‹ከ2ሺህ እስከ 4ሺህ ብር ቅጣት እየተጣለብን ነው› የባጃጅ አሽከርካሪዎች
ከሁለት ወራት በፊት አገልግሎት እንዳይሰጡ የተከለከሉትና ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ዳግም ስራ እንዲጀምሩ የተፈቀደላቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎች አሁን ላይ መደበኛ ስራቸውን ማከናወን ፈታኝ እንደሆነባቸው ለአሻም ገልፀውላታል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ ሦስት አካባቢዎች(ሰሚት፣ ሐይሌ ጋርመንትና ቦሌ አራብሳ) የሚሰሩ የባጃጅ አሽከርካሪዎች እንዳረጋገጡት ከ2ሺህ እስከ 4ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት እየተጣለባቸው ነው፡፡
ለቅጣቱ መነሻ ከተፈቀዱላቸው መንገዶች ውጪ ሲያሽከረክሩ በመገኘታቸው ምክንያት ቢሆንም ከዚህ ቀደም ይጣል ከነበረው የቅጣት ገንዘብ ጋር ሲመሳከር ግን እጅግ የተጋነነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከዚህ ቀደም ‹ ከሁለት መቶ እስከ አራት መቶ ብር ይቀጡ › እንደነበረ የሚያስታውሱት አሽከርካሪዎቹ ‹ አሁን ግን ከ2ሺህ እስከ 4ሺህ ብር ቅጣት እየተጣለባቸው መሆኑን › በምሬት ገልፀዋል፡፡
ለዚህ የአሽከርካሪዎች ቅሬታ ለአሻም ምላሽ የሰጡት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዳዊት ዘለቀ ‹ በአሽከርካሪዎቹ ላይ ከ2ሺህ እስከ 4ሺህ ብር ቅጣት እየተጣለ መሆኑን › አልሸሸጉም፡፡‹ነገር ግን ቅጣት የሚጣልባቸው የከተማ አስተዳደሩ ባወጠው መመሪየ ስር የሚገኙ መመሪያዎችን በመጣሳቸው ምክንያት› እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡
ምክትል የቢሮው ሃላፊው እንደሚሉት ‹ እስከ 4ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት የሚጣልባቸው በህግ ወጥ መልኩ በሚሰሩትና የከተማ አስተዳደሩ የማያውቃቸው ላይ መሆኑን › ተናግረዋል፡፡‹እስከ 2ሺህ ብር የሚቀጡት ደግሞ ምንም እንኳን ፍቃድ ቢኖራቸውም፣ በስምሪታቸው ቢሰሩም ክልከላዎቹን ተላለፈው በሚገኙት ላይ መሆኑን ጠቅሰው › አስረድተዋል፡፡
አሽከርካሪዎቹ በቅሬታነት ያነሱት ሌላኛው ጉዳይ በአስፓልትና ‹ በምቹ መንገዶች › እንዳይንቀሳቀሱ መከልከላቸውን ነው፡፡ ይህ ደግሞ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች መሠረተ ልማት በምልዓት የተስተካከለ ስላልሆነ ስራቸውን አስቸጋሪ አድርጎታልም ይላሉ፡፡ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ለዚህ በሰጡት ምላሽ እንዳሉት ከአዲስ አበባ መንግዶች ባለስልጣን ጋር ችግሩን እንዲቀረፍ ጥራት እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል፡፡
[Asham]
@YeneTube @FikerAssefa

መንግስት በፍራንኮ ቫሉታ ከውጪ እንዲገቡ የፈቀዳቸው ምርቶች ዋጋ ከመቀነስ ይልቅ በየጊዜው መጨመር አሣሣቢ ሆኗል ተባለ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ምርቶቹን በፍራንኮ ቫሉታ እንዲያስገቡ ከተፈቀደላቸው ነጋዴዎች ጋር ጋር በጌትፋም ሆቴል ውይይት አድርጓል።ዘይት ፣ ስኳር ፤ ሩዝና የህፃናት ወተት በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ የተፈቀዱ ምርቶች መሆናቸው ይታወሳል።ምርቶቹ በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ በመፈቀዱ ባለፉት አስር ወራት ብቻ መንግስት በታክስ መልክ ማግኘት የነበረበትን ከ10 ቢሊየን ብር በላይ አጥቷል ተብሏል።
ነገር ግን የምርቶቹ ዋጋ ከመቀነስ ይልቅ በየጊዜው ሲጨምር እንደሚታይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ድኤታ አቶ ተሻለ በልሁ ተናግረዋል።ጭማሪው እየታየ ያለዉ በአለም ላይ ዋጋቸው ቀንሶ ባለበት ወቅት ጭምር ነው ብለዋል።ምርቶቹ ወደ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ስርጭታቸውም ላይ ብዙ ግልፅነት እንደሌለ ተነግሯል።
እንደ ማሣያም ዘንድሮ በአስር ወራት ወደ ሀገር ውስጥ የገባው የምግብ ዘይት 97 ሚሊየን ሊትር እንደሆነ ተጠቅሷል።አምና በተመሣሣይ ጊዜ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ግን ከአንድ መቶ ሚሊየን ዶላር ነበር ተብሏል።እንዲያም ሆኖ በገበያው ላይ የምርት አቅርቦት ችግር የለም ነው የተባለው።ሁኔታው በስርጭቱ ላይ ችግር መኖሩን አመላካች እንደሆነ ተጠቅሷል።አስመጪዎች በበኩላቸው በብርና ዶላር መካከል ያለው ልዩነት ከጊዜ ወደ ጊዜ መስፋት የምርቶቹ ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
[Sheger FM]

የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገብረ ሚካዔል ‹ በትግራይ አስቸኳይ ምርጫ እንዲካሄድ › አሳሰቡ፡፡
የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገብረ ሚካዔል (ዶ/ር) "በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት ብቻ እንደሚያስተዳድር" አስታውሰው "በክልሉ ምርጫ እንዲካሄድ" አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡
ደብረፅዮን እንደሚሉት "ራስን በራስ ማስተዳደርን መሠረት አደርገን፤ በአስቸኳይ ወደ ምርጫ መግባት አለብን" ሲሉ ሰኞ እለት በፌስቡክ ገፃቸው ፅፈዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ይሁንና በሊቀመንበሩ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ይህንን ለማረጋገጥ አልተቻለም፡፡በዚሁ ዘገባ "ጊዜያዊ አስተዳደሩ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ምንም ቢቀረው የተጣለበትን ተግባር አጠናቅቆ ማስረከብ አለበት" ብለዋል፡፡
"የትግራይ ሕዝብ በመረጠው መመራት አለበት" የሚሉት ሊቀመንበሩ "ህወሓት እንኳን ማስተዳደር የለበትም" ሲሉ ፅፈዋል ነው የተባለው፡፡ምንም እንኳን ሊቀመንበሩ ይህን ቢሉም ከትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር በኩል ይህ ዘገባ እስከተጠኛቀረበት ጊዜ ድረስ የተሰጠ አስተያየት የለም፡፡
✍Asham

በሐዋሳ ከወ/ሪት ፅጌ መጠለፍ ጋር በተያያዘ 6 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!
ሰሞኑን በሐዋሳ ከተማ ወ/ሪት ፅጌ በላቸው የተባለች ወጣት በአንድ ግለሰብ የመጠለፏ ጉዳይ የማህበራዊ ሚዲያዎች አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል።የከተማዋ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ዛሬ መግለጫ ያወጣ ሲሆን ፥ ከጠለፋ ወንጀሉ ጋር የተጠረጠሩ 6 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ነው ያስታወቀው።የወንጀሉ ድሪጊት የተፈፀመው በሐዋሳ ከተማ በመናኸሪያ ክ/ከተማ መሆኑን የከተማው ፖሊስ ገልጿል፡፡
በዚህም ወ/ሪት ፅጌ በላቸው የተባለች ግለሰብ በቀን 15/9/2015 ዓ.ም ቤተሰቦቿ ተጠልፋ የት እንደደረሰች አናውቅም በማለት ለመነኸሪያ ክ/ከተማ ፖሊስ ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት ምርመራ መጀመሩ ተገልጿል።ይህን ተከትሎም መምሪያው ተፈፀመ ብሎ ባለው ወንጀል መሰረት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ብርቱ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም ነው የጠቆመው፡፡
በዚህም ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ጭምር አስፈላጊውን ጥረት እያደረግኩ ነውም ብሏል፡፡አክሎም በአንዳንድ ማህበራዊ የሚዲያ ተቋማት ከሚሰራጩ አሉባልታዎች የተበዳይ ቤተሰብም ሆነ ህዝቡ ሳይደናገር እንዲጠብቅና ለፖሊስ መረጃ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
በዚህም ከወ/ሪት ፅጌ በላቸው የጠለፋ ወንጀል ጋር የተጠረጠሩ ሥድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው፡፡በተጨማሪም ተጠርጣሪው ሣጅን የኋላ መብራቴ እና የተጠለፈችውን ወ/ሪት ፅጌ በላቸው ይዞ ከተሰወረበት ቦታ አድኖ ለመያዝ ጥረትና ክትትል እየተደረገ ነውም ብሏል ፖሊስ።ህብረተሰቡ የሚችለውን ሁሉ በ09 64 50 46 77 እና 09 69 41 52 72 ስልክ ቁጥሮች ጥቆማ እንዲሰጥ የከተማዋ ፖሊስ ጠይቋል።
Via FBC

ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው!
በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው ልዩ መልዕክተኛው እስከ መጭው ማክሰኞ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ጉብኝት ያደርጋሉ።በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም ከመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በተደረሰው የሰላም ስምምነት አተገባበር ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሽግግር ፍትህና ተጠያቂነትን የማስፈን ሂደትን እንዲሁም የትጥቅ ማስፈታት እና የመልሶ ማቋቋም ሂደቶችን ጨምሮ በሰላም ስምምነቱ በታዩ መሻሻሎች እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።ውይይቱ ከመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር የሚካሄድ መሆኑም ነው የተገለጸው።
በጅቡቲ ቆይታቸውም በአፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ ዕዝ እና የምስራቅ አፍሪካ የተቀናጀ የጋራ ግብረ ኃይል በጋራ በሚያስተናግዱት የምስራቅ አፍሪካ የደህንነት ፎረም ላይ ይካፈላሉ ተብሏል።በተጨማሪም ከጅቡቲ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ ትብብር እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩም ነው የተገለጸው።ከዚህ ባለፈም ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጋር ኢጋድ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያም ይወያያሉ ነው የተባለው።

👍1
መርጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል በቲክቶክ መቷል።
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ
👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።
ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ
👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883
ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah
👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ
tiktok.com/@u0917040506_0912718883

ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር ፣
ላንጋኖ ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች
✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን
✔️ ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን
✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር
✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን
✔️ ዘመናዊ ኪችኖች
✔️ የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣
♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣
♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን
♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣
♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን
♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣
♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡
🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ
በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511
ይደውሉልን,ይጎበኙን!
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት

🔥🔥አስቸኳይ ክፍት የስራ ቅጥር💥💥
🌕ድርጅታችን ከታች በተዘረዘሩ የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን በብዛት ይፈልጋል።
🔥ቀጥታ ወደ ስራ ቦታ እንልካለን።
💥NGO በማንኛውም
🔹የት/ደረጃ:ዲፕሎማ/ድግሪ
🔹የስራ ልምድ: 0 ዓመት
🔹ደሞዝ: 18,500+
💥ሹፌር በሁሉም
🔹የት/ደረጃ:መፃፍ ማንበብ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:13,500+
💥ስልክ ኦፕሬተር
🔹የት/ደረጃ: 10 ጀምሮ
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ: 6500
💥ጉዳይ አስፈፃሚ
🔹የት/ደረጃ:10
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ:7000
💥ባንክ ቤት ፅዳት ተላላኪ
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡4500
💥አካውንታንት
🔹የት/ት ደረጃ= ድግሪ/ድፕሎማ
🔹 ልምድ = 0-2 አመት
🔹ደሞዝ=8500
💥ካሸር አሰልጥኖ
🔹የት/ት ደረጃ= 12/ዲፕሎማ
🔹ልምድ= 0 አመት
🔹ደሞዝ= 5,500
💥ባርማን/ባሬስታ
🔹የት/ት ደረጃ= መፃፍ ማንበብ
🔹ልምድ= ያለው
🔹ደሞዝ=በስምምነት
💥 ዌተር የጧት እና የከሰዓት
🔹የት/ደረጃ: 10 ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ: 3500
💥ሪሴፕሽን ለገስት ሀውስ/ለሆቴሎች
🔹የት/ደረጃ:10ኛ- ከዚያ በላይ
🔹የስራ ልምድ: 0 አመት ጀምሮ
🔹ደሞዝ፡ 4,000
💥ቤቲንግ ቤት ካሸር (በፈረቃ)
🔹የት/ት ደረጃ= 10ኛ በላይ
🔹የስራ ልምድ=0
🔹ደሞዝ=5000
▶ለበለጠ መረጃ
🏘አድራሻ: አ.አ 22 ጎላጎል ሲደርሱ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብለው ሎተስ ህንፃ ግራውንድ ላይ ቢ.ቁ 006
👇👇https://tttttt.me/JobsAtHewan

Telegram
Jobs At Hewan
ይህ ቻናል አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያዎች በቀጥታ የሚተላለፍበት የምንግዜም ምርጥ ቻናል ነው
ይከታተሉ
ስልክ 09 91 33 39 43
09 91 33 40 43
ይከታተሉ
ስልክ 09 91 33 39 43
09 91 33 40 43
👍1
በሃዲያ ዞን ደመወዝ በወቅቱ እንዲከፈላቸው የጠየቁ የመንግሥት ሠራተኞች ታሰሩ!
በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን ምሥራቅ ባደዋቾ ወረዳ፣ ደመወዛቸው በወቅቱ እንዲከፈላቸው ጥያቄ ያቀረቡ የመንግሥት ሠራተኞችን ጨምሮ 40 ሰዎች መታሰራቸውን፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ሠራተኞች ገለጹ።ከመምህራን በስተቀር አብዛኞቹ የመንግሥት ሠራተኞች፣ አሁንም ለተከታታይ ሦስት ወራት ደመወዝ ስላልተከፈላቸው፣ ለከፍተኛ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር መጋለጣቸውን አመልክተዋል።
ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ፣ የምሥራቅ ባደዋቾ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኛ፣ ቀደም ሲል፣ ወርኀዊ ደመወዛቸው ወቅቱን ጠብቆ እንዲከፈላቸው ለተከታታይ ወራት ያቀረቡት ማመልከቻ ተቀባይነት ባለማግኘቱ፣ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ አቤቱታቸውን ለብዙኃን መገናኛ በማሰማታቸው፣ በወረዳው አስተዳደር፣ ተጨማሪ የመብቶች ጥሰቶች እንደተፈጸመባቸው አስታውቀዋል።በዚኽም ሳቢያ፣ 40 ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውንና ከእነርሱም መካከል 18ቱን ግለሰቦች እንደሚያውቋቸው የጠቀሱት ሠራተኛው፣ ግለሰቦቹ፥ በእስር ከአንድ ወር በላይ ቢያስቆጥሩም፣ እስከ አሁን ክሥ እንዳልተመሠረተባቸው ጠቁመዋል።
በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ ነን፤ ያሉት ሌላው ሠራተኛ አቶ ብርሃኑ አበበ፣ የሚደርስባቸውን በደል እና ጫና እንኳን እንዳይናገሩ መከልከላቸውን ገልጸዋል። “የፌዴራል መንግሥት እና ገለልተኛ አካል ችግሩን ይፍታልን፤” ሲሉ አቶ ብርሃኑ ተማፅነዋል።ከወረዳው የመንግሥት ሠራተኞች አንዱ አቶ ብሩክ ናዳሞ እንደገለጹት፣ ሠራተኞች ደመወዝ ስለማይከፈላቸው፥ የቤት ኪራይ እና ወርኀዊ የአስበዛ ወጪ መሸፈን አለመቻላቸውንና ልጆቻቸውም መጎሳቆላቸውን፣ በአጠቃላይ ለከፍተኛ ኢኮኖሚያው እና ማኅበራዊ ችግር መጋለጣቸውን አስረድተዋል።
ከመንግሥት ወገን ምላሽ ለማግኘት፣ ለዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ፣ ለዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ሻለቃ ተሾመ ባትሶ፣ እንዲሁም ለዞኑ የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ሓላፊ አቶ ሳሙኤል ሹጉጤ ስልክ ብንደውልም፣ ስብሰባ ላይ እንደኾኑ በመግለጽ እና ቀጠሮ ከሰጡ በኋላ ስልካቸውን በማጥፋት፣ ለማግኘት በመቸገራችን አስተያየታቸውን ለማካተት አልቻልንም።
ይኹን እንጂ፣ ከአንድ ወር በፊት፣ በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ፣ የሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ ችግር፣ ከዓመታት በፊት ለአርሶ አደሮች ከተሠራጨው የአፈር ማዳበርያ ግዥ ዕዳ ከፈላ ጋራ የተገናኘ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚኹ ጋራ በተገናኘ ሰዎች መታሰራቸውን አምነው፣ እስሩ፣ “በወንጀል ድርጊት በመሳተፋቸው ነው፤” ማለታቸው ይታወሳል።የባደዋቾ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ግን፣ ወርኀዊ ደመወዛቸው በወቅቱ እንዲከፈላቸው ከመጠየቅ በቀር፣ የተሳተፉበት የወንጀል ዐይነት አለመኖሩን በመግለጽ፣ አሁንም መብታቸው ተጠብቆ ለጥያቄያቸው ምላሽ እንዲሰጣቸው አመልክተዋል።
Via VoA

"በአመራርና አባላት መዉጣትና መግባት የሚናድ ፓርቲ አይደለም" - ኢዜማ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) "በአመራርና አባላቱ መግባትና መዉጣት እንዳይናድ አድርገን የገነባነዉ ፓርቲ ነዉ" ሲሉ የፓርቲዉ የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ ዋሲሁን ተስፋዬ ከሰሞኑ የአባላቱን መልቀቅ አስመልክቶ ከአሻም ወቅታዊ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ገልጸዋል፡፡ዋሲሁን እንደሚሉት "አመራርና አባለቱ የለቀቁት ስልጣን ለምን አላገኘንም" በሚል ቅሬታ እንጂ "ፓርቲዉ በቂ እድል ሰጥቷቸዋል"፡፡
"የለቀቁት አባላት ከባለፈው አንድ ዓመት ጀምሮ በአመራርነት ሚና ላይም ሆነ በተመረጡበት ወረዳ በቂ ተሳትፎ እያደረጉ ስላልነበረ በመዉጣታቸዉ በፓርቲዉ ተግባር ላይ ምንም አይነት ተጽእኖ አያመጣም" ሲሉ የፓርቲያቸዉን ጥንካሬ አስረድተዋል፡፡
"የለቀቁ አባላቶች ተስማምተንና ተግባብተን በዴሞክራሲ መንፈስ አብረን ብንሰራ ደስ ይለን ነበር" የሚሉት ሃላፊው "ነገር ግን ጠቅላላ ጉባኤው የወሰነውን አልቀበልም ብለዉ አመት ቆይተዉ ካፈነገጡ ምንም ማድረግ አንችልም" ብለዋል፡፡በቅርቡ የለቀቁት አባላት ያልተመቻቸዉና ያልተስማማችሁበት ጉዳይ ምንድነዉ ስትል አሻም ላነሳችው ጥያቄም ዋሲሁን ምላሽ አላቸው፡፡
አባላቱ የለቀቁት "ምርጫ ቦርድ በተገኘበት ያካሄድነዉን የጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ የተጭበረበረ ነው" በሚል መሆኑን ጠቅሰው "ይህ ግን ሰልጣን ፍለጋ ነው" ሲሉ የቀድሞው ባልደረቦቻቸውን ወቅሰዋል፡፡
"ባለፈዉ ዓመት በወርሃ ሰኔ ያካሄድነው ጠቅላላ ጉባዔ ቅሬታ የሚቀርብበት አይደለም" የሚሉት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ዋሲሁን ተስፋዬ ለዚህም እንደማሳያ ያነሱት "ምርጫ ቦርድ ታዝቦ ለሌሎች ፓርቲዎች አርአያ ሊሆን የሚችል ሲል ያሞካሸዉ" መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ጠቅላላ ጉባዔው ከተካሄደ አንድ ዓመት በኋላ "ውሳኔውን አንቀበልም" ማለት "ተገቢ አይደለም" ሲሉም የቀድሞው አባላቱን ተችተዋል፡፡
Via Asham

በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚፈጸም የሰብአዊ መብት ረገጣና የመስጊዶች ማፍረስ በአስቸኳይ እንዲቆም ኢሰመጉ አሳሰበ።
ኢሰመጉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ እና በአዲስ አበባ ከተማ ቤት ማፍረስ እየተከናወነ እንደሆነ መረጃ እንደደረሰው አትቷል። በዚህ ፈረሳ ከ19 በላይ መስጊዶች መፈረሳቸውን ከኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ያገኘው የቃል መረጃ እንደሚያመላክት አትቷል።በግንቦት 18 ቀን፣ 2015 ዓ.ም በአንዋር መስጊድ ተቃዎሞ ባሰሙ ሙስሊሞች ላይ “የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የፈጸሙ“ የመንግስት የጸጥታ አካላት መንግስት ተገቢውን ማጣራት በማድረግ በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርግ ሲልም አሳስቧል።

YeneTube
Photo
የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሰውና "ኦነግ ሸኔ" ሲል በአሸባሪነት ከፈረጀው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር በታንዛኒያ ጀምሮት የነበረው ውይይት "አሁን ባለበት ደረጃ እንደተቋረጠ ነው" ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ንግግሩ "የሚቀጥልበት ጊዜ ሲኖር ለመገናኛ ብዙኃን በይፋ የሚገለጽላቸው ይሆናል" ሲሉ የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል።የኦሮሞ ነጻነት ጦር ቃል አቃባይ ኦዳ ተርቢ ትናንት ባሰራጩት መረጃ "በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል እየተካሄደ ያለም ሆነ በዕቅድ የተያዘ ንግግር አለመኖሩን" ማስታወቃቸውን ትናንት ዘግበን ነበር።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ ለመገናኛ ብዘኃን በሰጡት መግለጫ በሱዳን በተቀሰቀሰው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት እስካሁን 30 ሺህ 691 ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውንና ከእነዚህ መካከል 17 ሺህ 576 ያህሉ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውንም ተናግረዋል።ይህንን ጉዳይ የሚመለከት ብሔራዊ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየሠራ ይገኛል ያሉት ቃል ዐቀባዩ ቁጥሩ ከሱዳን ተነስተው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚጠለሉ፣ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ሆነው በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፉትን እና ሱዳናዊያን ሆነው በኢትዮጵያ በኩል ወደ ሦስተኛ ሀገር የሚሄዱትን ያጠቃለለ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ዛሬ አዲስ አበባ የሚገቡበትን አንደምታ የተጠየቁት መለስ "በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የሚደረግ የተለመደ የዲፕሎማሲ ልውውጥ ተደርጎ ሊወሰድ ያስፈልጋል" ብለዋል።የኢትዮጵያ እና የቻይና ግንኙነት መተማመን ያለበት ግንኙነት እንደሆነና በቤጂንግ የዓለም አቀፍ ጥናት ዩኒቨርሲቲ በትምህርት መልክ ከሚሰጡ ብዙ ቋንቋዎች ውስጥ አማርኛ ቋንቋ አንዱ መሆኑን ፣ ሦስት የአማርኛ ቋንቋ መማርያ መጻሕፍትም መመረቃቸውንም በጋዜጣዊ መግለጫቸው ተናግረዋል ሲል DW ዘግቧል።
@Yenetube @Fikerassefa

በሶማሊያ ጦር እና በአልሸባብ መካከል በተፈጠረ ግጭት 17 ሰዎች ተገደሉ!
በሶማሊያ ጦር እና በአልሸባብ መካከል በቸፈጠረ ግጭቶ በትንሹ 17 ሰዎች መገደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።ጥቃቱ የተፈጸመው ከሞቃዲሹ 300 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ማጋሳዋ ግዛት ነው።
ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት ያለው አልሸባብ የጦር ማዘዣ ጣቢያ ላይ ባደረሰው ጥቃት ነው ሰዎች የተገደሉት።የማጋሳዋ ወታደራዊ ባለስልጣናት ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል።

👍2
በወረራ ተይዞ የነበረ 37 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ወደ መሬት ባንክ መግባቱ ተነገረ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተሰራው ስራ በወረራ ተይዘው የነበሩ መሬቶች እየተወረሱ ይገኛሉ ተብሏል፡፡በከተማ ደረጃ ከጸጥታ አካላት ጋር በተያያዘ በተሰራው የማጥራት ስራ፣ በህገ-ወጥ መንገድ ተይዞ የነበረን 37 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ወደ መሬት ባንክ እንደሚመለስ ተደርጋል ነው የተባለው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ማሾ ኦላላ፣ የህዝብ እና የሃገር ሃብት የሆነውን መሬት ላልተገባ እና በህገወጥ መንገድ ያስተላለፉ አመራሮች ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተናግረዋል፡፡ይህ እርምጃ እየተወሰደ ቢገኝም አሁንም መሬትን በህገወጥ መንገድ የሚሰጡ አመራሮች እና ሃፊዎች መኖራቸውን ነው የተናገሩት፡፡በመሬት ወረራ ተሳትፈው የተገኙ ደላሎች እና ዜጎችም ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል፡፡
የመሬት ወረራ እና ዝርፊያ መነሻው በሶስት ነገር ነው ያሉት አቶ ማሾ አንደኛው በአርሶአደሩ ስም የሚነግዱ ሰዎች ሲሆኑ ሁሉተኛው በመልካም አስተዳደር ምክንያት የሚፈጸም ነው፡፡ሶስተኛው ደግሞ በጥቃቅን እና የስራ እድል ፈጠራ ተመስርቶ የሚፈጸም የመሬት ወረራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡በነዚህ ምክንያቶች ዜጎች ከደላሎች እና ከአመራሮች ጋር በመቀናጀት የመሬት ወረራ እንደሚፈጽሙ ነው የተናገሩት፡፡በአሁኑ ሰአት ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ አቤቶታዎች እና ቅሬታዎች መቀነሳቸውንም አቶ ማሾ ተናግረዋል፡፡
[Ethio FM]

መንግስት "በደብረ ኤሊያስ በቅድስት ሥላሴ ገዳም አካባቢ የጀመረውን በከባድ መሣሪያ የታገዘ መጠነ ሰፊ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያቋም" እናት ፓርቲ ጠየቀ፡፡
ፓርቲው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል፡፡በመግለጫውም "መንግሥት በደብረ ኤሊያስ በቅድስት ሥላሴ ገዳም አካባቢ የጀመረውን በከባድ መሣሪያ የታገዘ መጠነ ሰፊ ጥቃት በአስቸኳይ በማቆም ለተፈጸመው ግድያና ለወደሙ ነዋያተ ቅድሳት ተጠያቂነት እንዲኖር፤ ስለጥቃቱ ሁኔታ ለእምነቱ ተከታዮች ማብራሪያ እንዲሰጥ እንዲሁም የተስተዋሉ ችግሮች ካሉም በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ" አሳስቧል።
መግለጫው ከግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ጎጃም ደብረ ኤልያስ በሚገኘዉ የቅድስት ሥላሴ ገዳም አካባቢ በከባድ መሣሪያ የተደገፈ ጥቃት እየተካሄደ እንዳለና በዚህም ጥቃት በገዳሙ የሚገኙ መናንያን መገደላቸውን መረጃ ደርሶኛል ብሏል፡፡በተመሳሳይ ወቅትም በአርሲ ሀገረ ስብከት በጢዮ ወረዳ በጨፌ ሚሶማ ቀበሌ ገበሬ ማኀበር ከአሰላ ከተማ በቅርብ ርቀት በሚገኘው በዴራ አማኑኤል አጥቢያ ቤተክርስቲያን ግንቦት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ላይ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ካህናትና ምዕመናን፤ በታጣቂዎች በተሰነዘረ ጥቃት ዘግናኝ ጭፍጨፋና ግድያ እንደተፈፀመባቸው ገልጿል።
መግለጫው በሌላ በኩል የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ"ሸገር ከተማ" ስም እያከናወነ ያለዉን አፍራሽ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም ጠይቋል፡፡መግለጫው በጎሰኝነት ላይ የተመሰረተ ነው ያለው ሀገረ መንግስት አወቃቀር አካል የሆነው አዲስ አበባ ባለቤት አልባ ሁኗል ያለ ሲሆን ዙሪያውን በማጠር አዲስ አበባን እርባና ቢስ እናደርጋታለን የሚል የተጠና ፕሮጀክት ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ መስበቱን ገልጿል፡፡
መግለጫው አክሎም መንግስት "የሸገር ከተማ" ብሎ በሰየመው አካባቢ የሚኖሩ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያዉያንን የማፅዳት ዘመቻ ሃይ ባይ ሳይኖረው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ቤት አልባና ተመጽዋች አድርጓቸዋል ሲል ወንጅሏል።መንግሥት ሕዝብን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ከመምራትና ከማስተዳደር ይልቅ በሕዝብ መከራና ሰቆቃ መሳለቅን መገለጫው አድርጎ ለመቀጠሉ ትልቅ ማሳያ እንደሆነም ገልጿል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ መንደርና ከተማ መስርቶ በሚኖርበት አካባቢ ሁሉ ለሥጋዊ ፍላጎቱ መሟላት ከሚያደርገዉ ሩጫ አስቀድሞ መንፈሳዊ አገልግሎቱን የሚያገኝበትና የሚያከናዉንበት አብያተ እምነት ግንባታ ግንባር ቀደም ሥራዉ ነዉ ያለው መግለጫው አዲስ አበባን እርባና ቢስ ለማድረግ የታለመው የሸገር ከተማ ግንባታም እስካሁን 19 መስጂዶችን እንዲፈርሱ አድርጓል ብሏል፡፡በዚህ ምክንያት ሕዝበ ሙስሊሙ ተቃዉሞዉን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ በወጣበት የጁምዓ ሶላት ላይ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት የኃይል እርምጃ ብዙዎች ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውንና የሦስት ሰዎች ሕይወታቸዉ ማለፉ በመግለጫው ተነስቷል፡፡

ችግሮን ልንፈታ ቤቶ ድረስ መጥተናል ማንኛውም መልዕክት ከአዲስ አበባ ቤቶ ተቀብለን ሀዋሳ ቤቶ ማድረስ ጀምረናል።
ስልክ :-
0962627762
0952626262
Call us 0980526262
0962627762
ቻናላችንን ይቀላቀሉ አዲስ ኤክስፕረስ
https://tttttt.me/+igJA4XrVAGw2ZjBk
ስልክ :-
0962627762
0952626262
Call us 0980526262
0962627762
ቻናላችንን ይቀላቀሉ አዲስ ኤክስፕረስ
https://tttttt.me/+igJA4XrVAGw2ZjBk
👉 _ አስደሳች ዜና
በተለያዩ መናፍስትና አጋንንት ውለሽ አይነጥላ ገርጋሪ በሽታወች ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ሀገር በቀል በሆኑና ከአባቶቻችን ባገኘናቸው ጥበቦች እያገለገልን ቆይተናል።
አሁን ደግሞ ለየት ያሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሰሩ
ከሱዳን ከሳውዲ አረቢያና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በምናስመጣቸው ፍቱን በሆኑ መድሀኒቶችና ገቢሮች የወገኖቻችን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጅታችን ጨርሰናል።
መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ
ማእከል
👉 _ለመካንነት ችግር በልጅ እራብ በልጅ ናፍቆት ለምትሰቃዩ ወገኖቸ አስደሳች ዜና ::
👉 _ለህገጠብቅ እየሔደ እየሔደይ የምንለውን ችግር ለመፍታት በታማኝነት ለመኖር አስተማማኝ የሱዳን መፍትሔ ::
👉 _ለስንፈተወሲብ ስንፈተወሲብ አራት አይነት ችግር ነው መቸኮል ፈፅሞ አለመነሳት ተነስቶ ዳር ሲደርስ ባዶ መሖን ሲነሳ ጥንካሬ ማጣት መልፈስፈስ በአስተማማኝ ከችግሩ ነፃ ይሆናሉ_
👉 _መስተፋቅር በተለያየ አይነት ማለትም ለህዝብ ለሚፈልጉት ሰው ብቻ እንዲሁም ሌሎች በልዩ ሁኔታ። ለምሳሌ በማየት በመሳቅ እንዲሁም በንግግር እና በሌሎች ነገሮች።
_ 👉የገቢያ በጥንቃቄ ለሱቅ ለሆቴል ለመጋዘን ለማንኛውም አይነት የገብያ ቦታ ።
👉 _ለሀብት ለለውጥ ለእድገት::
👉_ ራስወን ከማንኛውም ሊጎዳወት ከሚችሉና
ከሚያስብ ነገር መጠበቂያ።
👉 _ አሁን ሚኖሩበት ቦታ ወይም ሀገር አልመቸወት ብሎ ከሆነና በህይወትወ ደስታ ርቆወት ከሆነ የትኛው ቦታ ቢኖሩ መልካም እንደሆነ ማሳየትና ተለውጠው ደስተኛ ሚሆኑባቸውን ሁኔታወች ማመቻቸት።
👉_ የተበታተነ ሀሳብና ጭንቀት ነገሮችን የመወሰን ችግር ካለብወት ያማክሩን
👉_አሁን በሚሰሩት ስራ ውጤታማ ካልሆኑ ሊለወጡበትና ውጤታማ ሚሆኑባቸውን ስራወች ማመቻቸት ለምሳሌ ንግድ -ግብርና ወይም በትምህርት ዙሪያ
👉 _ በትዳርወ በገቢያ በስራ በልጅ ወይም በፍቅረኛወ ዙሪያ የሚገረግሩ ማንኛውንም አይነት ችግሮች አስተማማኝ መፍትሔ ::
👉_ በሚሰሩበት መስሪያ ቤት ወይም ድርጅት የስልጣን እድገት ቢፈልጉ ያማክሩን።
👉_ ተናግረው አለመደመጥና አለማሳመን ችግር ካለብወ አንደበትወ ተወዳጅና እርስወ ያሉበት ነገር ሁሉ ተፈላጊ ሚያደርጉ ነገሮችን መስራት።
👉_ ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም መድረክ ላይ ለመናር ሚፈሩ ከሆነና በራስ መተማመን ከሌለወት ያማክሩን።
ለትምሕርት ለሽምደዳ የተማሩትን ለመርሳት ችግር አስተማማኝ መፍትሔ ::
👉 _ እለታውዊ እጣወች ማይወጡለወት ከሆነ ማለትም እቁብና የመሳሰሉት አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንሰራለን።
👉 _ ሚፈልጉትን ሁሉ ያማክሩን እኛ ጋ የሌሉ ነገሮች የሉም። በታማኝነትና በግልፅነት እናግዝወታለን። ለስራችንም 100% ዋስትና እንሰጣለን። ለሚያገኟቸው ማንኛውም አይነት አገልግሎቶች ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
አድራሻ ባሕርዳር ቀበሌ 11 ዲያስቦራ በአዲሱ አስፓልት ንግድ ባንኩ ህንፃ
ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ
የቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2Y2h3Tx/
እኒህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማግኔት ይደውሉ
☎️ 0912718883
0917040506

TikTok
TikTok - Make Your Day
TikTok - trends start here. On a device or on the web, viewers can watch and discover millions of personalized short videos. Download the app to get started.