የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ
መሥፈርቶች
የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች
የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar
Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር
Contact Us:
@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58
☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇
🤳ስልክ ቁጥራችን 9445
Website
www.sabinaadvisors.com
👇👇 ለበለጠ መረጃ 👇👇👇
👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602
ከታላቅ አክብሮት ጋር !!!
https://tttttt.me/sabinaadvisor
https://www.facebook.com/sabinaadvisor
መሥፈርቶች
የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች
የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar
Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር
Contact Us:
@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58
☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇
🤳ስልክ ቁጥራችን 9445
Website
www.sabinaadvisors.com
👇👇 ለበለጠ መረጃ 👇👇👇
👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602
ከታላቅ አክብሮት ጋር !!!
https://tttttt.me/sabinaadvisor
https://www.facebook.com/sabinaadvisor
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው
Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy
Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL
Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚሰሩ ልማቶች ከወዲሁ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ ነው ተባለ፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ከወዲሁ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በመገባደድ ላይ በሚገኘው የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ጥናት ማድረግ ተጀምሯል።
ግድቡ ሲጠናቀቅ ኃይል ከመስጠቱ ባለፈ የቱሪስት መዳረሻ ስለሚሆን፣ ባለሃብቶችን በልማት ስራ ላይ ለማሰማራት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስተባባሪነት ማስተር ፕለን እየዘጋጀለት መሆኑ ተሰምቷል።የህዳሴ ግድብ ውሃው በተኛበት ቦታ ላይ ደሴቶች መኖራቸው ይታወቃል፤ እነዚህም ለቱሪስት መስህብነት እንደሚሆኑ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።በተጨማሪም ለባህር ትራንስፖርት ምቹ ስለሚሆን የቱሪዝም ዘረፉን ያነቃቃል ነው የተባለው።
ሌላው በአካባቢው ከፍተኛ የአሳ ርባታ ለማከናወን የሚያስችል ሁኔታ በመኖሩ፣ ግድቡ እንደተጠናቀቀ በእነዚህ ዘርፎች ላይ የሚሰሩ ስራዎች በጥናት ላይ የተመሠረቱ ለማደሰረግ ጥናቱ ተጀምሯል ነው ያሉት ሚኒስትሩ።ግድቡን ከዳር ለማድረስ አሁንም ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።አራተኛውን የግድቡን የውሃ ሙሌት ለማከናወን ዝግጅት መጀመሩንም ተሰምቷል።
[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa

የ8ኛ ክፍል ፈተና በመዲናዋ መሰጠት ተጀመረ!
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል፡፡በመዲናዋ 75 ሺህ 100 የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች÷ በ182 የመፈተኛ ጣቢያ እየተፈተኑ ነው፡፡ዛሬ መሰጠት የተጀመረው ፈተና ነገ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል፡፡በመዲናዋ 75 ሺህ 100 የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች÷ በ182 የመፈተኛ ጣቢያ እየተፈተኑ ነው፡፡ዛሬ መሰጠት የተጀመረው ፈተና ነገ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
መንገዶችን በሚያበላሹ የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊጀመር ነው ተባለ!
የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቀረት እንዲሁም በትራፊክ ፍሰት እና ደህንነት ላይ ተፅእኖ የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች ለማስቀረት ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ጥብቅ ቁጥጥር ሊጀምር መሆኑት በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኩማ ተናግረዋል።
በከተማዋ እየተገነቡ ከሚገኙ የተለያዩ የግንባታ ቦታዎች ተረፈ ምርቶችን እና አፈር እየጫኑ የሚንቀሳቀሱ የጭነት ተሽከርካሪዎች መንገዶችን ከማበላሸታቸው እና ከማቆሸሻቸው ባሻገር ለእግረኞች እና ለተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ስጋት እየሆኑ ስለሚገኙ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረግባቸዋል ተብሏል።
ተሽከርካሪዎቹ የጫኑትን ተረፈ ምርቶችና አፈር ሳይሸፍኑ ስለሚንቀሳቀሱ አስፓልቱን እያቆሸሹ የሚገኙ ሲሆን ተረፈ ምርቱን ጭነው ሲወጡ በጎማዎቻቸው ይዘው ወደ አስፈልት በሚወጡት ጭቃም መንገዱን በከፍተኛ ሁኔታ እያቆሸሹ ይገኛል።
ኤጀንሲው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን መሰረተ ልማቱን የሚጎዳ፣ የአሽከርካሪዎች እና የእግረኞች እንቅስቃሴ ላይ የመንገድ ደህንነት ስጋት የሚፈጥር እንዲሁም የከተማዋን መንገዶች የሚያቆሽሹ አሽከርካሪዎች በልዩ ሁኔታ ጥብቅ ቁጥጥር ያደርጋል።
በትራፊክ ጭነት ላይ ተገቢውን ምልክት ሳያደርግ ወይም ተሽከርካሪው ላይ የተጫነውን ጭነት በሚገባ ሳያስር ወይም ሳይሸፍን ያሽከረከረ እንዲሁም በመንገድ ላይ ያፈሰሰውን ወይም የጣለውን ፈሳሽ ወይም ጠጣር ነገሮችን ያላነሳ ወይም ያላጸዳ አሽከርካሪ ቅጣት የሚጣልበት መሆኑን ተጠቁሟል። የተለያዩ ግንባታዎችን እያከናወኑ የሚገኙ ተቋማት ባለቤቶች እና የጭነት ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች የሚጭኑ ተረፈ ምርቶች እና አፈር መንገድ ላይ እንዳይፈሱ በመሸፈን፣ ወደ አስፋልት ሲወጡ የተሽከርካሪያቸውን ጎማ በማጽዳት መንገድ ላይ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ተጠቀሟል።
ከተቀመጠው የእንቅስቃሴ ቅድመ ጥንቃቄዎች ውጭ በመንቀሳቀስ የከተማዋን አስፓልት ከማባላሸት እና ከማቆሸሽ ባሻገር ለእግረኞች እና ለተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ስጋት የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች ላይ የኤጀንሲው የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና ትራፊክ ፖሊሶች በጋራ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አቶ ብርሃኑ ኩማ ጨምረው ተናግረዋል።
[ዳጉ ጆርናል/ብስራት ሬዲዮ]

❤1
በሃገሪቱም ሆነ በኦሮምያ ክልል ውስጥ ኦነግ በሚል መጠሪያ የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ፓርቲ አንድ ብቻ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ የተመሰረተበትን ሃምሳኛ አመት ምክንያት በማድረግ የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ እንግዶች በተገኙበት ውይይት አድርጓል፡፡
በእለቱ የፓርቲውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በተለይ ከኦነግ ሸኔ ጋር በተያያዘ ያለው እውነታ ምንድን ነው ሃምሳኛ አመቱን እያከበረ ያለውስ የትኛው ኦነግ ነው ሲል አሃዱ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊን አቶ ለሚ ገመቹን አነጋግሯል፡፡
አቶ ለሚ በሰጡት ምላሽም በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስም የሚንቀሳቀሱ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደምም በኦሮምያ ክልል ውስጥ እንደነበሩ አስታውሰው አሁን ላይ ግን አብዛኞቹ እንደሌሉ እና እንደከሰሙ ገልጸዋል፡፡
አክለውም በአሁኑ ሰአት በክልሉም ሆነ በሃገሪቷ ውስጥ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፍቃድ ወስዶ በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው በኦቦ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው እና ያለፉትን ሃምሳ አመታት ለኦሮሞ ነጻነት እና እኩልነት የታገለው ኦነግ መሆኑን ተናረዋል፡፡ከዛ ውጪ በፓርቲው ስም የሚንቀሳቀሱም ሆነ የሚጠሩ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፓርቲው ምንም አይነት እውቅና የተሰጣቸው አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
[Ahadu]

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ባንክ ስራን በይፋ በዛሬው ዕለት አሰጀምረዋል።
በመረሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ፣ የክልሉ አፈጉባኤ ፣የባንኩ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ሀጢያ ፣ የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብርሀም ማርሻሎ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ባንክ በይፈ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አብስረው፤ ባንኩ ክልሉ እየሄደበት ያለውን ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
የክልሉ አስተዳደር ከባንኩ ጋር በጋራ በመስራት ለስራ ፈጣሪዎች የብድር አገልግሎት በመስጠት ብሎም ተደራሽነትን የማረጋገጥ ስራ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከፍተኛ የሆነ የበጀት ጉድለት ያገለባቸውን ተቋማት የወንጀል ምርምራ እንዲደረግባቸው ጉዳዩን ለፌደራል ፖሊሲ ኮምሽን አሳልፎ ሊሰጥ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
ከመመሪያ እና ደንብ ውጪ ያለአግባብ ክፍያ የፈጸሙ፤ ከተያዘላቸው በጀት ውጪ የተጠቀሙ እና ሌሎች ጉድለቶች የተገኘባቸው በርካታ ተቋማትን አስመልክቶ የፌደራል ዋና ኦዲተር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡
ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በተደጋጋሚ ለህዝብ ተወካዮዎች ምክርቤት በሚያቀርበው ሪፖርት መሰረት ተቋማቱ ተጠያቂ እንዲሆኑ ምን መደረግ አለበት ሲል አሀዱም የህግ ባለሙያዎችን ጠይቋል፡፡
የፌደራል ዋና ኦዲተር ባቀረበው ሪፖርት መሰረት የመንግስት ተጠሪ ተቋማት ህግ እና ስርዓትን መሰረት አድረገው በጀታቸውን እያስተዳደሩ እንዳልሆነ ማረጋገጥ ይቻላል ያሉት የህግ ባለሙያው አቶ ካሳሁን ሙላቱ ናቸው፡፡
ሪፖርት የሚቀርብበት ዋና ምክንያት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንደሆነ ለኦዲተር ዋና መስሪያቤት በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን ላይ በግልጽ የሚያመላክት የመሆኑንነ የተናገሩት የህግ ባለሙያው ከፍተኛ የሆነ የበጀት ጉድለት ያገኛባቸውን ተቋማት የወንጀል ምርምራ እንዲደርገባቸው ጉዳዩን ለፌደራል ፖሊስ ኮምሽን አሳልፎ መስጠት እና ፍርድ ቤትም በማቅርብ ሀላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

የፌዴራል የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የመንግሥት ከፍተኛ ተሿሚ ባለሥልጣናትን በስማቸው እና በቅርብ ቤተሰቦቻቸው ባለቤትነት የተመዘገቡ የንግድ ድርጅቶችን ወይም የአክሲዮን ድርሻዎችን እንዲያቋርጡ ወይም ለሌላ እንዲያስተላፉ የሚያስገድድ ደንብ ማዘጋጀቱን አስታወቀ።
ረቂቅ ደንቡ የመንግሥት ተሿሚዎች በሥራቸው ምክንያት ከሚከሰት የጥቅም ግጭት መራቅ አለባቸው ይላል።
በረቂቅ ደንቡ ክፍል ሦስት ውስጥ ባለስልጣናት የጥቅም ግጭትን ለመከላከል እና ለማስወገድ የጥቅም ግጭት መነሻ ከሆነው የግል ድርጅት ድርሻውን እንዲያስተላለፍ ወይም እንዲያቋርጥ፣ በግል የያዘውን ድርጅት በውክልና እንዲያሠራ እና ካፒታሉንና ትርፉን ማዘዝ በማይችልበት ሒሳብ ቁጥር እንዲያስቀምጥ እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት በቦርድ አባልነት ፣በዳይሬክተርነት የያዘውን ኃላፊነት እንዲለቅ የሚያደርግ ነው።
አንድ የሕግ ባለሙያ ለDW በሰጡት አስተያየት ይህ ረቂቅ ደንብ ግለሰቦች ባለስልጣን ስለሆኑ ብቻ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ያለ አግባብ የሚነካ ነው ብለዋል። የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ - ሙስና ኮሚሽን ከዚህ በፊት ባለሥልጣናቱ ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ጀምሮት የነበረውን ሥራ ማስቀጠል ሲገባው ሌላ ረቂቅ ሕግ ይዞ መምጣቱ የባለስልጣናቱን ሕገ መንግሥታዊ መብት የሚጋፋ ነው ያሉት እኚሁ የሕግ ባለሙያ ሙስናን ለመከላከል ዋናው መፍትሔ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ነው ብለዋል ሲል DW ዘግቧል።

በሀዋሳ ከተማ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትንና ውርጃን በሠላማዊ ሰልፍ አወገዙ ፡፡
ሠልፈኞቹ ድርጊቶቹን ያወገዙት በከተማው ዋና ዋና ጎዳናዎች በመዘዋወርና የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ነው። የተቃውሞ ሰልፉን ያስተባበሩት በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ 22 የቃለሕይወት አብያተ ክርስትያን ናቸው።
በሃዋሳ ዩኑቨርሲቲ የህግ መምህር እና ተመራማሪ አቶ ብርሃኑ ገኔቦ በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ የተመሳሳይ ጾታ ግኑኝነት ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚያስከትል ገልጸዋል።
Via DW

በአማራ ክልል፤ የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው “በግለሰብ በተፈጸመባቸው ጥቃት” ተገደሉ!
በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን የምትገኘው የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው በተከፈተባቸው ተኩስ ሲገደሉ ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታወቀ። ለወረዳዋ ፖሊስ አዛዦች ህልፈት ምክንያት የሆነውን ተኩስ ከፍቷል የተባለ ተጠርጣሪን ለመያዝ ፍለጋ እየተከናወነ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዘውዱ ታደለ እና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ሽመልስ ጥቃት የተፈጸመባቸው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 26፤ 2015 ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ እንደሆነ የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ጋሻዬ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የፖሊስ አዛዦቹ ላይ ተኩስ የተከፈተባቸው፤ በዛሬው ዕለት በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰጠ ያለውን “የስምንተኛ ክፍል ፈተና ደህንነት ለመከታተል ወደ አባይ ሸለቆ ትምህርት ቤት በመኪና እየተጓዙ በነበረበት ወቅት” መሆኑን የኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊው አስረድተዋል።
ሁለቱ የፖሊስ አዛዦች “ግልገሌ” የተባለች ቀበሌ ላይ ሲደርሱ “መንገድ ላይ ሲጠብቃቸው ነበር” በተባለ ግለሰብ ተኩስ እንደተከፈተባቸው አቶ ጌታሁን ተናግረዋል። በዚህ ጥቃት በጥይት የተመቱት የፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር ዘውዱ እና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ሹፌራቸው “እግሩ ላይ ተመትቶ” ጉዳት እንደደረሰበት ኃላፊው አክለዋል።
[Ethiopia Insider]

የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ረሜዲያል ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ትናንት ሰኔ 26/2015 ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ በፈተና ሂደት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር የሚከተሉትን ውሳኔዎች ያሳለፈ መሆኑን እንገልጻለን።
1) ሰኔ 26/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ
2)ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ
3)በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት የሚሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።
የትምህርት ሚኒስቴር!

እስከ 40 ሺሕ የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች ተገድለዋል ተባለ!
በኢትዮጵያ የመንግሥት ለውጥ ከተደረገበት 2010 ወዲህ ባሉት ዓመታት ከ25 ሺሕ እስከ 40 ሺሕ የሚገመቱ የአማራ ተወላጆች በአክራሪ ብሔርተኞች መገደላቸውን ካውንተር ፓንች በድህረ ገጹ አስነብቧል።
ዘገባው አብዛኞቹ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በሚል በሚጠራው እና በመንግሥት “ኦነግ ሸኔ” ተብሎ በተፈረጀው ኃይል የተገደሉ መሆናቸውን መገለጹን አዲስ ማለዳ ከድህረ ገጹ ዘገባ ተመልክታለች፡፡
ከዚህ ባለፈም፤ ከአምስት እስከ ሰባት ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎች በየጊዜው በሚፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው ነው የተገለጸው።
እንዲሁም በአገሪቱ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከጊዜ ወደ ጊዜ አደጋ ውስጥ እየገባ ነው የተባለ ሲሆን፤ የመሰበሰብ፣ የሚዲያ ነጻነት እና ሌሎች ተያያዥ ዴሞክራሲያዊ መብቶች አደጋ ውስጥ መግባታቸው ተጠቅሷል።
በዚህም ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ የአገር ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በግልጽ የሚናገሩ ጋዜጠኞች እና የግል የሚዲያ ተቋማት በነጻነት የመናገርና የመስራት መብታቸውን አጥተዋል ሲል የካውንተር ፓንች ዘገባ አመላክቷል።
ዘገባው መሰረቱን በአሜሪካ ያደረገ “ፍሪደም ሃውስ” የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅትን መረጃ ጠቅሶ፤ በኢትዮጵያ በስፋት መንግሥትን የሚተቹ አካላት ከእውቅናቸው ውጭ በሆነ መንገድ በመንግሥት የደህንነት አካላት በእጅ ስልካቸው ላይ ሳይቀር ሚስጥራዊ ክትትል እንደሚደረግባቸው ጠቁሟል።
በአገሪቱ የዘፈቀደ እስራት በተደጋጋሚ እንደሚፈጸም በመጥቀስም፤ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ አክቲቪስቶች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞች ከመኖሪያ ቤታቸው፣ ከሥራ ቦታቸው ወይም ከመንገድ ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በደህንነቶች ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ እንደሚወሰዱመወ ተገልጿል።
በአገሪቱ ሥር የሰደደ ሙስና መኖሩን የጠቀሰው ዘገባው፤ ገንዝብ ተቀብለው ፍርድ የሚያጣምሙ ዳኞች ላይ ሳይቀር ያለው ተጠያቂነትም እምብዛም ነው ብሏል።
የጋዜጠኞች መብት ተማጋች ሲፒጄ በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች ነጻነት አሳፋሪ ገጽታ እንዳለው በመጠቆም፤ ባለስልጣናት የታሰሩትን ጋዜጠኞች በሙሉ ሊለቁ እንደሚገባና እስር ቤት ውስጥ በነበሩበት ወቅት በደል ወይም ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል የሚለውን መመርመር ብሎም ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባቸው ማሳሰቡ ይታወሳል።
አብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ ትልቅ ተስፋ ጥሎበት የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስተዳደር፣ ቀስ በቀስ ራሱን ወደ አምባገነናዊ ስርዓት እየለወጠ ነው ሲልም ካውንተር ፓንች በዘገባው አመላክቷል።
Via Addis Maleda

ኢትዮጵያ ለምርጫ ስርዓት ማጠናከሪያ የ30 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች!
ኢትዮጵያ ዘላቂ ዲሞክራሲን ለማስፈን የሚያስችላትን የምርጫ ስርአት እንድታጠናክር ለማግዝ የሚውል የ30 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የፋናንስ ድጋፍ ስምምነት ፈርማለች።
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ብሐያረዊ ምርጫ ቦርድ እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት መካካል ተፈርሟል።
የበጀት ድጋፉ የምርጫ ቦርድ ተቋማዊ መዋቅርን ለማጠናከር ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ አሳታፊ ፣ተአማኒና ደረጃውን የጠበቀ ምርጫና ህዝበ ውሳኔ እንዲያካሂድ ተቋሙን ማጠናከር፣ ከሲቪክ ተቋማት በጋራ በመሆን በምርጫ ሂደት የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎን ለማሳደግ ይውላል ተብሏል።
እንዲሁም የበጀት ድጋፉ በኢትዮጵያ ነፃ ፍትሀዊ እና ተአማኒ ምርጫ እንዲያከሂድ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንደሚውልም የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ተቋማት እገዛ እንድታገኝ፤ የአሜሪካ መንግስት ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ ተናገሩ!
የኢትዮጵያ መንግስት እንደ ዓለም ባንክ እና አይ ኤም ኤፍ ካሉ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የሚፈልገውን እገዛ እንዲያገኝ፤ የአሜሪካ መንግስት ጠንካራ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ። መንግስት በዓለም አቀፍ ተቋማት በኩል “የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ” የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መንግስት በቅርቡ “ጠንካራ አቋሙን” እንደገለጸ የገንዘብ ሚኒስትሩ ለፓርላማ አባላት አስረድተዋል።
አቶ አህመድ ይህን የተናገሩት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለ2016 በተዘጋጀው የበጀት ረቂቅ ላይ ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 27፤ 2015 ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። “ከአሜሪካ መንግስት ጋር ያለው የዲፕሎማሲ ግንኙነት እጅግ የተሻለ” ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በዚሁ ማብራሪያቸው የገለጹት የገንዘብ ሚኒስትሩ፤ በጦርነቱ ምክንያት የተቋረጠው የአውሮፓ ህብረት የልማት እርዳታ ሊቀጥል እንደሚችል ጥቆማ ሰጥተዋል።
ህብረቱ ለኢትዮጵያ የልማት እርዳታ የሚሰጥበትን “multi-annual development program” እንደገና ለማስጀመር “ከጥቂት ወራት በኋላ” ስምምነት እንደሚፈረም አቶ አህመድ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ አጋሮች የሚጠብቀው እገዛ በበጀት ረቂቁ ውስጥ እንዳልተካተተ ያረጋገጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ፤ ይሁንና መንግስታቸው “የተሻለ ሁኔታ እንደሚኖር” ተስፋ ማድረጉን በንግግራቸው ጠቁመዋል።
Via Ethiopia Insider

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ በዛሬዉ እለት ተገድለዋል!
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ድንገት ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች በመገደላቸው ከተማ አስተዳደሩ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል ሲል ባወጣዉ መግለጫ አሳዉቋል።
አቶ አብዱ የመንግስት ኃላፊነታቸው ለመወጣት ሲሰሩ መገደላቸውን የከተማ መስተዳድሩ መግለጹን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል። ነፍሳቸውንም በጀነት እንዲያሳርፍና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ከተማ አስተዳደሩ ተመኝቷል።
በሸዋሮቢት ከነገ አመሻሽ 12 ጀምሮ የሰዓት እላፊ ታዉጇል። ይህም ይህንኑ የከተማዉ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ግድያን ተከትሎ የተወሰነ ነዉ።

YeneTube
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ በዛሬዉ እለት ተገድለዋል! የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ድንገት ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች በመገደላቸው ከተማ አስተዳደሩ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል ሲል ባወጣዉ መግለጫ አሳዉቋል። አቶ አብዱ የመንግስት ኃላፊነታቸው ለመወጣት ሲሰሩ መገደላቸውን የከተማ መስተዳድሩ መግለጹን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል። ነፍሳቸውንም በጀነት እንዲያሳርፍና…
በሸዋሮቢት እና አካባቢዋ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የተሽከርካሪም ሆነ የሰው እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጣለ!
ማክሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በሸዋሮቢት እና አካባቢዋ ከነገ ሰኔ 28/2015 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ማንኛውም ተሽከርካሪ ይሁን የሰው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የተገደበ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።
ጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፖስቱ ማምሻውን ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ፤ የሸዋሮቢት እና አካባቢዋ ነዋሪዎች የከተማዋ የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ እንዲሆን እና ዜጎች ያለ ስጋት ወጥተው የሚገቡበት ለማድረግ ብዙ ጥረት ተደርጎል ብሏል።
ነገር ግን "አሁንም ከተማዋን ሰው አልባ እንድትሆንና ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እንዲከሰት ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን በርካታ ማሳያዎች እየተስተዋሉ ነው" ያለው ኮማንድ ፖስቱ፤ የነዋሪዎችን እገዛ በማከል ጠንካራ የጸጥታና የሰላም ሥራዎችን መስራት እንደሚጠበቅ ገልጿል።
በዚህም መሰረት ከነገ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ማንኛውም ተሽከርካሪ ይሁን የሰው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የተገደበ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ የምሽት ክለቦችን ጨምሮ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከምሽቱ 12 ሰዓት በኃላ ምንም አይነት አገልግሎት እንዳይሰጡ ገደብ መጣሉንም አስታውቋል።
በተጨማሪም "የከተማው ነዋሪ ለጸጥታ መዋቅሩ እገዛውንና ድጋፍ በማድረግ ከተማዋን ካለባት ከፍተኛ የጸጥታ ችግር ልንታደጋት ይገባል።" ሲል በመግለጫው አሳስቧል።

የጉራጌ ዞን የደቡብ ክልል ምክር ቤት ተወካይ፤ “በመታወቂያ ዋስ” ከእስር ተለቀቁ!
ለሁለት ቀናት በእስር የቆዩት የደቡብ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ታረቀኝ ደግፌ፤ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 27፤ 2015 አመሻሽ ላይ “በመታወቂያ ዋስ” ከእስር መፈታታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። አቶ ታረቀኝ ዛሬ ረፋድ ላይ፤ የደቡብ ክልል ፖሊስ አባላት ወዴት እንደሆነ ወደ አላወቁት ቦታ “ሊወስዷቸው” ሞክረው እንደነበርም ገልጸዋል።
የጉራጌ ዞንን በመወከል የደቡብ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ታረቀኝ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በፌደራል ፖሊስ የተያዙት ከትላንት በስቲያ እሁድ ሰኔ 25 ምሽት 2፡30 ገደማ ነበር። አቶ ታረቀኝ ከመኖሪያ ቤታቸው “ትፈለጋለህ” ተብለው ከተያዙ በኋላ፤ በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መወሰዳቸውን ገልጸዋል።
አቶ ታረቀኝ በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው የመጡትን የፌደራል ፖሊስ አባላት የፍርድ ቤት የእስር ትዕዛዝ ይዘው እንደሆነ መጠየቃቸውን አስታውሰዋል። ለዚህ ጥያቄያቸው ምላሽ አለማግኘታቸውን የሚናገሩት አቶ ታረቀኝ፤ የደቡብ ክልል ምክር ቤት አባልነት መታወቂያቸውን በማሳየት “ያለመከሰስ መብት ያላቸው” መሆኑን ማስረዳታቸውን ጠቅሰዋል። ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳበት “ወረቀት” እንዳለ ቢጠይቁም፤ በተመሳሳይ መልኩ ምላሽ እንዳልተሰጣቸው አብራርተዋል።

🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥
🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan

👍1