YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አዲስ ነገር ከነዳጅ!!ስልፍ ቀረ‼️

በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በነዳጅ ማድያዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ሰዓታትን በሰልፍ ላይ እንደሚያጠፉ የከተማዋ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።

ይህንንም ተግዳሮት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዳጅ በተሰኝው መተግበሪያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች ያለውን ሰልፍ ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች በመጅመሪያ

ነዳጅ መተግበሪያን በመክፈት
STANDBY ሚለውን ይምረጡ❗️

የመዘገቡትን መኪና ይምረጡ

ሚቀዱትን መጠንና ነዳጅ አይነት ያስግቡ፦

🚀ወድያውኑ ስታንድ ባይ ኮድ ይሰጦታል❗️
አሽከርካሪው የሚደርሰውን ኮድ ለነዳጅ ቀጂው በሚሰጥበት ወቅት መተግበሪያው ላይ የሚመጣለትን  ሙሉ መረጃ በማረጋገጥ ግብይቱን በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላል።

ይህም የነዳጅ ቀጂው ሙሉ መረጃ አስገብቶ ግብይት እስኪፈጠር ደረስ ያለውን ጊዜ በመቆጠብ ከአላስፈላጊ ሰልፍ እና መንገላታት የነዳጅ ግብይቱን እንደሚያሳልጥ ተነግሯል።

በነዳጅ አፕ ይጠቀሙ ግዚዎትን ይቆጥቡ።

አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!

For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj


For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

#Nedaj #nedajapp
😁1
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊውን ለመለየት ሁለተኛ ዙር ድምጽ ሊሰጥ ይችላል!

በተጠባቂው የቱርክ ምርጫ ሁለቱም ዕጩዎች አሸናፊ የሚያደርጋቸውን የመራጮች ድምጽ እንዳገኙ እየገለጹ ቢሆንም፣ አሸናፊውን ለመለየት ወደ ሁለተኛ ዙር ድምጽ መስጠት ሊያመሩ ይችላሉ።ለ20 ዓመታት በሥልጣን የቆዩት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን በፓርቲያቸው ዋና ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ተጨማሪ አምስት ዓመት ለመምራት የሚያስችላቸው ድምጽ እንዳገኙ እርግጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።ተቀናቃኛቸው ከማል ኪሊዳሮግሉ ምርጫውን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ የሚጠቁሙ ምልክቶችም ታይተው ነበር።

ሆኖም ግን የመጀመሪያው ዙር ሲጠናቀቅ ያልተቆጠሩ ድምጾች በመገኘታቸው ከኤርዶዋን በታች ሆነዋል።የኤርዶዋን ጥምረት በምክር ቤት ከፍተኛውን መቀመጫ ሊያገኝም ይችላል።የቱርክ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለወራት ያህል ባደረጉት ንቅናቄ የኤርዶዋን የሥልጣን ዘመን እንዲያከትም ሲጥሩ ቆይተዋል።እአአ በ2016 የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከተካሄደ በኋላ ኤርዶዋን ሥልጣናቸውን እያራዘሙ እዚህ ደርሰዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ቲማቲም በ2 ሳምንት ውስጥ የ40 ብር የዋጋ ጭማሪ አሳየ!

በአዲስ አበባ ከተማ በአትክልትና ፍራፍሬ ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እየታየ ስለመሆኑ ቅሬታቸዉን ለብስራት ሬዲዮ ያቀረቡ ሸማቾች ገልጸዋል፡፡

ሽንኩርት በኪሎ 50 ብር ቲማቲም ከ 80 እስከ 90 ብር እየተሸጠ መሆኑን የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ በተለይ ቲማቲም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ  የ40 ብር ጭማሪ ማሳየቱን  እንዳስደነገጣቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።በአሁኑ ሰአት ገቢያቸው እና ኑሮው እየተመጣጠነ አለመሆኑ እና የሚፈልጉትን ሸምተው መኖር አለመቻላቸው ኑሮአቸውን እንዳከበደውም አክለዋል።

ሬዲዮ ጣቢያው በተለያዩ የገበያ ስፍራዎች ተዘዋውሮ ለማየት እንደሞከረው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ከመኖሩ ባሻገር የቲማቲም አቅርቦቱ ከእለት እለት እየቀነሰ መሆኑን ሃሳባቸውን ከሰጡ ነጋዴዎች ለመገንዘብ ተችሏል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
አሁን ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ስጋት ምክንያት ለቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል አባላት ለወራት ያልተከፈለ ደሞዝ በወቅቱ መክፈል እንዳልተቻለ ተገለጸ፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጉዳት ደርሶባቸው በአዲስ አበባ ለሚገኙ የቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል የጦር ቁስለኞች ለወራት ያልተከፈላቸውን ደሞዝ ማድረስ እንዳልተቻለ የገለጹት በቀድሞ የአማራ ልዩ ሃይል የጤና መምሪያ ሰው ሃብት አስተዳደር ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ሽታውዓለም አሰጋ ናቸው፡፡

ከባህር ዳር እስከ አዲስ አበባ የትራንስፖርት በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የፋይናንስ ባለሙያዎችን ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ በመላክ ለአባላቱ ደሞዝ መክፈል አልተቻለም ብለዋል፡፡
ለአንዳንድ አባላት በመተማመኛ እና በሂሳብ ቁጥራቸው ለወራት ያልገባላቸውን ደሞዝ መክፈል መቻሉን ገልጸው ተንቀሳቅሰው የሂሳብ ደብተር መክፈት ላልቻሉ ቁስለኞች ግን የፋይናንስ አባላትን በአየር ትራንስፖርት ወደ አዲስ አበባ በመላክ ገንዘባቸውን ለማድረስ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ቁስለኞቹ በአዲስ አበባ የተለያዩ ካምፖች በቂ የህክምና አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውንም ጠቅሰው ነገር ግን ለቀላል የህክምና አገልግሎቶች ተደጋጋሚ ቀጠሮ የመስጠት ሁኔታ እንደሚስተዋልም ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሩ እየተቀረፈ እንዳለም አንስተዋል፡፡

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
ቻይና ሲሰልለኝ ያዝኩት ያለችውን አሜሪካዊ በእድሜ ልክ እስራት ቀጣች!

ቻይና ሲሰልለኝ አግኝቸዋለሁ ያለችውን የ78 ዓመት አሜሪካዊ በእድሜ ልክ እስራት ቀጣች፡፡ቻይና ኑሮውን በቋሚነት በሆንግ ኮንግ ያደረገውን ጆን ሺንግ ዋን ልዩንግ እድሜ ይፍታህ የፈረደችበት በስለላ ወንጀል ክስ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሰውዬው ከሁለት ዓመት በፊት በቻይና የጸረ-ስለላ ተቋም በቁጥጥር ስር አውሎት እንደነበር እና ፍርድ ቤቱ በስለላ ክስ ጥፋተኛ ሆኖ ስላገኘው እድሜ ልክ እስራት እንደፈረደበት አስታውቋል፡፡

የሰውዬው እስር በሁለቱ ኃያላን አገራት መካከል የተጀመረውን የንግድ ጦርነት እና ፍጥጫ የበለጠ ሊያሻክረው ይችላል የሚል ስጋት መፍጠሩም ተመላክቷል፡፡

ሁለቱ አገራት በታይዋን ጉዳይ በደቡብ ቻይና ባህር፣ በኮሮና ወረርሽኝ መነሻ እንዲሁም አሜሪካ በአየር ክልሏ አግኝታ ባፈነዳቻቸው የቻይና ሰው አልባ ፊኛዎች ምክንያት ከፍተኛ መካረር ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ!

የድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርአት ዛሬ ተፈጽሟል። የድምጻዊቷ የቀብር ስነስርዓት ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የጥበብ አፍቃሪያን በተገኙበት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል።

ድምፃዊቷ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በዓለማዊ ሙዚቃና በመንፈሳዊ መዝሙሮች አገሯንና ህዝቧን ማገልገሏ በህይወት ታሪኳ ላይ ተገልጿል።

ድምጻዊቷ የሰባት ልጆች እናት የአስር ልጆች አያትና የሰባት ልጆች ቅድመ አያት እንደነበረች ኢፕድ ዘግቧል።ድምፃዊቷ ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ባሳለፍነው ግንቦት አራት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ አይዘነጋም።

@YeneTube @FikerAssefa
በአገር አቀፍ ደረጃ ከሐምሌ ወር ጀምሮ የመብራት አገልግሎት ክፍያ በዲጂታል ይደረጋል!

በአገር አቀፍ ደረጃ ከሐምሌ ወር ጀምሮ የመብራት አገልግሎት ክፍያ በዲጂታል ሥርዓት የሚደረግ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በአዲስ አበባ ከዚህ ወር ጀምሮ የድህረ መብራት ክፍያ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ይሆናል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ እስካሁን 30 በመቶ ብቻ የሚሆን ተገልጋይ የድህረ ክፍያ በዲጂታል የክፍያ አማራጭ የሚከፍል ሲሆን በአዲስ አበባ ከዚህ ወር ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የድህረ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በዲጂታል እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡

በቀጣይም በመላ አገሪቱ የሚገኙ አገልግሎት መስጫዎች ከተያዘው ዓመት ሐምሌ አንድ ጀምሮ ድህረ ክፍያ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል አማራጭ እንዲያደርጉ ይደረጋል ብለዋል፡፡ እንደ አቶ መላኩ ገለጻ፤ አብዛኞቹ ደንበኞች የድህረ ክፍያ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡

[ኢፕድ]
@YeneTube @FikerAssefa
በቤንች ወረዳ የገዛ ልጇን በገጀራ ቆራሪጣ የገደለች ተጠርጣሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች!!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ ዞን በሼይ ቤንች ወረዳ የገዛ ልጇን በገጀራ ቆራሪጣ የገደለች ተጠርጣሪዋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላለች ።

የልጁ አባት የለም ማን ያሳድጋል በሚል ስሜት ተነሳስታ የገዛ ልጇን ልክ እንደወለደች በገጀራ ቆራሪጣ የገደለችውን ተጠርጣሪዋን እናት በቁጥጥር የሼይ ቤንች ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኢንዶክትሬነሽንና የህዝብ ግንኙነቱ ማስተባበሪያ ኃላፊ ም/ኢ/ር ደሴ ጎንደር አስታውቋል።

በትናንትናው ዕለት በጋያሸማ ቀበሌ ሳዝንስ ተብሎ በሚጠራ መንደር የወለደችውን ልጅ በገጀራ ቆራሪጣ የገደለችውን ተጠርጣሪ ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ መሠረት ክትትል በማድረግ በቁጥጥር አወለናታል ነው ያሉት።

የምርመራ ክፍል ጉዳዩን እየመረመረ እንደሚገኝ ተናግረው ሴትዮዋ ባሏ ወደ ስራ ሂደው በመጥፋቱ ልጁን ማን ያሳድጋል በማለት ተነሳስታ እንደገደለች በሰጠችው ቃል መገንዘብ ችለናል ብለዋል።

Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
በሰርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት ሙሽራው እና አባትየው ህይወታቸው አለፈ!

በምዕራብ ጎጃም አስተዳደር  ዞን በቋሪት ወረዳ ወይበኝ ቀበሌ ልዩ ቦታው በተለምዶ አነሳት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ በባህሉ በወጉ መሰረት ልጃችንን ለልጃችሁ ተባብለው ሙሽሪትና ሙሽራው ሊጣመሩ የሙሽራው ቤተሰብና የሙሽሪት ቤተሰብ በስጋ ዝምድና ሊጣመሩ ቤት ባፈራው እንደአቅም ድግስ በመደገስ የሩቁና የቅርቡ ወዳጅ ዘመድ ልጃችንን ስለምንድር ልጃችንን መርቁልን ማለት የተለመደ ስርዓትና ወግ ነው፡፡

ታዲያ በዕለተ እሁድ ከሩቁ ከቅርብ የተጠራው ቤተዘመዱ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሙሽራው መምጫ ሰዓት ደረሰ ሙሽራው ከነሚዜወቹ ደረሱ የሙሽሪት ቤተሰቦች በጣም ደስ አላቸው እልልታውን አቀለጡት ሙሽራው ሙሽሪትን በቤተሰብ አስመርቆ ወደቤቱ ሊመለስ ሲል ሞቅ ያለ ጭፈራ ሆታ ተነሳ በጭፈራው መሃል ቅልጥ ያለ የጥይት ተኩስም ተተኮሰ በድንገት ጭፈራ ሲጨፈር የነበረው ሰው ፀጥ አለ በጭፈራው መሃል በተተኮስ ጥይት ሙሽራው እና የሙሽራው አባት ወዲያውኑ ህይታቸው ያልፋል፣ አንድ የሴት ሚዜ አና ሰርጉን ለማድመቅ የተገኙ 4 ሰወች በድምሩ አምስት ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን በተደረገላቸው ህክምና ህይወታቸው መትረፉን የወረዳው የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ረ/ኢ/ር ተመስገን ሙሉነህ ተናግረዋለወ። የወንጀል ድርጊት የተሳተፉትን በቁጥጥር ስር አድርገው ምርመራ እያጣሩ መሆኑን ገልፀዋል። መረጃው የምዕ/ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
❗️የአፋልጉን ማስታወቂያ❗️
በምስሉ የምትመለከቷት ወጣት እየሩሳሌም ከተማ የምትባል ሲሆን በትላንትናው እለት ግንቦት 06' 2015 ከመኖሪያ ሰፈሯ ቄራ ጎፋ ጀርመን፤በተለምዶ ገና ትምህርት ቤት፤ አካባቢ ጠዋት ላይ ቸርች ለመሄድ እንደወጣች አልተመለሰችም።
ልጃችንን እንድታፋልጉን በእ/ር ርህራሄ እንለምናቹሃለን።
ልዩ ምልክቶች
1_ ቁመት፡ 1:50
2_መልክ፡ ቀይ
3_እድሜ፡ 25
4_ከላይ የለበሰችው፡ ሮዝ ባለ ኮፍያ ጃኬት
5_ከታች፡ ጅንስ ሱሪ
6_ጫማ፡ ጥቁር ሸራ ጫማ
7_ከፊት ጥርሷ አንዱ የወለቀ ነው
8_የአእምሮ እድገት ውስንነት ስላለባት እራሷን በደንብ አትገልፅም
የቤተሰብ ስልክ ቁጥር
1_አቶ ከተማ፡ 0911627318 (አባት)
2_ወ/ሮ አለም፡ 0911059346(ቤተሰብ)
ማንኛዉንም መረጃ በመደወል አሳዉቁን።
በማህበራዊ ድረገፆቻቹህ ሁሉ አጋሩልን።
የእነ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ የርሃብ አድማ
ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸውን ጨምሮ 40 የሚሆኑ እስረኞች የርሃብ አድማ መጀመራቸው ተነገረ

በአማራ ክልል ከልዩ ሃይል መፍረስና ፋኖን ትጥቅ ከማስፈታት ጋር ተያይዞ ለእስር የተዳረጉ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች የርሃብ አድማ መጀመራቸው ተነግሯል።

እስረኞቹ የርሃብ አድማውን ማድረግ የጀመሩት በአማራ ክልል የሚካሄደውን እስርና አፈና በመቃወም መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ለሮሃ ቲቪ ተናግረዋል።

ከዛሬ ሰኞ ግንቦት ሰባት ጀምሮ እስከ ረቡእ ግንቦት 9 የሚቀጥል መሆኑንም ነግረውናል።

በዚህም " ሽብር፣ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራችኃል እየተባለ የአማራ ሙሁራንን፣ ጋዜጠኞችንና ወጣቶችን እንዲሁም የቀን ሠራተኞችን ማሰር ይቁም" በሚል እነ ረ/ፕ ሲሳይን ጨምሮ 40 የሚሆኑ ታስረው የሚገኙ የአማራ ሙሁራንና ሌሎች እስረኞች ናቸው የርሃብ አድማውን የጀመሩት።

አድማውን አስመልክቶ ስለጉዳዩ ያውቁ እንደሆን ያናገርናቸው የእስረኞቹ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝም ጉዳዩን ከእስረኞቹ ቤተሰቦች ከሰሙ በኋላ ወደ እስር ቤት በማምራት አድማ መጀመራቸውን እንዳረጋገጡ ነግረውናል።

Via:- ሮሃ ቲቪ
@Yenetube @Fikerassefa
😁1
ደቡብ አፍሪካ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ገለልተኛ ሆና እንደምትቀጥል ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ተናገሩ!

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሀገሪቱ በዩክሬን ጦርነት ላይ ያላትን አቋም እንድትቀይ "ያልተለመደ ጫና" እየተደረገባት መሆኑን ተናግረዋል።ሳምንታዊው የስራ ማብራሪያቸዉ ላይ  ራማፎሳ እንደገለጹት በሩሲያ እና በምዕራቡ ዓለም መካከል ባለዉ የፉክክር ጉዳዮች ላይ ከአንዱ ወግና እንደማትቆም ተናግረዋል ።

ራማፎሳ እንዲህ ሊናገሩ የቻሉት በደቡብ አፍሪካ የአሜሪካ አምባሳደር ሩበን ብሪጌቲ ደቡብ አፍሪካ ገለልተኝነቷን ብታሳውቅም በድብቅ ለሩሲያ የጦር መሳሪያ ትሰጣለች ሲሉ ከከሰሱ በኋላ ነው። አምባሳደር ብሪጌቲ በታህሳስ ወር ላይ በኬፕ ታውን የባህር ሃይል ጣቢያ ላይ በሩስያ መርከብ ላይ እንደተጫኑ የአሜሪካ የስለላ ድርጅት እርግጠኛ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ራማፎሳ የቀረበዉን የአሜሪካ ክስ ለመመርመር ተስማምተዋል ነገር ግን ውንጀላውን የሚያረጋግጥ ተጨባጭ ማስረጃ የለም ሲሉ አክለዋል።

[ዳጉ ጆርናል]
@Yenetube @Fikerassefa
በቢሾፍቱ ከተማ ባለ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት አራት ፖሊሶች ተገደሉ!

ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ገደማ ላይ በምትገኘው የቢሾፍቱ ከተማ “ማንነታቸው ያልታወቁ” ታጣቂዎች ትላንት እሁድ ግንቦት 6፤ 2015 ሌሊት በፖሊስ ጣቢያ ላይ በከፈቱት ጥቃት፤ አራት የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ተገደሉ። በጥቃቱ ጉዳት የደረሰበት አንድ የፖሊስ አባል፤ አዲስ አበባ ወደሚገኘው የፖሊስ ሆስፒታል ተወስዶ በህክምና ላይ መሆኑን የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች ገልጸዋል።

በቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስር በሚገኘው የክፍለ ከተማ ሶስት ፖሊስ ጽህፈት ቤት ላይ ታጣቂዎች ተኩስ የከፈቱት፤ ሌሊት ስድስት ሰዓት ገደማ ላይ መሆኑን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል። በከተማዋ መግቢያ ላይ “ሰንሻይን” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው በዚሁ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች፤ “ማንነታቸው የማይታወቅ” መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በዚሁ አካባቢ የሚኖሩ አንድ የዓይን እማኝ፤ በትላትናው ዕለት እኩለ ለሊት ገደማ በታጣቂዎቹ እና በፖሊስ አባላቱ መካከል “ከፍተኛ ድምጽ” ያለው የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ገልጸዋል። የተኩስ ልውውጡ ለአንድ ሰዓት ገደማ ያህል የቆየ እንደነበርም ተናግረዋል። ሌላው የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው፤ በፖሊስ ጣቢያው ፊት ለፊት በሚገኘው “ያቱ ሆቴል” ተረኛ የነበሩ የጥበቃ ሰራተኞች ላይ ጭምር ተኩስ ተከፍቶባቸው ነበር ብለዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
የመሬት ሊዝ ጨረታ ከአራት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወጣ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአራት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሬት ሊዝ ጨረታ አወጣ ። ለጨረታ የቀረቡት ይዞታዎች መነሻ ዋጋ ከፍተኛው 2,213 ብር መሆኑ ታውቋል።የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓም ይፋ እንዳደረገው፣ በከተማዋ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች 297 ይዞታዎችን ለተጠቃሚዎች በሊዝ ለማስተላለፍ ጨረታ ውጥቷል።

በሊዝ ጨረታ እንዲተላለፉ የተዘጋጁት 297 ይዞታዎች አጠቃላይ ካሬ ሜትር 143 ሺህ (14 ነጥብ 3 ሄክታር) ሲሆኑ፣ ይዞታዎቹ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ናቸው ብሏል።ለጨረታ ከሚቀርቡ ቦታዎች መካከልም ከዚህ ቀደም በምደባና በጨረታ ወስደው ያላለሙና እርምጃ የተወሰዳባቸው፣ በተለያዩ ጊዜያት በህገ ወጥ መንገድ የተወረሩና ወደ መሬት ባንክ የገቡ መሬቶች እንደሚገኙበት አስታውቋል።

ለጨረታ የቀረቡት ይዞታዎች ዝቅተኛው የጨረታ መነሻ ዋጋ በካሬ ሜትር 960.21ብር ሲሆን፣ ከፍተኛ የተባለው መነሻ ዋጋ 2,213. 25 ብር መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ከግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ከግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በመገኘት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መሳተፍ እንደሚችሉ ገልጿል።

ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ይዞታ የተቀመጠውን መነሻ ዋጋ መሠረት በማድረግ ከአጠቃላይ ዋጋው 20 በመቶውን ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል።

በዚህ ጨረታ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ግለሰቦች ፣ የንግድ ማኅበራት ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆኖ መወዳደር እንደሚቻል አመልክቷል።ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ ክፍለ ከተማ አዳራሽ እንደሚከፈት አስታወቋል።

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
Are you the one?

👉  Learning Management System Developers
👉  Tech Startups & Incubators
👉  Digital Solution Providers
👉  Music Streaming Service Providers
👉  Coding Learning Centers
👉  Digital Library Service Providers
👉  Social Media Training Centers
👉  Student Tutorial Service Providers
👉  Professional Toastmaster's Clubs
👉  Student Club Association
👉  Online Education Service Providers
👉  Digital Theology Service Platforms
👉  Distance Education Learning Centers
👉  Short-term Training Service Institutes

When Yes:
Don't miss a chance to exhibit at the

Edition
5th

Event
Back to School Africa
Festival, 2023.

When
May 19 - 21/2023

Dates
Friday, Saturday, & Sunday

Duration
9am - 7pm

Visit event website👇!  
www.backtoschoolafrica.com 

Follow us on👇
Facebook and LinkedIn

Contact us
 
    ☎️ :   +251 974 08 2036
              +251 974 08 2037

With Support of
FDRE Ministry of Education

     Sponsors
Oracle Academy
Study in Japan
BUKU Digital Platform
DSTV Ethiopia
መርጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል በቲክቶክ መቷል።

የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ

👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

    ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
                   👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
          0912718883

    ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah

👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ

tiktok.com/@u0917040506_0912718883
👍1
አዲስ ነገር ከነዳጅ!!ስልፍ ቀረ‼️

በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በነዳጅ ማድያዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ሰዓታትን በሰልፍ ላይ እንደሚያጠፉ የከተማዋ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።

ይህንንም ተግዳሮት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዳጅ በተሰኝው መተግበሪያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች ያለውን ሰልፍ ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች በመጅመሪያ

ነዳጅ መተግበሪያን በመክፈት
STANDBY ሚለውን ይምረጡ❗️

የመዘገቡትን መኪና ይምረጡ

ሚቀዱትን መጠንና ነዳጅ አይነት ያስግቡ፦

🚀ወድያውኑ ስታንድ ባይ ኮድ ይሰጦታል❗️
አሽከርካሪው የሚደርሰውን ኮድ ለነዳጅ ቀጂው በሚሰጥበት ወቅት መተግበሪያው ላይ የሚመጣለትን  ሙሉ መረጃ በማረጋገጥ ግብይቱን በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላል።

ይህም የነዳጅ ቀጂው ሙሉ መረጃ አስገብቶ ግብይት እስኪፈጠር ደረስ ያለውን ጊዜ በመቆጠብ ከአላስፈላጊ ሰልፍ እና መንገላታት የነዳጅ ግብይቱን እንደሚያሳልጥ ተነግሯል።

በነዳጅ አፕ ይጠቀሙ ግዚዎትን ይቆጥቡ።

አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!

For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj


For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

#Nedaj #nedajapp