"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665

ኢትዮጵያ የገዛችው አንድ ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጅቡቲ ወደብ ይደርሳል!
ኢትዮጵያ የገዛችው አንድ ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጅቡቲ ወደብ የሚደርስ መሆኑን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታወቀ። ተጨማሪ አንድ ሚሊዮን ስኳር ግዢ ለመፈፀም እየተሠራ ነው።
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኮርፖሬት ጉዳዮች ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዘመድኩን ተክሌ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በ2014 ዓመተ ምህረት የኮቪድ ወረርሽኝ በሀገራት ምርትና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በመፍጠሩ ከውጭ ሀገር ወደ ውስጥ ስኳር ማስገባት ትልቅ ፈተና ሆኖ ነበር።
በ2014 ዓመተ ምህረት የነበረው የኮቪድ ተጽዕኖ እና በ2015 ዓመተ ምህረት የነበሩ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች እስከ አሁን ድረስ ስኳር ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ተግዳሮት ሆነዋል ያሉት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ በ2016 ዓመተ ምህረት በ110 ሚሊዮን ዶላር ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እየተሠራ ነው ብለዋል።
እንደ አቶ ዘመድኩን ገለፃ፤ በ2014 ዓመተ ምህረት ስኳር ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የተጀመረው ሥራ አሁን ላይ ተስፋ እየታየበት ነው። በዚህም ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ሁለት ዓለም አቀፍ ስኳር አቅራቢዎች የጨረታ አሸናፊ ሆነዋል። በጨረታውም መሠረት አንደኛው ስኳር አቅራቢ አንድ ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ የብራዚል ወደብ ላይ መድረሱን ገልጿል።
[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ለአራተኛ ጊዜ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ!
“አልፋ ሚዲያ” የተሰኘው የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን መስራች እና ባለቤት የሆነው ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፤ ትላንት እሁድ ሐምሌ 30፤ 2015 የሁለተኛ ዲግሪ የምርቃት ስነ ስርዓት ተሳትፎ ወደ መኖሪያ ቤቱ ከተመለሰ በኋላ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሉን ቤተሰቦቹ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። በጋዜጠኛ በቃሉ መኖሪያ ቤት ዛሬ ማለዳ ከ12፡30 ጀምሮ ለአንድ ሰዓት ያህል የቆየ ፍተሻ መካሄዱንም ቤተሰቦቹ ገልጸዋል።
ሶስት የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ እና ሲቪል የለበሱ የጸጥታ አካላት፤ በአዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ አካባቢ ወደሚገኘው የጋዜጠኛው መኖሪያ ቤት በመጀመሪያ የመጡት ትላንት ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ እንደሆነ ቤተሰቦቹ አስረድተዋል። የሁለተኛ ዲግሪ ምርቃቱን ከቤተሰቦቹ ጋር እያከበረ የነበረውን ጋዜጠኛ በቃሉን፤ “ለጥያቄ እፈልግሃለን” ብለው ሜክሲኮ አካባቢ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደወሰዱትም አክለዋል።
ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአማርኛ ቋንቋ እና ስነ ጽሁፍ መጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው በቃሉ፤ በትላንትናው ዕለት ከ“ኒው ጀነሬሽን” ዩኒቨርሲቲ በ“Global study and international relations” በማስተርስ ዲግሪ ተመርቋል። ጋዜጠኛው ይህን ትምህርት የተከታተለው “ከመሳደድ እና እስር ጎን ለጎን” መሆኑን ከምርቃቱ በኋላ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ጽፎ ነበር።
Via Ethiopia Insider

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲትን ዛሬ ረፋድ ላይ ተቀብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተካሄደው ስብሰባ ወቅት መሪዎቹ በሁለትዮሽ ጉዳዮች በንግድ፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም በቀጠናው ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተካሄደው ስብሰባ ወቅት መሪዎቹ በሁለትዮሽ ጉዳዮች በንግድ፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም በቀጠናው ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈጻሚ የኾነው የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግርና ግጭት "በውይይት" እና "ድርድር" ሊፈታ የሚችልበት ኹኔታ ዝግ እንዳልኾነና ለዚኹም "ተከታታይ ጥረቶች" እንደሚደረጉ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ተቋሙ በክልሉ "ለዘረፋ የተደራጁ" ያላቸው ኃይሎች' መንግሥታዊ መዋቅሮች እንዲፈርሱ፣ የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት እንዲያቋርጡና ክልሉን ከአዲስ አበባ ጋር የሚያገናኙ አንዳንድ መንገዶች እንዲዘጉ በማድረግ፣ በክልሉ ሕዝብ ላይ "ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር" እየሞከሩ ነው ብሏል። "ከሽብር ቡድኖች"፣ "ከሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር" እና "ከሙስና" ጋር ግንኙነት ያላቸው ከ3 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደሚገኙም ተቋሙ ገልጧል። በአማራ ክልል ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ስንት ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ግን ተቋሙ አልጠቀሰም።
[ዋዜማ]

በኦሮሚያ ክልል ሊፈታ ያልቻለው የጸጥታ ችግር እንዳሳሰበው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አስታወቀ።
-መንግሥት በበኩሉ ለአገሪቱ አለመረጋጋት ሰላማዊ እልባትን እንደ ቀዳሚ አማራጭ ከመውሰድ ቦዝኜ አላውቅም ብሏል።
«ኦሮሚያ የፍቅርና የሰላም ቀዬ መሆን ሲገባት ጸረ-ሰላምና ጸረ-ኦሮሞነት መርህን የሚያቀነቅኑ ተፈራርቀውባት ሰላሟን አጥታለች» ሲል መግለጫ ያወጣው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በክልሉ ሰላም ማስፈን ይገባል ሲል አመለከተ።በኢትዮጵያ እየተስፋፋ መጥቷል ያለው ውስብስብ የፖለቲካ ሂደትም በኦሮሚያ የዜጎችን ሕይወት ክፉኛ ጎድቷል ያለው ኦነግ፤ ዘለቄታዊ መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባም በመግለጫው ጠይቋል።
የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ ለሚ ገመቹ ለዶቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት ኦነግ መግለጫውን ባሁን ወቅት እንዲያወጣ ያስገደደው፤ «በኢትዮጵያ እየተከሰተ ባለው የስርዓት መሸራረፍ እና አለመረጋጋት የዜጎቻችን ደህንነት ስጋት ውስጥ መግባቱ ነው» ብለዋል።ኦነግ በዚህ መግለጫ በተለይም ባለፉት አራት ዓመታት አገሪቱ መቋጫ በሌለው ግጭትና ጦርነት ውስጥ መግባቷ ከዴሞክራሲያዊ መብትም መጣስ ባለፈ የህልውና ፈተናን ደቅኖ ቆይቷል ብሏል።
ፓርቲው በመግለጫ በተለያዩ ጊዜያት በአገሪቱ ፖለቲካዊ ውይይቶች እንዲደረጉ የቀረቡ ጥሪዎችም ተቀባይነት ማጣታቸው አሁን ለሚስተዋለው የከፋ አለመረጋጋት ምክንያት ነው ብሎ እንደሚያምንም ጠቁሟል። ኦነግ በመግለጫው አክሎም አሁን ላይ በሰሜን ኢትዮጵያ ጎልቶ የተስተዋለው አለመረጋጋት ወደ ኦሮሚያ እንዳይሰፋና የበዛ ቀውስ እንዳይፈጥርም ጥንቃቄ መወሰድ አለበት ብሏል።ቃል አቀዩ አቶ ለሚ ገመቹም፤ «ኦነግ ጥሪ ሲያቀርብበት የነበረውና አሁንም የሚያምነው ለሚስተዋለው ፖለቲካዊ ቀውስ ፖለቲካዊ መፍትሄ የሆነው የውይይት መንገድ መፈለግ ነው» ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ኢትዮጵያ ባለፉት 3-4 ዓመታት እየገፋች ላለው የሰላም እጦትና ያለመረጋጋት መንገድ ለመውጣት ለውይይት ዕድል እሰጣለሁ ከማለት ቦዝኖ እደማያውቅ ተደጋጋሞ ይገለጻል። የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ይህንኑን በማስመልከት ዛሬ ለዶቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት በኢትዮጵያ አለመረጋጋቶች መንግስታዊ ለውጥን ተከትሎ መከሰቱን አስታውሰዋል።«መንግሥት በሆደ ሰፊነት በውጪም የነበሩትን ኃይሎች ጭምር ወደ አገር እንዲገቡ አውድ አመቻችቶ ነበር። ያ በሂደት ውሎ አድሮ በየአከባቢው አለመረጋጋት ፈጥሯል።»አሁን ላይ አማራ ክልልን ለከፋ የጸጥታ ችግር ዳርጓል ያሉት ክስተትም ከዚህ እንደማይለይ የገለጹት አቶ ከበደ በተለይም ለሁለት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረውን ጦርነት እንደ መልካም አጋጣሚ የተጠቀሙ አካላት ትልቅ ስጋት ሆነዋል ነው ያሉት።
ይሁንና መንግሥታቸው ጉዳዩን በሰላም ለመፍታት ከአገር ሽማግሌ እስከ የሃይማኖት አባቶች በመላክ ሰፊ ጥረት አድርጓል ያሉት አቶ ከበደ፤ አሁን አማራ ክልልን ጨምሮ በአገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች ላሉ ችግሮች ወታደራዊ እርምጃዎች የሚወሰዱት የሰላም መንገዱ በር ሲደፈን ብቻ ነው ብለዋል። «የዜጎች እንቅስቃሴ በመገደብ መከላከያ ሠራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይሄድ በማድረግ የሰላም ጥረቱ ፍሬ እንዳላፈራ በመታየቱ ነው መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አውጆ ዜጎችን ለመታደግ ወደ እርምጃው ለመግባት በዝግጅት ላይ ያለው።» ያሉት አቶ ከበደ አክለውም በአማራ ክልል አሁን ጎልቶ የሚስተዋለው የሰላም እጦት ወደ ሌላ አካባቢዎች እንዳይዛመትና ችግሩ እንዳይሰፋም መንግሥታቸው ዝግጅት ማድረጉን አመልክተዋል።
[DW]

👍3
✅✅✅ "Do or Die..!" ✅✅✅
የተዋጣለት የሺያጪ ቻናል ፈልገዋል..!!!
ቤት ...❓
መሬት...❓
መካዝን...❓
ኢንዳስትሪ...❓
ኢንቨስትመንት...❓
ሪል ስቴት ..❓
ለትርፍ የሚሆኑ ለ 2 ..3..የሚከፈሉ ቦታዎችን ፈልገዋል ..❓❓❓
አዲስ አበባ ውስጥ የግዙፍ የግዢ እና የሽያጪ ቻናላችን ነው
..የምትወዱትን ሰው የሆነ ፍጥረት ወደ ቻናሉ ቤተሰብ በማደረግ መረጃን በቤትዎ ያስገቡ ..
መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ በማደረግ ሀላፊነታችሁን ተወጡ..!!!
+251937736408
https://tttttt.me/shger21
Inbox @FikreabAmanu
ለበለጠ መረጃ.. ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/+U2S2JyiWsfAzNzc0
የተዋጣለት የሺያጪ ቻናል ፈልገዋል..!!!
ቤት ...❓
መሬት...❓
መካዝን...❓
ኢንዳስትሪ...❓
ኢንቨስትመንት...❓
ሪል ስቴት ..❓
ለትርፍ የሚሆኑ ለ 2 ..3..የሚከፈሉ ቦታዎችን ፈልገዋል ..❓❓❓
አዲስ አበባ ውስጥ የግዙፍ የግዢ እና የሽያጪ ቻናላችን ነው
..የምትወዱትን ሰው የሆነ ፍጥረት ወደ ቻናሉ ቤተሰብ በማደረግ መረጃን በቤትዎ ያስገቡ ..
መረጃን በቀላሉ እንዲያገኙ በማደረግ ሀላፊነታችሁን ተወጡ..!!!
+251937736408
https://tttttt.me/shger21
Inbox @FikreabAmanu
ለበለጠ መረጃ.. ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/+U2S2JyiWsfAzNzc0
👍3
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
🌹 የኔክሰስ ሆቴል
🌹 የግራንድ ሆቴል
🌹 የኢግል ፓክ ኢንዱስትሪያል እና
🌹 የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
👉ባለ 2 መኝታ
👉ባለ 3 መኝታ
👉የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
👉ግንባታቸው 90% የደረሰ !!!
👉ማስረከቢያ ጊዜ ከ6 ወር -1 አመት
👉ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
✍️100% በ1 አመት በ"4"ዙር
✍️50/50 ከባንክ ጋር ከ5-20 አመት
🙏🙏🙏🙏🙏
ለበለጠ መረጃ
@setu1988
+251936606665
👍1
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመላው ሀገሪቱ የሚታዩ ግጭቶች “ያላንዳች ቅደመ ሁኔታ ቆመው” “በአስቸኳይ” በምክክር እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ።
ኮሚሽኑ ባለድርሻ አካላትን “በማቀራረብ፣ የልዩነት አጀንዳዎችን ሰብስቦ ለማወያየት እና ለማመካከር አመቺ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ዝግጁ መሆኑን” አስታውቋል።
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የሚመለከታቸው አካላት ልዩነቶቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው በምክክር እንዲፈቱ የጠየቀው፤ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 2፤ 2015 በጽህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርዓያ በንባብ ባሰሙት መግለጫ፤ ለሀገራዊ ምክክሩ የተሳታፊዎች የተሳታፊዎች ልየታ እየተከናወነ ባለበት ሁኔታ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አየታዩ ያሉ “ደም አፋሳሽ ግጭቶች” የኮሚሽኑን ስራ “አዳጋች እያደረጉበት ይገኛሉ” ብለዋል።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

‹‹በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት ድንገቴ ሳይሆን ለዓመታት የታመቀ ብሶት፣ የመጠቃት ስሜትና ተስፋ መቁረጥ የወለደው ነው›› - ኢዜማ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ(ኢዜማ) ነሐሴ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ‹‹ በዚህ ወቅት በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት ድንገት የተከሰተ ሳይሆን መንግሥት ሃላፊነቱን በተገቢው ሁኔታ ባለመወጣቱ የተከማቹ ሀገራዊ የፖለቲካ ትኩሳቶች የግለታቸው ጫፍ ላይ ሲደርሱ የተፈጠረ ነው ›› ሲል ገልፀለታል፡፡ፓርቲው በመግለጫው ‹‹ ይህ ለዓመታት የታመቀው ብሶት፣ የመጠቃት ስሜት እና ተስፋ መቁረጥ ገደፉን አልፎ ክልሉን አሁን ላለበት ሁኔታ ዳርጎታል ›› ሲልም አመልክቷል፡፡
‹‹ የዚህ ቀውስ መሠረታዊ ምክንያት በብልፅግና ውስጥ ያለው የጋራ ርዕይ መጥፋት፣ በየክልሉ እርስ በእርስ በመጓተት ላይ ያሉ ካድሬዎች የሚመሩት የመንግሥት የአስተዳደር ድክመትና በደል እንደኾነ ሊታወቅ ይገባል ›› ባይ ነው - ኢዜማ፡፡
‹‹ችግሩን ለማባባስ ፅንፈኛ የዘውጌ ፖለቲካ አስተሳስብን የሚያቀነቅኑ ታጣቂ ኃይሎች በጠራራ ፀሀይ ሰዎችን በመግደል ሽብርና ፍርሃት በመንዛት እንዲሁም ከግል ትርፋቸው ውጪ አንድ ስንዝር አርቀው ማሰብ የማይችሉ ያላቸው ባለሀብቶች የገንዘብ ድጋፍ በማድረጋቸው መሆኑን ›› አመልክቷል፡፡ፓርቲው በመግለጫው እነዚህ ‹‹ ፅንፈኛ ›› እና ‹‹ አርቀው ማሰብ የማይችሉ ›› ያላቸው ባለሃብቶች እነማን እንደሆኑ ግን በግልፅ አላስቀመጠም፡፡
‹‹ በሰላማዊ መንገድ የሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ ባልተሰጣቸው ቁጥር መፍትሔዎች ከጉልበት ይመነጫሉ!›› የሚል አስተሳስብ መሬት እየያዙ እየመጡ መሆኑ ያሰጋኛል የሚለው ኢዜማ ‹‹ በክልሉ የተከሰተውን ቀውስ ከማርገብ ጎን ለጎን መዋቅራዊ የሆነ ሀገር አቀፍ የዘላቂ ሰላም መላ እንዲበጅ ›› ጠይቋል፡፡‹‹ይህ ቀውስ መንግስት ሀላፊነቱን ባለመወጣቱ የመጣ መሆኑን ተገንዝቦ በግልጽ ራሱን ተጠያቂ በማድረግ ማህበረሰቡን በይፋ ይቅርታ ይጠይቅ ›› ሲልም አበክሮ አሳስቧል፡፡
‹‹መንግስት የሚዘውራቸው ›› ያላቸውና በስም የጠራቸው ‹‹ እንደ ፋናና ዋልታ ያሉ መገናኛ ብዙሃን የመንግስት ብቻ ሳይሆን የችግሩን ምንጭን ከመሰረቱ በማሳየት በደሎች ተዳፍነው እንዳይቀሩ የመስራት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ›› ሲልም ጠይቋል፡፡‹‹መንግሥት ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን አገናዝቦ ሀገርአቀፍ የዘላቂ ሰላም ፍኖተ-ካርታ በማዘጋጀት መዋቅራዊ እና ሕጋዊ የሰላም ግንባታ በአስቸኳይ ሊተገብር እንደሚገባም ›› ገልጿል፡፡
የፌደራልና የክልል መንግስታት ላለፉት አምሥት ዓመታት የፈጸሟቸውን ‹‹ የፖለቲካ ምህዳሩን የሚያጠብቡ ›› ያላቸው ተግባራት በመፈተሽ የሀገሪቱን የፖለቲካ ብዝኃነት የሚያንፀባርቅ የአሳታፊነት መርህን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸውን አስታውሷል፡፡መንግስት በሁሉም አካባቢዎች ማኅበረሰቡ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማኅበራት፣ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለማዳመጥ የሚያስችል መድረክ ማመቻቸት ይተበቅበታል ሲልም አሳስቧል፡፡
‹‹ ህዝቡም በበደል ስሜትና በቁጭት ተነሳስቶ አውዳሚ ወደሆነ መንገድ እንዳይጓዝ ደግሞ ደጋግሞ እንዲያስተውል ›› ሲል የጠየቀው ፓርቲው ‹‹ ከአብራኩ የወጣውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት በሚገባው ክብር ልክ በመረዳት አላስፈላጊ መስዋዕትነቶች እንዳይከፈሉ የሚቻለውን ሁሉ እንዲያደርግ ›› ጠይቋል፡፡በአራት ገፅ የተቀነበበው የኢዜማ መግለጫ ለታጠቁ አካላት ባስተላለፈው መልዕክት ‹‹ ታጣቂ ኃይሎች እንታገልለታለን ለምትሉት ማህበረሰብም ሆነ ክልል ከመሳሪያ አፈሙዝ የሚወጣ ዘላቂ ሰላም እንደማይገኝ በመረዳት ወደሰላማዊ መንገድ እንድትመጡ ›› ሲልም ጥሪውን ምክረ ሀሳቡን አቅርቧል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረዉ ግጭት ምክንያት የልማት ባንክ የተበላሸ ብድር 11 ቢሊዮን ብር ደርሶ እንደነበር ተገለፀ።
በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረዉ ጦርነት ምክንያት ብሔራዊ ባንክ የእፎይታ መመሪያ እስኪያወጣ ድረስ፣ ወደ 11 ቢሊዮን ብር የተበላሸ ብድር እንደነበረዉ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ዩሐንስ አያሌዉ አስታዉቀዋል።በትግራይ የነበሩ ፕሮጀክቶች ከጦርነቱ በፊት በአብዛኛው ጤናማ የሚባሉ እንደነበሩ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ ባንኩ 43 በመቶ የተበላሸ ብድር በነበረበት ወቅት 10 በመቶ ብቻ ድርሻ እንደነበራቸዉ ተናግረዋል።
ጦርነቱ ከተጀመረ በኃላ ግን ግንኙነቱ ስለተቋረጠ ሁሉም በሚባል ደረጃ ወደ ተበላሸ ብድር ገብተዋል ብለዋል በማብራሪያቸው።የተበላሸ ብድር የሚባለዉ ብድር መክፈያ ጊዜዉ እየተቆጠረ ሲሆን ሶስት ደረጃዎች አሉት፣ ያንን መተግበር ሳይቻል በሶስት ዓመት መክፈል ካልተቻለ ወደ ተበላሸ ብድር ዉስጥ እንደሚገባ አንስተዋል።
ከፕሪቶሪያዉ የሰላም ስምምነት በኃላ በትግራይ ያሉ ፕሮጀክቶች ያሉበትን መገምገሙን የተናገሩት አቶ ዩሐንስ፣ ብዙዎቹ ሙሉ ለሙሉ ያልተጎዱበትና ጥሩ ሁኔታ ላይ መኖራቸዉን ገልጸዋል።አሁን ላይ በትግራይ ያሉ ፕሮጀክቶች 80 በመቶ ወደ ስራ የገቡና ብድር በማግኝት ወደ እንቅስቃሴ መግባታቸዉን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአንድ ዓመት ከስድስት ወር የፎይታ ግዜ እንደሰጣቸዉ የሚገልፁት አቶ ዩሐንስ፣ በዚህ ዓመት ዉስጥ ባንኩም ድጋፍ እያደረገላቸዉ ወደ ጤናማ መንገድ ለማስገባት እየተሰራ እንደሆነ አብራርተዋል።ባለፈዉ ዓመት በአማራ እና አፋር ክልሎች በተመሳሳይ መንገድ ተሰርቶ በርካታ ፕሮጀክቶች ከተበላሸ ብድር ወጥተዉ ወደ ጤናማ መንገድ መግባታቸዉንም ገልፀዋል።
[Ethio FM]

👍2
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አቋርጦት የከረመውን እርዳታ ‹‹ ከብዙ ትችት ›› በኋላ በዝግታ መጀመሩን ይፋ አደረገ፡፡
የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለአምስት ወራት ገደማ በኢትዮጵያ አቋርጦት የቆየውን ሰብዓዊ ረድዔት ‹‹ በአነስተኛ መጠን ›› መጀመሩን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
የዓለም ምግብ ፕሮግራም እዚህ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ አስቀድሞ ከግብረሰናይ ድርጅቶችና የጤና ባለሙያዎች በኩል ‹‹ በመቶዎች የሚቆጠሩት በረሃብ በሚሞቱበት ሀገር እርዳተውን ማቋረጡን ኢ-ሞራላዊ ›› በማለት ሲተቹ መክረማቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡ድርጅቱ ይህን ‹‹ በዝግታና አነስተኛ መጠን ›› የጀመረው እርዳታ ‹‹ ለሙከራ ›› መሆኑን ጠቅሶ ለዚህም መንግስት በሂደቱ ላይ ሚናውን ስለመወጣቱ ዕውቅና ችሯል፡፡
ልክ እንደ ዓለም ምግብ ፕሮግራም ሁሉ ሰብዓዊ ረድዔቷን ያቋረጠችው ዩናይትድ ስቴትስ፣ እርዳታው በተቋረጠበት እንደሚቀጥል ገልፃ፣ ጎን ለጎን ‹‹ ለረዥም ጊዜ በክልል ባለስልጣናት ቁጥጥር ስር የሚገኘው አሰራርን ለማሻሻል የሚደረገው ድርድርን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንደምታካሄድ ›› አመልክታለች፡፡
ሁለቱ ተቋማት እርዳታ በማቋረጣቸው ምክንያት ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀጥር አንድ ስድስተኛው ወይም 20 ሚሊዮኑ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ የጠቀሰው የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ ከዚህ በተጨማሪ ስምንት መቶ ሺህ ያህሉ ስደተኞች መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለአሶሼትድ ፕሬስ በፅሑፍ በሠጠው ምላሽ ‹‹ በትግራይ ክልል በአራት ቅርንጫፎች፣ ለ100ሺህ ያህል ሰዎች እ.አ.አ. ከሐምሌ 31 2023 ወዲህ መጀመሩን ›› አመልክቷል፡፡
ድርጅቱ በአዲ አሰራሩ ምዝገባዎችን የሚያከናውነው ‹‹ በዲጂታል ›› መሆኑን ጠቅሷል፡ ለሰብዓዊ ረድዔት ሰራተኞችም ስልጣና ሰጥቼያለሁ ብሏል፡፡ ይህ አዲስ ያለው አሰራር በተቀረው የኢትዮጵያ ክፍልም እንደሚጀምር የገለፀው ድርጅቱ ‹‹ ሰብዓዊ ረድዔቶች ›› ለሚያስፈልጋቸው ብቻ እንዲደርሱ ያደርጋል የሚል ተስፋ መሰንቁንም ገልጧል፡፡
✍Asham