YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የሰዴን ሶዶ የወረዳ አመራር ተገድለው መገኘታቸው ተገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፤ የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ከቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱ ከኹለት ቀን በኃላ ተገድለው መገኘታቸው ተገለጸ።የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ቅዳሜ ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተሰወዱ በኋላ ማክሰኞ ተገድለው መገኘታቸውን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሃይሉ አብዶ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግረዋል።

ኃላፊው፤ "በቀለ ቃቻ በአዳማ ከተማ ስብሰባ ላይ ነበሩ። ባለፈው ቅዳሜ ወደ ቤተሰብ ተመለሱ፤ በዕለቱ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ከቤታቸው ባልታወቁ ሃይሎች ታፍነው ተወስደዋል፡፡" ሲሉ ተናግረዋል።ቅዳሜ ምሽት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው የተወሰዱት የወረዳው አስተዳዳሪ ላለፉት ኹለት ቀናት የት እንዳሉ ሳይታወቅ ቆይቶ ባለፈው ማክሰኞ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ተገድለው ተገኝተዋል ሲሉም ገልጸዋል።

የአስተዳዳሪው አስክሬን በቶሌ ወረዳ፣ ኢሉ ወረዳ እና በበቾ ወረዳ መካከል በጸጥታ ኃይሎች አሰሳ መገኘቱም ተመላክቷል።በቀለ፤ የወረዳው አስተዳዳሪ በመሆን ለኹለት ዓመታት ማገልገላቸው፤ ከዚያ በፊት በትውልድ አካባቢያቸው በዳዎ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ማገልገላቸውን ኃይሉ ገልጸዋል።

ኃይሉ፤ ለግድያው ተጠያቂው በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው መንግሥት "ኦነግ - ሸኔ" የሚለው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ሃይል መሆኑን ጠቅሰዋል።"አዎ፣ እንደ ሕዝብ ጥቆማ እንደዛ የሚባል ነገር አለ። በተግባር ከወረዳችን ከተለያዩ ቦታዎች ሰዎች እየታገቱ ነው። የሚያግተው ይኸው አካል ነው። አንዳንድ ጠቆማዎችም አሉ፣ ታግተው የተለቀቁ ሰዎችም አሉ፡፡" ሲሉም ተናግረዋል።

መንግሥት 'ኦነግ ሸኔ' የሚለው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ስለ ውንጀላው እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም።በመንግሥት ባለስልጣናት እና በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎችን በተመለከት ግን ታጣቂ ቡድኑ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲያስተባብል ነበር።

የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ቅዳሜ ዕለት ከቤታቸው ከታገቱ ከአንድ ቀን በኋላ ታጣቂዎቹ በቀለ ቃቻ እንዲለቀቁ “10 ሚሊየን ብር” መጠየቃቸውን ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች መስማቱን ገልጿል።የወረዳው የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ፤ “ጉዳዩ ተጨማሪ ምርመራ የሚጠይቅ ቢሆንም ታጣቂዎቹ ለተወሰኑ ሰዎች በወረዳው አስተዳዳሪ ስልክ ደውለው እስከ 10 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸውን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡” ሲሉ ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ ለወረዳው አስተዳዳሪ ቀደም ብለው የሰጡት ማስጠንቀቂያ / ዛቻ አለ? ወይንም በግላቸው ደውለውላቸው የጠየቁት ገንዘብ አለ? ተብለው የተጠየቁት ኃይሉ፤ የአስተዳዳሪው ስልክ በታጣቂዎቹ እጅ ስለገባ ይሄን ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል። "ዛቻ ወይም ማስጠቀቂያ እየተነዛበት እንደሆነ ሪፖርት ቀርቦ የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ " ሲሉም አክለዋል።

ታጣቂዎቹ የወረዳውን አስተዳዳሪ ከእገታ ለማስለቀቅ የጠየቁት ገንዘብ ተሰጥቷቸው እንደሆነ ግልፅ የሆነ ነገር ባይኖርም የተገደሉት "የጠየቁት ገንዘብ ስላልተሰጠ" ነው የሚል ግምት መኖሩንም ተመላክቷል።ኃይሉ ግን "ከዚህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ነገር ግን በቀጣይ ምርመራ ይታወቃል፡፡" ሲሉ ተናግረዋል።

በኹለት ቀናት ውስጥ የጸጥታ ሃይሎች አስተዳደሪውን ለማስለቀቅ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተገልጿል።የተገደሉት አስተዳዳሪ ከ30ዎቹ - 40ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ባለትዳር እና የልጆች አባት ነበሩ።

የወረዳው ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊው ኃይሉ፤ “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ነን የሚሉ የታጠቁ ሃይሎች (መንግሥት ኦነግ - ሸኔ የሚላቸው) በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወረዳ ውስጥ ግለሰቦችን እያገቱ ብዙ ገንዘብ እየጠየቁ በማሰቃየትና በመግደል ላይ ናቸው፡፡” ሲሉ ተናግረዋል።"ፖለቲካ የማያውቁ እና ማንም ነገር ውስጥ የማይገቡ ገበሬዎችን በየቀኑ እያፈኑ፤ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እየተጠየቀ ነው።" ያሉት አቶ ኃይሉ፤ " ገንዘብ የሌለው ግለሰብ ኹለት መቶ ሺሕ ፣ ሦስት መቶ ሺሕ፣ አምስት መቶ ሺሕ ብር ዘመዶቹ እየሰበሰቡ መስጠት የተለመደ ሆኗል፡፡" ሲሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ፤ ልጆቻቸውን የማገትና በአሰቃቂ ሁኔታ የመግደል ሁኔታ መጨመሩንም አስረድተዋል።የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኃይሉ አብዶ፤ "መፍትሄው እርስ በእርስ ከመገዳደል ፤ አንድ ቋንቋ እየተናገርን ከመጨራረስ ይልቅ በውይይት መፍታት ነው፡፡" ሲሉም ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ውስጥ ኹለት ሳምንት ባለሞላ ጊዜ ውስጥ የወረዳ አስተዳዳሪ ሲገደል ይህ ለኹለተኛ ጊዜ ሺኆን፤ ሰኔ 1 ቀን በምዕራብ ሸዋ ዞን የአዳ ባርጋ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አብዲሳ ቀነኒ በበካቴ ከተማ በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ በታጣቂዎች ተገድለዋል።በተያዘው ዓመት በመጋቢት ወር ላይ የነቀምት ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ ደሳለኝ በኮንጃ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች መገደላቸውም ይታወሳል፡፡

[BBC/Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የጣሪያ እና ግድግዳ ግብርን ምክንያት በማድረግ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት እንደማይቻል ቢገለጽም አሁንም ችግሩ እንዳልተፈታ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ውይይት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር የማይቻል መሆኑን መወሰኑን ይታወሳል::

ይህንኑ እውነታ መነሻ በማድረግ በተለይ ከጣራና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ የቤት ክራይ ጭማሪ በነዋሪው ላይ እየተደረገ መሆኑን አንስቶ አሐዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የንብረት ግብር ማስተግበሪያ ጊዜያዊ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ አስማማው ሙሉጌታ አነጋግሯል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በተደረገ ክትትል ማረጋገጡን የገለጹት አቶ አስማማው ችግሩን ለማስወገድ እና በተከራዮች ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ በተለያዩ ጊዜያቶች ከተማ አስተዳደሩ ህግ እያወጣ ቁጥጥር ለማድረግ እየጣረ መሆኑን አስታውሰው በተፈጻሚነቱ ላይ ካቢኔው ጠንካራ የሆነ አቋም መያዙንም ተናግረዋል፡፡

[አሐዱ]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ኩራዝ ቴክኖሎጂስ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና የሚያዘጋጁ ኮርሶችን የያዘ አገልግሎት በዛሬው እለት በይፋ አስጀምሯል።

የኦንላንይን መማሪያዎችን የያዘዉ በኩራዝ ቴክኖሎጂ የበለፀገዉ የስልክ መተግበሪያ የተለያዩ የመማሪያ መፅሀፍትን ከእንላይን ኮርስ ጋር የያዘና ከየትኛውም ቦታ ሆኖ በቀላሉ ማግኘት የሚቻል ነው።

ኮሮሶቹን እንዲያዘጋጁ የተደረጉት  ከዚህ ቀድም የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተናን ወስደው 600 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች መሆናቸውን የኩራዝ ቴክኖሎጂስ መስራች እና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ብስራት ሀይሉ ተናግረዋል።

አገልግሎቱን በስልክ እና ከዌብሳይቶች ላይ ማግኘት እንደሚቻል የገለፁት አቶ ብስራት ክፍያውንም በቴሌ ብር መፈጸም እንደሚቻል ገልፀዋል።ፕላትፎርሙን ለመጠቀም ለአንድ ኮርስ 150 ብር ክፍያን ይጠይቃል ተብሏል።

ይህንን ክፍያ በዲጂታል በማንኛዉም የዲጅታል መክፈያ አማራጭ መፈፀም እንደሚቻልም ተገልጿል።አዲሱ አገልግሎት "ኩራዝቴክ" ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲዘጋጁበት ከማስቻሉም ባሻገር ደራሲያን መጻህፎቻቸውን ለአንባቢያን በቀላሉ ተደራሽ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል ተብሏል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ ኢትዮጵያ ዘንድሮ ሕዳሴ ግድብን ለአራተኛ ጊዜ በውሃ ለመሙላት ዝግጅት ላይ መኾኗን ዛሬ በድንበር ዘለል ወንዞች አጠቃቀም ዙሪያ ዛሬ በአዲስ አበባ በመከረው የቀጠናው ከፍተኛ የሚንስትሮች ስብሰባ ላይ መናገራቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

ደመቀ፣ “ሕዳሴ ግድብ የአገራት የጋራ ሃብት የኾነውን ወንዝ ለብቻቸው መጠቀም የሚፈልጉ ኃይሎችን አሉታዊ ትርክት በመቋቋም፣ ወደ መጠናቀቂያው ምዕራፍ እየተቃረበ" መኾኑን ገልጸዋል ተብሏል። ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በበኩሉ፣ ደመቀ "ሕዳሴ ግድብ የፍትሃዊና ምክንያታዊ ውሃ አጠቃቀም ተምሳሌት ነው" በማለት መናገራቸውን በትዊተር ገጹ ገልጧል። በስብሰባው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ፣ ኡጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ተገኝተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
1
የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ

መሥፈርቶች

የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች

የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar

Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር


Contact Us:

@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58

☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇

🤳ስልክ  ቁጥራችን 9445



Website
www.sabinaadvisors.com
    👇👇  ለበለጠ መረጃ 👇👇👇

👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ  7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር  702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://tttttt.me/sabinaadvisor

https://www.facebook.com/sabinaadvisor
👍2
#ADVERTISEMENT

👉ምርጥ የ ኮንስትራክሽን ቻናል ጥቆማ

📜የ ግንባታ ጨረታዎች እና የ ስራ ቅጥር ማስታወቂያ ምታገኙበት
📄እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ሌክቸር ትምህርቶች ሚሰጥበት🗒
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ በቀላሉ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይኖች🏠

💻ኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን📀
📙 ኮንስትራክሽን መፅሃፍቶች📚
🎬የ ኮንስትራክሽን ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል

💫እመኑኝ ታተርፉበታላቹ

ቻናልችን ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ

https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
ኢትዮጵያዊ መጻሕፍትን በኢቡክ እና በትረካ ለማግኘት ቱባ መተግበሪያን ያውርዱ!

የሚወዷቸውን መጻሕፍት በተመጣጣኝ ዋጋ ቱባ ላይ ያንብቡ!

Download Tuba: https://tuba.et

@tuba_books    @tuba_books
#የቻናል_ጥቆማ❗️

🏗በ እትዮጵያ ብቸኛ ቡዙ ተከታዮችን  ማፍራት የቻለው የconstruction ዘርፍ መረጃዎችን ትምህርቶችን ምታገኙበት channel 👇

https://tttttt.me/ethioengineers1

~ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣ የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች  እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሌክቸር የምታገኙበት👇

https://tttttt.me/ethioengineers1

~ የኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭና ገዢ የሚገናኙበት ምርጥ ቻናል ለማገኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን👇

©️Telegram 👇

https://tttttt.me/ethioengineers1
በሲዳማ ክልል በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የተጠረጠሩ ፖሊሶች ተባረሩ!

“የዜጎችን ሕጋዊ እና ሰብዓዊ መብቶች ጥሰዋል”፤ ያላቸውን 157 የፖሊስ አባላት እና አዛዦች፣ ከሥራ ማሰናበቱን፣ የሲዳማ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።

ከተባረሩት መካከል 27ቱ፣ በሕግ እንደሚጠየቁና ሌሎች 305 አባላት ደግሞ፣ ከባድ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው፣ የቢሮው ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

ከሥራ መባረራቸው የተገለጸው የፖሊስ አባላት፣ ከሳጂን እስከ ኢንስፔክተር እና የወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ ደረጃ ድረስ የሚገኙ ሲኾኑ፤ ምርመራው የተደረገባቸውም፣ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ እንደኾነ፣ የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሓላፊ አስታውቀዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
የስምንት ዓመት ሕጻን መደፈሯን ተከትሎ በደላንታ ወረዳ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ!

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በአንዲት የስምንት ዓመት ሕጻን ልጅ መደፈሯን ተከትሎ በትናንትናው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉ ተሰምቷል።ሕጿኗ የተደፈረችው ረቡዕ ሰኔ 14/ 2015 ማታ 11 ሰዓት አካባቢ ሲሆን፤ የሰልፉ መነሻ ሕጻኗን “የመከላከያ ሰራዊት አባል ነው የደፈራት” በሚል ምክንያት መሆኑን አዲስ ማለዳ ከአካባቢው ነዋሪዎችና ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘችው መረጃ ያመለክታል፡፡

ማኅበረሰቡ ሰልፍ ወጣው የሕጻኗን መደፈር ምክንያት አደርጎ ቢሆንም፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ረቡዕ ዕለት ከ11 ሰዓት ጀምሮ ራሱን “ፋኖ” ብሎ በሚጠራው ተጣቂ ኃይል እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

መከላከያ በደላንታ ወረዳ ዙሪያ ጊዜያዊ ካምፕ እንዳለው የጠቆሙት ነዋሪዎቹ፤ ከታጣቂ ኃይሉ ጋር የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ተከትሎ በአካባቢው የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት አካባቢውን ለቆ መውጣቱን ጠቁመዋል፡፡በጉዳዩ ላይ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የደላንታ ወረዳ የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ መዝገበ ፈንታው፤ የመከላከያ አባካቱ ረቡዕ ሰኔ 14/2015 አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

የሰላማዊ ሰልፉ ዋና አላማ “በመከላከያ ሰራዊት አባል ተደፍራለች የተባለችውን ሕጻን ፍትህ እንዲሰጣትና የመከላከያ ሰራዊት ከከተማዋ ይውጣ የሙል አቋም የተንጸባረቀበት እንደሆነ መዝገበ አብራርተዋል፡፡ተድፍራለች የተባለችው የስምንት ዓመት ሕጻን በከተማው ጤና ጣቢያ በሕክምና ላይ መሆኗን የጠቆሙት መዝገበ፤ "በተኩስ ልውውጡ እና በሰላማዊ ሰልፉ የተጎዳ አካል መኖሩን ማረጋጋጥ አልቻልንም" ብለዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube@FikerAssefa
ዘምዘም ባንክ ለዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ግንባታ የሚጠቀምበትን ቦታ መረከቡን አስታወቀ!

በኢትዮጽያ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በመጀመር ፈር ቀዳጅ የሆነው ዘምዘም ባንክ፤ ለዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ግንባታ የሚውል ቦታ በልደታ ክፍለ ከተማ (ሰንጋ ተራ አካባቢ) መረከቡን አስታውቋል።

ባንኩ ይህን ያስታወቀው በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲስ ሆቴል ባዘጋጀው መድረክ ላይ ሲሆን፤ በመድረኩም የልደታ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ተወካይ ጽ/ቤት ኃላፊ ነጂባ አብደላ፣ የዘምዘም ባንክ ቦርድ ዳይሬክተር ሰብሳቢ ዶ/ር ናስር ዲኖ፣ የዘምዘም ባንክ የቦርድ ዳይሬክተር አባላት፣ የባንኩ የሸሪዓ መማክርት አባላት እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተውበታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ተፋላሚዎች ለኢድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል መዳረሻ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበላቸው፡፡

ጥሪው ያቀረበው የእስልምና ትብብር ድርጅት /OIC/ እንደሆነ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡

የሱዳን መንግስት ጦር እና በምህፃሩ RSF የተሰኘው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ከ2 ወራት በላይ በውጊያ ላይ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡

ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ የተኩስ አቁም ለማድረግ ቢስማሙም በአብዛኛው የተኩስ አቁማቸው ተከባሪ አልነበረም፡፡

ለተኩስ አቁሞቹ መጣስ ተፋላሚዎቹ በአንተ ነህ ፤ አንተ ነህ መካሰሱን ልማዳቸው እንዳደረጉት ይነገራል፡፡

🖋Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎችን “ከቤት ግብር ነጻ ለማድረግ ጥናት እያደረግሁ ነው” አለ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ከቤት ግብር ነጻ እንዲሆኑ አሊያም መጠነኛ ክፍያ እንዲከፍሉ ለማድረግ ጥናት እያደረገ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ። የከተማ አስተዳደሩ ከቤት ግብር እስካሁን ድረስ 600 ሚሊዮን ብር ገደማ ገቢ መሰብሰቡን ከንቲባዋ ገልጸዋል።

አዳነች አቤቤ ይህንን ያስታወቁት ለብሔራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ነው። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ትላንት ሐሙስ ሰኔ 15፤ 2015 ምሽት የተላለፈው የከንቲባዋ ቃለ ምልልስ ዋነኛ ትኩረቱን ያደረገው፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ የተመን ማሻሻያ ባደረገበት የቤት ግብር አፈጻጸም ላይ ነው። የከተማ አስተዳደሩ ይህን ማሻሻያ ማድረጉን ተከትሎ፤ የመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ጭማሪ መታየቱ እና አዲሱ ተመን “በነዋሪዎች ላይ ኢኮኖሚያዊ ጫና ያመጣል” መባሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መነጋገሪያ ሆኖ ከርሟል።

የከተማይቱ ከንቲባ የግብር ተመን ማሻሻያው በራሱ የኑሮ ውድነትን ያባብሳል ብሎ ለማመን እንደሚያስቸግራቸው ገልጸዋል። “እንዴት ነው የአዲስ አበባን ህዝብ እቺን ግብር በማሻሻል የኑሮ ውድነትን ጫና የምናመጣበት? አንደኛ ዝቅተኛ ገቢ ያለው ላይ አይደለም ይሄ ሁኔታ እየታየ ያለው። የተሻለ ገቢ ያለው ነው የግብር አከፋፈሉን እየተቃወመው ያለው። ሚዲያም የመክፈል አቅም ያለው እርሱ ነው” ሲሉ “በርካታ የማህበረሰብ ክፍል” የግብር ተመኑ ላይ ተቃውሞ እንደሌለው ተናግረዋል።

ሙሉ ዘገባው: https://ethiopiainsider.com/2023/11260/

@YeneTube @FikerAssefa
"በኢንተርኔት ላይ የተጣለው ዕቀባ መንግስትን እንጂ እኔን አይመለከትም" -ኢትዮ-ቴሌኮም

የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ "በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የተጣለው ዕቀባ መንግስትን እንጂ" እርሳቸው የሚመሩት ተቋምን እንደማይመለከት ተናግረዋል፡፡ፍሬሕይወት ይህን የተናገሩት የተቋማቸውን የዘጠኝ ወራት የሥራ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡

የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀማቸውን ያቀረቡት ስራ አስፈፃሚዋ ተቋሙ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግና የተጠቃሚን ቁጥር ለመጨመር በተለያዩ የኔት ወርክ ደረጃዎች ወደ ሕዝቡ ለመድረስ መስራቱን አመልክቷል፡፡

በዚህም ከ84 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ማፍራት መቻሉን ገልፀዋል፡፡ የመንግስትና የንግድ ተቋማት የክፍያ ስርዓታቸውን በቴሌ ብር እንዲፈፅሙ በማድረግ 30.5 ሚሊየን ብር በላይ የቴሌ ብር ተጠቃሚዎችን ማፍራት እንደቻሉ የጠቀሱት ፍሬሕይወት በዚህም 394.7 ቢሊየን ብር በላይ በቴሌ ብር ግብይት መፈፀሙን ስራ ተናግረዋል፡፡

ከስራ አስፈፃሚዋ ሪፖርት በኋላም ከቋሚ አባላቱ በኩል የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ‹ ጦርነት በነበረባቸው አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረውን የቴሌኮም አገልግሎት መልሶ ለማስጀመር ምን እየተሰራ ነው› ፤ " ገደብ የተጣለበት ኢንተርኔት ተቋሙ ለሚያካሄደው ስራዎች እንቅፋት እየሆነ ነው ይህን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው" የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ኢትዮ-ቴሌኮም በጦርነት በነበረባቸው አካባቢዎች የተቋረጠውን የቴሌኮም አገልግሎት መልሶ ለመገንባት ተቋሙ ጥረት እያደረገ መሆኑ የጠቀሱት ስራ አስፈፃሚዋ የተወሰኑ ቦታዎች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልፀዋል፡፡በቴሌኮም መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችንና ስርቆቶችን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑን ሀላፊዋ ጠቅሰዋል፡፡

"በኢንተርኔት ላይ የተጣለው ገደብ ተቋሙን የሚመለከት ሳይሆን በመንግስት አካል የተጣለ ገደብ ስለሆነ ከሚመለከተው አካል በሚሰጥ ፍቃድ የሚነሳ መሆኑን" ስራ አስፈፃሚዋ አብራርተዋል፡፡የትኛው የመንግስት አካል እንደሆነ ግን ከመግለፅ ተቆጥበዋል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
ኦነግ 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ሊያከብር ነዉ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ለኦሮሚያ የሰላም ችግር መፍትሄው ሰላማዊ ውይይት ነው አሉ፡፡ አቶ ዳውድ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መንግስት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ለዉይይት መቀመጥ አለበት ብለዋል።አቶ ዳውድ፤ ከአንድ ሳምንት በኋላ መከበር የሚጀምረውን የኦነግ 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን በማስመልከት ለመገናኛ ብዙሃንን ጠርተው መግለጫ ሲሰጡ፤ ከአምስት ዓመታት በፊት በፓርቲያቸውና በመንግስት መካከል የተፈረመው ስምምነት “መጣሱ” ላለፉት አምስት ዓመታት በኦሮሚያ ለታየው አለመረጋጋት ዋናው ምክኒያት ነው ብለዋል፡፡

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ሊፍት የሚሰጡ መስለው ዝርፊያ የፈፀሙ ሁለት ወንጀል ፈፃሚዎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ!

ወ/ሮ በላይነሽ ሸዋዓለም የተባሉ ግለሰብ ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 7 ሰዓት ከ 50 ላይ ከጦር ኃይሎች ወደ አየር ጤና ትንስፖርት በመጠበቅ ላይ እንዳሉ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 02402 ቶዮታ መኪና እቆሙበት ስፍራ መድረሱን ተከትሎ ከግል ተበዳይ ጋር ትራንስፖርት የሚጠብቅ መስሎ የቆመው ግለሰብ ተሽከርካሪውን ሊፍት ጠይቆ በማስቆም የግል ተበዳይም እንዲገቡ ያደርጋል፡፡

ትንሽ እንደተጓዙ አጉስታ ከሚባለው ስፍራ ሲደርሱ ሊፍት የጠየቀው ግለሰብ ወርቅ ጠፋኝ በማለት ከሹፌሩ ጋር በመተባበር ግለሰቧን በማደናገር እና በማስጨነቅ 5 ግራም ባለ 21 ካራንት የጣት ቀለበት እና 9ሺ ብር ይዘርፋሉ፡፡

በስራ ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላት እና በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ግለሰቧ ያሰሙትን የድርሱልኝ ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ተጠርጣሪዎቹን እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቋል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎች ልዩ ልዩ ስልቶች በመጠቀም ወንጀል እንደሚፈፅሙ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ፖሊስ መልዕክቱን እያስተላለፈ እነዚህን ወንጀል ፈፃሚዎች በመያዝ ትብብር ላደረጉ የአካባቢው ሰዎች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ምንጭ ፡- አ.አ ፖሊስ
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የጀርመን ምክር ቤት በተለያዩ ሙያ የሰለጠኑ ከአዉሮጳ ህብረት ሃገራት ዉጭ የሆኑ ሰራተኞች ወደ ጀርመን እንዲገቡ የሚፈቅደዉን አዲስ ደንብ ዛሬ አፀደቀ።

አዲሱ ደንብ ባለሙያዎች፣ የጀርመንኛና የእንግሊዝኛ ቋንቋ እስከቻሉ ድረስ ያለ ብዙ ዉጣ ዉረድ ወደ ጀርመን እንዲገቡና ጀርመን ዉስጥ እንዲሰሩ የሚፈቅድ ነዉ። ይህ ደንብ በጀርመን ለሚገኙ በርካታ ስደተኞች እድል የሚሰጥ ነዉ። በካናዳ ደንብና አሰራር መሠረት የተቀረፀ እንደሆነ የሚነገረዉ ደንብ በተለይ እንደ መስተንግዶ፣ ጤና፣ ግንባታና ቴክኖሎጂን በመሳሰሉ መስኮች ጀርመን ያለባትን የባለሙያ እጥረት ለማቃለል ይረዳል ተብሏል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa