YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአንዋር መስጊድ አካባቢ የጸጥታ ሀይሎች ተኩስ መክፈታቸው ተሰማ።

ስማቸው ለደህንነታቸው ሲባል እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የዓይን እማኝ ለአሻም አንደነገሯት ‹ በአንዋር መስጂድ አካባቢ የተቃውሞ ሰልፍ ባይኖርም የጸጥታ ሀይሎች በቦታው ተኩስ መክፈታቸውን እና በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል ›

ከአዲስ አበባ ፖሊስ አልያም ከሌላ ገለልተኛ ተቋም ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ማረጋገጫ ባይሰጥበትም ‹ በተከፈተው ተኩስ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን የአይን እማኙ › ለአሻም አረጋግጠዋል።

በተመሳሳይ ባለፈው ሳምንት ዐርብ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም በአንዋር መስጂድ ውስጥ እና በተለያዩ አካባቢዎች በሸገር ከተማ በመንግስት አካላት በፈረሱ መስጂዶች ጉዳይ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ተቃውሞ የጸጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ የሁለት ሰዎ ህይወት ማለፉን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ግንቦት 23 እና 24 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጡት መግለጫ ማረጋገጣቸው ይታወሳል፡፡

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Call +251921256367 or 0987971996
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

አስቸኳይ መልዕክት ለመንግስት የፀጥታ ኃይሎች

በታላቁ አንዋር መስጂድ የጁምዓ ሰላቱን ለመስገድ ከቤቱ የወጣን እና በመስጂድ ያለን ንፁሃን ህዝበ ሙስሊም ላይ ያለምንም ርህራሄ በጥይት የሀይል እርምጃ መውሰድ ኢ ሰብዓዊ ተግባር ነው::

ባዶ እጁን ለሰላት በወጡ ንፁሀን ላይ እየተወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ የፀጥታ ኃይሎች ያቆሙ ዘንድ አሳስባለሁ።

በመስጂዱ ተጠልለው የሚገኙ እና ያለህራሄ በጥይት ተመትተው በመስጂዱ ውስጥ እና ዙሪያውን ወድቀው የሚገኙት ወንድሞቻችን በአስቸኳይ ወደ ህክምና ቦታ ይወሰዱ ዘንድ አምቡላንስ ወደ ቦታው እንዲገባ መንገዱን ክፍት ልታደርጉ ይገባል።

@Yenetube @Fikerassefa
ዘመነ ካሴ ነፃ ነህ መባሉ ተሰማ!

መስከረም ወር 2015 በቁጥጥር ሥር የዋለው ዘመነ ካሴ፤ ዛሬ ግንቦት 25 /2015 በባህርዳር ከተማ እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት “ነፃ ነህ” መባሉ ተሰምቷል።።ዘመነ ካሴ በመስከረም ወር በቁጥጥር ሥር ውሎ መስከረም 23/ 2015 በባህርዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ የ7 ቀናት ቀጠሮ ተሰጥቶት እንደነበር የሚታወስ ነው።

ምርመራውን የያዘው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን "በተሰጠኝ 10 ቀናት ውስጥ ምርመራዬን ማጠናቀቅ አልቻልኩም" በማለት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል።የዘመነ ካሴ ጠበቆችም ወንጀል የተባለውን ጉዳይ ለማጣራት በሚል ፖሊስ ላለፉት አራት ወራት ያጣራ በመሆኑ እና ፍርድ ቤቱ ባለፈው ችሎት ውሎ የፈቀደው 10 ቀናት በቂ መሆኑን እና ሌሎችን መከራከሪያዎች አቅርበዋል፡፡ ስለዚህም ”የጊዜ ቀጠሮ መስጠት አያስፈልግም“ በማለት ተከራክረው ዘመነ ካሴ በዋስ እንዲለቀቅ ለፍርድ ቤቱ ጠይቀዋል።

የምርመራ ቡድኑ ያቀረበው ምክንያት በቂ አይደለም ያለው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ መርማሪ ቡድኑ ከጠየቀው 14 ቀናት ውስጥ የ7 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ በመስጠት ፖሊስ እስከ ጥቅምት 01/2015 ድረስ ምርመራውን እንዲያጠናቅቅ ትዕዛዝ ተሰጥቶት፤ ዘመነ ካሴም ወደ ባህርዳር ማረሚያ ቤት መመለሱን ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል።"በከባድ የሰው መግደል ወንጀል" ተከሶ የነበረው የዘመነ ካሴ ጠበቆች የክስ መቃወሚያ ማቅረባቸውን ተከትሎ፤ ዐቃቤ ሕግ መልስ ለመስጠት የክስ ችሎት ለማሰማት ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱም አይዘነጋም።

ፍርድ ቤቱም ዐቃቤ ሕግ በጠየቀው መሠረት ለኅዳር 12/2015 ቀን ዘጠኝ ሰዓት በድጋሜ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ፤ ዘመነ ካሴ ለፍርድ ቤቱ የቃልና የጽሑፍ አቤቱታን እንዲያቀርብ ተደርጓል።በመጨረሻም ዛሬ ግንቦት 25 /2015 ቀን ሰባት ሰዓት በዋለው ችሎት፤ ዘመነ ካሴ ከወንጀል ነፃ ነህ መባሉ ተሰምቷል።ይህ ዘገባ እስተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ዘመነ ከማረሚያ ቤት እንዳልወጣ ማወቅ ተችሏል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
Photo
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ በአንዋር መስጅድ በደረሰው "ሁከት" እና "አለመረጋጋት" ጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት ርምጃ "ከፍተኛ ጉዳት" መድረሱን መረዳቱን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በሸገር ከተማ አስተዳደር የመስጅዶች መፍረስ "ሙስሊሙን ኅብረተሰብ አስቆጥቷል" ያለው ጉባኤው፣ ጸጥታ ኃይሉ "የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅ ተግባሩን በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያከናውን" ጥሪ አድርጓል።

ጉባኤው፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ችግሩን ከመንግሥት ጋር ተነጋግሮ እስኪፈታ ሙስሊሞች በትዕግሥት እንዲጠብቁም ጠይቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኢትዮጵያ አየር መንገድ “የመዘዋወር መብት ገድቧል” በሚል ተከሠሠ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ “አድሏዊ አሠራር ተከትሏል” በሚል ክሥ ቀረበበት፡፡ አየር መንገዱ በበኩሉ፣ የፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደሌለ ጠቅሶ ምላሽ ሰጥቷል፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከትግራይ ክልል ተነሥተው ወደ ዐዲስ አበባ የሚጓዙ የትግራይ ተወላጆችን የመዘዋወር መብት ገድቧል፤ ሲል፣ “ቅድሚያ ለሰብአዊ…
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትግራይ የሚነሱና ወደ ትግራይ የሚጓዙ መንገደኞች ላይ "ብሄርን፣ ጾታንና የትኬት ዋጋን መሠረት ያደረገ አድልዖ ይፈጽማል" ተብሎ የቀረበብኝ ውንጀላ "ሐሰተኛ ውንጀላ ነው" ሲል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስተባብሏል።

በፌደራል መንግሥቱና ሕወሃት መካከል የተደረሰውን የግጭት ማቆም ስምምነት ተከትሎ፣ ታህሳስ 20 ላይ ወደ መቀሌ ከዚያም ወደ ሽሬ ከተሞች በረራ መጀመሩን የጠቀሰው አየር መንገዱ፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ሁለቱ ከተሞች በቀን ዘጠኝ በረራዎችን እያደረገ መኾኑን ገልጧል። አየር መንገዱ "ብሄርን፣ ጾታንና ዕድሜን መሠረት ያደረገ አድልዖ" እንደማያደርግና መንገደኞችን የብሄር ማንነት ሰነድ እንደማይጠይቅ ገልጧል። አየር መንገዱ የመንገደኞችን ፍላጎት እያጠናኹ ወደፊት ወደ ክልሉ የማደርገውን በረራ እጨምራለኹ በማለትም ቃል ገብቷል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ በአንዋር መስጅድ በደረሰው "ሁከት" እና "አለመረጋጋት" ጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት ርምጃ "ከፍተኛ ጉዳት" መድረሱን መረዳቱን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በሸገር ከተማ አስተዳደር የመስጅዶች መፍረስ "ሙስሊሙን ኅብረተሰብ አስቆጥቷል" ያለው ጉባኤው፣ ጸጥታ ኃይሉ "የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅ ተግባሩን በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያከናውን" ጥሪ አድርጓል።…
ከፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የተሰጠ መግለጫ

ህዝበ ሙስሊሙ ለሀገራችን ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ጽኑ እምነት ያለው፣ ሀገር እየጠበቀ፣ እየገነባና የራሱን ድርሻ እያበረከተ መሆኑ ይታወቃል።

ሰሞኑን መስጅዶች ፈርሰዋል በሚል ምክንያት በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም የፀጥታ አካላት የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ መስዋዕትነት ከፍለው የከተማውን ሰላም ማረጋጋታቸው የሚታወቅ ነው።

ሌላ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስም የአዲስ አበባ ፖሊስ የከተማውን ሰላምና ደህንነት ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በሰጠው መግለጫ ማሳሰቡ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ መስጅዶች የተካሄደው የጁምአ ሶላት በሰላም ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቶች ያስተላለፉትን ሰላማዊ መልዕክት በመተላለፍ በታላቁ አንዋር መስጅድ የጁምዓ ሶላት በሰላም ተጠናቆ ህዝብ ሙስሊሙ እየተመለሰ ባለበት ሁኔታ ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ የሴራ ቡድኖች የሰላቱን ሰላማዊ ሥነ-ሥርዓት ለማስከበር በተሰማሩ የፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት ለማድረስ በተነሳ ረብሻ የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በተወሰኑ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።

በንብረት ላይም እስከ አሁን ግምቱ ያልተወቀ ኪሳራ የደረሰ ሲሆን ለፀጥታ ሥራ በተሰማሩ 63 የፖሊስ አመራር እና አባላት ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

ፀረ-ሰላም ኃይሎች የእምነቱ ተከታዮች በህጋዊ መንገድ ያቀረቡትን ጥያቄ በመጥለፍ የራሳቸውን እኩይ ዓላማ ለማሳካት ረብሻውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማዛመት ያደረጉት ጥረት የፀጥታ ኃይሉ፣ ህዝበ ሙስሊሙ እና የሀይማኖቱ አባቶች በጋራ በመሆን ባደረጉት ርብርብ መቆጣጠር ተችሏል፡፡

ግብረ-ኃይሉ የከተማውን ብሎም የሀገራችንን ሠላምና ደህንነት ለማስከበር የጀመረውን ህግ የማስከበር ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እየገለፀ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት እና በህገ-ወጥ ተግባሩ ላይ የተሳተፉ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ በመቀጠል በቀጣይ ውጤቱን ለህዝቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ሰላም የሁሉም የእምነት ተቋማት የአስተምሮታቸው መሠረት በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ የሚያነሳውን ማንኛውንም ጥያቄ በህግ አግባብ በሰላማዊ መንገድ ማስተናገድ የሚቻልበት ሥርዓት መኖሩን በመገንዘብ ለፀረ-ሠላም ኃይሎች መጠቀሚያ ሳይሆን የፀጥታ አካላት የከተማውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት በመደገፍ ህዝበ ሙስሊሙ የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይሉ ጥሪውን ያቀርባል።

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል
ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
1
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🌕ድርጅታችን ከታች በተዘረዘሩ የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል። 

🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥NGO በማንኛውም

     🔹የት/ደረጃ:ዲፕሎማ/ድግሪ
     🔹የስራ ልምድ: 0 ዓመት
     🔹ደሞዝ: 18,500+

💥ሹፌር በሁሉም

     🔹የት/ደረጃ:መፃፍ ማንበብ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:13,500+

💥ስልክ ኦፕሬተር

     🔹የት/ደረጃ: 10 ጀምሮ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 6500

💥ጉዳይ አስፈፃሚ

     🔹የት/ደረጃ:10
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:7000

💥ባንክ ቤት ፅዳት ተላላኪ

    🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ፡4500

💥አካውንታንት

🔹የት/ት ደረጃ= ድግሪ/ድፕሎማ
🔹 ልምድ = 0-2 አመት
🔹ደሞዝ=8500

💥ካሸር አሰልጥኖ

🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500

💥ባርማን/ባሬስታ

🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት

💥 ዌተር የጧት እና የከሰዓት

     🔹የት/ደረጃ: 10 ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 3500


💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች

     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,000

💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)

🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
👍1
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Call +251921256367 or 0987971996
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel
በሕንድ የባቡር አደጋ ከ280 በላይ ሰዎች ሞቱ!

በሕንድ ምሥራቃዊ ኦዲሻ ግዛት፣ ባላሶሬ በሚባል አውራጃ ሁለት በተለያየ መስመር የሚዘወሩ ባቡሮች ተላትመው 288 ተሳፋሪዎች ሲሞቱ 850 የሚሆኑት ቆስለዋል።አደጋውን ተከትሎ 200 አምቡላንሶች ወደ ስፍራው የተንቀሳቀሱ ሲሆን ከአደጋው የተረፉ ተሳፋሪዎች የከፋ ጉዳት የደረሰባቸውን ሌሎችን ለማዳን ሲረባረቡ ታይተዋል።

አደጋው የደረሰው ትናንት ዐርብ ሲሆን አንድ የመንገደኞች ባቡር መስመሩን ስቶ ከወጣ በኋላ በሌላ ከተቃራኒ አቅጣጫ እየከነፈ ይመጣ በነበረ ባቡር መገጨቱን ተከትሎ ነው በርካታ ሰዎች ሊጎዱ የቻሉት።

ይህ አደጋ በሕንድ በዚህ 21ኛው ክፍለ ዘመን ከደረሱ የባቡር አደጋዎች የከፋው ነው ተብሏል።የአካባቢው ባለሥልጣናት የሟቾች ቁጥር አሁን ካለበት በብዙ ሊያሻቅብ እንደሚችል ሰግተዋል።የሕንድ የባቡር አስተዳደር እንዳለው በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ኮሮማንዴል ኤክስፕረስ እና ሆውራሽ ሱፐርፋስት ኤክስፕረስ ባቡሮች ናቸው።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
"በሰሜን አትዮጵያ ጦርነት የወደመወን፣ መልሶ ለመገንባት ኢትዮጵያ አቅም የላትም" - ነእፓ

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ "ድህረ ጦርነት ማገገሚያ ፕሮግራም በኢትዮጵያ " በሚል ፕሮግራም ግንቦት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ሲቪል ማህበራት እና ባለድርሻ አካላት ውይይት አካሂዷል።በውይይቱም የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ሊቀመንበር አብዱልቃድር አደም(ዶ/ር) "ሁለት አመት የዘለቀው የሰሜኑ ኢትዮጵያ ጦርነይ በትግራይ ቢቀሰቀስም ወደ አማራና ወደ አፋር ክልሎች መዛመቱን › አስታውሰዋል፡፡

በዚህም ‹ በክልሎቹ የሚገኝ በመቶሺ የሚቆጠሩት ሞተዋል፤ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ደግሞ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን › የገለፁት ሊቀመንበሩ ‹ አሁንም ድረስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናት ከትምህርት ርቀው እንደሚገኙ › ጠቁሟል፡፡እንደ ሊቀመንበሩ ከሆነ ‹ በጦርነት የወደመውን መልሶ መገንባት ኢትዮጵያ ካላት ሃብት በላይ ነው፡፡›በውይይቱ ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት 15ኛ መደበኛ ጉባዔ የተቋቋመው የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
በራያ አላማጣ የሚገኙ ስድስት ወረዳዎች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ ሊያስገቡ መሆኑ ተገለጸ!

​​በራያ አላማጣ የሚገኙ ስድስት ወረዳዎች በዋናነት በጀት እንዲለቀቅላቸው የሚጠይቅና በፊርማ የተደገፈ አቤቱታ በቀጥታ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊያስገቡ መሆኑ ተገልጿል።ለዚህም ከኹለት ሳምንት በፊት ተደርጓል የተባለው ፊርማ የማሰባሰብ ዘመቻ በዋግኽምራ ዞን ሥር ባሉ ኮረም፣ ዛታ፣ ወፍላ ወረዳዎች እንዲሁም፤ በሰሜን ወሎ ዞን ሥር በሚገኙ አላማጣ፣ ራያ አላማጣ እና ራያ ባላ ወረዳዎች መከናወኑን የኮረም ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ገብረእግዚአብሔር ደረጀ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም የወሰንና የማንነት ጥያቄ ከአራት ዓመት በፊት ለፌዴሬሽን ምክር ቤቱ መግባቱን ጠቅሰው፤ "አሁን የሚላከው አቤቱታ ዋና ዓላማው የአካባቢው በጀት ወደ ትግራይ ሳይሆን ወደ አማራ ክልል እንዲገባ ለመጠየቅ ነው።" ብለዋል።

"ከሕዝቡ የተሰበሰበው በፊርማ የታገዘ አቤቱታ ተደራጅቶ ወደ ምክር ቤቱ መላክ ነው የቀረው" ያሉት ኃላፊው፤ "በኮረም ከተማ የተደረገው ጥናት 74 በመቶ የሚሆኑት ወደ አማራ ክልል መካለል የሚፈልጉ መሆናቸውን አመላክቷል።" ሲሉ ተናግረዋል።11 በመቶ የሚሆኑት መሀል ላይ የሚወላውሉ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ቀሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እንካለል ያሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አላማጣ ላይ ደግሞ 90 በመቶ የሚሆኑ ነዋሪዎች በአማራ ክልል ሥር መጠቃለልን የሚፈልጉ መሆናቸውንም አስረድተዋል። ኃላፊው አቤቱታው በቅርቡ ለምክር ቤቱ እንደሚገባም አመላክተዋል።"2010 ገደማ ያስገባነውን የማንነት ጥያቄ ምክር ቤቱ እያየው እንደሆነ እናምናለን፣ በአሁኑ አቤቱታ የምንጠይቀው በጀቱ ወደ አማራ ክልል ገብቶ ወደ ወረዳዎች እንዲተላለፍ፤ የባንክ፣ የቴሌኮሙኒኬሽን እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት የአሰራር ሥርዓቱም ወደ አማራ ክልል እንዲዞር ነው።" ሲሉ ተደምጠዋል።

ኃላፊው በጀት ባለመለቀቁ ለመንግሥት ሠራተኞች በቂ ደሞዝ እየተከፈለ አለመሆኑን ጠቅሰው፤ የፌዴራል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አሰራር ወደ አማራ ክልል ባለመዞሩ ምክንያት፣ ለአብነት የመብራት ቆጣሪ እንደማያነብ ገልጸዋል።ነዋሪዎቹ "መንግሥት ጥያቄያችን በአስቸኳይ ሊፈታልን ይገባል" የሚል ሰልፍ አድርገው እንደነበር የገለጹ ገብረእግዚአብሔር፤ የማንነት ጥያቄያቸው ስላልተመለሰ በበጀት ላይ የሚያቀርቡት ጥያቄም መልስ እንዳላገኘ ጠቁመዋል፡፡

"የሕወሓት መሪዎች "አካባቢው የትግራይ ክልል አካል ነው።" በማለት በጀት እየጠየቁ ይገኛል፣ እኛም እየጠየቅን ነው። ይህ የሚፈታው ግን ለመንግሥት ያቀረብነው የማንነት ጥያቄ መልስ ሲሰጠው ነው።" ሲሉ ጠቁመዋል።ነዋሪዎቹ የራያ ግዛቶች ከ1984 በፊት በዋግኽምራ እና በራያ ቆቦ አውራጃ ይተዳደሩ እንደነበር ጠቁመው፤ ለረዥም ጊዜ የምናነሳው የማንነት ጥያቄ በአግባቡ ሊመለስልን ይገባል ብለዋል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
አስተያየታችሁን እንሻለን

ሰላም እንዴት ዋላችሁ በዚህ ቻናል ብዙ ዘመን አብረን ስንብተናል ቆይተናል ለአምስት አመታት ያህል አብረን ቆይተናል።

እንደ ቻናል አድሚን ብዙ አይነት መልእክቶች ይደርሱና ከዛ ውስጥ ያመንነበትን እናስተናግዳለን።

ከዚህ በፊት ብዙ የተጎዱ እንዲሁም የተቸገሩ  ሰዎችን በትንሹ ፖስት በማድረግ እንዲሁም ባለን አቅም ወደ አካውንት በማስገባት  የምንችለውን እያደረግን ቆይተናል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ በቻናላችን በኩል የሚላኩልን በህመም ምክንያት ሀገር ውስጥ መታከም የማይችሉ ህሙማን ፣ የተቃጠሉ ቤተክርስቲያን፣ በተለያዩ ምክንያቶች የተቃጠሉ እንዱሁም የፈረሱ መስጂዶችን ለማሰራት ብር ማሰባሰቢያ አካውንቶች ሲላኩልን ከርመዋል።

ቻናላችን የኔቲዩብ ቤተሰቦች ምንም እንኳን የመርዳት ፍላጎት ያላቸው ቢሆንም ሁሉንም መልቀቅ ስለማንች አንድ መፍትሄ አዘጋጅቷል።

ልክ እንደ Gofundme አይነት የኔቲዩብ የራሱን የሆነ ሲስተም በማበልፅግ ላይ እንደ ሆነ ለማብሰር እንወዳለን እንዲሁም ሲስተማችን በሰዓታት ውስጥ በቀጥታ ወደ ሚሰበሰብበት አካውንት እንዲገባ የሚያስችል ሲስተም እየተሰራ እና ወደ እናንተ ለማቅረብ በሂደት ላይ መሆናችችን ለማብሰር እንወዳለን።


ምን ያህሎቻችሁ ናቸው ሀሳባችንን የወደዳችሁት??

እያበለፅግን ያለውን ፈንድራይዚንግ(fundraising) ሲስተማችን ስም በትክክል ለገመቱ ሽልማት አዘጋጅተናል።
መንግስት < በደብረ ኤሊያስ ሥላሴ ገዳም እርምጃ የወሰዱሁት እስክንድር ነጋንና ግብረ አበሮቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው > አለ።

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ግንቦት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ባወጣው መግለጫ <በደብረ ኤሊያስ ገዳም ሳካሂድ ቆይቻለሁ > ያለው < ወታደራዊ ዘመቻ ዓላማው እስክንድር ነጋ ላይ እርምጃ ለመወሰድ መሆኑን > አረጋግጧል።የጋራ ግብረሀይሉ በመግለጫው < በጎጃም ደብረ ኤልያስ ሥላሴ ገዳም መሽገው መንግሥትን በትጥቅ ትግል ለመጣል ሲንቀሳቀሱ > ነበሩ ባላቸው <እስክንድር ነጋና ግብረዓበሮቹ ላይ በተወሰደው እርምጃ ክልሉን የማተራመስ ሴራቸው ከሽፏል > ብሏል።

መግለጫው አክሎም < በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ የሚገኘውን የሥላሴ ገዳም ከለላ በማድረግ መንግሥትን በትጥቅ ትግል ለመጣል ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ጥቂት ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ እርምጃ ተወደስዷል> ሲል ይፋ አድርጓል።በዚህም <በእስክንድር ነጋና በግብረዓበሮቹ ለውጊያ ሲውል የነበረው ምሽግ መሰበሩንና በ200 ታጣቂዎችም ላይ እርምጃ መወሰዱን > አስታውቋል፡፡

<የታጣቂ ቡድኑ መሪና አስተባባሪ የነበረው > ያላቸው <እስክንድር ነጋና ጥቂት ግብረዓበሮቹ ከአካባቢው ለመሰወር ቢሞክሩም በዋናነት የመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ለማዋል እግር በእግር በመከታተል የተቀናጀ ኦፕሬሽን እያካሄዱ መሆኑንም > አመልክቷል።

<ግለሰቡ[እስክንድር] ይህ እንዳልተሳካለት ሲያውቅ፤ መንግሥትን በኃይል ለመጣል በማቀድ የአማራ ሕዝባዊ ግንባር የተባለ አደረጃጀት በመፍጠር ሽመልስ ስማቸው፣ ሰውመሆን ወረታውና መንበሩ ካሴ ከተባሉ ግብረዓበሮቹ እንዲሁም ከሌሎች ጥቂት የክልሉ ጽንፈኛ ኃይሎች ጋር በመቀናጀትና በህቡዕ በመንቀሳቀስ ታጣቂዎችን ሲመለምል፣ ሲያደራጅና ስምሪት ሲሰጥ ነበር > ሲል ወንጅሏል።

< ግንባሩን በሀገር ውስጥ ራሱ ሲመራ በውጭ ደግሞ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ የተባለ ግለሰብ ያስተባብራል > ሲል የገለፀው መግለጫው፤ < ሁለቱ በፈጠሩት ትስስር በክልሉ የትጥቅ ትግል በማድረግ ሕዝቡን ወደማያባራ ጦርነት ለማስገባት ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል > ሲል ከስሷል።

<የሃይማኖት ሽፍንና እንደ ከለላ ለመጠቀም ከሌሎች የቡድኑ ታጣቂዎች ጋር ወደ ምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ በማቅናት ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ በሥላሴ ገዳም አካባቢ ምሽግ ቆፍረው መንግሥትን በትጥቅ ትግል ለመጣል በህቡዕ ሲያሴሩ እንደነበርም > መግለጫው አስታውሷል።

<በተለይ የገዳሙ አስተዳዳሪ የሆኑትን አባ ኤልሳን ለዚህ ሕገወጥ ተግባር ሲጠቀሙ ነበር > ብሏል።< አስተዳዳሪውም ከሃይማኖቱ አስተምህሮ ውጭ በገዳሙ ውስጥ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴ እንዲደረግ ከመፍቀድ ባሻገር ከሌሎች መነኮሳት ጋር በማበርና የጦር መሣሪያ ጭምር በማንገብ ከጽንፈኛ ቡድኑ አባላት ጋር ተሰማርተው ነበር > ሲል ወንጅሏቸዋል።

<የጥፋት ቡድኑ አባላት ሕገ ወጥ እንቅስቃሴውን እንዲያቆሙና በውይይት ወደ ሰላም እንዲመጡ ከክልል እስከ ወረዳ በሚገኙ አካላት ተደጋጋሚ ጥረት > እንዳደረገ የሚገልፀው መግለጫው ይህ ግን ፍሬያማ ሊሆን እንዳልቻለ አስታውቋል።

<200 የጽንፈኛ ቡድኑ አባላት ታጣቂዎች መደምሰሳቸውነና የቀሩትም ከመማረካቸውና ከመሸሻቸው ውጪ፤ ቡድኑ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በሚነዛባቸው የማኅበራዊ ትስስር ገፆች በመንግሥት ጸጥታ አካላት በገዳሙና በምዕመናን ጉዳት እንዳደረሰ ተደርጎ የሚሠራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው > ሲል አጣጥሏል።

መግለጫው በመቋጫው <በቀጣይም ክልሉ ከጥቂት ጽንፈኛ ኃይሎች ጸድቶ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲሰፍን ለሚደረገው ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ ኅብረተሰቡ የጋራ ጥረቱንና አጋርነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል > ጥሪ አስተላልፏል፡፡

[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa
"ተቃውሞ አቀናጅታችኋል" የተባሉ ወጣቶች ከየቤቱ ታድነው እየታሰሩ መሆኑ ተገለጸ

እስከአሁን የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነግሯል


ባሳለፍነው አርብ በአዲስ አበባ ከተማ፣ መርካቶ በሚገኘው አንዋር መስጊድ አካባቢ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በአማኙ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት፤ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ስምንት ሰዎች ሲሞቱ፤ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁት ደግሞ ከፍተኛ እና መካከለኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዘመድኩን ብሩ፤ "በዕለቱ ከጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል" ሲሉ ለአዲስ ማለዳ የገለጹ ሲሆን፤ ከሟቾች መካከልም አንድ ግለሠብ መታወቂያ ባለመያዙ ምክንያት እስከአሁን ማንነቱ ሊታወቅ አለመቻሉን አስረድተዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም፤ "ሰልፍ አቀናጅታችኋል" የተባሉ ወጣቶች ከየቤቱ ታድነው እየታሰሩ መሆኑን በመግለጽ፤ "ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል" ሲሉ ተናግረዋል።

ሟቾችን ለመቅበር የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ መዋቀሩን የተናገሩት ኃላፊው፣ ትናንት ቅዳሜ ግንቦት 26/2015 ኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መካነ መቃብር የአራት ምዕመናን ሥርዓተ ቀብር መፈጸሙን ገልጸዋል፡፡ የቀሩትንም ወደ ትውልድ ሥፍራቸው በአስቸኳይ ለመሸኘትና ማንነቱ ያልታወቀውን ምዕመን ማንነት ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

"በተለያዩ ሚዲያዎች ሕዘበ ሙስሊሙ ምንም ዓይነት የተቃውሞ ድምጽ ሳያሰማ በሰላም ሰግዶ ሲወጣ ከጸጥታ ኃይሎች ተኩስ እንደተከፈተበት የሚወራው እውነት ነው ወይ?" የሚል ጥያቄ ከአዲስ ማለዳ ቀርቦላቸውም፤ "እሱን ገና በማጣራት ላይ ነን" ሲሉ መልሰዋል፡፡

በተያያዘ በዕለቱ፤ በጅማ ከተማ በተለያዩ መስጅዶች ተመሳሳይ ችግሮች ተፈጥረው እንደነበር በሥፍራው የነበሩ የአዲስ ማለዳ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ለአብነትም መንቲና ወይም ሰቃ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ሙኒር መስጂድ፣ አጂፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ፈቲ መስጂድ እንዲሁም ሀሰን ጋራዥ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ራሕማ መስጂድ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ነግረውናል፡፡

በሥፍራው ከጠዋት ጀምሮ የጸጥታ ኃይሎች በብዛት ይታዩ እንደነበር የነገሩን የመረጃ ምንጫችን፣ የእምነቱ ተከታዮች ሰግደው ሲወጡ ከሰሞኑ እየፈረሱ ስላሉት መስጂዶች ድምጻቸው ማሰማታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህ ሰዓት በአካባቢው የነበሩት የጸጥታ አካላት የተኩስ ድምጽ ማሰማታቸውን የነገሩን ሲሆን፤ በዚህ የተደናገጡት የእምነቱ ተከታዮች ለመሸሽ በሚያደረጉት ጥረት በርካታ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡

በሐረር፣ ሻሸመኔ እና ዶዶላ ከተሞችም መሰል ችግሮች ተከስተው እንደነበር በሥፍራው የሚገኙ ቤተሰቦቻችን ዘግበዋል ሲል አዲስ ማለዳ ዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
1👍1
በየቲዩብ በኩል ለሚበለፅገው ለተቸገሩ ህሙማን፣ ድርጅቶች እንዲሁም ቤተክርስቲያናት ፣ መስጂዶች ገንዘብ ማዘባሰቢያ ፕላትፎርም የኔቲዩብ ቤተሰብች መርዳት ለሚፈልጉት እንዲሁም በግልም በመንቀሳቀስ እንደ Gofundme እርዳት ማግኘት የሚያስችል ፕላትፎርም ስም አውጡልን ባልነው መሰረት ብዙ ሰው የተሳተፈ ቢሆንም ያልሰማ አለ እና አሁንም በድጋሚ ለምለቀቅ ተገደናል።

ማን ይሁን ስማችን
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🌕ድርጅታችን ከታች በተዘረዘሩ የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል። 

🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥NGO በማንኛውም

     🔹የት/ደረጃ:ዲፕሎማ/ድግሪ
     🔹የስራ ልምድ: 0 ዓመት
     🔹ደሞዝ: 18,500+

💥ሹፌር በሁሉም

     🔹የት/ደረጃ:መፃፍ ማንበብ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:13,500+

💥ስልክ ኦፕሬተር

     🔹የት/ደረጃ: 10 ጀምሮ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 6500

💥ጉዳይ አስፈፃሚ

     🔹የት/ደረጃ:10
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:7000

💥ባንክ ቤት ፅዳት ተላላኪ

    🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ፡4500

💥አካውንታንት

🔹የት/ት ደረጃ= ድግሪ/ድፕሎማ
🔹 ልምድ = 0-2 አመት
🔹ደሞዝ=8500

💥ካሸር አሰልጥኖ

🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500

💥ባርማን/ባሬስታ

🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት

💥 ዌተር የጧት እና የከሰዓት

     🔹የት/ደረጃ: 10 ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 3500


💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች

     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,000

💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)

🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
ካናዳ 🇨🇦 የትምህርት እድል ማግኘት በጣም ቀላል ሆኗል Eyob Travel Consultancy ህልዎን ለማሳካት ተዘጋጅቷል
ከናንተ የሚጠበቀው በተጠቀሱት አድራሻዎች መፃፍ ወይንም መደወል ነው

Telegram channel ይቀላቀላሉ
https://tttttt.me/eyob_travel_consultancy

Telegram : @Eyobtravel
Call +251921256367 or 0987971996
Facecook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100093020628881&mibextid=ZbWKwL

Tiktok: tiktok.com/@eyobtravel