‹‹ በኢትዮጵያ የግፍ ወንጀሎች በሀገሪቱ እየተፈፀሙ እንደሆነ እና ይህም ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል ›› - ተ.መ.ድ.
የተባበሩት መንግስታት ድርጀት የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያዎች ኮሚሽን ‹‹ በኢትዮጵያ የግፍ ወንጀሎች በሀገሪቱ እየተፈፀሙ እንደሆነ እና ይህም ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል ›› ሲሉ አስጠነቅቋል፡፡የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ቡድን ማክሰኞ ዕለት ባወጣው አዲስ ሪፖርት ‹‹ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሚባል ግፍ እንደተፈፀመና ችግሩም እየከፋ ሊሄድ እንደሚችል በማስጠንቀቅ አለምአቀፍ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ›› ጠይቀዋል።
ይኽው ሪፖርት ‹‹ በትክክለኛ መረጃና ማስረጃ ላይ የተመሰረቱ ምንጮች እንደሚያመላክቱት የጭካኔ ወንጀሎች በሀገሪቱ ዜጎች ላይ በኢትዮጵያ መፈፃማቸውን ›› አመልክቷል።የጭካኔ ወንጀሎች በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ከባድ ወንጀሎች ሲሆኑ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መሰረት የዘር ማጥፋት፣ የጦር ወንጀሎች እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ናቸው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን (ICHREE) ያቀረበው ሪፖርት እንዳመለከተው ከሆነ ‹‹ ስምንቱም የተለመዱ የአደጋ መንስኤዎች እና አብዛኛዎቹ የጭካኔ ወንጀሎች ልዩ ስጋት አሁን በኢትዮጵያ እየተፈፀሙ ይገኛሉ ›› ሲል አትቷል።‹‹የቅርብ ጊዜ ዝርዝር ግኝቶች በሰው ልጆች ላይ እጅግ በጣም ከባድ የሆኑ ወንጀሎች ተብለው የሚታሰቡትን የጭካኔ ወንጀሎች አስጊ ሁኔታዎችን በመገምገም ነው ›› ሲል ዘገባው አመልክቷል።
‹‹ እነዚህ ወንጀሎች - የዘር ማጥፋት፣ የጦር ወንጀሎች እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ጨምሮ - በተባበሩት መንግስታት የጭካኔ ወንጀሎች ትንተና ማዕቀፍ ውስጥ ተለይተዋል ›› ሲል መግለጫው አክሎ አመላክቷል።ኮሚሽኑ አክሎም በአማራ ክልል እየተባባሰ መምጣቱን የገለፀው ህገ -ወጥ ግድያ፣ የጅምላ እስራትና ሌሎች በርካታ በሰው ልጆች ላይ ሊፈፀሙ የማይገባቸው ወንጀሎች በከፍተኛ ደረጃ ተበራክተዋል ብሏል፡፡
በዚህም እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚያመላክቱት ድርጊቱ የባለሙያዎችን፣ ተንታኞችን እና የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ስቧል ሲል ገልጿል።የኮሚሽኑ አባል የሆኑት ራዲካ ኩማራስዋሚ በበኩላቸው ‹‹ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በግልጽ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ በመሆኑ ጉዳዩ የብዙዎች እይታ እያገኘ ነው ይህም አስፈላጊ ነው ›› ብለዋል።
በኢትዮጵያ መንግስት እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሀት) መካከል በፕሪቶሪያ የተደረገውን የግጭት ማቆም ስምምነት ከአንድ አመት ገደማ በኋላ አሁንም በሀገሪቱ እየታዩ ያሉት የሰብአዊ መብት ሁኔታዎች አሳሳቢ መሆናቸውን በሪፖርቱ ተመላክቷል።ዘገባው አያይዞም በትግራይ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ዞኖች በተለይም በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ እና በደቡብ የሚገኙ በርካታ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ከፍተኛ አለመረጋጋት እያጋጠማቸው ሲሆን የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ አለመሆን ችግር አሁንም ድረስ በከፍተኛ ደረጃ ቀጥሏል ነው ያለው።
የኢትዮጵያ መንግስት በሪፖርቱ ላይ እስካሁን የሰጠው አስተያየት እንደሌለ የአናዶሉ ዘገባ ያመላክታል። ምንም እንኳን መንግስት በዚህ አዲስ ሪፖርት ላይ ምላሽ አይሰጥበት እንጂ ከዚህ ወደም የኮሚሽኑን ሪፖርት ደጋግሞ አጣጥሎታል፡፡
[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa

👍53❤7👎3
ፖሊስ በከተማው በተለያዩ ጊዚያት የተሰረቁ ተሽከርካሪዎችን በመያዝ ለባለቤቶቻቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ገለፀ!
መስከረም 23/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ፖሊስ በከተማው ባደረገው ጥናትና ክትትል በተለያዩ ጊዚያት የተሰረቁ 9 ተሽከርካሪዎችን በመያዝ ለባለቤቶቻቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ገለፀ፡፡
ከወንጀሉ ጋር የተለያየ ድርሻ አላቸው የተባሉ 26 ተጠርጣሪዎችንም በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገልጿል፡፡
በዚህም የአዲስ አበባ ፖሊስ የምርመራና የክትትል ቡድን በማቋቋም ተሰርቀው በአዲስ አበባ የሚገኙና ወደተለያዩ የክልል ከተሞች ተወስደው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ለባለቤቶቻቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል፡፡
በቅርብ ቀናት ውስጥ ብቻ 9 የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ለባለቤቶቻቸው የተመለሱ ሲሆን 3 አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ደግሞ በጋራዥ ውስጥ ተፈታተው መያዛቸውም ተመላክቷል፡፡
በዚህም ወንጀል የተለያየ ተሳትፎ ያላቸውን 26 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሆነ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የተሽከርካሪ ባለቤቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች የመኪናቻቸውን ቁልፍ በጥንቃቄ በመያዝና አስተማማኝ ጥበቃ ባለበት ቦታ በማቆም ንብረታቸውን ማስጠበቅ እንዳለባቸው ፖሊስ አሳስቧል፡፡

👍43👎7❤3😭2🔥1
መርጌታ ላቀው የባህል መድህኒት ፈውስ እና ጥበብ ይ በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 0915968136
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
☟☟☟☟☟ ☟☟☟☟☟
☞ ለመፍትሄ ሀብት
☞ ለህመም
☞ ለሁሉ ሠናይ
☞ ቡዳ ለበላው
☞ ለገበያ
☞ ሚስጥር የሚነግር
☞ ለቀለም(ለትምህርት)
☞ ለመፍትሔ ስራይ
☞ ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ
☞ ሌባ የማያስነካ
☞ ለበረከት
☞ ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
☞ ለግርማ ሞገስ
☞ መርበቡተ ሰለሞን
☞ ለዓይነ ጥላ
☞ ለመክስት
☞ ጸሎተ ዕለታት
☞ ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
☞ ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
☞ ለትዳር
☞ ለድምፅ
ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ
ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
☎ 0915968136

👍13❤1
አዋሽ ባንክ "ታታሪዎቹ" የተሰኘዉን ሁለተኛ ዙር የስራ ፈጠራ ውድድር አስጀመረ!
አዋሽ ባንክ ጀማሪ የስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት በሚል ያስጀመረዉ "ታታሪዎቹ /ቀጠሌዋን" የተሰኘዉ የስራ ፈጠራ ዉድድር ሁለተኛው ዙር መጀመሩን አሳዉቋል።
በዚህ የስራ ፈጠራ ዉድድር ማስጀመሪያ ሥነሥርዓት ላይ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራዉ እንደተናገሩት " ዉድድሩ አዳዲስ የስራ ፈጠራ ክህሎት ኖሯቸዉ በፋይናንስ እጥረት ምክንያት ተግባራዊ ማድረግ ያልቻሉ ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ያለመ ነዉ" ብለዋል።
አዳዲስ ችግር ፈቺ የሆኑ የስራ ፈጠራ ሀሳቦች ያላቸው እና እድሜያቸው ከ18 በላይ እንዲሁም ከአስረኛ ክፍል በላይ የሆኑ ወጣቶች ተሳታፊ መሆን ይችላሉ ተብሏል።
መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ የጀመረው ሁለተኛ ዙር የስራ ፈጠራ ዉድድር ላይ አሸናፊ ለሆነዉ ቢዝነስሱን የሚያስቀጥልበት 1 ሚሊዮን ብር እና ከዋስትና ዉጪ ብድር እንደሚመቻች ተገልጿል።
ተወዳዳሪ የስራ ፈጣሪዎች ከጥቅምት 12 እስከ ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም. በበይነ መረብ ( ኦን ላይን) ወይም በሁሉም በባንኩ ቅርንጫፎች በአካል በመገኘት ማመልከት እንደሚችሉ ተነግሯል።
(ካፒታል)

👍7❤5
በአዲስ አበባ 100 ኪሎ ጤፍ 15 ሺህ ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል፡፡
(በኢትዮ ኤፍ ኤም)
አንደኛ ደረጃ ማኛ በመባል የሚታወቀው ጤፍ ወፍጮ ቤቶች ላይ 15ሺህ ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ኢትዮ ኤፍ ኤም ባደረገው ቅኝት ለመታዘብ ችሏል፡፡በአዲስ አበባ በተለያዩ ወፍጮ ቤቶች በተሰናበትነው 2015 ዓ.ም 100 ኪሎ ጤፍ እስከ 10 ሺህ ብር ድረስ ሲሸጥ ነበር፡፡
አሁን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የ4ሺህ ብር እና የ5ሺህ ብር ጭማሪ አሳይቶ እስከ 15 ሺህ ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል፡፡ኢትዮ ኤፍ ኤም በተለያዩ ወፍጮ ቤቶች ያለዉን የጤፍ ዋጋ በአካል በመገኘት ለማጣራት ሞክሯል።በዚህም መሰረት ነጭ ጤፍ (ማኛ) በኪሎ ከ140 እስከ 150 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ታዝበናል፡፡
እንደዚሁም ሰርገኛ እና ነጭ 100 ኪሎ ጤፍ ደግሞ እስከ 13 ሺህ ብር ይሸጣል፡፡የጤፍ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ሸማቾች፣ ነጋዴዎች እና የወፍጮ ቤት ባለቤቶችም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡የነዋሪዎችን አቅም ከተፈታተነው የዋጋ ጭማሪ ባሻገር፣ በገበያው በቂ የሚባል የጤፍ አቅርቦትም የለም ሲሉ የወፍጮ ቤት ባለንብረቶች ነግረውናል፡፡
አስተያየት ሰጭዎች እንዳሉት በሸማች ማህበራት 100ኪሎ ጤፍ በ10ሺህ ብር ድረስ ይሸጣል ያሉ ሲሆን የጤፉን አይነትና ደረጃ ግን ለመግለጽ እንደሚቸገሩ ገልጸዋል፡፡ከሰሞኑ በጤፍ ዋጋ ላይ የታየው ጭማሪ መሰረታዊ ምክንያቱ ምን ይሆን?
ለዚህ ጥያቄ ነጋዴዎች እና ወፍጮ ቤቶች ተከታዩን ምላሽ ሰጥተውናል፡፡ነጋዴዎች ጤፍ ጠፍቶ ሳይሆን ወደ ገበያ አለመቅረቡ ነው ይላሉ፡፡ለዚህ ደግሞ በሃገሪቱ የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር አስተዋጽኦ እንዳደረገ ነው የተናሩት፡፡
ከፍተኛ መጠን ያለው የጤፍ ምርት የሚቀርበው ከጎጃም ነበር የሚሉት ነጋዴዎች፣ አሁን በክልሉ ባለው አለመረጋጋት የጤፍ ምርት ወደ ገበያ እየቀረበ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ኢትዮ ኤፍ ኤም በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የወፍጮ ቤት ባለቤቶችንም ጠይቋቸው ነበር፡፡
ወፍጮ ቤቶች ጤፍ በበቂ እንደማያገኙ ተናግረው ፍላጎቱ ከወትሮው የተለየ ነው ብለዋል፡፡ከዚህ በፊት 50 ኩንታል እና ከዛ በላይ ይቀርብልን የነበረው ጤፍ አሁን በግማሽ ቀንሶብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ጤፍ ያስረክቡን የነበሩ ነጋዴዎችም ሌላ ደንበኞችን መያዝ ጀምረዋል ያሉት ነጋዴዎቹ፣ ሌሎች ደንበኞች የሚሏቸው ሆቴል ቤቶች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ በጤፍ ገበያ ላይ እጃቸውን ያስገቡ ደላሎች በቀጥታ ጤፍ ሸማቹ እጅ ላይ እንዳይገባ እየሰሩ ናቸው፤ ከሆቴል ቤቶች ጋር በመመሳጠር የዋጋ ንረት እንዲፈጠር እያደረጉ ናቸው ሲሉ ትዝብታችን ነግረውናል፡፡ሰዎች ነገ ይበልጥ ይጨምራል በሚል ብዙ ለመግዛት የሚያደርጉት ግብግብ ዋጋው ይበልጥ እንዲጨምር አድርጎታል፤በቂ አቅርቦት ቢኖር ግን ይህ አይፈጠርም ነበር ብለዋል የወፍጮ ቤት ባለንብረቶች፡፡

👍28😭15❤6
መንግሥት ለተጎጂዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይደርስ ሆን ብሎ እንቅፋት እየሆነ ነው ሲል ኦነግ ገለጸ!
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ማክሰኞ መስከረም 22/2016 ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ የብልጽግና መንግሥት ለተጎጂዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይደርስ ሆን ብሎ እንቅፋት እየሆነ ነው ሲል ገልጿል፡፡
በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎች ሕዝቡ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ክፉኛ መዳከሙን ያወሳው ኦነግ፤ "ለነዚሁ ተጎጂዎች ድጋፍ እንዳይደረግ እንቅፋ እየሆነ ያለው ሥልጣን የጨበጠው ብልጽግና መራሹ መንግሥት ነው።" ሲል በመግለጫው አስነበቧል፡፡
በተለይም በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የኦሮሚያ ክፍሎች ያለው ወረርሽን እና ረሃብ እጅግ አስከፊ ሁኔታ ላይ መድረሱን በመግለጽ፤ ይሁንና የእነዚህን ወገኖች ሕይወት ለመታደግ በመንግሥት በኩል ምንም አይነት ጥረት ሲደረግ አልታየም ብሏል፡፡
"ይህ ደግሞ ከዚህ ቀደም ደጋግመው “አሳውን ለማጥፋት ቅድሚያ ባሕሩን ማድረቅ” ብለው እንደተናሩት፤ ያሉትን በተግባር ላይ በማዋል ከአፈሙዝ የተረፈውን ሕዝባችንን በረሃብ እና በበሽታ እንዲያልቅ ፈርደውበታል።" ሲል ኦነግ ገልጿል፡፡
"ከወራት በፊት በምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ በተለይም ጉጂ እና ቦረና የተለያዩ ቦታዎች ለተከሰተው ድርቅ ሕዝቡ አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳያገኝ እና እንዳያገግም እንቅፋ ሲሆን የነበረው ራሱ መንግሥት ነው።" በማለትም ወቅሷል፡፡
"አሁንም በምእራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ እና ኢሉባቦርን በመሳሰሉ ዞኖች ለረሃብ እና ለተለያዩ በሽታዎች የተጋለጠው ሕዝብ ድምጹ እንዳይሰማ በማፈን እና ቀዳዳዎችን ኹሉ በመድፈን በተለይም የተለያዩ መድሃኒቶችን እንዲሁም የእርዳታ እህሎችን ከተከማቹበት እንዳይወጣ ከላይ እስከታች ያለው የአገዛዙ ክንፍ ተናቦ ይህን ሥራ እየሰራ መሆኑን ኦነግ ያምናል።" ብሏል፡፡
አሁን ላይ ሕዝባችን በወባ፣ ኮሌራ፣ ሳንባ፣ ስኳር እና ለሌሎችም በሽታዎች ከቀን ወደ ቀን እንደቅጠል እየረገፈ ነው ያለው ኦነግ፤ "ከዚህ በተጨማሪም በመንግሥት ታጣቂ በየዕለቱ ይገደላል።" በማለት አውስቷል፡፡
ግንባሩ "ከተለያዩ ምንጮች አረጋግጫለሁ" እንዳለው ከሆነ በምእራብ ወለጋ ዞን በተለይም በቤጊ፣ ቆንዳላ፣ ላሎ አሳቢ፣ መንዲ፣ ነጆ፣ ቦጂ ጮቆርሳ፣ ቦጂ ቢርመጂ እንዲሁም ባቦ ጋምቤልን በመሳሰሉ ወረዳዎች በወባ ወረርሽኝ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፡፡
ከጤና ተቋማት በተገኘ መረጃ መሰረት በምዕራቡ የኦሮሚያ ክፍል በ16 ዞኖች ሥር በሚገኙ 117 ወረዳዎች፣ በቄለም ወለጋ ሥር በሚገኙ 12 ወረዳዎች እንዲሁም፤ በ7 ሰባት ከተማ መስተዳድሮች በሽታው በወረርሽኝ ደረጃ መኖሩን አረጋግጫለሁ ሲል ኦነግ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
በተለይም በቤጊ እና ቆንዳላ ወረዳዎች በ36 ቀበሌዎች ከሚኖሩ 345 ሺሕ በላይ ሰዎች መካከል በቆንዳላ ወረዳ ከ36 ሺሕ በላይ የሚሆኑት በበሽታ እና በረሃብ እየተሰቃዩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
በተመሳይይ "በቤጊ ወረዳ በበሽታ እና በረሃብ ከ 86 ሺሕ በላይ ሰዎች መጠቃታቸውን ከተለያዩ ምንጮች አጣርቻለሁ።" ብሏል፡፡
"አሁን ባለው ተጨባጭ ኹኔታ በእነዚህ ወረዳዎች በቀን እስከ 1 መቶ ሰው በረሃብ እና በበሽታ እንደሚሞት እና በአንድ መቃብር ከሦስት እስከ አራት ሰው እንደሚቀበር ከነዋሪዎች አረጋግጫለሁ።" በማለት በመግለጫው አካቷል፡፡
በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለተጎጂዎች ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች በቀጠናው ባለው ግጭት ምክንያት አካባቢውን ሙሉ ለሙሉ ለቀው መውጣታውን ያወሳው ኦነግ፤ ይህም ችግሩን የበለጠ ውስብስብ አድርጎታል ብሏል፡፡
በመሆኑም ምግባረ ሠናይ ተቋማት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ወገኖች እንዲሁም ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ለእነዚህ ተጎጂዎች ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው እና ድምጽ እንዲሆኗቸው ግንባሩ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
Via Addis Maleda

👍31❤10👎3
በመዲናዋ የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደረጉ!
በአዲስ አበባ ከተማ ቅዳሜ መስከረም 26/2016 የሚከበረው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።
በዓሉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የገለጸው ፖሊስ፤ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀሙም አሳስቧል፡፡
በዚህም መሰረት ከአርብ መስከረም 24/2016 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በዓሉ ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ፦
- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ
- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 22 ማዞሪያ
- ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መስቀለኛ ወይም ወዳጅነት ፓርክ
- ከፒያሳ በቸርቸር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ
- ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
- ከጀሞ በትንባሆ ሞኖፖል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
- ከቄራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቡልጋርያ ማዞሪያ
- በአዲሱ መንገድ ከቄራ በቂርቆስ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ታቦት ማደሪያ
- ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎተራ ማሳለጫ
- ከቦሌ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ አትላስ ሆቴል አካባቢ
- ከአዋሬ ወደ ካሳንቺዝ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ
- ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ ፖሊስ አካባቢ
- ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ አምስተኛ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ
- ከመርካቶ በራስ ቴአትር ወደ ጎማ ቁጠባ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ ያሉት መንገዶች፤ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እንዲሁም 011-1-26- 43-59፣ 011- 5- 52- 63-02/03 ፣ 011-542-40-77፣ 011-5-54-36-81 የስልክ መስመሮች መጠቀም እንደሚችልም ፖሊስ አስታውቋል።

👎58👍35❤8
ዛሬ የሚደረጉ የዩሮፓ ሊግ እና ኮንፈረንስ ሊግ የተመረጡ ጨዋታዎች የቤቲንግ ግምትና መረጃዎች
አስቶንቪላ፣ ዌስትሃም፣ ሌቨርኩዘን፣ ፌኔርባቼ፣ አልክማር እና ክለብ ብሩጅን የተመለከቱ የቤቲንግ መረጃዎች እና ግምቶች በቤትስኬት
ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ👇👇
http://www.betsket.com/ዛሬ-የሚደረጉ-የዩሮፓ-ሊግ-እና-ኮንፈረንስ/
ሁል ጊዜ የሚለቀቁ መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👉 @betskett

👍7❤3
በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት በሻማ በተነሳ የእሳት አደጋ 3.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድመ!
በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት ከቀኑ 6 ሰዓት ከ20 ገዳማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 መሿለኪያ ጤና ጣቢያ አካባቢ በአንድ ቪላ መኖሪያ ቤት ላይ የተነሳው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የእሳት አደጋዉ በአንድ ግለሰብ ቪላ መኖሪያ ቤት ላይ የደረሰ ሲሆን በእሳት አደጋዉ 3.5 ሚሊየን የሚገመት ንብረት መውደሙን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።የእሳት አደጋዉ የተነሳዉ በቤት ዉስጥ ተለኩሶ በተረሳ ሻማ ምክንያት ነው።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አራት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ከ29 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ተሰማርተዋል። አደጋዉን ለመቆጣጠር በተደረገ ጥረት በአቅራቢያዉ ባሉ ህንጻዎች ሳይዛመት በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለ ሲሆን በዚህ ሂደት 150 ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት ማዳን ተችሏል።
በእሳት አደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።
[ዳጉ ጆርናል/ብስራት ሬድዮ]

👍31❤7😭3
በአቃቂ ቃሊቲ የውሃ ማሞቂያ ፈንድቶ የሦስት ሰዎች ሕይዎት አለፈ!
በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የውሃ ማሞቂያ ፈንድቶ የሦስት ሰዎች ሕይዎት ማለፉ ተሰማ፡፡
አደጋው የተፈጠረው ዛሬ ከቀኑ 10:35 ሲሆን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የቀድሞ አቃቂ ጨረቃ ጨርቅ ጊቢ ዉስጥ በሚገኝ ሶሻል ሳሙናና ኘላስቲክ ፋብሪካ ዉስጥ ነው፡፡
በአደጋው የዉሃ ማሞቂያ ቦይለር ፈንድቶ የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፥ ለጊዜዉ ቁጥራቸዉ ያልታወቀ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።
Via FBC

😭59👍33❤6👎3
መርጌታ ላቀው የባህል መድህኒት ፈውስ እና ጥበብ ይ በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 0915968136
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
☟☟☟☟☟ ☟☟☟☟☟
☞ ለመፍትሄ ሀብት
☞ ለህመም
☞ ለሁሉ ሠናይ
☞ ቡዳ ለበላው
☞ ለገበያ
☞ ሚስጥር የሚነግር
☞ ለቀለም(ለትምህርት)
☞ ለመፍትሔ ስራይ
☞ ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ
☞ ሌባ የማያስነካ
☞ ለበረከት
☞ ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
☞ ለግርማ ሞገስ
☞ መርበቡተ ሰለሞን
☞ ለዓይነ ጥላ
☞ ለመክስት
☞ ጸሎተ ዕለታት
☞ ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
☞ ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
☞ ለትዳር
☞ ለድምፅ
ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ
ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
☎ 0915968136
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
☟☟☟☟☟ ☟☟☟☟☟
☞ ለመፍትሄ ሀብት
☞ ለህመም
☞ ለሁሉ ሠናይ
☞ ቡዳ ለበላው
☞ ለገበያ
☞ ሚስጥር የሚነግር
☞ ለቀለም(ለትምህርት)
☞ ለመፍትሔ ስራይ
☞ ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ
☞ ሌባ የማያስነካ
☞ ለበረከት
☞ ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
☞ ለግርማ ሞገስ
☞ መርበቡተ ሰለሞን
☞ ለዓይነ ጥላ
☞ ለመክስት
☞ ጸሎተ ዕለታት
☞ ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
☞ ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
☞ ለትዳር
☞ ለድምፅ
ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ
ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
☎ 0915968136
👍9👎5❤3
⚡️ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመራቂዎች : ለ12ኛ ክፍል ፡ ህልምዎ በግሎብዶክ ይጀምራል! እድሎ በቅርብ ርቀት ላይ ናቸው፣ ከእኛ ጋር አስደሳች እድሎችን ይጠቀሙ።
ወደ ህልምዎ እና ከፍተኛ ትምህርትዎ ቀጣዩን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነዎት❓
Join us here:
🔻Telegram: t.me/GlobeDockConsultancy
🔻TikTok: https://www.tiktok.com/@globedockedu
📞 +251969959595 or +251942202070

👍28❤5🔥2
ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ያቋረጠችውን የምግብ ርዳታ ሥርጭት ልትጀምር ነው!
ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ አቋርጣው የነበረውን የርዳታ ምግብ የማከፋፈል ሥራ አንድ እንደምትጀምር ዛሬ አስታወቀች። ርዳታውን፣ አንድ ሚሊዮን ለሚደርሱ ተረጂዎች ብቻ በማደል እንደሚጀመር፣ ዩናይትድ ስቴትስ ገልጻለች፡፡
ይህም ኾኖ የምግብ ርዳታው፣ በተቀነባበረ መንገድ ከታለመለት ዓላማ ውጭ መዋሉ መረጋገጡን ተከትሎ ዕደላው በተቋረጠባቸው አብዛኞቹ አካባቢዎች፣ አሁንም እንደማይቀጥል ታውቋል።የርዳታ ምግብ ዕደላው በፍጥነት የሚጀመረው፥ ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከሶማሊያ እና ከኤርትራ ተሰደው በኢትዮጵያ በሚገኙት 28 የስደተኛ ካምፖች ውስጥ ለተጠለሉ ስደተኞች እንደኾነ፣ ዩናይትድ ስቴትስ አመልክታለች።
በትግራይ ክልል ለሁለት ዓመታት ከተካሔደው አሠቃቂ ጦርነት በማገገም ላይ በሚገኙት አካባቢዎች ይሰጥ የነበረው የምግብ ርዳታ፣ ከታለመለት ዓላማ ውጭ የሚውልበትን አሠራር ለማስቆም የሚያስችሉ ርምጃዎች ተግባራዊ ማድረግ እስኪቻል ድረስ እንደተቋረጠ እንደሚቆይ ተገልጿል።“የምግብ ዋስትና ችግር ላለባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች የምናደርገው ድጋፍ፣ ለታለመላቸው ተጠቃሚዎች ብቻ እንደሚደርስ ማረጋገጫ እስክናገኝ ድረስ እንደተቋረጠ ይገኛል፤" ሲሉ፣ የዩናይትድ ስቴትሷ የዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት ቃል አቀባይ ጄሲካ ጄኒን ተናግረዋል።
"ድርጅቱ ቅድሚያ የሚሰጠው፣ በሁሉም ክልሎች ለተቸገሩ ወገኖች በተቻለ ፍጥነት የምግብ ርዳታ እደላውን ማስቀጠል ነው። በመኾኑም፣ አስተማማኝ የአሠራር ለውጥ ተግባራዊ እንደተደረገ ሥራውን ለመጀመር ዝግጁ ነን፤" ብለዋል።የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ በተመሳሳይ ምክንያት ከአራት ወራት በፊት አቋርጦት የነበረውን የምግብ ርዳታ ዕደላ፣ ቀስ በቀስ መጀመሩን ከዚኽ ቀደም ማስታወቁን መዘገባችን አይዘነጋም። በአንዳንድ ቦታዎች በአነስተኛ መጠን ርዳታ በማከፋፈል ላይ እንደኾነ የገለጸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ መንግሥት፣ አሁንም በሒደቱ ውስጥ ሚና አለው፤ ብሏል።
Via VoA

👍32❤4👎2
‹‹መንግሥት በምክክር ሂደቱ የሚደረስባቸውን መግባባቶች ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ነግሮኛል›› - ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ‹‹ መንግሥት በምክክር ሂደቱ የሚደረስባቸውን መግባባቶች ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቆኛል ›› ሲል መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጠውና ለአሻም በላከላት መግለጫ አመልክቷል፡፡ኮሚሽኑ በሳምንቱ ውስጥ አካነውኛቸዋለሁ ያላቸውን አራት አቤይት ተግባራት በዙሁ መግለጫው ዘርዝሯል፡፡
የሳምንቱ የኮሚሽኑ ቀዳሚ ስራ በመሆን በመግለጫው ላይ የተቀመጠው የተሳታፊዎች ልየታን በተመለከተ ያከናወናቸውና ሊያከናውናቸው ያቀዳቸውን የዘረዘረበት ነው፡፡በዚሁም ‹‹ በአፋር እና በኦሮሚያ ክልሎች ተሳተፊዎችን በመለየት ሂደት ከኮሚሽኑ ጋር በቅንጅት የሚሰሩ ተባባሪ አካላትን በመለየት ስልጠና ለመስጠት ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ›› ገልፆ
‹‹በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያም የውክልና ሂደቱ ባልጠናቀቀበት የደቡብ ኦሞ ዞን የማጠቃለያ ስራ ለመስራት ባለሙያዎቹ ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ›› ይፋ አድርጓል፡፡‹‹በተመሳሳይ በሶማሌ፣ በአማራ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ እንዲሁም በትግራይ ክልል ሂደቱን ለማከናወን የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን እያከናወነ ይገኛል ›› ብሏል፡፡
ኮሚሽኑ በሳምንቱ አከናውንሁት ያለው ሌላኛው ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ጨምሮ ከከፍተኛ የፌደራሉ መንግስት የሥራ ሃለፊዎች ጋር ያደረገውን ውይይት ነው፡፡
በውይይቱ ‹‹ መንግስት እንደ አንድ የምክክሩ ሂደት ባለድርሻ አካል የኮሚሽኑን ገለልተኝነትና ነጻነት በጠበቀ መልኩ እስካሁን ሲያደርጋቸው የነበሩ ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያረጋገጠበት ነው ›› ሲል አድንቋል፡፡ኮሚሽኑ ከወጣቶች ማህበራት እና በወጣቶች ላይ ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል የሴቶች ጥምረት ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት ያደራቸው ውይይቶች የኮሚሽኑ ሦስትና አራተኛ የሳምንቱ ክንውን መሆናቸውን ከመግለጫው መረዳት ተችሏል።፡፡
Via Asham

👎28👍23🔥5❤3😭2
በሱሉልታ ከተማ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች 9 ሰዎችን አግተው መውሰዳቸው ተሰማ
ታጣቂዎቹ ለእያንዳንዱ ታጋች 300 ሺሕ ብር ጠይቀዋል
አርብ መስከረም 25 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል አዲስ በተዋቀረው ሸገር ከተማ ሱሉልታ ክፍለ ከተማ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው እና በመንግሥት “ኦነግ ሸኔ” ተብሎ በአሸባሪነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡድን፤ ከሱሉልታ ከተማ 9 ሰዎችን አፍኖ መውሰዱን የአካባው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ፡፡
ታጣቂ ቡድኑ ድርጊቱን የፈጸመው ማክሰኞ መስከረም 22/2016 በከተማ መስተዳድሩ በተለምዶ አዲሱ ኬላ ወጥም ቆዳ ፋብሪካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደሆነ ነዋሪዎቹ አውስተዋል፡፡
ታጣቂ ቡድኑ ወደ ስፍራ ያቀናው መስከረም 22 ለ23 አጥቢያ ሌሊት ስድስት ሰዓት አካባቢ እንደሆነ የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ እስካሁን ድረስ ቁጥራቸው 9 መሆኑ የተረጋገጠ ሰዎችን ወደ ቤታቸው ዘልቆ በመግባት አፍኖ መውሰዱን አስረድተዋል፡፡
በሰዓቱ በአካባው ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበርም በመግለጽ፤ ይሁንና የታፈኑትን ሰዎች ማስጣል እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡
ለነዚሁ ለተወሰዱ ሰዎች ለእያንዳንዳቸው 300 ሺሕ ብር መጠየቃቸውን እና ቤተሰብ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንዳሉ የአካባቢው ነዋሪዎች አውስተዋል፡፡
የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በእነዚህ ሰዎች የእጅ ስልክ እና በሌሎችም ላይ እየደወሉ “ይህን ያህል ብር ካላዘጋጃችሁ እንመጣላችኋለን” ብለው ያስፈራሩ እንደነበር እና ይህንኑ በተግባር እንደፈጸሙት ተናግረዋል፡፡
ነዋሪዎቹ አክለው እንደተናገሩት “የሱሉልታ ከተማ ከአገሪቱ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ በ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ቢሆንም፤ ታጣቂ ቡድኑ በዚህ ልክ ወደ ከተማው እየገባ የሚፈልገውን አፍኖ ሲወስድ ማየት ግራ የሚያጋባ ጉዳይ እንደሆነባቸው ገልጸዋል፡፡
የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ድርጊቱን ከሚፈጽሙበት በቅርብ ርቀት ላይ “ሚዛን” በሚባል አካባቢ የአገር መከላከያ ሠራዊት ካምፕ እንዳለ የተነገረ ሲሆን፤ ሆኖም በተደጋጋሚ መሰል ተግባራት ሲፈጸሙ ምንም አይነት የተወሰደ እርምጃ አለመኖሩንም ተናግረዋል፡፡
እነዚሁ ታጣቂዎች ከዚህ ቀደም በዚሁ በሱሉልታ ክፍለ ከተማ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አካባቢ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ በመግባት፤ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችን ወስደው መሰወራቸውን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል፡፡
አዲስ ማለዳም ጉዳዩን ለማጣራት የሱሉልታ ክፍለ ከተማ የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ ወደ ሆኑት ታገል መለሠ በተደጋጋሚ ብትደውልም፤ ስልክ ሊያነሱ ባለመቻላቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም::
Via:-Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa

😭35👍28❤7👎4🔥3
ሩሲያ በኑክሌር ኃይል ሚሠራ አዲስ ተወንጫፊ ሚሳኤል በተሳካ ሁኔታ መሞከሯን አስታወቀች!
ሩሲያ በኑክሌር ኃይል የሚሠራ አዲስ የተወንጫፊ ሚሳኤል “የመጨረሻ ስኬታማ ሙከራ” ማድረጓን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስታወቁ።ከአምስት ዓመት በፊት በሙከራ ደረጃ ላይ መሆኑ ሲገለጽ የነበረው ይህ ተወንጫፊ ሚሳኤል፣ ያልተገደበ ርቀት ተጉዞ ጥቃት ማድረስ የሚችል መሆኑ ተነግሮለታል።
ነገር ግን የጦር መሳሪያው ያለው ብቃት ምን እንደሆነ በይፋ የሚታወቀው የተወሰነ ነገር ነው። ከዚህ ቀደም የተደረጉ ሙከራዎች ከሽፈው እንደነበር ሪፖርቶች ያመለክታሉ።አዲሱን ሚሳኤል በተመለከተ ፕሬዝዳንት ፑቲን አሁን ይፋ ያደረጉት መረጃ በገለልተኛ ወገን ያልተረጋገጠ እና የሩሲያም መከላከያ ሚኒስቴርም ምንም አይነት መግለጫ ያለስጠበት ነው።
በዚህ የመስከረም ወር የወጡ የሳተላይት መስሎች እንደሚያሳዩት ግን ሶቪየት ኅብረት የኑክሌር መከራ ታደርግበት በነበረው የአርክቲክ ደሴት ላይ ሩሲያ አዲስ የኑክሌር የሙከራ ማዕከል መገንባቷን አመልክተዋል።“ከጥቂት ዓመታት በፊት ባሳወቅኩት መሠረት አሁን ዘመናዊ ስልታዊ የጦር መሳሪያ አይነቶችን የመገንባት ሥራችንን አጠናቀናል” ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን በጥቁር ባሕር የመዝናኛ ከተማ ከተማ ሶቺ በተደረገ ስብሰባ በቀጥታ በቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግራቸው ይፋ አድርገዋል።
ፑቲን ጨምረውም በኑክሌር ኃይል የሚሠራው እና በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኝን ኢላማ ሊመታ ይችላል ያሉት “ቡሬቬስተኒከ” የተባለው ይህ እጅግ ዘመናዊ ሚሳኤል “የመጨረሻ እና የተሳካ ሙከራ ተደርጓል” ብለዋል።
Via BBC

👍39❤3🔥3👎1
በግብአት እጥረት ምክንያት በዶሮና እንቁላል ምርቶች ላይ የአቅርቦት እጥረት ችግር መኖሩ ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ ሚሊዮን ከግብአት እጥረት ጋር ተያይዞ የተወሰነ የዶሮና የእንቁላል አቅርቦት ችግር መኖሩን ተናግረዋል፡፡ በዚህ የተነሳ የዶሮና የእንቁላል ዋጋ በፊት ከነበረው አንጻር ከፍ ያለበት ሁኔታ እንዳለም አንስተዋል፡፡
የግብአት አቅርቦት ችግር የሚስተዋለው በዋናነት ጫጩቶችን ለማስፈልፈል የሚሆኑ የመስራች ዶሮዎች ዝርያ ክምችት ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ጫጩቶች ከሌሉ ደግሞ የእንቁላልም ሆነ የስጋ ዶሮ ማድረስ እንደማይቻል ነው የተናገሩት፡፡ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ደግሞ ለግብአት አቅርቦት ችግሩ መንስኤ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡በግብርና ሚኒስቴር የዶሮ ሃብት ልማት ዴስክ ኃላፊ አቶ ዮናታን ዘውዴ በበኩላቸው የዶሮና እንቁላል ምርት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢመጣም ህብረተሰቡ መግዛት ከሚችልበት አቅም ጋር ሲነጻጸር በቂ አቅርቦት አለ ለማለት እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡
ዶሮና እንቁላልን ለማምረት በግብአትነት የሚያገለግሉ ምርቶች ውድነት በገበያ ውስጥ የዶሮና እንቁላል ዋጋ ከፍ እንዲል ማድረጉንም አንስተው ቅድመ መስራችና መስራች የዶሮ ዝርያ በበቂ ሁኔታ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡የህብረተሰቡ ዶሮና እንቁላል ተጠቃሚነትንም በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ በፍላጎቱ ልክና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ ብዙ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡
[Ahadu]

👍24😭2
በተመድ የሰብአዊ መብት ቡድን የሥራ ዘመን ማብቃት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ቅሬታውን ገለጸ!
የተመድ የሰብአዊ መብት ም/ቤት፣ ለኢትዮጵያ ያቋቋመው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሞያተኞች ቡድን የሥራ ዘመን ሳይራዘም በመቅረቱ፣ የም/ቤቱ አባል ሀገራት፥ ሰለባዎች ፍትሕ ለማግኘት ያላቸውን አንድያ ተስፋ እንዲጨልም አድርገዋል፤ ሲል፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ቅሬታውን ገልጿል።
የም/ቤቱ አባል ሀገራት፣ በኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ወቅት የተፈጸሙ ጥሰቶችን የሚያጣራው ብቸኛ ገለልተኛ ተቋም የሥራ ጊዜው እንዲያከትም አድርገዋል፤ ሲል፣ የሰብአዊ መብት ቡድኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።የባለሞያዎቹ ቡድን ሥራ እንዳይቀጥል የተደረገው፣ በኢትዮጵያ “ተጨማሪ ሠቆቃዎች የመፈጸም ዕድላቸው ሰፊ ነው፤” በማለት ቡድኑ እያሳሰበ ባለበት ወቅት ነው፤ ሲል አክሏል አምነስቲ።
የምክር ቤቱ አባላት፣ የባለሞያዎቹን ቡድን የሥራ ዘመን ሳያድሱ፣ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ እንዲያከትም በመወሰናቸው፣ በኢትዮጵያ በመፈጸም ላይ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዳላየ አልፈዋል፤ ሲል አምነስቲ ወቅሷል።የሥራ ዘመኑ ሳይታደስ በመቅረቱ፣ ቡድኑ ሥራውን እንዲያቆም ይገደዳል።የባለሞያዎቹ ቡድን ባለፈው ማክሰኞ በሰጠው መግለጫ፣ “ወደፊት ግፍ የመፈጸም ዕድል በመኖሩ፣ በኢትዮጵያ ተጨማሪ ገለልተኛ ምርመራ መደረጉ አስፈላጊ ነው፤” ሲል አስጠንቅቋል።
በትግራይ ክልል፣ “ከባድ እና እየቀጠለ ያለ” ግፍ በመፈጸም ላይ እንደኾነ፣ ባለፈው ወር ያስታወቀው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የምርመራ ቡድን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ተጠያቂነትን ለማስፈን ያለውን ቁርጠኝነት አስመልክቶ ጥያቄ አንሥቷል። የተፈጸሙ ጥሰቶችን መመርመር እንደተሳነው፣ እንዲሁም “የሽግግር ፍትሕ ምክክር የሚል፣ ጉድለት የሚታይበት ሒደት በማከናወን ላይ ይገኛል፤” ሲል፣ ቡድኑ ቅሬታውን ገልጾ ነበር።በኢትዮጵያ ያለው ኹኔታ እንደሚያሳስባቸውና ወደፊት ግፍ ሊፈጸም እንደሚችል አመልካቾች መኖራቸውን፣ የቡድኑ አባላት አስታውቀዋል።

👍30❤1