YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአማራ ክልል ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ተወሰነ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ የሕዝብን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በአማራ ክልል ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወሰነ።

የክልሉ መንግስትም በአማራ ክልል ያጋጠመው የፀጥታ መደፍረስ፣ በክልሉ ሰብዓዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያስከተለ የሚገኝ መሆኑን በመግለጽ፣ ሁኔታውን በመደበኛው የህግ ማስከበር ሥርዓት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ፣ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በኢፌድሪ ህገ መንግስት መሰረት እንዲደነግግ እና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጥያቄ ማቅረቡን አስታውሷል፡፡

በመሆኑም መደበኛ የህግ ስርዓትን መሰረት አድርጎ ይህን ፈር የለቀቀ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አዳጋች ሁኔታ በመፈጠሩ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በህገመንግስቱ የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ስላለበት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆነ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 23ኛው መደበኛ ስብሰባ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው  ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲሆን ወስኗል።

ውሳኔው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ መፈጸም እንደሚያስችላቸው የታመነበት በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚሁ መሰረትም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ሆኖ አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ነፃነቱ ተጠብቆ መንቀሳቅስ እንዲችል፣ በትምህርት ዘርፍ ለተጀመረው የሪፎርም እንቅስቃሴ ፈር ቀዳጅ ሆኖ እንዲወጣ እድል ይፈጥርለታል ተብሏል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ስርዓትን በቀዳሚነት ተግባራዊ እንደሚያደርግና ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተምሳሌት እንደሚሆን ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የኮርፓሬት ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት አቶ ዓባይነህ ሙሉጌታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የኮርፓሬት ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት አቶ ዓባይነህ ሙሉጌታ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት (ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም) በ37 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍1
ሀዋሳ ናችሁ?

የዴሊቨሪ ሀዋሳን መተግበሪያ ያውርዱ በመጀመሪያ ኦርደሮ ቦነሶችን ያግኙ።

ሲመዘገብ 50 ብር ይሰጦታል

👌 shorturl.at/bKVZ3
#ሰበር_ዜና

የተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ

የአብን ፓርቲ አባልና ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ሃምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በፌደራል ፖሊስ አማካይነት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሚያመላክቱ መረጃዎች በማህበራዊ ትስስር ገፆች በስፋት እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።

የፓርቲው አባል እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ያስተላለፏቸው መልዕክቶች ለእስራቸው ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል።

አባሉ ምንም እንኳን ያለ መከሰስ መብት ቢኖራቸውም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አማካይነት በቁጥጥር ስር ሳይውሉ እንዳልቀረ ተጠቁሟል።

ያም ሆኖ ግን አቶ ክርስቲያን ታደለ ታስረዋል መባሉን ተከትሎ ከፓርቲያቸው አብን ሆነ እስሩን ፈፅሟል ከተባለው የመንግስት አካል በኩል የተሰጠ ምላሽ እና ማብራሪያ በይፋ አልወጣም።

Via ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
👍3
Forwarded from YeneTube
   "Do or Die..!" 

የተዋጣለት የሺያጪ ቻናል ፈልገዋል..!!!

ቤት ...
መሬት...
መካዝን...
ኢንዳስትሪ...
ኢንቨስትመንት...
ሪል ስቴት ..
ለትርፍ የሚሆኑ ለ 2 ..3..የሚከፈሉ ቦታዎችን ፈልገዋል ..

አዲስ አበባ ውስጥ የግዙፍ የግዢ እና የሽያጪ ቻናላችን ነው

..የምትወዱትን ሰው የሆነ ፍጥረት ወደ ቻናሉ ቤተሰብ በማደረግ መረጃን በቤትዎ ያስገቡ ..

መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ በማደረግ ሀላፊነታችሁን ተወጡ..!!!

   +251937736408
https://tttttt.me/shger21
  Inbox @FikreabAmanu

ለበለጠ መረጃ.. ቻናላችንን  ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/+U2S2JyiWsfAzNzc0
1👍1
Forwarded from YeneTube
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
    🌹 የኔክሰስ ሆቴል
    🌹 የግራንድ ሆቴል
    🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
    🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
        ✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
        ✍️50/50  ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
1
መንግሥት በአማራ ክልል በሚወስዳቸው እርምጃዎች ለነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲደረግ ኢሰመኮ ጠየቀ!

በአማራ ክልል በመከላከያና በታጣቂ ሚሊሻዎች፣ ፋኖ የተነሳው ግጭት መባባሱን ተከትሎ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ።መንግሥት በሚወስዳቸው እርምጃዎች ነዋሪዎች ለበለጠ ጉዳት እንዳይጋለጡ ጥንቃቄ እንዲደረግ ኢሰመኮ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

“በአማራ ክልል ሰላም እና ደኅነነት ለማረጋገጥ መንግሥት በሚወስዳቸው እርምጃዎች ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ነዋሪዎች እንዳይዳረጉ ጥንቃቄ እንዲደረግም” ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም በአማራ ክልል ያለው “በትጥቅ የተደገፈ ህገወጥ እንቅስቃሴ በመደበኛ የሕግ ማስከበር ስርዓት ለመቆጣጠር ወደማይቻልበት ደረጃ መሸጋገሩንም” በመግለጽ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተላልፏል።

ኢሰመኮ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅትም ሰብዓዊ መብቶች ሊከበሩ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባም አስታውሷል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማናቸውም ሁኔታ የማይገደቡ መብቶችን የመጠበቅ፣ የተመጣጣኝነት እና ከመድልዎ ነጻ መርሆችን ባከበረ መልኩ እንዲተገበርም አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ነባሩ የደቡብ ክልል፤ በህዝበ ውሳኔ የተመሰረተው አዲሱ የ“ደቡብ ኢትዮጵያ” ክልል ስልጣን አስረከበ!

አስራ ሁለተኛ ክልል በመሆን ፌዴሬሽኑን የተቀላቀለው አዲሱ የ“ደቡብ ኢትዮጵያ” ክልል፤ ከነባሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ስልጣን ተረከበ። ነባሩ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለአዲሱ ክልል ስልጣኑን ያስረከበው፤ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 29፤ 2015 ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ነው።

አዲሱን ክልል በህዝበ ውሳኔ የመሰረቱት ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ምክር ቤቶች አፈጉባኤዎች፤ የየመጡባቸውን “ህዝብ ወክለው” ስልጣኑን ከነባሩ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ ተረክበዋል። አዲሱን የ“ደቡብ ኢትዮጵያ” ክልል የመሰረቱት የጌዲኦ፣ የወላይታ፣ የጋሞ፣ ጎፋ፣ የኮንሶ፣ የደቡብ ኦሞ ዞኖች እንዲሁም የቡርጂ፣ የአማሮ፣ የደራሼ፣ የባስኬቶ እና የአሌ ልዩ ወረዳዎች ናቸው።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለ12ኛው ክልል ስልጣን ከማስረከቡ በፊት፤ በነባሩ እና በአዲሱ ክልል መካከል የሚኖረው አስተዳደራዊ እና ህጋዊ ጉዳዮች የሚመሩበትን ስርዓት ለመወሰን የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ውይይት አድርጓል። የክልሉ ምክር ቤቱ ከዚህ በፊት በህዝበ ውሳኔ ለተመሰረቱ ሁለት ክልሎች ስልጣን ሲያስረክብም ተመሳሳይ አካሄድን መከተሉ ይታወሳል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
👍2
ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ።

👇👇

ጦርነት መፍትሄ አይኾንም፤ ከትናንት እንማር፤ ችግሮችን በውይይት እንፍታ! የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሃገራችን አንዳንድ አከባቢዎችና በተለይም በአማራ ክልል

ከዕለት ወደ ዕለት ተባብሶ የቀጠለውን የፀጥታ መደፍረስ ሁኔታ በአንከሮ እየተከታተለው ይገኛል።

በሀገራችን ሰሜናዊ ክፍል ለሁለት ዓመታት የተካሄደው ጦርነት ካደረሰብን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ገና በቅጡ እንኳ ባላገገምንበት በዚህ ወቅት፣ ዳግም ወደ ሌላ መጠነ ሰፊ የእርስ በርስ ግጭት መግባት በሕዝባችን ላይ የሚያደርሰው ማኀበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ ልቡናዊ ጉዳት በእጅጉ የሚያሳስብ ነው።

ጦርነት ከፍተኛ መጠን ያለው ሰብኣዊ እልቂትን እና ቁሳዊ ውድመትን ከማስከተል በቀር፣ ለችግሮቻችን መፍትኄ እንደማያስገኝ ከቅርብ ጊዜው ተሞከሯችን መማር አለመቻላችን እጅግ አሳዛኝ ነው። ይልቁንም በሀገር ውስጥ የሚካሄድ ጦርነት የሀገር አንድነት ፀንቶ የቆመባቸውን የእሴት እምዶች በማፍረስ የሕዝባችንን አንድነት የሚንድ በመኾኑ፣ ሁሉም አካላት ሁኔታውን ከማባባስ እንዲቆጠቡና ወደ ውይይት መምጣት የሚቻልበትን መላ እንዲያፈላልጉ ምክር ቤታችን በአንክሮ ለማሳሰብ ይወዳል።

ስለዚህም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ እጅግ አውዳሚና አክሳሪ ከኾነው ጦርነት የችግር መፍትኄን ከመጠበቅ ይልቅ፣ በአስቸኳይ ወደ ውይይት እንዲመጡ ጠቅላይ ምክር ቤታችን ይህን የሰላም ጥሪያችንን እያቀረብን ይህ እንዲሳካ ምከር ቤታችን አስፈላጊውን ለማድረግ ያለውን ዝግጁነት በዚሁ አጋጣሚ እንገልፃለን፡፡

አላህ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን!!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

አዲስ አበባ

ሐምሌ 29 ቀን 2015

@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📢 Don't miss out on amazing deals! Upgrade to Telegram Premium now! 🚀

Enjoy exclusive features:

📅 3 months = 1848 ETB 💎
📅 6 months = 2464 ETB
📅 1 year = 4466 ETB 🌟

🔥 Grab your Premium subscription today and elevate your Telegram experience! 🔥

💬 Hurry, limited time offer! Act fast! 💬

👉 For more information or to upgrade, contact @rudacx now! 👈
👍1
ከአዲስ አበባ ወደ ባሕርዳር በረራ መቋረጡን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬት ለቆረጡ ደንበኞች በሜሴጅ አስታውቋል ።

@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ ጠዋት በGlobal Study and international relation የተመረቀው ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ዛሬ ከሰዐት መታሰሩን ሰምተናል።

@Yenetube @Fikerassefa
የከንባታ ዞን የነባሩ ክልል በክላስተር መከፈሉን ተከትሎ የከንባታ ዞን 1 የክልል ቢሮ ብቻ መቀመጫ በመደረጉ ህዝቡ ለተቃውሞ አደባባይ መውጣቱን ከተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ተመልክተናል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍2
"ዳኜ ዋለ ከእስር ተለቋል‼️

በማህበራለዊ ገፁ "ሰለሁሉም ነገር እግዚያብሄር ይመስገን ሰላም ወጥተናል ዛሬ እኔ እና አርቲስት ቤዛዊት መስፍን" ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

@Yenetube @Fikerassefa
   "Do or Die..!" 

የተዋጣለት የሺያጪ ቻናል ፈልገዋል..!!!

ቤት ...
መሬት...
መካዝን...
ኢንዳስትሪ...
ኢንቨስትመንት...
ሪል ስቴት ..
ለትርፍ የሚሆኑ ለ 2 ..3..የሚከፈሉ ቦታዎችን ፈልገዋል ..

አዲስ አበባ ውስጥ የግዙፍ የግዢ እና የሽያጪ ቻናላችን ነው

..የምትወዱትን ሰው የሆነ ፍጥረት ወደ ቻናሉ ቤተሰብ በማደረግ መረጃን በቤትዎ ያስገቡ ..

መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ በማደረግ ሀላፊነታችሁን ተወጡ..!!!

   +251937736408
https://tttttt.me/shger21
  Inbox @FikreabAmanu

ለበለጠ መረጃ.. ቻናላችንን  ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/+U2S2JyiWsfAzNzc0