሬስቶራንት እና ካፌ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ ሰገነት እና ሌሎች መገልገያዎች።
🔔 የመረጡትን ቤት ተመላሽ በሚሆን 200,000 ብር ለ15 ቀን ማስያዝ ይችላሉ።
ለሳይት ጉብኝት እና ለቢሮ ቀጠሮ፡
📞 0923254077 ይደውሉልን!
ቴሌግራም- @E192087
አኮያ ፕሮፐርቲስ
ከነገ ለተዛመደ!

❤4👍4👎1
የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ማህበር ስምንት ሺህ ታካሚዎች ህክምና ለማድረግ ወረፋ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ አስታወቀ
የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ማህበር በ2024 በጀት ዓመት ከ12 ሺህ በላይ የተመላላሽ የልብ ሕክምና ክትትል እና 669 ለሚጠጉ ታካሚዎች ደግሞ የህክምና አገልግሎት መስጠቱን አስታውቋል።
ለታካሚዎች የሰጠው አገልግሎት በገንዘብ ሲተመን ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ የልብ ቀዶ ሕክምና እና በ ደም ስር በኩል የሚሰጥ የህክምና አገልግሎት መሆኑን በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ዳዊት እሸቱ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
ማዕከሉ ምንም እንኳን ነጻ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ቢሆንም አንድ ቀዶ ህክምና ለመስራት ተቋሙ የሚያወጣው ወጪ ከ100 ሺህ ብር በላይ እንደሚሆን ተጠቁሟል። አንድ ታካሚ መጀመሪያ ከታየበት ቀን አንስቶ ቀዶ ህክምና እስከሚሰራበት ቀን ድረስ ለዓመታት ወረፋ ሊጠብቅ እንደሚችል ተጠቁሟል።
በተጨማሪም በተያዘው በ2025 ዓመት ከ17,000 በላይ ለሚሆኑ ታካሚዎች አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም 352 የልብ ቀዶ ህክምና እና 334 በደም ስር በኩል የሚሰጥ ህክምና ለመስጠት በዕቅድ መያዙን ተጠቁሟል።በአሁን ሰዓት አጠቃላይ ታካሚዎች ቁጥር 20 ሺህ ሲሆን ወረፋ የሚጠብቁ ታካሚዎች ደግሞ ስምንት ሺህ መሆናቸውን አንስተዋል። ይሁን እና ተቋሙ ለህክምናው የሚያስፈልጉ እቃዎችን ለማሟላት ችግር እንደሆነባቸው ገልጸዋል። በተለይም መድሃኒቶች በበቂ ሁኔታ አለመኖራቸው በታቀደው ልክ ህክምና መስጠት እንዳይቻል ትልቅ ተግዳሮት መሆኑን ዶክተር ዳዊት እሸቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

👍15❤2🔥1
"[ሕወሓት] ምዕራብ ትግራይ [ወልቃይት] ሲባል ለሰሊጥ መሬቱ እንጂ ስለ ተፈናቃዮቹ ተጨንቆ አያውቅም" - ጌታቸው ረዳ
አቶ ጌታቸው ረዳ በትግርኛ ቋንቋ ያስተላለፉት መልእክት ትርጉም
"ባለፉት ሃያ ቀናት በትግራይ የሚታየው ፖለቲካዊ ትርምስ ስልጣን ወይም የሞት ሽረት ብሎ የተነሳው ኋላቀር ቡድን ላለፉት ሁለት ዓመታት የተበተበው ሴራ የመጨረሻ ጡዘት/ምዕራፍ መድረሱን ያመላክታል::
ህግና ስርዓት ያስከብራሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸው አንዳንድ የተሻለ ታሪክ የነበራቸው ዝነኛ ሰው ሳይቀሩ የሥርዓቱ ጭቃ ውስጥ ገብተው የሚያቦኩበት ከፍታ ላይ ነው የተደረሰው::
ከማህተም መልቀም ዘመቻ በኋላ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን በጉልበት የተቆጣጠረው ኃይል እስካሁን ያከናወናቸው ነገሮች ሁለት ብቻ ናቸው።
በመጀመሪያ ተቆጣጥሬያቸዋለሁ በሚላቸው ዋና ዋና ከተሞች ደጋፊዎቼ ለሚላቸው መሬት ማከፋፈል እና ለገቢ ምንጩ ሽያጭ የሚውል ሰፋፊ መሬት መውረር ይጠቀሳል።
ዋነኛ ትኩረቱም በመቐሌ/ሓድነት፣ በሽሬ/በታች ቆራሮ፣ በአክሱም/፣ በማይጨው እና በአዲግራት እና በአካባቢው ተጀምሮ ከምእራብ ትግራይበስተቀር በሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች ይቀጥላል።
ያገኘውን መሬት ለመከፋፈልና ለመሸጥ እንጂ የጠፋውን ለመመለስ ምንም ፍላጎት ወይም ተነሳሽነት የሌለው ኃይል በመሆኑ ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት ለመመለስና የትግራይን ሉዓላዊ መሬት ለማስመለስ ከመፈክር ያለፈ ጥያቄ እንኳን ሲያቀርብ አልታየም። ስለሆነም መላው የትግራይ ወጣቶች መሬታችሁን ከሽፍቶች ጠብቁ።
በማህተም ቀሚዎች የተወሰኑ ውሳኔዎች ህጋዊ ተቀባይነትን ተፈጻሚነት እንደማይኖራቸው በመገንዘብ በመሬት ወረራ እንድትሳተፉ በመጋበዝ ላይ የምትገኙ ባለሀብቶችም ገንዘባችሁ ቁምነገር ላይ መዋሉን አረጋግጡ።
ሁለተኛው የዚህ ኋላቀር ቡድን ትኩረት አዲስ አበባ እየተመላለሰ ስልጣን ይገባኛልና አጽድቁልኝ እያለ ደጅ መጥናት ነው።
'ሰላም ፈላጊዎች ነን፤ የፕሪቶሪያውን ውል እናስፈጽማለን፤ ብቻ ወንበር እንረከብ' በማለት እየተማለደ ይገኛል።
ፕሬዚዳንት መሾም ስልጣኑ እንዳልሆነ እየተቀበለ ነገር ግን እነእገሌ ለፕሬዝዳንትነት አጭቻለሁ እያለ፤ እጩዎች የሚላቸውንም በየሦስት ቀኑ እየቀያየረ ዕድሉን እየሞከረ ነው። አሁንም ቢሆን ስለተፈናቃዮችና ምእራብ ትግራይ ተሳስቶም የሚያነሳበት አጋጣሚ የለም፤ አጀንዳውም አይደለም።
ምዕራብ ትግራይ ሲባል የሰሊጥ መሬት እንጂ የተፈናቀለው መከራና ስቃይ ላይ የሚገኘው ህዝብ አይታየውም::
ይህ ቡድን እና አሽከሮቹ በህልማቸውም ሆነ በእውናቸው የማይፋቷቸው ሁለት አጀንዳዎች ካሉ መሬት እና ስልጣን ብቻ ናቸው።
የመላው ህዝባችን ሰላም፣ የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ተስፋ እና የትግራይ ወጣቶችን መጻኢ ህልምና ነገን ቀምተው ሊፋቱት ያልቻሉትን አመላቸው ለማርካት ወደሌላ ዙር የጥፋት አዙሪት ሊያስገቡን ቋምጠዋል"ብሏል።

👍41👎5❤3🔥1
YeneTube
Photo
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ግሪንላንድ ከዴንማርክ ጋር ያላትን ግንኙነት እንድታቋርጥ አሳሰቡ
አወዛጋቢውን የአሜሪካ ግሪንላንድን የመጠቅለል ግስጋሴ ሲቀጥል የዩናይትድ ስቴይስ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ደሴቲቱ ከዴንማርክ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት እንድታቋርጥ እና በምትኩ ከዋሽንግተን ጋር አጋር እንድትሆን ጥሪ አቅርበዋል። ዴንማርክ በግሪንላንድ ኢንቨስት እያደረገች ነው ሲሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በሰሜናዊ ግሪንላንድ የሚገኘውን የርቀት የዩናይትድ ስቴትስ ፒቱፊክ የጠፈር ጣቢያን ባደረጉት አጭር ጉብኝት ቫንስ እንዳሉት "በምድር ላይ ያለች ብቸኛዋ የግሪንላንድ ሉዓላዊነት እና ደህንነታቸውን የምታከብር ሀገር አሜሪካ ነች" ብለዋል።
ዴንማርክ "በግሪንላንድ ህዝብ ላይ ኢንቨስት አድርጋችኋል እናም በዚህ አስደናቂ ውብ መሬት ደህንነት ላይ ኢንቨስት አድርጋችኋል" ሲሉም ለዴንማርክ ተናግረዋልል። ቫንስ ተጨማሪ የህዝብ ቦታዎችን ቢጎበኝ ተቃውሞ እንደሚገጥማቸው ሪፖርቶች ከወጡ በኋላ የመጀመሪያውን የጉዞ እቅድ ሰርዘዋል። ቫንስ ከዩናይትድ ስቴትስ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ማይክ ዋልትዝ እና የኢነርጂ ፀሀፊ ክሪስ ራይት ጋር በመሆን በደሴቲቱ ላይ ያለውን የአሜሪካ ሰራዊት ቆይታ ለመጨመር ፈጣን እቅድ ዋሽንግተን የላትም ነገር ግን የባህር ሃይል መርከቦችን እና ወታደራዊ የበረዶ መንሸራተቻዎችን ጨምሮ ተጨማሪ ሀብቶችን እንደሚመድቡ ተናግረዋል ።
19 ዲግሪ ሴልሺየስ ቅዝቃዜ ባለበት በግሪን ላንድ፣ የቫንስ ጉብኝት ለጥቂት ሰአታት ብቻ የቆየ ነበር።የግሪንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጄንስ ፍሬድሪክ ኒልሰን ጉብኝቱ “ለግሪንላንድ ሕዝብ አክብሮት እንደሌለው ያሳያል” ብለዋል። የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚቲ ፍሬድሪክሰን ሀገሯ የአርክቲክ መከላከያ ወጪዎችን በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳደገች በመግለጽ፣ አዳዲስ የስለላ ስርዓቶችን እና የረጅም ርቀት አውሮፕላኖችን እንዲሁም መርከቦችን ጨምሮ ማሰማራቷን በማንሳት የአሜሪካን አስተያየት ውድቅ አድርገዋል።"ለበርካታ አመታት ከአሜሪካውያን ጎን ለጎን ቆመናል" ስትል ተናግራለች። "ስለዚህ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዴንማርክን የሚያመለክቱበት ትክክለኛ መንገድ አይደለም" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሯ አክለዋል።

👍20❤3👎1👀1
ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሰጠ መግለጫ
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ በዛይሴ ወዘቃ፣ ፃናኦ ቀበሌ በግለሰብ ቤት ላይ በተፈፀመ የቤት ማቃጠል ጥቃት ቤት ንብረት መውደሙ እና የሁለት ህፃናት ህይወት ማለፉን ለማወቅ ችለናል፡፡
በዚህ አሰቃቂ ሕገወጥ ድርጊት ድርጅታችን ኢዜማ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ የክልሉ መንግስት ድርጊቱን የፈፀሙትን አካላት ሕጋዊውን መንገድ ተከትሎ እንዲያጣራ እና በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን ለፍርድ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን፡፡ከዚህ አሳፋሪ እና አስነዋሪ ተግባር ጀርባ ያለ የትኛውም አካል ቢሆን በጋራ ሊወገዝ የሚገባው መሆኑንም ኢዜማ በፅኑ ያምናል።
ይህን በጭካኔ የተሞላ አስነዋሪ ድርጊት ተከትሎ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያዎች እና የመንግስት አካላት የድርጅታችንን ስም አላግባብ እያነሱ መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህን መሰል ስም ማጥፋት በቸልታ የማናየው መሆኑ እንዳለ ሆኖ ኢዜማ በእንደዚህ አይነት ሕገወጥ ተግባር ውስጥ የማይገኝ ብሎም ከቆመለት የሰላማዊ ትግል መርሆ ውጪ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ሳናነሳ የማናልፈው ጉዳይ ቢኖር ወንጀል የፈፀሙ አካላትን ለፍርድ በማቅረብ ሂደት ውስጥ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ አይነት የፖለቲካ ልዩነትን መሰረት ያደረጉ ንፁሐንን ከአጥፊዎች ያለየ የጅምላ እስርና ህገወጥ አፈና እንዳይኖር የህግ አስከባሪ አካላትም ሕግና ሕግን ብቻ መሰረት አድርገው እንዲሰሩ በአፅንኦት ለማሳሰብ እንወዳለን ፡፡
ስለሆነም ይህን አሰቃቂ ወንጀል የፈፀሙ አካላት በአስቸኳይ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ የፀጥታ አካላትም የደረሱበትን ግኝት ደረጃ በደረጃ ለሕብረተሰቡ እንዲያሳውቁ እየጠየቅን ኢዜማም ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ እንደሚከታተል ለማሳወቅ እንወዳለን።
በተፈፀመው ሕገወጥ እና በጭካኔ ለተሞላ አስነዋሪ ተግባር ቤት ንብረታቸውን እና ህፃናት ልጆቻቸውን ላጡ ቤተሰብ፣ ወዳጅ እና ዘመድ መፅናናትን እንመኛለን፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
መጋቢት 22/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

👍25😁4❤3
አደይ አበባ ስታዲየምን ለማጠናቀቅ የ18 ቢሊዮን ብር ውል ተገባ!
በአዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘውን አደይ አበባ ስቴዲየም ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 18 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው ተገልጿል::አሁን የአደይ አበባ ስቴዲየም ቀሪ ስራዎችን ከሁለት አመት ባነሰ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ተብሏል።
የስታዲየሙን የማጠናቀቂያ ሥራዎች ለማከናወን 18 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር መገባቱን የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚንስቴር አስታውቋል።ግንባታውን ለማጠናቀቅ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ከቻይናው ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራርሟል።
የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ የአሁኑ ስምምነት የስቴዲየሙን ምዕራፍ ሁለት ደረጃ ሁለት እና ሦስት ስራዎችን ለማጠናቀቅ የተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።ባለፉት 7 ወራት ግንባታውን ለማፋጠን ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት በተገኝ የ57 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ያስታወሱት ሚንስትሯ ለቀሪው ስራ 18 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ውል መያዙን አሳውቀዋል።
ከኤች ኤም ኢንጂነሪግ የስቴዲየሙ ግንባታ አማካሪ መሰለ ሀይሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው የምዕራፍ ሁለት ደረጃ ሁለት እና ሦስት ስራዎች የጣሪያ ገጠማ እና የውስጥ ስራዎችን እንደሚይዝ ተናግረዋል።የካፍ እና የፊፋን ደረጃ ባሟላ መልኩ እየተገነባ መሆኑን ያሳወቁት አማካሪው ግንባታው ከሁለት አመት ባነሰ ጊዜ እንደሚጠናቀቅም ተናግረዋል።
በተጨማሪም የስቴዲየሙ የመያዝ አቅም 60 ሺህ መሆኑ መሰለ ሀይሌ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።የአደይ አበባ ስታዲየም ግንባታው በ2008 ዓ.ም መጀመሩ የሚታወስ ነው::
Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa

👎54👍39😁22😭10❤2👀2
“በዱባይ ወንጀል ሠርተው በኢትዮጵያ የተሸሸጉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እየተከናወነ ይገኛል” ሲል ፌደራል ፖሊስ አሳወቀ
በዱባይ ወንጀል ሠርተው በኢትዮጵያ የተሸሸጉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል አስታወቁ።
ኮሚሽነሩ ይህንን ያስታወቁት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የዱባይ ፖሊስ የምርመራ ቡድን ጋር በወንጀል ምርመራ ዙሪያ በተወያዩበት ወቅት ነው።
በዉይይቱ በሁለቱም ሀገራት ተፈላጊ የሆኑ ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ በመስጠት በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ስለሚቻልበት ሁኔታም መወያየታቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በዱባይ ወንጀል ሠርተው በኢትዮጵያ ተሸሸገው የነበሩ እና በቁጥጥር ስር ውለው ምርምራ እየተካሄደባቸው ናቸው የተባሉት ተጠርጣሪዎች ብዛትም ይሁን የወንጀሉ አይነት ፌደራል ፖሊስ በመረጃው ያለው ነገር የለም መባሉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።
በውይይቱም ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በጋራ የወንጀል ምርመራ ቡድን በማቋቋም እና የልምድ ልውውጥ በማድረግ ለመስራት መነጋገራቸውን መረጃው አመላክቷል።
Via አዲስ ስታንዳርድ

👍35😁2❤1🔥1
የክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የቆይታ ጊዜ የማራዘም ስልጣን፤ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው!
የፌደራል መንግስት በክልሎች የሚያቋቁመውን ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ዘመን፤ ለሁለት ጊዜ የማራዘም ስልጣን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ በነገው ዕለት ለፓርላማ ሊቀርብ ነው። የአዋጅ ማሻሻያው፤ የአፈ ጉባኤው ውሳኔ በፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ተቀባይነት ካላገኘ፤ ጊዜያዊ አስተዳደር በተቋቋመበት ክልል “በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ” “ምርጫ እንዲደረግ” ያስገድዳል።
ይህ የህግ ረቂቅ፤ የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ስርአት ለመደንገግ በ1995 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ የሚያሻሽል ነው። የአዋጅ ማሻሻያው በነገው የፓርላማ መደበኛ ስብሰባ የሚቀርበው፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የስልጣን ዘመን ለማራዘም “የህግ ማሻሻያ” እንደሚያስፈልግ ከተገለጸ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው።
በነባሩ አዋጅ ላይ የጊዜያዊ አስተዳደሩን የመቆያ ጊዜ “አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ” የማራዘም ስልጣን የተሰጠው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ነበር። በዚህ ድንጋጌ ትግበራ ሂደት ላይ “ባለፉት ዓመታት የተስተዋሉ ሁለት ችግሮች” እንዳሉ የአዋጅ ማሻሻያውን ለማብራራት የቀረበ ሰነድ ያስረዳል።የመጀመሪያው ችግር “የጊዜያዊ አስተዳደሩን ቆይታ ለማራዘም ውሳኔ የሚሰጠው የፌደሬሽን ምክር ቤት፤ በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ የሚሰበሰብ” ከመሆኑ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ማብራሪያው ይገልጻል።
Via Ethiopia Insider

😁31👍26❤5⚡2🔥1😭1
👍 ተከታዮችን በፍጥነት ማግኘት ይፈልጋሉ?
Boostgram Promo ይጠቀሙ - ተከታዮችዎን በአጭር ጊዜ ይጨምሩ!
Boostgram Promo መፍትሄው ነው!
👉 ዛሬውኑ ይሞክሩት: https://tttttt.me/boostgramPromoBot/boostgram
ከሌሎች ጀማሪዎች ልዩ ይሁኑ - የማህበራዊ ሚዲያ ተከታታዮችዎን በቀላሉ ያሳድጉ!
Boostgram Promo ይጠቀሙ - ተከታዮችዎን በአጭር ጊዜ ይጨምሩ!
ጀማሪ ኢንፍሉዌንሰር ከሆኑ
ተከታዮችን በፍጥነት ማሳደግ ከፈለጉ
ተጽዕኖዎን ለማሳደግ ከፈለጉ
Boostgram Promo መፍትሄው ነው!
👉 ዛሬውኑ ይሞክሩት: https://tttttt.me/boostgramPromoBot/boostgram
ከሌሎች ጀማሪዎች ልዩ ይሁኑ - የማህበራዊ ሚዲያ ተከታታዮችዎን በቀላሉ ያሳድጉ!
👍6❤3

👍10