YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የትግራይ ትምህርት ቢሮ ዋልታ ኢፕድ'ን ጠቅሶ የሰራዉ ዘገባ የተሳሳተ መሆኑን አስታወቀ!

የትግራይ ትምህርት ቢሮ ዋልታ የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅትን ጠቅሶ የሰራዉ ዘገባ የተሳሳተ መሆኑን አስታዉቋል። በትናንትናው እለት የዜና ተቋሙ በሰራዉ ዘገባ በትግራይ ከ 1 ሺህ 2 መቶ በላይ ትምህርት ቤቶች ዳግም ተከፍተዋል ብሎ ነበር።

የትምህርት ቢሮዉም የወጣዉ ዜና ስህተትና መታረም የሚገባዉ ነዉ ብሏል። የተጠቀሱት አሃዛዊ መረጃዎችም ስህተት ናቸዉ ብሏል። አያይዞም 5 መቶ 52 ት/ት ቤቶች አሁንም ትምህርት አለመጀመራቸውን አስታዉቋል።

በዚህም በ 2ሺህ 4መቶ 92 አንደኛ እና ሁለተኛ ትምህርት ቤቶች ዉስጥ በምዕራብም ትግራይ 2 መቶ 22 ፣ ደቡብ ትግራይ 1 መቶ 82 ፣ሰሜን ምዕራብ ትግራይ 75 ፣ ምስራቅ ትግራይ 46 ፣መካከለኛዉ ትግራይ 12 ፣ ሰሜን ትግራይ 15 በድምሩ 5 መቶ 52 ትምህርት ቤቶች አሁንም ትምህርት እንዳልተጀመረባቸዉ ጠቅሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
91 የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ይፍ ተደረጉ

የኢትዮጵ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ለብስራት ሬዲዮ በላከው መግለጫ መሰረት በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ሳያሟሉ ተመርተው እየቀረቡ ያሉ ምርቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳስቧል፡፡

የተከለከሉት በአጠቃላይ 91 የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች መሆናቸውን የባለስልጣኑ የሕዝብ የኮሙንኬሽ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ አበራ ደመቀ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡46 ዓይነት አይኦዳይዝድ ጨው፣ 27 ዓይነት የምግብ ዘይት፣ 10 ዓይነት ከረሜላ ፣5 ዓይነት አቼቶ 2 ዓይነት የለውዝ ቅቤ እና 1 የቫኔላ ፍሌቨር ምርቶችን እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡

ባለስልጣን በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ስለማያሟሉ በተጨማሪም በቁጥጥር ወቅት የተገኙ ግኝቶች እንደሚያሳዩት ምርቶቹ በአብዛኛው በሚባል መልኩ የመጠቀሚያ ጊዜ፣የአምራች ድርጅታቸው ስም ፣አስገዳጅ ደረጃ ምልክት፣መለያ ቁጥርም ሆነ አድራሻቸው ምርቱ ላይ ያልተገለጸና የሌላቸው በመሆኑ የተነሳ ነዉ፡፡

ምርቱ ሊይዛቸው የሚገቡ ንጥረ ነገሮች በውል ለማይታወቅ በተጨማሪም ከሚመለከታቸው የጤና ተቆጣጣሪ አካላት ፍቃድ የሌላቸው በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንዳያውላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡ ለጥንቃቄ የምርቱ ዓይነትና የተገኙትን ክፍተቶች ይፋ በማድረግ ህብረተሰቡ በትኩረት ተመልክቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ባለስልጣን መስሪያቤቱ አሳስቧል፡፡ የምርቶቹን ዓይነትና አምራች ድርጅቶቹን በተመለከት ዝርዝር መረጃዉን በብስራት ሬዲዮ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መመልከት ይቻላል፡፡


የምርት ዓይነቶች እና ብራንድ ስማቸው
የምግብ ጨዉ
1. ሳባ የገበታ ጨው(Saba IODIZED Salt)
2. ንጋት የገበታ ጨው(Nigat IODIZED SALT)
3. አዲስ ብርሃን የገበታ ጨው ADDIS BERHAN IODIZED SALT
4. ሙና የገበታ ጨው(MUNA TABLE SALT)
5. ቤዝ የገበታ ጨው/BASE IODIZED SALT
6. ጉስቶ የገበታ ጨው/GUSTO IODIZED SALT
7. ማክ የገበታ ጨው/MAK IODIZED SALT
8. አባይ የገበታ ጨው/ABAY TABLE SALT
9. መስቱራ ባለ አዮዲን የተፈጨ ጨው MESTURA REFINED & IODIZED SALT
10. መነስ ጨው /MENES IODIZED SALT
11. ሙሉ የገበታ ጨው /Mulu Table Salt
12. ኢርኮ አዮዳይዝድ ጨው ERKO IODIZED SALT
13. አርዲ የገበታ ጨው/ARDI IODIZED SALT
14. ዘመን የገበታጨው/ZEMEN IODIZED SALT
15. ዘመን የገበታጨው/ZEMEN IODIZED SALT
16. ጨረቃ የገበታ ጨው/IODIZED SALT
17. ፋና የገበታጨው/Fana Table Salt
18. ዳናት የገበታጨው
19. ሶም የገበታጨው/som iodized salt
20. ጉግሳ በአዮዲን የበለፀገ የገበታጨው/GUGSA Iodised Salt
21. ሸጋ ጨው/SHEGA Iodized SALT
22. ፍዳክ የገበታ ጨው/FDAK IODIZED SALT
23. ኡሚ የገበታ ጨው/UMI IODIZED SALT
24. ጊዜ አዮዳይዝድ ጨው/GIZE IODIZED SALT
25. ባማክ የገበታ ጨው/bamak Iodized Salt
26. ማዚ የገበታ ጨዉ/MAZI IODIZED SALT
27. አዲስ የገበታ ጨዉ/ADDIS Iodized Salt
28. የገበታ ጨው/Iodized salt
29. TANA TABLE SALT/ጣና የገበታ ጨው
30. ጣና የገበታ ጨው
31. ማኢዳ የገበታ ጨው/MAEEDA IODIZED SALT
32. አሚን ጨው/Amin iodized salt
33. ሆም የገበታ ጨው/HOME IODIZED SALT
34. ጂኤም የገበታ ጨው/GM IODIZED SALT
35. ገዳ አዮዳይዝድ የታጠበ የገበታ ጨው/ GEDA IODIZED SALT
36. ዛማ አዮዳይዝድ የታጠበ ባለ አዮዲን ጨው /ZAMA SALT
37. ሶሲ የአዮዲን ጨው/Sosi Iodized Salt
38. ብቁ የገበታ ጨው/Biku iodized salt
39. H.T.F TABLE SALT /ኤች.ቲ.ኤፍ
40. AFRAN Iodized Salt
41. ኤምሬት ጨው/Emirate IODIZED SALT
42. ስፔሻል የገበታ ጨው/Special Iodized Salt
43. ሊያ የገበታ ጨው/ LIYA IODIZED SALT
44. አፊ ጨው/AFI IODIZED SALT
45. ዩስራ ጨው/ YUSERA SALT
46. ቡዜ የገበታጨው/BUZE IODIZED SALT

የምግብ ዘይት
1. ነጃ ንጹህ የምግብ ዘይት/ NEJA Pure Edible Oil
2. ረና ንጹህ የምግብ ዘይት/ Rina Edible Pure Food Oil
3. የኛ ንጹህ የምግብ ዘይት/Yegna Pure Edible Oil
4. ኑራ ንጹህ የምግብ ዘይት /Nura Pure Edible oil
5. ሕይወት ንጹህ የምግብ ዘይት /HIWOT Edible Cooking Oil
6. ሚድ ንጹህ የምግብ ዘይት /MID Pure Edible Oil
7. ጉና ንጹህ የኑግ የምግብ ዘይት/GUNA Pure Niger Edible Oil
8. አዲስ ንጹህ የምግብ ዘይት
9. ኑር ንጹህ የምግብ ዘይት/Nur Pure Edible Oil
10. ኑራ ንጹህ የምግብ ዘይት/NuraPure Edible Oil
11. ሶፊ ንጹህ የምግብ ዘይት/Sofi Pure Edible Oil
12. ደሴት ንጹህ የምግብ ዘይት/Deset Pure Food Oil
13. HADI COOKING OIL
14. Arif cooking oil
15. ሰነዓ ንፁህ የምግብ ዘይት /Senea pure food oil
16. ቃል ንፁህ የምግብ ዘይት/Kale Pure Food Oil
17. ናዲ የተጣራ ንጹህ የምግብ ዘይት/ Nadi pure food oil
18. ሰላም ንፁህ የምግብ ዘይት/Selam pure food oil
19. ኑኑ ንፁህ የምግብ ዘይት /Nunu pure food oil
20. MIFTAH pure food oil
21. ቤላ የተጣራ የኑግ ዘይት/BELLA Pure Niger Oil
22. ጣዝማ ንፁህ የምግብ ዘይት
23. ሚና ንፁህ የምግብ ዘይት
24. ብሌን ንፁህ የምግብ ዘይት/Blen Pure Edible Oil
25. ደስታ የተጣራ የኑግ ዘይት
26. ሐዲ የተጣራ የምግብ ዘይት
27. ሳራ የኑግ የምግብ ዘይት/Sara Niger Oil

የከረሚላ ምርቶች
1. ማሂ ከረሚላ/Mahi candy
2. ኢላላ ጣፋጭ ከረሚላ/Elaala sweet candy
3. ፋፊ ሎሊፖፐ/Fafi lolipop
4. ኢላላ ሎሊፖፕ ቢግ ጃር/Elaala lolypop big jar
5. ኮከብ ከረሚላ/KOKEB candy
6. ከረሚላ
7. ከረሚላ
8. ኤም ቲ ሎሊፖፕ/MT Loliipop
9. ኤ.ኤ ከረሚላ/A.A candy
10. ምንም ገለጭ ፁሑፍ የሌለው ከረሜላ
👍31
የአቼቶ ምርቶች
1.  ሮያል አቼቶ/Royal VINEGAR
2.  ዋልታ አቼቶ
3.  ሮያል  አቼቶ/ROYAL Vinegar
4.  ሌመን  አቼቶ/LEMEN ACETO
5.  ሸገር  አቼቶ/SHEGER ACETO
  የለዉዝ ቅቤ
1.  በእምነት ኦቾሎኒ ቅቤ/BEMNET PEANUT BUTTER
2.  ናይስ/Nice peanut butter
  የቫኔላ ፍሌቨር
1.  ምንም ገላጭ ጽሑፍ የሌለው የቫኔላ ፍሌቨር
👍1
በአዲስ አበባ የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ በመተላለፍ ከታሪፍ በላይ ሲሸጡ የተገኙ 89 የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ ተወሰደ!

መንግስት ያወጣውን የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ በመተላለፍ ከታሪፍ በላይ ሲሸጡ የተገኙ 89 የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

መንግሥት ያወጣው የሲሚንቶ የማከፋፈያና የችርቻሮ ተመን ዋጋ እንዲከበር ተደጋጋሚ ውይይት ማድረጉን ያስታወቀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ፣ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያዎችን በተላለፋ የዘርፉ ተዋንያኖች ላይ እርምጃ መውሰዱን ነው ቢሮው የገለፀው።

እርምጃው የተወሰደባቸው በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በለሚኩራ ክፍለ ከተማ የሚገኙ አለአግባብ ከተተመነው የሲሚንቶ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በላይ በመሸጥ፤ምርት በመደበቅ መሸጫ ቦታቸውን ዘግተው በመጥፋት የተገኙ ሲሚንቶ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች እንደሚገኙበት ቢሮው አመልክቷል።ቢሮው የተጀመረውን አሰራር የማስጠበቅ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት በቅርቡ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ተነገረ
ጂዳ ሳዑዲ አረብያ ውስጥ የሚነጋገሩት የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባቸው ተሰማ።

የሱዳን ጦር ሠራዊትና የፈጥኖ ደራሹ ኃይል የተኩስ አቁምና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ስምምነት ላይ ለመድረስ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ እየተነጋገሩ ቢሆንም እስከ ትናንት ድረስ የተጨበጠ ውጤት ላይ አለመድረሳቸው ነበር የተሰማው።

ሆኖም አንድ ሸምጋይን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው የሁለቱ ወገኖች ድርድር ውጤት እያሳየ ነው፤ በቅርቡም የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሌላ ምንጭም ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባቸውን ተናግረዋል።

ንግግሩ ትናንት ለሊትም ቀጥሎ እንደነበርም ገልጸዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ከጤፍ ዱቄት ጋር የተለያዩ ባዕድ ነገሮችንና የእንጨት ፍቅፋቂ (ሰጋቱራ) በመቀላቀል ለሕብረተሰቡ ሊያከፋፍሉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!

ከጤፍ ዱቄት ጋር የተለያዩ ባዕድ ነገሮችንና የእንጨት ፍቅፋቂ (ሰጋቱራ) በመቀላቀል ለህብረተሰቡ ሊያከፋፍሉ የነበሩ ግለሰቦችን በሕብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ሕገ-ወጥ ተግባሩ ሲፈፀም የነበረው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ አጠራሩ ቆሼ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ መጋዘን ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።

በመጋዘኑ ውስጥ 47 ኩንታል ምንነታቸው ያልታወቀ ስራ ስርና የእንጨት ፍቅፋቂ ሰጋ ቱራ 167 ኩንታል የጤፍ ዱቄት ተከማችቶ የተገኘ ሲሆን፤ ባዕድ ነገሩን ከዱቄቱ ጋር የሚደባልቅ መጋዘኑ ውስጥ እንዳይወጣ የተቆለፈበት ሠራተኛ በፍተሻ መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል።

ከአካባቢው ማህበረሰብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የጅማ በር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በህግ አግባብ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በሥራ ላይ የነበረውን ተጠርጣሪ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ሥር አውሎ ባደረግው ተጨማሪ ምርመራ፤ የንብረቱን ባለቤትን አፈላልጎ በመያዝ ተገቢው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚሞክሩትን ሕገ-ወጥ ነጋዴዎችን ሕብረተሰቡ ሲመለከት ለፖሊስ አጋልጦ በመስጠት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪውን አቅርቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በተጋነነ የክፍያ ጭማሪ ምክንያት ትምህርትቤቶችና ወላጆች ለሁለት ተከፈሉ!

የግል ትምህርት ቤቶች ለ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የጠየቁት ከፍተኛ የክፍያ ጭማሪ ወላጆችና ትምህርት ቤቶች ለሁለት ተከፍለዋል።

በአዲስ አበባ ካሉ 1558 የግል ትምህርት ቤቶች፣ ጭማሪውን ለማድረግ ፍላጎት ያሳዩት 1253 ትምህርት ቤቶች ቢሆኑም፣ 1031 ትምህርት ቤቶች ብቻ ከወላጆች ጋር ስምምነት ላይ ቢደርሱም 226ቱ መስማማት እንዳልቻሉ፣ የትምህርት ስልጠናና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።ባለስልጣኑ ይህንን ያስታወቀው ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ እንደገለፁት፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙት 1558 የግል ትምህርት ቤቶች 1253 የክፍያ ጭማሪ ለማድረግ ፍላጎት አሳይተዋል።226 ትምህርት ቤቶች ጋር መግባባት ላይ መድረስ ያልተቻለ ቢሆንም፣ በቀጣይ መግባባት እንዲፈጠር ባለስልጣኑ ውይይት የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ከ2016 ዓም የትምህርት ዘመን ጀምሮ ማንኛውም የግል ትምህርት ቤቶች ከወርሃዊ ክፍያ ውጭ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ አክለው ገልፀዋል።በአሁኑ ወቅት ጭማሪ ለማድረግ መግባባት ላይ የደረሱት ትምህርት ቤቶች፣ ከ20 በመቶ ጀምሮ ጭማሪ ለማድረግ መወሰናቸውን አቶ ዳኘው ተናግረዋል።

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት  በጦርነቱ ወቅት የጦርነት ቀጠና በነበረችው የአፋሯ ዳርሳጊታ(#ካሳጊታ)ላይ ተቀብሮ ዛሬ ላይ ንፁሀን እና ሮጠው ያልጠገቡ ህፃናትን፣ ሴቶችን እየፈጀ ያለውን #ፈንጂ መንግስት ምርመራ አድጎ ከአካባቢው በማፅዳት በየቀኑ የሚጠፋውን የሰው ህይወት መታደግ አለበት ለነገ የማይባል ስራ ነው።

ይድረስ ለመንግስታችን።

ከአፋር ማህበረሰብ
@Yenetube @Fikerassefa
Are you the one?

👉  Learning Management System Developers
👉  Tech Startups & Incubators
👉  Digital Solution Providers
👉  Music Streaming Service Providers
👉  Coding Learning Centers
👉  Digital Library Service Providers
👉  Social Media Training Centers
👉  Student Tutorial Service Providers
👉  Professional Toastmaster's Clubs
👉  Student Club Association
👉  Online Education Service Providers
👉  Digital Theology Service Platforms
👉  Distance Education Learning Centers
👉  Short-term Training Service Institutes

When Yes:
Don't miss a chance to exhibit at the

Edition
5th

Event
Back to School Africa
Festival, 2023.

When
May 19 - 21/2023

Dates
Friday, Saturday, & Sunday

Duration
9am - 7pm

Visit event website👇!  
www.backtoschoolafrica.com 

Follow us on👇
Facebook and LinkedIn

Contact us
 
    ☎️ :   +251 974 08 2036
              +251 974 08 2037

With Support of
FDRE Ministry of Education

     Sponsors
Oracle Academy
Study in Japan
BUKU Digital Platform
DSTV Ethiopia
መርጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል በቲክቶክ መቷል።

የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ

👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

    ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
                   👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
          0912718883

    ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah

👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ

tiktok.com/@u0917040506_0912718883
አዲስ ነገር ከነዳጅ!!ስልፍ ቀረ‼️

በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በነዳጅ ማድያዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ሰዓታትን በሰልፍ ላይ እንደሚያጠፉ የከተማዋ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።

ይህንንም ተግዳሮት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዳጅ በተሰኝው መተግበሪያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች ያለውን ሰልፍ ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች በመጅመሪያ

ነዳጅ መተግበሪያን በመክፈት
STANDBY ሚለውን ይምረጡ❗️

የመዘገቡትን መኪና ይምረጡ

ሚቀዱትን መጠንና ነዳጅ አይነት ያስግቡ፦

🚀ወድያውኑ ስታንድ ባይ ኮድ ይሰጦታል❗️
አሽከርካሪው የሚደርሰውን ኮድ ለነዳጅ ቀጂው በሚሰጥበት ወቅት መተግበሪያው ላይ የሚመጣለትን  ሙሉ መረጃ በማረጋገጥ ግብይቱን በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላል።

ይህም የነዳጅ ቀጂው ሙሉ መረጃ አስገብቶ ግብይት እስኪፈጠር ደረስ ያለውን ጊዜ በመቆጠብ ከአላስፈላጊ ሰልፍ እና መንገላታት የነዳጅ ግብይቱን እንደሚያሳልጥ ተነግሯል።

በነዳጅ አፕ ይጠቀሙ ግዚዎትን ይቆጥቡ።

አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!

For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj


For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

#Nedaj #nedajapp
👍1
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
👍1
 አንጋፋዋ ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

አንጋፋዋ ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ባደረባት ሕመም በ83 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

ድምፃዊቷ ወደ ሙዚቃው ዓለም በ1949 ዓ.ም እንደገባች እና ረጅም የሙዚቃ ጊዜዋን በፖሊስ ሠራዊት ኦርኬስትራ እንዳሳለፈች የሕይወት ታሪኳ ያስረዳል።

ሂሩት በቀለ በተለይ “ኢትዮጵያ” በሚል የተጫወተችው ዘፈን በአገር አቀፍ ደረጃ የሚታወቅ እና ትንሽ ትልቁ በሀገር ፍቅር ስሜት የሚያዜመው ነው።
@Yenetube @Fikerassefa