YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዘንድሮ 240 ሺሕ የሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ተገለጸ!

በ2015 በመንግሥትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሰበሰበው መረጀ መሠረት 240 ሺሕ የሚደርሱ ተማሪዎች በበይነ-መረብ የመውጫ ፈተና ለመስጠት መዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትምህርት ሚኒስቴርን የ2ዐ15 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም ላይ ይገኛል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ኘሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት፤ በ2015 በመጀመሪያ ዲግሪ ኘሮግራም ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ብሉ -ኘሪንት መዘጋጀቱን የገለጹ ሲሆን፤ የመውጫ ፈተና የክፍያ ተመን ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱንም አብራርተዋል፡፡የመውጫ ፈተናን ለመተግበር የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱንም የገለጹት ሚኒስትሩ፤ የመውጫ ፈተና ስትራቴጂ ማስፈፀሚያ መመሪያ እና የድርጊት መርሃ-ግብር ዝግጅት መጠናቀቁንም አብራርተዋል፡፡

በመውጫ ፈተና የሚካተቱ የትምህርት ዓይነቶች (ኮርሶች) ተለይተው፤ በቅድመ-ምረቃ በሚሰጡ በኹሉም የትምህርት መስኮት የፈተና ንድፍ ማሳያ መዘጋጀቱንም ኘሮፌሰር ብርሃኑ አስረድተዋል፡፡ከዚህ ቀደም በጤናና በሕግ የትምህርት መስኮች ለሚመረቁ ተማሪዎች ብቻ የመውጫ ፈተና ሲሰጥ መቆየቱን የሚታወስ ሲሆን፤ በያዝነው ዓመት ከመጭው ሐምሌ ወር ጀምሮ ከየትኛውም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ላይ ያሳለፈው የእግድ ውሳኔ ተቃወመ፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ለኢትዮ ባወጣው መግለጫ ፤ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ላይ ያሳለፈው የእግድ ውሳኔ ህጋዊ ግዴታውን የጣሰ ነው ሲል ገልጿል።

ይህ የእግድ ውሳኔ ምክንያቱ ሕጋዊ ሆነም አልሆነ በመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 1238/2021 አንቀጽ 73 ፣ 76 እና 81(2) የተጠቀሱትን በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ የመስጠትም ሆነ የሚዲያ ተቋሙ ራሱን እንዲከላከል ቀድሞ እድል የመስጠት ሕጋዊ ግዴታውን የጣሰ ነው ሲል ኢዜማ ገልጿል።

ተቋማት የሚወስዷቸው እርምጃዎች በእርግጥም ሕግን ከማስከበር መነሻነት ይልቅ በማን አለብኝነት ድርጅታዊ ፍላጎትን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ነው " ያለው ኢዜማ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ላይ የወሰደው እርምጃ ይህን በግልፅ ያስረዳል ብሏል።ተቋማት ከእንደዚህ አይነት ወጥነትና ገለልተኝነት የጎደለው ተግባር በአስቸኳይ እንዲወጡም አሳስቧል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በሰቆጣ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ!

በሰቆጣ ከተማ 02 ቀበሌ ቀጠና 9 በተለምዶ ዝቋላ መውጫ ኬላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው የተሸከርካሪ አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።

የፖሊስ ጽ/ቤቱ የአደጋ ፕላን መርማሪ ንዑስ ክፍል ኃላፊ ዋና ሳጅን አሻግሬ ጊደይ፤ መነሻውን አበርገሌ ኒሯቅ ከተማ መድረሻውን ደግሞ ሰቆጣ ከተማ ያደረገው ንብረትነቱ የግል የሆነ ኮድ 2 02942 ባለ አንድ ጋቤና ቲዮታ ተሸከርካሪ፤ ትላንት ግንቦት 14/2015 ከቀኑ 8፡00 በተለምዶ ዝቋላ መውጫ ኬላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግምት ከ2 መቶ ሜትር በላይ ከዋናው መንገድ በመውጣት በደረሰበት አደጋ ሦስት ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በአደጋው በአንድ ግለሰብ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት፣ በኹለት ሰዎች ደግሞ ቀላል አደጋ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ በንብረት ላይም ከ48 ሺሕ ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት መውደሙን ገልጸዋል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ቢሆንም፤ ተሸከርካሪው 5 ኩንታል እህልና 9 ሰዎችን ከአቅም በላይ ጭነት መጫኑንና በከፍተኛ ፍጥነት ምክንያት የፍሬን ችግር ያጋጠመው ሲሆን፣ ለአደጋው መንስኤ መሆኑን መገንዘብ እንደሚቻል ዋና ሳጅን አሻግሬ አስረድተዋል።

ከከተማዋ ወደ ተለያዩ ወረዳዎች የሚደረጉ ጉዞዎች አብዛኞቹ የትራፊክ ሕጉን ያልጠበቁ ሰውንና እቃን በአንድ ላይ በመጫን ከአሁን በፊትም አደጋ መስተናገዱን በመግለጽ፤ አሁንም በንብረት እና በሰው ላይ ጉዳት ደርሷል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

‹‹አካባቢያችን ከፍተኛ የሆነ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት እጥረት ያለበት በመሆኑ ምክንያት ማህበረሰባችን ባገኘው የትራንስፖርት አማራጭ እንዲጠቀም ተገድዷል፡፡›› ያሉት ኃላፊው፤ ማህበረሰቡ ራሱን ለአደጋ ከሚያጋልጡ ጉዞዎችን እንዲጠብቅ እንዲሁም ኹሉም አካል ህገ-ወጦችን በማጋለጥና በመጠቆም የትራፊክ አደጋን እንዲከላከል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የአዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ምልመላና ምርጫ የሚያከናውን 7 ሊቃነ ጳጳሳት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ መምረጡ ተገለጸ!

የግንቦቱ ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተወያይቶ  ውሳኔ ካሳለፈባቸው አጀንዳዎች መካከል የአዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫና ሢመት አንዱና ዋነኛው ነው።

በመሆነም በጉዳዩ ዙሪያ ለሦስት ቀናት ከተወያየ በኋላ ለአሁኑ ችግር ባላባቸውና አስፈላጊ በሆነባቸው ዘጠኝ አህጉረ ስብከት ላይ በዚህ ዓመት  2015 ዓ/ም  9 አዳዲስ ኤጲስ ቆጳሳት እንዲሾሙና በጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቤተ ክርስቲያን እውነትና ቀኖናን እንዲሁም መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት ባደረገ  መልኩ እንዲሁ አባቶች በሚያስፈልጉባቸው አህጉረ ስብከት የአዳዲስ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ጉዳይን እንደሚመለከተው ውሳኔ አስተላልፏል።

ስለሆነም በዚህ ዓመት በሚካሄደው ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት የሚሾሙ አባቶች የሚመደቡባቸው   የ(9)ኙ አህጉረ
ስብከት ስም ዝርዝር

፩. ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
፪. ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
፫. ሆሮ ጉድሩ  ወለጋ ሀገረ ስብከት
፬. የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት
፭ ምዕራብ አርሲ (ሻሸመኔ) ሀገረ ስብከት
፮. ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
፯.ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
፰.ጌዴኦ ቡርጅና አማሮ ሀገረ ስብከት
፱.ዳውሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት መሆናቸው ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም ምልዓተ ጉባኤው ይህን ጉዳይ በጥናትና በቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና መሠረት የሚለይና  የሚያከናውን 7 ሊቃነ ጳጳሳት የተካተቱበት አስመራጭ ኮሚቴ መምረጡም ተገልጿል።

የአስመራጭ ኮሚቴው  አባላትም ስም ዝርዝርም

1) ብፁዕ አቡነ ሄኖክ
2) ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
3) ብፁዕ አቡነ ማርቆስ
4) ብፀዕ አቡነ ናትናኤል
5) ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
6) ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ
7) ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል  በመሆን ኮሚቴው ተዋቅሯል።

አስመራጭ ኮሚቴው ጥናቱንና ምልምላውን ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር በመናበብ የቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት በማድረግ ለመጨረሻ ምርጫ  ለምልዓተ ጉባኤ የሚያቀርብ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤው  እንደሥርዓቱ  በመምረጥ 9ኙን  መነኮሳት የሚለይ ይሆናል።

በምልዓተ ጉባኤው የተመረጡ 9ኙ መነኮሳት አባቶች  ሥርዓተ ሢመት ሐምሌ 9/2015 ዓ/ም  በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ  ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ እንደሚፈጸም  ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Via ተሚማ
@YeneTube @FikerAssefa
የሲሚንቶ ግብይትን በዲጂታል መንገድ ለማከናወን የዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተገለጸ!

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሲሚንቶ ግብይትን በዲጂታል መንገድ ለማከናወን የዝግጅት ስራዎች እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡በሚኒስቴሩ የሀገር ውስጥ ንግድና ሸማቾች ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ መስከረም ባህሩ የሲሚንቶ ግብይት በቴክኖሎጂ ታግዞ እንዲፈፀም የዝግጅት ስራዎችን የመለየት ስራ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የሲሚንቶ ግብይት በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዞ መካሄዱ ሲሚንቶ በተተመነለት ዋጋ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ፣ ስርጭቱ ከፋብሪካው ጀምሮ እስከ ተጠቃሚ ድረስ ያለውን ሰንሰለት ለመከታተል፣ የዘርፉን የግብይት ሥርዓት በማዘመን የግብይት ሰንሰለቱን ለማሳጠር እና ከህገወጥ ደላሎች የፀዳ የንግድ ሥርዓትን ለመዘርጋት ያግዛል ብለዋል፡፡

የዲጂታል ግብይት ሥርዓትን መተግበር በንግዱ ዘርፍ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ይቀርፋል ያሉት ኃላፊዋ የሲሚንቶ ግብይት በድጅታል ቴክኖሎጂ ታግዞ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ ከፋብሪካዎች ጋር ውይይቶችን የማድረግ፣ የክፍያ አማራጮችን የመለየትና መሰል የዝግጅት ስራዎችን በመለየት ሂደት ላይ እንደሚገኝ መግለፃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ትምህርት ሚንስቴር “ከቀረቡልኝ የማስረጃ ይረጋገጥልን ጥያቄ 40 በመቶ የትምህርት ማስረጃዎች ሀሰተኛ ሆነው አገኘሁ” አለ!

ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት 18 ሽህ የትምህር ማስረጃዎች ትክክለኛ ተፈትሾ 921 (አምስት በመቶዎቹ) ህገ-ወጥ ሆነው እንዳገኛቸው ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ።ቀጣሪ ተቋማት ለሚንስቴሩ ይረጋገጥልን ብለው ባቀረቡት ጥያቄ ደግሞ 225 የትምህርት ማስረጃዎች ተመርምረው 40 በመቶዎቹ ሀሰተኛ ሆነው መገኘታቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ትምህርት ሚንስቴር የዘጠኝ ወር ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርብ፤ አባላቱ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በስፋት መሰራጨት እንዳሳሰበው ተናግረዋል።ገዙ ምናዬ የተባሉ የምክር ቤት አባል "በአንዳንድ የግል የትምህርት ተቋማት የሚወጡ የሀሰት የትምህርት ማስረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ ስለሆነና ይህም በሀገር አሉታዊ ጫና ስላለው እነዚህን ተቋማት እውቅና ከማሳጣት አንፃር ምን እየተሰራ ይገኛል?" ሲሉ ጠይቀዋል።የትምህርት ማስረጃ ማጣራትን ከራሳችን ጀምረናል ያሉት የትምህርት ሚንስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፤ በዚህ ዓመት ሁሉም የፊደራል ተቋማት ሰራተኞች ማስረጃ እንደሚጣራ ገልጸዋል።

"በሁሉም የፌደራል ተቋማት የሰራተኞችን ማህደር መመርመር ጀምረናል። ምን ያህሉ እውነተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዞ ነው? ምን ያህሉ አይደለም የሚል ምርመራ እያካሄድን ነው፤ ከራሳችን ጀምረን። ማህበረሰቡ ልክ እንደፈተናው [የ12ተኛ ክፍል ፈተና] እንዲያውቅልን የምንፈልገው ከአሁን በኋላ በተጭበረበረ ድግሪ፤ በተጭበረበረ ዲፕሎማ የሚሰራ ስራ አይኖርም የሚለውን ለማሳወቅ ነዉ። በዚህ ዓመት እሱን እንጨርሳለን ብለን እናስባለን" ብለዋል።ይህን ለማድረግ ችግሩን ያልደበቁት ሚንስትሩ "ችግሩ ግን የሚታወቅ ነው፤ ሀገሩ የደላላ ሆኗል፤ ቀጥተኛ የሆነ የግብይት ስርዓትና ንፁህ የሆነ ስራን ለመስራት በጣም ብዙ ስራ ይቀረናል" በማለት ተናግረዋል።

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ሀገር ውስጥ የሚልኩት መልዕክቶች አሉ?
- ሙሉ የIsuzu ጭነት
-ግማሽ ጭነት
-ፓስታዎች
-የተለያዩ መልዕክቶች
በታማኝነት ፣ በፍጥነት ፣ በኃላፊነት ፣ እናጓግዝሎት።

0980526262
0962627762

T.me/deliveryhawassaexpress
የወዳጅ ዘመድዎን ፎቶዎች ከፈለጉት ጽሁፎችና ዲዛይኖች ጋር፣ ሳቢና ማራኪ በሆነ የእንጨት ስራ ቀርፀው ለዘላለም ያስቀምጡ፣ በስጦታ መልክ ያበርክቱ።
ለበለጠ መረጃ @pulsengravings ብለው ያግኙን
ከፈለጉም 0911876009 ላይ ሃሎ ይበሉን
https://tttttt.me/photoengravings ላይ ይቀላቀሉ
መርጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል በቲክቶክ መቷል።

የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ

👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

    ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
                   👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
          0912718883

    ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah

👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ

tiktok.com/@u0917040506_0912718883
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
በኢትዮጵያ የህጻናት የካንሰር ስፔሻሊስት ሃኪሞች ብዛት ስምንት ብቻ መሆናቸዉ ተነገረ

በኢትዮጵያ በህጻናት የካንሰር ህክምና አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ሃኪሞች ቁጥር ስምንት ብቻ መሆናቸውን የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሆስፒታል አስታዉቋል፡፡በሆስፒታሉ የህጻናት የደምና የካንሰር ሰብ ስፔሻሊስት ሃኪም የሆኑት ዶክተር ማሙዴ ድንቅዬ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የህፃናት ካንሰርን አስቀድሞ ለመከላከል በሽታው ቶሎ ከተገኘና ህክምናው በጊዜው ከተጀመረ  የመዳን እድሉ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ እንደ ሃገር በዚህ የህክምና ዘርፍ ያሉት የሃኪሞች ቁጥር ከስምንት ያልበለጡ መሆናቸውን ተከትሎ  በርካታ ህጻናት በቂ ህክምናን እንዳያገኙና  የመዳን እድላቸው ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡ይህም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የካንሰር ህክምና አገልግሎት ሽፋንን ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጎታል ያሉት የህክምና ባለሙያው ችግሩን ለመቅረፍ አዳዲስ የህክምና ባለሙያዎች በዘርፉ እንዲሰማሩ ማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል፡፡

አያይዘውም በዘርፉ ያለውን የህክምና ባለሙያዎች እጥረትን ለማስወገድ ቀጣይነት ያላቸው ስልጠናዎች በተለያዩ የኢትዮጵያ ስፍራዎች በሚገኙ ከፍተኛ  የትምህርት ተቋማት እየተሰጡ ይገኛሉ ሲሉ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡


Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
ትምህርት ሚንስቴር “የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍ የአንድ ትውልድ እድሜን ይጥይቃል” አለ።

የዘጠኝ ወር አፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረበው ትምህርት ሚንስቴር በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ከትምህርት ጥራት እስከ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ፍትኃዊነት ከትምህርት ፈተናና ምዘና እስከ አዲሱ የትምህርት ፖሊሲ ድረስ ጥያቄ ቀርቦለታል። የትምህርት ሚንስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) "የትምህርት ስርዓት ጊዜ ወስዶ ከተበላሻ በኋላ መልሶ ለመጠገንም ልክ የዛኑ ያህል ጊዜ ይወስዳል።

የዚህን ሀገር የትምህርት ስርዓት በአንድና ሁለት ዓመት የምንጨርሰዉና የምናሻሽለው ቢሆን እኮ ደስ ይለናል። የጉዳቱ ስፋት እኮ አንድ ትውልድ ነው።

ሌላ ትውልድ እንዳይበላሽ ነው እንቅስቃሴ እያደረግን ያለነው። ማሻሻያዎቹ በአንድ ጊዜ ለውጥ ይወጣሉ ተብሎ መጠበቅ የለበትም" ብለዋል።የትምህርት ሚንስትሩ ችግሮችን ለመፍታት በመደበኛ አካሄድ መፍታት ባለመቻላችን "ለየት ያለ እንቅስቃሴ" ለማድረግ ተገደናል ብለዋል።

Via Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
ኦነግ የአመራር አባላቱ በቡራዩ ፖሊስ መምሪያ እንደሚገኙ አስታወቀ!

በኦሮሚያ ክልል ቡራዩ ከተማ፣ በእስር ላይ እንደሚገኙና ለአንድ ወር ያህል ማንም ጎብኚ እንዳላያቸው ሲነገር የቆየው፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራር አባላት፣ ማምሻውን ወደ ቡራዩ ፖሊስ መምሪያ መመለሳቸውን ጠበቃቸው አስታወቁ። ፓርቲው፥ እስረኞቹ ያሉበት ኹኔታ እንደሚያሳስበው ገልጿል።ለአራት ዓመታት ያህል በእስር ላይ የሚገኙት የኦነግ አመራሮች ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ፣ ታሳሪዎቹ፣ በመጀመሪያ፣ ቡራዩ ፖሊስ መምሪያ ታስረው እንደነበር፣ በኋላም ለአንድ ወር ያህል የት እንደነበሩ ሳይታወቁ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ጠበቃው ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ያለፈውን አንድ ወር በዱከም ፖሊስ መምሪያ በእስር ያለፉት አመራሮቹ፣ አኹን ደግሞ ወደ ቡራዩ ፖሊስ መምሪያ መመለሳቸውን ገልጸዋል። እስረኞቹ ለምን ከአንዱ ፖሊስ መምሪያ ወደ ሌላው እንደሚዛወሩ፣ የተነገራቸው ምክንያት አለመኖሩን፣ ጠበቃው አክለው ተናግረዋል።የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ ለሚ ገመቹ፣ እስረኞቹ ያሉበት ኹኔታ አሳሳቢ እንደኾነ አመልክተዋል። ቃል አቀባዩ አያይዘውም፣ ስለ እስረኞቹ ኹኔታ፣ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ለተባሉ ተቋማት ኹሉ አቤቱታ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ ከኦሮሚያ ክልል እና ከፌዴራል መንግሥት ቃል አቀባዮች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ይኹንና ከዚኽ ቀደም፣ የአሜሪካ ድምፅ የጠየቃቸው፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ፣ “የታሰረ የኦነግ አመራር የለም፤” ሲሉ፣ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ቀደም ሲል አውጥቶት በነበረው መግለጫ፣ “ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራር አባላት በአፋጣኝ እንዲፈቱ፣ አልያም ያሰራቸው አካል ሕጋዊ ሒደቱን ተከትሎ፣ የክሥ መዝገብ ከፍቶ በአግባቡ እንዲጠይቃቸው አሳስቦ እንደነበር ይታወሳል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ የሩሲያን ድንበር ተሻግሮ ከተፈጸመው ጥቃት ራሷን አራቀች።

ሩሲያንና ዩክሬን ከሚያዋስናቸው አንዱ በሆነው የቤልጎሮድ ግዛት በኩል ሰኞ እለት ታጣቂዎች ገብተው ጥቃት ፈጽመዋል ተብሏል።ሩሲያ በዩክሬን ወረራ ከፈጸመች በኋላም የሩሲያን ድንበር የተሻገረ ወረራ ሲፈጸም የመጀመሪያው ነው።ሩሲያ በቤልጎሮድ ግዛት አሜሪካ ሰራሽ ሃምቪስን ጨምሮ በርካታ ከጥቅም ውጭ የሆኑ የምዕራባውያን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ምስሎችን አውጥታለች።

አሜሪካ በበኩሏ “ በሩሲያ ውስጥ ጥቃቶችን አላበረታታንም” ስትል ተናግራለች።በዚህ ጥቃት ላይ አሜሪካ ያቀረበችው የጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ መዋላቸውን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያና በሌሎችም መድረኮች ላይ እየተሰራጩ ያሉ ዘገባዎችን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አምነዋል።

ነገር ግን አገራቸው “የእነዚህ ዘገባዎች ትክክለኛነትን በተመለከተ በዚህ ጊዜ ትጠራጠራለች” ብለዋል።ማቲው ሚለር ማክሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ይህንን ጦርነት እንዴት መምራት እንዳለባት የመወሰን የዩክሬን ጉዳይ ነው” ሲሉ አክለዋል።በድንበር አቅራቢያ የሚገኙ የቤልጎሮድ መንደሮች ነዋሪዎች በደረሰው ከባድ መሳሪያ ጥቃት ተፈናቅለዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቤጂንግ ገባ!

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቻይና ቤጂንግ ገባ።ልዑኩ ቤጂንግ ሲደርስ በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎች፣ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች እና በቻይና የዳይስፖራ ማህበረሰብ ተወካዮች አቀባበል ተደርጎለታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ክልል ‹ በአዲስ አበባ ቤተ መንግስት እንዲገነባ ክልላዊ ህገ መንግስቱ ይፈቅድለታል › አለ፡፡

የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ሐይሉ አዱኛ ከአሻም ወቅታዊ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት ‹ ክልሉ በአዲስ አበባ ቤተ መንግስት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ተቋማትን የመገንባት መብት እንዳለው ይደነግጋል› ብለዋል፡፡

አክለውም ‹ ይህ እንደ አዲስ ጥያቄ የሚያሰነሳ ጉዳይ አይደለም › ብለዋል፡፡ሃላፊው ‹‹ ፊንፊኔ ›› እያሉ የሚጠሯት አዲስ አበባ የክልሉ መቀመጫ ከሆነች 30 ዓመታት ማስቆጠሩንም ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን እርሳቸው ይህን ቢሉም የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ የተቀየረው በ1997 ዓ.ም መሆኑን አሻም ብትጠይቃቸው እርሳቸው ግን 30 ዓመታትን አስቆጥሯል ባይ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በማያወላዳ መልኩ አዲስ አበባ የፌደራሉ መንግስት መቀመጫና የሀገሪቱ መዲና መሆኗን ቢደነግግም የቢሮው ሃላፊ ግን ‹ የክልሉ ህገ መንግስት አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ መሆኗን ደንግጓል › ሲሉ ሞግተዋል፡፡

እርሳቸው ይህን ቢሉም አሻም ‹ የህግጋት ሁሉ የበላይ የሀገሪቱ ህገ መንግስት መሆኑን › አስታውሳ ብተጠይቃቸውም ‹ የክልሉ ህገ መንግስት አዲስ አበባ የኦሮሚያ መቀመጫ መሆኗን ይደነግጋል › ሲሉ መልሰዋል፡፡

Via Asham TV
@YeneTube @FikerAssefa
1
ጋምቤላ-በሁለት ጎሳ አባላት ግጭት 7 ተገሉ!

በጋምቤላ ክልል በሚኖሩ በሁለቱ ነባር ብሄረሰብ አባላት መካከል ካለፈዉ እሁድ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 7 ሰዎች ተገደሉ።የክልሉ ነዋሪዎች እንዳሉት በግጭቱ ምክንያት የጋምቤላና የኢታንግ ከተሞች የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትና የተለያዩ መደብሮች ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ተዘግተዋል።

በጋምቤላ ክልል በርካታ ቁጥር ባላቸዉ በኑዌርና በአኙዋክ ቤሔረሰብ አባላት መካከል ግጭቱ የተቀሰቀሰበት ምክንያት እስካሁን በዉል አልታወቀም።የኑዌር ብሔረሰብ ተወላጅ የሆኑት የኢታንግ ከተማ ነዋሪ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ እንደተናገሩት ኢታንግ ዉስጥ በተደረገዉ ግጭት ከሁለቱም ወገን 4 ሲገደሉ ሌሎች 5 ቆስለዋል፡፡

የአኙዋክ ብሔር ተወላጅ የሆኑት የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው ሰዎች መገደላቸውን አስታውሰው፣ የመንግስት ስራ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ እንደሌለና የአገልግሎት መስጫ ተቋማትም ዝግ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ቤተክርስትያኗ የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤን መጠናቀቅ አስመልክቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፋለች!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ከግንቦት 1 ጀምሮ እስከ ግንቦት 16 ድረስ ሲደረግ የነበረው የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤን መጠናቀቅ አስመልክቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፋለች።በዚህም በሀገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፈን በሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ የሰላም ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሰይሟል።

እንዲሁም በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ግንኙነትን በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ ተሰይሞ በስራ ላይ ያለው ልዑክ የጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲቀጥል ምላዕተ ጉባኤው ውሳኔ አሳልፏል።በተጨማሪም ጉባኤው በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት የትግራይ ወገኖች ያሉበትን ከፍተኛ ችግር ታሳቢ በማድረግ 20 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶሱ ወስኗል።

በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ አህጉረ ስብከት በነበረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት በአህጉረ ስብከትና በአብያተ ክርስትያናት የተቋረጠው አገልግሎት እንዲቀጥል፤ ችግሮችም በዘላቂነት እንዲቀረፉ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳት ከፌደራልና ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር በመወያየት ችግሮቹ እንዲፈቱ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል።

ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትን በተመለከተ ክፍት በሆኑና በተደራቢነት በተያዙ ጉልህና አንገብጋቢ ችግሮች ባሉባቸው ኦሮሚያና ደቡብ ክልል ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ አስመራጭ ኮሚቴ እንደሚሰየም ቅዱስ ሲኖዶስ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa