ኢትዮጵያ ለምርጫ ስርዓት ማጠናከሪያ የ30 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች!
ኢትዮጵያ ዘላቂ ዲሞክራሲን ለማስፈን የሚያስችላትን የምርጫ ስርአት እንድታጠናክር ለማግዝ የሚውል የ30 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የፋናንስ ድጋፍ ስምምነት ፈርማለች።
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ብሐያረዊ ምርጫ ቦርድ እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት መካካል ተፈርሟል።
የበጀት ድጋፉ የምርጫ ቦርድ ተቋማዊ መዋቅርን ለማጠናከር ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ አሳታፊ ፣ተአማኒና ደረጃውን የጠበቀ ምርጫና ህዝበ ውሳኔ እንዲያካሂድ ተቋሙን ማጠናከር፣ ከሲቪክ ተቋማት በጋራ በመሆን በምርጫ ሂደት የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎን ለማሳደግ ይውላል ተብሏል።
እንዲሁም የበጀት ድጋፉ በኢትዮጵያ ነፃ ፍትሀዊ እና ተአማኒ ምርጫ እንዲያከሂድ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንደሚውልም የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ተቋማት እገዛ እንድታገኝ፤ የአሜሪካ መንግስት ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ ተናገሩ!
የኢትዮጵያ መንግስት እንደ ዓለም ባንክ እና አይ ኤም ኤፍ ካሉ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የሚፈልገውን እገዛ እንዲያገኝ፤ የአሜሪካ መንግስት ጠንካራ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ። መንግስት በዓለም አቀፍ ተቋማት በኩል “የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ” የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መንግስት በቅርቡ “ጠንካራ አቋሙን” እንደገለጸ የገንዘብ ሚኒስትሩ ለፓርላማ አባላት አስረድተዋል።
አቶ አህመድ ይህን የተናገሩት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለ2016 በተዘጋጀው የበጀት ረቂቅ ላይ ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 27፤ 2015 ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። “ከአሜሪካ መንግስት ጋር ያለው የዲፕሎማሲ ግንኙነት እጅግ የተሻለ” ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በዚሁ ማብራሪያቸው የገለጹት የገንዘብ ሚኒስትሩ፤ በጦርነቱ ምክንያት የተቋረጠው የአውሮፓ ህብረት የልማት እርዳታ ሊቀጥል እንደሚችል ጥቆማ ሰጥተዋል።
ህብረቱ ለኢትዮጵያ የልማት እርዳታ የሚሰጥበትን “multi-annual development program” እንደገና ለማስጀመር “ከጥቂት ወራት በኋላ” ስምምነት እንደሚፈረም አቶ አህመድ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ አጋሮች የሚጠብቀው እገዛ በበጀት ረቂቁ ውስጥ እንዳልተካተተ ያረጋገጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ፤ ይሁንና መንግስታቸው “የተሻለ ሁኔታ እንደሚኖር” ተስፋ ማድረጉን በንግግራቸው ጠቁመዋል።
Via Ethiopia Insider

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ በዛሬዉ እለት ተገድለዋል!
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ድንገት ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች በመገደላቸው ከተማ አስተዳደሩ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል ሲል ባወጣዉ መግለጫ አሳዉቋል።
አቶ አብዱ የመንግስት ኃላፊነታቸው ለመወጣት ሲሰሩ መገደላቸውን የከተማ መስተዳድሩ መግለጹን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል። ነፍሳቸውንም በጀነት እንዲያሳርፍና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ከተማ አስተዳደሩ ተመኝቷል።
በሸዋሮቢት ከነገ አመሻሽ 12 ጀምሮ የሰዓት እላፊ ታዉጇል። ይህም ይህንኑ የከተማዉ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ግድያን ተከትሎ የተወሰነ ነዉ።

YeneTube
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ በዛሬዉ እለት ተገድለዋል! የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ድንገት ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች በመገደላቸው ከተማ አስተዳደሩ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል ሲል ባወጣዉ መግለጫ አሳዉቋል። አቶ አብዱ የመንግስት ኃላፊነታቸው ለመወጣት ሲሰሩ መገደላቸውን የከተማ መስተዳድሩ መግለጹን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል። ነፍሳቸውንም በጀነት እንዲያሳርፍና…
በሸዋሮቢት እና አካባቢዋ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የተሽከርካሪም ሆነ የሰው እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጣለ!
ማክሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በሸዋሮቢት እና አካባቢዋ ከነገ ሰኔ 28/2015 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ማንኛውም ተሽከርካሪ ይሁን የሰው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የተገደበ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።
ጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፖስቱ ማምሻውን ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ፤ የሸዋሮቢት እና አካባቢዋ ነዋሪዎች የከተማዋ የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ እንዲሆን እና ዜጎች ያለ ስጋት ወጥተው የሚገቡበት ለማድረግ ብዙ ጥረት ተደርጎል ብሏል።
ነገር ግን "አሁንም ከተማዋን ሰው አልባ እንድትሆንና ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እንዲከሰት ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን በርካታ ማሳያዎች እየተስተዋሉ ነው" ያለው ኮማንድ ፖስቱ፤ የነዋሪዎችን እገዛ በማከል ጠንካራ የጸጥታና የሰላም ሥራዎችን መስራት እንደሚጠበቅ ገልጿል።
በዚህም መሰረት ከነገ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ማንኛውም ተሽከርካሪ ይሁን የሰው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የተገደበ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ የምሽት ክለቦችን ጨምሮ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከምሽቱ 12 ሰዓት በኃላ ምንም አይነት አገልግሎት እንዳይሰጡ ገደብ መጣሉንም አስታውቋል።
በተጨማሪም "የከተማው ነዋሪ ለጸጥታ መዋቅሩ እገዛውንና ድጋፍ በማድረግ ከተማዋን ካለባት ከፍተኛ የጸጥታ ችግር ልንታደጋት ይገባል።" ሲል በመግለጫው አሳስቧል።

❤1
የጉራጌ ዞን የደቡብ ክልል ምክር ቤት ተወካይ፤ “በመታወቂያ ዋስ” ከእስር ተለቀቁ!
ለሁለት ቀናት በእስር የቆዩት የደቡብ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ታረቀኝ ደግፌ፤ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 27፤ 2015 አመሻሽ ላይ “በመታወቂያ ዋስ” ከእስር መፈታታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። አቶ ታረቀኝ ዛሬ ረፋድ ላይ፤ የደቡብ ክልል ፖሊስ አባላት ወዴት እንደሆነ ወደ አላወቁት ቦታ “ሊወስዷቸው” ሞክረው እንደነበርም ገልጸዋል።
የጉራጌ ዞንን በመወከል የደቡብ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ታረቀኝ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በፌደራል ፖሊስ የተያዙት ከትላንት በስቲያ እሁድ ሰኔ 25 ምሽት 2፡30 ገደማ ነበር። አቶ ታረቀኝ ከመኖሪያ ቤታቸው “ትፈለጋለህ” ተብለው ከተያዙ በኋላ፤ በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መወሰዳቸውን ገልጸዋል።
አቶ ታረቀኝ በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው የመጡትን የፌደራል ፖሊስ አባላት የፍርድ ቤት የእስር ትዕዛዝ ይዘው እንደሆነ መጠየቃቸውን አስታውሰዋል። ለዚህ ጥያቄያቸው ምላሽ አለማግኘታቸውን የሚናገሩት አቶ ታረቀኝ፤ የደቡብ ክልል ምክር ቤት አባልነት መታወቂያቸውን በማሳየት “ያለመከሰስ መብት ያላቸው” መሆኑን ማስረዳታቸውን ጠቅሰዋል። ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳበት “ወረቀት” እንዳለ ቢጠይቁም፤ በተመሳሳይ መልኩ ምላሽ እንዳልተሰጣቸው አብራርተዋል።

🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥
🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan

👍1
በዜጎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቆም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትህ እና የህግ ቋሚ ኮሚቴ ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
የሰብዓዊ መብት ኮምሽን በዜጎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተመለከተ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ በተለያየ ጊዜያት ሪፖርት እና መግለጫዎችን ያወጣል፡፡
መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ ከተፈጸመ በኃላ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ከመፈጸሙ አስቀድሞ የመከላከል ስራ መስራት እንዳለበት ለአሀዱ የተናገሩት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፎረም ዋና ዳይሬክተር አቶ ተረፈ ጠጌቲ ናቸው፡፡
የሰብዓዊ መብት ኮምሽን እና ሌሎች ተቋማትን ጨምሮ በሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ የሚያወጡትን ሪፖርት ወስዶ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ክልሎችን ጨምሮ ተቃራኒ የሆነ ምላሽ የመስጠት ሁኔታዎች ይስተዋላል ነው ያሉት፡፡
በኮምሽኑም ሆነ በመንግስት በኩል የሚወጡ የተለያዩ መግለጫዎችና ሪፖርቶች ማህበረሰቡ ላይ ግራ መጋባትን የሚፈጥር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የሰብዓዊ መብት ኮምሽን የሚያወጣው ሪፖርት በመንግስት በኩል ተግባራዊ እንዲሆን የጋራ አሰራርን ለመዘርጋት እንዲቻል የህዝብ ተወካይዎች ምክር ቤት የፍትህ እና የህግ ቋሚ ኮሚቴ መመሪያ በማዘጋጀት ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

ኮኬይን የተባለ አደገኛ ዕፅ በነጩ ቤተመንግስት መገኘቱ አነጋጋሪ ሆነ!
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መኖሪያ በሆነው ነጩ ቤተመንግስት ኮኬይን የተባለ አደገኛ ዕፅ መገኘቱ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡
ዌስት ዊንግ በተባለው የቤተ መንግስቱ ክፍል የፕሬዝዳንቱ የሚስጥር ጥበቃዎች የተለመደ የፍተሻ ስራ ሲያከናውኑ የጎብኝዎች ስልክ ማስቀመጫ ቦታ ላይ ዕፁን ማግኘታቸው ተመላክቷል፡፡
ዕፁ በተገኘበት ወቅት ፕሬዝዳንት ባይን እና ቤተሰባቸው ሜሪላንድ በሚገኘው የፕሬዝዳንቶች ማረፊያ በሆነው ካምፕ ዴቪድ እንደነበሩም ተገልጿል፡፡
የዕፁ መገኘትን ተከትሎ ሰራተኞች ለአጭር ጊዜ ከቤተመንግስት እንዲወጡ ተደርጎ እንደነበርና በተገኘው ነጭ ዱቄት ላይ በተደረገው ምርመራ ኮኬይን ሆኖ መገኘቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የፕሬዝዳንቱ የሚስጥር ጥበቃ አገልግሎት ዕፁ ቤተመንግስት እንዴት ሊገባ እንደቻለ የደህንነት ካሜራ እና የጎብኝዎችን መመዝገቢያ ማህደር በመጠቀም ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
ኮኬይን በአሜሪካን አገር የተከለከለ አደገኛ ዕፅ ሲሆን በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ቁጥጥር ለህክምና አገልግሎት ካልሆነ በስተቀር ዕፁን ይዞ መገኘት በከባድ ወንጀልነት ያስቀጣል፡፡
ዌስት ዊንግ ትልቅ የቤተመንግስቱ ክፍል ሲሆን የፕሬዝዳንት ቢሮዎች፣ ኦቫል ኦፊስ፣ የስችዌሽን ክፍል፣ የምክትል ፕሬዝዳንት፣ የዋይት ሀውስ የሰራተኞች ኃላፊ፣ የፕሬስ ሴክሬታሪ እና የሌሎች ሰራተኞችን ክፍል የያዘ እንደሆነም መረጃው አመላክቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ ይሰጣሉ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ አዲስ ማለዳ ከምክር ቤቱ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ሰኔ 29/2015 ያካሂዳል፡፡
ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን ያጸድቃል፡፡

በቤኒሻንጉል ክልል የኢቦላ ቫይረስ እንዳይከሰት ስጋት መኖሩ ተነገረ!
በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን የኢቦላ ቫይረስ ተጠርጣሪዎች መገኘት እና ሞት መመዝገቡን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ይገባል የሚል ስጋት እንዳለ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቃል።
በተለይ በሱዳን የተፈጠረውን የእርስ በእርስ ግጭት ተከትሎ የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ክልሉ በአጎራባች ወረዳዎች በኩል በከፈተኛ ሁኔታ ከመግባታቸው ጋር ተያይዞ በሽታው ሊገባ እንደሚችል ተገልጿል።
የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ጤና ቢሮ የህብተሰብ ጤና ጣቢዎች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ፍቃዱ አየለ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በሱዳን ዳባላይ በምትባል ስፍራ ከ150 በላይ በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች እንዳሉ የተነገረ ሲሆን እሱን ለማጣራት ከዓለም የጤና ድርጅት እና ከሌሎች አካላት አካላት ጋር በመሆን ጥናት እየተደረገ ይገኛል።

‹ ኢቢሲ የመንግስት አፍ መሆን የለበትም › - ዐብይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ‹ ብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቢሲ) የመንግስት አፍ መሆን የለበትም › ሲሉ ተናግረዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም የቴሌቪዥን ጣቢያው አንድ ዓመት ከስድስት ወር ገደማ በወሰደ ጊዜ ያጠናቀቀውን ‹ የስቱዲዮ ግንባታ › መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው፡፡
ዐብይ ስለ ብሔራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲናገሩ ‹ ከሰፈር ሹኩቻ የወጣ ሚዲያ፣ ለመንግስት ብቻ የሚያገለግል ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የሚያገለግል ሚዲያ እንደምታደርጉት ተስፋ ይደረጋል › ሲሉ ለተቋሙ ሰራተኞች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ይህ አንድ ዓመት ከመንፈቅ የወሰደ ግንባታ ‹ ድንቅ ስራ ነው › ያሞካሹት ዐብይ ከተቋሙ መንግስታቸው የሚጠብቀውን አብራርተዋል፡፡
‹ኢቢሲ ድምፅ ማጉያ አይደለም› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹የሚነገርን ድምፅ የሚያጎላ ሳይሆን ድምፅ የሚፈጥር መሆን አለበት› ሲሉም ተናግረዋል፡፡‹መንግስት ሲያበላሽ ቆንጠጥ አድርጎ የሚጠይቅ፣ የመንግስት አፍ ያልሆነ የኢትዮጵያን ልዕልና ከፍ የሚያደርግ መሆን አለበት› ሲሉም አሳስበዋል፡፡
‹የኢቢሲ ግንባታ የተቋማት ግንባታ መሳያ ነው› ሲሉ ያደነቁት ዐብይ ለክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ለካቢኔ አባላቶቻቸውም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመንግስት አመራሮች ባስተላለፉት መልዕክትም - የሚመሩትን ተቋማት እንደ ኢቢሲ እንዲያስውቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ለዚህም ምክንያታቸው ‹ ኢትዮጵያ በተቋማቷ ስለምትለካ ነው › ብለዋል፡፡ ተቋማቱ ካልተዋቡ ግን ‹ እነርሱን አይተው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን › እንደሚንቁ ተናግረዋል፡፡
✍Asham

አባቱን እና ወንድሙን በቁማቸዉ በእሳት አቃጥሎ የገደለዉ ተጠርጣሪ ተያዘ!
"ቤተሰቦቼ ለእኔ ምንም ቦታ የላቸውም " በሚል ምክንያት ወላጅ አባቱንና ታላቅ ወንድሙን ቤንዚል በመርጨት በቁማቸዉ ያቃጠለዉ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዉሏል።
ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ክብረ ደመና ሙሉ ወንጌል አካባቢ ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
ተከሳሹ ግለሰብ ከዚህ ቀደም በሌላ ወንጀል ተከሶ ታስሮ የነበረና በፍርድ ቤት ዋስትና የተለቀቀ ሲሆን " ከእናቴ በስተቀር ለእኔ የሚያስብልኝ የለም " በሚል ምክንያት ከሳምንት በፊት በአንድ ሺህ ስድስት መቶ ብር ቤንዚል በመግዛት አባቱና ታላቅ ወንድሙ የግል ጉዳያቸውን ፈፅመው በመምጣት ቤት ውስጥ ቁጭ ባሉበት እናትዬውን ውሃ አምጭልኝ ብሎ ከቤት መውጣታቸውን ጠብቆ ቤንዚሉን አርከፍክፎባቸው ክብሪት በመለኮስ ማምለጥ እንዳይችሉ በሩን ቆልፎ ለማምለጥ ሲል በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ተጎጂዎችን ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመተባበር ወደ ህክምና ቢወስዱም አባትዬው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ታላቅ ወንድሙ በህክምና ላይ ይገኛል።በተከሳሹ ላይ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።

በትግራይ ክልል ረሃብ 'በከፍተኛ መጠን' መጨመሩን ተመድ አስታወቀ!
በጦርነት በተጎዳው የትግራይ ክልል ለከፋ የምግብ እጥረት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን እና፣ በቅርቡ የምግብ ርዳታ መቆሙን ተከትሎ፣ ሁኔታዎች እየተባባሱ ሊሄዱ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰሞኑን ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ፤ሰኞ ዕለት ይፋ ባደረገው ወቅታዊ ሪፖርት፣ በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በድርቅ ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በተጨማሪ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚኖሩ 8.8 ሚሊየን ሰዎች የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቋል።
በኢትዮጵያ መንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ለሁለት ዓመት የተካሄደውን ጦርነት ያስቆመው የሰላም ስምምነት በኅዳር ወር ከተፈረመ ወዲህ ወደ ክልሉ የሚገባው የርዳታ መጠን ቀስ በቀስ እንዲጨምር አስችሎ የነበረ ቢሆንም፣ በከፍተኛ ምግብ እጥረት ምክንያት ለውስብስብ የጤና ችግር የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨምረ መሆኑን ክልሉ ይፋ አድርጓል።
"ባለፈው ዓመት በሚያዚያ ወር ከነበረው ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር፣ በትግራይ፣ በከፍተኛ በሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ወደ ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎች ቁጥር በ196 ከመቶ ጨምሯል" ያለው የኦቻ ሪፖርት፣ የአሃዙ መጨመር "በከፊል የተሻለ የጤና ተቋማት ተደራሽነት እና የመረጃ አሰባሰብ" በመኖሩ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አመልክቷል።
"ለትግራይ ክልል ይሰጥ የነበረው የምግብ እርዳታ ለተረጂዎቹ እንደማይደርስ ገልፀው ድጋፍ ሰጪ ተቋማት እርዳታ ማቋረጣቸውን ተከትሎ፣ በትግራይ ለችግር ተጋላጭ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል የምግብ ዋስትና እጦት እየተባባሰ ሄዷል" ብሏል ኦቻ በሪፖርቱ።
በተመሳሳይ ሁኔታ ባለፈው ዓመት ከጥር እስከ ሚያዚያ ወር ከነበረው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር፣ በመላ ሀገሪቱ በከፍተኛ የምግብ እጥረት ምክንያት ወደ ህክምና ተቋማት የሚገቡ ሰዎች ቁጥርም በ15 ከመቶ መጨመሩን ኦቻ በሪፖርቱ አስታውቋል።
Via VoA

ምርጫ ቦርድ፤ የወላይታ ዞን ህዝበ ውሳኔን በድጋሚ ለመሰረዝ የሚያስገድዱ ችግሮች አጋጥመውት እንደነበር የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ተናገሩ!
ድጋሚ በተደረገው የወላይታ ዞን ህዝበ ውሳኔ ላይ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሂደቱን በድጋሚ “እንዲሰረዝ” የሚያስገድዱ ተግባራት በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሲፈጸሙ እንደነበር የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ተናገሩ። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በህዝበ ውሳኔው ዕለት፤ ምርጫ ቦርድ “ሌላ ውሳኔ እንደሰጠ” አድርገው መልዕክት ሲያስተላልፉ እንደነበርም አቶ ውብሸት ገልጸዋል።
የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ይህንን ያሉት፤ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 28፤ 2015 በተካሄደ የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ ነው። አቶ ውብሸት በንባብ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝበ ውሳኔ አጠቃላይ ሪፖርት፤ ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔውን ለማካሄድ ያለፋቸውን ሂደቶች፣ የተገኘውን ውጤት እንዲሁም ያጋጠሙትን ችግሮች ዘርዝረዋል።
በ26 ገጾች በተዘጋጀው በዚሁ ሪፖርት ውስጥ በችግርነት ከተጠቀሱ ጉዳዮች ውስጥ፤ በወላይታ ዞን ተከስተው ነበር የተባሉ የህግ ጥሰቶች ይገኙበታል። በወላይታ ዞን ባለፈው ጥር ወር የተካሄደው ህዝበ ውሳኔ እንዲሰረዝ ምክንያት የሆኑ የህግ ጥሰቶችን አጽንኦት ሰጥተው ያነሱት ምክትል ሰብሳቢው፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 94 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12፤ 2015 በወላይታ ዞን በድጋሚ ህዝበ ውሳኔ ሲያካሄድም ችግሮች እንዳጋጠሙት አቶ ውብሸት በዛሬው ሪፖርታቸው ጠቁመዋል።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
ድጋሚ በተደረገው የወላይታ ዞን ህዝበ ውሳኔ ላይ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሂደቱን በድጋሚ “እንዲሰረዝ” የሚያስገድዱ ተግባራት በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሲፈጸሙ እንደነበር የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ተናገሩ። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በህዝበ ውሳኔው ዕለት፤ ምርጫ ቦርድ “ሌላ ውሳኔ እንደሰጠ” አድርገው መልዕክት ሲያስተላልፉ እንደነበርም አቶ ውብሸት ገልጸዋል።
የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ይህንን ያሉት፤ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 28፤ 2015 በተካሄደ የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ ነው። አቶ ውብሸት በንባብ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝበ ውሳኔ አጠቃላይ ሪፖርት፤ ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔውን ለማካሄድ ያለፋቸውን ሂደቶች፣ የተገኘውን ውጤት እንዲሁም ያጋጠሙትን ችግሮች ዘርዝረዋል።
በ26 ገጾች በተዘጋጀው በዚሁ ሪፖርት ውስጥ በችግርነት ከተጠቀሱ ጉዳዮች ውስጥ፤ በወላይታ ዞን ተከስተው ነበር የተባሉ የህግ ጥሰቶች ይገኙበታል። በወላይታ ዞን ባለፈው ጥር ወር የተካሄደው ህዝበ ውሳኔ እንዲሰረዝ ምክንያት የሆኑ የህግ ጥሰቶችን አጽንኦት ሰጥተው ያነሱት ምክትል ሰብሳቢው፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 94 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12፤ 2015 በወላይታ ዞን በድጋሚ ህዝበ ውሳኔ ሲያካሄድም ችግሮች እንዳጋጠሙት አቶ ውብሸት በዛሬው ሪፖርታቸው ጠቁመዋል።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥
🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 6ኛውን፣ 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 28ኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡
ምክር ቤቱ በስብሰባው የ27ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔን መርምሮ አጽድቋል፡፡
የምክር ቤት አባላትም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌደራል መንግስት የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የተከበሩ አቶ መሀመድ አህመድ " ህወሓት አሁንም ዉድቀቱ ያልተማረ መሆኑ እና ዛሬም የትግራይ ክልልን እና መላዉ ኢትዮጵያን መልሶ ጦርነት ዉስጥ ለመክተት እየተንቀሳቀሰ እንዳለ አሁንም ይነሳል።
ወቅታዊ የትግራይ ክልል ሁኔታ ማብራሪያ ይሰጥበት?" ለጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ የቀረበ ጥያቄ።
@Yenetube @Fikerassefa
ወቅታዊ የትግራይ ክልል ሁኔታ ማብራሪያ ይሰጥበት?" ለጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ የቀረበ ጥያቄ።
@Yenetube @Fikerassefa
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የአብን እና የምክርቤቱ አባል ለጠ/ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ -
ጠ/ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢኮኖሚዉ ታሟል፣ ወጣቶች ሀገራቸዉ ዉስጥ ተስፋ በማጣታቸው ስደትን ምርጫቸዉ አድርገዋል ፣ ዜጎች በጠራራ ፀሀይ ይታገታሉ ፣ ብልጽግና መራሹ ፓርቲ ሀገሪቱ ከገባችበት ቅርቃር ማዉጣት ስለማይችሉ ስልጣኖን ለጊዜያዊ አስተዳደር እንዲያስረክቡ ሲሉ ጠይቀዋል።

"ሙሉ አማራ ክልል አዲስ የጦርነት ቀጠና ሆኗል ፤ ከፊል ኦሮሚያ በተመሳሳይ የጦር ቀጠና ናቸዉ። ከ 200 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግስት ቤታቸዉ ፈርሶ ሜዳ ላይ ወድቀዋል። እንደ ብልጽግና ሹማምንት አባባል ህጋዊ ደሃ ተደርገዋል። በሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በጦርነቱ እና በማንነት ጥቃት ተፈናቅለዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ለዚህ ሁሉ ቀዉስ ዋነኛ ተጠያቂው የብልጽግና መንግስት እና የእርሶ(የጠ/ሚኒስተሩ ) የወደቀ አመራር ነዉ።" የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለ ጠ/ሚ አብይ ካነሷቸዉ ጉዳዮች መካከል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
‹ኢትዮጵያ የደም ምድር ሆናለች - ፓርላማው ይበተን - አዲስ ምርጫ ይደረግ› - ደሳለኝ ጫኔ
የህዘብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን በማከሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተገኙ ሲሆን ከአባላቱ በኩል በርከት ያሉ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል፡፡ ከእረሱም መካከል የተቃዋሚው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) አባሉ ደሳለኝ ጫኔ የጠየቋቸው ጥያቀዌች ይገኙበታል፡፡
ሰፊ ጊዜ ወስደው የዐብይን መንግስት የተቹት ደሳለኝ ‹ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መንግስት የወደቀ › ሲሉ በይነውታል፡፡
ደሳለኝ በማብራሪያቸው ‹ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ስልጣን ከወጡበት መጋቢት 2010 ዓመት ጀምሮ እየተወሳሰቡ የመጡት የሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ወደሁለንታዊ ቀውስ መሸጋገራቸውን መሸፋፈን በማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል › ብለዋል፡፡
‹ ብልፅግና መራሹ መንግስትዎ የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም ወጥቶ የሚገባበት፣ ነጋዴው ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ፣ ሰርቶና ነግዶ የሚኖርበት፣ ገበሬው አርሶ የሚበላበትና ከተሜውን የሚቀልብበትን ሁኔታ መፍጠር አልቻለም › ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
‹ የኢትዮጵያ ህዝብ በችጋር እየተጠበሰ፣ በረሃብ እየተሰቃየ ነው › ሲሉም ተናግረዋል፡፡
‹ የኑሮ ውድነቱ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ወገናችን ከእጅ ወደአፍ የሆነውን ኑሮ እንኳ መግፋት ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል፤ ኢኮኖሚው ታምሟል፤ መካከለኛ ነዋሪ የነበረውም ተመትቶ ወደ ድህነት ወለል ወርዷል › ሲሉ አብራርተዋል፡፡
‹ ስራ አጥነት ተስፋፍቷል፤ ወጣቶች ስደትን ምርጫ አድርጓል፤ ዜጎች በጠራራ ፀሃይ ይታገታሉ፤ ሚሊዮን ብር ይጠይቅባቸዋል የመንግስት የፀጥታ መዋቅር በተለይም ፖሊስ አማራ ዎችንና የአማራ ሊህቃንን የአማራን ህዝብ ጥያቄዎችን በመንሳታቸው መንግስትን በተለያየ መንገድ በመጠየቃቸው ብቻ የፈጠራ ወንጀል እየተሰጣቸው በማንነታቸው በጅምላ ይታሰራሉ፣ በጅምላ ይከሰሳሉ፤ ፍርድ ቤትም ነፃ ሲላቸው ፖሊስ ግለሰቦችን አስሮ ያቆያል › ሲሉ የፍትሕ ስርዓቱን ኮንነዋል፡፡
‹ የኢትዮጵያ መልዓካ ፖለቲካ በሙሉ ያደረሰ በሚባል ደረጃ ሀገራችን ሁሉም አካባቢዎች የደም ምድር ሆኗል፤ ሙሉ አማራ ክልል አዲስ የጦርነት ቀጣና ተደርጓል፤ ከፊል የኦሮሚያ ክልል ሆኖ ባጅቷል፤ ትግራይ፣ አማራና አፋር ፋይዳ ባልነበረው የብልፅግናና ህወሓት የስልጣን ጦርነት ምክንያት ደቅቋል፡፡ ቤኒሻንጉል ጋምቤላ… የተለዩ አይደሉም › ሲሉ የሀገሪቱን ሁኔታን የተረዱበትን መንገድ አስረድተዋል፡፡
‹ ከሁለት መቶሺህ በላይ ሰዎች ቤት አልባ ሆነዋል፤ በብፅልግና ሹማምንት አገላለፅ ህጋዊ ደሃ ተደርገዋል › ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
‹ ለዚህ ቀውስና ሀገራዊ ሀገራዊ መክሸፍ ዋነኛ ተጠያቂ የብልፅግና መንግስት እና የእርስዎ የወደቀ አመራር ነው › ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የወነጀሉት ደሳለኝ ‹ መንግስትዎ ብልፅግናን አመጣለሁ ቢልም ያመጣው ግን ጉስቁልና ነው › ሲሉ ገልጸውታል፡፡
‹ ለወደቀው የእርስዎና የበልፅግና አመራር መፍሔው ምንድን ነው › ሲሉ የጠየቁት የምክር ቤት አባሉ የእርሳቸውን መፍትሔን ግን ካማመላከትአላመነቱም፡፡
‹ እንደ አንድ ህዝብ ተወካይ ብልፅግናም ሆነ ፓርላማው ኢትዮጵያ ከገባችበት ፖለቲካ ቅርቃር ማውጣት ስለማይችሉ ስልጣኑን ለጊዜያዊ ሲቪል አስተዳደር እንዲያስረከቡ፣ የሕዝብ እንደራሰዌች ምክር ቤት አባላትም በምክር ቤቱ ፍቃድ ምክር ቤቱን እንዲበተኑ ለአዲስ ምርጫ መንገዱን እንዲጠርጉ መጠየቅ እፍለጋለሁ፡፡ › ብለዋል፡፡
ደሳለኝ ይህን ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅት የምክር ቤቱ አበላት ሲስቁ ተስተውሏል፡፡ ከዚህ ወደም በተመሳሳይ መልኩ የአብን የምክር ቤት አባል ክርስቲያን ታደለ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ‹ ስልጣን የመልቀቅ ሃሳብ እንዳላቸው › ጠይቀዋቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ በሰጡት ምላሽ ‹ ስልጣን ልቀቅ ሳይሂን አብረን እንልቀቅ ነው የሚባለው › ማለታቸው ይታወሳል፡፡
[Asham]