መንግስት 2 ሚሊዮን የስራ ስምሪት ጥያቄ ከዉጭ ሀገራት እንደቀረበለት አስታወቀ!
ጠ/ሚ አብይ አህመድ የስራ እድል እና ፈጠራ ክህሎት በሚኒስቴር ደረጃ ኢትዮጵያ ውስጥ ተቋቁሞ እንደማያውቅ ለተወካዮች ምክር ቤት በሚያብራሩበት ወቅት ገልፀዋል።ከተለያዩ ዓለም ሀገራትም መንግስት 2 ሚሊየን ገደማ የሰራተኛ ስምሪት ጥያቄ ቀርቦለት እየተፈራረመ መሆኑን ጠ/ሚንስትሩ ተናግረዋል።
በዚያ ደረጃ እንዲቋቋም የተፈለገበት ደረጃ ስራ አጥነትን መቀነስ ነው ስራ አጥነትን መቀነስ ሰላም ያመጣል ብለዋል።ሰፋፉ የስራ እድል ቢፈጠር ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ይቀነሳል የሚል እምነት በመያዙ ተቋሙ በሪፎርሙ በሚኒስትር ደረጃ እንዲቋቋም መደረጉን ገልፀዋል።
ከፍተኛ ለውጥ እያመጡ ካሉ የፌደራል ተቋማት አንዱ የስራ እድል እና ፈጠራ አንዱ መሆኑን አንስተዋል። በተጨማሪ የስራ ስምሪት ቁጥጥር በሀገር ውስጥ መቶ በመቶ በሚቀጥለው ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል ። ማን ስራ እንደያዘ እና የት ስራ እንደያዘ ስለሚታወቅ የውሸት ሪፖርቶችን ለማስቀረት ይረዳል ብለዋል ።
ባለፉት 11 ወራት 3.1ሚሊየን ገደማ ሰዎች ስራ መያዛቸውንም ገልፀዋል። ከነዚህም ውስጥ በግብርና 1.2ሚሊየን የሚጠጋ ሰው፣በኢንደስትሪ 600ሺ ገዳማ፣ አገልግሎት፣1.2ሚሊየን ገደማ፣ለውጭ ህጋዊ በሆነ መንገድ 100ሺ ሰው ገደማ ስራ መያዙን ጠቅሰዋል።
@YeneTube @FikerAssefa

የህዳሴ ግድብ ሙሌት እስከ መስከረም መጀመሪያ እንደማይከናወን ጠ/ሚ ዐቢይ ተናገሩ!
ኢትዮጵያ የሱዳንን እና ግብፅ ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ የህዳሴ ግድብ ሙሌቱ እስከ መስከረም መጀመሪያ እንደማታከናዉን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ተናግረዋል።ከዚህ ቀደም ሀምሌ አጋማሽ የግድቡን የዉሃ ሙሌት ስናከብር ነበር ያሉት ጠ / ሚኒስትሩ ዘንድሮ ግን በቂ የዉሃ መጠን ለሁለቱ ሀገራት ከደረሰ በኋላ ሙሌቱ እንደሚከናወን መናገራቸው ተሰምቷል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዙር ሙሌት የተከናወነ ሲሆን በዘንድሮዉ ክረምት አራተኛዉ ሙሌት ለማከናወን እቅድ ተይዞ ነበር። ሆኖም ኢትዮጵያ የሁለቱ ሀገራትን ጥያቄ በማክበር ይህን እቅድ ማራዘሟን ነዉ ጠ/ሚኒስትሩ የተናገሩት።
ሱዳን እና ግብፅ በተደጋጋሚ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ አሳሪ ስምምነት እንዲፈጸም ፍላጎት እንዳላቸዉ ሲገለጽ ቆይቷል። በተለይም ግብፅ ለአፍሪካ ኅብረት፣ ለአረብ ሊግ፣ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ለኃያላኑ ምዕራባውያን በተደጋጋሚ ከግድቡ ጋር በተያያዘ አቤቱታዋን ስታሰማ እንደነበር ይታወቃል።

‹‹በመንግስት በጀት የተሰሩ 130 ሺህ ኮንዶሚኒየሞች በዚህ ክረምት ለተጠቃሚ እናስረክባለን፡፡›› -ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
በአዲስ አበባ በመንግስት በጀት የተሰሩ 130 ሺህ ኮንዶሚኒየሞች እና 5 ሺህ ቁጠባ የኪራይ ቤቶች ተሰርተዉ ማለቃቸዉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡እነዚህን ቤቶች በዚህ ክረምት ለነዋሪዎች እናስረክባለን ነዉ ያሉት፡፡
በመንግስት የሚሰራዉ በመንግስት በጀት፣ በልመና የሚሰራዉ በልመና እንዲሁም ደግሞ በትብብር የሚሰራዉ በትብብር ይሰራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እንደዚህ ዓይነት ስራዎችን መደገፍ ካልቻልን ዝም ማለት ይሻላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከለዉጡ በፊት 3መቶ ሺህ ዳቦ ይመረት ነበር ያሉ ሲሆን አሁን ግን 4ሚሊየን ዳቦ የማምረት አቅም አለን ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በቀን 2መቶ 80ሺህ እንጀራ መጋገር የሚችል ፋብሪካ ሰርተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ቁጥሩን ብንጨምር የአዲስ አበባን 20-30 በመቶ ህዝብ እንጀራን እንደ ዳቦ በማንኛዉም ሰዓት ገዝተዉ እንዲመገቡ ማድረግ እንችላለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
✍Ethio FM

የአማራና ትግራይ ክልሎች በይገባኛል የሚወዘገቡባቸው ስፍራዎች በህዝበ ውሳኔ መፍትሔ ሊሰጣቸው እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐበይ አህመድ ፍንጭ ሰጡ፡፡
‹የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ድግሱን አብን አብሮን ሲያፋፋም ነበር› - ዐብይ አህመድ
የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 28ኛ መደበኛ ጉባዔው እንደቀጠለ ነው፡፡ ምክር ቤቱ ለእረፍት ከመውጣቱ በፊት ለተነሱት ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ምላሽ እየሰጡበት ነው፡፡ከእነዚህም መካከል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የምክር ቤት አባሉ ደሳለኛ ጫኔ ያነሱት ጥያቄ ይገኝበታል፡፡
ደሳለኝ ‹ ምክር ቤቱ እንዲበተንና አዲስ ምርጫ እንዲደረግ › በጠየቁበት ወቅት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ‹ የብልፅግናና ህወሓት የስልጣን ጦርነት › ሲል መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ ዐብይ ስለሰሜን ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ በሚሰጡበት ወቅት ለምክር ቤቱ አባል ደሳለኝ ጫኔ አገላለፅ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
‹እንደተባለው የቲ.ፒ.ኤል.ኤፍ. እና ብልፅግና ችግር ከሆነ አብኖች የት ነበራችሁ?፤ ለምን አታስታርቁም ነበር? የሚል ጥያቄ አብሮ ይነሳል › ያሉት ዐብይ ‹ አስታራቂ ሲጠፋ ነው ግጭት የሚበዛው፤ እና ድግሱን አብረን ስናፋፋም ቆይተን አሁን ለተወሰኑ ወገኖች መስጠት ሳይሆን….ማንም ይጀምረው ማን ግጭቱ ጥሩ አይደለም - ጥፋት ነው › ሲሉ መልሰዋዋል፡፡
‹ ነግር ግን ከጦርነት በኋላ ኢትዮጵያ የእፎይታ ጊዜ ትፈልጋለች › ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የጦርነቱ ቀስቃሽ ማን ነው? ለሚለው ግምገማ ይፈልጋል ያሉት ዐብይ የምክር ቤት አባሉን ፍረጃ አልተቀበሉትም፡፡‹የግምገማ ጊዜ …. አሁን እንዴት ተጀመረ?፤ እነማን ጀመሩት?፤ እነማን ደገሱት?፤ እነማን አዋጉ?፤ እነማን አስጨረሱ?፤ እነማን ደግሞ አሁን ተቀምጠው ይቀልዳሉ? የሚለውን መገምገም ይፈልጋል › ሲሉም አክለዋል፡፡
‹ ኪሳራና ጥቅሙን ለማወቅ ግምገማ ያስፈልገዋል › ያሉት ዐብይ ‹ ለነገሩ የባለፈውንም ሳንገመግም አዳዲስ ጦርነቶች ናቸው የሚታሰቡት ግን መገምገም ይፈልጋል፤ ከግምገማ በኋላ መልሶ ግንባታ ያስፈልጋል › ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ‹ ሰላም ከፈለግህ ትርክትህን መቀየር አለብህ › ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
በሌላ በኩል የአማራና ትግራይ ክልሎች ስለሚዘገቡባቸው ቦታዎች ማብራሪያ የሰጡት ዐብይ ‹ ታላቁ › ሲሉ ያደነቋቸው ‹የአማራና ትግራይ ሕዝብ ይህን ጉዳይ በስክነት እንዲመለከቱት እመክራለሁ › ብለዋል፡፡ ‹ ቦታ የፀብ ምንጭ መሆን የለበትም › የሚሉት ዐብይ ‹ ሰዎች የትኛው ክልል መኖር እንደሚፈልጉ መወሰን ይችላሉ › ሲሉ ምልከታቸውን አጋርተዋል፡፡
የእነዚህ ቦታዎች ውዝግብ በህዝበ ውሳኔ ሊፈታ እንደሚችልም ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ለዚህ እንደ ዋቢነት የተጠቀሙት ትናንት ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም 12ኛ ክልል ሆኖ እንዲመሰረት ውሳኔ የተላለፈለትን የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች የተሰኘውን ክልል ውሳኔ በመጥቀስ ነው፡፡ዐብይ በማብራሪያቸው ‹ ይህን በሲዳማ አድርገነዋል፤ በደቡብ ምዕራብ አድርገነዋል › ብለዋል፡፡ ‹ በሰከነ መንገድ ሰው ሳይሞት ማድረግ ይቻላል፤ ከዚያ ውጭ ያለው አማራጭ ጥሩ አይደለም › ሲሉ አሳስበዋል፡፡
✍Asham

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ የሰሜኑ ጦርነት በተካሄደበት ወቅት ጦርነቱ እንዲቆም መግለጫ ባለመስጠቱ እና በወቅቱ በትግራይ ክልል ተገኝቶ ሕዝቡን ባለመጠየቁና ባለማጽናናቱ ይቅርታ ጠየቀ!
ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ልዩ ጉባኤ ማጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሚዲያዎች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በሁለት ዐበይት አጀንዳዎች መወያየቱን ገልጾ የኤጲስ ቆጶሳትን ሹመት በተመለከተ የተመረጡ ቆሞሳትን ይፋ በማድረግ የፊታችን ሐምሌ ዘጠኝ ሢመቱ እንደሚፈጸም አስታውቋል።
በሌላ በኩል በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመስጠቷ፣ በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ፣ ሊቃውንተ ቤተ
ክርስቲያንንና መላው ሕዝበ ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ፣ ጦርነቱ ቁሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ፣ በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ መጠየቁን በንባብ ከተሰማው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።
Via ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

የ2016 በጀት 801 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ!
የፌደራል መንግስት የ2016 በጀት 801 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸድቋል፡፡የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2016 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀት ላይ የቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡ምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት በጀትን አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ ነው መርምሮ የበጀት አዋጁን ያጸደቀው፡፡

ፕሮፐርቲ ታክስ በኢትዮጵያ አለመጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ!
ፕሮፐርቲ ታክስ ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ መደረግ አለመጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረጋገጡ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ከፕሮፐርቲ ታክስ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ÷ አዲስ አበባ የራሱ ገቢ ያለው እና በራሱ የሚተዳደር ከተማ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ፕሮፐርቲ ታክስ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለመጀመሩ በአዲስ አበባም እንዳልተጀመረ ገልጸው፤ ከተማው የጀመረው ከዚህ ቀደም የነበረውን የጣሪያ እና ግርግዳ ግብር ህግ ዘንድሮም በማሻሻል እየተገበረ እንደሆነ ጠቁመዋል።
[FBC]

Forwarded from YeneTube
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥
🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan

ኢሰመኮ በእስር ላይ በሚገኙ የኦነግ አመራሮች ዙሪያ ለመወያያት ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር ቀጠሮ መያዙን ገለጸ!
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በእስር ላይ በሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮች ዙሪያ ለመወያያት ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር ቀጠሮ መያዙን ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጅማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በዳሳ ለሜሳ፤ ኮሚሽኑ በእስር ላይ ስለሚገኙ የግንባሩ አመራር፣ አባላት እና ደጋፊዎችን ኹኔታ ሲከታተል እንደነበር አውስተዋል።
ኃላፊው አክለውም፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እንዲሁም የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባላት እና ደጋፊዎች ከሕግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ በጅምላ ተይዘው በእስር ቤት እንደሚገኙ በመጠቆም፤ ኮሚሽኑ ባደረገው ብርቱ ክትትል ከእስር የተፈቱ ቢኖሩም፣ አሁንም ሰባት የሚሆኑ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮች በማረሚያ ቤት ውስጥ ናቸው ብለዋል። ለዚህም እልባት ለመስጠት ከክልሉ መንግሥት ጋር በቅርቡ ውይይት እንደሚደረግ ነው የገለጹት፡፡
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚያወጣቸው መግለጫዎች እና በሚያዘጋጃቸው መድረኮች አመራሮቼ፣ አባላት እና ደጋፊዎቼ ከሕግ አጋባብ ውጭ በእስር ላይ ይገኛሉ በማለት በተደጋጋሚ ሲገልጸ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በሌላ በኩል፤ በክልሉ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በዜጎች እና በሕግ ታራሚዎች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እያደረሱ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጨምሮ ገልጿል።
የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች በሚኖሩ ሰላማዊ ዜጎች ላይም በክልሉ ፖሊስ እና ሚሊሻ ከፍተኛ ድብደባ እንደሚፈጸም እና ሰብዓዊ መብታቸው እንደሚጣስ ነው የተጠቀሰው።
ፍርድ ቤት የዋስ መብት አክብሮላቸው ወይም "ነጻ ናችሁ" ተብለው ከተበየነላቸው በኋላ ፖሊስ ታራሚዎችን ከእስር ያለመልቀቅ ሁኔታ በስፋት የሚስተዋል መሆኑም ተመላክቷል።
የኮሚሽኑ የጅማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሰዎችን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዛ ይዞ በጅምላ ማሰር የተለመደ ተግባር መሆኑን በመጥቀስ፤ "በተለያዩ መድረኮች እንደዚህ አይነት ተግባር እንዲቆም አሳስበን የነበረ ቢሆንም ጉዳዩ ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መጥቷል።" ነው ያሉት።
ስለሆነም በንጹሃን ዜጎችና በሕግ ታራሚዎች ላይ የሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን አንስተው፤ "የሚመለከተው አካል የመፍትሄ እርምጃ ሊወስድበት ይገባል።" ሲሉ አሳስበዋል፡፡

👍1
የኦዲት ግኝቶችን ተከትሎ ክስ የመመስረት ስልጣን እንደሌለው የፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ገለጸ፡፡
በየአመቱ በፌደራል ኦዲተር መስሪያ ቤት አማካኝነት በሚቀርቡ ሪፖርቶች የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ላይ ከፍተኛ የኦዲት ክፍተት እንደተገኘ ይፋ የሚደረግ ቢሆንም ከሪፖርት ባለፈ መልኩ ግን ተቋማቱም ሆነ በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች ተጠያቂ ሲደረጉ አይስተዋልም፡፡
አሐዱ ለምን ተጠያቂ ማድረግ አልተቻለም ሲል የፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አበበ አለሙን ጠይቋል፡፡በምላሻቸውም ባለስልጣኑ የተገኘውን ክፍተት ተከታትሎ ለሚመለከታቸው ተቋማት ከማቅረብ ባለፈ ክስ የመመስረት ስልጣን የለውም ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በየጊዜው የተቋማቱን አሰራር በመከታተል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ለገንዘብ ሚንስቴር እና ለፍትህ ሚንስቴር ከማሳወቅ ባለፈም እርምጃ እንዲወሰድ ግፊት የማድረግ ስራዎችን እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
[አሐዱ]

ከ60 ሺሕ በላይ ሰዎች ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለጸ!
በሱዳን ያለውን ግጭት በመሸሽ ከ60 ሺሕ በላይ ሰዎች በአማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ እና በጋምቤላ ክልሎች በኩል ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ገልጿል።
በአጠቃላይ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት መካከልም ከ30 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ከ15 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ሱዳናውያን ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹ ከ13 ሺሕ የሚበልጡት ደግሞ የሌላ አገር ዜጎች መሆናቸው ተጠቁሟል።
የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት በአገሪቱ በተቀሰቀሰው ግጭት ከ25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጸ ሲሆን፤ በአገሪቱ ጾታዊ ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን አስታውቋል።
እንዲሁም ጦርነቱ ከተጀመረበት ባለፈው ሚያዚያ ወር አንስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን፣ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውና ከግማሽ ሚሊዮን የሚልቁት ደግሞ ወደ ጎረቤት አገራት መሰደዳቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት መረጃ ያመላክታል።
የአገሪቱ ወጣቶች ጦሩን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ያቀረቡት የሱዳን ጦር መሪ ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን፤ የግጭቱ ዋነኛ ተፋላሚ ኃይል ከሆነው ከፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ ጄነራል ሀምዳን ዳጋሎ ጋር "መቼም ቢሆን ቁጭ ብዬ አልነጋገርም" ማለታቸው ይታወሳል።
ጄነራል ሀምዳን ዳጋሎ በበኩላቸው፤ በአንድ ሰሞን ከጄነራል አል ቡርሃ ጋር መነጋገር ዋጋ የለውም ብለው የነበረ ሲሆን፣ ቆይተው ደግሞ "ጄኔራል አል ቡርሃ ጦርነቱን ካቆመ የመነጋገር እድል ይኖራል" ሲሉ ተደምጠዋል።
ሆኖም የተለያዩ አገራት በተለይም አሜሪካና ሳውዲ አረቢያ የሱዳኑ ግጭት ያበቃ ዘንድ ኹለቱን ተፋላሚ ኃይሎች ለማደራደር ሲያደርጉት የነበረው ጥረት ፍሬ ሳይፈራ ቀርቶ፣ ግጭቱ ሦስተኛ ወሩን አስቆጥሯል።

ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፦ Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ለኢንትራንስ ፈተናን ይዘጋጁ፡፡ አፕሊኬሽኑ
✅ ከ9 - 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ እና የማትሪክ ፈተናዎችን ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያቸው የያዘ ነው፡፡
✅ የ7 ዓመት የኢንትራንስ ፈተና ከ2008 - 2014/15ዓም የያዘ ሲሆን በተጨማሪ የ3ዓመት የማትሪክ ፈተና ከ2008 - 2010ዓም ይዟል፡፡
✅ ጥያቄዎችን በየክፍሉ እና በየመእራፉ ከፋፍሎ ያስቀመጠ ነው፡፡
ከ180,000 በላይ ተማሪዎች የሚጠቀሙት አፕሊኬሽን ሲሆን ፤ አፕሊኬኑን ለመጠቀም ከታች ካለው ሊንክ ዳውንልድ ያድርጉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric

❤1
ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ለኢትዮጵያ የተቋረጠው ርዳታ እንዲቀጥል ጥሪ አደረገ!
ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን(ሜዲሳን ሳን ፍራንቴር) ወይም በእንግሊዘኛው ምኅጻሩ MSF፣ ተቋርጦ የነበረውና ለኢትዮጵያ ሲሰጥ የነበረው የምግብ ርዳታ በአፋጣኝ መልሶ እንዲቀጥል፣ ዛሬ ዐርብ ጥሪ አስተላልፏል።
ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን፣ የምግብ ርዳታው እንዲቋረጥ የተወሰነው፣ “እጅግ አሳሳቢ” የተመጣጠነ ምግብ ዕጦት ባለበት ወቅት ነው፤ ብሏል።
ለተጎጂዎች የተላከው ርዳታ፣ ላልታሰበለት ዓላማ ውሏል፡፡ በዚኽም፣ የመንግሥት አካላት፥ ተሳታፊ እና ተጠያቂ ናቸው፤ በሚል፣ የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም(WFP) እና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት(USAID)፣ ከአንድ ወር በፊት የምግብ ርዳታውን አቋርጠው ነበር። በቅርቡ ግን፣ ውሱን ዐይነት ርዳታዎች መልሰው መለቀቅ እንደሚጀምሩ፣ የአሜሪካ መንግሥት አስታውቋል።
የምግብ ርዳታው ከመቋረጡም በፊት፣ በኢትዮጵያ፣ 20 ሚሊዮን ሰዎች በርዳታ ላይ ጥገኛ ኾነው ይኖሩ እንደነበርና በአንዳንድ ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎች ዘንድ፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረቱ “እጅግ አሳሳቢ” እንደኾነ፣ ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን ገልጿል።
“የምግብ ርዳታው መቋረጡ አሳሳቢ ነው፤ ምክንያቱም፣ እንዲቋረጥ የተወሰነው፣ ወትሮውንም በቂ ያልኾነ የርዳታ ምግብ ሥርጭት በነበረበትና በመላ አገሪቱ ያለው ሰብአዊ ኹኔታ አሳሳቢ በኾነበት ወቅት ነው፤” ሲሉ፣ የቡድኑ የኢትዮጵያ ዲሬክተር ካራ ብሩክስ መናገራቸውን፣ የኤኤፍፒ ዘገባ ጠቅሷል።
የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ(OCHA) በበኩሉ፣ በዚኽ ሳምንት እንዳስታወቀው፣ በትግራይ ክልል፣ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፣ ብሏል። ርዳታው በመቋረጡ ምክንያት፣ ወትሮውንም ተጋላጭ የነበሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ለተጨማሪ ሥቃይ እንደተዳረጉ አክሎ ገልጿል።
Via VoA

በጅግጅጋ ከተማ በእሳት አደጋ ከ900 በላይ ሱቆች ወደሙ!
በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ትናንት ሌሊት በተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።በጅግጅጋ ከተማ ‘ታይዋን’ ተብሎ በሚጠራው የገበያ ማእከል ትናንት ሌሊት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የተከሰተው ከፍተኛ የእሳት አደጋ በገበያው በሚገኙ የንግድ ሱቆችና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ አድርሷል።
እሳቱን ለመቆጣጠር የክልሉ የእሳት አደጋ ማጥፊያ ግብረ ሀይልና ከሐርጌሳ ከተማ የተላከለ የእሳት አደጋ አጥፊ ቡድን የእሳት አደጋውን ለማጥፋት ባደረጉት ርብርብ እሳት አደጋውን መቆጣጠር መቻሉን የክልሉ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል።
በእሳት አደጋው ሳቢያ 932 ሱቆች ሲወድሙ የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱም ነው የተገለጸው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከእንግሊዙ የአውሮፕላን ሞተር አምራች “ሮልስ ሮይስ” ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ!
ስምምነቱ አየር መንገዱ በቀጣይ ለሚረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ሞዴል ሞተሮች አጠቃላይ የሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa
ስምምነቱ አየር መንገዱ በቀጣይ ለሚረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን ሞዴል ሞተሮች አጠቃላይ የሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa
በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የ 9 ሰዉ ህይወት አለፈ!
በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በቆንጋ ቀበሌ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ12 ሰዎች ደግሞ ከባድ አደጋ ደርሷል፡፡
ከዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ እንደተገኘው መረጃ ከሆነ፤ አደጋው የደረሰው መነሻውን ያቤሎ አድርጎ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ የነበረው መኪና በመገልበጡ እንደሆነ የይርጋጨፌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ታምራት ምትኩ የገለፁት።
በተከሰተው የመኪና አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የገለፁት ኢንስፔክተር ታምራት ከሞት በተጨማሪ 12 ከባድና 19 ቀላል አደጋ ማስከተሉን ነዉ የገለፁት።
የአደጋ መንስኤ በማጣራት ሂደት ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ኢንስፔክተር ታምራት ምትኩ በአደጋ ምክንያት ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በዲላ ሪፈራል አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለአዲስ አበባ ከተማ የ2016 በጀት 140.2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ጸደቀ!
የአዲስ አበባ ከተማ የ2016 በጀት 140.29 ቢሊዮን ብር ሆኖ በከተማዋ ምክር ቤት ጸደቀ፡፡ በዘንድሮው የ2016 በጀት ዓመት ለከተማ አስተዳደሩ የተያዘው በጀት ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ40.2 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋን በጀት ያጸደቀው ዛሬ እሁድ ሐምሌ 2፤ 2015 ለሁለተኛ ቀን ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ነው፡፡ በዛሬው የምክር ቤቱ ውሎ ትላንት ለተጀመረው የ2016 በጀት ዓመት የሚውል የበጀት ዝርዝር የያዘ አዋጅ ለምክር ቤት አባላቱ ቀርቧል፡፡ የከተማ ምክር ቤቱ በበጀት አዋጁ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ በ87 ድጋፍ እና በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ የ2016ን በጀት ጸድቋል፡፡
Via Ethiopia Insider