YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በጎፋ ዞን ከታራሚዎች ማምለጥ ጋር በተያያዘ በ18 የፖሊስ አባላት ላይ ውሳኔ ተላለፈ

በጎፋ ዞን በነፍስ ግድያ ፣ አስገድዶ መድፈር ፣ ወንብድና እንዲሁም ዝርፊያ ወንጀል ተከሶ በተላለፈበት ውሳኔ በሣውላ ማረሚያ ተቋም የሕግ ታራሚ የሆነን ኤልያስ ማናዬ ማራ እና ሌሎች ታራሚዎች ከማረሚያ ቤት ማምለጥ ጋር በተያያዘ 18 የፖሊስ አባላት በወንጀል ተከሰው በህግ እንዲጠየቁ መደረጉ ተነግሯል ።የሕግ ታራሚ ኤልያስ ማናዬ  ግብረአበሮቹ ተብለው ተከሰው ውሳኔ የተላለፈባቸውን ጨምሮ 8 የሚሆኑ የሕግ ታራሚዎችን በማስተባበር ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ በሣውላ ከተማ የጣለውን ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በማድረግ በር ሰብረው የማምለጥ ሙከራ ማድረጋቸውን እና በዕለቱ በተደረገው ክትትል 7 የሕግ ታራሚዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ኤልያስ ማናዬ ማምለጡን ተነግሯል ።

የሣውላ ማረሚያ ተቋም ፣ የጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያና የዛላ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት የወንጀል ምርመራና ክትትልና ቡድን ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ርብርብ ከ5 ቀናት ፍለጋ በኋላ የሕግ ታራሚ ኤልያስ ማናዬን በሕይወት ለመያዝ ከፍተኛ ጥረትና ሙከራ መደረጉን የሣውላ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አሸብር ሲንሳ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ። ነገር ግን የፖሊስ አባላት የሕግ ታራሚውን በሠላማዊ መንገድ ለመያዝ ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካና ታራሚው እጅ ከመስጠት ይልቅ በሁለት እጁ ጦርና ገጀራ በመያዝ በአንድ የፖሊስ አባል ላይ ጦር በመወርወር ለመግደል ሙከራ በማድረጉ የፖሊስ አባሉ ሕይወቱን ለማዳን ሲል በወሰደው እርምጃ በጥይት እግሩ ተመትቶ ወደ ሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል ቢገባም በደም መፍሰስ ምክንያት ሕይወቱ አልፏል።

ውሳኔ የተላለፈባቸው የፖሊስ አባላት ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰኔ 7 ቀን 2015 ዓ.ም የሕግ ታራሚው በሕግ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ጥቂት የተቋሙ ፖሊስ አባላት ወደ ሣውላ ከተማ በሚገቡበት ወቅት ያለተቋሙ እውቅና ጥይት ያለአግባብ በመተኮስ የሕዝቡን ሠላምና ደህነት በማናጋት ከፖሊስ አባል የማይጠበቅ የስነ-ምግባር ጥሰት ፈፅመዋል። ስለሆነም ከታራሚዎች ማምለጥ ጋር በተያያዘ እና ያመለጠ ታራሚ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በተፈፀመ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት የፖሊስ አባላቱ በወንጀል ተከሰው በህግ እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፏል ። በዚህ መሰረት ሁለት የፖሊስ አባላት ከታራሚዎች ማምለጥ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ ከስራ እንድሰናበቱ ተወስኗል ። ሦስት የፖሊስ አባላት በበኩላቸው የህግ ታራሚን በእንዝላልነት እንድያመልጥ በማድረግ ወንጀል ተከሰው በህግ እንዲጠየቁ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል ።ሌሎች 13 የፖሊስ አባላት  ያለአግባብ ከትዕዛዝ ውጭ ጥይት ከተማ ውስጥ በመተኮስ የህዝቡን ሰላም ያናጉ በመሆናቸው በከባድ ዲስፒልን ተከሰው እንዲቀጡ እና የተኮሱትን የጥይት ዋጋ እንዲከፍሉ ውሳኔ መተላለፉን ዋና ኢንስፔክተር አሸብር ጨምረው ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

[ዳጉ ጆርናል]
@Yenetube @Fikerassefa
👍1
በትግራይ ክልል በጦርነት ለተጎዱ ባለሀብቶች የዕዳ ስረዛ እንዲደረግ ተጠየቀ!

መነሻውን በትግራይ ክልል ያደረገው፣ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ ከፍተኛ ጉዳት ላደረሰባቸው የትግራይ ክልል ባለሀብቶች፥ ዕዳ እንዲሰረዝ፣ የክልሉ የንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ፕሬዚዳንት ጥሪ አቀረቡ።ፕሬዚዳንቱ ጥሪውን ያቀረቡት፣ ክልሉ፣ በጦርነቱ ምክንያት የደረሰበትን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት በሚል፣ በመቐለ ከተማ በተዘጋጀ ውይይት ላይ ነው። የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነርም፣ ለባለሀብቶች ድጋፍ ሊደረግ እንደሚገባ፣ በውይይቱ ወቅት አሳስበዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
ቅዴፓ "የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ ከ1 ሺህ 500 በላይ የቅማንት ብሔረሰብ ተወላጆች ህይወት አልፏል"  አለ።

የቅማንት ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ(ቅዴፓ) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ፓርቲው በመግለጫው በተለይም ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ  በብሔረሰቡ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ባለው ግድያና እስር ከ1 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ 334 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ንብረት  ወድሟል ብሏል።

አሁንም ድረስ በማረሚያ ቤቶች ያለ ፍርድ እየተሰቃዩ የሚገኙ የብሄረሰቡ ተወላጆች መኖራቸውም አመልክቷል።

ጥያቄያችን ብሔረሰቡ የሚኖርበትን ቦታ የብሔሩ ተወላጆች ያስተዳድሩት፤ ቋንቋውም ይደግ ነው ነገር ግን በክልሉ መንግስት የሚሰጠው ምላሽ ተገቢ አለመሆኑን የፓርቲው አመራሮች አንስተዋል።

እኛ የማንም ተላላኪ አይደለንም ያለው ፓርቲው ጥያቄያችን ህገመንግስታዊ ነው ሲሉም አክለዋል።

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞዋ አፈጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም መረጃ በማጥፋታቸው የራያ አላማጣ የማንነት ጥያቄ እንዲጓተት ምክንያት ሆኗል ተባለ

የራያ አላማጣ ማህበረሰብ የማንነት ጥያቄ እልባት እንዲሰጠው በሚል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የላከው ደብዳቤ በቀድሞ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም አማካኝነት እንዲጠፋ ተደርጓል ተብሏል።

የአላማጣ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሞገስ እያሱ፤ የራያ አላማጣ የማንነት እና የበጀት ጥያቄ ከ2011 ጀምሮ ለፌደሬሽን ምክርቤት ሲቀርብ እንደነበር ገልጸው፤ “የወቅቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ኬሪያ ኢብራሂም የማንነት ጥያቄውን ለማዳፈን በማሰብ ለምክር ቤቱ የገባው መረጃ እንዲጠፋ አድርገዋል፡፡” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

በዚህም ለምክር ቤቱ የገባው መረጃ እንዲጠፋ መደረጉ፤ የራያ አላማጣ ማህበረሰብ የማንነት ጥያቄ መፍትሄ ሳያገኝ ለአራት ዓመታት እንዲጓተት ምክንያት ሆኗል ነው ያሉት።

“አፈጉባኤዋ ስልጣን ከለቀቁ በኋላ በገባው ደብዳቤ መሰረት የማንነት ጥያቄው መልስ እንዲያገኝ የፌዴሬሽን ምክር ቤቱን ስንጠይቅ፤ መረጃው መጥፋቱ ስለተነገረን ቅጂውን በድጋሜ ለማስገባት ተገደናል፡፡” ሲሉ ጠቁመዋል።

ባሳለፍነው ሰኞ ሰኔ 12/2015 የራያ አላማጣ እና ባላ አካባቢዎች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ከ150 ሺሕ በላይ የሕዝብ ፊርማ ተሰብስቦ ለፌደሬሽን ምክር ቤት መግባቱን የጠቀሱት ኃላፊው፤ “ዋና ዓላማውም የማንነት ጥያቄያችን ተፈቶ ወደ አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን እንድንካተትና በጀቱ በትግራይ ክልል ሳይሆን በአማራ ክልል በኩል እንዲለቀቅልን ነው፡፡” ብለዋል።

አክለውም፤ በተለይ የፌደራል ተቋማት በአካባቢው የተሟላ አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆኑ፣ ከባንክ፣ ከኤሌክትሪክና ከኢንተርኔት ጋር ያለው አገልግሎት በቶሎ ምላሽ ሊስጠው እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ለዚህም አራት ዓመታትን ያስቆጠረው የራያ አላማጣ የማንነት እና የበጀት ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ኮሚቴ ተቋቁሞ፤ ሰኞ ሰኔ 12/2015 ለፌድሬሽን ምክር ቤት መግባቱ ነው የተገለጸው።

ሕወሓት ለራያ እና አላማጣ አካባቢዎች አመራር መድቧል በሚል የሚነሳውን ጉዳይ በተመለከተም መድቧል ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ አምስት አመራሮችን የቀያየረ መሆኑን ጠቁመው፤ “ወደ ራያ እና አላማጣ ግን ሊመጡ አይችሉም፡፡” ሲሉ ተናግረዋል።

ራያ አላማጣ ለኹለት ዓመታት ያለ በጀት መቆየቱን የገለጹት ኃላፊው፤ የማንነት ጥያቄው እና ለኹለት ዓመት የተቋረጠው በጀት በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠው ህዝቡ በተደጋጋሚ በመጠየቅ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ላይ ከፌደሬሽን ምክር ቤት ፅሕፈት ቤት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ጥረት ብታደርግም ሳይሳካ ቀርቷል።

በተያያዘም፤ በዛሬው ዕለት የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ''መንግሥት የማንነት ጥያቄቸውን ሕጋዊ እንዲያደርግላቸው'' በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁ ሲሆን፤ ነዋሪዎቹ በሰላማዊ ሰልፉ “አማራ ነን እንጂ አማራ እንሁን አላልንም”፣ “የፌደራል መንግሥት ተቋማት ዲስትሪክት ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ይዛወሩልን”ና ሌሎች የተለያዩ መፈክሮችን ማሰማታቸውን የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዋር ሱሳ ከሰኔ 21 ቀን 2023 ጀምሮ  ከስራ አስፈፃሚነታቸው ተነሱ።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ሁለት ትምህርትት ቤቶች በቀጣይ ዓመት በሚያደርጉት የክፍያ ጭማሪ ላይ ከወላጆች ጋር መግባባት ባለመቻላቸዉ  ምዝገባ እንዳያከናዉኑ ታገዱ!

በአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ቅዱስ ሚካኤል ት/ቤቶች እና ብራስ ዩዝ አካዳሚ የተሰኘ ትምህርት ቤቶች በቀጣይ ዓመት የተማሪዎች ምዝገባ እንዳያከናውኑ ማገዱን አስታዉቋል።ባለስልጣኑ ፤ ማንኛዉም ት/ት ቤት በቀጣይ አመት ለሚያደርገዉ የወርሃዊ ክፍያ ጭማሪ ከተማሪ ወላጆች ጋር ከስምምነት ደርሶ መሆን አለበት ቢልም ፤ ት/ት ቤቶቹ እና ወላጆች ከፍ በሚደረገዉ የክፍያ መጠን ላይ መስማማት አልቻሉም።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ ለብስራት ራዲዮ እንደተናገሩት ፤ ብራስ ዩዝ አካዳሚ ለቀጣዩ የ 2016 አመት የ 40 በመቶ ጭማሪ ለማድረግ ቢያቅድም ከወላጆች ጋር በተደረገው ዉይይት ተቀባይነት አላገኘም። በአንጻሩ ወላጆች ለቅድመ መደበኛ የ 25 በመቶ እና ለመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች የ 30 በመቶ ለሚደረግባቸዉ ጭማሪ እሺታቸዉን ሰጥተዉ ነበር።

ሆኖም ትምህርት ቤቱ በወላጆች በኩል የቀረበዉን ሀሳብ ዉድቅ አድርጎታል። በዚህም መሰረት የአዲስአበባ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ሁለቱን አካላት ለማስማማት ጥረት አድርጎ ነበር። በዚህም የ 30 በመቶ የጭማሪ ሀሳብ በባለስልጣኑ ቀርቦ ወላጆችም ከስምምነት ደርሰዉ የነበረ ቢሆንም ትምህርት ቤቱ ሳይቀበለዉ ቀርቷል።

በተመሳሳይ ቅዱስ ሚካኤል ትምህርት ቤቶች በቀጣዩ ዓመት ከ100 እጥፍ በላይ ጭማሪ ለማድረግ ቢያቅድም ከወላጆች ጋር በተደረገዉ ዉይይት 80 በመቶ ጭማሪ ለማድረግ ወስኗል። ሆኖም ወላጆች ከ 50 በመቶ በላይ ጭማሪ ለማድረግ ፈቃደኞች አልሆኑም። ባለስልጣኑ ሁለቱን አካላት በ 60 በመቶ ጭማሪ ለማስማማት ቢሞክርም በተመሳሳይ ትምህትት ቤቱ ዉድቅ አድርጎታል።

በዚህም መሰረት ባለስልጣኑ በወላጆችና በት/ት ቤቶቹ መካከል ስምምነት አለመደረሱን ተከትሎ ሁለቱም ት/ት ቤቶች ለሚቀጥለዉ አመት የተማሪዎች ምዝገባ እንዳያከናዉኑ ጊዜያዊ እግድ የተጣለባቸው መሆኑን ገልጸዋል።በዚህ ሳምንት ሁለቱም ት/ት ቤቶች ምላሻቸዉን ያሳዉቃሉ ብለዉ እንደሚጠብቁ የተናገሩት ወ/ሮ ፍቅርተ ፤ ከወላጆች ጋር ከስምምነት ይደርሳሉ ብለዉ ተስፋ እንደሚያደርጉ ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ሕገ-ወጥ የማዕድን አምራቾችን ስርዓት ለማስያዝ የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል - አቶ አሻድሊ ሀሰን

መንግስት ሕገ-ወጥ የማዕድን አዘዋዋሪዎችን እና አምራቾችን ስርዓት ለማስያዝ የጀመረውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማዕድን ቁጥጥር ኮማንድ ፖስት ባለፉት ሶስት ወራት የተከናወኑ ሥራዎችን በዘርፉ የተሠማሩ ባለሃብቶች በተገኙበት ገምግሟል፡፡

በመድረኩ አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ በመከላከያ ሠራዊት የ404ኛ ኮር አዛዥ ጄነራል ሰይፈ አንጌን ጨምሮ የጸጥታ እና የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ርዕሰ-መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን÷ በማዕድን ዘርፉ ላይ የሚስተዋለው ህገ-ወጥ ተግባር ሀገርን ወደ ኢኮኖሚ ስብራት ለማስገባት ያለመ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የግብርና ሚኒስቴር የአትክልት ማሳዎች ወደ ስንዴ ማሳነት ተቀይረዋል የሚለውን መረጃ ሀሰት ነው ሲል አስተባበለ፡፡

ከሰሞኑ ከሽንኩርትና ቲማቲም ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ አትክልት ነጋዴዎች የዋጋ ንረቱ የተከሰተዉ ማሳዎቹ ስንዴ እንዲመረትባቸዉ መደረጉ ነዉ ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ይህንን ተከትሎ በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት መሪ ሃላፊ ደረጄ አበበ ለአሻም በሰጧት ምላሽ መረጃው ሀሰት ነው፤ የህገወጥ ደላሎች ሴራ ነዉ ሲሉ ጉዳዩን አስተባብለዋል፡፡

አሻም በአዲስ አበባ ከተማ የቄራ አትክልት ተራ አክሲዮን ማህበር የቦርድ አባልን አነጋግራ በሰራችዉ ዘገባ የሽንኩርትና ቲማቲም ዋጋ አልቀመስ ለማለቱ የአትክልት ማሳዎቹ መንግስት በያዘዉ አቅጣጫ ማሳዎቹ ስንዴ እንዲመረትባቸዉ በመደረጉ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክንያት ማህበሩ ሽንኩርት ከመቀሌ፣ከሱዳንና ከጅጅጋ እያስመጣ እንደሚገኝ ለአሻም መጥቀሳቸው አይዘነጋም፡፡በሽንኩርትና ቲማቲም ምርት የሚታወቁት ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙት የኦሮሚያ አካባቢዎች አርሶአደሮቻቸዉ በስንዴ ምርት ላይ እንዲጠመዱ መደረጉ ለአትክልት እጥረትና ዋጋ ንረቱ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት ሃላፊው ደረጄ አበበ የስንዴ ምርትም ሆነ የአትክልት ምርቶች ሁለቱም የኛው ናቸዉ ይላሉ፡፡ ‹ የሽንኩርትና የቲማቲም ማሳዎች ወደ ስንዴ ምርትነት ገቡ › ፤ ‹ ሽንኩርት ከመቀሌ እያስመጣን ነው › ሲሉ የሚያስወሩት የሕገወጥ ደላሎች ስራ እንጂ እውነተኛ መረጃ አይደለም ሲሉ አጣጥለውታል፡፡የአትክልት አምራች አካባቢዎች ወደ ስንዴ ምርትነት እንዲቀየሩ ተደርጓዋል መባሉም ትክክኛ መረጃ አለመሆኑን ጠቅሰው አስተባብለዋል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
አል ሸባብ በኢትዮጵያና ሶማሊያ ወታደሮች የጦር ግቢ ላይ ጥቃት ፈጸመ!

አል ሻባብ በሶማሊያ የሚገኝ አንድ ወታደራዊ ሰፈርን ዛሬ ማጥቃቱን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።ሁለት የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ፍንዳታዎች የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ወታደሮች በሚገኙበትና ባርዴር በተሰኘችው ደቡባዊ ከተማ ባለ ወታደራዊ ሰፈር መፈጸሙን ምንጮች ተናግረዋል።ወዲያውም የከባድ መሣሪያ ተኩስ ተሰምቷል።

ጥቃቱ የተከሰተው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ወታደሮችን መቀነስ መጀመሩን ባስታወቀበት ወቅት ነው።አል ሻባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን በወሰደበት ጥቃት ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ ወዲያውኑ ማወቅ እንዳልተቻለ ዘገባው አመልክቷል።

የመጀመሪያው ፍንዳታ የኢትዮጵያ ወታደሮች፣ የሶማሊያ ወታደሮችን በሚያሰለጥኑበት ግቢ መግቢያ በር ላይ እንደነበር የአካባቢው የፖሊስ አባል የሆነው አብዲ ባሬ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግሯል።ሁለተኛውም ፍንዳታ ከ5 ደቂቃ ቆይታ በኋላ እንደተስማና ተጎጂዎችም ሊኖሩ እንደሚችሉ፣ ነገር ግን ዝርዝር መረጃ እንደሌለ የፖሊስ አባሉ ጨምሮ ገልጿል። ከመጀመሪያው ፍንዳታ በኋላ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እንደነበር ጨምሮ ተናግሯል።

ጥቃቱን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት እስከአሁን ያለው ነገር የለም።ባለፈው ወር የአልሸባብ ተዋጊዎች የአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ልዑክ ላይ ባደረሱት ጥቃት 54 የኡጋንዳ ወታደሮች መሞታቸው ይታወሳል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
አየር መንገዱን በተመለከተ የሚናፈው የፈጠራ ዜና ከዕውነታ የራቀ እና መሠረተ-ቢስ ነው ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ!

“የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት (ካርጎ እና ሎጂስቲክስ) ክፍል ወደሌላ ሀገር በሽያጭ ሊተላለፍ ወይም ለብድር መያዣነት ሊውል ነው” በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው የፈጠራ ዜና ከዕውነታ የራቀ እና መሠረተ-ቢስ ነው ሲል አየር መንገዱ አስታወቀ።

አየር መንገዱ ጉዳዩን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ “ድርጅታችን በጥቂት የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ላይ እየተናፈሰ ያለውን ‘የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት (ካርጎ እና ሎጂስቲክስ) ክፍል ወደሌላ ሀገር በሽያጭ ሊተላለፍ ወይም ለብድር መያዣነት ሊውል ነው’ የሚል የፈጠራ ዜና ተመልክቷል፤ ዜናው ፍጹም ከዕውነታ የራቀ እና መሠረተ-ቢስ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያረጋግጣል” ብሏል።

“ይህ ከእውነት የራቀ ወሬ የብሔራዊ አየር መንገዳችንን ስም እና ገፅታ የሚጎዳ ስለሆነ ወሬውን የሚያሰራጩ ወገኖችን ይህንን ከማድረግ እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን” ሲልም አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
👍1
የሥራ ቪዛ ቼክ ሪፐብሊክ

መሥፈርቶች

የታደሰ ፖስፖርት እድሜ ከ 19_49
ነርስ
የ ኮንስትራክሽን ስራዎች
የ ፊኒሽንግ ስራዎች
አጠቃላይ የብረታብረት ብየዳ ስራዎች

የስራ ሰአት በቀን ከ10 - 12 ሰአት
ደሞዝ ከ 1680_2000 dollar

Accommodation አለው
የፕሮሰስ ግዜ 2 - 3 ወር


Contact Us:

@Sabinavisa2
@Sabina_5757
@SabinaA58

☎️☎️☎️📞📞👇👇👇👇

🤳ስልክ  ቁጥራችን 9445



Website
www.sabinaadvisors.com
    👇👇  ለበለጠ መረጃ 👇👇👇

👉 ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 ሃያ ሁለት የአብ ሕንፃ  7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር  702
እና ታውን ስኩዬር ህንፃ 6ኛ ቢሮ ቁጥር 602

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://tttttt.me/sabinaadvisor

https://www.facebook.com/sabinaadvisor
#ADVERTISEMENT

👉ምርጥ የ ኮንስትራክሽን ቻናል ጥቆማ

📜የ ግንባታ ጨረታዎች እና የ ስራ ቅጥር ማስታወቂያ ምታገኙበት
📄እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ሌክቸር ትምህርቶች ሚሰጥበት🗒
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ በቀላሉ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይኖች🏠

💻ኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን📀
📙 ኮንስትራክሽን መፅሃፍቶች📚
🎬የ ኮንስትራክሽን ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ምርጥ ቻናል

💫እመኑኝ ታተርፉበታላቹ

ቻናልችን ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ

https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
https://tttttt.me/ETCONp
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
ኢትዮጵያዊ መጻሕፍትን በኢቡክ እና በትረካ ለማግኘት ቱባ መተግበሪያን ያውርዱ!

የሚወዷቸውን መጻሕፍት በተመጣጣኝ ዋጋ ቱባ ላይ ያንብቡ!

Download Tuba: https://tuba.et

@tuba_books    @tuba_books
#የቻናል_ጥቆማ❗️

🏗በ እትዮጵያ ብቸኛ ቡዙ ተከታዮችን  ማፍራት የቻለው የconstruction ዘርፍ መረጃዎችን ትምህርቶችን ምታገኙበት channel 👇

https://tttttt.me/ethioengineers1

~ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣ የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች  እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሌክቸር የምታገኙበት👇

https://tttttt.me/ethioengineers1

~ የኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭና ገዢ የሚገናኙበት ምርጥ ቻናል ለማገኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን👇

©️Telegram 👇

https://tttttt.me/ethioengineers1
ለአምስት የውጭ አገር ባንኮች ፈቃድ ሊሰጥ መሆኑ ተገለጸ!

አምስት የውጭ አገር ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸው ፈቃድ እንደሚሰጣቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማትን ከማጠናከር ጎን ለጎን የውጭ ባንኮችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እየሰራ መሆኑን የባንኩ የገንዘብ ተቋማት ዘርፍ ምክትል ገዥ ሠለሞን ደስታ ለኢፕድ ገልጸዋል።

‹‹ሥራውን አሁን እያጠናቀቅን ነው፡፡ አዋጁን የመከለስ ሥራውንም እያጠናቀቅን ነው:: ከለጋሾች አንዳንድ ግብዓቶችን እየጠየቅን ነው:: በወራት ዕድሜ ለህዝብ እንደራሴዎች ይቀርባል:: ስለዚህ ሥራው እየተፋጠነ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከሦስት እስከ አምስት ለሚደርሱ የውጭ ባንኮች ፈቃድ ለመስጠት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንም የገለጹት ምክትል ገዥው፤ የውጭ ባንኮች የአገር ውስጥ ባንኮችን ከገበያ እንዳያስወጧቸው የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት አቅም ግንባታ ላይ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ለዚህም የተቀመጠ አሰራር መኖሩን አመልክተዋል::

ተቋማቱ ከመደበኛ በጀታቸው ኹለት ከመቶ የሚሆነውን ለአቅም ግንባታ እንዲያውሉትና፤ ይህም ለባንኮች ከረጅም ዓመታት በፊት የተላለፈ መሆኑን በመግለጽ፤ አሁንም ድረስ በዚሁ አግባብ ክትትል እንደሚደረግ ሠለሞን ጨምረው አስረድተዋል::

@YeneTube @FikerAssefa
የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስያሜውን ወደ ቀድሞ መጠሪያው ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ሊቀይር ነው፡፡

የ98 አመቱ አንጋፋው የቀድሞ ተፈሪ መኮንን ፣የአሁኑ እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስያሜውን ወደ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ሊቀይር መሆኑን አስታውቋል።የኮሌጁ ምክትል ዲን አቶ በላይ ከፋለ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ፣ታሪካዊ ስሙን ለማስመለስ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብልዋል።

የትምህርት ቤቱ የቀድሞው ምሩቃን ኮሚቴ አዋቅረው፣ኮሌጁ በቀድሞው ስሙ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት እንዲጠራ እየጠየቁ መሆኑን አቶ በላይ ተናግረዋል።ከሁለት ዓመት በኋላ አንድ ክፍለ ዘመን የሚሞላው ይህ አንጋፋ የትምህርት ተቋም መቶኛ ዓመቱን ሲያከብር በቀድሞው ስሙ እንደሚሆን ተገልጿል።

የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት በ1917 ዓ.ም የተመሠረተና በደርግ ዘመነ መንግስት ወደ እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንደተቀየረም ምክትል ዲኑ አስታውሰዋል።አሁን ያለው ስያሜ የተቋሙን ታሪክና ቦታ የማይወክል በመሆኑ የቀድሞው ስሙ እንዲመለስለት ተጠይቋል።

ኮሌጁ አሁን ላይ 11 የትምህርት መስኮችና ከ 40 በላይ ስልጠናዎችን እየሰጠ የሚገኝ አንጋፍ ተቋም መሆኑንም አቶ በላይ ተናግረዋል።ኮሌጁ ከሁለት ዓመት በኋላ መቶኛ ዓመቱን በድምቀት ለማክበር ከወዲሁ ዝግጅት መጀመሩም ተገልጿል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ማምረት ጀመረ!

በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ወደማምረት ስራ ተሸጋገረ።ፋብሪካው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሚኒባስ፣ ሚድባስ እና የከተማ አውቶብስ ተሽከርካሪዎችን ማምረት መጀመሩን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሰጠኝ እንግዳው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።ፋብሪካው በመጀመሪያ ዙር 216 መኪኖችን ለመገጣጠም አቅዶ እየሰራ መሆኑንም ነው የገለጹት።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ስምምነት ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፈረንሳይ ፓሪስ በአዲስ የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ስምምነት ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ፈረንሳይ መግባታቸው ይታወሳል።

በጉባዔው ላይ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የሳዑዲ ዓረቢያ ልዑል አልጋወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ተገኝተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa