YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጉራጌ ዞን በነዋሪዎች ላይ ግድያና እገታ እየፈጸሙ ነው ተባለ!

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በተለይም ሶዶ ወረዳ፤ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራውና መንግሥት "ኦነግ ሸኔ" በሚል በአሸባሪነት የፈረጀው ኃይል በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ግድያና እገታ እንደሚፈጽም ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

በተለይ የዱግዳ ጎሮ ቀበሌ ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፤ የታጣቂ ቡድኑ አባላት በነዋሪዎች ላይ ተከታታይ ግፍና በደል እየፈጸሙ ነው ብለዋል።

በዚህም የቡድኑ አባላት ነዋሪዎችን አግተው በመውሰድ አርደን የምንበላው ከብት ስጡን፣ የግል የጦር መሳሪያችሁን እንዲሁም ብር አምጡ በማለት በደል እንደሚፈጽሙ ተነግሯል።

ባለፈው ሃሙስ ሰኔ 22/2015 በነዋሪዎቹ ቤት በመግባት "የመንግሥት የጸጥታ አካላትን ትደብቃላችሁ እንዲሁም ያሉበትን ጥቆማ አልሰጣችሁንም" በሚል ነዋሪውን ሲያሰቃዩ እንደነበርና በዚህም ምክንያት አንድ የቀበሌው ነዋሪ የነበሩ አርሶ አደርን መግደላቸው ነው የተገለጸው።

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአካባቢው ከስድስት ወር በፊት ጀምሮ በተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ ነበር ያሉት ነዋሪዎቹ፤ ከባለፈው ሰኔ 20/2015 ጀምሮ ግን ግድያ እና እገታ እየፈጸሙ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ነዋሪዎችን አግተው በመውሰድ እስከ 200 ሺሕ ብር እንደሚጠይቁ በመጥቀስም፤ በአካባቢው (በቀበሌው) በቂ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ባለመኖራቸው ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ተናግረዋል።

የታጣቂ ቡድኑ አባላት ወደ ቀበሌው ዘልቀው የሚገቡት ከኦሮሚያ ክልል በመንግሥት የጸጥታ አካላት ሲሳደዱ መሆኑም ተጠቁሟል።

በዚህም ምክንያት በሶዶ ወረዳ ከምሽቱ ኹለት ሰዓት እስከ ጠዋት 12 ሰዓት ድረስ በሰውና በተሽከርካሪዎች ላይ የእንቅሰቃሴ ገደብ መጣሉን ነው የተመላከተው።

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳው በጉዳዩ ላይ መረጃ እየተሰባሰበ መሆኑን ጠቅሰው፤ "ሙሉ መረጃ ሲገኝ የምንገልጽ ይሆናል።" ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

እንዲሁም ከጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ ላጫ ጋሩማን እና ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የተደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ ስልክ ባለማንሳታቸው ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።

Via Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በመንግሥት የጸጥታ አካላትና በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መካከል ጠንካራ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በመንግሥት የጸጥታ አካላት እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራውና በመንግሥት "ኦነግ ሸኔ" ተብሎ በአሸባሪነት በተፈረጀው ታጣቂ ቡድን መካከል ከባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጀምሮ በተለየ መልኩ ጠንካራ ውጊያ እየተደረገ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ገልጸዋል፡፡

ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአካባቢው ነዋሪዎች፤ "በዞኑ በኹለቱ ኃይሎች መካከል ውጊያ መደረግ ከጀመረ ዓመታት ቢቆጠሩም፣ ካለፈው ሳምንት ሰኔ 17/2015 ጀምሮ እየተደረገ ያለው ውጊያ ግን ጠንካራ ነው።" ብለዋል።

ውጊያው በዞኑ በተለይም ኮምቦሻ እና ጮመን ጉዱሩ ወረዳዎች በስፋት እየተካሄደ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን በእነዚህም አካባቢዎች የንጹሃን ዜጎች ሕይወት መጥፋቱና እና በርካታ የቤት እንስሳት መሞታቸው ተመላክቷል።

በተለይም በኮምቦሻ ወረዳ ቱሉ ሀቢብ ቀበሌ ከአንድ አካባቢ ብቻ ቁጥራቸው ከአስር በላይ የሚሆን ንጹሃን ዜጎች ሕይወታቸው ማለፉን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

ነዋሪዎቹ አክለውም፤ የመንግሥት የጸጥታ አካላት በዋናንተ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአካባቢው እያደረጉት ባለው ኦፕሬሽን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የኦነግ ሸኔ አባላት ሳይገደሉ እንዳልቀረ ነው የጠቀሱት።

የአካባቢው ማህበረሰብ በየጊዜው በሚካሄዱ ውጊያዎች ከቀዬው ሲፈናቀል እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፤ በዚህ ወቅትም ብዙዎች አካባቢያቸውን ለቀው እየወጡ ነው ተብሏል።

በዚህም ጠንካራ ውጊያ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚፈናቀሉ ሰዎች በብዛት ወደ ሻምቡ ከተማ እንዲሁም ሀባቦ ወረዳና ወደ ሌሎች አንጻራዊ ሰላም ወዳለባቸው የተለያዩ ሥፍራዎች እንደሚሄዱ ተገልጿል።

በአካባቢው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄዱ ተደጋጋሚ ውጊያዎች አርሶ አደሮች ማረስ፣ ተማሪዎችም መማር አለመቻላቸው እንዲሁም የንግድ እንቅስቃሴ ማከናወን አስቸጋሪ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፤ የአካባቢው ሠላም ተመልሶ ማህበረሰቡ የተረጋጋ ሕይወት መምራት ይችል ዘንድ መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።

Via Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa
አንድን ግለሰብ በመግደል አስከሬኑን ቆራርጠው መጸዳጃ ቤት ውስጥ የጣሉት ተከሳሾች በሞት እንዲቀጡ ተወሰነ!

678 ሺህ ብር የሚያወጣ በዱቤ የተሸጠን በቆሎ ለግል ጥቅማቸው ለማዋል የንብቱን ባለቤት በመግደል አስከሬኑን በመቆራረጥ መጸዳጃ ቤት ውስጥ የጣሉት ሁለት ተከሳሾች በሞት እንዲቀጡ ተወሰነ፡፡ድርጊቱ የተፈጸመው በሀዲያ ዞን ዱና ወረዳ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከተከሳሾቹ አንዱ የንብረቱን ባለቤት በጥይት ከገደለ በኋላ አስከሬኑን ሁለቱም ተከሳሾች ቆራርጠው በማዳበሪያ በመጠቅለል መጸዳጃ ቤት ውስጥ መክተታቸው ተገልጿል፡፡የወረዳው ፖሊስም ለአራት ቀናት ያህል ባደረገው ፍለጋ÷ አገልግሎት መሥጠት ባቆመ አሮጌ መጸዳጃ ቤት ውስጥ የሟችን የተቆራረጠ አስከሬን ማግኘቱን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ!

ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ተጨማሪ ጨዋታ እየቀረው የ2016 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሀድያ ሆሳዕና ያገናኘው የ29ኛ ሳምንት ጨዋታ÷ 9፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡

በጨዋታውም÷ ቸርነት ጉግሳ በመጀመሪያው አጋማሽ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን ረትቷል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ክፍት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን። 
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
      🔹የት/ደረጃ:10
      🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
      🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል ያለው
💥ካሸር አሰልጥኖ
      🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
      🔹ልምድ= 0 አመት
      🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
      🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
      🔹ልምድ= ያለው
      🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=0
     🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው  ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ

መሥፈርቶች

የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች

የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar

Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር


Contact Us:

@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58

☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇

🤳ስልክ  ቁጥራችን 9445



Website
www.sabinaadvisors.com
    👇👇  ለበለጠ መረጃ 👇👇👇

👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ  7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር  702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://tttttt.me/sabinaadvisor

https://www.facebook.com/sabinaadvisor
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚሰሩ ልማቶች ከወዲሁ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ ነው ተባለ፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ከወዲሁ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በመገባደድ ላይ በሚገኘው የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ጥናት ማድረግ ተጀምሯል።

ግድቡ ሲጠናቀቅ ኃይል ከመስጠቱ ባለፈ የቱሪስት መዳረሻ ስለሚሆን፣ ባለሃብቶችን በልማት ስራ ላይ ለማሰማራት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስተባባሪነት ማስተር ፕለን እየዘጋጀለት መሆኑ ተሰምቷል።የህዳሴ ግድብ ውሃው በተኛበት ቦታ ላይ ደሴቶች መኖራቸው ይታወቃል፤ እነዚህም ለቱሪስት መስህብነት እንደሚሆኑ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።በተጨማሪም ለባህር ትራንስፖርት ምቹ ስለሚሆን የቱሪዝም ዘረፉን ያነቃቃል ነው የተባለው።

ሌላው በአካባቢው ከፍተኛ የአሳ ርባታ ለማከናወን የሚያስችል ሁኔታ በመኖሩ፣ ግድቡ እንደተጠናቀቀ በእነዚህ ዘርፎች ላይ የሚሰሩ ስራዎች በጥናት ላይ የተመሠረቱ ለማደሰረግ ጥናቱ ተጀምሯል ነው ያሉት ሚኒስትሩ።ግድቡን ከዳር ለማድረስ አሁንም ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።አራተኛውን የግድቡን የውሃ ሙሌት ለማከናወን ዝግጅት መጀመሩንም ተሰምቷል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የ8ኛ ክፍል ፈተና በመዲናዋ መሰጠት ተጀመረ!

በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል፡፡በመዲናዋ 75 ሺህ 100 የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች÷ በ182 የመፈተኛ ጣቢያ እየተፈተኑ ነው፡፡ዛሬ መሰጠት የተጀመረው ፈተና ነገ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
መንገዶችን በሚያበላሹ የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊጀመር ነው ተባለ!

የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቀረት እንዲሁም በትራፊክ ፍሰት እና ደህንነት ላይ ተፅእኖ የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች ለማስቀረት ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ጥብቅ ቁጥጥር ሊጀምር መሆኑት በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኩማ ተናግረዋል።

በከተማዋ እየተገነቡ  ከሚገኙ የተለያዩ የግንባታ ቦታዎች ተረፈ ምርቶችን እና አፈር እየጫኑ የሚንቀሳቀሱ የጭነት ተሽከርካሪዎች መንገዶችን  ከማበላሸታቸው እና ከማቆሸሻቸው ባሻገር  ለእግረኞች እና ለተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ስጋት እየሆኑ ስለሚገኙ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረግባቸዋል ተብሏል።

ተሽከርካሪዎቹ የጫኑትን ተረፈ ምርቶችና አፈር ሳይሸፍኑ ስለሚንቀሳቀሱ አስፓልቱን እያቆሸሹ የሚገኙ ሲሆን ተረፈ ምርቱን ጭነው ሲወጡ በጎማዎቻቸው ይዘው ወደ አስፈልት በሚወጡት ጭቃም መንገዱን በከፍተኛ ሁኔታ እያቆሸሹ ይገኛል።

ኤጀንሲው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን መሰረተ ልማቱን የሚጎዳ፣ የአሽከርካሪዎች እና የእግረኞች እንቅስቃሴ ላይ የመንገድ ደህንነት ስጋት የሚፈጥር እንዲሁም የከተማዋን መንገዶች የሚያቆሽሹ አሽከርካሪዎች በልዩ ሁኔታ ጥብቅ ቁጥጥር ያደርጋል።

በትራፊክ ጭነት ላይ ተገቢውን ምልክት ሳያደርግ ወይም ተሽከርካሪው ላይ የተጫነውን ጭነት በሚገባ ሳያስር ወይም ሳይሸፍን ያሽከረከረ እንዲሁም በመንገድ ላይ ያፈሰሰውን ወይም የጣለውን ፈሳሽ ወይም ጠጣር ነገሮችን ያላነሳ ወይም ያላጸዳ አሽከርካሪ ቅጣት የሚጣልበት መሆኑን ተጠቁሟል።   የተለያዩ ግንባታዎችን እያከናወኑ የሚገኙ ተቋማት ባለቤቶች እና የጭነት ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች የሚጭኑ ተረፈ ምርቶች እና አፈር መንገድ ላይ እንዳይፈሱ በመሸፈን፣ ወደ አስፋልት ሲወጡ የተሽከርካሪያቸውን ጎማ በማጽዳት መንገድ ላይ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ተጠቀሟል።

ከተቀመጠው የእንቅስቃሴ ቅድመ ጥንቃቄዎች ውጭ በመንቀሳቀስ የከተማዋን አስፓልት ከማባላሸት እና ከማቆሸሽ ባሻገር ለእግረኞች እና ለተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ስጋት የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች ላይ የኤጀንሲው የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና ትራፊክ ፖሊሶች በጋራ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አቶ ብርሃኑ ኩማ ጨምረው ተናግረዋል።

[ዳጉ ጆርናል/ብስራት ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
1
በሃገሪቱም ሆነ በኦሮምያ ክልል ውስጥ ኦነግ በሚል መጠሪያ የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ፓርቲ አንድ ብቻ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ የተመሰረተበትን ሃምሳኛ አመት ምክንያት በማድረግ የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ እንግዶች በተገኙበት ውይይት አድርጓል፡፡

በእለቱ የፓርቲውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በተለይ ከኦነግ ሸኔ ጋር በተያያዘ ያለው እውነታ ምንድን ነው ሃምሳኛ አመቱን እያከበረ ያለውስ የትኛው ኦነግ ነው ሲል አሃዱ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊን አቶ ለሚ ገመቹን አነጋግሯል፡፡

አቶ ለሚ በሰጡት ምላሽም በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስም የሚንቀሳቀሱ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደምም በኦሮምያ ክልል ውስጥ እንደነበሩ አስታውሰው አሁን ላይ ግን አብዛኞቹ እንደሌሉ እና እንደከሰሙ ገልጸዋል፡፡

አክለውም በአሁኑ ሰአት በክልሉም ሆነ በሃገሪቷ ውስጥ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፍቃድ ወስዶ በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው በኦቦ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው እና ያለፉትን ሃምሳ አመታት ለኦሮሞ ነጻነት እና እኩልነት የታገለው ኦነግ መሆኑን ተናረዋል፡፡ከዛ ውጪ በፓርቲው ስም የሚንቀሳቀሱም ሆነ የሚጠሩ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፓርቲው ምንም አይነት እውቅና የተሰጣቸው አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ባንክ ስራን በይፋ በዛሬው ዕለት አሰጀምረዋል።

በመረሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ፣ የክልሉ አፈጉባኤ ፣የባንኩ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ሀጢያ ፣ የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብርሀም ማርሻሎ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ባንክ በይፈ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አብስረው፤ ባንኩ ክልሉ እየሄደበት ያለውን ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

የክልሉ አስተዳደር ከባንኩ ጋር በጋራ በመስራት ለስራ ፈጣሪዎች የብድር አገልግሎት በመስጠት ብሎም ተደራሽነትን የማረጋገጥ ስራ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከፍተኛ የሆነ የበጀት ጉድለት ያገለባቸውን ተቋማት የወንጀል ምርምራ እንዲደረግባቸው ጉዳዩን ለፌደራል ፖሊሲ ኮምሽን አሳልፎ ሊሰጥ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ከመመሪያ እና ደንብ ውጪ ያለአግባብ ክፍያ የፈጸሙ፤ ከተያዘላቸው በጀት ውጪ የተጠቀሙ እና ሌሎች ጉድለቶች የተገኘባቸው በርካታ ተቋማትን አስመልክቶ የፌደራል ዋና ኦዲተር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡

ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በተደጋጋሚ ለህዝብ ተወካዮዎች ምክርቤት በሚያቀርበው ሪፖርት መሰረት ተቋማቱ ተጠያቂ እንዲሆኑ ምን መደረግ አለበት ሲል አሀዱም የህግ ባለሙያዎችን ጠይቋል፡፡

የፌደራል ዋና ኦዲተር ባቀረበው ሪፖርት መሰረት የመንግስት ተጠሪ ተቋማት ህግ እና ስርዓትን መሰረት አድረገው በጀታቸውን እያስተዳደሩ እንዳልሆነ ማረጋገጥ ይቻላል ያሉት የህግ ባለሙያው አቶ ካሳሁን ሙላቱ ናቸው፡፡

ሪፖርት የሚቀርብበት ዋና ምክንያት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንደሆነ ለኦዲተር ዋና መስሪያቤት በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን ላይ በግልጽ የሚያመላክት የመሆኑንነ የተናገሩት የህግ ባለሙያው ከፍተኛ የሆነ የበጀት ጉድለት ያገኛባቸውን ተቋማት የወንጀል ምርምራ እንዲደርገባቸው ጉዳዩን ለፌደራል ፖሊስ ኮምሽን አሳልፎ መስጠት እና ፍርድ ቤትም በማቅርብ ሀላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የፌዴራል የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የመንግሥት ከፍተኛ ተሿሚ ባለሥልጣናትን በስማቸው እና በቅርብ ቤተሰቦቻቸው ባለቤትነት የተመዘገቡ የንግድ ድርጅቶችን ወይም የአክሲዮን ድርሻዎችን እንዲያቋርጡ ወይም ለሌላ እንዲያስተላፉ የሚያስገድድ ደንብ ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ረቂቅ ደንቡ የመንግሥት ተሿሚዎች በሥራቸው ምክንያት ከሚከሰት የጥቅም ግጭት መራቅ አለባቸው ይላል።
በረቂቅ ደንቡ ክፍል ሦስት ውስጥ ባለስልጣናት የጥቅም ግጭትን ለመከላከል እና ለማስወገድ የጥቅም ግጭት መነሻ ከሆነው የግል ድርጅት ድርሻውን እንዲያስተላለፍ ወይም እንዲያቋርጥ፣ በግል የያዘውን ድርጅት በውክልና እንዲያሠራ እና ካፒታሉንና ትርፉን ማዘዝ በማይችልበት ሒሳብ ቁጥር እንዲያስቀምጥ እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት በቦርድ አባልነት ፣በዳይሬክተርነት የያዘውን ኃላፊነት እንዲለቅ የሚያደርግ ነው።

አንድ የሕግ ባለሙያ ለDW በሰጡት አስተያየት ይህ ረቂቅ ደንብ ግለሰቦች ባለስልጣን ስለሆኑ ብቻ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ያለ አግባብ የሚነካ ነው ብለዋል። የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ - ሙስና ኮሚሽን ከዚህ በፊት ባለሥልጣናቱ ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ጀምሮት የነበረውን ሥራ ማስቀጠል ሲገባው ሌላ ረቂቅ ሕግ ይዞ መምጣቱ የባለስልጣናቱን ሕገ መንግሥታዊ መብት የሚጋፋ ነው ያሉት እኚሁ የሕግ ባለሙያ ሙስናን ለመከላከል ዋናው መፍትሔ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ነው ብለዋል ሲል DW ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሀዋሳ ከተማ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትንና ውርጃን በሠላማዊ ሰልፍ አወገዙ ፡፡

ሠልፈኞቹ ድርጊቶቹን ያወገዙት በከተማው ዋና ዋና ጎዳናዎች በመዘዋወርና የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ነው። የተቃውሞ ሰልፉን ያስተባበሩት በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ 22 የቃለሕይወት አብያተ ክርስትያን ናቸው።

በሃዋሳ ዩኑቨርሲቲ የህግ መምህር እና ተመራማሪ አቶ ብርሃኑ ገኔቦ በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ የተመሳሳይ ጾታ ግኑኝነት ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚያስከትል ገልጸዋል።

Via DW
@Yenetube @Fikerassefa
በአማራ ክልል፤ የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው “በግለሰብ በተፈጸመባቸው ጥቃት” ተገደሉ!

በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን የምትገኘው የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው በተከፈተባቸው ተኩስ ሲገደሉ ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታወቀ። ለወረዳዋ ፖሊስ አዛዦች ህልፈት ምክንያት የሆነውን ተኩስ ከፍቷል የተባለ ተጠርጣሪን ለመያዝ ፍለጋ እየተከናወነ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዘውዱ ታደለ እና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ሽመልስ ጥቃት የተፈጸመባቸው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 26፤ 2015 ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ እንደሆነ የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ጋሻዬ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የፖሊስ አዛዦቹ ላይ ተኩስ የተከፈተባቸው፤ በዛሬው ዕለት በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰጠ ያለውን “የስምንተኛ ክፍል ፈተና ደህንነት ለመከታተል ወደ አባይ ሸለቆ ትምህርት ቤት በመኪና እየተጓዙ በነበረበት ወቅት” መሆኑን የኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊው አስረድተዋል።

ሁለቱ የፖሊስ አዛዦች “ግልገሌ” የተባለች ቀበሌ ላይ ሲደርሱ “መንገድ ላይ ሲጠብቃቸው ነበር” በተባለ ግለሰብ ተኩስ እንደተከፈተባቸው አቶ ጌታሁን ተናግረዋል። በዚህ ጥቃት በጥይት የተመቱት የፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር ዘውዱ እና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ሹፌራቸው “እግሩ ላይ ተመትቶ” ጉዳት እንደደረሰበት ኃላፊው አክለዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ረሜዲያል ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ትናንት ሰኔ 26/2015 ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በፈተና ሂደት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር የሚከተሉትን ውሳኔዎች ያሳለፈ መሆኑን እንገልጻለን።

1) ሰኔ 26/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ

2)ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ

3)በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት የሚሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።

የትምህርት ሚኒስቴር!
@Yenetube @Fikerassefa
እስከ 40 ሺሕ የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች ተገድለዋል ተባለ!

በኢትዮጵያ የመንግሥት ለውጥ ከተደረገበት 2010 ወዲህ ባሉት ዓመታት ከ25 ሺሕ እስከ 40 ሺሕ የሚገመቱ የአማራ ተወላጆች በአክራሪ ብሔርተኞች መገደላቸውን ካውንተር ፓንች በድህረ ገጹ አስነብቧል።

ዘገባው አብዛኞቹ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በሚል በሚጠራው እና በመንግሥት “ኦነግ ሸኔ” ተብሎ በተፈረጀው ኃይል የተገደሉ መሆናቸውን መገለጹን አዲስ ማለዳ ከድህረ ገጹ ዘገባ ተመልክታለች፡፡

ከዚህ ባለፈም፤ ከአምስት እስከ ሰባት ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎች በየጊዜው በሚፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው ነው የተገለጸው።

እንዲሁም በአገሪቱ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከጊዜ ወደ ጊዜ አደጋ ውስጥ እየገባ ነው የተባለ ሲሆን፤ የመሰበሰብ፣ የሚዲያ ነጻነት እና ሌሎች ተያያዥ ዴሞክራሲያዊ መብቶች አደጋ ውስጥ መግባታቸው ተጠቅሷል።

በዚህም ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ የአገር ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በግልጽ የሚናገሩ ጋዜጠኞች እና የግል የሚዲያ ተቋማት በነጻነት የመናገርና የመስራት መብታቸውን አጥተዋል ሲል የካውንተር ፓንች ዘገባ አመላክቷል።

ዘገባው መሰረቱን በአሜሪካ ያደረገ “ፍሪደም ሃውስ” የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅትን መረጃ ጠቅሶ፤ በኢትዮጵያ በስፋት መንግሥትን የሚተቹ አካላት ከእውቅናቸው ውጭ በሆነ መንገድ በመንግሥት የደህንነት አካላት በእጅ ስልካቸው ላይ ሳይቀር ሚስጥራዊ ክትትል እንደሚደረግባቸው ጠቁሟል።

በአገሪቱ የዘፈቀደ እስራት በተደጋጋሚ እንደሚፈጸም በመጥቀስም፤ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ አክቲቪስቶች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞች ከመኖሪያ ቤታቸው፣ ከሥራ ቦታቸው ወይም ከመንገድ ላይ  ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በደህንነቶች ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ እንደሚወሰዱመወ ተገልጿል።

በአገሪቱ ሥር የሰደደ ሙስና መኖሩን የጠቀሰው ዘገባው፤ ገንዝብ ተቀብለው ፍርድ የሚያጣምሙ ዳኞች ላይ ሳይቀር ያለው ተጠያቂነትም እምብዛም ነው ብሏል።

የጋዜጠኞች መብት ተማጋች ሲፒጄ በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች ነጻነት አሳፋሪ ገጽታ እንዳለው በመጠቆም፤ ባለስልጣናት የታሰሩትን ጋዜጠኞች በሙሉ ሊለቁ እንደሚገባና እስር ቤት ውስጥ በነበሩበት ወቅት በደል ወይም ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል የሚለውን መመርመር ብሎም ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባቸው ማሳሰቡ ይታወሳል።

አብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ ትልቅ ተስፋ ጥሎበት የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስተዳደር፣ ቀስ በቀስ ራሱን ወደ አምባገነናዊ ስርዓት እየለወጠ ነው ሲልም ካውንተር ፓንች በዘገባው አመላክቷል።

Via Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa