YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ 9 አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ ውሳኔ አሳለፈ!

የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ውሎው ችግር ባለባቸውና አስፈላጊ በሆኑባቸው አህጉረ ስብከት ዘጠኝ አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ ውሳኔ አሳልፏል።አዳዲሶቹ ኤጲስ ቆጶሳት እነማን እንደሆኑና በየትኞቹ አህጉረ ስብከቶች እንደተሾሙ የተገለጸ ነገር የለም።

[የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት]
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ሃይሎችን ከ85 እስከ 90 በመቶ የሚሆን ትጥቅ የማስፈታት ስራ መፈፀሙ ተሰማ።

የፕሪቶሪያ ውል አፈጻጸም ለመገምገምና አሁናዊ ሁኔታን ለመመልከት የ43 ሃገራት ወታደራዊ አታሼዎች ከአለፈው አርብ ጀምሮ በትግራይ ጉብኝት ሲያደርጉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

በአፍሪካ ሕብረት የሰላም ስምምነቱ ተቆጣጣሪ ልኡክ መሪ ሜጀር ጀነራል ስቲፈን ራዲና ዛሬ በመቐለ ከተማ በተሰጠው መግለጫ እንዳሉት የሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ነው።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ የኤርትራ መንግስት የዕርዳታ እህል ለሕዝቡ እንዳይዳረስና የአፍሪካ ሕብረት የስምምነቱ ትግበራ ተቆጣጣሪ ስራውን እንዳያከናውን እያደናቀፈ ነው ሲሉ ከሰዋል ሲል DW ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የዓረብ ሊግ በሕዳሴ ግድብ ላይ ያሳለፈው የውሳኔ ሃሳብ እንደማትቀበል ገለጸች!

ኢትዮጵያ÷የዓረብ ሊግ በሕዳሴ ግድብ ላይ ያሳለፈው የውሳኔ ሃሳብ እንደማትቀበለው አስታውቃለች፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷በቅርቡ የተካሄደው የዓረብ ሊግ የመሪዎች ጉባኤ ያሳለፈው የውሳኔ ሀሳብ የኢትዮጵያን መንግስት እንዳሳዘነ ገልጿል፡፡

ውሳኔው በተለይም በግድቡ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ ድርድር አንዲፈታ እየሰሩ ያሉትን የአፍሪካ ህብረትን እና አባል ሀገራትን ሚና የሚያኮስስ ነው ሲል አብራርቷል፡፡

የውሳኔ ሃሳቡ ታሪክን ከሚጋራው የአፍሪካ እና የዓረብ ሀገራት ግንኙነት በተቃራኒ የተወሰነ ውሳኔ መሆኑንም አስገንዝቧል፡፡፡በሊጉ የተላለፈው የውሳኔ ሃሳብ የግብጽን የናይል ወንዝ ፍትሃዊ ያልሆነ አጠቃቀም የሚደግፍ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ስራዎች እየዘመኑና ቴክኖሎጂዎቹ ያለ እረፍት ስራዎችን ማከናወን መቻላቸውን ተከትሎ ብዙ ስራዎች ከሰው ልጆች እጅ እየወጡ ናቸው፡፡

ከሰው ልጅ ተነጥቀው በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሚተኩ የስራ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው?
በፎቶ እድሜ የሚናገረው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ
በዚህም መሰረት በአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ከሚተኩ ስራዎች መካከል ጸሀፊነት፣ መረጃ ትንተና፣ መረጃ ማደራጀት፣ የዲዛይን ስራ (ዲዛይኒንግ) እና የምስል አርትኦት (ቪዲዮ ኢዲቲንግ) ዋነኞቹ ናቸው ተብሏል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ሙያዎች በአርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የሚሸፈኑ በመሆናቸው የሰው ልጆች መማር የማይጠበቅባቸው ሙያዎች ናቸው ሲል ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡

Via:-አልአይን
@Yenetube @Fikerassefa
የወዳጅ ዘመድዎን ፎቶዎች ከፈለጉት ጽሁፎችና ዲዛይኖች ጋር፣ ሳቢና ማራኪ በሆነ የእንጨት ስራ ቀርፀው ለዘላለም ያስቀምጡ፣ በስጦታ መልክ ያበርክቱ።
ለበለጠ መረጃ @pulsengravings ብለው ያግኙን
ከፈለጉም 0911876009 ላይ ሃሎ ይበሉን
https://tttttt.me/photoengravings ላይ ይቀላቀሉ
👍1
መርጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል በቲክቶክ መቷል።

የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ

👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

    ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
                   👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
          0912718883

    ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah

👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ

tiktok.com/@u0917040506_0912718883
👍1
አዲስ ነገር ከነዳጅ!!ስልፍ ቀረ‼️

በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በነዳጅ ማድያዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ሰዓታትን በሰልፍ ላይ እንደሚያጠፉ የከተማዋ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።

ይህንንም ተግዳሮት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዳጅ በተሰኝው መተግበሪያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች ያለውን ሰልፍ ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች በመጅመሪያ

ነዳጅ መተግበሪያን በመክፈት
STANDBY ሚለውን ይምረጡ❗️

የመዘገቡትን መኪና ይምረጡ

ሚቀዱትን መጠንና ነዳጅ አይነት ያስግቡ፦

🚀ወድያውኑ ስታንድ ባይ ኮድ ይሰጦታል❗️
አሽከርካሪው የሚደርሰውን ኮድ ለነዳጅ ቀጂው በሚሰጥበት ወቅት መተግበሪያው ላይ የሚመጣለትን  ሙሉ መረጃ በማረጋገጥ ግብይቱን በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላል።

ይህም የነዳጅ ቀጂው ሙሉ መረጃ አስገብቶ ግብይት እስኪፈጠር ደረስ ያለውን ጊዜ በመቆጠብ ከአላስፈላጊ ሰልፍ እና መንገላታት የነዳጅ ግብይቱን እንደሚያሳልጥ ተነግሯል።

በነዳጅ አፕ ይጠቀሙ ግዚዎትን ይቆጥቡ።

አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!

For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj


For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

#Nedaj #nedajapp
👍1
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
👍1
በትግራይ ክልል ህዝባዊ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ነዉ!

በዛሬዉ እለት በትግራይ ክልል ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በትናንትናው እለት ዳጉ ጆርናል በትግራይ ከሚገኙ ነዋሪዎች ሰምቶ በዛሬዉ እለት ሰላማዊ ሰልፍ አንደሚከናወን ዘግቦ ነበር።

በሰልፉ ነዋሪዉ ከአለማቀፍ ረድዔት ተቋማት የተቋረጠዉ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲጀመር ፣ ህጻናት ትምህርት እንዲጀምሩ ፣ የኤርትራ እና ሌሎች ታጣቂ ሀይሎች ከክልሉ እንዲወጡ በሰልፉ በመጠየቅ ላይ መሆኑን ከትግራይ ቴሌቪዥን ዘገባ መመልከት ችለናል።

ሰልፉ የክልሉን ርዕሰ መዲና መቀለ ጨምሮ በሽረ እንደስላሴ ፣ ዓብይ ዓዲ እና ዓዲግራት በመከናወን ላይ ይገኛል። በተጨማሪም ሰልፈኞች የአሜሪካ ፣የአዉሮፓ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አርማዎችን ይዘዉ በሰልፉ ታይተዋል።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
ከሱዳን በቀን እስከ 800 ፍልሰተኞች በመተማ በኩል ይገባሉ!

የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች፣ ካለፈው ወር ሚያዝያ ሰባት ቀን ጀምሮ፣ በካርቱም እና በሌሎች አካባቢዎች በሚያካሒዱት ግጭት ምክንያት፣ 25ነጥብ7 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች፣ አስቸኳይ ሰብአዊ ርዳታ ፈላጊዎች ኾነዋል።ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት(IOM)፣ ረቡዕ ዕለት ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በመላው ሱዳን ቢያንስ 843ሺሕ130 ሰዎች ሲፈናቀሉ፣ ወደ 259ሺሕ የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል።

ግጭቱ ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ፣ ኢትዮጵያንና ሱዳንን ወደምታገናኘው መተማ ከተማ፣ በቀን ከ700 እስከ 800 የሚደርሱ ሰዎች፣ የሱዳንን ድንበር ተሻግረው ይገባሉ። የቻይና ማዕከላዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ የኾነው ሲሲቲቪ ከአነጋገራቸው ስደተኞች መካከል አንዱ የኾነው እስማኤል ሁሴን፣ ግጭቱ ከመጀመሩ በፊት፣ እሱ እና ነፍሰ ጡር ሚስቱ፣ በካርቱም ይኖሩ እንደነበር ገልጾ፣ አለመረጋጋቱ መኖሪያ ቤታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ እንዳስገደዳቸው ይናገራል።

“እዚኽ ለመድረስ በጣም ብዙ ቀናትን ወስዶብናል። በየመንገዱ የፍተሻ ጣቢያዎች አሉ። ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ከደረስን በኋላ፣ ለሌላ ዙር የደኅንነት ፍተሻ ወደ አልቃድሪፍ ተልከን ነበር፤” የሚለው እስማኤል፣ መተማ ለመድረስ፣ ለእርሱ እና ለነፍሰ ጡር ባለቤቱ በጣም ከባድ እንደነበርና በሱዳን የነበረውን ሁሉንም ነገር በማጣቱ ሕይወትን እንደገና ከምንም መጀመር እንዳለበት ገልጿል።

በሱዳን ይሠሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያንም፣ ደኅንነታቸውን ለማረጋገጥ ሌላ አማራጭ ስላልነበራቸው ወደ ትውልድ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ከእነዚኽ አንዱ፣ በሱዳን ስደት ላይ ይኖር የነበረው ነብሱ መሐመድ ኑር አንዱ ነው።በዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት(IOM) የኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቢባቱ ዌን-ፎል እንደሚያስረዱት፣ ከሱዳን እየሸሹ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞች፣ አስቸኳይ መሠረታዊ ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ቢኾንም፣ በቂ ድጋፍ ግን እያገኙ አይደለም።

“ተፈላጊው የርዳታ መጠን እጅግ ከፍተኛ ነው። ከረጅም ጉዞ በኋላ እዚኽ መድረስ የቻሉ ሰዎች አሉ። በአስከፊ ኹኔታ ውስጥ ያሉ፣ የመጠለያ፣ የምግብ፣ የትራንስፖርት፣ የውኃ አቅርቦት እና የመጸዳጃ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ገና እየመጡ ነው። እነዚኽ አገልግሎቶች የሚያስፈልጓቸው ቢኾንም፣ ርዳታው የለም፤” ብለዋል ዌን-ፎል፡፡

የ21 ዓመቷ ሰራዌይን እድሪስ አሌ፣ ገና መተማ ከተማ መድረሷ ነው። ቤተሰቦቿን፣ ጓደኞቿን፣ ጎረቤቶቿንና መኖሪያዋን አጥታለች። “ሰላምንና ደኅንነትን እመኛለኹ። የተኩስ ድምፅ መስማት አልፈልግም፤” የምትለው እድሪስ፣ “የሚሰማኝን ፍርሃት መርሳት ብችልና ትምህርቴን ብቀጥል ደስ ይለኛል። ጤና እና ምግብ እሻለኹ፤ መኖር እፈልጋለኹ፤” ያለች ሲኾን፣ አሁን ለመለወጥ ግን፣ ምኞቷ ብቻ እንደቀራት ትናገራለች።

የሱዳን ጦር፣ በትላንትናው ዕለት፣ በዋና ከተማዪቱ ካርቱም የአየር ድብደባ ማድረጉን ነዋሪዎች ለሮይተርስ ገልጸዋል። ጦሩ ጥቃቱን የፈጸመው፣ አንድ ሳምንት የሚቆየው የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ ከመኾኑ ከሰዓታት በፊት ነው።በዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሠረት፣ እስከ አሁን በግጭቱ፣ 705 ሰዎች ሲሞቱ፣ ቢያንስ 5ሺሕ287 ጉዳት ደርሶባቸዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
👍31