YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ምርቴን እቀንሳለሁ ማለቷ የነዳጅ ዋጋን ከፍ አደረገ!

ሳዑዲ አረቢያ ከነዳጅ ምርቷ በቀን 1 ሚሊዮን በርሜል እቀንሳለሁ ማለቷን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ከፍ አለ።ሌሎች የዓለማችን ነዳጃ አምራች አገራትም በተመሳሳይ የነዳጅን ዋጋን ለማረጋጋት በማሰብ የምርት አቅርቦታቸውን ለመቀነስ ተስማምተዋል።ሳዑዲ አረቢያ በቀጣዩ ሀምሌ ወር በየቀኑ 1 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ከምርት አቅርቦቷ ላይ እንደምትቀነስ የገለጸች ሲሆን የነዳጅ ላኪዎች ሀገራት ማህበር ወይም ኦፔክ+ እንደ አውሮፓውያኑ በ2024 ዕለታዊ የነዳጅ አቅርቦት በ1.4 ሚሊዮን በርሜል እንደሚቀንስ ገልጿል።

ኦፔክ+ የዓለምን 40 በመቶ የነዳጅ ፍላጎት የሚያሟላ ሲሆን ውሳኔው በዓለም የነዳጅ ምርት ዋጋ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል።የሳዑዲን ውሳኔ ተከትሎ በእስያ ገበያ የደፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ 2.4 በመቶ አሻቅቦ በበርሜል 77 ዶላር ሆኗል።በሩሲያ የተመራውና 7 ሰዓታት የፈጀው ስብሰባ እያሽቆለቆለ ለመጣው የነዳጅ ዋጋ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ነው።

የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክስአንድር ኖቫክ እንደገለጹት ከሆነ ኦፔክ+ የምርት አቅርቦቱን ለመቀነስ ከወሰነበት ጊዜ ጀምሮ ከእለታዊ ምርቱ 3.6 ሚሊዮን ነዳጅ ምርት መቀነስ ችሏል።የኦፔክ አባል ሀገራት እና አጋሮቻቸው ዕለታዊ የነዳጅ አቅርቦታቸውን በሁለት ሚሊዮን በርሜል ለመቀነስ ቀደም ብለው ተስማምተው ነበር። ይህ ምርት የዓለም የነደጃ ፍላጎትን በ 2 በመቶ የሚቀንስ ነው።አዲሱ ውሳኔ ቀደም ብሎ የነበረውን እስከ ቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ያራዘመ መሆን የሩሲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ገልጸዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከሰሞኑ በአንዳንድ መስጂዶች ላጋጠሙ ጉዳቶችና ጥፋቶች ምርመራ እያደረኩ ነዉ ሲል መንግስት አስታወቀ!

ከሰሞኑ በአንዳንድ መስጂዶች ላጋጠሙ ጉዳቶችና ጥፋቶች መንግስት ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም አስታዉቀዋል።ሚኒስትሩ በዛሬዉ እለትም በፌዴራል እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት አማካኝነት ከተቋቋመ ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል ተብሏል።

ውይይቱ በቅርቡ በአንዳንድ አካባቢዎች መስጅድ ፈርሷል በሚል የተፈጠረውን ችግር ከሚመለከተው አካል ጋር ተቀራርቦ በመነጋገር የጋራ መፍትሄ ለማበጀት ያለመ ነው የተባለ ሲሆን በውይይት መድረኩ ከፌዴራል መጅሊስ ፣ ከአዲስ አበባ መጅሊስ እና ከኦሮሚያ መጅሊስ የተወከሉ የሐይማኖት አባቶች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ተገኝተዋል።

መስጅዶች በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ፈርሰዋል በሚል ምክንያት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሁለት መስጅዶች ላይ በሁለት የጁምዓ ሶላት ቀናት አመፅ ለመቀስቀስ ተሞክሯል በሚል በመድረኩ የተነሳ ሲሆን እነዚህ አካላት በቀሰቀሱት ግጭት ምክንያት የንብረትና የአካል ጉዳት እንዲሁም በሰው ህይወት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።ይህ አላስፈላጊ ጉዳት መድረሱ በፍፁም አግባብ እንዳልነበረና ከመፈጠሩ በፊት ሊወገድ የሚችል ችግር እንደነበር በውይይቱ መግባባት ላይ መደረሱን ብስራት ራዲዮ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ብናልፍ አንዷለም በውይይት መድረኩ የትኛውንም ችግር መፍታት የሚቻለው በንግግርና በውይይት ብቻ መሆን እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡የተፈጠሩት ችግሮች ከሃይማኖቱ አባቶች እና ከመንግስት አቅም በታች በመሆናቸው ይህ ኮሚቴ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር በቅርበት መነጋገር መጀመሩ አበረታች ነው ብለዋል፡፡ የተጀመረው ውይይት ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሄም እንደሚያስገኝ እምነታቸው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ኮሚቴው ለዚህ ወቅታዊ ችግር መፍትሄ በጋራ ማፈላለግ ዋነኛ ተልዕኮው ነው ያሉት አቶ ብናልፍ በዚህ አላስፈላጊ ግጭት ምክንያት ላጋጠሙ ጉዳቶችና ጥፋቶች ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም አረጋግጠዋል።የመጅሊስ ተወካይ የኮሚቴው አባላት በበኩላቸው ለሚፈጠሩ ማንኛውም ችግሮች ተቀራርቦ መነጋገርና መወያየት ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያመጣ ጠቁመዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
"በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር ድርጊት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል" -ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎች እየጨመረ የመጣውን የአስገድዶ መሰወር (Enforced Disappearance) እና ተይዘው የሚገኙበት ሁኔታ ሳይታወቅ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ጉዳይ ሲከታተል መቆየቱን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

በተለይም ይህ አሳሳቢ ሁኔታ በተከሰተባቸው የአዲስ አበባ ከተማ፣ የኦሮሚያ ክልል እና የአማራ ክልል ኮሚሽኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን መንግሥታዊ ኃላፊዎች በማነጋገር፣ በልዩ ልዩ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ቦታዎች በመዘዋወር እና ከቤተሰቦችና ከሌሎች የመረጃ ምንጮች መረጃዎችን ሲያሰባስብ እንደቆዬ አመልክቷል።

ኢትዮጵያ ገና ያላጸደቀችው ቢሆንም ሁሉንም ሰዎች ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ በተደረገው ዓለም አቀፍ ስምምነት (International Convention for the Protection of All Persons from Enforced Disappearance) መሠረት አስገድዶ መሰወር ማለት “በመንግሥት ወኪሎች ወይም ከመንግሥት ፈቃድ ወይም ድጋፍ በተሰጣቸው ሰዎች ወይም ቡድኖች ወይም በመንግሥት ስምምነት አንድን ሰው በማሰር፣ አፍኖ በመውሰድ፣ ወይም በሌላ በማናቸውም መንገድ ነጻነቱን በማጥፋትና፤ በቁጥጥር ስር መዋሉን በመካድ፣ በመደበቅ፣ የአለበትን ቦታ ባለማሳወቅ ወይም ደብዛውን በማጥፋት ፈጽሞ ከሕግ ጥበቃ ውጪ እንዲሆን ማድረግ’’ ነው።

በሌላ በኩል አንድን ሰው የሚገኝበት ቦታና ሁኔታ ሳይታወቅ በእስር መያዝ ማለት በተለይ በከባድ ወንጀል ተጠርጥሯል የተባለን ሰው ለወንጀል ምርመራ በሚል ምክንያት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ እንዳይገናኝ አድርጎ በእስር የማቆየትን ተግባር የሚገልጽ ፅንሰ ሐሳብ ሲሆን፤ እነዚህ ሁለቱም ድርጊቶች ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ናቸው።

በተለይ በአስከፊነቱ የሚታወቀው የአስገድዶ መሰወር ተግባርን የሚያቋቁሙት ዋነኛ አላባዎች ሦስት ዋና ጉዳዮች ናቸው ያለው ኮሚሽኑ፣በማናቸውም ዓይነት መንገድ ቢሆን አንድን ሰው ከፈቃዱ ውጪ ነጻነቱን መንፈግ/ማጥፋት፣ መንግሥት በጉዳዩ ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ፈቃድ ወይም ድጋፍ ወይም ስምምነት በመስጠት ተሳታፊ መሆን እና
አስገድዶ የተሰወረውን ሰው ያለበትን ቦታ እና ሁኔታ መካድ፣ አለመቀበል ወይም ለማሳወቅ ፈቃደኛ አለመሆን መሆናቸውን አብራርቷል፡፡

ኢሰመኮ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ከደረሱት አቤቱታዎችና ጥቆማዎች በመነሳት ሲያደርግ በነበረው ክትትል መሠረት በርካታ የአስገድዶ መሰወርን ድርጊት የሚያቋቁሙ ድርጊቶች መከሰታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

አብዛኛውን ጊዜ የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው፣ ከሥራ ቦታ ወይም ከመንገድ ላይ የሲቪልና የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታና ደኅንነት ሠራተኞች ያለ ፍርድ ቤት የመያዣ ትእዛዝ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ወዳልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ እንዲሰወሩ የተደረጉ ሲሆን፤ ከፊሎቹ ከተወሰኑ ቀናት፣ ሳምንታት ወይም ወራት መሰወር በኃላ የተገኙ መሆናቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ ሌሎች ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ በግዳጅ እንደተሰወሩ የቀጠሉ ናቸው።

ከእነዚህ ተጎጂዎች መካከል የተወሰኑት ሲያዙ በወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ መሆኑ ተነግሯቸው ወደ መደበኛ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ የተሰወሩ ሲሆን ከፊሎቹ ደግሞ ምንም ሳይነገራቸው በጸጥታ ኃይሎች ተወስደው የተሰወሩ ናቸው ብሏል፡፡

ለምሳሌ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በማስገደድ ተሰውረው ከነበሩ ሰዎች ውስጥ ከተለያየ የጊዜ መጠን መሰወር በኃላ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው የተገኙ ሲኖሩ፣ አስገድደው በተሰወሩበት ወቅት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ውስጥ ገላን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ የቀድሞው ልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ ተይዘው እንደቆዩ ለመረዳት ተችሏል። በአስገድዶ መሰወሩ ወቅት ተፈጽሟል ስለተባለ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ ወይም የማሰቃየት ተግባር ኮሚሽኑ ምርመራውን የቀጠለ ሲሆን የምርመራ ሥራው እንደተጠናቀቀ ትክክለኛውን መረጃ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “ይህ አስከፊ የሆነ የአስገድዶ መሰወር ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም መንግሥት አስፈላጊውን ጊዜያዊ እና ዘለቄታዊ እርምጃዎች ሁሉ እንዲወስድ፣ የተሰወሩ ሰዎች ሁሉ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ፣ በተሰወሩበት ጊዜ ሁሉ የተፈጸሙ ድርጊቶች ላይ የተሟላ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም ችግሩ የደረሰበትን አሳሳቢ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ሀገር አቀፍ ገለልተኛ አጣሪ የሥራ ቡድን በማዋቀር የድርጊቱ ሰለባ የሆኑ ሰዎችን ማፈላለግ እና ፍትሕን ማረጋገጥ ይገባል” በማለት አሳስበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ ኤች .ሲ.ፒ ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ከሐምሌ 3-7 2015 ዓም ይሰጣል።ለዚህም ይረዳ በሰኔ ወር ባሉ ሁሉም ቅዳሜ እና እሁዶች የልየታ ስራ ይሰራል ስለሆነም በነፃ የስልክ 976 ደውለው ይመዝገቡ!

@YeneTube @FikerAssefa
ኩዌት በወርሃዊ የ300 ዶላር ክፍያ ኢትዮጵያን ሰራተኞችን ልትቀጠር መሆኑ ተገለጸ!

ኩዌት የሦስት ወራት አስገዳጅ ስልጠና የወስዱ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ለመቀበል ከመንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መድረሷ ተገልጿል።በኹለቱ መንግሥታት በኩል መግባባት ላይ መደረሱን ተከትሎም፤ በጥቂት ቀናት ውስጥ የጋራ የሥራ ስምምነት እንደሚፈረም የአረብ ታይምስ ዘገባ አመላክቷል።

ከስምምነቱ በኋላ በኢትዮጵያ የሚገኙ 600 የሚሆኑ የሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሰው ኃይል በማቅረብ እንደሚሰሩ የተነገረ ሲሆን፤ ሰራተኞች ቢያንስ ብቃቱ ከተረጋገጠ ተቋም የ3 ወር ስልጠና መውሰድ አለባቸው ተብሏል።ኩዌት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የቤት ሰራተኞች የምታገኘው ከፊሊፒንስ ሲሆን፤ በኹለቱ አገራት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ አገሪቱ የሰራተኛ እጥረት በማጋጠሙ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ለመቀበል ማቀዷን ነው ዘገባው ያመላከተው።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከኩዌት መንግሥት ጋር በተስማሙት መሰረት፤ አንድ ሰራተኛ በወር 90 ኩዌት ዲናር (300 ዶላር) ይከፈለዋል የተባለ ሲሆን፤ ይህም በወቅታዊው የምንዛሬ ተመን ወደ 16 ሺሕ የኢትዮጵያ ብር የሚጠጋ ይሆናል። ወደ ፊትም ወርሃዊ ክፍያዉ እስከ 500 ዶላር ከፍ ሊል እንደሚችልም ተጠቁሟል።የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም ኩዌትን ጨምሮ ከቤሩት፣ ከእስያ እና አውሮፓ አገራ ጋር የስምምነት ሥራዎች እንደተጀመሩ መግለጹ ይታወሳል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የካራማራው ጀግና ዓሊ በርኬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል የነበሩት የካራማራው ጀግና ዓሊ በርኬ ባደረባቸው ሕመም በ72 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሰኔ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል!

የሁሉም ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከግንቦት 29 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በግንቦት ወር ሲሸጥ በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሠረት ፡-
1. ቤንዚን ………………………………………ብር 69.52 በሊትር
2. ነጭ ናፍጣ………………………………….ብር 71.15 በሊትር
3. ኬሮሲን ……………………………………...ብር 71.15 በሊትር
4. የአውሮፕላን ነዳጅ ………………………ብር 65.35 በሊትር
5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ…………………………ብር 57.97 በሊትር
6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ………………………….ብር 56.63 በሊትር የሚሸጥ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
Join our channel and view the latest offers at https://tttttt.me/AGSmigration
Forwarded from YeneTube
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
👍1
Forwarded from YeneTube
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🌕ድርጅታችን ከታች በተዘረዘሩ የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል። 

🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥NGO በማንኛውም

     🔹የት/ደረጃ:ዲፕሎማ/ድግሪ
     🔹የስራ ልምድ: 0 ዓመት
     🔹ደሞዝ: 18,500+

💥ሹፌር በሁሉም

     🔹የት/ደረጃ:መፃፍ ማንበብ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:13,500+

💥ስልክ ኦፕሬተር

     🔹የት/ደረጃ: 10 ጀምሮ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 6500

💥ጉዳይ አስፈፃሚ

     🔹የት/ደረጃ:10
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:7000

💥ባንክ ቤት ፅዳት ተላላኪ

    🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ፡4500

💥አካውንታንት

🔹የት/ት ደረጃ= ድግሪ/ድፕሎማ
🔹 ልምድ = 0-2 አመት
🔹ደሞዝ=8500

💥ካሸር አሰልጥኖ

🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500

💥ባርማን/ባሬስታ

🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት

💥 ዌተር የጧት እና የከሰዓት

     🔹የት/ደረጃ: 10 ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 3500


💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች

     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,000

💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)

🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Call +251921256367 or 0987971996
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
አሜሪካ፣ ቻይናን ለመገዳደር ከህንድ ጋር ያላትን ግንኙነት ከፍ በማድረግ ጉዳይ ዙሪያ ተወያየች

የአሜሪካ እና የህንድ የአምስት አመት የመከላከያ ኢንዱስትሪ ትብብር ፍኖተ ካርታ የውጊያ እና የእንቅስቃሴ ቴክኖሎጂዎችን እንዲያመርቱ ይረዳል ተብሏል

የአሜሪካ የመከላከያ ጸኃፊ ሊልዮድ  ኦስቲን  ከቁጥር አንድ የጦር መሳሪያ ገዥ ከሆነችው ህንድ ጋር ግንኙነታቸውን ከፍ ለማካደግ ተነጋግረዋል።

ባለስልጣናቱ እንደገለጹት ትብብራቸውን ከፍ ለማድረግ የፈለጉት ሁለቱም ሀገራት በቻይና ኢኮኖሚያዊ የበላይነት እና ተንኳሽነት መቸገራቸውን በመግለጽ ነው።

ኦስቲን ህንድን የጎበኙት ህንድ ከረጅሞ ጊዜ የጦር መሳሪያ አቅራቢዋ ሩሲያ በመላቀቅ በሀገር ውስጦ የመከላከያ ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት ማድረጓን ተከትሎ መሆኑ ተዘግቧል።
ኦስቲን እና የህንድ አቻቸው ሁለቱ ሀገራት አስተማማኝ ትብብር ለማድረግ መስማማታቸውን የህንድ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የአሜሪካ እና የህንድ የአምስት አመት የመከላከያ ኢንዱስትሪ ትብብር ፍኖተ ካርታ የውጊያ እና የእንቅስቃሴ  ቴክኖሎጂዎችን እንዲያመርቱ ይረዳል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት በስለላ፣ በቅኝት እንዲሁም በባህር ስለሚደረግ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በትበብር ይሰራሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዜጎች ምክክር ሊደረግባቸው ይገባል የሚሉትን ጉዳዮች እንዲጠቁሙ ጠየቀ!

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዜጎች እንደ ሀገር ምክክር ሊደረግባቸው ይገባል ብለው የሚያምኑባቸውን ጉዳዮች እንዲጠቁሙና ለዚህ ሀገራዊ ጉዳይ በንቃት አንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአካል በመገኘት፣ በስልክ ቁጥር 0111261196 ፤ 0975554500፣ በፖስታ ሳጥን ቁጥር 32623፣ በኢ-ሜይል አድራሻ ethiopianndc@gmail.com ጉዳያቸውን እንዲያቀርቡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል።

የኮሚሽኑ በስልክ፣ በፖስታ፣ በኢ-ሜይልና አዲስ አበባ ሽሮሜዳ አከባቢ በሚገኘው ቢሮው በአካል በመቅረብ አጀንዳቸውን እያቀረቡ ያሉ ዜጎች መኖራቸውንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የቀጣዩ ዓመት በጀት 801.6 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ተወሰነ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2016 ዓመት የፌዴራል መንግስት በጀት ብር 801.65 ቢሊየን እንዲሆን ወሰነ።

በዚሁ መሰረትም ለፌደራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች ብር 369.6 ቢሊየን፣ ለካፒታል ወጪዎች ብር 203.9 ቢሊየን፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ብር 24.07 ቢሊዮን፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ ብር 14 ቢሊየን ፣ በጠቅላላው ብር 801.65 ቢሊየን እንዲሆን ተወስኗል፡፡

የሚንስትሮች ምክር ቤት በቀረበው የፌዴራል መንግሥት የ2016 በጀት ረቂቅ አዋጅ ተቀብሎ በማጽደቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት ሂዩማን ራይትስ ዎች ያወጣው ሪፖርት ተቀባይነት የለውም አለ!

መንግስት ሂዩማን ራይትስ ዎች ያወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ምላሹም ከላይ ተያይዟል።👆👆

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ኢዜማ ‹ ከመንግስት ጋር በመስራቴ አገር እንድትተርፍ አድርጌያለሁ › አለ፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ‹ ከመንግስት ጋር በመስራቴ ሀገር እንድትተርፍ አድርጌያለሁ › ሲል ተናግሯል፡፡ፓርቲው የተለያዩ ሚዲያዎች ባለፉት ሁለት ሳምንታት ያቀረቡትን ዘገባዎች ተከትሎ በአባላቱ፣ ደጋፊውና ማኅበረሠቡ ውስጥ ብዥታ ፈጥረዋል ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይም ፓርቲው ከመንግስት ጋር በመስራቱ ምን አተረፈ በሚል ከጋዜጠኖች በኩል ጥያቄ ቀርቦለታል፡፡ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የኢዜማ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ ሙሉዓለም ተገኘወርቅ ‹ ከመንግስት ጋር አብረው በመስራታቸው ኢትዮጵያ እንድትተርፍ አድርገናል › ብለዋል፡፡

‹ባለፉት ሶስትና አራት አመታት ወደኋላ ተመልሳችሁ ካያችሁ የነበረን ውይይት ይህ ሀገር ይቀጥላል፣ እንበታተናለን ወይንም ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እንገባለን የሚል ስጋት ውስጥ እንደነበርን አትረሱትም› ያሉት ሃላፊው ‹ በዚህ መሀል ኢዜማ ስጋቱ እውን እንዳይሆን የየትኛውም ግጭትን የሚቀሰቅስ ጉዳይ ላይ ባለመሳተፍ ከሀገሩ ጎን በመቆም ሀገሩን የማትረፍ ሂደት ላይ ትልቅ ስራ ሰርቷል ብለን እናምናለን፡፡› ሲሉ የፓርቲያቸውን አቋም አንፀባርቀዋል፡፡

‹ ቀጣይ ትውልድን በመፍጠር ስራ ውስጥ የአቅማችንን እየሰራን መሆኑ የምንኮራበት ስራ ነው › የፓርቲያቻውን ተግባር አሞካሽተዋል፡፡አክለውም ‹ የልዩ ሀይል መፍረስ ሂደት ላይ ያሉብንን ችግሮች አሳይተናል፤ በመፍረሱ ወይንም ወደ ሌሎች የፌደራል የፀጥታ መዋቅሮች በመካተቱ ግን በጣም ደስተኞች ነን፤ ይህም አንዱ ውጤት ነው ብለን ነው የምናስበው › ሲሉ ተናግረዋል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ምክርቤት 13 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላት “በህግ በማስከበር ሽፋን በአማራ ላይ ተከፈተ” ያሉት ጦርነት በአፋጣኝ እንዲቆም በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠየቁ።

በመንግስት ከፍተኛ ስልጣን የተሰጣቸው የአብን አባላት በክልሉ ህዝብ ላይ እየደረሰ ነው ያሉት በደል እንዲያቆም ድምፃቸውን ያሰሙ አሊያ ስልጣናቸውን ይልቀቁ በማለት አንድ የንቅናቄው አባል ገልጠዋል፡፡አባላቱ ባወጡት መግለጫ “ከሁለት ዓመት የሰሜኑ ጦርነትና ከጦርነት ጫናዎች የተረፈው ወገናችን በሌላ ጦርነት እየተገደለ፣ ሀብትና ንብረቱ እየወደመ ነው” ሲሉ አመልክተዋል፡፡

የአማራ ክልል ከፍተኛ የፀጥታ ችግር ባለበት በአሁኑ ወቅት የክልሉ ልዩ ኃይልና ፋኖ እንዲበተን ማድረግ ተገቢ እንዳልሆነ የገለጹት 13ቱ የአብን ተወካዮች የአማራ ክልል መንግስት ምክር ቤት “የተለየ ሁኔታ አጋጥሞኛል” በሚል የፌደራል መንግስቱንና የመከላከያን ድጋፍ ባልጠየቀበት ሁኔታ በፌደራል የሚገኙ «ጥቂት» ያሏቸውን የክልሉን ተወላጅ ሹመኞችን በመጠቀምና በእነርሱ አማካኝነት ክልሉን ከአዲስ አበባ የመምራት ፍላጎትና ሙከራ በተደጋጋሚ እንደሚታይና “ያልታወጀ” ያሉት ጦርነትም በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ፀጋ በላቸውን የጠለፈው ተጠርጣሪ ወንጀለኛ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ፀጋ በላቸውን የጠለፈው ተጠርጣሪ ወንጀለኛ በሁላ ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ተፈላጊ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ የኃላመብራት ወልደማሪያምን በቅርበት ሲከታተል የነበረው የክልሉ የፀጥታ ግብረ ኃይል በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር ማዋሉን ነው ቢሮው ባወጣው መረጃ ያመላከተው።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በሚቀጥለው ዓመት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ይካሄዳል-ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በሚቀጥለው ዓመት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ።የዝግጅት ምዕራፍ አካል የሆኑትን የተሳታፊ መረጣና የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራ የ2015 በጀት ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት ለመጨረስ እየተሰራ መሆኑንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።ኮሚሽኑ የተሳታፊዎች ልየታን በሚያካሂድበት ወቅት ግልፅነት፣ አካታችነት፣ ፍትሐዊ ውክልና፣ አዳዲስ ከዋኞችና ተባባሪዎች እንዲሁም በቂ ጊዜ ታሳቢ እንደሚደረጉ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር፣ የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የእድሮች ማህበራት ጥምረት፣ የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ፣ የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ የወረዳ (ልዩ ወረዳ) አስተዳደር ተወካዮች በተሳታፊ ልየታ ተባባሪነት ተመርጠዋል።በሀገራዊ ምክክሩ የሚሳተፉ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተመረጡ ሲሆን እነሱም፤ እራሳቸውን የሚገልፁበት ዋና መተዳደሪያ ያላቸው ሰዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ዕድሮች፣ የማህበረሰብ መሪዎች /አባቶች/ እናቶች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ መምህራን፣ የእጅ ባለሙያዎች፣ የንግድ ማህበረሰብ ናቸው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የዝግጅት ምዕራፍ ማጠናቀቂያ የሆኑት የአጀንዳ መሰብሰብና የተሳታፊዎች ልየታ ስራ እየተከናወነ ይገኛል።በየአካባቢው ተፈናቅለው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በያሉበት የመጠለያ ስፍራ እንደ 10ኛ ባለድርሻ አካል የራሳቸውን ተወካዮች የሚያመጡበትን አሰራር ተዘርግቷል ብለዋል።በአሁኑ ወቅት በድሬዳዋ፣ በሀረሪ፣ በሲዳማ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው፤ በሚቀጥሉት 10 ቀናት በነዚህ አካባቢዎች የተጀመረው የልየታና የማሰባሰብ ስራ ይጠናቀቃል ነው ያሉት።

ዜጎች በየትኛውም መንገድ አልተወከልንም ብለው ካሰቡ አጀንዳዎቻቸውን ለኮሚሽኑ በአካል፣ በፖስታ፣ በስልክ፣ በበይነ መረብ የሚያስገቡበት አሰራር መዘርጋቱንም ተናግረዋል።ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የምክክር ዝግጅቶችን ለማከናወን የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ከየአካባቢው አስተዳደሮች ጋር ውይይት በማድረግ በጋራ ለመስራት መግባባት መፈጠሩንም ጠቅሰዋል።ኮሚሽኑ በተንቀሳቀሰባቸው አካባቢዎች ህዝቡ ሰላም እንደሚፈልግ እና ጥያቄዎቹንም በውይይት የመፍታት ፅኑ አቋም እንዳለው ተረድተናል ነው ያሉት።

ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርም በምክክሩ አስፈላጊነትና አካሄድ ላይ ውይይት አድርጎ ወደ ስራ ለመግባት ደብዳቤ ተፅፎ ምላሽ እየተጠባበቅን ነው ብለዋል።በመሆኑም ትግራይ ክልልን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ወረዳዎች የተሳታፊዎች ልየታና አጀንዳ የማሰባሰብና የመረጣ ስራ አስቸጋሪ ሁኔታ ካላጋጠመ በስተቀር የ2015 በጀት ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት እንደሚጠናቀቅ ጠቁመዋል።ይህን በስኬት በማጠናቀቅ በሚቀጥለው ዓመት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ሀገራዊ ምክክሩን ለማካሄድ ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

እያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል ከየወረዳዎች 50 ሰዎችን በተሳታፊነት እንደሚልክ ጠቅሰው በሀገራዊ ምክክሩ እስከ 700 ሺህ ኢትዮጵያውያን በቀጥታ ሊሳተፉ እንደሚችሉም ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ደረጃ ለሚደረጉ የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራዎች ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ሁለት ሁለት ተወካዮችን ይመርጣሉ ብለዋል፡፡የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን፣ ወጣቶችን ጨምሮ ሁሉም ለኮሚሽኑ እያደረጉ ያሉትን ትብብር አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
😁1