በትግራይ ክልል ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች እስካሁን ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም ተባለ!
በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ የወደሙ እና ወደ ሥራ ያልተመለሱ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስዩም ሀጎስ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ምዕራብ ትግራይ በሌሎች ኃይሎች ቁጥጥር ሥር በመሆኑ ትምህርት ለማስጀመር እንዳልተቻለ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ እንደ እቅድ ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ ከታሰበው 2 ነጥብ 45 ሚሊየን ተማሪዎች ውስጥ እስካሁን ወደ ትምህርት መመለስ የተቻለው 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ያክል ተማሪዎችን ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከነዚህም ውስጥ ባለው ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡"በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ቢሞከርም፤ ባለው የምግብ አቅርቦት ችግር እና በሌሎችም ተደራራቢ ጫናዎች ምክንያት ታዳጊዎቹ ለልመና እና ለቀን ሥራ እየተዳረጉ በመሆኑ ጥረቱን አስቸጋሪ አድርጎታል" ብለዋል፡፡
"በመጠለያ ውስጥ ያለው የእርዳታ አቅርቦት የሚፈለገውን ያህል ባለመሆኑ ወላጆቻቸውም ሰርተው ልጆቻቸውን ማስተማር የሚችሉበት ሁኔታ ላይ ባለመሆናቸው፤ በተለይም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናት ምግብ ለማግኘት ወደ ልመና ይሰማራሉ" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አክለውም አሁን በክልሉ የሚስተዋለው ፖለቲካዊ ውጥረትም ለችግሩ መባባስ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡መንግሥትም ሆነ ረጂ ተቋማት እጃቸውን እንዲዘረጉ የጠየቁት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ፤ "እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱት ሕጻናት እንዲማሩ ለማድረግ መረባረብ የሕፃናቱን ነገ መስራት ነው" ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ግጭት ብሎም ሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋ በተከሰተባቸው ክልሎች በርካታ ሕጻናት እና ወጣቶች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸው የሚገለጽ ሲሆን፤ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚህ ዓመት እንደ ሀገር ከ7 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።
Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa

😭12👍7👀3❤1
የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት በቁጥጥር ስር ዋሉ!
የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር (ዶር) በጁባ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፓርቲያቸው የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የረጅም ጊዜ ተፎካካሪ የሆኑት ማቻር "20 ከባድ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች" በተሳተፉበት ኦፕሬሽን ከቤታቸው ተወስደዋል ሲል ፓርቲያቸው ኤስፒኤልኤም-አይኦ (SPLM-IO) አስታውቋል።
ፓርቲው የፀጥታ ኃላፊዎች "ኢ-ሕገመንግስታዊ ድርጊት" ፈጸመዋል ሲል ድርጊቱን አውግዟል። በተጨማሪም ሪክ ማቻር በቁጥጥር ስር የዋሉበት ምክንያት "ግልፅ አለመሆኑንም" ገልጿል።
በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮ እስሩ ሀገሪቷን ወደ አዲስ ግጭት እንዳያስገባ አስጠንቅቋል። የድርጅቱ ኃላፊ ኒኮላስ ሃይሶም መሪዎቹ ወደ ሰፊ ግጭት መመለስን ለማስወገድ ራሳቸውን መቆጣጠር እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገለጸው፤ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለኪር እና ለማቻር ታማኝ በሆኑ ኃይሎች መካከል ግጭት ተከስቷል። የተፈጠረው ውጥረትም እያየለ ባለበት ወቅት ኖርዌይ እና ጀርመን ኤምባሲዎቻቸውን ለጊዜው ዘግተዋል።
ካለፈው ወር ጀምሮ ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች ከእላኛው ናይል አካባቢ መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል ሲል የጀርመን ድምጽ ዘግቧል።

👍19👀4❤2
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአፍሪካ የመጀመሪያው ነው የተባለለትን የማስተር ካርድ የክፍያ ሥርዓት አስጀመረ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካርድ ክፍያ ሥርዓቱን አንድ ደረጃ ከፍ ያደርጋል የተባለለትና በኢንተርኔት ኦን ላይን መጠቀም የሚያስችል ቨርቿል ማስተር ካርድ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር ያቀረበው ማስተር ካርድ፤ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ የዓለም አቀፍ ዲጂታል ክፍያዎችን በቨርቹዋል ካርዶችን ለመጠቀም የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
ይህም የቨርቿዋል ቴክኖሎጂ ካርድ ወደ ሥራ ማስገባቱን በዛሬው ዕለት ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በሞባይል ባንኪንግ ቨርቹዋል ካርዱን ማግኘት እንደሚቻል ተነግሯልል።
ባንኩ ዓለም አቀፍ ግልጋሎት የሚያስገኝለትን ቨርቿል ካርድ ማስጀመሩ በተመለከተ ሀሳባቸውን የሰጡት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ፤ 85 በመቶ የሚሆነው ዜጋ የኦንላይን ባንኪንግ የሚጠቀምበት ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹ ሲሆን፤ "ለዲጂታል ኢትዮጵያ ዕውን መሆን ትልቅ እርምጃ የሚሆን ሥራ ነው" ብለዋል።
ከ40 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የባንኩ ደንበኞች አገልግሎቱን ለማስጀመር ከማስተር ካርድ ጋር የተሰራው ሥራ ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጥምረት ለመስራት ያደረገውን ሥራ ያደነቁት የማስተር ካርድ የአፍሪካ ፕሬዝዳንት ማርክ ኤሊየት በበኩላቸው፤ "በዛሬዉ ዕለት አዲስ ካርድ ሳይሆን እያስተዋወቅን ያለነው ለማህበረሰቡ የሚረዳ ቨርቹዋል ካርድ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ዲጂታል የክፍያ አማራጮችን በማቅረብ፣ ንግድ ባንክ እና ማስተር ካርድ በፋይናንሺያል አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ያለውን ክፍተት ለመቅረፍ፣ የላቀ ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎን ለማጎልበት እና የፋይናንስ አካታችነትን ለማጎልበት የታለመ መሆኑንም አንስተዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በ2025 የዲጂታል ኢትዮጵያን ለመመስረት እያደረገው ያለው ሥራ የሚበረታታ መሆኑን በማንሳት፤ "አካታች የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት ለመፍጠር ይረዳል" ብለዋል።ማስተር ካርድ በ200 ሀገራት ደንበኞችን በማፍራት የሚታወቅ ሲሆን፤ ዘላቂ ኢኮኖሚ ለመግንባት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

👍37❤6😁4👎2🔥1
የፋኖ ታጣቂዎች በሚፈልጓቸው የአውሮፓ ሀገሮችና አደራዳሪዎች አማካይነት ድርድር እንዲደረግ መንግሥት ‘ፈቃደኛ’ ነው ተባለ!
በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ታጣቂዎች በሚፈልጓቸው የአውሮፓ አገሮችና አደራዳሪዎች አማካይነት ድርድሮች እንዲደረጉ መንግሥት ‘ፈቃደኛ’ መሆኑን የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት አስታወቀ።የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ያየህይራድ በለጠ፣ ምክር ቤቱ ሁለት ዓመቱን ሊደፍን የተቃረበውን የአማራ ክልል ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁለቱም አካላት ወደ ድርድርና ውይይት እንዲመጡ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።
በዚህም በሁለቱም አካላት በኩል ለውይይትና ለድርድር “ፈቃደኛነት መታየቱን” ገልጸው "የፌደራል መንግሥት በየጊዜው ለሠላምና ለድርድር ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ዝግጁነቱን በተደጋጋሚ ገልጧል፤ በፋኖ ወገኖቻችን በኩልም በምናደርገው ግንኙንት ድርድርና ውይይት እንደማይጠሉ ነግረውናል" ብለዋል።አንደኛው ሌላኛውን ያለማመን አዝማሚያ ለውይይት የሚደረገውን ጥረት አስቸጋሪ እንዳደረገው ጠቅሰው አለመተማመኑን ለማስወገድ የፋኖ ታጣቂዎች በሚፈልጓቸው የአውሮፓ አገሮችና አደራዳሪዎች አማካይነት ድርድሮች እንዲደረጉ መንግሥት ‘ፈቃደኝነት’ ማሳየቱን ጠቁመዋል።
ይህን አስመልክቶ ከአብዛኛዎቹ የፋኖ ታጣቂዎች ጋር “ውይይቶችን እንዳደረጉ” የገለፁት አቶ ያየህይራድ፣ ከፋኖ አመራሮች ምላሽ በመጠበቅ ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል።የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት በክልሉ በሚንቀሳቀሱት የፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግሥት መካከል እየተካሄደ የሚገኘውን ጦርነት በውይይት እና በድርድር ለመቋጨት የአመቻችነት ሚናውን እንዲወጣ ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም መመስረቱ የሚታወስ ነው።
Via AS

👍65😁37👎12❤9🔥1
አየር መንገዱ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውሮፕላኖችን አገልግሎት ላይ ለማዋል ስምምነት ተፈራረመ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድና አርቸር አቪዬሽን በተለያዩ ዘርፎች በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸውን አየር መንገዱ አስታወቀ፡፡
ስምምነቱ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውሮፕላኖችን በአየር ትርንስፖርት አገልግሎት ላይ ለማዋልና በአርቸር ኤር የበረራ ፕሮግራም መሰረት በሌሊት የሚደረጉ የጭነት በረራ አገልግሎቶችን ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል፡፡
ዘመኑ የደረሰበትን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ከማስቻሉ ባለፈም ለአየር ንብረት ጥበቃ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል ብሏል፤ አየር መንገዱ፡፡

👍21😁17👎10😭8❤4👀3
ፋና ሚዲያ ምሽት 3 ሰዓት ላይ "የብርቱካን እዉነት" የሚል ፕሮግራም በቴሌቪዥን ጣቢያዉ ላይ እንደሚያሰራጭ አሳዉቋል።
ከሰሞኑ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ ቀርባ የነበረችዉ ብርቱካን ተመስገን ፕሮግራሟ ከተሰራጨ በኋላ ዉዝግብ አስነስቶ ጣቢያዉም ምላሽ ሰጥቶበት ነበር። በወቅቱ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ገጽ ላይ ተለጥፎ የነበረዉ የወጣቷ ታሪክን የሚዳስሰዉ ፕሮግራም ዉሉ ባልታወቀ ምክኒያት እንዲጠፋ ተደርጓል።
ብርቱካን በወቅቱ የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረችበት ወቅት "ታግቼ ነበር" ማለቷን ተከትሎም ዩኒቨርስቲው ማስተባበያ እንደሰጠ ዳጉ ጆርናል መረጃዉን ማድረሱ ይታወሳል።
ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት መነጋገሪያ የነበረዉ የብርቱካን ተመስገንን ጉዳይ ይሁን ሌላ በዉል ሳያሳዉቅ ግን መንግስታዊዉ ሚዲያ ፋና "የብርቱካን እዉነት" የሚል ፕሮግራሙ ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት ይሰራጫል ብሏል።
@Yenetube @Fikerassefa

👎115👍44😁15❤2
የአዲስ አበባ ባንኮች እስከ ምሽት 3 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ ተጠየቀ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ ባንኮች እስከ ምሽት 3 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ ለብሔራዊ ባንክ ጥያቄ አቅርቧል።
የንግድ ቢሮው እንዳለዉ እንደማንኛውም አገልግሎት ሰጪ የንግድ ተቋማት ዋና ዋና መንገድ ላይ የሚገኙ ባንኮች እስከ ምሽቱ 3 : 30 ድረስ አገልግሎት የሚሰጡበት አሰራር እንዲዘረጋ የትብብር ጥያቄ የቀረበዉ።
ዋና ዋና መንገድ ላይ የሚገኙ የንግድ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3:30 ድረስ እንዲሰሩ ከተወሰነ ብዙ ባንኮችም በዚሁ መስመር ላይ የሚገኙ በመሆኑ የአገልግሎት ሰዓታቸውን ማራዘም ለንግድ እንቅስቃሴ እንዲሳለጥ ያደርጋል ያደርጋል መባሉን ቅዳሜ ገበያ ሰምታለች።
ይህን ተከትሎ ቢሮው በቀጥታ ባንኮችን የማዘዝ ስልጣን ስለሌለው የትብብር ጥያቄው በደብዳቤ ለማዕከላዊ ባንኩ ማቅረቡን ነዉ ለመረዳት የተቻለዉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ደምብ 185/2017 የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ምሽት 4 ሰዓት ድረስ በመንገድ ዳር የሚገኙ የንግድ ተቋማት ደግሞ ምሽት 3:30 ድረስ እንዲቆዩ የሚያስገድድ ደምብ ከመጋቢት 10 ጀምሮ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል።
《ቅዳሜገበያ》
@YeneTube @Fikerassefa

👍96👎44😁23❤3
🇪🇹 የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የሆነው “ፊቼ ጫምባላላ” በሀዋሳ ጉዱማሌ በመከበር ላይ ይገኛል
በዚህ የአደባባይ በዓል ላይ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ከብሄሩ ተወላጆች ጋር ታድመዋል።
የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ፍቼ ጨምባላላ” ከአስር ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ እና ባህል ድርጅት “ዩኔስኮ” የሰው ልጆች ወካይ የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወስ ነው።

👍10❤5👎1
ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ ጋር በስልክ ማውራታቸው ተገለጸ!
ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሮብዮ ጋር በስልክ ማውራታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስ ትላንት መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ማርክ ሩብዮ እና ጠ/ሚኒስትር አብይ በስልክ የተወያየቱ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ዙሪያ መሆኑን ቃል አቀባዩ አመላክተዋል።ቅድሚያ የሰጧቸው ተብለው በቃል አቀባዩ ከተዘረዘሩት ጉዳዮች መካከልም የአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት አንዱ መሆኑን አስታውቀዋል።
ቃል አቀባዩ በተጨማሪም መሪዎቹ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ተወያይተዋል ብለዋል።ለኢትዮጵያ ሰላም እና ብልጽግን አሜሪካ ድጋፏን እንደምታጠናክር ማርክ ሩብዮ ለጠ/ሚኒስትር አብይ አረጋግጠውላቸዋል ሲሉ ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።
የትራምፕ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ በከፍተኛ አመራር ደረጃ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይት ሲደረግ የትላንቱ የማርክ ሩብዮ እና የጠ/ሚኒስትር አብይ የመጀመሪያ ነው።

👍35😁31👀4❤2🔥2
አኮያ ፕሮፐርቲስ
🔔 ከፒያሳ በቅርብ ርቀት ላይ ሰሜን ማዘገጃ ሳሬም ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ሳይታችን ላይ የኢድ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የሆነ ከ 5%-13% የሚደርስ ቅናሽ ስናደርግ በታላቅ ደስታ ነው ።
🔔 በካሬ 80,000 ብር ሲሸጥ የነበረውን የኢድ በአልን አስመልክተን ለ 3 ቀን ብቻ በካሬ 76,000 ብር! ከ 10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
🔔 2B+G+18 በሆነው አፓርትመንታች ላይ የእንጦጦ ንፁህ እና ነፋሻማ አየር እየሳቡ የተረጋጋ ህይወት ይኖራሉ!
🔔 ከ ባለ 1 እስከ ባለ 4 መኝት በተለያየ ካሬ አማራጭ
📌 ባለ አንድ መኝታ- 81 ካሬ
-ጠቅላላ ዋጋ= 6,171,390 ብር
-10% ቅድመ ክፍያ= 617,139 ብር
📌 ባለ ሁለት መኝታ-110 ካሬ
-ጠቅላላ ዋጋ= 8,380,900 ብር
-10% ቅድመ ክፍያ= 838,090 ብር
📌 ባለ ሶስት መኝታ-130 ካሬ
-ጠቅላላ ዋጋ= 9,904,700 ብር
-10% ቅድመ ክፍያ= 990,470 ብር
📌 ባለ አራት መኝታ- 211 ካሬ
-ጠቅላላ ዋጋ=16,076,090 ብር
-10% ቅድመ ክፍያ=1,607,609 ብር
🔔 በዚህ የመኖሪያ ህንፃ ላይ፡
💥የከርሰ-ምድር ውሀ
💥400 KVA ጄኔሬተር
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥2 ሊፍት
💥በቂ የተሰየመ የመኪና ማቆሚያ
💥መዋኛ ገንዳ
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥 ሬስቶራንት እና ካፌ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ ሰገነት እና ሌሎች መገልገያዎች።
🔔 የመረጡትን ቤት ተመላሽ በሚሆን 200,000 ብር ለ15 ቀን ማስያዝ ይችላሉ።
ለሳይት ጉብኝት እና ለቢሮ ቀጠሮ፡
📞 0923254077 ይደውሉልን!
ቴሌግራም- @E192087
አኮያ ፕሮፐርቲስ
ከነገ ለተዛመደ!

👍20
ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች ታገደ።
ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች በካውንስሉ በምዝገባ ቁጥር 03111 የተመዘገበች የሃይማኖት ተቋም መሆኗ ይታወቃል
ይሁን እንጂ ቤተክርስቲያኒቱ የካውንስሉ አባል ስትሆን ልታከናውናቸው ከሚገቡ መመሪያዎችና ደንቦች መካከል አንዱ የካውንስሉ አባላት ስነ ምግባር መመሪያ ሲሆን በስነ ምግባር መመሪያው አንቀጽ 9.3 ላይ የስነ ምግባር ግድፈቶች ተብለው በዝርዝር የተገለጹትን ተግባራት በቤተክርስቲያኒቱ መሪ መፈጸሙን አረጋግጠናል።
በመሆኑም ጉዳዩ በካውንስሉ ሥነ መለኮት ኮሚሽን እና የሕግ ኮሚሽን ታይቶ በሚመለከታቸው አካላት የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ የቤተክርስቲያኒቱ ፈቃድ ታግዶ የሚቆይ ሲሆን ሁሉም የካውንስሉ አስተዳደራዊ መዋቅሮችና የሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት ይህንንና ከዚህ በኋላ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን እንድታስፈጽሙ በግልባጭ ተመዝግቦላችኋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል

👍92😁39👎8❤6👀2
ዲሽ እና ዲኮደር መጠቀም ሳያስፈልግ የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ማግኘት የሚቻልበት ስርዓት ይፋ ተደረገ።
ኢትዮቴሌኮም እና መልቲቾይስ አፍሪካ የቴሌኮምን አገልግሎት ከመዝናኛ ጋር ያጣመረውን የ"ዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል"ን ይፋ አድርገዋል።የዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል የኢትዮ ቴሌኮምን የፊክስድ ብሮድባንድና የሞባይል ኢንተርኔት ዳታ አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ከጠበቁት የዲኤስቲቪ የመዝናኛና ስፖርት ይዘቶች ጋር በአንድ ያዋሃደ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ትብብሩ ኢትዮ ቴሌኮም የደረሰበትን ሁሉንም አይነት አገልግሎት ዲጂታላይዝ የማድረግ ጉዞ ማሳያ ነው ብለዋል።የመልቲቾይስ ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ገሊላ ገ/ሚካኤል ኢትዮ ቴሌኮም እየሰጠ ያለው ፋይበር ኔትዎርክ የሚጠቀም ደንበኛ ከዲኤስቲቪ አገልግሎት በላቀ መልኩ የኦንላይን ትምህርት እንዲሁም ስራዎችን ጨምሮ ለደንበኞች ህይወትን ሊያቀሉ የሚችሉ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችል ገልፀዋል።
ዲኤስቲቪ እና ኢትዮቴሌኮም ለዚህ የዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል ከመደበኛው አገልግሎታቸው ክፍያዎች በተለየ መልኩ ልዩ ቅናሽ ያደረጉበት ሲሆን ደንበኞች የስትሪሚንግ አገልግሎቱን በመመዝገብ ብቻ ዲሽና ዲኮደር ሳያስፈልጋቸው በቀላሉ መጠቀም ያስችላቸዋል።ይህም ደንበኞች በፈለጉት ዓይነት ዲቫይስ ወይም በስልክ፣ ታብሌት፣ ላፕቶፕና ቴሌቪዥን ቦታ እና ግዜ ሳይገድባቸው ከ70በላይ ይዘቶችን ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።
Via Arts TV

👍50❤9😁3
5 የኢቢኤስ ሰራተኞች በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ!
የፌደራል ፖሊስ “በሽብር ወንጀል ጉዳይ” ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን አምስት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች፤ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት አቀረበ። ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ፖሊስ በጠየቀው የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ላይ ብይን ለመስጠት ለመጪው ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የፌደራል ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮውን የጠየቀው፤ በስምንት ተጠርጣሪዎች ላይ እያካሄደ ያለውን የምርመራ ስራ በሰውና በሰነድ ማስረጃ በስፋት ለማጣራት በሚል ነው። ከስምንቱ ተጠርጣሪዎች ውስጥ ባለፈው ሳምንት እሁድ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ በተሰራጨ ዝግጅት ላይ “የሀሰት ታሪኳ” ቀርቧል የተባለው ብርቱካን ተመስገን ትገኝበታለች።
ኢትዮጵያ ኢንሳይደር እንደዘገበው፤ የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና ስራ አስኪያጅና የመገናኛ ብዙሃኑ አንዱ ባለድርሻ የሆኑት አቶ ነብዩ ጥዑመልሳንም በተጠርጣሪነት ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በቴሌቭዥን ጣቢያው በፕሮግራም ዳይሬክተርነት የሚሰራው ጋዜጠኛ ታሪኩ ኃይሌ፣ የስቱዲዩ ዳይሬክተሩ አቶ ንጥር ደረጀ፣ ረዳት የፕሮግራም አዘጋጇ ህሊና ታረቀኝና የካሜራ ባለሙያ ቶማስ ደመቀም ፍርድ ቤት ቀርበው የዛሬውን ሂደት ተከታትለዋል።

😁97👍57👎35❤7🔥5👀1
ሶማሊያ አሜሪካ የአየር ማረፊያዎቿን እና ወደቦቿን በብቸኛነት እንድትቆጣጠር ሀሳብ አቀረበች!
ሶማሊያ ስትራቴጂካዊ የአየር ማረፊያዎቿን እና ወደቦቿን አሜሪካ "በብቸኛነት እንድትቋጣጠር" ሀሳብ ማቅረቧ ተገለፀ።የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ሀሳቡን ያቀረቡት ለዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጻፉት ደብዳቤ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በአንድ የአከባቢው ዲፕሎማት የተረጋገጠው ደብዳቤው፣ ሶማሊያ አሜሪካ በብቸኛነት እንድትቆጣጠራቸው ሀሳብ ካቀረበችባቸው መካከል በባሊዶግሌ የሚገኘውን የአየር ማረፊያ ጨምሮ የበርበራ እና የቦሳሶ ወደቦችን እንደሚያካትት ይገልጻል።ደብዳቤው አክሎም ቦታዎቹ ስትራቴጂካዊ መሆናቸውን ጠቅሶ ሀሳቡ በቀጠናው የአሜሪካን ተሳትፎ ለማጠናከር እድል እንደሚፈጥር አመላክቷል።
በተጨማሪም ለአሜሪካ "ያልተቋረጠ ወታደራዊ እና ሎጂስቲካዊ መዳረሻን" እንደሚያረጋግጥ እና በቀጠናው የውጭ ሀይሎች መሰረት እንዳይጥሉ እንደሚከላከል ተጠቁሟል።ሀሳቡ ሶማሊያ የራሷ ግዛት እንደሆነች በምትገልፀው ሶማሊላንድ ግዛት ውስጥ የሚገኘውን የበርበራ ወደብን ያካትታል ተብሏል።
የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱራህማን ዳሂር አደን በበኩላቸው አሜሪካ "ሙሰኛ አገዛዝ" ሲሉ ከጠሩት የሶማሊያ መንግስት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት ትታለች ሲሉ በመግለጽ ሀሳቡን ውድቅ አድርገዋል።አክለውም ዋሽንግተን አሁን ላይ ሰላማዊ፣ የተረጋጋ እና ዴሞክራሲያዊ ሀገር መሆኗን ለአለም ካሳየችው ሶማሊላንድ ጋር ለመገናኘት ዝግጁ ነች ብለዋል። በተጨማሪም "አሜሪካ ሞኝ አይደለችም። በርበራ ወደብን በተመለከተ ከማን ጋር መገናኘት እንዳለባት ታውቃለች" ሲሉ ተናግረዋል።

👍31👎18😁9❤6🔥6

👍28❤3😭1