YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🌕ድርጅታችን ከታች በተዘረዘሩ የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል። 

🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥NGO በማንኛውም

     🔹የት/ደረጃ:ዲፕሎማ/ድግሪ
     🔹የስራ ልምድ: 0 ዓመት
     🔹ደሞዝ: 18,500+

💥ሹፌር በሁሉም

     🔹የት/ደረጃ:መፃፍ ማንበብ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:13,500+

💥ስልክ ኦፕሬተር

     🔹የት/ደረጃ: 10 ጀምሮ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 6500

💥ጉዳይ አስፈፃሚ

     🔹የት/ደረጃ:10
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:7000

💥ባንክ ቤት ፅዳት ተላላኪ

    🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ፡4500

💥አካውንታንት

🔹የት/ት ደረጃ= ድግሪ/ድፕሎማ
🔹 ልምድ = 0-2 አመት
🔹ደሞዝ=8500

💥ካሸር አሰልጥኖ

🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500

💥ባርማን/ባሬስታ

🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት

💥 ዌተር የጧት እና የከሰዓት

     🔹የት/ደረጃ: 10 ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 3500


💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች

     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,000

💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)

🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
በትግራይ በጦርነቱ ወቅት የወጡ ሕጎች እንዲሻሩ ተጠየቀ!

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል፣ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ከመፈረሙ በፊት፣ ህወሓት ልዩ ልዩ የአስቸኳይ ጊዜ ሕጎች ደንግጎ እንደነበር ያስታወሰው ፓርቲው፣ ኾኖም ሒደቱ፣ ሕጋዊነትን የተከተለ እንዳልነበረና የሕጎቹ ይዘትም፣ ከክልሉ እና ከፌዴራሉ ሕገ መንግሥቶች ጋራ እንደማይጣጣም ገልጿል፡፡ ሕጎቹ ሥራ ላይ በዋሉባቸው ጊዜያትም፣ የተለያዩ ችግሮች ማስከተላቸውን ፓርቲው አመልክቷል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ እነዚኽን ሕጎች እንዲሽራቸው የጠየቀው ፓርቲው፣ ካልሆነ ግን፣ ጉዳዩን ወደ ሕገ መንግሥት አጣሪ አካል እንደሚወሰደው፣ የፓርቲው የሕግ እና የሥነ መንግሥት ክፍል ሓላፊ አቶ ተስፋኣለም በርኸ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ፣ ከትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ አስተያየት ለማግኘት የተደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ ከፍተኛ የሥራ ሓላፊ ግን፣ ቢሮው ሕጎቹን እየሻረ፣ ወደ መደበኛው የፍትሕ አሠራር ለመግባት እንቅስቃሴ መጀመሩንና በሕጎች ተከሠው ስለተፈረደባቸው ሰዎችም፣ የባለሞያዎች ቡድን ተቋቁሞ ጥናት እያደረገ እንደኾነ ጠቁመዋል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የመንግሥት የጸጥታ አካላት ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን እንዲያከብሩ ተጠየቀ!

የመንግሥት የጸጥታ አካላት ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን በተገቢው ሁኔታ እንዲያከብሩና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች ላይ ከመፈጸም እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ጠየቀ፡፡

ተቋሙ ይህን ያለው በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ ግንቦት 18/2015 ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል በመጠቀም የተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን መፈጸማቸውን ለመግለጽ ትናንት ግንቦት 23/2015 ባወጣው መግለጫ ነው፡፡

በዚህ ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ የሰው ሕይወት መጥፋቱን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ንብረት መውደሙንና በእምነቱ ተከታዮች ላይ እስራት መፈጸሙን አሰመጉ ገልጿል፡፡ ይህን የፈጸሙ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ላይ መንግሥት ተገቢውን ማጣራት በማድረግ በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርግም ጠይቋል፡፡

ኢሰመጉ በመግለጫው ‹‹በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ያለው የቤት ፈረሳ እንቅስቃሴ የኃይማኖት ተቋማትንም የጨመረ ነው፡፡ ከኦሮሚያ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ከ19 በላይ መሰጊዶች መፍረሳቸውን ለመረዳት ችያለሁ›› ብሏል፡፡

ስለሆነም እየተፈጸሙ ያሉ መስጂዶችን የማፍረስ እንቅስቃሴዎች፤ በሰዎች የኃይማኖት፣ የእምነትና የአመለካከት ነጻነት መብት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ የሚፈጥሩ መሆናቸውን በመግለጽ፤ የፈረሳ እንቅስቃሴዎችን በማቆም ከእምነቱ ተከታዮችና መሪዎች ጋር ተገቢውን ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ እንዲደረስ አሳስቧል፡፡

እንዲሁም፤ መንግሥት የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶችን እንዲያከብር የጠየቀው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ፤ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ እየተፈጸሙ ስላሉ የቤት ፈረሳና የግዳጅ ማፈናቀል እንቅስቃሴዎች ዝርዝር ዘገባ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ጠቁሟል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነቱ ወዲህ በምዕራብ ትግራይ ተወላጆች ላይ የዘር ማፅዳት ዘመቻ መቀጠሉን ሂዩማን ራይትስ ዎች አስታወቀ።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ሂዩማን ራይትስዎች በፌደራሉ መንግስትና በህወሓት መካከል የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኃላ ምዕራብ ትግራይ እያለ በጠራው አካባቢ የሚገኙ ባለስልጣናትና የአማራ ሃይሎች የዘር ማፅዳት ዘመቻ እያካሄዱ ነው ሲል ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት በምዕራብ ትግራይ ከፍተኛ የመብት ረገጣ ላይ የተሳተፉ የጸጥታ ሃይሎችንና ባለስልጣናትን ማገድ፣ መመርመርና ለህግ ማቅረብ እንዳለበት አስታውቋል።

አክሎም ከቤታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የመመለስ መብት እንዳላቸው አለም አቀፉ ህግ ቢደነግግም አሁን ላይ በምዕራብ ትግራይ ያለው ሁኔታ ምቹ አለመሆኑን ገልጿል፡፡ሂዩማን ራይትስ ዎች ቀደም ሲል ባደረገው ጥናት በደል ሲፈፅሙ የነበሩ ሲል በስም የጠቀሳቸው ባለስልጣናት አሁንም ድረስ በዘፈቀደ በማሰርና በማሰቃየት ላይ ይገኛሉ ሲል ሪፖርት አመልክቷል፡፡የሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ላቲሺያ ባደር በዞኑ በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው የዘር ማፅዳት አላበቃም ብለዋል፡፡

አክለውም የኢትዮጵያ መንግስት እውነተኛ ፍትህ የሚፈልግ ከሆነ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በገለልተኛ አካል ይመርመር መባሉን መቃወም ማቆምና ተሳታፊ የነበሩ ባለስልጣናትና አዛዦችን ተጠያቂ ማድረግ አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ለተፈጸመው ግፍ ተጠያቂ የሆኑትን ለፍርድ ለማቅረብ ፍላጎት አላሳየም ያለው ሪፖርቱ የተፈጸሙ ጥሰቶችን እንደሚያጣራ ቢገልፅም እስካሁን ድረስ ስለእነዚህ ምርመራዎች ዝርዝር መረጃ እንዳልሰጠና ለከባድ ጥሰቶች ተጠያቂነት እንዳልሰፈነ ተገልጿል።

ምንም እንኳን ገለልተኛ አካል ባይኖርም ሂዩማን ራይትስ ዎች እስካሁን ድረስ ምርመራዎችን ማድረጉን ገልፆ የእርቅ ስምምነቱ ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ መንግስታት በተጠያቂነት ላይ ተጨባጭ መሻሻል ከመፈለግ ይልቅ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ባለስልጣናት ጋር መቀራረብ ይፈልጋሉ ብሏል።ምንም እንኳን ገለልተኛ አካል ባይኖርም ሂዩማን ራይትስ ዎች እስካሁን ድረስ ምርመራዎችን ማድረጉን ገልፆ የእርቅ ስምምነቱ ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ መንግስታት በተጠያቂነት ላይ ተጨባጭ መሻሻል ከመፈለግ ይልቅ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ባለስልጣናት ጋር መቀራረብ ይፈልጋሉ ብሏል።

በሚያዝያ ወር የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ጋር ባለው የወደፊት ግንኙነት ላይ መደበኛ ድምዳሜዎችን ቢያደርግም በፍትህ ላይ የሚታየውን መሻሻል አላስቀመጠም ሲል ወቅሷል።አክሎም ከኢትዮጵያ ጋር እንደገና መገናኘቱ ለተፈጸሙት ጥሰቶች ፍትህን ከማስፈንና ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ ጋር የተያያዘ መሆን አለበት ብሏል።በዞኑ በደረሰው ከባድ በደል የተሳተፉ የአማራ ባለስልጣናትን ጨምሮ የሲቪል ባለስልጣናት ተግባራቸው እስኪጣራ ድረስ ከስራ እንዲታገዱ እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች ጭምር ለከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ተጠያቂ የሆኑትን ሁሉ በተገቢው መንገድ ለህግ እንዲቀርቡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ጠይቋል።

Asham
@YeneTube @FikerAssefa
ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት የተመሰረተው ራሚስ ባንክ የስራ ማስጀመሪያ ይፋዊ የምረቃ ፕሮግራሙን በቀጣይ እሁድ ግንቦት 27 እንደሚያከናውን አስታወቀ።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ከ60 በመቶ በላይ ማህበረሰብ ህገ መንግስቱ ስለመሻሻሉ ፍቃደኛ ነው በሚል በጥናት ተረጋግጧል ቢባልም በሀገራዊ የምክክር ኮምሽኑበኩል በጥልቀት በድጋሚ እንደሚታይ ተገለጸ፡፡

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት አከናወንኩት ባለው ጥናት ከትግራይ ክልል ውጪ 60 ከመቶ በላይ የሚሆነው ማህበረሰብ ህገ መንግስቱ እንዲሻሻል ፍቃደኛ መሆኑን አረጋግጫለው ማለቱ ይታወሳል፡፡አሐዱ ጥናቱ ለኮምሸኑ ስራ ምን ያህል አጋዥ ነው ሲል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ እና አባል ዶክተር ዬናስ አዳዬን አነጋግሮ በሰጡት ምላሽ የማህበረሰብ ጥያቄዎች እና አስፈላጊ ጉዳዮችን በተመለከተ ኮሚሽኑ በ3 መንገዶች ማለትም ከታች ወደ ላይ፤ከላይ ወደ ታች እንዲሁም ወደ ጎን መረጃ የማሰባሰብ ስራ እንደሚያከናውን ተናግረዋል፡፡

ከ60 በመቶ በላይ ማህበረሰብ ህገ መንግስቱ ስለመሻሻሉ ፍቃደኛ ነው በሚል የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩቱ ሰራሁት ባለው ጥናት ቢያሳውቅም በስፋት እና በጥልቀት በሀገራዊ የምክክር ኮምሽኑ በድጋሜ እንደሚታይ ገልጸዋል፡ሳይንሳዊ ምርምሮችና ጥናቶች እየተጠኑ ለማህበረሰቡ ይፋ መደረጋቸው ጠቃሚ ናቸው ያሉት ሀላፊው ኮሚሽኑም እንደ ግበዓት እንደሚጠቀምበት ተናግረዋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
ፀጋ በላቸው ከእገታ ነጻ መውጣቷ ተሰማ!

ከሰሞኑ እጅግ መነጋገሪያ የነበረችውና ለ10 ቀናት ያክል በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ታግታ የቆየችው ፀጋ በላቸው፤ ከአጋቿ ቁጥጥር ነጻ በመውጣት ወደ ሐዋሳ መመለሷን አዲስ ማለዳ ዘግባለች።

በጉዳዩ ላይ በአሁኑ ሰዓት የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ እና የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሸን መግለጫ እየሰጡ ሲሆን፣ አዲስ ማለዳ በቦታው ካሉ ምንጯቿ ያገኘችው መረጃ እንደሚያመላክተው፤ ጸጋ ነጻ ብትወጣም እገታውን የፈጸመው የፖሊስ አባል አለመያዙ ታውቋል፡፡

ግንቦት 15/2015 የግል ተበዳይ ፀጋ በላቸው፤ ከሥራ ወጥታ ወደ ግል ጉዳይ በምታመራበት ወቅት በተለምዶው አሮጌው መነሃሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጠለፋው እንደተፈፀመባት በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የመነሐሪያ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለአዲስ ማለዳ መግለጹ ይታወሳል።ጸጋ መታገቷ ከተሰማ በኋላ ፖሊስ ከፍተኛ ክትትል ሲዲርግ መቆየቱን የገለጸ ሲሆን፤ እሳካሁን ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የጠጠረጠሩ ስምንት ሰውች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ፀጋ በላቸው ከእገታ ነጻ መውጣቷ ተሰማ! ከሰሞኑ እጅግ መነጋገሪያ የነበረችውና ለ10 ቀናት ያክል በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ታግታ የቆየችው ፀጋ በላቸው፤ ከአጋቿ ቁጥጥር ነጻ በመውጣት ወደ ሐዋሳ መመለሷን አዲስ ማለዳ ዘግባለች። በጉዳዩ ላይ በአሁኑ ሰዓት የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ እና የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሸን መግለጫ እየሰጡ ሲሆን፣ አዲስ ማለዳ በቦታው ካሉ…
ተጨማሪ መረጃ!!

በሲዳማ ብሔራዊ ክልል የፀጥታ ግብረ ሀይል በተደረገ የተቀናጀና በቴክኖሎጂ የታገዘ ጠንካራራ ክትትል ወሪ/ት ፀጋ በላቸውን ከተጠርጣሪ ወንጀለኛ ማስመለጥ መቻሉ ተነግሯል፡፡

የፀጥታ ግብረ ሀይሉ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ የኃላመብራት ወ/ማሪያምን በቁጥጥር ስር ለማዋል ባደረገው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ከትላንት 23/09/2015ዓ.ም ጀምሮ በምስራቅ ጉጂ ዞን ቦሬ ወረዳ ጀምሮ ተጠርጣሪ ወንጀለኛውን በመከታተልና መፈናፈኛ በማሳጣት በዛሬው እለት በሻፋሞ ወረዳ ሹሮ ቀበሌ ወሪ/ት ፀጋ በላቸውን ከግለሰቡ ማስጣል ተችሏል፡፡ግለሰቡ ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ወደጫካ የገባ ቢሆንም የፀጥታ ግብረ ሀይሉ ያልተቋረጠ ክትትል በማድረግ ተጠርጣር ወንጀለኛን በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡

ለዚህ ስምሪት መሳካት ከፍተኛ አስተወጽኦ ላበረከቱ ለብሔራዊ መረጃ ደህንነት፣ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል፣ ለሻፋሞ ወረዳ አስተዳደርና የህብረተሰብ ክፍል የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮና የፀጥታ ግብረ ሀይል ልባዊ ምስጋና ያቀርባል፡፡

ተጠርጣሪ ወንጀለኛውንም በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ ለማቅረብ በጫካው ውስጥ አሰሳ እየተካሄደ ሲሆን የሚገኙ ውጤቶችን ለመላው የሀገራችንና የክልላችን ህዝቦች የምናሳውቅ ይሆናል ብሏል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ፓርቲው ከመርህ ውጪ አካሄዱን ካስተካከለ ወደ ፊት አብረው ሊሰሩ የሚችሉበት መንገድ ሊኖር እንደሚችል ከኢዜማ የለቀቁ አባላት ገለፁ፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ከኢትዮጵያ ለማህበራዊ ፍትሀ /ኢዜማ/ ፓርቲ የለቀቁ አባላት በቀጣይ ምን ለማድረግ ነው ያሰባችሁት ሲል አሐዱ ያነጋገራቸው የቀድሞ የኢዜማ ከፍተኛ አመራር እና በቅርቡ ፓርቲውን ከለቀቁ አባላት አንዱ አቶ የሺዋስ አሰፋ ፓርቲው ሲቋቋም ይዞ የተነሳው መርህ በመኖሩ፣ ከፓርቲው መርህ ውጪ የወጣው አካል ነው ወደ አባላቱ እና ህዝብ መመለስ ያለበት ብለዋል፡፡

ፓርቲው ከመርህ ውጪ መሄዱን እና አካሄዱን የሚያስተካክል ከሆነ እና ወደ ህዝብ ከተመለሰ ከአባላቱ ከደጋፊው ህዝብ ጋር ከታረቀ፣ ከባልደረቦቻቸው ጋር ተማክረው አብረው ለመስራት የሚችሉበት አጋጣሚ እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ የዲሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎች ገና ባለመመለሳቸው፣ እነዚህን ጥያቄዎች ለመፍታት በግለሰብም ሆነ በቡድን መታገል ግዴታ ነው ያሉት አቶ የሺዋስ፡ እውነተኛ ሀገራዊ ስብስብ እና ሰላማዊ አማራጭ በሚያስፈልግብት በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ህዝቡን አንተወውም ብለዋል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለም ተጨማሪ 41 የሚደርሱ የፓርቲው የምርጫ ወረዳ አመራርና መደበኛ አባላት ድርጅቱን ለቀው መውጣታቸውም እየተነገረ ይገኛል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በደቡብ ክልል ሃድያ ዞን ምስራቅ ባድዋቾ ወረዳ እና በሾኔ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት አገልግት መስጫ ተቋማት ሙሉ በሙሉና በከፊል አገልግሎት ማቋረጣቸውን ተገልጋዮችና ሠራተኞች ገለጹ፡፡

ተቋማቱ አገልግሎታቸውን ያቋረጡት የወረዳውና የከተማ አስተዳደሩ ለሠራተኞቻቸው ደሞዝ አለመክፈላቸውን ተከትሎ ሠራተኞቹ ሥራ መግባት በማቆማቸው ነው ተብሏል፡፡በወረዳው እና በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት የአገልግት መስጫ ተቋማት አብዛኞቹ ሙሉ በሙሉና ገሚሶቹ ደግም በከፊል አገልግሎት ማቋረጣቸውን ሥማቸው በሚስጥር እንዲያዝላቸው የጠየቁ ቅሬታ አቅራቢዎች ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ ሠራተኞቹ ወደ ተቋማቱ ገብተው እየሠሩ እንዳልሆነ የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ “በዚህም የተነሳ ከባለፈው የመጋቢት ወር መግቢያ አንስቶ አሥፈላጊ የሚባሉ የወረዳው እና የከተማው መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት መስጠት አቁመዋል፡፡በተለይ ነዋሪው ጤናን የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ማግኘት ባለመቻሉ ህክምና ፍለጋ ወደ አጎራባች የዎላይታ እና ሀላባ ዞኖች ለመጓዝ ተገዷል“ ብለዋል፡፡

በወረዳውና በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ከሁለት ሺ በላይ ሠራተኞች ላለፉት ሦስት ወራት የደሞዝ ክፍያ አለመፈጸሙ ለተቋማቱ መዘጋት ወይም መዳከም ምክንያት መሆኑንም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ሠራተኞች ከነቤተሰቦቻቸው ችግር ላይ ከመውደቃቸውም በላይ የቀን ሥራ ፍለጋ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሄዱ ሠራተኞች መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡የወረዳውና የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞቹ ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ በማስተወቂያ ጥሪ ቢያደርጉም ሠራተኞቹ ግን ደሞዝ ካልተከፈለን ወደ ሥራ አንመለስም በሚል ፍቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን አሰተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል፡፡

በሠራተኛው ውሳኔ የተበሳጩት የመስተዳድሮቹ አመራሮች ግን ሠራተኛው ሥራ እንዳይገባ አስታባብረዋል ባሏቸው ግለሰቦች ላይ ማስፈራሪያና እሥርና እየፈጸሙ እንደሚገኙ የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ “ እስከአሁን 40 የሚሆኑ ሠራተኞች የደሞዝ ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ ታሥረው ይገኛሉ፡፡ ሠራተኞቹ ከታሠሩ አንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ቢያስቆጥሩም እከከአሁን ክስ እንኳን አልተመሠረተባቸውም“ ብለዋል፡፡

ዶቼ ቬለ በነዋሪዎቹና በመንግሥት ሠራተኞቹ ቅሬታ ዙሪያ የምስራቅ ባድዋቾ ወረዳ ፣ የሃድያ ዞን መስተዳድር እና የደቡብ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የሥራ ሃላፊዎችን ለማነጋገር ቢሞክረም እንዳንዶች ስብሰባ ሌሎች ደግሞ በጉዞ ላይ ነኝ በሚል ምክንያት ምላሽ ለመስጠት ተባባሪ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡በሃድያ ዞን የምስራቅ ባድዋቾ ወረዳ እና የሾኔ ከተማ አስተዳደሮች የመንግሥት ሠራተኞችን ደሞዝ በዋስትና በመስያዝ የወሰዱትን የአፈር ማዳበሪያ ዕዳ ባለመክፈላቸው የተነሳ ሠራተኞች በደሞዝ እጦት በችግር ላይ መውደቃቸውን ከዚህ በፊት መዘገቡ ይታወሳል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
       👉   _ አስደሳች ዜና

   በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
       አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉  _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና  ::
👉  _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
   👉  _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
  👉  _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር  እና በሌሎች ነገሮች።
   _  👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
  👉  _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
    👉_  ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና         
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
  👉   _  አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
  👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
   👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ  ንግድ -ግብርና  ወይም በትምህርት ዙሪያ
  👉 _  በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ  ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉_  በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
     👉_  ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
      👉_  ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
   👉 _  እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
  👉  _  ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።

አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ

ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ

የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
  እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
        ☎️  0912718883
               0917040506
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥

🌕ድርጅታችን ከታች በተዘረዘሩ የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል። 

🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።

💥NGO በማንኛውም

     🔹የት/ደረጃ:ዲፕሎማ/ድግሪ
     🔹የስራ ልምድ: 0 ዓመት
     🔹ደሞዝ: 18,500+

💥ሹፌር በሁሉም

     🔹የት/ደረጃ:መፃፍ ማንበብ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:13,500+

💥ስልክ ኦፕሬተር

     🔹የት/ደረጃ: 10 ጀምሮ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 6500

💥ጉዳይ አስፈፃሚ

     🔹የት/ደረጃ:10
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ:7000

💥ባንክ ቤት ፅዳት ተላላኪ

    🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ፡4500

💥አካውንታንት

🔹የት/ት ደረጃ= ድግሪ/ድፕሎማ
🔹 ልምድ = 0-2 አመት
🔹ደሞዝ=8500

💥ካሸር አሰልጥኖ

🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500

💥ባርማን/ባሬስታ

🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት

💥 ዌተር የጧት እና የከሰዓት

     🔹የት/ደረጃ: 10 ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
     🔹ደሞዝ: 3500


💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች

     🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
     🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ    
     🔹ደሞዝ፡ 4,000

💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)

🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000

ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006

👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan
👍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ “የመዘዋወር መብት ገድቧል” በሚል ተከሠሠ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ “አድሏዊ አሠራር ተከትሏል” በሚል ክሥ ቀረበበት፡፡ አየር መንገዱ በበኩሉ፣ የፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደሌለ ጠቅሶ ምላሽ ሰጥቷል፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከትግራይ ክልል ተነሥተው ወደ ዐዲስ አበባ የሚጓዙ የትግራይ ተወላጆችን የመዘዋወር መብት ገድቧል፤ ሲል፣ “ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች” የተሰኘ ድርጅት፣ ለፌደራሉ ከፍተኛ

ፍርድ ቤት ክሥ አቀረበ። ድርጅቱ በአቀረበው የክሥ ዝርዝር ላይ፣ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ በፕሪቶርያው ስምምነት ከቆመ በኋላ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታኅሣሥ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ወደ መቐለ በረራ መጀመሩን አውስቷል፡፡ ኾኖም፣ ጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በተላለፈ የኢሜይል መልዕክት፣ በአየር መንገዱ በረራ ላይ ገደብ መጣሉን ያመለክታል። በዚኽም፣ አየር መንገዱ ከመቐለ ወደ ዐዲስ አበባ እና ከሽረ ወደ ዐዲስ አበባ የሚጓዙትን ሰዎች መብት መጣሱን ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ፣ ክሡን ተቃውሞ በጹሑፍ ለፍርድ ቤቱ በሰጠው ምላሽ፣ “ተከሣሽ፣ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ ማንኛውም ተቋም፣ ለአገልግሎቱ መክፈል ለሚችሉ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ያቀርባል እንጂ፣ ከሣሽ እንደሚሉት፣ በትውልድ ቦታ ወይም ማንነት ላይ ተመሥርቶ ልዩነት አያደርግም፤” ብሏል፡፡

ከዚኽም በተጨማሪ፣ ድርጅቱ ባቀረበው የክሥ ዝርዝር ላይ፣ አየር መንገዱ፥ “ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል ናቸው፤” የሚለውን የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 32ን ተላልፏል የሚል ክሥ ተጠቅሷል። አካሔዱ፣ የትግራይ ተወላጆችን በእኩልነት የመገልገል ሕገ መንግሥታዊ መብትን የጣሰ እንደኾነ፣ የድርጅቱ የሕግ አማካሪ አቶ መብርሂ ብርሃነ ገልጸው፣ ኹኔታው፥ ተጓዦችን ለእንግልት ከመዳረጉም ባሻገር፣ ለሕገ ወጥ አሠራር በር መክፈቱን ተናግረዋል፡፡

አየር መንገዱ ባቀረበው የክሥ መቃወሚያ፣ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 60 ዓመት የኾኑ የትግራይ ተወላጆችን ትኬት እንዳይቆርጡ ክልከላ ለማስተላለፍ፣ በሕግ የተሰጠው መንግሥታዊ ሥልጣን እንደሌለው ገልጿል፤ የተባለውንም ክልከላ “አላደረግኹም” ብሏል፡፡

አየር መንገዱ፣ በማቋቋሚያ ደንቡ ከተሰጠው አገልግሎት ውጪ፣ በሕግ ለሌሎች የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተሰጡትን፣ የቁጥጥር ወይም የሕግ ማስከበር ሥራዎች እንደማያከናውንና የተባለው “የዕድሜ ገደብ ክልከላ”ም ተከሣሽን እንደማይመለከት አስገንዝቧል፡፡

አሁን ላይ፣ እንደ ማንኛውም የሀገር ውስጥ በረራ፣ ከመቐለ ወደ ዐዲስ አበባ ወይም ከሽረ ወደ ዐዲስ አበባ፣ ያለምንም ልዩነት በረራዎች እየተደረጉ በመኾናቸው፣ ፍርድ ቤቱ ክሡን ዘግቶ እንዲያሰናብተው አየር መንገዱ በክሥ መቃወሚያው ጠይቋል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
1
የኦሮሞ ፌደራሊስት ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር እና በአዲስ አባባ መንግሥት የሚካሄደውን የግለሰብ ቤቶችንና ቤተ እምነቶችን የማፍረስ ዘመቻ እንዲቆም ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

ፓርቲው የቤት ማፍረስ ዘመቻው ቆሞ፣ ባለሥልጣናት የውሳኔውን ሕጋዊነትና አተገባበር እንደገና እንዲፈትሹ ጥሪ አድርጓል። ፓርቲው ድርጊቱን፣ ጊዜውን ያላገናዘበ፣ አማራጭ መፍትሄዌችን ከግምት ያላስገባ፣ ሕጋዊ አካሄድን ያልተከተለ እና በተሳሳተ ፖሊሲ ላይ የተመሠረተ በማለት ተችቶታል። ዘመቻው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ቤት አልባ ያደረገና መስጅዶች እና የኦርቶዶክስና ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያናትን ጭምር ያፈረሰ መኾኑን ገልጧል።

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር የተካሄደውን የመስጅዶች ማፍረስ ድርጊት "አንዳንድ አካላት ለፖለቲካ ዓላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ እየሞከሩ" ነው በማለት ከሷል።

ቀደም ሲል ያቋቋመው ኮሚቴ ለችግሩ መፍትሄ ለመፈለግ ከመንግሥት ጋር እየሠራ መኾኑን የገለጠው ምክር ቤቱ፣ ሕዝበ ሙስሊሙ ውጤቱን በትዕግስት እንዲጠብቅ አሳስቧል። የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የቤት ማፍረስ ዘመቻው በእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ አይደለም በማለት ትናንት የሰጠውን መግለጫ፣ ምክር ቤቱ እንዳልተቀበለው ገልጧል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረዉ እርዳታ ሊቀጥል መሆኑ ተገለፀ፡፡

ወደ ትግራይ ክልል የሚገባዉ እርዳታ በተለያዩ ህገ ወጥ ምክንያቶች ተቋርጦ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በዚህም ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ዜጎች ለከፋ የምግብ እጦት ተዳርገዉ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡የአለም የምግብ ፕሮግራም እንዲሁም የአሜሪካዉ ተራድኦ ድርጅት ዩ ኤስ አይ ዲ እየተላኩ ያሉት የእርዳታ ቁሳቁሶች በአግባቡ እየደረሱ ባለመሆኑ ምክንያት ድርጊቶቹ እስኪጣሩ ድረስ እርዳታ ማቋረጡን አሳዉቆ ነበር፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የፌደራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለአሐዱ በሰጠዉ መረጃ መሰረት የእርዳታ ስራዉ መልሶ ሊቀጥል መሆኑን አመላክቷል፡፡በዚህም በሚቀጥሉት 72 ሰአታት ዉስጥ እረዳታዎችን የመዉሰድ ስራዉ ሊጀመር እንደሚችል የተናገሩት የፌደራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዉ አቶ አታለል አቡሃይ ናቸዉ፡፡

ተፈጥሮ የነበረዉን ችግር ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በመሆን ክትትል እናደርጋለን ነገር ግን እርዳታዉ መቀጠል አለበት በሚል በተደረገዉ ዉይይት መሰረት እንዲቀጥል መደረጉንም አንስተዋል፡፡ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የአሜሪካዉ ተወካይ ማይክ ሀመር በቀጠናዉ ባሉ ችግሮች ላይ እና በፕሪቶሪያ ስለተደረገዉ የሰላም ስምምነት አተገባበር ዉይይታ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ይታወቃል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa