YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች:

-  ከፒያሳ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ዋናው መንገድ ቴድሮስ አደባባይ 

-  ከጎተራ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ሪቼ የሚወስደው መንገድ  ለከባድ ተሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ እንዲሁም ለአነስተኛ ተሽከርካሪዎች  ጥላሁን አደባባይ ወይም የቀድሞ 4ኛ ክፍለ ጦር  ጋር

-  ከኬኬር ህንፃ ጀርባ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ የድሮ ለገሃር ግምሩክ

-  ከከፍተኛ ፍርድ ቤት  ፣ በፖሊስ ሆስፒታል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አል ሳም ጨለቅለቅ በስርና በላይ መንገድ

-  ከጎማ ቁጠባ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ

-  ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ መብራት

-  ከሜትሮሎጂ በጥቁር አንበሳ ወደ ፖስታ ቤት የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መ/ቤት

-  ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ኦርማ ጋራዥ  የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት

-  ከአራት ኪሎ  እና ከእሪ በከንቱ የሚመጡ መንገዶች  ፓርላማ መብራት ጋር

-  ከሲግናል ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ

-  ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ ስታዲዩም የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ ወይም  ደንበል ሲቲ ሴንተር  

-  ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅድስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን መስቀለኛ ላይ ከላይና ከታች

-  ከተክለ ኃይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ  ጥቁር አንበሳ ሼል 
-  ከተክለ ሃይማኖት ጎላ ሚካኤል የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ

-  ከጎፋ ፣ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር የሚወስደው አዲሱ መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው  ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከማለዳ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡ 

በመሆኑም ህብረተሰቡ ከፖሊስ የተሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያስተላፈ ሲሆን፤ ለእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የፍቅር፣ የሰላምና የደስታ እንዲሆን በፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ሥም መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የኢድ አል አድሃ (አረፋ)በዓል በሰላም እንዲከበር እያከናወነ ላለው ተግባር ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እና የእምነቱ አባቶች እያደረጉት ላለው ድጋፍ ምስጋናውን እያቀረበ ትብብሩ ተጠናክሮ  እንዲቀጥል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥመው ወይም የፖሊስ አገልግሎት ለማግኘት በአዲስ አበባ ፖሊስ የመረጃ ስልኮች 011-1 11-01-11 ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 መረጃ መስጠት እንደሚቻል ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 

@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተፈታ

ዛሬ ጠዋት ሰኔ 20 ቀን፣ 2015 ዓ.ም. ጠዋት 12: 30 ላይ በፀጥታ ኃይሎች ከመኖር ቤቱ እንደተወሰደ የተነገረለት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዳግም መፈታቱ ተገለጸ ። ተመስገን በአዲስ አበባ ሜኪሲኮ አካባቢ በሚገኘው በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለ6 ሰዓታት ታስሮ እንደነበረም ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለዶቼ ቬለ (DW) ገልጾ ነበር።

ከዚህ ቀደም ተከሶ ነጻ በተባለበት ክስ ለሐምሌ 7 ዳግም ታስሮ እንዲቀርብ ትእዛዝ እንደሰጠበትም ተዘግቧል ።

@Yenetube @Fikerassefa
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች፤ እንኳን ለ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ!
አዋጭ ላልሆኑ አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎት ለማዳረስ በጀት መመደብ ኃላፊነቱ እንዳልሆነ ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ

የቴሌኮም ዘርፉ ለውድድር ገበያ በመከፈቱ የቴሌኮም አገልግሎት ላልተዳረሰባቸውና አዋጭ ላልሆኑ የገጠር አካባቢዎች በጀት መመደብ ኃላፊነቱ እንዳልሆነ፣ ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን ያስታወቀው የሁሉን አቀፍ ተደራሽነት ኃላፊነትን ለመወጣት በጀት መበጀቱን አስመልክቶ፣ የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ላነሱት ጥያቄ ነው፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ የተቋማቸው የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በፓርላማው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዓርብ ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲገመገም ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፣ የቴሌኮም አገልግሎት ያልተዳረሰባቸው አካባቢዎችን ለማዳረስ ተፈላጊው በጀት ተበጅቷል ወይ? ካልተበጀተ ምን ታስቧል? የሚሉ ይገኙበታል፡፡

በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ለውድድር ክፍት በመሆኑ ሁሉን አቀፍ ተደራሽነት ለማረጋገጥ በገጠር አካባቢዎችና አዋጭ ባልሆኑ አካባቢዎች በጀት መበጀት የኢትዮ ቴሌኮም የሥራ ድርሻ ብቻ ተደርጎ ሊወሰድ እንደማይገባ፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ለቀረቡት ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ አስረድተዋል፡፡

ዘርፉን የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን በመሆኑ፣ ባለሥልጣኑ ከመንግሥትም ሆነ ከሌሎች አካላት በጀት አፈላልጎ በኢንዱስትሪው አሠራር መሠረት ለቴሌኮም ኦፕሬተሮች እንደሚያቀርብ፣ እስካሁን ውይይቶች ከመደረጋቸው ውጪ የቀረበ ነገር አለመኖሩን ወ/ሪት ፍሬሕይወት ለቋሚ ኮሚቴው አባላት አብራርተዋል፡፡

Source: Reporter
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲሱ ቤት ግብር ተመን ላይ የተደረገው ክርክር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከቤት ግብር የሚያገኘውን ገቢ ለማሳደግ ያደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ሕጋዊነት ላይ የተለያዩ አመለካከቶች እየተንፀባረቁ ነው፡፡ አስተዳደሩ በበኩሉ፣ የቤት ግብር የታሪፍ ማሻሻያው ከ45 ዓመት በፊት የወጣውን የከተማ ቦታና ቤት ኪራይ አዋጅ መሠረት አድርጎ እንዲተገበር የተደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ማሻሻያውን በተመለከተ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑር እንዳመለከቱትም፣ የቤት ግብር (የንብረት ግብር) እስካሁን ሲተገበር የቆየ መሆኑንና በቅርቡ የተደረገ የታሪፍ ማሻሻያ በ1968 ዓ.ም. የወጣውን አዋጅ ተንተርሶ የተደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

አዲሱ ነገርም ከ45 ዓመት በፊት በነበረ የዋጋ ተመን ተሠልቶ ሲከፈልበት የነበረው የቤት ግብር ተመን ተሻሽሎ ተግባራዊ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

አዋጁ ላይ በግልጽ እንደተመለከተው የግብር መጠኑ መሠረት የሚያደርገው ዓመታዊ የኪራይ ግምት ዋጋ መሆኑን፣ ነገር ግን ይህ የኪራይ ግምት በየጊዜው ወቅታዊ ባለመደረጉ የወቅቱን ዋጋ የሚገልጽ ግመታ መሠራቱን ጠቁመዋል፡፡

 ስለዚህ አሁን የተደረገው ነገር ወቅታዊው የኪራይ ዋጋ ተጠንቶ ለግብሩ መሠረት እንዲሆን በማድረግ ተፈጻሚ እንዲሆን መወሰኑን ከተሰጠው ማብራሪያ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡  

Source: Reporter
@Yenetube @Fikerassefa
ክፍት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን። 
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
      🔹የት/ደረጃ:10
      🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
      🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል ያለው
💥ካሸር አሰልጥኖ
      🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
      🔹ልምድ= 0 አመት
      🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
      🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
      🔹ልምድ= ያለው
      🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=0
     🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው  ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ

መሥፈርቶች

የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች

የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar

Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር


Contact Us:

@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58

☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇

🤳ስልክ  ቁጥራችን 9445



Website
www.sabinaadvisors.com
    👇👇  ለበለጠ መረጃ 👇👇👇

👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ  7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር  702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://tttttt.me/sabinaadvisor

https://www.facebook.com/sabinaadvisor
👍1
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
የወርቅ ማዕድን ሲያሸሹና ህገወጥ የጦር መሣሪያ ይዘው የተገኙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና በጋምቤላ ክልል ከ838 ግራም በላይ የወርቅ ማዕድን ሲያሸሹና ህገወጥ ጦር መሣሪያ ይዘው የተገኙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቢሮ ወረዳና በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ 20 ክላሽንኮቭ ከ934 መሰል ጥይቶች ጋር፣ 8 ሽጉጥ ከ54 መሰል ጥይቶች ጋር፣ ሁለት ኤፍ ዋን ቦንቦች፣ አንድ GPS፣ 172 የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦች፣ ከ838 ግራም በላይ የወርቅ ማዕድን፣ 7 የወርቅ ማቅለጫ ማሽኖች፣ 10 የወርቅ ሚዛን፣ ከ1 ሚልዮን 653 ሺህ ብር በላይ በአሶሳ ዞን ኩምሩክ የፍተሻ ጣቢያ መያዙን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ሊውሉ የቻሉት የማዕድን ግብይት አዋጅ ቁጥር 1144/2011 የተደነገገውን ክልከላ በመተላለፍ በሕገ-ወጥ መንገድ የወርቅ ማዕድን በማሸሽ ለግል ጥቅማቸው ለማዋል ሲሉ ነው፡፡

በተጨማሪም በጣቢያው በተካሄደው ፍተሻ 20 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፤ ከ934 መሰል ጥይቶች ጋር እና ስምንት የተለያዩ ሽጉጦች ከ54 መሰል ጥይቶች ጋር፣ ሁለት ቦንቦች፣ አንድ ጂፒኤስ ተገኝቷል፡፡

ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያን በመጣስ በግለሰብ ደረጃ ከመቶ ሺህ ብር በላይ ከ1 ሚሊየን 653 ሺህ ብር በላይ ይዘው ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳዩ በምርመራ እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል።


በመሆኑም ኅብረተሰቡ በመሰል የወንጀል ድርጊቶች የተሰማሩ ግለሰቦችና ቡድኖችን በማጋለጥ አሳልፎ ለፀጥታ አካላት በመስጠት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ጥሪውን አቅርቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
በላስ ቬጋስ ኢትዮጵያውያን የበዙበት አካባቢ “ትንሿ ኢትዮጵያ” በሚል እንዲሰየም ተወሰነ!

የላስ ቬጋስ ከተማ ክላርክ ወረዳ ኮሚሽን፣ ባለፈው ሳምንት ተሰብስቦ፣ ኢትዮጵያውያን በዝተው የሚኖሩበት አካባቢ፣ “ትንሿ ኢትዮጵያ” የሚል ስያሜ እንዲያገኝ ውሳኔ አሳልፏል።

በኒቫዳ ላስሼጋስ ከተማ፣ “ትንሽዋ ኢትዮጵያ” ተብሎ የሚጠራው የመንገድ ስያሜ፣ በከተማዋ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መጽደቁንና ይህንኑም ሥራ ላይ ለማዋል በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ፣ በላስቬጋስ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ንኡስ ኮሚቴ አባላት አስታወቁ።የዚኹ ኮሚቴ አስተባባሪ እና ሊቀ መንበር አቶ ግርማ ዘይድ በሰጡት ማብራርያ፣ ኮሚቴው፥ ይህን ስያሜ ለማጸደቅ፣ ብዙ ውጣ ውረዶችን እንዳለፈና እልክ አስጨራሽ እንደነበር ተናግረዋል።

የስያሜው መጽደቅ፣ በከተማዋ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ኾነ ለውጭ አገር ዜጎች ላቅ ያለ ጠቀሜታ እንደሚሰጥና የኢትዮጵያን ባህል በማስተዋወቁ ረገድ ክፍተኛ እስተዋፅኦ እንደሚኖረው፣ በንግድ እና በመሳስሉት ሥራዎች ላይ የተሠማሩት የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በዚኹ የመንገድ ስያሜ በተሰጠው ሥፍራ፣ ዐዲስ ማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ተቋማት ለማሳደግ ዕቅድ እንዳለም፣ በንኡስ ኮሚቴው ማብራርያ ተጠቁሟል። በላስ ሼጋስ፣ ወደ 40 ሺሕ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ነዋሪዎች እንደሚገኙ ይታውቃል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል በይፋ ጥያቄ ማቅረቧ ተገለጸ!

ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል በይፋ ጥያቄ ማቅረቧን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፤ በመግለጫቸውም ኢትዮጵያ ጥቅሞቿን ሊያስጠብቁ ከሚችሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር መስራቷን ትቀጥላለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ በብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የተመሰረተው ብሪክስን ለመቀላቀል በይፋ ጥያቄ ማቅረቧ ተገልጿል።

"ብሪክስ ከኢትዮጵያ ለቀረበለት ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ እንደሚሰጠን እንጠብቃለን።" ያሉት አምባሳደር መለስ፤ ከሌሎች ብሔራዊ ጥቅሞችን ሊያስጠብቁ ከሚችሉ ተቋማት ጋር መስራታችንን እንቀጥላለንም ብለዋል።

አባል አገራት ያቀረቡትን የእንቀላቀል ጥያቄ ምላሽ እንደሚሰጥ ተገልጿል።ሳውዲ አረቢያ፣ አረብ ኢምሬትስ፣ ኢራን፣ ቱርክ፣ ግብጽ እና አልጀሪያ ብሪክስን ለመቀላቀል ጥያቄ ካቀረቡ አገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ስራ ካቆመ ሶስት ወራት ማስቆጠሩ ተገለጸ

በአዲስአበባ የሚገኘዉ ከቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያመነጨው ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ስራ ካቆመ ሶስት ወራት ማስቆጠሩን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 26ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ሪፖርት ያቀረቡት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ። ለዚህም ተቋሙ ከኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የሚደረግለት ክትትልና ድጋፍ የሌለ መሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል።

የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫዉ በሰዓት 50 ሜጋ ዋት ለማመንጨት የተቋቋመ የነበረ ቢሆንም ከሶስት ወራት በፊት መስሪያቤቱ ባደረገዉ ክትትል 13 ሜጋ ዋት ብቻ እያመነጨ የነበረ መሆኑን ጨምረዉ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

ባለስልጣኑ ዉፍረታቸዉ 0.03 ሚሊ ሜትር እና ከዚያ በታች የሆኑና ከአፈር ጋር በቀላሉ የማይቀላቀሉና የማይበሰብሱ ምርቶችን ተለይቶ ከተቀመጠው አገልግሎት በቀር ወደ ሀገር እንዳይገቡ ወይም እንዳይመረቱ ተከታታይነት ባለዉ መልኩ ክትትል ማድረግ ሲገባዉ ይህን ያለከናወነ መሆኑ ፤ ከህግ ዉጪ የሰሩ ተቋማትንም እርምጃ እንዲወሰድባቸው ያላደረገ እንዲሁም በርካታ ሀላፊነቶቹን ያልተወጣ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ፊት ተናግረዋል።

Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ተገለጸ!

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከሰኔ 23/2015 እስከ ሐምሌ 30/2015 ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሁሉም ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ በሰኔ ወር በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

በዚሁ መሠረት፦
1. ቤንዚን ……………………………………… ብር 69.52 በሊትር
2. ነጭ ናፍጣ…………………………………… ብር 71.15 በሊትር
3. ኬሮሲን ……………………………………... ብር 71.15 በሊትር
4. የአውሮፕላን ነዳጅ …………………………. ብር 65.35 በሊትር
5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ………………………….. ብር 57.97 በሊትር
6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ………………………….. ብር 56.63 በሊትር የሚሸጥ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ፍትህ ሚንስቴር በሕክምና ሙያ ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የተመለከተ የምርመራና ክስ የተግባር መመሪያ አዘጋጅቶ ለባለድርሻ አካላት ለውይይት ማቅረቡን የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል።

የተግባር መመሪያው የተዘጋጀው፣ በሕክምና አገልግሎት ወቅት በሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ የሚካሄዱ ምርመራዎችና የሚመሠረቱ ክሶች የሚመሩባቸውን መርኾዎች ለመቅረጽ፣ የምርመራና ክስ ሂደቶች የሕክምና ሙያን ልዩ ባሕሪያት እንዲያገናዘቡ ለማድረግና የተጎጂዎችን ጥቅም ለማስከበር እንደኾነ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።በሕክምና ወቅት በሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ ምርመራ ለማድረግና ክስ ለመመስረት እንዲኹም ፍርድ ቤቶች ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት ሲቸገሩ ይስተዋላል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ክፍት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

🔴በሁሉም ስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት እንፈልጋለን። 
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥ጉዳይ አስፈፃሚ/smart phone ያለው/
      🔹የት/ደረጃ:10
      🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
      🔹ደሞዝ:5000+ የቀን አበል ያለው
💥ካሸር አሰልጥኖ
      🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
      🔹ልምድ= 0 አመት
      🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
      🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
      🔹ልምድ= ያለው
      🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,500
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
     🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
     🔹የስራ ልምድ=0
     🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው  ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
Forwarded from YeneTube
የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ

መሥፈርቶች

የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች

የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar

Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር


Contact Us:

@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58

☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇

🤳ስልክ  ቁጥራችን 9445



Website
www.sabinaadvisors.com
    👇👇  ለበለጠ መረጃ 👇👇👇

👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ  7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር  702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://tttttt.me/sabinaadvisor

https://www.facebook.com/sabinaadvisor
👍1
Forwarded from YeneTube
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥስት ክስ በማንሳት ምንም የፋይናንስ ድጋፍ ክልከላ እንደማይደረግባት አስታወቀች!

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥስት ክስ በማንሳት አገሪቱ ከዚህ በኋላ ምንም አይነት የፋይናንስ ድጋፍና አቅርቦት ክልከላ እንደማይደረግባት አስታወቀች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰነድን ዋቢ አድርጎ ፎሬይን ፖሊሲ መፅሄት እንደፃፈው፤ ዋሽንግተን በኢትዮጵያ ላይ የምታነሳውን የሰብዓዊ መብት ጥስት ክስን ጥላለች።

ለአገሪቱ ኮንግረስ የተላከው ይህ የውስጥ ማስታወሻ አሜሪካ ይህንን ክስ በማንሳቷ ከዚህ በኋላ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ኢትዮጵያ ከዋሽንግተንም ሆነ ከሌሎች ዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ገንዘብ እንዳታገኝ ሲያደርግ የነበረውን መከላከል ያቆማል ይላል።

የአሜሪካ ውሳኔ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) እና ከዓለም ባንክ የገንዘብ  ድጋፍና ብድር እንድታገኝ የሚያስችል ነው።

ውሳኔው ዋሽንግተን በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የሻከረውን የኹለቱን አገራት ግንኙነት ለማደስ ፍላጎት እንዳላት ያሳያል መባሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በተፈናቃዮች በተጨናነቁት የደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፖች የኩፍኝ ወረርሽኝ ተከሠተ!

በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኙ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፖች ውስጥ የኩፍኝ ወረርሽኝ እንደተከሠተ፣ የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡የኩፍኙ ወረርሽኝ ከተከሠተ፣ ሁለት ሣምንት መቆጠሩን የገለፁት የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሓላፊ አቶ በቀለ ገብሬ፣ እስከ አሁን 80 ሰዎች በኩፍኝ መያዛቸውን ገልፀዋል።
በበሽታው የተያዙት ሰዎች ቁጥር፣ የመምሪያ ሓላፊው ከተናገሩት እንደሚበልጥ፣ በልዩ ልዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚኖሩ ተፈናቃዮች ይናገራሉ፡፡

በበሽታው እስከ አሁን የሞት አደጋ አለመድረሱንና እንዳይስፋፋ ግን፣ 10ሺሕ ለሚደርሱ ተፈናቃዮች ክትባት ሲሰጥ እንደቆየ፣ ሓላፊው አክለው ገልጸዋል፡፡20ሺሕ ተፈናቃዮች ይኖሩበታል በሚባለው ቻይና ካምፕ፣ የተፈናቃዮቹ አስተባባሪ የሆኑት ቤትዬ ደርቤ፣ የኩፍኙ ክሥተት አሳሳቢ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡

ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉና በጤናው ዘርፍ እንደሚሠሩ የተናገሩ አንድ የከተማዋ ነዋሪ በበኩላቸው፣ “በሽታው ከመጠለያ ጣቢያዎቹ ውጭ ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋት አድሮብናል፤” ብለዋል፡፡ከዚህ ቀደም የመጠለያ ካምፖች አቅንቶ በነበረበት ወቅት ያናገራቸው ተፈናቃዮች፥ በቂ የመጸዳጃ፣ የውኃ፣ የምግብ እና የመጠለያ አቅርቦት በሌለበት በማንኛውም ሰዓት ወረርሽኝ ሊከሠት ይችላል፤ የሚል ስጋት እንዳለባቸው፣ ተፈናቃዮቹ መናገራቸው
ተዘግቦ ነበር፡፡

ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ልየ ዞኖች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኙ ስድስት መጠለያ ጣቢያዎች የሚኖሩ ተፈናቃዮች ቁጥር 30ሺሕ እንደሚደርስ፣ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
ጀሞ መስታወት ፋብሪካ ጀርባ በደረሰ የእሳት አደጋ ስድስት የንግድ ሱቆች ተቃጠሉ!

በአዲስ አበባ ከተማ ትላንት ምሽት 1:44 ሰዓት ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ አንድ ጀሞ መስታወት ፋብሪካ ጀርባ በደረሰ የእሳት አደጋ ስድስት የንግድ ሱቆች  መቃጠላቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አራት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና 28 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች  የተሰማሩ ሲሆን፤ የእሳት አደጋዉ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርሰ መቆጣጠር መቻሉ ተገልጿል። በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፤ ምሽት 3:43 ሰዓት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጣፎ 2 ኛ በር አካባቢ መንገድ ሲጠቀም የነበረ የ44 ዓመት እግረኛ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-53457 በሆነ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ተገጭቶ ሕይወቱ ማለፉ ተነግሯል።የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሽከርካሪዉ ተጭኖት የነበረዉን አስከሬን በማሽነሪ ተጠቅመዉ ማውጣታቸውም ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa