YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በጎንደር ከተማ እስራኤላዊ ዜጋ ታገተ በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ ገለጸ!

በጎንደር ከተማ አንድ እስራኤላዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ ታገተ በሚል በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው ሲል የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገለጸ፡፡የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮምሽነር አየልኝ ታክሎ፤ ሰሞኑን በአንዳንድ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች አንድ እስራኤላዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ በጎንደር ከተማ ታገተ በሚል በሀሰት የተለቀቀው መረጃ ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ እገታ ተፈጽሞብናል የሚል አቤቱታ ያቀረበ አካል እንደሌለም ተናግረዋል።ረዳት ኮምሽነሩ አክለውም፤ ተጨባጭ እና ባልተረጋገጠ መረጃ እገታ ተፈፅሟል የሚሉ አካላት የኅብረተሰቡን ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚያውክ በመሆኑ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ይህን ይበል እንጂ፤ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ፤ በዜግነት እስራኤላዊ የሆነ አንድ ግለሰብ በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ታግቶብኛል ሲል አስታውቋል፡፡የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመግለጫው፤ ግለሰቡ ጎንደር አቅራቢያ መታፈኑን ሰኞ ዕለት ሪፖርት እንደተደረገለት የገለጸ ሲሆን፤ አፋኞቹ ወንጀል ለመፈጸም ተነሳስተው ያደረጉት ነው ሲልም ገልጿል። ዲፕሎማቶች ከአከባቢው የጸጥታ ሀይሎች እና ከኢንተርፖል ጋር በመቀናጀት ታጋቹን ለማስለቀቅ እየሰሩ እንደሚገኙም አስታውቋል፡፡

የእስራኤል የመገናኛ ብዙሃን በበኩላቸው፤ እስራኤላዊው ታጋች እድሜው በ70ዎቹ የሚገመት መሆኑን ጠቅሰው፤ ከቀናት በፊት ወደ ጎንደር ከተማ ያቀናው ሕክምና ለማግኘት እንደነበር ገልጸዋል፡፡ከአጋቾቹ ጋር ኢንተርፖል እና የአከባቢው የጸጥታ ሀይሎች ግንኙነት ለማድረግ መሞከራቸውን ዘገባዎቹ ያመላከቱ ሲሆን፤ በወቅቱም ማስለቀቂያ ገንዘብ መጠየቃቸው ጠቁመዋል።

አጋቾቹ ግለሰቡን ለመልቀቅ በመጀመሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ጠይቀው እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ ካጋቾቹ ጋር በተደረገ ውይይት ገንዘቡ ወደ ሺዎች መውረዱም ነው የተጠቀሰው፡፡ታጋቹ እስራኤላዊ በድምጽ ለቤተሰቦቹ በላከው መልዕክት “እርዱኝ፣ በጫካ መሃል ላይ እገኛለሁ” ማለቱን ዘገባዎቹ ያስነበቡም ሲሆን፤ “ዝናብ እየዘነበብኝ ነው እርዱኝ፤ እሁድ ዕለት መምጣት ነበረብኝ ግን መቆየቴ አይቀርም፤ ልጆቼ እርዱኝ፣ አሁን ያለሁበት ሁኔታን ለጠላቶቼም አልመኘውም" ሲል መደመጡንም ገልጸዋል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
👍2
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፦ Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ለኢንትራንስ ፈተናን ይዘጋጁ፡፡ አፕሊኬሽኑ

ከ9 - 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ እና የማትሪክ ፈተናዎችን ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያቸው የያዘ ነው፡፡
የ7 ዓመት የኢንትራንስ ፈተና ከ2008 - 2014/15ዓም የያዘ ሲሆን በተጨማሪ የ3ዓመት የማትሪክ ፈተና ከ2008 - 2010ዓም ይዟል፡፡
ጥያቄዎችን በየክፍሉ እና በየመእራፉ ከፋፍሎ ያስቀመጠ ነው፡፡

ከ180,000 በላይ ተማሪዎች የሚጠቀሙት አፕሊኬሽን ሲሆን ፤ አፕሊኬኑን ለመጠቀም ከታች ካለው ሊንክ ዳውንልድ ያድርጉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
ከአዲስ አበባ የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ውል ባለመፈጸማቸው፤ ሁለተኛ ለወጡ ተጫራቾች ጥሪ ቀረበ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአንድ ወር በፊት የመሬት ሊዝ ጨረታ ባካሄደባቸው ቦታዎች ላይ ተጫርተው አንደኛ ከወጡ አሸናፊዎች ውስጥ፤ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በተሰጣቸው ጊዜ ውስጥ ውል አለመፈጸማቸውን የከተማዋ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው ውል ካልፈጸሙት አሸናፊዎች ውስጥ “የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የተጫረቱ” ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ግምት እንዳለው ገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከአራት ዓመት በኋላ የተደረገውን የመሬት ሊዝ ጨረታ ያወጣው በግንቦት 2015 መጀመሪያ ላይ ነበር። በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ 297 ቦታዎች በቀረቡበት በዚህ ጨረታ፤ ተወዳዳሪዎች ለአንድ ካሬ ሜትር መሬት እስከ 700 ሺህ ብር በሚጠጋ የመወዳደሪያ ዋጋ ተጫርተዋል። የከተማይቱ ቢሮ በግንቦት ወር መጨረሻ የ287 ቦታዎች አሸናፊዎች በለየበት ወቅት፤ ለአንድ ካሬ ሜትር 414 ሺህ ብር ካቀረቡ ተጫራች ከፍተኛው የማሸነፊያ ዋጋ መመዝገቡ ይፋ ተደርጓል።

የጨረታ አሸናፊዎቹን ዝርዝር ሰኔ 11፤ 2015 ያሳወቀው የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ፤ ተጫራቾች በአስር የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዳቸው ላይ ያቀረቡትን ቅድመ ክፍያ ፈጽመው ውል እንዲያስሩ ጥሪ አቅርቦ ነበር። ሆኖም በተሰጣቸው ቀነ ገደብ ውስጥ ውል የፈጸሙት የጨረታ አሸናፊዎች 131 ያህሉ ብቻ መሆናቸውን የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮው የለማ መሬት ማስተላለፍ ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ማዕድን በምቹ የግብይ ሥርዓት እንዲከናወን የሚያግዝ ዲጂታል መገበያያ ማዕከል ተከፈተ፡፡

የማዕድን ዲጂታል መገበያያ ማዕከልን ያስተዋወቀው በቀድሞ አጠራሩ “የኢትዮጵያ ማዕድን ነዳጅና ባዮፊውል ኮርፖሬሽን በአሁኑ መጠሪያው ደግሞ የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ነው፡፡ኮርፖሬሽን በማዕድን ዘርፍ ልማት ላለፉት 60 ዓመታት በውጭ ምንዛሪ ግኝት፣ በሰፊ ዕድል በፈጠራና በማህበረሰብ ልማት በርካታ ውጤቶችን ያስመዘገበ ተቋም መሆኑን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ራሄል ጌታቸው ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ከማዕድን ፍለጋና ልማት ሥራዎች በተጨማሪ የማዕድን ምርመራ ቁፋሮ (ድሪሊንግ)ና የማዕድን ላቦራቶሪ ፣ የማዕድን ጥናት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡ኮርፖሬሽናችን በትላንትናው ዕለት በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነውን የጌጣጌጥ ማዕድናት የኤሌክትሮኒክ ግብይት ሥርዓት ይፋ አድርጓል፡፡

ዲጂታል የግብይት ሥርዓት በመጠቀም ለጊዜው በጌጣጌጥ ማዕድናት ወደፊት ደግሞ ሌሎችንም ማዕድናት ለማስተዋወቅ ፣ ለመሸጥና ለመግዛት የሚያስችል መሆኑ ተነግሮለታል፡፡ይህ አዲስ ዲጂታል የግብይት ሥርዓት ለማዕድን ላኪዎች የንግድ መዳረሻዎችን ለማስፋት የሚያግዝ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ማዕድናት ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ነው ሲሉ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት በነበረው የጌጣጌጥ ማዕድናት የግብይት ሥርዓት ገዢና ሻጭን በተግቢው ደረጃ ለማገናኘት ከፍተኛ ችግር ያለበት፣ ግልጽኝነት የሌለውና ለኢ-መደበኛ የንግድ ሁኔታዎች የተጋለጠ መሆኑ ተነስቷል፡፡የዲጂታል ማዕድን የግብይት ሥርዓቱ በዓለም ላይ የሚገኙ እንደ ኦፓል፣ ሩቢ፣ ኤመራልድ፣ ሳፋየር፣ እና ሌሎች በርካታ የጌጣጌጥ ማዕድን ዓይነቶችን ከሸማቾች ጋር እንዲያገናኝ ተደርጎ መሰራቱ ተጠቅሷል፡፡

በዚህም የእያንዳንዱን የጌጣጌጥ ማዕድን ባህሪያት፣ የጥራት ደረጃ ከየት አገርና ቦታ እንደተመረቱ መግለጫ አለው ተብሏል፡፡የኢትዮጵያ ማዕድናት ዲጂታል የግብይት ሥርዓት በኢግል ላየን ቴክኖሎጂ ሲስተም ሶፍትዌሩ የተዘጋጀ ሲሆን ወጪው ደግሞ በዳሽን ባንክ እንደተሸፈነ ሰምተናል::

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዳይሬክተር ጂማ ዲልቦ በፈቃዳቸው ከኃፊነታቸው ለቀቁ!

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጂማ ዲልቦ በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።ዳይሬክተሩ ከአራት ዓመታ በላይ ከመሩት ተቋም ስራቸውን ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ በመንግስት ተቀባይነት ማግኘቱን ተናግረዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ኃላፊ ስራቸውን ለምን እንደለቀቁ ያሉት ነገር የለም።

ጂማ ዲልቦ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "ዘርፉ ከነበረበት ድባቴ ወጥቶ ለሀገር ልማትና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ አስተዋጽኦ ማበርከት መጀመሩ በቀጣይ ዓመታት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።ዋና ዳይሬክተሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ተሻሽሎ ተቋሙ ዳግም ሲደራጅ ጀምሮ ነበር በኃላፊነት ላይ የነበሩት።

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ 1 ሺህ 3 መቶ ገደማ ሰዎች በረሃብ ህይወታቸው ማለፉን የክልሉ ጊዜያዊ መስተዳድር አስታወቀ!

በትግራይ ክልል በዓለም አቀፍ ተቋማት ሲቀርብ የነበረዉ የሰብዓዊ ድጋፍ በክልሉ ተፈጽሟል ከተባለዉ ስርቆት ጋር በተያያዘ ከተቋረጠ ወራት አስቆጥሯል። የትግራይ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር የሆኑት ዶ/ር ገብረህይወት ገብረእግዚአብሔር ለብስራት ራዲዮ እንደተናገሩት ፤ በክልሉ በድምሩ 1 ሺህ 2 መቶ 98 ሰዎች በረሃብ ህይወታቸውን እንዳጡ ተናግረዋል።

በምዕራብ ትግራይ ዞኖች ከሚገኙ ተፈናቃዮች 5 መቶ 70 ሰዎች በምግብ እጥረት ህይወታቸው ማለፉን ኮሚሽነር ዶ/ር ገብረህይወት ገልጸዋል። በሌላ በኩል በሽሬ ፣ አዲግራት እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይና በመቀሌ ዙሪያ ባሉ ዞኖች እና ወረዳዎች 7 መቶ 28 ሰዎች በረሃብ ምክንያት መሞታቸዉን ከብስራት ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

እንደ ዶ/ር ገብረህይወት ገለጻ ፤ በክልሉ ያለዉ የረሃብና ቸነፈር ከፍተኛ በመሆኑ እንደ አክሱም እና ሌሎች መረጃ ባልተሰበሰባቸዉ አካባቢዎች ቀሪ ሶስት ዞኖች ያለዉ ወቅታዊ መረጃ ሲገኝ ደግሞ ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችል ጠቁመዋል። ከሟቾቹ ዉስጥ ነፍሰጡሮች ፣ ህጻናት እና እድሜያቸዉ የገፋ ሰዎች ከፍተኛዉን ድርሻ ይይዛሉ ብለዋል።

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በክልሉ ከ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጦርነቱ ምክንያት እርዳታ ጠባቂ እንዲሆኑ ተገድደዋል ብለዋል። ዶ/ር ገብረህይወት ለብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና ለአለማቀፍ ተራድዖ ድርጅቶች ችግሩ ከአቅም በላይ ደረጃ ላይ መድረሱን ብናሳዉቅም ድጋፍ እየቀረበልን አይደለም ብለዋል።

ብስራት ራዲዮ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አታለል አቦሀይን የሟቾች ቁጥርን በሚመለከት የጠየቀ ቢሆንም ቁጥሩ የተጋነነ መሆኑን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ለክልሉ እስከ ቅርብ ሳምንታት ድረስ ድጋፍ ማቅረቡንም ገልጸዋል። በጉዳዩ ላይም ጣቢያችን በተጨማሪ መረጃ ይመለሳል።

[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ25 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ!

ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ25 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ፡፡

አገልግሎቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለመሰብሰብ ካቀደው 27 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ውስጥ 25 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታውቋል።

በዚህም የዕቅዱን 93 በመቶ ማሳካት የተቻለ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ4 ነጥብ 665 ቢሊየን ብር ብልጫ ማሳየቱ ተጠቁሟል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ የሚገኙ የቤተክርስቲያኗ ሊቀ ጳጳሳት ሐምሌ 9 እናካሂደዋለን ያሉትን የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ መንግሥት እንዲያስቆም ጠይቋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳና ሌሎች የፌደራልና ክልል ባለሥልጣናት ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ "መንግሥታዊ እገዛ" እንዲያደርጉና "የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹም" ሲኖዶሱ ጥሪ አቅርቧል። በትግራይ የሚገኙ ጳጳሳት የውይይት በሮችን በመዝጋትና "መዋቅራዊ አደረጃጀትን በመጣስ" እናካሂዳለን ያሉት የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ "ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ"፣ "የቤተክርስቲያኗን ማዕከላዊነት የሚጥስ"፣ "አንድነቷን የሚጎዳ"፣ "ሕዝብን የማይጠቅም" እና "ተገቢነት የሌለው" መኾኑን ሲኖዶሱ ጠቅሷል። ሲኖዶሱ ባለፈው ሳምንት ለትግራይ ሕዝብና ጳጳሳቱ ላቀረበው ይቅርታ፣ ጳጳሳቱ አዎንታዊ ምላሽ አለመስጠታቸው "በእጅጉ አሳዛኝ" እንደኾነም ገልጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፦ Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ለኢንትራንስ ፈተናን ይዘጋጁ፡፡ አፕሊኬሽኑ

ከ9 - 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ እና የማትሪክ ፈተናዎችን ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያቸው የያዘ ነው፡፡
የ7 ዓመት የኢንትራንስ ፈተና ከ2008 - 2014/15ዓም የያዘ ሲሆን በተጨማሪ የ3ዓመት የማትሪክ ፈተና ከ2008 - 2010ዓም ይዟል፡፡
ጥያቄዎችን በየክፍሉ እና በየመእራፉ ከፋፍሎ ያስቀመጠ ነው፡፡

ከ180,000 በላይ ተማሪዎች የሚጠቀሙት አፕሊኬሽን ሲሆን ፤ አፕሊኬኑን ለመጠቀም ከታች ካለው ሊንክ ዳውንልድ ያድርጉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
👍1
የአማራ ክልል በአወዛጋቢዎቹ የአማራና ትግራይ አካባቢዎች ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ማቀዱን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቃወመ!

የአማራ ክልል መንግስት አወዛጋቢ በተባሉ የአማራና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ማቀዱ እንደሚቃወም የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ።የአማራ ክልል መንግስት በሐይል በተያዙ ባላቸው አከባቢዎች ሕገወጥ ስራዎች እየከወነ ነው ሲል የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ከሷል። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ቺፍ ካቢኔ ሴክሬታሪያት አቶ አማኑኤል አሰፋ ከምዕራብ ትግራይ እና ራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀያቸው እንዲመለሱ የፌደራሉ መንግስት ሐላፊነቱ ሊወጣ ይገባል ሲሉም ለዶቼቬለ ተናግረዋል።ከዚህ በተጨማሪ ህዝብ ተፈናቅሎ ባለበት በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ ማቀድ፥ በኃይል የተያዘ ላሉት መሬት ሕጋዊ ሽፋን መስጠት ነው ሲል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የተባለ በትግራይ የሚንቀሳቀስ ተቃዋሚ ፓርቲ ገልጿል።

የአማራ ክልላዊ መንግስት ላለፉት 30 ዓመታት ይገባኛል ጥያቄ ይነሳባቸው ነበሩ ያሏቸው በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ ያሉ አካባቢዎች፣ ውዝግቡ በህዝበ ውሳኔ እንዲፈታ ጥረት እያደረገ መሆኑ በቅርቡ በክልሉ ኮምኒኬሽን ቢሮ በኩል ተገልጿል። በትግራይ ያለው ጊዚያዊ አስተዳደር ይህን የአማራ ክልል መንግስት ህዝበ ውሳኔ የማካሄድ ፍላጎት እንደማይቀበለው አስታውቋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ከትግራይ ክልል አስተዳደር በኩል ስላለው አቋም የጠየቅናቸው የግዚያዊ አስተዳደሩ ቺፍ ካቢኔ ሴክሬታሪያት አቶ አማኑኤል አሰፋ የአማራ ክልላዊ መንግስት ሕጋዊ ያሏቸው የትግራይ ግዛቶች ላይ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ማቀዱ ሕገወጥ ግዛት የማስፋፋት ተግባር ብለው የኮነኑት ሲሆን የሀገሪቱን ሕገ መንግሥትም ወደጎን የገፉ ሲሉ ገልፀውታል።

በትግራይ የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የተባለ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲም በበኩሉ የአማራ ክልላዊ መንግስት እና የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከወሰንና ማንነት ጋር በተያያዘ አወዛጋቢ በተባሉ የአማራና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ጉዳዩ ወደ ህዝበ ውሳኔ እንዲያመራ ማቀዳቸውን ሕገወጥ አካሄድ ብሎታል። ከጦርነቱ በኃላ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባ የነበረው የትግራይ ግዛታዊ አንድነትን ማስከበር፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ እና የመሳሰሉ ጉዳዮችን ወደጎን በመተው የትግራይን ግዛት በኃይል ወሮ በመያዝ፣ የተወረረ ላሉት ግዛት ሕጋዊ ሽፋን ለመስጠት የሚደረግ እንቅስቃሴ ሲሉ ያወገዙት የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ኮምኒኬሽን ሐላፊ አቶ ኃይለአብ ኃይለስላሴ ይህ አካሄድ በዘላቂ ሰላም እና በህዝቦች ጉርብትና ላይም አሉታዊ ጫና የሚፈጥር ብለውታል።የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ቺፍ ካቢኔ ሴክሬታሪያት አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የፈረመውን የፕሪቶርያ ውል አክብሮ በትግራይ ያሉ የውጭ ኃይሎችን እንዲያስወጣ፣ ሕገወጥ ተግባራትንም እንዲከላከል ፣ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
1👍1
እስራኤል በጎንደር ታግቶብኛል ያለችዉን ዜጋዋን ይፋ አደረገች!

የእስራኤል የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቀናት በፊት በጎንደር ከተማ አቅራቢያ እድሜዉ 79 አመት የሆነ ግለሰብ ትግቶብኛል ሲል መግለጫ ማዉጣቱ ይታወሳል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የጎንደር ከተማ መስተዳድር ፖሊስ መምሪያ ምንም የቀረበለት ሪፖርት አለመኖሩን ብስራት ራዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።

ከዚህ ዉዝግብ በኋላ እስራኤል ታግቷል ያለችዉን ዜጋዋን ይፋ አድርጋለች። "ዉዶ አደባባይ" የተኘዉ የ 79 አመት ግለሰብ ወደ ኢትዮጵያ ለህክምና እና በጎንደር የሚገኙ ዘመዶቹን ለመጎብኘት መምጣቱን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የእገታው አላማ ከቤተሰቦቹ ገንዘብ ለመቀበል ያለመ እንደሆነ ጠቅሷል። አፋኞቹ ከቤተሰቦች ጋር አደረጉት በተባለዉ ንግግር እስከ 2.5 ሚሊዮን ብር ድረስ ጠይቀዉ ነበር አቪ የተሰኘ የታጋቹ ግለሰብ ወንድ ልጅ ተናግሯል።

አለማቀፉ የወንጀል ፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ግለሰቡን ለማስለቀቅ የኢትዮጵያ የጸጥታ አካላትን እያነጋገረ ነዉ ቢባልም ፤ የጎንደር ከተማ መስተዳድር ፖሊስ መምሪያ ከእገታዉ ጋር በተያያዘ የቀረበልኝ አቤቱታም ሆነ የማዉቀዉ ጉዳይ የለም ማለቱ ይታወሳል።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በታጣቂዎች በተሰነዘረ ጥቃት ስምንት ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት አርብ ሰኔ 30 በታጣቂዎች በተሰነዘረ ጥቃት፤ ሶስት የአካባቢ ሚሊሺያዎችን ጨምሮ ስምንት ሰዎች  መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። ሌሎች 16 ሰዎች ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ላይ መሆናቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋሙ ገልጿል። 

ኢሰመኮ በታጣቂዎች ጥቃት የሰዎች ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት መድረሱን የገለጸው፤ ትላንት ሐሙስ ሐምሌ 6፤ 2015 ምሽት ባወጣው መግለጫ ነው። ኮሚሽኑ ከጥቃቱ በኋላ አደረግኩት ባለው ክትትል፤ ድርጊቱን የፈጸሙት “ከመንግሥት ጋር በተደረገው ስምምነት መሠረት ትጥቅ ለማስፈታት በሚል አንድ ካምፕ ውስጥ እንዲሰፍሩ የተደረጉ የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) ታጣቂ ቡድን አባላት” መሆናቸውን እንደደረሰበት ገልጿል።

ኢሰመኮ የአካባቢውን ነዋሪዎች እና የአስተዳደር ኃላፊዎች በማናገር “ጥቃቱን ያደረሱት የጉህዴን ታጣቂዎች ናቸው” ይበል እንጂ፤ የጉህዴን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ደርጉ ፈረንጅ ግን “እነሱ እንደሚያወሩት አይደለም” ሲሉ የኮሚሽኑን መግለጫ ተቃውመዋል። “የጉህዴን ታጣቂ ተብለው የሚጠሩት ታጣቂዎች “ትጥቃቸውን እንዲፈትቱ አድርገናል” የሚሉት አቶ ደርጉ፤ በሌሎች የመተከል ዞኖች የገቡ የጉህዴን ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታታቸውን ተናግረዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
ፐርፐዝ ብላክ ለሚገነባው "ከገበሬው ታወር" የቢጂአይ ኢትዮጵያን ዋና ቢሮን ሕንጻ ጨረታ በ5 ቢሊዮን ብር ማሸነፉን አስታወቀ!

ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች በአዲስ አበባ ከተማ መሀል ሜክሲኮ ላይ ለሚገነባው "ለገበሬው ታወር ሼር ሆልደር ሞዴል ሕንጻ" የቢጂአይ ኢትዮጵያን ዋና ቢሮ ሕንጻን ጨረታ፤ በ5 ቢሊዮን ብር በማሸነፍ የ1 ቢሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ መፈጸሙን በዛሬው ዕለት በስካይላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል።

ፐርፐዝ ብላክ ባለ 115 ወለል የከገበሬው ታወር እና በዙሪያው የሚገነቡትን ለመኖሪያ፣ ለንግድ፣ ለመዝናኛ እንዲሁም፤ ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውሉ 6 ሕንጻዎችን ያካተተውን "ታወር ሼር ሆልደር ሞዴል" የተሰኘ የአክሲዮን ሥርዓት ባለፈው ታሕሳስ ወር በይፋ ማስጀመሩ ይታወሳል።

ኩባንያው ፕሮጀክቱን ካስተዋወቀበት ጊዜ አንሥቶ የከገበሬውን ታወር ግንባታ ለማከናወን የሚያስችለውን ቦታ በሜክሲኮ፣ በለገሃር፣ እና ፍልውሃ አካባቢ ሲፈላልግ መቆየቱን የፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ ተናግረዋል።

በስተጨረሻም ቢጂአይ ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያ ቤቱን ወደ ሰበታ ማዘዋወሩን ተከትሎ በመሃል ሜክሲኮ የሚገኘውን የተቋሙን ዋና መሥሪያ ቤት በጨረታ ለሽያጭ ማቅረቡን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ፐርፐዝ ብላክ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ጨረታውን በቀዳሚነት ማሽነፍ መቻሉን ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት ኩባንያው ሰማይ ጠቀሱን የከገበሬው ታወር እንዲሁም በታወር ሼር ሆልደር ሞዴል ፕሮጀክት ሥር የሚገነባቸውን ሕንጻዎች ለመገንባት በጨረታ ያሸነፈውን የቢጂአይ ኢትዮጵያ ዋና ሥሪያ ቤት ጨረታ ግዢ፤ 1 ቢሊዮን ብር ቅድ ክፍያ መፈጸሙን አስረድተዋል።

ፐርፐዝ ብላክ የቅድመ ክፍያዉን ጨምሮ በሦስት ግዜ ክፍያ የሚፈጸም ዉል ከቢጂአይ ኢትዮጵያ ጋር ማሰሩንም በመግለጽ፤ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር እና 1.5 ቢሊዮን ብር ቀሪ ክፍያ በቀጣይ እንደሚከፈል ተናግረዋል።ኩባንያው ሊገነባው ያሰበው ሕንጻ የቢጂአይ ዋና መስሪያቤት ሕንጻን ጨምሮ 30 ሺሕ ካሬ ሜትር ላይ እንደሚያርፍ የተነገረ ሲሆን፤ ግንባታው የመኖሪያ አፓርታማን ጨምሮ ሌሎች ሕንጻዎች እንደሚያካትትም ተገልጿል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ኩባንያው ግንባታዎቹን ለማከናወን ባዘጋጀው የአክሲዮን ሥርዓት ልዩ ልዩ እቅስቃሴዎች ሲያከናውን መቆየቱን የተናገሩት ዶ/ር ፍሰሃ፤ ቀደም ሲል ከግንቦት21 እስከ ሰኔ 06 2015 ለአንድ ሺሕ ዕድለኞች አዘጋጅቶት በነበረው እና 100 ካሬ ላይ የሚያርፍ ባለ 3 መኝታ መኖሪያ ቤት በስጦታነት በሚያስኘው ልዩ የ1.5 ሚሊዮን ብር የማስታወቂያ አክሲዮን ሽያጭ እንደንደነበር ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት ከሕንጻዎቹ መካከል አንዱን ምድር ቤትን ያካተተባለ 54 ፎቅ የመኖሪያ አፓርታማ አክሲዮንን ለገዙ 1 ሺሕ ዕድለኛ ባለአክሲዮኖች ግንባታው እንደተጠናቀቀ በስጦታ የሚያበረክትበት ዕድል ማመቻቸቱን ገልጿል።በተጨማሪም ኩባንያው ከሐምሌ 1 እስከ ሐምሌ 16 2015 በሚቆይ ኹለተኛ ዙር የታወር ሼር ሆልደር ሞዴል አክሲዮን ሽያጭ ለ750 ቀዳሚ ዕድለኞች ማዘጋጀቱ አስታውቋል።

በዚህም እንደቀደመው አክሲዮን 100 ካሬ ላይ የሚያርፍ ባለ 3 መኝታ መኖሪያ ቤት በ3.5 ሚዮን ብር የአክሲዮን ዋጋ ሌላኛውን አፓርታማ ለባለአክሲዮኖቹ በስጦታ ለማበርከት በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።የአክሲዮን ሽያጩ ዋጋው 3.5 ሚሊዮን ብር ሆኖ በቅድሚያ 3 ሚሊዮን ብር ተከፍሎ ቀሪው 500 ሺሕ ብር ክፍያ በ5 ዓመታት የጊዜ ገደብ ከወለድ ነጻ በሆነ ሥርዓት እንደሚፈጸም ተገልጿል።

ፐርፐዝ ብላክ ሊገነባው ካሰበው ለገበሬው ታወር ሼር ሆልደር ሞዴል ሕንጻ" ጋር በተያያዘ ብዙ ውዝግቦች ሲነሱ መቆየታቸው ይታወቃል።ከዚህም ጋር ተያይዞ በቦታዉ ግዢ ሂደት ላይ የፌደራል ፖሊስ ተገቢዉን ምርመራ አከናዉኖ የገንዘቡ ምንጭ ሕጋዊነት ተረጋግጦ የቢጂአይ ኢትዮጵያ ዋና መስሪያቤትን ባለቤት ለመሆን መብቃቱን ዶ/ር ፍሰሃ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት የብአዴን ከፍተኛ አመራር አቶ ታደሰ ካሳ በነጻ ከእስር እንዲለቀቁ ወሰነ።

ከተፈረደባቸው ስምንት ዓመት ከአምስት ወር እስር ውስጥ ግማሽ ያህሉን ያጠናቀቁት የቀድሞው የብሔር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ከፍተኛ አመራር አቶ ታደሰ ካሳ፤ ከእስር እንዲፈቱ የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ አስተላልፏል።የሰበር ሰሚ ችሎቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው፤ የአማራ ክልል ጠቅላይ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች እንዲሁም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጧቸውን ውሳኔዎች በመሻር ነው።

ከሌላኛው የብአዴን ጎምቱ ፖለቲከኛ አቶ በረከት ስምኦን ጋር በቀረበባቸው ክስ ተፈርዶባቸው የነበሩት አቶ ታደሰ፤ ከቀረበባቸው ክስ ነጻ ያደረጋቸው ውሳኔ በፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት የተላለፈው ትላንት ሐሙስ ሐምሌ 6፤ 2015 እንደሆነ ጠበቃቸው ህይወት ሊላይ ለ“ኢትዮጵያር ኢንሳይደር” ተናግረዋል።ሰበር ሰሚ ችሎቱ በትላንትናው ዕለት ውሳኔ ለመስጠት ቀጥሮ የነበረው፤ አቶ ታደሰ ለችሎቱ ያቀረቡትን ቅሬታ ሲመረምር ከቆየ በኋላ መሆኑን ጠበቃቸው ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ገልጸዋል።

አቶ ታደሰ በ2011 ዓ.ም በአማራ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ የቀረበባቸው፤ በስራ አስፈጻሚነት ሲመሩት ከነበረው ጥረት ኮርፖሬት ጋር በተያያዘ ነው።ከቀድሞው የአማራ ክልል ገዢ ፓርቲ ብአዴን ጋር ግንኙነት የነበረው ጥረት ኮርፖሬት፤ “በቂ ጥናት ሳይደረግ ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር ለመስራት ውል ገብቷል። በዚህም ድርጅቱ ጉዳት ደርሶበታል” በሚል ነበር አቶ ታደሰ የተከሰሱት።

ከህዳር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ተጠሪነቱ ለአማራ ክልል ምክር ቤት እንዲሆን የተደረገው ጥረት ኮርፖሬት፤ ዳሸን ቢራ ፋብሪካ፣ አምባሰል የንግድ ስራዎች የመሳሰሉ ተቋማትን እና በእርሻና የመጓጓዣው ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎችን የሚያስተዳድር ነው።በቀረበባቸው ክስ በግንቦት 2012 ዓ.ም ጥፋተኛ የተባሉት አቶ ታደሰ፤ የአማራ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስምንት ዓመት ከአምስት ወራት እስር እንዲሁም የ15 ሺህ ብር ቅጣት አስተላለፎባቸው ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
የሩስያ ምክር ቤት ጾታ መቀየርን ዛሬ በሕግ አገደ።

የሩስያ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት ዱማ በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው አዲሱ ሕግ ጾታ መቀየርን ሕገ ወጥ ያደርጋል። ሕጉ ስራ ላይ እንዲውል በሩስያ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እና በፕሬዝዳንት ፑቲን መጽደቅ አለበት።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፦ Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ለኢንትራንስ ፈተናን ይዘጋጁ፡፡ አፕሊኬሽኑ

ከ9 - 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ እና የማትሪክ ፈተናዎችን ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያቸው የያዘ ነው፡፡
የ7 ዓመት የኢንትራንስ ፈተና ከ2008 - 2014/15ዓም የያዘ ሲሆን በተጨማሪ የ3ዓመት የማትሪክ ፈተና ከ2008 - 2010ዓም ይዟል፡፡
ጥያቄዎችን በየክፍሉ እና በየመእራፉ ከፋፍሎ ያስቀመጠ ነው፡፡

ከ180,000 በላይ ተማሪዎች የሚጠቀሙት አፕሊኬሽን ሲሆን ፤ አፕሊኬኑን ለመጠቀም ከታች ካለው ሊንክ ዳውንልድ ያድርጉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከተቀመጡት ተማሪዎች ውስጥ 40.65 በመቶዎቹ የማለፊያ ነጥብ አስመዘገቡ!

ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከተቀመጡት ተማሪዎች ውስጥ 40 ነጥብ 65 በመቶዎቹ የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገባቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ከሰኔ 30 ቀን ጀምሮ ለስድስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የዩኒቨርሲቲ ትምህርት መውጫ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ገልፀዋል።

ለመውጫ ፈተና ሊቀመጡ ይችላሉ ተብሎ ተገምቶ ከነበረው 240 ሺህ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን 194 ሺህ 239 ተማሪዎች ብቁ ሆነው ለፈተና መመዝገባቸውንም ነው የተናገሩት።

ከዚህ ውስጥ ከ48 የመንግስት ተቋማት 84 ሺህ 627 ተማሪዎች እና ከ171 የግል ተቋማት 109 ሺህ 612 ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውም ነው የገለጹት።

የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡት ውስጥ ከመንግስት ተቋማት 77 ሺህ 981 ተማሪዎች እንዲሁም ከግል ተቋማት 72 ሺህ 203 ተማሪዎች በድምሩ 150 ሺህ 184 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 61 ሺህ 54 ተማሪዎች ወይም 40 ነጥብ 65 በመቶ የማለፊያውን ነጥብ አስመዝገበዋል ነው የተባለው፡፡

ለተቋማትም የተማሪዎቻቸውን ውጤት የመላክ ሥራ መጀመሩንም ጠቁመዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሙሽራ ሸኝተው በመመለስ ላይ ሳሉ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሟቾች ቁጥር 10 ደረሰ!

በስልጤ ዞን ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ጃረሞ ሰምቦዬ ቀበሌ ጀኔ ማዞሪያ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሟቾች ቁጥር አሥር መድረሱን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የስልጤ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሸምሱ ኢክማ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ አደጋው የደረሰው ትናንት ምሽት በግምት 5፡00 ገደማ ነው፡፡

አደጋው የደረሰባቸው ሰዎችም ሙሽራ ሸኝተው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ ናቸው ብለዋል፡፡                                                
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ ኤክስፕረስ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት።

ዛሬ ከአዲስ አበባ እቃ ይላኩ
ነገ በጠዋት ይቀበሉ።

አዳማ
ሀዋሳ
ሻሸመኔ
አዲስ አበባ

📞0962627762
🤳0980526262
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ተከናወነ!

የኤጲስ ቆጶሳቱ ሹመት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ መሪነት በመንበረ ፓትሪያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባደረገው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ መሠረት ለዘጠኙ ቆሞሳት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መሪነት በሊቃነ ጳጳሳት አንብሮተ ዕድ ተፈጽሟል።

በዚህ መሰረት
1. ቆሞስ አባ ክንፈ ገብርኤል ተ/ማርያም አባ ገሪማ ተብለው የጌዲኦ፣ አማሮና ቡርጅ ሀገረ ስብከት፣

2. ቆሞስ አባ ሳህለ ማርያም ቶላ አባ ገብርኤል ተብለው የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣

3. ቆሞስ አባ ስብአት ለአብ ሀይለማርያም አባ ጢሞቲዎስ ተብለው የዳወሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት፣

4. ቆሞስ አባ አምደሚካኤል ኃይሌ አባ ኤልሳዕ ተብለው የምስራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት፣

5. ቆሞስ አባ ሀይለማርያም ጌታቸው አባ በርቶሎሜዎስ ተብለው የድሬደዋ ሀገረ ስብከት፣

6. ቆሞስ አባ ጥላሁን ወርቁ አባ ኤፍሬም ተብለው የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት፣

7. ቆሞስ አባ ዘተ/ሀይማኖት ገብሬ አባ ኤጲፋንዮስ ተብለው የሆሮ ጉድሩ ሀገረ ስብከት፣

8. ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ገብሬ አባ ዳንኤል ተብለው የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት እና

9. ቆሞስ አባ ወ/ገብርኤል አበበ አባ ኒቆዲሞስ የምስራቅ ሀረርጌ ሀገረ ስብከት ሆነው መሾማቸውን የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa