YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሰው ሰራሽ ፀጉር(ዊግ) በመጠቀም ራሳቸውን ቀይረው ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የዘረፉት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በኦሮሚያ  ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ  ሰው ሰራሽ ጸጉር በማድረግ በግለሰቦች መኖሪያ ቤት ውስጥ ዝርፊያ የፈፀሙ ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸውን  የሰሜን ሸዋ ዞን አቃቢ ህግ  ጽ/ቤት አቃቢ ህግ አቶ በላይ ቶልቻ  በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ግለሰቦቹ ሰው ሰራሽ ጸጉር ተጠቅመው ራሳቸወን በመቀየር በነዋሪዎች ቤት በመግባት በስለት አስፈራርተው ግማሽ ሚሊዮን ብር  መዝረፋቸው ተረጋግጧል።

ተከሳሾቹ ገረመው ደበሌ እና አሻግሬ ደስታ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ሲሆነ ከምሽቱ 2 : 30 እስከ 5 ሰዓት ድረስ ከአምስት ቤቶች 580ሺ ብር  ዘርፈው በመውሰድ ከተሰወሩ በኋላ በተመሳሳይ ድርጊት 81ሺህ  አምስት መቶ ብር ከሶስት ግለሰቦች ቤት ደግሞ ዘርፈዋል።

ሁለቱ ግለሰቦች በጸጥታ ሀይል በተወሰደው ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል። የተከሳሾቹ የክስ መዝገብ ተጣርቶ በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 25 ቀን በዋለው ችሎት እያንዳንዳቸው በ25 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ መተላለፉን አቃቢ ህግ አቶ በላይ ቶልቻ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

@Yenetube @Fikerassefa
በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ ገባ!

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ ገብቷል፡፡

ልዑካኑ ኪንግ ካሊድ አውሮፕላን ማረፊያ ሲድርስ የሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በሳዑዲ ዓረቢያ የኢፌዴሪ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ እና የኤምባሲው ሰራተኞች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት በሳዑዲ በሚካሄደው አይ ኤስ ኤስ የሽብር ቡድንን ለመዋጋት ከተቋቋመው ዓለም አቀፍ ጥምረት የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ነው ሪያድ የገቡት፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ወይዘሪት ፀጋ በላቸውን በመጥለፍ ወንጀል የተጠረጠረው የኋላ መብራቴ ፍርድ ቤት ቀረበ!

ወይዘሪት ፀጋ በላቸውን በመጥለፍ የወንጀል ድርጊት ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የኋላ መብራቴ ፍርድ ቤት መቅረቡን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።የመምሪያው ሀላፊ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለኢዜአ እንደገለጹት ተከሳሹ ትናንት ፍርድ ቤት ቀርቧል።

በተከሳሽ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ ዐቃቤ ህግ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ ማቅረቡንም ገልጸዋል።

ፍርድ ቤቱ በዐቃቤ ህግ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ የቀረበውን የጊዜ ቀጠሮ ከመረመረ በኋላ የ12 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱን ኢንስፔክተር መልካሙ ተናግረዋል።ወይዘሪት ፀጋ በላቸው ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓም ከስራ ቦታዋ ወደ ቤት ስታቀና የጠለፋ ወንጀል ተፈጽሞባት በጸጥታ አካላት ክትትል እንድትለቀቅ መደረጉ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሸገር ከተማ ዉስጥ ካሉት 800 የኹሉም እምነት ተቋማት መካከል 656 የሚሆኑት ከፕላን ዉጭ የተሠሩ መሆናቸው ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ!

መንግስት ለተለያዩ የሀይማኖት ተከታዮች የእምነት እና የመቃብር ቦታን የማመቻቸት ግዴታ አለበት ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡በውይይታቸው አቶ ሽመልስ ÷ሰሞኑን በተከሰተው አለመረጋጋት ለጠፋው የሰው ህይወትና በወደመው ንብረት ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡ለተጎጂ ቤተሰቦችም መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

የተከሰተውን አለመረጋጋት ለማርገብ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የኦሮሚያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ላደረገው ጉልህ ድርሻ ምስጋና አቅርበዋል፡፡የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እንደቀደመው ሁሉ ችግሮች ሲያጋጥሙ ወሰን የሌለውን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

የመሬት አጠቃቀምና ልማት መሰረተ ልማት ችግሮችን ለመፍታት የተዘጋጀው የመሬት አስተዳደር ህግ በጨፌ ኦሮሚያ ፀድቆ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።ርእሰ መስተዳድሩ የኦሮሚያ ሀይማት ተቋማት ጉባኤ አራት ዋናዋና ጉዳዮች ላይ ድጋፍ እንዲያደርግም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠይቀዋል፡፡ከፕላን ውጭ የተሰሩ 656 የእምነት ቤቶች ወደ ወደ ፕላን እንዲገቡ ለማድረግ ጉባኤው ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ!

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ያልተጠራ የበጀት ጉድለት መሆኑ ተገለጸ።የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የበጀት ሪፖርት እንደገለጹት ለ2016 ዓ.ም. በጀት ዓመት የቀረበው አጠቃላይ በጀት አብዛኛው ከአገር ውስጥ የገቢ ምንጮች የሚሸፈን ነው።

ነገር ግን ለበጀቱ መሸፈኛ ይገኛል ተብሎ በታቀደው አጠቃላይ ገቢና ወጪ ይሆናል በተባለው 801.65 ቢሊዮን ብር መካከል፣ 281 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ የበጀት ጉደለት መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ የበጀት ጉድለት የሚሸፈነውም ከአገር ውስጥና ከውጭ ብድር እንደሚሆን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ ከአጠቃላይ የበጀት ጉድለቱ ውስጥ 39 ቢሊዮን ብር ከውጭ ብድር እንደሚሸፈን ተናግረዋል። የተቀረው 242 ቢሊዮን ብር ደግሞ ከአገር ውስጥ ብድር እንደሚሸፈን ገልጸዋል።

ይገኛል ተብሎ ከታቀደው የአገር ውስጥና የውጭ ብድር ውስጥ 53.7 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ተመልሶ ለአገር ውስጥና ለውጭ ዋና ብድር ክፍያ የሚውል በመሆኑ፣ የበጀት ዓመት የተጣራ የበጀት ጉድለት 227 ቢሊዮን ብር እንደሚሆንና ይህም ከአጠቃላይ የአገር ምርት ያለው ድርሻ 21 በመቶ መሆኑን ተናግረዋል።

ለበጀት ጉድለቱ መሸፈኛ የሚሆነው አብዛኛው ብድር ከአገር ውስጥ ምንጮች የሚወሰድ ከመሆኑ አኳያ የዋጋ ንረት ሊያስከትል የሚችል ቢሆንም በዋጋ ንረት ላይ የጎላ ተጽዕኖ እንዳይፈጥር ብድሩ በግምጃ ቤት ሰነድና የመካከለኛ ዘመን ቦንድ በመሸጥ ለማግኘት መታቀዱን ገልጸዋል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
‹ከዚህ በኋላ የእምነት ተቋማትን አላፈርስም› - የኦሮሚያ ክልል

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ‹ በሸገር ከተማ የመስጂዶችን መፍረስ በተመለከተ አስቀድሞ ውይይት አለመደረጉ ስህተት መሆኑን › ተናገሩ፡፡የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ‹ በኦሮሚያ ክልል፣ ሸገር ከተማ መስጂዶች መፍረስ በተመለከተ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባላት ጋር ለአምስት ሰዓታት የፈጀ ውይይት መደረጉን › ተከትሎ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው ይህ የተገለፀው፡፡

በመግለጫው ‹ በሸገር ከተማ አስተዳደር ውስጥ ያለፕላንና ሕጋዊነት ተሰርተዋል በሚል የፈረሱት 22 መስጂዶች › መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ይህ አምስት ሰዓታት ፈጅቷል በተባለው ውይይት በሙስሊም ተወካዮች በኩል 7 ያህል ነጥቦች መነሳታቸውን መግለጫው ያስረዳል፡፡ከእነዚህም ውስጥ ‹ የሸገር ከተማ አስተዳር ከፕላን ውጪ ተሠርተዋል ያላቸውን መስጂዶች ለማፍረስ ሲነሳ የሚመለከተውን የእስልምና ጉዳዮች አካላትን እንዳላወያየ፣ እንዲሁም በጉዳዩ ላይ እንወያይ በሚል በተደጋጋሚ ጊዜ የቀረበውን ጥያቄ ተቀብሎ ለማወያየት አለመሞከሩ ተገቢ አለመሆኑ › ተጠቅሷል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በውይይቱ ወቅት 12 ያህል ነጥቦችን አንስተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ‹ ውይይት አለመደረጉን › በተመለከተ ለተነሳው ቅሬታ በሰጡት ምላሽ ‹ ቀደም ብሎ በጉዳዩ ላይ ውይይት አለመደረጉ ስህተት መሆኑን › አምነዋል፡፡ፕሬዝዳንቱ ሌላው ያነሱት ጉዳይ ‹ በሸገር ከተማ ውስጥ ካሉት ስምንት መቶ (800) ያህል የእምነት ተቋማት መካከል ስድስት መቶ ሀምሳ ስድስት (656) ከፕላን ውጪ የተሰሩ ናቸው › ያሉበት ነው፡፡

ፕሬዝዳንቱ በማብራሪያቸው ‹ እነዚህ የሚገነባውን ከተማ የማይመጥኑት፣ በህጋዊና ከተማውን በሚመጥኑት ለመተካት በሚደረገው ሂደት የኦሮሚያ ክልል መጅሊስም ባለበት የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አቅሙን በማጠናቀከር በውይይት የእምንት ተቋማቱ ራሳች መፍረስ ያለባቸውን አደንዲፈርሱ እንጂ ከአሁን በኋላ መንግስት በራሱ ማፍረስ እንደሚያቆም › አረጋግጠዋል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
የቀጣዩ ዓመት የመከላከያ በጀት 50 ቢሊዮን ብር ሆኖ ቀረበ!

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት በጀት ውስጥ ለመከላከያ ሚኒስቴር 50 ቢሊዮን ብር ሲመደብ ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የወደሙ ተቋማትና አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ደግሞ 20 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙ ተገለጸ።

በ2015 በጀት ዓመት ለመከላከያ ሚኒስቴር 84 ቢሊዮን ብር ተይዞ የነበረ ሲሆን በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ባስከተለው ተጨማሪ ወጪን ለመሸፈን በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ወራቶች ቀርቦ ከጸደቀው የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ውስጥም መከላከያ ሚኒስቴር የአንበሳውን ድርሻ በማግኘቱ የሠራዊቱ የ2015 አጠቃላይ በጀት ለመጀመሪያ ጊዜ መቶ ቢሊዮን ብር በላይ ተሻግሯል።

የሰሜኑ ጦርነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መፍትሔ ማግኘቱን ተከትሎ መከላከያ ሚኒስቴር ለ2016 በጀት ዓመት 50 ቢሊዮን ብር እንደተያዘለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቀረበው የቀጣዩ ዓመት ረቂቅ በጀት ለመረዳት ተችሏል።

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው ረቃቅ በጀት ውስጥ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የወደሙ መሠረተልማቶችን ወደነበሩበት ለመመለስ 20 ቢሊዮን ብር እንደተያዘም ሰነዱ ያመለክታል።ለ2016 በጀት ዓመት ለክልሎች ድጎማ 214 ቢሊዮን ብር የተመደበ ሲሆን በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከሁለት ዓመታት
በላይ ከፌዴራል መንግስት የበጀት ድጎማ ያለገኘው የትግራይ ክልል ለቀጣዩ በጀት ዓመት 12.5 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል።

ለክልሎች ድጎማ ከተያዘው በጀት ውስጥ እንደሁልጊዜው ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት ኦሮሚያ ፣ አማራና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች ሲሆኑ ፤ እንደቅደም ተከተላቸውም ብር 71.9 ቢሊዮን ፣ ብር 45.1ቢሊዮን እና ብር 26.9 ቢሊዮን ተመድቦላቸዋል።

በተጨማሪም ፣ ሶማሌ 20.8 ክልል ቢሊዮን ብር፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝች ክልል 6.4 ቢሊዮን ብር፣ ሲዳማ ክልል 8.5 ቢሊዮን ብር ተደልድሎ በረቂቅ በጀቱ ቀርቧል፡፡በተመሳሳይ ፤ ለአፋር ክልል 6.3 ቢሊዮን ብር፣ ለቤንሻንጉል ክልል 3.8 ቢሊዮን ብር፣ ለጋምቤላ ህዝቦች ክልል 2.7 ቢሊዮን ብር፣ ለሃረሪ ህዝብ ክልል 1.5 ቢሊዮን ብር፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስታደዳር 5.2 ቢሊዮን ብር፣ ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳዳር 1.8 ቢሊዮን ብር ሆኖ በረቂቁ ተደልድሏል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
Join our channel and view the latest offers at https://tttttt.me/AGSmigration
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ትዛዝ አእናመጣለን ክፍለ ሀገርም እንልካለን ።
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉
https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🌕ድርጅታችን ከታች በተዘረዘሩ የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል። 

🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥NGO በማንኛውም

     🔹የት/ደረጃ:ዲፕሎማ/ድግሪ
     🔹የስራ ልምድ: 0 ዓመት
     🔹ደሞዝ: 18,500+

💥ሹፌር በሁሉም

     🔹የት/ደረጃ:መፃፍ ማንበብ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:13,500+

💥ስልክ ኦፕሬተር

     🔹የት/ደረጃ: 10 ጀምሮ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 6500

💥ጉዳይ አስፈፃሚ

     🔹የት/ደረጃ:10
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:7000

💥ባንክ ቤት ፅዳት ተላላኪ

    🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ፡4500

💥አካውንታንት

🔹የት/ት ደረጃ= ድግሪ/ድፕሎማ
🔹 ልምድ = 0-2 አመት
🔹ደሞዝ=8500

💥ካሸር አሰልጥኖ

🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500

💥ባርማን/ባሬስታ

🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት

💥 ዌተር የጧት እና የከሰዓት

     🔹የት/ደረጃ: 10 ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 3500


💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች

     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,000

💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)

🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Call +251921256367 or 0987971996
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
የርዳታ እህል ለተረጂ ያልደረሰው “በመጠነ ሰፊና የተቀናጀ ዘመቻ” እንደኾነ ዩኤስኤአይዲ አስታወቀ!

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የምትለግሰው የምግብ ርዳታ እንዲቋረጥ ያደረገችው፣ “ለተረጂው አይደርስም” በማለት እንደኾነ በይፋ አስታወቀች፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (USAID)፣ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው የምግብ ርዳታ፣ “ለተረጂዎች አይደርስም” ሲል፣ ርዳታውን ማቋረጡን፣ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

“ለተቸገረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መድረስ የሚገባው የምግብ ርዳታ፣ ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲቀየስ የሚያደርግ፣ መጠነ ሰፊ እና የተቀናጀ ዘመቻ መኖሩን”፣ ዩኤስኤአይዲ እና የኢትዮጵያ መንግሥት በመተባበር ባደረጉት ማጣራት ከድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን፣ የድርጅቱ ቃል አቀባይ በይፋ በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል።

ኾኖም፣ ርዳታው ለተረጂ ወገኖች እንዳይደርስ ከሚደረገው ዘመቻ ጀርባ ያለው ማን እንደኾነ፣ በመግለጫው ተለይቶ አልጠቀሰም። ዩናይትድ ስቴትስ፣ የአፍሪካ ቀንድንና አካባቢውን ክፉኛ ከጎዳው ድርቅ እና በቅርቡ ከአበቃው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋራ በተያያዘ፣ ለርዳታ ጠባቂነት የተጋለጡትን ጨምሮ፣ ቁጥሩ 20 ሚልዮን ለሚደርሰው ተረጂ ሕዝብ ዋናዋ ለጋሽ ሃገር ናት።

ሮይተርስ የዜና ወኪል በተመለከተው እና በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ የረድኤት ሥራ ለሚያከናውኑ የውጭ ለጋሽ ቡድኖች የቀረበ አንድ ሰነድ፣ “የርዳታ ምግቡ፥ ለአገሪቱ ልዩ ልዩ ወታደራዊ ክፍሎች እንዲሰጥ ተደርጓል፤” ብሎ፣ ዩኤስኤአይዲ እንደሚያምን ይጠቁማል።

ርዳታውን ከታለመለት ዓላማ ውጭ የማዋሉ ድርጊት፣ “በፌዴራል እና በክልል መንግሥታት አካላት የተቀነባበረ ዘመቻ፣ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ወታደራዊ ክፍሎች፣ ለሰብአዊ ርዳታ የመጣው ምግብ ተጠቃሚ ናቸው፤” ሲል፣ ዩኤስኤአይዲ’ን ያካተተው ይኸው የለጋሾች ቡድን ሰነድ አመልክቷል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በአዲስ አበባ ከተማ ትላንት ምሽት በደረሰ የእሳት አደጋ 7 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ!

በአዲስ አበባ ከተማ ትላንት ሰኔ 1 ቀን ከምሽቱ 5:51 በንፋስ ሰልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ዮሴፍ ታቦት ማደሪያ አካባቢ በተነሳ የእሳት አደጋ አራት መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በእሳት አደጋዉ ሰባት ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ጉዳት ከደረሰባቸዉ መካከል አንዱ የእሳት አደጋ ሰራተኛ መሆኑን ገልፀዋል።የእሳት አደጋዉን  ለመቆጣጠር ስምንት  የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሀምሳ አንድ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩ ሲሆን እሳቱን ለማጥፋትም ሶስት ሰዓት ፈጅቷል።

የእሳት አደጋዉ በአቅራቢያዉ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል።የእሳት አደጋ ሰራተኛዉ ከባድ ጉዳት ደርሶበት  በየካቲት 12 ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት እንደሚገኝ አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በሌላ በኩል ትላንት ምሽት በአራዳ ክፍለ  ከተማ  አራዳ ህንጻ ላይ በሊፍት የተያዘን ሰዉ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች  መታደግ ችለዋል።

[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በምስጢራዊ ሰነድ አያያዝ ክስ ቀረበባቸው!

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዋይት ሐውስን ከለቀቁ በኋላ ምስጢራዊ ሰነዶችን የያዙበት መንገድ ተገቢ አይደለም ተብለው ክስ ቀረበባቸው።የ76 ዓመቱ ትራምፕ ያለአግባብ ምስጢራዊ ስነዶችን ይዘዋል የሚለውን ጨምሮ ሰባት ክሶች ቀርቦባቸዋል።ክሶቹ እስካሁን ለሕዝብ ይፋ አልተደረጉም።ትራምፕ ክስ ሲቀርብባቸው ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፣ የቀድሞ ፕሬዝደንት በፌዴራል ደረጃ ክስ ሲቀርብበት ትራምፕ የመጀመሪያው ናቸው።

ዶናልትድ በ2024 ድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ለመሆን የምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ ናቸው።የሕግ አዋቂዎች እንደሚሉት ክሱ ትራምፕ ለፕሬዝደንትነት በሚያደርጉት ጥረት ላይ እክል አይሆንም።ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው ማኅበራዊ ሚድያቸው ትራምፕ ‘ከደሙ ንፁህ’ መሆናቸውን ገልጸው በፍሎሪዳ ግዛት ማያሚ በሚገኝ አንድ የፌዴራል ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ መታዘዛቸውን አመልክተዋል።በሚመጣው ማክሰኞ ትራምፕ ወደ ፍርድ ቤቱ በመሄድ በቁጥጥር ሥር ውለው የቀረበባቸውን ክስ ያደምጣሉ።

“ለአንድ እንኳን የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት እንዲህ ዓይነት ነገር ይገጥመዋል ብዬ አስቤ አላውቅም” ብለዋል።“ይህ ለአሜሪካ ድቅድቅ ጨለማ የሰፈነበት ቀን ነው። በፍጥነት እያሽቆለቆልን ያለ አገር ሆነናል። ነገር ግን በጋራ አሜሪካን እንደገና ታላቅ እናደርጋታለን።”የትራምፕ ጠበቃ ኪም ትረስቲ፤ ሲኤንኤን ለተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት የቀድሞው ፕሬዝደንት በምን ጉዳይ እንደተከሰሱ ይፋ ተደርጎላቸዋል።

ጠበቃው እንደሚሉት መዝገቡ፤ ሴራ፣ የሐሰት መግለጫ፣ ፍትህን ማጓተት እና በአገር ክህደት ውስጥ የሚካተተው ጥብቅ መረጃዎችን መያዝ የሚሉ ክሶችን ይዟል።የአሜሪካ ፍትሕ መሥሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት የተቆጠበ ሲሆን፣ ክሱ ለሕዝብ ይፋ አልሆነም።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ምዝገባ የልደት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ግዴታ ነው!

ለ2016 የትምህርት ዘመን ምዝገባ ወላጆች የልጆቻቸውን የልደት ምስክር ወረቀት የማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ።ምዝገባውን ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በቅንጅት እያከናወነ እንደሆነም ገልጿል።

ኤጀንሲው “የልደት ምዝገባ ለሁሉም ተማሪ” በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው ንቅናቄ በትናንትናው እለት የተማሪዎች የልደት ምዝገባ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት አሳይ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አከናውኗል።

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በወቅቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ በአገሪቱ ከሥነ-ህዝብ ለውጥ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ያለው በመሆኑ የሕዝብ ብዛትና እድገትን ማወቂያ መንገድ ነው። ይህም መንግስት ለሚያከናውናቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ እቅዶችና የአስተዳደራዊ አገልግሎቶች ዝግጅት የመረጃ ምንጭ ይሆናል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መብት በመሆኑ መንግስታት ይህን መብት ለማስፈጸም አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስዱ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ያዛሉ። ይህም ሀገራት ከወሳኝ ኩነት ምዝገባ ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ ያደርጋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በአዲስ አበባ ለ2016 የትምህርት ዘመን ምዝገባ ወላጆች የልጆቻቸውን የልደት ምስክር ወረቀት ማቅረብ እንደሚኖርባቸው ገልጸዋል።

“በንቅናቄው ሁለት ጉዳዮችን እያከናወነ ነው። አንደኛ ለተማሪዎች የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የሚኖረውን ጠቀሜታ ማስገንዘብ ሲሆን፤ ሁለተኛ የልደት ምዝገባ ማከናወን ነው” ያሉት አቶ ዮናስ፤ መንግስት ህብረተሰቡ የሚፈልገውን ለማሟላት የወሳኝ ኩነት መረጃ ያስፈልገዋል፤ ለዚህም ለ2016 የትምህርት ዘመን ምዝገባ የልደት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አስገዳጅ ሆኗል ብለዋል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ በበኩላቸው፤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ “የልደት ምዝገባ ለሁሉም ተማሪ” በሚል መሪ ቃል በአሳይ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የልደት ምዝገባ መጀመሩን አብስረው፤ በአሳይ ትምህርት ቤት ብቻ ለአንድ ሺህ ሁለት መቶ ተማሪዎች የልደት ምዝገባ ለማድረግ እቅድ መያዙን ገልጸዋል።

በ2016 የትምህርት ዘመን አንድም ተማሪ ያለ ልደት ካርድ ምዝገባ እንዳይካሄድ ተወስኗል ያሉት ኃላፊው፤ በትምህርት ቤቶች የልደት ምዝገባ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ በክፍለ ከተማው በሚገኙ በሁሉም ትምህርት ቤቶች እንደሚሰጥ ገልጸው፤ በዚህም የልደት ሰርተፍኬት የሚሰጠው ከዚህ በፊት የልደት ሰርተፍኬት ለሌላቸው ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን ማህበር ለመንግሥት ሰራተኞች ደሞዝ እንዲከፈል ጠየቀ!

በትግራይ ጦርነቱ ሲካሄድ በቆየባቸዉ ዓመታት ደሞዝ ማግኘት ላልቻሉ የመንግሥት ሰራተኞች ክፍያ እንዲፈጸምላቸዉ የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን ማህበር በጻፈው ደብዳቤ ጠይቋል።

ማህበሩ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ለትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጊዚያዊ አስተዳደር፣ ለኢፌዴሪ ህዝቦች ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ለፌዴሬሽን ምክርቤት በጻፈው ደብዳቤ፤ “በትግራይ የመንግሥት ሰራተኞች እንዲከፈላቸው ይገባ የነበረው ደሞዝ ባለመከፈላቸው ምክንያት፤ ከነበሩበት የኪራይ ቤት እንዲወጡ እና ከእነቤተሰባቸው ኑሮኣቸው ጎዳና ላይ እንዲሆን ተደርገዋል።” ብሏል።

በተጨማሪም ሰራተኞቹ የሚበሉት እና የመሚጠጡት አጥተው በረሃብ እየተሰቃዩ እንደሚገኙ የገለጸው ማህበሩ፤ ለህልፈት የተዳረጉም በጣም ብዙ መሆናቸውን አስታውቋል። እንዲሁም፤ ደብተር እና የመሳሰሉት የትምህርት ቁሳቁስ ገዝተው ልጆቻቸውን ማስተማር እማይታሰብበት ሁኔታ መፈጠሩን በመግለጽ፤ “ራሳቸው እና ማንኛውም የቤተሰብ አባል ቢታመምም ሊታከም የሚችልበት እድል ዝግ ሆኖባቸዋል። ” ሲልም ገልጿል።

ይህም “የፕሪቶርያው ስምምነት በተሟላ መልኩ ባለመተግበሩ፤ የመንግሥት ሰራተኞች ደሞዛቸው ባለመከፈሉ፣ ጡረተኞች የጡረታ አበላቸው ስለተከለከሉ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት መስጠት የነበረባቸው ተቋማት አገልግሎቱ መስጠት ባለመቻላቸው እና በመሳሰሉት ምክንያቶች” የተፈጠረ መሆኑን ማህበሩ ገልጿል።

“በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ቢያንስ በብዙ የትግራይ አካባቢዎች ዉግያ እንዳይኖር እና የጥይት ድምፅ እንዳይሰማ የተደረገ ቢሆንም፤ አሁንም ግን የትግራይ ሕገ መንግስታዊ ግዛት፣ በስምምነቱ መሰረት ትግራይ ዉስጥ መኖር ባልነበረባቸው የኤርትራ ወራሪ ሃይሎች እና የአማራ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር በመሆኑ በእነዛ ቦታዎች ግፉ እና ሰቆቃው እየቀጠለ ለመሆኑ የአለም ህዝብ የሚያውቀው ጉዳይ ነው።” ያለው ማህበሩ፤ የፕሪቶርያ ስምምነት በተሟላ መልኩ ባለመተግበሩ ምክንያት አሁንም በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በተመሳሳይ ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው ለተለያዩ እንግልቶች እንደተዳረጉ እንደሚገኙ አስታውቋል።

የጥይት ድምፅ በማይሰማባቸው ቦታዎችና አከባቢዎችም ቢሆን እልቂቱ፣ ረሃቡ እና እርዛቱ ገና አለመቆሙንም ገልጿል።ስለዚህም የስምምነቱ ዋና አላማን ታሳቢ በማድረግም ስምምነቱ በተሟላ መልኩ ተተግብሮ የተፈናቀሉት ዜጎች ወደየቀያቸው እንዲመለሱ፣ የመንግሥት ሰራተኞችም እስካሁን ድረስ ያልተከፈላቸው ደሞዝ፣ ጥቅማ ጥቅምና ካሳ እንዲከፈላቸውና በቀጣይነትም እነዚሁ የሚገቧቸው ክፊያዎች በሙሉ ሳይቆረጡና ሳይቆራረጡ እንዲከፈላቸው የትግራይ ዩኒቨርስቲዎች ምሁራን ማህበር በደብዳቤው ጠይቋል።

👉ማህበሩ የጻፈው ደብዳቤ ከላይ ተያያዟል
@YeneTube @FikerAssefa
‹ በፈረሱት ሸራ ቤቶች ውስጥ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ሲፈፀም እንደነበረ በጥናት አረጋግጬያለሁ › - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ

የቢሮው ሃላፊ ሊዲያ ግርማ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለመንግስት ቅርበት ላላቸው መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ቢሯቸው አድርጎታል ባሉት ጥናት ‹ በሸራ ቤቶቹ ውስጥ ከአስገድዶ መድፈር አንስቶ ከትንሽ እስከ ከባባድ ወንጀሎች እየተፈፀሙ መሆናቸውን › አረጋግጠዋል፡፡ከዚህ ውጪም ‹ የሸራ ቤቶችን ለሦስተኛ ወገን ሲተላለፉ › ነበር ብለዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ‹ በከተማዋ ኢ-መደበኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች እየበዙ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ሊያስከትሉ ይችላሉ የሚል ስጋት መኖሩን በጥናት ተለይቷል › ባይ ነው።በዚሁ ተደርጓል በተባለው ጥናት መሰረት ‹ ወደ መደበኛ የንግድ ስርዓት እንዲገቡ እንዲሁም በዘላቂነት መልክ ለማስያዝ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን › ኢዜአ ዘግቧል።

በዚህም በከተማዋ በሚገኙ በሸራ የተሰሩ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ተከትሎ ቅሬታዎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።የቢሮ ሃላፊዋ ‹ ከተማ አስተዳደሩ ዜጎች በጊዜያዊነት ለስራ እድል ፈጠራ በተዘጋጁ የሸራ ቤቶች ውስጥ በአነስተኛ የንግድ ስራ እንዲሰማሩ ባመቻቸው ዕድል በአግባቡ የተለወጡ መኖራቸውን › አመላክተዋል።

ምንም እንኳን ሃላፊዋ እኒዘህ የሸራ ቤቶች ‹ በከተማ አስተዳደሩ ዕውቅና በጊዜያዊነት እንደተዘጋጁ › ይግለፁ እንጂ አሻም ከሁለት ሳምንት ገዳማ በፊት በሰራችው ዘገባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ‹ የሸራ ቤቶች የፈረሱት ህገ ወጥና የጽንፈኞች መነኸሪያ በመሆናቸው ነው › ማለታቸው ይታወሳል፡፡‹ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ህግንና አሰራረን መሰረት ያደረጉ › ናቸው ያለው ከተማ አስተዳደሩ ‹ እርምጃውን በተሳሳተና መሰረተ ቢስ በሆነ መንገድ የሚያናፍሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ › አሳስበዋል።

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
በባህሬን በአሰሪዋ ተደብድባና ተደፍራ ያረገዘችው ኢትዮጵያዊ ወጣት ፍትህ እንድታገኝ መደረጉ ተገለጸ!

በባህሬን አንዲት ወጣት 4 ዓመት ሙሉ ስትሰራበት የነበረበት ቤት ውስጥ በአሰሪዋ በመደፈር፣ በመደብደብ እና የመግደል ዛቻ ሲደርስባት በመቆየቱና የድረሱልኝ ጥሪዋን በማሰማቷ ምክንያት፤ በባህሬን የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት እና በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በጋራ በመሆን ለሚመለከተው የሕግ አካል በማመልከት ፍትሕ እንድታገኝ መደረጉ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ አሰሪዋ “አልደፈርኩም” ብሎ የሕክምና ወረቀት በማቅረብ ጉዳዩ ትኩረት እንዳያገኝ በማድረግ ወጣቷን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም፤ ጽ/ቤቱና በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ከ6 ወራት በላይ በመከራከርና የDNA ምርመራ በማስደረግ በተገኘው የምርመራ ውጤት መሰረት፤ ወጣቷ የስድስት ወር እርጉዝ መሆኗና የእርሱም ልጅ እንደሆነ ፍርድ ቤት መወሰኑ ተነግሯል።

በዚህም መሠረት፤ የወጣቷን እና የልጇንና መብት በማስከበር 64 ሺሕ 800 የባህሬን ዲናር (9 ሚሊዮን 344 ሺሕ 886 ብር) በየአራት ዓመት ክፍያ እንዲከፍል አሰሪው የተስማማ ሲሆን፤ ለመጀመሪያ አራት ዓመት የሚሆን ቅድመ ክፍያ 14 ሺሕ 200 የባህሬን ዲናር (2 ሚሊዮን 47 ሺሕ 799 ብር) በመቀበል ፍርድ ቤት ፈርሞበት ወጣቷ ፍትህ እንድታገኝ መደረጉን በባህሬን የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አስታውቋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa