YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ1 ማይል የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ ክብረ-ወሰን በመያዝ አሸነፈች!

በላቲቪያ ሪጋ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው በ1 ማይል የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት ድርቤ ወልተጂ 4 ደቂቃ ከ21 ሰኮንድ በመግባት አዲስ ክብረ-ወሰን በማስመዝገብ አሸንፋለች፡፡

በርቀቱ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡

በውድድሩ ተጠባቂ የነበረችው ኬኒያዊቷ አትሌት ፌይዝ ኪፒዬጎ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍6313👎4🔥1😭1
መርጌታ ላቀው የባህል መድህኒት ፈውስ እና ጥበብ ይ በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን  0915968136
                

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
☟☟☟☟☟ ☟☟☟☟☟

☞  ለመፍትሄ ሀብት
☞  ለህመም
☞  ለሁሉ ሠናይ
☞  ቡዳ ለበላው
☞  ለገበያ
☞  ሚስጥር የሚነግር
☞  ለቀለም(ለትምህርት)
☞  ለመፍትሔ ስራይ
☞  ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ
☞  ሌባ የማያስነካ
☞  ለበረከት
☞  ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
☞  ለግርማ ሞገስ
☞  መርበቡተ ሰለሞን
☞  ለዓይነ ጥላ
☞  ለመክስት
☞  ጸሎተ ዕለታት
☞  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
☞  ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
☞  ለትዳር
☞  ለድምፅ

ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ


ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
0915968136
 
👍13👎137
አትሌቶች ከሰአት አቅጣጫ በተቃራኒው   የሩጫ ሜዳ   ላይ የሚሮጡት ለምንድን ነው?


  በተቃራኒ ሰዓት አቅጣጫ ስንሮጥ ሴንትሪፉጋል ሃይል በሰውነታችን ላይ ከግራ ወደ ቀኝ ይሰራል።  በሰዓት አቅጣጫ ስንሮጥ ደግሞ  ከቀኝ ወደ ግራ ነው ይሰራል።  በዚህ ኃይል ምክንያት የሚጎዳው የሰውነታችን ክፍል  "የላይኛው  ቬና ካቫ "ነው።

   መልስ አንድ *
📌የላይኛው  ቬና ካቫ የደም ሥር ሲሆን ከሰውነት ግማሽ ክፍል  ወደ   ደምን መጦ ወደ ሚገፋው ልብ ድረስ ያልተጣራ  ደም ሰብስቦ ያደርሳል። 

*  የላይኛው ቬና ካቫ ትልቁ የደም ሥር ነው።  ይህ የደም ሥር ደም ከግራ ወደ ቀኝ ይሸከማል።በሰዓት አቅጣጫ ተቃራኒ ስንሮጥ  ምክንያት ሴንትሪፉጋል ሃይል ደም  ለመምጠጥ ይረዳዋል  ።የደም ፍሰትም ጥሩ ይሆናል።  ነገር ግን በሰዓት አቅጣጫ መሮጥ  የደም ፍሰት ይቀንሳል። ጤናም ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

መልስ ሁለት *
እ.ኤ.አ. በ 1896 የመጀመሪያው ዘመናዊ የኦሎምፒክ ጨዋታዎች በአቴንስ ፣ ግሪክ ተካሂዷል ።  በዚህ  ውድድር ሯጮቹ በሰዓት አቅጣጫ እንዲሮጡ ተደርጓል።  ይህም ከአትሌቶቹ ብዙ ቅሬታ ቀርቦበታል።  በነዚህ ቅሬታዎች ምክንያት ነው አይኦሲ በ1913 ተሰብስቦ የአሁኑን በተቃራኒ ሰዓት አቅጣጫ  ሩጫ እንዲካሄድ የተስማማው ።   በተቃራኒ ሰዓት አቅጣጫ ስንሮጥ   በተፈጥሮ ውስጥ ያለው ሁሉም ነገር በተቃራኒ ሰዓት አቅጣጫ ወደ እንቅስቃሴ ይሄዳል ። 

ተመልካች ሯጮቹን ስንከታተል ዓይኖቻችን ከግራ ወደ ቀኝ ሲንቀሳቀሱ በደንብ ማስተዋል ይችላል።።  የሰው አካል በልብ ምክንያት ከቀኝ  በኩል ትንሽ ይከብዳል እና በተቃራኒ ሰዓት አቅጣጫ ሲሮጥ ሰውነቱ በትንሹ ወደ ግራ ማዘንበል ይጀምራል።

[Fidelpost]
@YeneTube @FikerAssefa
👍255🔥1
የመንግሥት ኃይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች ትናንት በላሊበላ ከተማ አቅራቢያ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ ማካሄዳቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎች መስማቱን ጠቅሶ ዶይቸቨለ ዘግቧል።

የኹለቱ ወገኖች ግጭት የተካሄደው፣ ከላሊበላ 32 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በብልብላ ጊዮርጊስ ቀበሌ እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል። ግጭቱን ተከትሎ፣ በላሊበላ ከተማ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ዝግ ኾነው እንደዋሉ የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍24😭4👎31
‹‹ ፓርቲው ውስጥ የማይነካም ሆነ የማይተካ አባልም ሆነ አመራር የለም ››- ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ(ኢዜማ) የፓርቲውን ሊቀመንበር ጫኔ ከበደን በተመለከተ መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.መ ባወጣው መግለጫ ‹‹ ኢዜማ ውስጥ የማይነካም ሆነ የማይተካ አባልም ሆነ አመራር የለም›› ብሏል፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር በቁጥጥር ስር የዋሉት በፓርቲው ውስጥ ‹‹ ባላቸው ኃላፊነት ሳይሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በኮማንድ ፖስቱ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ መሆኑን መረጃዎች ›› አግኝቼያለሁ ባይ ነው፡፡

ኢዜማ አገኘሁት ካለው መረጃ በኋላ የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም አደርጎታል ባለው አስቸኳይ ስብሰባ በጉዳያ ላይ መወያየቱን አመልክቷል፡፡

‹‹ በመርህም ሆነ በተግባር በዜግነት የፖለቲካ አስተሳሰብ እና በፀና የሰላማዊ ትግል መስመር የሚያምን፣ ይህንኑ መርኅ ብቻ ተከትሎ የምሥራ ›› ድርጅት ነኝ የሚለው ኢዜማ ‹‹ በማንኛውም ዓይነት ሁኔታ በዘውግ ተኮር የፖለቲካ እንቅስቃሴም ሆነ በኃይል መንግሥታዊ ሥልጣን ለመያዝ በሚደረግ ትግል ውስጥ ፈጽሞ አልሳተፍም ›› ሲል በመግለጫውይፋ አድርጓል፡፡

የፓርቲው መግለጫ ሲቀጥል ‹‹ ኢዜማዊነት በምንም መንገድ ሁለት የማይታረቁ ሃሳቦችን እያጣቀሱ መሄድን የማይፈቀድ እንደሆነ መላው አባላቱ፤ እንደዚሁም በክብር፣ በነፃነት እና በእኩልነት የመኖር ዋስትና እንዲረጋገጥለት ዘወትር የምታገልለት ›› ሲል የጠራው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይወቅልኝ ሲል ጥሪ አቀርቧል፡፡

ኢዜማዊያን ሲል ለጠራቸው አካላት ባስተላለፈው ‹‹ ይህን በውል በመገንዘብ ከሰላማዊ ትግል እና ከዜግነት ፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውጭ ያለን የፖለቲካ እንቅስቃሴ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ መደገፍ፣ የሀሳብም ሆነ የተግባር ተሳትፎም ሆነ ትብብር ማድረግ ከኢዜማዊነት መርኅ ማፈንገጥ መሆኑን ለማስገንዘብ ›› እወዳለሁ ብሏል፡፡

‹‹ በቁጥጥር ስር የሚገኙት የፓርቲው ሊቀመንበር ጫኔ ከበደ ጉዳይም በዚሁ መርሕ የሚታይ ነው ›› ያለው ኢዜማ ሊቀመንበሩ በግልፅና በውል ከሰላማዊና ከኢዜማ መርሕ ውጪ ስለመንቀሳቀስ/አለመንቀሳቀሳቸው ያለው ነገር የለም፡፡

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
👎37👍207🔥2
ለ1977ቱ የኢትዮጵያ ረሃብ እርዳታ ማሰባሰቢያ የነበረው ሙዚቃ ወደ መድረክ ሊመጣ ነው!

በኢትዮጵያ ለተከሰተው የ1977ቱ አስከፊ ረሃብ እርዳታ እንዲውል በገንዘብ ማሰባሰቢያነት ከ38 ዓመታት በፊት የተዘጋጀው የሙዚቃ ዝግጅት ዳግም ወደ መድረክ ሊመጣ ነው።‘ላይቭ ኤይድ’ የሚል ስያሜ የተሰጠው እና በርካታ ሙዚቀኞችን ያሰባሰበው የሙዚቃ ዝግጅት በዝነኛነቱ አሁንም ዓለማችን ከምታወሳቸው አንዱ ነው።

በቀጥታ የተላለፈው የሙዚቃ ዝግጅትም ተዘጋጅቶ በመድረክ ሙዚቃነት በሚቀጥለው ዓመት በለንደን ይቀርባል።የመጀመሪያው የሙዚቃ ዝግጅት በአውሮፓውያኑ ሐምሌ 13/1985 በዌምብሌይ ስታዲየም የቀረበ ነው።ታዋቂው ሙዚቀኛ ቦብ ጌልዶፍ እና ሚጅ ዩሬ ናቸው ከ38 ዓመታት በፊት የነበረውን ኮንሰርት ያዘጋጁት።

‘ጀስት ፎር ዋን ደይ’ በሚል ስያሜ ወደ መድረክ የሚመለሰው ይህ የሙዚቃ ቅንብር ኩዊን፣ ሰር ኤልተን ጆን፣ ሰር ፖል ማካርቲኒ እና ስቲንግ የተጫወቷቸው ዘፈኖችን አካቷል።በለንደን ኦልድ ቪክ ቲያትር ከጥር አጋማሽ እስከ መጋቢት የሚቀርብም ይሆናል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍26😭61
በሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት ለህወሓት ተሰልፈዉ ህይወታቸዉ ላለፉ ታጣቂ ቤተሰቦች በጥቅምት መጀመሪያ መርዶ መነገር ይጀመራል ተባለ

በጥቅምት ወር መጀመርያ ክልላዊ የሀዘን ቀን በትግራይ አንደሚታወጅ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንትና የካቢኔ ሴክረቴርያት የሰላምና ፀጥታ ሓላፊው ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ተናግረዋል።

ሓላፊው በዛሬው እለት በትግራይ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ለሁለት ዓመት ገደማ በተካሄደው ጦርነት መስዋእት የሆኑት ታጋዮች መርዶ በሚመጣው ጥቅምት ወር በይፋ እንደሚነገርና በየእያንዳናዳቸው ቤት መስዋእትነታቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ለቤተሰቦቻቸው እንዲደርስ እንደሚደረግ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

በተላያዩ የማህበራዊ መገናኛ መንገዶች ወላጆች የልጆቻቸውን በህይወት መኖርና አለመኖር ለማወቅ በሚሞክሩበት ወቅት ገንዘብ ከመጠየቅ ጀምሮ የተለያዩ ችግሮች እየገጠሙዋቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገለፅ የነበረ ሲሆን ፤ ሓላፊውም ወላጆች የልጆቻቸውን ሁኔታ ለማወቅ መንገላታት አይገባቸውም ብለዋል።

አያይዘዉም የተለያዩ ደላላዎች በሰማእታቱ ስም ንግድ ጀምረዋል ያሉ ሲሆን ለወላጆች የሰማእት የልጆቻቸውን ሁኔታ ማሳወቅ የኛ ሀላፊነት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በመጨረሻም አሁን በየአከባቢው እየተደረገ ያለው መርዶ የመንገር ሂደት ግምታዊና ክብራቸውን የማይመጥን ነው ያሉ ሲሆን ህዝቡ ይፋዊ በሆነ መልኩ እስኪነገረው ድረስ አንዲጠብቅ ማሰሰባቸውን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።


Via:-ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
👍37😭268👎5
መርጌታ ላቀው የባህል መድህኒት ፈውስ እና ጥበብ ይ በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን  0915968136
                

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
☟☟☟☟☟ ☟☟☟☟☟

☞  ለመፍትሄ ሀብት
☞  ለህመም
☞  ለሁሉ ሠናይ
☞  ቡዳ ለበላው
☞  ለገበያ
☞  ሚስጥር የሚነግር
☞  ለቀለም(ለትምህርት)
☞  ለመፍትሔ ስራይ
☞  ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ
☞  ሌባ የማያስነካ
☞  ለበረከት
☞  ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
☞  ለግርማ ሞገስ
☞  መርበቡተ ሰለሞን
☞  ለዓይነ ጥላ
☞  ለመክስት
☞  ጸሎተ ዕለታት
☞  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
☞  ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
☞  ለትዳር
☞  ለድምፅ

ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ


ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
0915968136
 
👍8👎83😭1
አቶ አህመድ ሽዴ ከአውሮፓ ሕብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ጋር ተወያዩ!

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከአውሮፓ ሕብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ጋር ተወያይተዋል።በአውሮፓ ሕብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።

በዛሬው ዕለትም ከገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ጋር በሁለትዮሽ ትብብርና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።የኢትዮጵያና የአውሮፓ ሕብረትን ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም የሚመክሩ ይሆናል።

የአውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ የ650 ሚሊየን ዩሮ ዓመታዊ የባለብዙ ዘርፍ የድጋፍ መርሐ-ግብርም ዛሬ ከሰዓት በኋላ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን በቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ ከአፍሪካ ሕብረት ከፍተኛ አመራሮችና ቀጣናዊ ልዑካን ጋር ይወያያሉ መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍171👎1
YeneTube
አቶ አህመድ ሽዴ ከአውሮፓ ሕብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ጋር ተወያዩ! የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከአውሮፓ ሕብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ጋር ተወያይተዋል።በአውሮፓ ሕብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል። በዛሬው ዕለትም ከገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ…
#update

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ መንግስት መስጠት ያቋረጠውን ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍ ለመቀጠል፤ አሁንም መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ አስታወቀ።

ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ወደ ነበረበት ለመመለስ “የደረጃ በደረጃ አካሄድን” እንደሚከተል ገልጿል።ሃያ ሰባት አባል ሀገራትን በስሩ ያቀፈውን የአውሮፓ ህብረትን አቋም ያሳወቁት፤ የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ዩታ ኡርፒላይነን ናቸው። ኮሚሽነሯ ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ጋር ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 22፤ 2016 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል ውይይት ካደረጉ በኋላ፤ የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን አሁንም እንደ “ስትራቴጂካዊ አጋር” እንደሚመለከታት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የአውሮፓ ህብረት እና የኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነት፤ በጥቅምት 2013 በትግራይ ክልል ከተቀሰቀሰው ጦርነት ወዲህ ተቀዛቅዞ ቆይቷል። ህብረቱ በጦርነቱ ምክንያት ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠውን 90 ሚሊዮን ዩሮ ከሚጠጋው የበጀት ድጋፍ ማገዱ ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ በተመሳሳይ ምክንያት ለኢትዮጵያ ያዘጋጀውን አንድ ቢሊዮን ዩሮ የልማት እርዳታ ሳይያጸድቅ ቀርቷል።

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠውን ቀጥተኛ በጀት እንደገና ለመልቀቅ አስቦ እንደው ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጥያቄ የቀረበላቸው ኮሚሽነሯ፤ ይህ የገንዘብ ድጋፍ ከመደረጉ በፊት በኢትዮጵያ በኩል መሟላት የሚገባቸው “ፖለቲካዊ ሁኔታዎች” እንዳሉ ተናግረዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa
👍174👎3
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጨምሮ በስሩ የሚገኙት ኢትዮ-ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፓርትና ሎጂስቲክስ፣ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት እና የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ (Ethiopian Securities Exchange - ESX) መስራች አባል መሆን የሚያስችላቸውን ስምምነት አደረጉ፡፡

መንግስት የካፒታል ገበያው ሲቋቋም የመንግስት ተቋማት እስከ 25 በመቶ ድርሻ እንዲይዙ ለማድረግ በአዋጅ በደንገጉ ይታወሳል፡፡በቅርቡ ስራ ይጀምራል የተባለው የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ በምስረታው የአንድ ቢሊየን ብር ግድም ካፒታል ሊኖረው እንደሚችል ነው የሚጠበቀው፡፡
በተመሳሳይ ኩባንያው የቦርድ አባላት የተሰየሙለት ሲሆን ከአመታት በፊት በዘመን ባንክ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ሲያገለግሉ የሚታወቁት እና አሁን በከፍተኛ የማማከር ስራ እያገለገሉ ያሉት አቶ ህላዊ ታደሰ ሰብሳቢ ተደርገዋል፡፡

ሌሎች አባላት እሌኒ ገብረመድህን (ዶር)፣ አቶ ፍቃዱ ጴጥሮስ፣ ወ/ት ሂንጃት ሻሚል፣ ቴዎድሮስ መኮንን (ዶር)፣የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ያዝሚን ወሃብረቢ እና አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ናቸው፡፡አብዛኞቹ የቦርድ አባላት ከመንግስት ስልጣን ውጭ የሆኑ ናቸው፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
👍175
የ12ኛ ክፍል የመልስ መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ወደ እርማት አዳራሽ ሊገባ ነበር የተባለ ግለሰብ ተከሰሰ!

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 33 የመልስ መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ወደ ፈተና ማረሚያ አዳራሽ ሊገባ ነበር የተባለ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ሠራተኛ ተከሰሰ።በተደረገ ክትትል በፍተሻ የመልስ መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ወደ እርማት አዳራሽ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል የተባለው የተቋሙ ሠራተኛ ስልጣንን ያለአግባብ መገልግል የሙስና ወንጀል ተከሷል።

ተከሳሹ ይድነቃቸው ተኮላ ይኼይስ የሚባል ሲሆን÷ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ተረኛ ችሎት ነው።የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ በተከሳሹ ላይ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ 2 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፏል በማለት ነው ክስ ያቀረበበት።

በቀረበው ክስ ላይ እንደተመላከተው ተከሳሹ ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው የስራ ማስታወቂያ ተመዝግቦ በፈተና አመቻችነትና ለእርማት ስራ በጊዜያዊነት መቀጠሩ በክሱ ተጠቅሷል።በተለይም ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ በብርሀንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ውስጥ የተቀመጡና ለእርማት የተዘጋጁ የ18 ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መልስ መስጫ ወረቀቶችን ይዞ መውጣቱ በክሱ ሰፍሯል።

ከዚህም በኋላ በነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ 30 አካባቢ በፈተና ወቅት የተፈታኝ ተማሪዎች የመልስ መስጫ ወረቀቶች ያልሆኑና የፈተና መልስ ተቀልሞባቸው (ተሞልቶባቸው) የተዘጋጁ 33 የመልስ መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ወደ ፈተና ማረሚያ አዳራሽ ሊገባ ሲል በተደረገ ቁጥጥር በፍተሻ የተያዘ በመሆኑ በክስ ዝርዝሩ ላይ ተገልጿል።በተጨማሪም በተከሳሹ በመኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ 44 የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ ፈተና የተማሪዎች የመልስ መስጫ ወረቀቶችና 10 ደግሞ ተመሳስለው የተዘጋጁ ሀሰተኛ የመልስ መስጫ ወረቀቶች የተገኙ መሆኑን ጠቅሶ ዐቃቤ ህግ በክስ ዝርዝሩ ላይ አስፍሯል።

በዚህ መልኩ ተከሳሹ ሥልጣንን አላግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሲሆን ፥ በተረኛ ችሎት ክሱ እንዲደርሰው ከተደረገ በኋላ የዋስትና መብት ጥያቄ አቅርቧል።በተከሳሹ የዋስትና ጥያቄ ላይ አቃቤ ህግ ዋስትና ሊፈቀድ እንደማይገባ ገልጾም ተከራክሯል።ተረኛ ችሎቱ የግራ ቀኝ ክርክሩን መርምሮ በዋስትናው ላይ ብይን ለመስጠት በይደር የቀጠረ ሲሆን ፥ ተከሳሹ በቀረበበት ክስ ላይ የክስ መቃወሚያ ካለው ለመጠባበቅ ደግሞ ለጥቅምት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ተቀጥሯል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
👍246😭3👎1
ካርቱም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ፡፡

ሱዳን ካርቱም ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ በተፈጸመ የከባድ መሣሪያ ጥቃት ጉዳት መድረሱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከኢምባሲዉ አረጋጧል፡፡ይሁን እንጅ ጥቃቱ በሰዉ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳላደረሰ ከኤማባሲዉ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ዛሬ በተፈፀሙ ሁለት የአየር ጥቃቶች በኤምባሲዉ ቅጥር ግቢ የሚገኝ የዜጎች ማገገሚያና ማረፊያ ህንጻ መመታቱን ተሰምቷል፡፡በዚህም አንደኛዉ ሮኬት በህንፃዉ ላይ ጉዳት ሲያደርስ ሁለተኛዉ ደግሞ መሬት ላይ አርፏል ነዉ የተባለዉ፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ተመሳሳይ የሚሳኤል ጥቃት በኤምባሲዉ ላይ ተፈፅሞ አንድ ሰዉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም ኤምባሲዉ አስታዉቋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
👍347
YeneTube
#update የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ መንግስት መስጠት ያቋረጠውን ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍ ለመቀጠል፤ አሁንም መሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ አስታወቀ። ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ወደ ነበረበት ለመመለስ “የደረጃ በደረጃ አካሄድን” እንደሚከተል ገልጿል።ሃያ ሰባት አባል ሀገራትን በስሩ ያቀፈውን የአውሮፓ ህብረትን አቋም ያሳወቁት፤ የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር…
ኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ!

ኢትዮጵያ እና አውሮፓ ህብረት የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ።ድጋፉ 650 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 8.5 ቢሊየን ብር ሲሆን የድጋፍ ማዕቀፉ ከፈረንጆች 2024 እስከ 2027 ይቆያል ነው የተባለው፡፡

ድጋፉ በዋናነት በአረንጓዴ ልማት፣ ሰው ሃብት ልማት እና የሰላም ዘርፎች ላይ እንደሚውልም ተገልጿል።

ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የተፈራረሙት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የድጋፍ ማዕቀፉ ባለፉት ዓመታት ተቀዛቅዞ የነበረውን የህብረቱን እና የሀገሪቱን ግንኙነት ወደ ቀደመ ከፍታው ይመልሰዋል ብለዋል።

(አዲስ ዋልታ)
@YeneTube @FikerAssefa
👎29👍253
መርጌታ ላቀው የባህል መድህኒት ፈውስ እና ጥበብ ይ በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን  0915968136
                

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
☟☟☟☟☟ ☟☟☟☟☟

☞  ለመፍትሄ ሀብት
☞  ለህመም
☞  ለሁሉ ሠናይ
☞  ቡዳ ለበላው
☞  ለገበያ
☞  ሚስጥር የሚነግር
☞  ለቀለም(ለትምህርት)
☞  ለመፍትሔ ስራይ
☞  ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ
☞  ሌባ የማያስነካ
☞  ለበረከት
☞  ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
☞  ለግርማ ሞገስ
☞  መርበቡተ ሰለሞን
☞  ለዓይነ ጥላ
☞  ለመክስት
☞  ጸሎተ ዕለታት
☞  ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
☞  ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
☞  ለትዳር
☞  ለድምፅ

ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ


ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
0915968136
 
👍131😭1
የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔውን አነሳ።

435 መቀመጫ ያለው ምክር ቤት ዛሬ ከቀትር በኋላ ለአርባ አምስት ደቂቃ ባካሄደው የድምፅ ሥነ ሥርዓት የአፈጉባዔው ቢሮና መቀመጫው ክፍት እንዲሆን የወሰነው 216 ለ210 በሆነ ድምፅ ሲሆን ዴሞክራቲክ እንደራሴዎች የአፈጉባዔውን መነሳት ደግፈዋል።ኬቭን ማካርቲ ቦታቸውን ላለማጣት ከአምስት በላይ ሪፐብሊካን እንደራሴዎች መነሳታቸውን መደገፍ ያልነበረባቸው ቢሆንም ስምንቱ እንዲነሱ ደግፈው ድምፅ ሰጥተዋል።

ሥራ ላይ ያለ አፈጉባዔ በዚህ ሁኔታ በራሱ ፓርቲ እንደራሴዎች ከመንበሩ ሲነሳ በሃገሪቱ ታሪክ የዛሬው የመጀመሪያ ነው።ማካርቲ ከስምንት ወራት በፊት ቦታውን የያዙት በራሳቸው ፓርቲ ውስጥ በተነሳ ውዝግብ ምክንያት ተቃውሞ ከበዛበት ከተራዘመና ለ15 ጊዜ ከተደጋገመ የድምፅ ሥርዓት በኋላ ነበር።

የአፈጉባዔውን መዶሻ ለመጨበጥ በፓርቲያቸው ውስጥ ከተቀናቃኞቻቸው ጋር ባደረጉት ድርድር ለዛሬው መነሳታቸው ቀላል መሠረት የጣለ ግዴታ ገብተው የነበረ ሲሆን እርምጃው በምክር ቤቱ ታሪክ እጅግ አቅመቢስ አፈጉባዔ ያደረጋቸው እንደነበር ሲነገር ቆይቷል።ተከታዩ አፈጉባዔ ማን እንደሚሆንና እስከዚያም ምክር ቤቱ በማን እንደሚመራ የታወቀ ነገር የለም።

አፈጉባዔው እንዲነሱ የውሣኔ ሃሳብ ያቀረቡት የፍርሎሪዳ እንደራሴ ማት ጌትዝ ናቸው።ጌትዝ የማካርቲ ቢሮና ቦታ ክፍት እንዲሆን ለኮንግረሱ ጥያቄ ያስገቡት የሃገሪቱን መንግሥት በከፊል ከመዘጋት ያዳነ የ45 ቀናት የበጀት ክፍተት ማሟያ ስምምነት ባለፈው ዓርብ፤ መስከረም 19 የበጀት ዓመቱ ያለገንዘብ ከመጠናቀቁ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ከዴሞክራቶቹ ጋር ከደረሱ ባኋላ ነበር።

ማካርቲ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ደጋፊዎች አንስተውት በነበረ ኮንግረሱን አደጋ ላይ የጣለ ወረራና ሁከት ላይ በተከታታይ በያዙት ትረምፕ ዘመም አቋም፣ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ላይ ኮንግረሱ የክስና የማስነሳት ምርመራ (ኢምፒችመንት ኢንኳየሪ) እንዲከፈት በማዘዛቸውና በዴሞክራቶቹ ሙሉ ድጋፍ የበጀት ክፍተት ማሟያ ድምፁ በተሰጠ ማግሥት ዴሞክራቶቹን መልሰው ጥፋተኛ አድርገው በመገናኛ ብዙኃን በመናገራቸው “የዛሬውን ዕለት ሊያስሾልኳቸው ይችሉ ነበር” እያሉ ተንታኞችና እራሳቸውም ዴሞክራቶቹ የሚናገሩላቸውን እንደራሴዎች ማስቆጣታቸው ተሰምቷል።

በህገመንግሥቱ መሠረት የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ፕሬዚዳንቱ በአጋጣሚ ባይኖር ቦታውን ለመተካት ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ቀጥሎ ያለ ሰው ነው።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍157
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ አሁንም በሲሚንቶ እጥረት ምክንያት እየተስተጓጎለ ይገኛል ተብሏል፡፡

ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተመድቦለት ወደ ግንባታ የገባው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ በህክምናው ዘርፍ አዳዲስ ገጽታዎችን አካቷል፡፡በአንድ ጊዜ አምስት ታካሚዎችን ሊያስተናግድ የሚችል የጨረር ህክምና መስጫ ማእከል እና ለታካሚዎች የሚሰጠውን ጨረር የሚያመርት ፋብሪካም በውስጡ የያዘ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የግንባታው ሂደት በተለያዩ ምክንያቶች ሲቋረጥ በመቆየቱ መጠናቀቅ ከነበረበት ጊዜ እንዲዘገይ ምክንያት ሆኗል፡፡የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ አማካሪ መሃንዲስና ፕሮጀክት አስተባበሪ አቶ ሳሙኤል አባይ ለአሃዱ እንደገለጹት ግንባታው በአጠቃላይ ከ72 በመቶ በላይ ቢደርስም የሲሚንቶ እጥረት አሁንም ለግንባታው ሂደት እንቅፋት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ስራ ተቋራጩ የሚፈልገውን አይነት ሲሚንቶ በበቂ ሁኔታ ማግኘት አለመቻሉን አንስተዋል፡፡

የማስፋፊያ ግንባታው የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡አብዛኞቹን የማጠናቀቂያ ስራዎች ለማከናወን የግንባታ ዕቃዎቹ ከውጭ የሚገቡ በመሆናቸው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሌላው ችግር መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ከስራ ተቋራጩ ጋር እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በመፍታት አጠቃላይ ስራውን በመጪው ጥር ለማጠናቀቅ መታቀዱንም ተናግረዋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
👍205