YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
🇪🇹 የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የሆነው “ፊቼ ጫምባላላ” በሀዋሳ ጉዱማሌ በመከበር ላይ ይገኛል

በዚህ የአደባባይ በዓል ላይ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ከብሄሩ ተወላጆች ጋር ታድመዋል።

የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ፍቼ ጨምባላላ” ከአስር ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ እና ባህል ድርጅት “ዩኔስኮ” የሰው ልጆች ወካይ የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወስ ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
👍105👎1
ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ ጋር በስልክ ማውራታቸው ተገለጸ!

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሮብዮ ጋር በስልክ ማውራታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስ ትላንት መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ማርክ ሩብዮ እና ጠ/ሚኒስትር አብይ በስልክ የተወያየቱ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ዙሪያ መሆኑን ቃል አቀባዩ አመላክተዋል።ቅድሚያ የሰጧቸው ተብለው በቃል አቀባዩ ከተዘረዘሩት ጉዳዮች መካከልም የአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት አንዱ መሆኑን አስታውቀዋል።

ቃል አቀባዩ በተጨማሪም መሪዎቹ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ተወያይተዋል ብለዋል።ለኢትዮጵያ ሰላም እና ብልጽግን አሜሪካ ድጋፏን እንደምታጠናክር ማርክ ሩብዮ ለጠ/ሚኒስትር አብይ አረጋግጠውላቸዋል ሲሉ ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

የትራምፕ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ በከፍተኛ አመራር ደረጃ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይት ሲደረግ የትላንቱ የማርክ ሩብዮ እና የጠ/ሚኒስትር አብይ የመጀመሪያ ነው።

Via AS
@YeneTube @Fikerassefa
👍35😁31👀42🔥2
አኮያ ፕሮፐርቲስ

🔔 ከፒያሳ በቅርብ ርቀት ላይ ሰሜን ማዘገጃ ሳሬም ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ሳይታችን ላይ የኢድ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የሆነ ከ 5%-13% የሚደርስ ቅናሽ ስናደርግ በታላቅ ደስታ ነው ።

🔔 በካሬ 80,000 ብር ሲሸጥ የነበረውን የኢድ በአልን  አስመልክተን ለ 3 ቀን ብቻ በካሬ 76,000 ብር! 10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

🔔 2B+G+18 በሆነው አፓርትመንታች ላይ የእንጦጦ ንፁህ እና ነፋሻማ አየር እየሳቡ የተረጋጋ ህይወት ይኖራሉ!

🔔 ከ ባለ 1 እስከ ባለ 4 መኝት በተለያየ ካሬ አማራጭ

📌 ባለ አንድ መኝታ- 81 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 6,171,390 ብር
       -10% ቅድመ ክፍያ= 617,139 ብር

📌  ባለ ሁለት መኝታ-110 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 8,380,900 ብር
     -10% ቅድመ ክፍያ= 838,090 ብር

📌 ባለ ሶስት መኝታ-130 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 9,904,700 ብር
     -10% ቅድመ ክፍያ= 990,470 ብር

📌 ባለ አራት መኝታ- 211 ካሬ
      -ጠቅላላ ዋጋ=16,076,090 ብር
    -10% ቅድመ ክፍያ=1,607,609 ብር

🔔 በዚህ የመኖሪያ ህንፃ ላይ፡
💥የከርሰ-ምድር ውሀ
💥400 KVA ጄኔሬተር
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥2 ሊፍት
💥በቂ የተሰየመ የመኪና ማቆሚያ
💥መዋኛ ገንዳ
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥 ሬስቶራንት እና ካፌ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ ሰገነት እና ሌሎች መገልገያዎች።

🔔 የመረጡትን ቤት ተመላሽ በሚሆን 200,000 ብር ለ15 ቀን ማስያዝ ይችላሉ።

  ለሳይት ጉብኝት እና ለቢሮ ቀጠሮ፡
  📞 ⁨0923254077⁩  ይደውሉልን!
ቴሌግራም- @E192087
  
       አኮያ ፕሮፐርቲስ
         ከነገ ለተዛመደ!
👍20
ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች ታገደ።

ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች በካውንስሉ በምዝገባ ቁጥር 03111 የተመዘገበች የሃይማኖት ተቋም መሆኗ ይታወቃል

ይሁን እንጂ ቤተክርስቲያኒቱ የካውንስሉ አባል ስትሆን ልታከናውናቸው ከሚገቡ መመሪያዎችና ደንቦች መካከል አንዱ የካውንስሉ አባላት ስነ ምግባር መመሪያ ሲሆን በስነ ምግባር መመሪያው አንቀጽ 9.3 ላይ የስነ ምግባር ግድፈቶች ተብለው በዝርዝር የተገለጹትን ተግባራት በቤተክርስቲያኒቱ መሪ መፈጸሙን አረጋግጠናል።

በመሆኑም ጉዳዩ በካውንስሉ ሥነ መለኮት ኮሚሽን እና የሕግ ኮሚሽን ታይቶ በሚመለከታቸው አካላት የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ የቤተክርስቲያኒቱ ፈቃድ ታግዶ የሚቆይ ሲሆን ሁሉም የካውንስሉ አስተዳደራዊ መዋቅሮችና የሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት ይህንንና ከዚህ በኋላ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን እንድታስፈጽሙ በግልባጭ ተመዝግቦላችኋል፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል

@Yenetube @Fikerassefa
👍92😁39👎86👀2
ዲሽ እና ዲኮደር መጠቀም ሳያስፈልግ የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ማግኘት የሚቻልበት ስርዓት ይፋ ተደረገ።

ኢትዮቴሌኮም እና መልቲቾይስ አፍሪካ የቴሌኮምን አገልግሎት ከመዝናኛ ጋር ያጣመረውን የ"ዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል"ን ይፋ አድርገዋል።የዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል የኢትዮ ቴሌኮምን የፊክስድ ብሮድባንድና የሞባይል ኢንተርኔት ዳታ አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ከጠበቁት የዲኤስቲቪ የመዝናኛና ስፖርት ይዘቶች ጋር በአንድ ያዋሃደ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ትብብሩ ኢትዮ ቴሌኮም የደረሰበትን ሁሉንም አይነት አገልግሎት ዲጂታላይዝ የማድረግ ጉዞ ማሳያ ነው ብለዋል።የመልቲቾይስ ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ገሊላ ገ/ሚካኤል ኢትዮ ቴሌኮም እየሰጠ ያለው ፋይበር ኔትዎርክ የሚጠቀም ደንበኛ ከዲኤስቲቪ አገልግሎት በላቀ መልኩ የኦንላይን ትምህርት እንዲሁም ስራዎችን ጨምሮ ለደንበኞች ህይወትን ሊያቀሉ የሚችሉ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችል ገልፀዋል።

ዲኤስቲቪ እና ኢትዮቴሌኮም ለዚህ የዲኤስቲቪ ስትሪም ጥቅል ከመደበኛው አገልግሎታቸው ክፍያዎች በተለየ መልኩ ልዩ ቅናሽ ያደረጉበት ሲሆን ደንበኞች የስትሪሚንግ አገልግሎቱን በመመዝገብ ብቻ ዲሽና ዲኮደር ሳያስፈልጋቸው በቀላሉ መጠቀም ያስችላቸዋል።ይህም ደንበኞች በፈለጉት ዓይነት ዲቫይስ ወይም በስልክ፣ ታብሌት፣ ላፕቶፕና ቴሌቪዥን ቦታ እና ግዜ ሳይገድባቸው ከ70በላይ ይዘቶችን ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

Via Arts TV
@YeneTube @FikerAssefa
👍509😁3
5 የኢቢኤስ ሰራተኞች በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ!

የፌደራል ፖሊስ “በሽብር ወንጀል ጉዳይ” ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን አምስት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች፤ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት አቀረበ። ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ፖሊስ በጠየቀው የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ላይ ብይን ለመስጠት ለመጪው ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የፌደራል ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮውን የጠየቀው፤ በስምንት ተጠርጣሪዎች ላይ እያካሄደ ያለውን የምርመራ ስራ በሰውና በሰነድ ማስረጃ በስፋት ለማጣራት በሚል ነው። ከስምንቱ ተጠርጣሪዎች ውስጥ ባለፈው ሳምንት እሁድ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ በተሰራጨ ዝግጅት ላይ “የሀሰት ታሪኳ” ቀርቧል የተባለው ብርቱካን ተመስገን ትገኝበታለች።

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር እንደዘገበው፤ የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና ስራ አስኪያጅና የመገናኛ ብዙሃኑ አንዱ ባለድርሻ የሆኑት አቶ ነብዩ ጥዑመልሳንም በተጠርጣሪነት ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በቴሌቭዥን ጣቢያው በፕሮግራም ዳይሬክተርነት የሚሰራው ጋዜጠኛ ታሪኩ ኃይሌ፣ የስቱዲዩ ዳይሬክተሩ አቶ ንጥር ደረጀ፣ ረዳት የፕሮግራም አዘጋጇ ህሊና ታረቀኝና የካሜራ ባለሙያ ቶማስ ደመቀም ፍርድ ቤት ቀርበው የዛሬውን ሂደት ተከታትለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
😁97👍57👎357🔥5👀1
ሶማሊያ አሜሪካ የአየር ማረፊያዎቿን እና ወደቦቿን በብቸኛነት እንድትቆጣጠር ሀሳብ አቀረበች!

ሶማሊያ ስትራቴጂካዊ የአየር ማረፊያዎቿን እና ወደቦቿን አሜሪካ "በብቸኛነት እንድትቋጣጠር" ሀሳብ ማቅረቧ ተገለፀ።የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ሀሳቡን ያቀረቡት ለዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጻፉት ደብዳቤ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በአንድ የአከባቢው ዲፕሎማት የተረጋገጠው ደብዳቤው፣ ሶማሊያ አሜሪካ በብቸኛነት እንድትቆጣጠራቸው ሀሳብ ካቀረበችባቸው መካከል በባሊዶግሌ የሚገኘውን የአየር ማረፊያ ጨምሮ የበርበራ እና የቦሳሶ ወደቦችን እንደሚያካትት ይገልጻል።ደብዳቤው አክሎም ቦታዎቹ ስትራቴጂካዊ መሆናቸውን ጠቅሶ ሀሳቡ በቀጠናው የአሜሪካን ተሳትፎ ለማጠናከር እድል እንደሚፈጥር አመላክቷል።

በተጨማሪም ለአሜሪካ "ያልተቋረጠ ወታደራዊ እና ሎጂስቲካዊ መዳረሻን" እንደሚያረጋግጥ እና በቀጠናው የውጭ ሀይሎች መሰረት እንዳይጥሉ እንደሚከላከል ተጠቁሟል።ሀሳቡ ሶማሊያ የራሷ ግዛት እንደሆነች በምትገልፀው ሶማሊላንድ ግዛት ውስጥ የሚገኘውን የበርበራ ወደብን ያካትታል ተብሏል።

የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱራህማን ዳሂር አደን በበኩላቸው አሜሪካ "ሙሰኛ አገዛዝ" ሲሉ ከጠሩት የሶማሊያ መንግስት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት ትታለች ሲሉ በመግለጽ ሀሳቡን ውድቅ አድርገዋል።አክለውም ዋሽንግተን አሁን ላይ ሰላማዊ፣ የተረጋጋ እና ዴሞክራሲያዊ ሀገር መሆኗን ለአለም ካሳየችው ሶማሊላንድ ጋር ለመገናኘት ዝግጁ ነች ብለዋል። በተጨማሪም "አሜሪካ ሞኝ አይደለችም። በርበራ ወደብን በተመለከተ ከማን ጋር መገናኘት እንዳለባት ታውቃለች" ሲሉ ተናግረዋል።

Via AS
@YeneTube @Fikerassefa
👍31👎18😁96🔥6
አኮያ ፕሮፐርቲስ

🔔 ከፒያሳ በቅርብ ርቀት ላይ ሰሜን ማዘገጃ ሳሬም ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ሳይታችን ላይ የኢድ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የሆነ ከ 5%-13% የሚደርስ ቅናሽ ስናደርግ በታላቅ ደስታ ነው ።

🔔 በካሬ 80,000 ብር ሲሸጥ የነበረውን የኢድ በአልን  አስመልክተን ለ 3 ቀን ብቻ በካሬ 76,000 ብር! 10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

🔔 2B+G+18 በሆነው አፓርትመንታች ላይ የእንጦጦ ንፁህ እና ነፋሻማ አየር እየሳቡ የተረጋጋ ህይወት ይኖራሉ!

🔔 ከ ባለ 1 እስከ ባለ 4 መኝት በተለያየ ካሬ አማራጭ

📌 ባለ አንድ መኝታ- 81 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 6,171,390 ብር
       -10% ቅድመ ክፍያ= 617,139 ብር

📌  ባለ ሁለት መኝታ-110 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 8,380,900 ብር
     -10% ቅድመ ክፍያ= 838,090 ብር

📌 ባለ ሶስት መኝታ-130 ካሬ
       -ጠቅላላ ዋጋ= 9,904,700 ብር
     -10% ቅድመ ክፍያ= 990,470 ብር

📌 ባለ አራት መኝታ- 211 ካሬ
      -ጠቅላላ ዋጋ=16,076,090 ብር
    -10% ቅድመ ክፍያ=1,607,609 ብር

🔔 በዚህ የመኖሪያ ህንፃ ላይ፡
💥የከርሰ-ምድር ውሀ
💥400 KVA ጄኔሬተር
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥2 ሊፍት
💥በቂ የተሰየመ የመኪና ማቆሚያ
💥መዋኛ ገንዳ
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥 ሬስቶራንት እና ካፌ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ ሰገነት እና ሌሎች መገልገያዎች።

🔔 የመረጡትን ቤት ተመላሽ በሚሆን 200,000 ብር ለ15 ቀን ማስያዝ ይችላሉ።

  ለሳይት ጉብኝት እና ለቢሮ ቀጠሮ፡
  📞 ⁨0923254077⁩  ይደውሉልን!
ቴሌግራም- @E192087
  
       አኮያ ፕሮፐርቲስ
         ከነገ ለተዛመደ!
👍283😭1
እግድ

የፌደራል መንግስቱ በመቀሌ የሚገኘውን ኤፍ ኤም 104.4 የባንክ አካውንት ማገዱን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ሰዎች ገልፀዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍8😁21👎1
🌍 የአፍሪካ ሀገራት የጥቁር ባህር የእህል ስምምነት በድጋሚ እንዲጀመር ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው ሲሉ አልጄሪያዊው ባለሙያ ተናገሩ

🗣 "የአፍሪካ አህጉር እርምጃውን በጉጉት እየጠበቀ ነው፤ በተለይም የምግብ እጥረት የገጠማቸው ደቡባዊ የአህጉሪቱ ሀገራት። ይህ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር እና የእህል ፍላጎቶችን ለመሸፈን ጥሩ አጋጣሚ ነው" ሲሉ በአልጄሪያ ፈርሃት አባስ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ፋሬስ ሃባቼ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

በሩሲያ የእህል ምርት ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ማንሳት ሩሲያ የአፍሪካ ቀዳሚ ምግብ አቅራቢ መሆኗን እንደሚያጠናክር ያነሱት ፕሮፌሰሩ፤ እ.አ.አ 2024 ሩሲያ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የለገሰችውን 200 ሺህ ቶን እህል አስታውሰዋል።

የፑቲን እና ትራምፕን ንግግር ተከትሎ ሩሲያ እና አሜሪካ የጥቁር ባህር ስምምነትን በድጋሚ ለመጀመር ተስማምተዋል። ስምምነቱ በሩሲያ የግብርና ባንክ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ጨምሮ የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸው ላይ የተንጠለጠለ ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
👍182
አስገራሚ ዜና

ሶማሌላንድ ለአሜሪካ የጦር ሰፈር ለመስጠት እና በምላሹ የሀገርነት እውቅና ለማግኘት ማቀዷን የሰሙት የሶማሊያ መሪዎች እነሱ ደሞ የተሻለ ያሉትን ሀሳብ ለአሜሪካ በደብዳቤ ልከዋል፡፡ አሜሪካ ሁሉንም የሶማሊያ ወደቦች የአየር ማረፊያዎች ለብቻዋ ያለ ምንም ተቀናቃኝ መቆጣጠር እንድትችል ጥያቄ ማቅረባቸውን ሮየተርስ ዘግቧል፡፡
ሶማሊላንድ በበኩሏ "አሜሪካ የሚጠቅማትን ታውቃለች" የሚል አጭር ምላሽ ለሶማሊያ አመራሮች ሰጥታለች።

Via:- አዩዘሀበሻ
@Yenetube @Fikerassefa
😁63👍197😭7
🇿🇦 የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የውጭ የስለላ ተቋም ለማቋቋም የሚያስችል የሕግ ማሻሻያ ፈረሙ

የተሻሻለ ቁጥጥርና የመንግሥት የደህንነት ኤጀንሲን መሻር ጨምሮ የሕግ ማሻሻያው በደቡብ አፍሪካ የስለላ አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል።

የተሻረው ኤጀንሲ በውጭ መረጃ አገልግሎት እና የሀገር ውስጥ መረጃ ኤጀንሲ እንደሚተካም በመግለጫው ተጠቅሷል። ለሀገር ውስጥ እና ውጭ ስለላ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ መረጃ አካዳሚ እና የመረጃ ስልጠና ኢኒስቲትዩት በድጋሚ እንደሚቋቋሙም ጽ/ቤቱ ጨምሮ ገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍14
🇪🇹 ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የባሕረኞች ማሠልጠኛ አካዳሚ ልትከፍት ነው

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የማሰልጠኛ አካዳሚውን ለመክፈት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋር ተፈራርሟል። 

አካዳሚው ከባቦጋያ ሎጅስቲክሰ እና ማሪታይም አካዳሚ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ማሪታይም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ቀጥሎ ለሀገሪቱ ሶስተኛው ማሰልጠኛ እንደሚሆን ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ኢትዮጵያ በ2022 በሎጅስቲክስ አፈፃፀም ከአፍሪካ ቀዳሚ እንድትሆን ለማድረግ እንዲሁም ባሕረኞችን አሠልጥኖ ለዓለም ገበያ በማቅረብ ከመጀመሪያዎቹ አምስት የዓለም ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ እየሠራ እንደሚገኝ በማህበራዊ ትሥሥር ገፁ አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍435😁5🔥41
ዒድ ሙባረክ!
👍45😭135👎4
በማይናማር የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ1,600 በላይ ደርሷል ከ3,400 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭20👍6
ጨረቃ ዛሬ በመታየቷ የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ ይከበራል

የሸዋል ወር ጨረቃ ዛሬ ቅዳሜ በመታየቷ 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ እሁድ መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚከበር ተገልጿል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ 1 ሺህ 446ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አስተምኅሮቱን በመተግበር ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👍36😭36😁7
👍 ተከታዮችን በፍጥነት ማግኘት ይፈልጋሉ?

Boostgram Promo ይጠቀሙ - ተከታዮችዎን በአጭር ጊዜ ይጨምሩ!

ጀማሪ ኢንፍሉዌንሰር ከሆኑ
ተከታዮችን በፍጥነት ማሳደግ ከፈለጉ
ተጽዕኖዎን ለማሳደግ ከፈለጉ


Boostgram Promo መፍትሄው ነው!

👉 ዛሬውኑ ይሞክሩት: https://tttttt.me/boostgramPromoBot/boostgram
ከሌሎች ጀማሪዎች ልዩ ይሁኑ - የማህበራዊ ሚዲያ ተከታታዮችዎን በቀላሉ ያሳድጉ!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍52