አጫጭር መረጃዎችና የቤቲንግ ግምቶች ዛሬ ምሽት በሚደረጉ ጨዋታዎች ዙሪያ
ሊቨርፑል፣ አርሰናል፣ ኢንተር፣ አስቶንቪላና ሜሜሎዲን የተመለከቱ የቤቲንግ መረጃዎች እና ግምቶች በቤትስኬት
ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ👇👇
http://www.betsket.com/አጫጭር-መረጃዎችና-የቤቲንግ-ግምቶች-ዛሬ/
ሁል ጊዜ የሚለቀቁ መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👉 @betskett

👍9👎2❤1
አዲሱን አወቃቀር በመቃወም በምሥራቅ ቦረና ከ50 ሺህ በላይ ተማሪዎች ሳይመዘገቡ መቅረታቸው ተነገረ!
በጉጂ ዞን ስር የነበረው ጎሮ ዶላ ወረዳ ነዋሪዎች ምሥራቅ ቦረና በሚል እንደ አዲስ ወደ ተዋቀረው ዞን መካተታቸውን በመቃወም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ለመላክ አለመፈለጋቸውን ገለጹ።ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እና የወረዳው ትምህርት ቢሮ ሠራተኞች እንደገለጹት በዚህም ሳቢያ ከጉጂ ዞን ወደ ምሥራቅ ቦረና ከተጠቃለሉ ወረዳዎች አንዱ በሆነው ጎሮ ዶላ ከ50 ሺህ በላይ ተማሪዎች በተቃውሞ እስካሁን ለዓመቱ ትምህርት አልተመዘገቡም።
በጎሮ ዶሎ ወረዳ ብቻ ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ የሚናገሩት የወረዳው ትምህርት ቢሮ ሠራተኛ በሁሉም ትምህርት ቤቶች እስካሁን ድረስ አንድም ተማሪ አለመመዝገቡን ለቢቢሲ ተናግረዋል።የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ በአጠቃላይ በክልሉ 11 ሚሊዮን ተማሪዎች ለትምህርት መመዝገባቸውን በመግለጽ ነዋሪዎች የሚያቀርቡት ቅሬታን ያስተባብላል።
በኦሮሚያ ክልል ከወራት በፊት ምሥራቅ ቦረና የሚል አዲስ የዞን መዋቀሩን ተከትሎ የተነሳው ውዝግብ እና ተቃውሞ እስካሁን ድረስ መቋጫ አላገኘም።የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ከነሐሴ 25 እስከ ጳጉሜ 5/2015 ዓ.ም. ድረስ የተማሪዎች ምዝገባ ሲያካሂድ ቆይቷል።
ክልሉ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች እስከ መስከረም 16/2016 ዓ.ም. ድረስ እንዲመዘገቡ በሚል የምዝገባ ጊዜውን ማራዘሙን ለቢቢሲ ተናግሯል።በኦሮሚያ ክልል ሙሉ በሙሉ መስከረም 14/2016 ዓ.ም ትምህርት ተጀመሯል።
Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

👍18❤3👎3
❤58👍27🔥11👎4
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።
በማንኛውም Social Media Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::
ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።
Telegram: @adsommar
📞0929334267

👍3❤2
በሰሜን ጎንደር በተከሰተው ድርቅ 452 ሺሕ ዜጎች ተጎድተዋል ተባለ!
በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር በተከሰተው ድርቅ 452 ሺሕ ዜጎች መጎዳታቸውንና 202 ሺሕ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ሰላምይሁን ሙላት ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በዞኑ ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮ በተከሰተው ድርቅ 452 ሺሕ ዜጎች ተጎድተዋል፡፡ በተለይ 202 ሺሕ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡
እንደ ሰላምይሁን ገለጻ፤ በዞኑ በሚገኙ ጃናሞራ፣ ጠለምት፣ የበየዳ ወረዳዎችን ጨምሮ፣ ምሥራቅና ምዕራብ ጠለምትና የተወሰኑ የደባርቅ አካባቢዎች በድርቅ ተጎድተዋል፡፡ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮ ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ ሳቢያ በዞኑ በሚገኙ ስድስት ወረዳዎች ለድርቅ ተጋልጠዋል ያሉት ሰላምይሁን፤ በድርቁ ሳቢያ 19 ሺሕ አምስት መቶ ሄክታር ሰብል ጉዳት እንደደረሰበት አመላክተዋል፡፡
በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎች በተከሰተው የዝናብ እጥረት 103 ሺሕ እንስሳት ለድርቅ አደጋ መጋለጣቸውን ጠቁመው፤ 53 ሺሕ የሚደርሱ እንስሳት በድርቁ ሳቢያ መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡
በጠለምትና ጃናሞራ ወረዳዎች በድርቁ ምክንያት ከአራት ሺሕ በላይ ዜጎች ከአካባቢያቸው ለቀው ወደ ወረዳ ማዕከላት መምጣታቸውን በመግለጽ፤ ዞኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ድጋፍ ለማቅረብ ጥረት በማድረግ ላይ ነው ብለዋል፡፡የድርቅ አደጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ክልሉ ከአንድ ሺሕ አምስት መቶ ኩንታል በላይ የምግብ ድጋፍ ማድረጉን የገለጹት ሰላምይሁን፤ “ድጋፉን የችግሩ ተጋላጭ ለሆኑ 14 ሺሕ ዜጎች ማድረስ ተችሏል፡፡” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በድርቁ አካባቢዎች ላይ ተላላፊ በሽታዎች በተለይም የኮሌራ በሽታ መከሰታቸውን አስታውቀው፤ የዞንና የክልሉ ጤና ቢሮዎች ችግሩን ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ ለሚገኙ ዜጎች አስቸኳይ የዕለት ምግብ፣ መድኃኒቶች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ውሃና የእንስሳት መኖ ድጋፍ አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
“ዞኑ የተለያዩ ግብረ ኃይሎችን በማቋቋም ሀብት የማፈላለግ ሥራ ጀምሯል፡፡” ያሉት ኃላፊው፤ የችግሩ ኹኔታ ከቀን ወደቀን እየከፋ በመሄዱ የሚመለከታቸው አካላት የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡በድርቁ ሳቢያ ዜጎች ለከፋ ችግር እየተጋለጡ በመሆኑ ኹሉም አካላት ሊረባረቡ እንደሚገባ በመግለጽ፤ መንግሥት፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ አጋር አካላት የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያቀርቡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
Via EPA

👍17❤2
የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ ሁለት ሴቶች በከሰል ጭስ ህይወታቸው አለፈ!
በአዲስ አበባ ከተማ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሁለት ሴቶች በከሰል ጭስ ታፍነዉ ህይወታቸው ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንና አስታውቋል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴለቪዥን እንደተናገሩት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታዉ ሰኔ ዘጠኝ ትምህርት ቤት ጀርባ ባለ መኖሪያ ቤት ዕድሜያቸዉ 35 እና 39 የሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ ሁለት ሴቶች በከሰል ጢስ ታፍነዉ ህይወታቸዉ አልፏል።
ህይወታቸዉ ባለፈበት ቤት ዉስጥ ጢሱን ያልጨረሰ ከሰል በማሰገባት በር ዘግተዉ በመተኛታቸዉ ሁለቱም ሰዎች በተኙበት ህይወታቸዉ አልፏል።
በሌላ በኩል የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከበዓላቱ አስቀድሞ በተለያዩ አማራጮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት ከበዓላቱ አስተባባሪዎችና ከሀይማኖት አባቶች እንዲሁም ከጸጥታ ሀይሎች ጋር በጋራ በመሰራቱ በዓላቱ ያለእሳት አደጋ ክስተት በሰላም መጠናቀቅ መቻሉን አቶ ንጋቱ ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡
Via Bisrat FM

👍19❤5😭1
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዐማራ እና የኦሮሚያ ክልሎች ኹኔታ “አሳስቦኛል” አሉ!
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ በዐማራ እና በኦሮሚያ ክልል ያለው ኹኔታ አሳስቦኛል፤ ሲሉ እንደተናገሩ፣ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ቃል አቀባይ ማት ሚለር አስታውቀዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ ትላንት በስልክ የተነጋገሩት ብሊንከን፣ በክልሎቹ ያሉትን ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት፣ የፖለቲካ ውይይትንና የሰብአዊ መብቶች መከበር አስፈላጊነትን አጽንዖት እንደሰጡበት ታውቋል። ዓለም አቀፍ ለጋሾች ያቆሙት የምግብ ርዳታም ይቀጥል ዘንድ፣ የሰብአዊ ኹኔታ ቁጥጥር ተሻሽሎ ስለሚቀጥልበትም አሠራር ተወያይተዋል።
እውነተኛ፣ ታማኝ እና ሁሉን አካታች የሽግግር ፍትሕ ሒደትን ለመፍጠር እየተከናወነ ያለውን ሥራ፣ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመልካም እንደተቀበሉት ተጠቁሟል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በአፍሪካ ቀንድ ስለሚታየው የጸጥታ ተግዳሮት፣ እንዲሁም አንዲት፣ ሰላማዊት እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማየት ያላቸውን የጋራ ግብ አስመልክቶም እንደተወያዩ ታውቋል።

👍35❤7🔥2👎1
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ!
በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በዚህም መሠረት ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2016 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
በዚሁ መሠረት
1. ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
2. ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
3. ነጭ ጋዝ በሊትር 76 ብር ከ75 ሳንቲም
4. የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 70 ብር ከ83 ሳንቲም
5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ83 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

👎82👍23❤3
መንግሥት ለትግራይ ክልል ተፈናቃዮች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ መላክ እንደ ጀመረ ተገለጸ!
የፌዴራሉ መንግሥት፣ በዚኽ ሳምንት፣ ከ126 ሺሕ ኩንታል በላይ የምግብ ርዳታ ወደ ትግራይ ክልል እንደላከ፣ የክልሉ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡ርዳታው፣ ለ745ሺሕ ተፈናቃዮች እንደሚውል ተጠቁሟል፡፡
የኮሚሽኑ የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ ዲሬክተር አቶ ገብረ እግዚአብሔር አረጋዊ፣ በክልሉ 23 ወረዳዎች እንደተከሠተ በገለጹት ድርቅ፣ የርዳታ ፈላጊው ቁጥር እንደሚጨምር አመልክተዋል፡፡
Via VoA

👍18❤6👎4
በአፋር ክልል በአራት ወረዳዎች አሳሳቢ ድርቅ መከሰቱ ተገለጸ!
በአፋር ክልል ዞን ኹለት ውስጥ በሚገኙ አራት ወረዳዎች አሳሳቢ ድርቅ መከሰቱን የክልሉ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ገልጿል፡፡
የአፋር ክልል የመንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሙሃመድ አሊ ቢኢዶ፤ በክልሉ በብዛት አርብቶ አደሮች ባሉበት እና ከትግራይ ክልል ጋር አጎራባች በሆኑ ምስራቃዊ አፋር አካባቢዎች በክረምቱ ወቅት መዝነብ የነበረበት ዝናብ ባለመዝነቡ ድርቅ መከሰቱን ገልጸው፤ በዚህም በሰዎች እና በእንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
ሥማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ የክልሉ የግብርና ባለሙያ በበኩላቸው፤ በዞን ኹለት ውስጥ በሚገኙ አራት ወረዳዎች ከፍተኛ ድርቅ በመከሰቱ ከ3 ሺሕ 500 ሄክታር በላይ ሰብል ወድሟል ብለዋል፡፡
ባለሙያው አክለውም በአብኣላ፣ ብርሃሌ፣ ደሎል እና ቆነባ በተባሉ አራት ወረዳዎች ዝናብ የዘነበው በሚያዚያ እና ግንቦት ወር ብቻ መሆኑን ጠቁመው፤ "አርሶ አደሮች ዝናብ ይዘንባል በሚል ተስፋ የእርሻ ማሳቸውን በቆሎ እና ማሽላ የዘሩ ቢሆንም፣ ዝናቡ ሳይዘንብ በመቅረቱ ከ200 ሄክታር መሬት በላይ ሰብል ተዘርቶ ሳበቅል ቀርቷል።" ነው ያሉት።
በአራቱ ወረዳዎች በዝናብ እጥረት ታረሶ ያልተዘራ ከአንድ ሺሕ ሄክታር መሬት በላይ የእርሻ መሬት መኖሩንም ጠቁመዋል፡፡በክልሉ ከተከሰተው ድርቅ በተጨማሪ ከነሐሴ 04 እስከ ነሐሴ 10/2015 ድረስ ተከስቶ በነበረው የአንበጣ መንጋ በአብአላ ወረዳ ብቻ ከ480 ሄክታር መሬት በላይ ሰብል መውደሙንም ተናግረዋል፡፡
አርሶ አደሮች ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በብዛት የሚያመርቱት የበቆሎ እና የማሽላ ሰብል ቢሆንም፤ በአንበጣ መንጋ እና በድርቁ ምክንያት ሰብላቸው ከጥቅም ውጭ በመሆኑ ነዋሪዎች አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡
በሰው እና በእስንሳት ላይ የደረሰው አጠቃላይ ጉዳት ምን ያህል እንሆነ ጥናት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመውም፤ በክልሉም ይሁን በፌደራል መንግሥት በኩል እስካሁን ምንም ዓይነት ድጋፍ እንዳልተደረገ ገልጸዋል።
በድርቁ ምክንያት ችግር ላይ ለወደቁ ሰዎች አንዳንድ በጎ ፈቃደኞች በቤተክርስቲያን እና በመሰጂድ ገንዘብ በማሰባሰብ እንዲሰጣቸው እያደረጉ ቢሆንም፤ "ይህ በቂ ባለመሆኑ ችግሩ ሳይባባስ እርዳታ ሊደረግላቸው ይገባል።" ሲሉ አሳስበዋል፡፡በአፋር ክልል ከተከሰተው ድርቅ በተጨማሪ በትግራይ ክልል 27 ወረዳዎች እንዲሁም በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ጎንደር ዞኖች በተከሰተው አስከፊ ድርቅ የሰዎች ሕይወት እያለፈ ይገኛል።
Via Addis Maleda

👍33❤5
በመስቀል ደመራ ዋዜማ መስከረም 15/2016 በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን በኦንቆሎ ዋቤ ወረዳ ብሎ ቀበሌ የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ስድስት አገልጋይ ካህናት እና ምዕመናን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ እንደተገደሉ ማረጋገጡን እናት ፓርቲ ይፋ አድርጓል።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
👍52🔥12❤11😭8👎5
ዛሬ የሚደረጉ የአውሮፓ ሊጎች የተመረጡ ጨዋታዎች የቤቲንግ ግምትና መረጃዎች
ፍሬቡርግ፣ ሮማ፣ ሌስተር፣ ቫይኪንግ እና ዩኤስጂን የተመለከቱ የቤቲንግ መረጃዎች እና ግምቶች በቤትስኬት
ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ👇👇
http://www.betsket.com/ዛሬ-የሚደረጉ-የአውሮፓ-ሊጎች-የተመረጡ-ጨ-2/
ሁል ጊዜ የሚለቀቁ መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👉 @betskett
ፍሬቡርግ፣ ሮማ፣ ሌስተር፣ ቫይኪንግ እና ዩኤስጂን የተመለከቱ የቤቲንግ መረጃዎች እና ግምቶች በቤትስኬት
ሊንኩን በመጫን በነጻ ያንብቡ👇👇
http://www.betsket.com/ዛሬ-የሚደረጉ-የአውሮፓ-ሊጎች-የተመረጡ-ጨ-2/
ሁል ጊዜ የሚለቀቁ መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👉 @betskett
👍10❤3
በቱርክ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አቅራቢያ በተፈፀመ “የሽብር ጥቃት” ጉዳት ደረሰ!
በቱርክ መዲና አንካራ በሚገኘው የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አቅራቢያ በተፈፀመ “የሽብር ጥቃት” ሁለት የፖሊስ መኮንኖች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የአገሪቷ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ።ሚኒስትር አሊ የርሊካያ እንዳሉት ዛሬ እሑድ ረፋድ 3: 30 ሁለት ጥቃት አድራሾች በንግድ ተሽከርካሪ ወደ አካባቢው በማምራት ጥቃቱን አድርሰዋል።
አንደኛው ጥቃት አድራሽ በሚኒስቴሩ ሕንጻ ፊት ለፊት ራሱን ያጠፋ ሲሆን ሌላኛው መገደሉን ሚኒስትሩ ጨምረው ተናግረዋል።ፍንዳታው ያጋጠመው ምክር ቤቱ ከሦስት ወራት እረፍት በኋላ ስብሰባውን ከማካሄዱ ከሰዓታት በፊት ነው።
ሚኒስትር የርሊካያ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍም “የመጨረሻው ሽብርተኛ እስከሚጠፋ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል” ብለዋል።ስለ ፍንዳታው ቀድሞ የዘገበው የአገሪቷ ሚዲያ በአካባቢው የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር የገለጸ ሲሆን የድንገተኛ አገልግሎት ሠጪ አካላትም ወደ ሥፍራው እየሄዱ ነው ብሎ ነበር።
የእሳትና ድንገተኛ አገልግሎት እንዲሁም የህክምና ባለሙያዎች ቡድንም በፍጥነት ወደ ሥፍራው እንዲሄዱ ወደ አካባቢው የሚወስዱ መንገዶች ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ዝግ መደረጋቸውም ተገልጿል።ጥቃቱን የፈፀሙት እነማን እንደሆኑ ግልጽ አይደለም። እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካልም የለም።

👍20🔥2❤1