‹‹ መላው የአማራ ሕዝብ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚያጠለሹ መልዕክቶችን ይፀየፍ ›› - አብን
ማህበራዊ መሠረቱ የአማራ ሕዝብ መሆኑን የሚገልፅው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ለአማራ ሕዝብ የተለያዩ ጥሪዎችን አቅርቧል፡፡
በዚህም ‹‹ መላው የአማራ ህዝብ ከሌላው የሀገሪቱ ህዝብ ጋር ያለውን የወንድማማችነት እሴቶች ከሚንዱ ቅስቀሳዎች፤ በራሱ እና በልጅቹ የተመሰረቱ ተቋማትን በተለይም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከሚያጠለሹ መልዕክቶች እንዲሁም የአማራ ህዝብ ማህበራዊ ረፍት እንዲያጣ ከሚመኙ አካላት በስልት የሚሰጡትን አጀንዳዎች እንዲፀየፍ ›› ጠይቋል፡፡
አክሎም ‹‹ ወደ ሰላም መድረክ የሚያመሩ መንገዶችን ሁሉ ለመጥረግ አቅሙ የፈቀደውን ርብርብ እንዲያደርግ በአደራ ጭምር ›› አሳስባለሁ ብሏል፡፡አብን በክልሉ ላይ አለኝ ያለውን አቋም በ16 ነጥቦች ዘርዝሮ አንፀባርቋል፡፡
በዚህም ‹‹ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአጭር ግዜ እንዲያልቅ፣ አዋጁን ለማስፈፀም የተሰማሩ አካላትም ከማንነት ተኮር ፍረጃዎች፣ ወከባዎች፣ ከዘፈቀደ እስራትና አካላዊ ጥቃቶችን ›› እንዳይፈፅሙ አሳስቧል፡፡
‹‹ የፌደራሉ መንግስት አካላት ሚና ለህዝቡ የሚመጥን አስተዳደር እንዲዋቀር መደላድል በመፍጠር እንዲወሰን፣ ህዝባዊ የውይይት መድረኮችም እንዲፈጠሩ፣ ህዝቡም የሰላም ጥረቶችን እንዲደግፍ ›› ጥሪ አቅርቧል። አክሎም ‹‹ ክልሉ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተዳደር በአፋጣኝ እንዲወጣም ›› ጠይቋል፡፡መግለጫው ‹‹ መንግስት ለድርድር እና ንግግር ጥሪ እንዲያደርግ ›› ጥሪ አቅርቧል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

በጎንደር በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው እና ሆስፒታሉ የመድኃኒት እና የኦክሲጂን እጥረት እንዳጋጠመው ተገለጸ!
በአማራ ክልል በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት በጎንደር ሆስፒታል ውስጥ የደም፣ ኦክስጂን እና የተወሰኑ መድኃኒቶች እጥረት ማጋጠሙን የሆስፒታሉ ምንጮች ለቢቢሲ ገለፁ።በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ባለፉት ቀናት ከፍተኛ ግጭት እና የተኩስ ልውውጥ ከገጠማቸው የአማራ ክልል ከተሞች መካከል የጎንደር ከተማ አንዷ ስትሆን፣ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በከተማዋ እና በዙሪያዋ ባለፉት ቀናት በነበረው ግጭት አብዛኞቹ ሰላማዊ የሆኑ ወደ 20 የሚደርሱ ሰዎች እንደሞቱ እና ከ200 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ጎንደር ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎቹ ለቢቢሲ ገልጸዋል።ወደ ጎንደር ሆስፒታል በጥይት ተመትተው ከመጡ ሰዎች መካከል የ16 ዓመት ታዳጊ እንደሚገኝበት እና ተጎድተው ከመጡት መካከል በእድሜ ትልቅ የሆኑት ደግሞ የ50 ዓመት ሴት መሆናቸውን አንድ ዶክተር ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ተጎድተው ወደ ሆስፒታሉ ከመጡ በኋላ የሞቱ ሰዎች አብዛኛዎቹ “ሰላማዊ ሰዎች እና ተዋጊዎች” መሆናቸውን የሕክምና ባለሙያዎቹ ጠቅሰው፣ እስካሁን ተጎድተው ወደ ሆስፒታሉ የመጡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት አለመኖራቸውን ተናግረዋል።በግጭቱ የተነሳ በከተማዋ ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በመስተጓጎላቸው በሆስፒታሉ ውስጥ ለሚገኙ ህሙማን እጅግ አስፈላጊ የሆኑት የደም፣ የኦክስጂንእና የመድኃኒት አቅርቦቶች እጥረት ማጋጠሙን የጎንደር ሆስፒታል ምንጮች ተናግረዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሆስፒታሉ ባጋጠመው የኦክስጂን እጥረት ምክንያት ምንም ዓይነት ቀዶ ሕክምና ማከናወን አለመቻሉን የሆስፒታሉ ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል።የቢቢሲ ምንጮች ጨምረውም ለቀናት በከተማዋ ባጋጠመው አለመረጋጋት የተነሳ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ባለመኖሩ በሆስፒታሉ ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን የሚቀርብ ምግብ እጥረት ማጋጠሙንም ገልጸዋል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች እንዳሉት በከተማዋ ለሦስት ቀናት በዘለቀው ግጭት የተጎዱ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል ለማድረስ ምንም ዓይነት የትራንስፖርት አገልግሎት ባለመኖሩ የተጎዱ ሰዎች በቃሬዛ መምጣታቸውን አመልክተዋል።
Via BBC

👍1
አርቲስት አብነት ዳግም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!
አርቲስት አብነት ዳግም በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡አርቲስት አብነት በበርካታ ቴአትሮች ፣ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ በተዋናይነት በመሳተፍ እውቅናን ያተረፈ ተዋናይ ነበር።
@YeneTube @FikerAssefa
አርቲስት አብነት ዳግም በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡አርቲስት አብነት በበርካታ ቴአትሮች ፣ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይ በተዋናይነት በመሳተፍ እውቅናን ያተረፈ ተዋናይ ነበር።
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፊታችን ነሐሴ 8 አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ!
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን መርምሮ ውሳኔ ለማሳለፍ የፊታችን ነሐሴ 8 ቀን ለአባላት የአስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ አስተላልፏል፡፡
ሰሞኑን በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ የሚኒስትሮች ም/ቤት በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀፅ 1 (ሀ) መሰረት ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 መደንገጉ ይታወሳል፡፡
ከዚሁ ጋር በተገናኘ በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀፅ 2 (ሀ) እና (ለ) መሠረት በሚኒስትሮች ም/ቤት የሀገሪቷን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርቦ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ቢደነገግም ምክር ቤቱ በዕረፍት ላይ እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡
በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 58 (4) እና በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 15 (1) ምክር ቤቱ በዕረፍት ላይ እያለ የምክር ቤቱን ውሳኔ የሚሹ አስቸኳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡
በዚህም መሠረት ለምክር ቤቱ አማካሪ ኮሚቴ አጀንዳው ቀርቦ በሙሉ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን÷ ምክር ቤቱ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

👍2
ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ተግባራት ገምግሟል፡፡
የዕዙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ዕቅድ በባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ በደብረ ብርሃን፣ በላሊበላ፣ በጎንደርና በሸዋ ሮቢት አካባቢ የተሰባሰበውን በዘረፋ እና በጥፋት የተሰማራ ቡድን በመምታትና ከተሞቹን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ መመለስ ነበር። እነዚህ አካባቢዎች የተመረጡት ብዙ ሕዝብ የሚኖርባቸው፣ ከፍተኛ የንግድና የቱሪስት እንቅስቃሴ ያለባቸው፣ የፖለቲካና የኢንዱስትሪ ማዕከላት በመሆናቸው ነው።
በዚህ መሠረት በስድስቱ ከተሞች ዙሪያ የመጣው የጥፋት ቡድን መሣሪያውን እንዲያስረክብና እጁን እንዲሰጥ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀሙ እርምጃ ተወስዶበታል፣ የሕግ የበላይነትም እንዲከበር ተደርጓል። የክልሉ ሕዝብ በዚህ ዘራፊ ቡድኑ የተማረረ በመሆኑ፣ የህግ አስካባሪ አካላት ተልዕኮዋቸውን በስኬት እንዲወጡ ተገቢውን ድጋፍ አድርጓል። ጠቅላይ መመሪያ እዙም የክልሉ ህዝብ ላደረገለት ትብብር ምስጋናውን ያቀርባል።
በአሁኑ ሰዓት ከተሞቹ ከዘረፊዉ መንጋ ስጋት ነጻ ሆነዋል። የመከላከያ ሠራዊቱ እና የክልሉ ህግ አስከባሪ አካላት በየሥርቻው የተራረፈውን ዘራፊ በማጽዳት ላይ ናቸው። ማኅበረሰቡም መረጃ በመስጠት፣ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ለዚህ ስራ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ሽንፈት የተከናነበው የፅንፈኞች ቡድን በአንዳንድ አካባቢዎች ወደ ቅርስ ቦታዎችና የእምነት ተቋማት በመግባት ለመደበቅ እየሞከረ ነው።
የመከላከያ ሠራዊቱ እና የክልሉ ህግ አስከባሪ አካላት ህግ፣ ሥርዓትና ሞራልን ባከበረ መንገድ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛል። በቀጣይም የመጨረሻውን የማጽዳት እና የመልቀም ተግባር በማከናወን ከተሞቹ በአጭር ጊዜ ወደ ተሟላ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለሱ ይደረጋል።
በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የጠቅላይ መምሪያ ዕዙ እስካሁን 14 ተጠርጣሪዎችን በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን ወደፊትም እንደሁኔታው በቁጥጥር ሥር የሚያውላቸውን ግለሰቦች አስመልክቶ አስፈላጊውን መረጃ ለህዝብ ይፋ ያደርጋል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ ዕቅድ የተያዘው ከተሞቹን ከዘራፊ የጥፋት ቡድን የማጽዳቱ ተግባር እየተጠናቀቀ በመሆኑ፣
1. ከሐሙስ ነሐሴ 4 ጀምሮ ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች መደበኛ የአውሮፕላን በረራ ይጀመራል፤
2. ከባጃጅና ከሞተር ሳይክል በስተቀር ሁሉም ዓይነት የከተማ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ወደ አገልግሎት ይገባሉ፤
3. የመንግሥት፣ የማኅበረሰብ አገልግሎት፣ የንግድ፣ የጤና፣ የፋይናንስ፣ ወዘተ. ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል።
በዚሁ አጋጣሚ የክልሉ ሕዝብ ራሱን ከዘራፊውና ከጽንፈኛው መንጋ በመነጠልና በመከላከል፣ ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመሰለፍ ላደረገው ተጋድሎ ዕዙ በድጋሚ ምስጋናውን ያቀርባል።
ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓም
አዲስ አበባ

Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።
በማንኛውም Social Media Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::
ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።
Telegram: @adsommar
📞0929334267

ከህግ አግባብ ውጪ ሲሰሩ በተገኙ 107 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ!
ከህግ አግባብ ውጪ ሲሰሩ በተገኙ 107 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡እርምጃ የተወሰደባቸው ንግድ ድርጅቶች ከተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ መስኮችና ዓላማዎች ውጪ ሲሰሩ የነበሩ፣ ለኢንስፔክሽን ስራ ፍቃደኛ ያልሆኑ እና ባልፀና ወይም ባልታደሰ ንግድ ፈቃድ ሲነግዱ የተገኙ ናቸው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ባስመዘገቡት የስራ አድራሻ ያልተገኙ እንዲሁም የቅርንጫፍ አድራሻ ያላስመዘገቡ ድርጅቶች እንደሚገኙበት ተመላክቷል።
ሚኒስቴሩ ባደረገው ክትትልም በ49 ንግድ ድርጅቶች ላይ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሲሆን በ58 ንግድ ድርጅቶች ላይ ደግሞ የእግድ እርምጃ ተወስዷል፡፡በቀጣይም በንግድ ድርጅቶች ላይ የሚደረገው የቁጥጥርና የክትትል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

👀1
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ መልካሙ ሹምዬ በገዛ ፈቃዳቸዉ ሀላፊነታቸውን እንደለቀቁ አስታወቁ!
አቶ መልካሙ ሀላፊነታቸውን መልቀቃቸዉን በማስመልከት ተከታዩን ደብዳቤ ለፓርቲዉ በመጻፍ ከሀላፊነታቸው የለቀቁ መሆኑን ያሳወቁ ሲሆን በፓርቲዉ እንዲሁም በማዕከላዊ አባልነታቸዉ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ሙሉ ደብዳቤያቸው እንደሚከተለዉ ቀርቧል....
እኔ መልካሙ ሹምዬ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) መስራች አመራሮች አንዱ ስሆን ፣ ድርጅታችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ማዕከላዊ ኮሚቴ መጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው የማእከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባ የድርጅታችን ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ እንደገና እንዲዋቀር ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ በምክትል ሊቀመንበርነት እንዳገለግል እንደመረጠኝ ይታወሳል። እኔም ከተመረጥኩበት እለት ጀምሮ አቅሜ በፈቀደ መጠን ድርጅታዊ ኃላፊነቴን እና ማእከላዊ ኮሚቴው የጣለብኝን አደራ በአስቸጋሪ ፖለቲካዊ ሂደት ውስጥ በማለፍ ጭምር ስወጣ ቆይቻለሁ።
በቆይታየም ድርጅታችን የተተነተነ እና የተደራጀ ሃሳብ ይዞ የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ የበኩሌን አስተዋጽኦ ሳደርግ የቆየሁ ሲሆን ፣ ድርጅታችንን በመወከል በዲኘሎማሲው መስክ እና በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ እና በሌሎች ተመሳሳይ መድረኮች በሚደረጉ ውይይቶች በንቃት በመሳተፍ የሕዝባችንን ድምጽ ለማሰማት ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ። በተጨማሪም ድርጅታችን አብን ያጋጠሙትን ውስጣዊ ችግሮች ለማረም የጀመረው የሪፎርም ሥራ እንዲሳካ እና ፓርቲያችን ጠንክሮ እንዲወጣ የበኩሌን ጥረት ሳደርግ የቆየሁ ሲሆን ፤ ለወደፊቱም ጥረቴን አጠናክሬ የምቀጥል ይሆናል ማለታቸዉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።
በእስካሁኑ ቆይታየ በግል እና በድርጅት ሥራዎች ያጋጠሙ ፈተናዎችን ለመቋቋም የበኩሌን ጥረት ሳደርግ የቆየሁ ቢሆንም ከአብላጫው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ያለኝ የአቋም ልዩነት እየሰፋ ስለሄደ እና የሃሳብ እና የአቋም ልዩነቱ ከሕዝባችን መብት ፣ ጥቅም እና ኅልውና መከበር አንጻር ያለው ትርጉም እና ውጤት ከፍ ያለ መሆኑን ስላመንኩ ፣ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ውስጥ አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር እና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆኖ መቀጠል የድርጅታችንን እና የሕዝባችንን ጥቅም የሚያስከብር ሆኖ ባለማግኝቴ ኃላፊነቴን በፈቃዴ ለመልቀቅ ወስኛለሁ።
በመሆኑም የድርጅታችን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነቴን ይዥ የምቀጥል መሆኑን እያስታወስኩ፣ ድርጅታችን የአማራ ብሐራዊ ንቅናቄ የጀመረው ሪፎርም እንዲሳካ ፣ ፓርቲያችን የተቋቋመበትን ዓላማ እንዲያሳካ ፣ የቆመለትን ሕዝብ በሃቅ እንዲያገለግል እና ጠንካራ አታጋይ ድርጅት ሁኖ እንዲወጣ በድርጅት እና በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነቴ ትግሌን እንደምቀጥል እረጋገጥኩ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበርነት እና የብሔራዊ የሥራ አስፈጻሚ አባልነት በፈቃዴ የለቀኩ መሆኑን አሳውቃለሁ። በዚህ አጋጣሚ የድርጅታችን ማዕከላዊ ኮሚቴ ክፍተት እንዳይፈጠር በቦታው ተገቢ ነው ብሎ የሚያምነውን ሰው እንዲተካ ጥሪየን አቀርባለሁ።

«በትግራይ የምግብ እርዳታ ከተቋረጠ ወዲህ 1411 ሰዎች በረሃብ ሞተዋል» የትግራይ አስተዳደር
የትግራይ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን ኮምሽነር ዶክተር ገብረሕይወት ገብረእግዚአብሔር "እስካሁን 1411 ሰዎች በረሃብ ምክንያት ሕይወታቸው እንዳለፈ፣ እነዚህ ሕይወታቸው ያለፈ ደግሞ ሽማግሌዎች፣ ሴቶች፣ ህፃናት መሆናቸው ፥ የምግብ እርዳታው ከቆመ በኃላ ከዞኖች፣ ወረዳዎች ሪፖርት ተደርጎልናል።ይህ የሟቾች ቁጥር ምዕራብ ትግራይ ዞን፣ የደቡብ ትግራይ ዞን 6 ወረዳዎች፣ የማእከላዊ ዞን 22 ወረዳዎች እንዲሁም የመቐለ 7 ክፍለከተሞች እንደማይጨምር የትግራይ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ኮምሽነር ዶክተር ገብረሕይወት ገብረእግዚአብሔር ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
ለተቸገሩ ዜጎች የሚቀርብ የምግብ እርዳታ ተዘርፏል በሚል ምክንያት ከአምስት ወራት በፊት በትግራይ ጨምሮ በአጠቃለይ በሀገሪቱ ለሚገኙ እርዳታ ፈላጊዎች ያቀርበው የነበረ የምግብ አቅርቦት ማቋረጡ የገለፀው የዓለም የምግብ ድርጅት ቀስበቀስ የምግብ እርዳታ ማቅረብ መጀመሩ በትላንትናው ዕለት የተዘገበ ቢሆንም እንደ የትግራይ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን ገለፃ ግን የተጀመረው፥ ለረዥም ግዜ በትግራይ ተቋርጦ የነበረ የሴፍትኔት ፕሮግራም እንጂ የአስቸኳይ ሕይወት አድን ሰብአዊ እርዳታ አለመሆኑ ተገልጿል።ኮምሽነሩ ዶክተር ገብረሕይወት፥ ዓለምአቀፍ ለጋሾች እስካሁን በትግራይ ላሉ እርዳታ ፈላጊዎች ያቀረቡት እገዛ የለም ይላሉ።
"ይህ የተጀመረው 'food for work' ምግብ ለስራ የሴፍትኔት ፕሮግራም ነው። እንደሚታወቀው ከጦርነቱ በፊትም የነበረ፣ ከ700 ሺህ እስከ 1 ሚልዮን የሚጠጋ የትግራይ ህዝብ ይሳተፍበት የነበረ ፕሮግራም ነው። ለተቸገረ የሕብረተሰብ ክፍል ወይ ለተፈናቃይ የሚሆን የተጀመረ የምግብ እርዳታ ግን የለም። ሴፍቲኔት፥ ፕሮግራም እንጂ አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት አይደለም" የሚሉት ኮምሽነሩ "በመቐለ እና ሌሎች ወረዳዎች መጋዝን ያለ እርዳታ ግን ለህዝቡ እንዲሰራጭ የተሰጠ ፍቃድ የለም" ሲሉ አክለዋል።በዚህ ጉዳይ ዙርያ በዓለም የምግብ ድርጅት (WFP) የመቐለ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት በአካል እንዲሁም በአዲስአበባ ከሚገኙ የድርጅቱ ተወካዮች በስልክና ኢሜይል ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት ለግዜው አልተሳካም።
[DW]

✅✅✅ "Do or Die..!" ✅✅✅
የተዋጣለት የሺያጪ ቻናል ፈልገዋል..!!!
ቤት ...❓
መሬት...❓
መካዝን...❓
ኢንዳስትሪ...❓
ኢንቨስትመንት...❓
ሪል ስቴት ..❓
ለትርፍ የሚሆኑ ለ 2 ..3..የሚከፈሉ ቦታዎችን ፈልገዋል ..❓❓❓
አዲስ አበባ ውስጥ የግዙፍ የግዢ እና የሽያጪ ቻናላችን ነው
..የምትወዱትን ሰው የሆነ ፍጥረት ወደ ቻናሉ ቤተሰብ በማደረግ መረጃን በቤትዎ ያስገቡ ..
መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ በማደረግ ሀላፊነታችሁን ተወጡ..!!!
+251937736408
https://tttttt.me/shger21
Inbox @FikreabAmanu
ለበለጠ መረጃ.. ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/+U2S2JyiWsfAzNzc0

"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665

🔥1
Facebook, Twitter, Instagram እና በመሳሳሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ድርጅትዎን ፤ አገልግሎትዎን እና ምርትዎን ማስተዋወቅ ፈልገዋል? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር ነው።
በማንኛውም Social Media Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::
ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።
Telegram: @adsommar
📞0929334267
በማንኛውም Social Media Boost ለማድረግ ካሰቡ ይደውሉልን፤ በተመጣጣኝ ዋጋ ታማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን::
ከዚህም በተጨማሪ የቴሌግራም ፕሪሚየም ጨምሮ ለተለያዩ ኢንተርናሽናል አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈጸም ካስፈለግዎ ከስር በተቀመጡ አድራሻዎች ያናግሩን።
Telegram: @adsommar
📞0929334267
ያለርዳታ 10 ወራትን ያስቆጠሩ በትግራይ መጠለያዎች የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች በእጅጉ እንደተቸገሩ ገለጹ!
ላለፉት ዐሥር ወራት የርዳታ እህል እንዳልተሰጣቸው የገለጹ፣ በትግራይ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች፣ በእጅጉ መቸገራቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡
ለደኅንነታቸው በመስጋት ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አስተያየት ሰጭዎች፣ ከሥፍራው በስልክ እንደገለጹልን፣ በማይ ዓይኒ እና በዓዲ ሓሩሽ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ፣ 1ሺሕ700 ስደተኞች ይኖራሉ፡፡ ኾኖም፣ በመጠለያ ጣቢያዎቹ፣ መሠረታዊ አገልግሎት ባለመኖሩ፣ ለከባድ ችግር እንደተጋለጡ አስታውቀዋል፡፡ በሕክምና ዕጦት ምክንያት፣ በቅርቡ የ20 ሰዎች ሕይወት ማለፉንም ገልጸዋል፡፡
ስለ ጉዳዩ፣ ከኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት፣ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር/UNHCR/ በበኩሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በኢሜይል በሰጠው ምላሽ፣ “ስደተኞቹ፣ በዚያ አካባቢ ኾነው አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ አስቀድመን ነግረናቸዋል፡፡ አሁንም ወደ ቦታው መግባት አንችልም፤” በማለት ገልጿል፡፡
Via VoA
Photo: File

የ1 ዓመት ህጻን ልጅ ሰርቃ በገንዘብ ለመደራደር የሞከረችው የቤት ሰራተኛ በእስራት ተቀጣች!
በሸገር ከተማ አስተዳደር መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ህጻን በማገት ከፍተኛ ብር ሲጠይቁ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸውን የመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርምራ ክፍል ዋና ኃላፊ ኢንስፔክተር ብርሃኔ ወየሳ ተናግረዋል።
አንደኛ ተከሳሽ ኡርጌ በቀለ የተባለችው ግለሰብ በአንድ መኖሪያ ቤት በቤት ሰራተኝነት ስትሰራ የአንድ ዓመት ከስድስት ወር እድሜ ያላትን ልጅ ለመጠበቅ ከተቀጠረችበት ቤት ልጅ ሰርቃ በገንዘብ ለመደራደር መሞከሯ ተገልጿል።ግለሰቧ በተቀጠረች በሁለተኛው እለት ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ አቡሽ ከተባለ ግብረአበሯ ጋር በመሆን ልጅ ሰርቃ በመውሰድ ለተባባሪዋ አስረክባዋለች።
ልጅቷን መታገቷን እና ገንዘብ ከፍለው ልጃቸውን መውሰድ እንደሚችሉ በማለት የህጻኗን ቤተሰቦች ያስፈራራሉ።ወላጆች ጉዳዩን ወዲያውኑ ወደ መልካ ኖኖ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ያመለክታሉ፡፡ ፖሊስም ባደረገው ክትትል ተከሳሽ ኡርጌ በቀለ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።
ግለሰቧ በቁጥጥር ስር ከዋለች በኀላ ህጻኗን ያገቱበትን ቦታ ለፖሊስ በመጠቆሟ ህጻኗን ማግኘት ተችሏል።በተጨማሪ ተከሳሿ ከተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት የተለያዩ ጌጣጌጥ ፣ አልባሳት እና የሞባይል ስልክ ግምቱ ከ36 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት መስረቋ ተረጋግጧል።
ፖሊስ በተከሳሾች ላይ ምርመራውን አጣርቶ መዝገቡን ለሸገር ከተማ ዓቃቢህግ ጽ/ቤት በመላክ ክስ እንዲመሰረት አድርጎል።ክሱ የቀረበለት የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለቱን ተከሳሾች ጥፋተኛ በማለት በ12 ዓመት እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ኢንስፔክተር ብርሃኑ ወይሳ ጨምረው ተናግረዋል።
[ዳጉ ጆርናል/Bisrat]

❤1
‹‹ በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ሰብዓዊ ረድዔት ማቅረቤን በጊዜያዊነት ለማቆም ተገድጄያለሁ ›› - ሴቭ ዘ ቺልድርን
የሕፃናት አድን ድርጅት(ሴቭ ዘ ቺልድርን) የሚዲያ ኮሚኒኬሽንና አድቮኬሲ ክፍል ሃላፊ ሕይወት እምሻው በክልሉ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ‹‹ ተባብሶ በቀጠለው ግጭት ›› ምክንያት ‹‹ የሰብዓዊ ረድዔት አቅርቦቱን በጊዜያዊነት ለማቋም መገደዱን ›› ለአሻም ነግረዋታል፡፡
ድርጅቱ ‹‹ በክልሉ ለሚገኙ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ህፃናትና ሌሎች ዜጎች እርዳታ ለማድረስ ምቹ ሁኔታዎች እንዲኖር ›› በሚል ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ያወጣውን ጋዜጣዊ መግለጫ አስመልክቶ ከአሻም ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉት ሃላፊዋ ‹‹ በክልሉ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ ከ580 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚገኙ ›› አመልክተዋል፡፡
‹‹ ለተፈናቃዮቹ የተለያዩ የሰብዓዊ እርዳታዎችን ሲያቀርብ መቆየቱን ›› ገለፁት ሕይወት ‹‹ አሁን ላይ ግን በክልሉ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ሳቢያ በመተማ፣ በሰሜን ወሎ ባሉ ፕግራሞች እንዲሁም ከሰቆጣ ቢሮው ተነስቶ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ሲቀርቡ የነበሩ የእርዳታ አይነቶች ለጊዜው ለማቆም መገደዱን ›› ነግረውናል፡፡
‹‹ ይህም በተለይ ከባለፈው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ የተፈናቃይ ቁጥር ላለበትና የእለት ደራሽ የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ከባድ መሆኑን ›› ጠቁመዋል፡፡
ሀላፊዋ አክለውም ‹‹ በሁሉም ወገን ያሉ የግጭቱ ተሳታፊ አካላት የሰብዓዊ እርዳታ በምንም ዓይነት መንገድ መቋረጥ ስለሌለበት ለዚህ መተባበር እንዲኖርባቸው ›› አመልክተው ‹‹ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያቀርቡ ሰራተኞችንም ከአደጋ ጥበቃ እንዲያደርጉላቸው ›› ጠይቀዋል፡፡
[Asham]

ተቋርጦ የነበረው ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ) መደበኛ በረራ ነገ እንደሚጀመር ተገለጸ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት አቋርጦት የነበረውን ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ) መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 5/2015 እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡
በዚህም መንገደኞች በአየር መንገዱ ድረ-ገጽ (www.ethiopianairlines.com) ወይም የሞባይል መተግበሪያዎቹ (https://www.ethiopianairlines.com/aa/ethiopian-app) በመጠቀም ለጉዟቸው የሚያስፈልጉ ተግባራትን ካሉበት መከወን እንደሚችሉ ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአማራ ክልል ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ፤ ማክሰኞ ነሐሴ 2/2015 ባወጣው መግለጫ፤ ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ)፣ ጎንደር፣ ላሊበላ እና ባህርዳር የሚደረጉ በረራዎች፤ ለሦስት ተከተታይ ቀናት መሰረዛቸውን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ይህንንም ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ፤ ዛሬ ነሐሴ 4/2015 እንደሚጀምር በትናንትናው ዕለት አስታውቆ ነበር፡፡