በደብረ ማርቆስ ከተማ የተከመረ የኤሌክትሪክ ፖል ላይ ሲጫወቱ የነበሩ 2 ሕጻናት ሕይወት አለፈ!
👉🏼ሌሎች ሦስት ሕጻናት ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታዉቋል
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 2ዐ ልዩ ቦታው እነራታ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ትናንት ሰኞ ሚያዚያ 23/2015 ከቀኑ 11 ፡3ዐ ላይ ለኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚውል የተከመረ ኮንክሪት ፖል ላይ ሲጫወቱ ከነበሩ አምስት ሕጻናት ውስጥ ፖሉ ተንከባሎ ወድቆባቸው የኹለት ሕጻናት ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ ሦስቱ በአካላቸው ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው የከተማው ፖሊስ አስታወቀ።
ሕይወታቸው ያለፈው የ15 እና የ16 ዓመት እድሜ ያላቸው ሕጻናት ሲሆኑ፤ የ6፣ የ8 እና የ1ዐ ዓመት እድሜ ያላቸው ሦስቱ ሕጻናት ደግሞ በአካላቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸው ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የ1ኛ ፖሊስ ጣቢያ ሀላፊ ኮማንደር ጌትነት መስፍን ገልጸዋል፡፡
ሕብረተሰቡ ለማህበረሰብ አገልግሎት የሚውሉ የኤክትሪክ ፖል እና መሠል አገልግሎት የሚሰጡ ማቴሪያሎች ላይ ሕፃናት እንዳይጫወቱ የማድረግ ሀላፊነትን የመወጣት እና በየአካባቢው ጉዳት የሚያደርሱ ነገሮችን ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ጉዳት በማያደርስ ሁኔታ እንዲቀመጥ ማድረግ የሚገባ መሆኑን ኮማንደር ጌትነት አሳስበዋል፡፡
[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa

በአዲስ አበባ ከግንቦት ወር ጀምሮ ያለ ዲጂታል መታወቂያ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር አይቻልም!
በአዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ያለ ዲጂታል መታወቂያ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር እንደማይቻል የከተማው የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ኤጀንሲው የሞተር ብስክሌት መንቀሳቀሻ ፈቃድን በዲጂታል መታወቂያ (Digital ID) መተግበሪያ ስራ ላይ ሊያውል በሂደት ላይ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል።
በዚህም በመዲናዋ የሚንቀሳቀሱ የሞተር ብስክሌት ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች የመንቀሳቀሻ ፈቃዳቸውን ጂፒ ኤስ ባስገጠሙበት ተቋም የዲጂታል መታወቂያውን እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲወስዱ ኤጀንሲው ጠይቋል፡፡ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሞተር ብስክሌቶች ላይ በሚደረገው ጥብቅ ቁጥጥር ያለ ዲጂታል መታወቂያ በሚንቀሳቀሱት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ዲጂታል መገናኛ ዘዴዎች እንዲከፈቱ ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጥሪ ቀረበ!
የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ ጨምሮ 47 የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በጻፉት ደብዳቤ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሀገሪቱ ተዘግቶ የሚገኘዉን የኢንተርኔት እና የዲጂታል መገናኛ ዘዴዎች እንዲከፍቱ እና ህዝብ ያለ ምንም እንቅፋት መጠቀም እንዲችል ሲሉ ጥሪ አቀረቡ።ድርጅቶቹ በጻፉት ደብዳቤ በኢትዮጵዮያ የኢንተርኔት መዘጋት ለመሳርያነት መዳረጉ እንዳሳሰባቸዉ ጠቅሰዋል።
በአማራ ክልል መጋቢት 25 ቀን የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት ተዘግቷል ከዚህ ሌላ መንግሥት የካቲት ወር ዉስጥ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች መዘጋጃታቸዉን ተጠቅሰዋል።የኢንተርኔት አገልግሎት ጥቅም ላይ እንዳይዉል መዝጋት መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶችን አለማክበር እና የጋዜጠኞችን ነፃነትና ደህንነት የሚያዳክም ነው ሲሉም ድርጅቶቹ በጻፉት ደብዳቤ አሳስበዋል።
[DW]

የተመድ ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል "በዕርዳታ ምግብ ዝርፊያ" ሳቢያ ሥራውን ለጊዜው ማቋረጡን አሶሴትድ ፕሬስ ከረድኤት ሠራተኞች መስማቱን ጠቅሶ ዘግቧል።
ድርጅቱ፣ በክልሉ የምግብ ዕርዳታ ሥርጭት ማቆሙን ከ10 ቀናት በፊት ለአጋሮቹ ማሳወቁን ዘገባው አመልክቷል። ዜና ምንጩ በጉዳዩ ዙሪያ ለድርጅቱ ላቀረብኩት ጥያቄ ምላሽ አላገኘኹም ብሏል። ድርጅቱ በክልሉ ከሽራሮ ከተማ መጋዘኑ ላይ በተፈጸመ ለ100 ሺህ ተረጂዎች የሚበቃ የሰብዓዊ ዕርዳታ ዝርፊያ ዙሪያ ምርመራ ስለመጀመሩ ከሦስት ሳምንታት በፊት ተዘግቦ እንደነበር ይታወሳል።

በአዲስ አበባ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ!
በአዲስ አበባ ከተማ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ።
የዋጋ ማስተካከያው ከሚያዝያ 24 ቀን 2015 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በዚሁ መሠረት፦
ቤንዚን ---- 69 ነጥብ 43 ብር በሊትር
ነጭ ናፍጣ ----- 71 ነጥብ 08 ብር በሊትር
ኬሮሲን ------ 71 ነጥብ 08 ብር በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ ------- 66 ነጥብ 60 ብር በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ ----------- 57 ነጥብ 84 ብር በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ ----------- 56 ነጥብ 50 ብር በሊትር ሆኗል።
Via EBC

አዲስ ነገር ከነዳጅ!!ስልፍ ቀረ‼️
በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በነዳጅ ማድያዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ሰዓታትን በሰልፍ ላይ እንደሚያጠፉ የከተማዋ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።
ይህንንም ተግዳሮት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዳጅ በተሰኝው መተግበሪያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች ያለውን ሰልፍ ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች በመጅመሪያ
✅ ነዳጅ መተግበሪያን በመክፈት
STANDBY ሚለውን ይምረጡ❗️
✅ የመዘገቡትን መኪና ይምረጡ
✅ሚቀዱትን መጠንና ነዳጅ አይነት ያስግቡ፦
🚀ወድያውኑ ስታንድ ባይ ኮድ ይሰጦታል❗️
አሽከርካሪው የሚደርሰውን ኮድ ለነዳጅ ቀጂው በሚሰጥበት ወቅት መተግበሪያው ላይ የሚመጣለትን ሙሉ መረጃ በማረጋገጥ ግብይቱን በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላል።
ይህም የነዳጅ ቀጂው ሙሉ መረጃ አስገብቶ ግብይት እስኪፈጠር ደረስ ያለውን ጊዜ በመቆጠብ ከአላስፈላጊ ሰልፍ እና መንገላታት የነዳጅ ግብይቱን እንደሚያሳልጥ ተነግሯል።
በነዳጅ አፕ ይጠቀሙ ግዚዎትን ይቆጥቡ።
✅ አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!
For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj
For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926
#Nedaj #nedajapp

ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር ፣
ላንጋኖ ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች
✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን
✔️ ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን
✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር
✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን
✔️ ዘመናዊ ኪችኖች
✔️ የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣
♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣
♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን
♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣
♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን
♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣
♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡
🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ
በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511
ይደውሉልን,ይጎበኙን!
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት

Meri Geta Tibebu
👉አስደሳች ዜና ማየት ማመን ነው
መፍትሔ ስራይ ወአይነጥላ
መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማእከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሔ ስራይ
👉ለአስም (ለሳይነስ)
👉 ለአይነጥላ ለሰው እጅ ለገርጋሪ👇
እንዲሁም የተለያዩ የጤና ችግሮች መቶ ተመርምሮ የለብወትን ችግር አውቆ መታከም ይችላሉ
እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት
አገልግሎቶቻችን ውጤት እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ።
እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት መላላክ ይቻላል
👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።
ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ
👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883
ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah
👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ

የስርቆት ተጠርጣሪዎችን መብት ጥሰዋል የተባሉ የቀበሌ ሓላፊዎች ተያዙ!
በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ፣ በርዳታ እህል ስርቆት በተጠረጠሩ አራት ወጣቶች ላይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ፈጽመዋል የተባሉ፣ ስምንት የቀበሌ አስተዳደር ሓላፊዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የያቤሎ ወረዳ ወረዳ አስታወቀ።በስርቆት ተጠርጣሪ ወጣቶቹ ላይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ፈጽመዋል በሚል የክሥ አቤቱታ የቀረበባቸው፣ የሄርወዩ ቀበሌ ሊቀ መንበር እና ሌሎች ሰባት ሰዎች በሕግ ጥላ ሥር ውለው፣ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መኾኑን፣ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጎቡ ጨና ተናግረዋል። የያቤሎ ወረዳ ፖሊስ ሓላፊም፣ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ውለው የክሥ መዝገብ መከፈቱን ተናግረዋል።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጎቡ ጨና፣ ከትላንት በስቲያ እሑድ፣ ሚያዝያ 22 ቀን 2015 ዓ.ም. በርዳታ እህል ስርቆት ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ሥር በዋሉ ወጣቶች ላይ፣ በቀበሌ ሓላፊዎቹ ተፈጸመ ስለተባለው ቅጣት ሲያስረዱ፤ “በአጭሩ የተፈጸመው ነገር፣ በያቤሎ ወረዳ ሄርወዩ ቀበሌ፣ በአንድ የእህል መጋዘን ውስጥ የነበረ 12 ኩንታል የርዳታ እህል፣ ተሰርቆ ይወጣና ለአንድ ነጋዴ ይሸጣል። በበነጋው የቀበሌው አስተዳደር፣ ተሰርቆ የተሸጠውን የርዳታ እህል፣ በነጋዴው ቤት ያገኘውና ነጋዴው ሲጠየቅ፣ እህሉን የሸጡልኝ ወጣቶች ናቸው፤ ሲል ይናገራል፡፡” ሲሉ ኹኔታውን ማስረዳት ይቀጥላሉ።
“በነጋዴው የተጠቆሙት ወጣቶች ተይዘው ሲጠየቁ፣ ድርጊቱን ስለ መፈጸማቸው ይክዳሉ፡፡ ሚያዝያ 18 ቀን ወጣቶቹ በድጋሚ ቃል እንዲሰጡ ተደርገው ቢጠየቁም ድርጊቱን መፈጸማቸውን ይክዳሉ፡፡ ለሁለተኛ ቀን ፖሊስ ጣቢያ ቢያድሩም፣ አልፈጸምንም የሚለው ቃላቸው ባለመለወጡ አሳድረው ጠዋት ላይ ለቀቋቸው።ኾኖም፣ እሑድ ጠዋት ላይ በድጋሚ ይዘው አሰሯቸው።” ብለዋል።
በመሠረቱ ወጣቶቹ፣ ቀደም ሲል ድርቅ በርትቶ በነበረበት ወቅት፣ ከአካባቢው ጤና ጣቢያ፣ የልጆች ምግብ በመስረቅ ተጠርጥረው፣ ከመካከላቸው አንደኛው ተፈርዶበት ነበር፡፡ በመኾኑም፣ ከዚኽም በፊት ተመሳሳይ ስርቆት ፈጽማችኋል፤ በሚል፣ ከቀበሌው አስተዳዳሪ ትዕዛዝ እንደወረደላቸው የተናገሩትየቀበሌ ሚሊሻዎች፣ “በቦረና ነዋሪ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አላስፈላጊ ድርጊት ፈጸሙባቸው።” ብለዋል።
በተጠርጣሪ ወጣቶቹ ላይ የተፈጸመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰትም፣ በማኅበራዊ መገናኛ ትስስሮች መሠራጨቱን ተከትሎ የመወያያ ርእስ ኾኗል። በማኅበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት የተጋራውን የወጣቶቹን ምስል፣ የአሜሪካ ድምፅ ማረጋገጥ ባይችልም፣ በምስሉ ላይ አንደኛው ወጣት በመሬት ላይ አንደኛው ደግሞ በዕንጨት ላይ፣ በገመድ እጃቸውን የፊጥኝ ታስረው ከጎናቸው የሕግ አስከባሪ ልብስ የለበሱ ግለሰቦች ይታያሉ። በዚኽ ዐይነቱ ኢሰብአዊ አያያዝ ላይ የተሳተፉ የሄልወዩ ቀበሌ አስተዳዳሪን ጨምሮ ሌሎችም ሓላፊዎች በቁጥጥር መዋላቸውን፣ አቶ ጎቡ ጨና ተናግረዋል።
የያቤሎ ወረዳ አዛዥ ኢንስፔክተር ማልቸ ጃርሶ፣ “የቀበሌ ሓላፊዎቹ መነሻ፣ ልጆቹ ከዚኽ በፊት በስርቆት የተጠረጠሩ መኾናቸው ይመስለኛል፡፡” ካሉ በኋላ “ይኹንና፣ ተጠርጣሪዎችም ቢኾኑ ይህን አግባብነት የሌለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ፈጽመዋል የተባሉ ስምንት ሰዎችን በቁጥጥር አውለናል፡፡ የተጠያቂዎቹ ቁጥር ከዚኽም ሊጨምር ይችላል፡፡ ጉዳዩን እያጣራን ነው፤ የክሥ መዝገብ ተከፍቶ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቀንበታል፤ ፍርድም የሚሰጥበት ይኾናል።” ብለዋል።የያቤሎ ወረዳ አስተዳደር፣ በተጠቀሰው ኢሰብአዊ አድራጎት የተሳተፉ፣ ቀሪ ሁለት ሰዎች መኖራቸውንና ፖሊስ እያፈላለጋቸው እንደኾነም ጠቁሟል።
[VoA]

የ2024 ዲቪ ሎተሪ እድለኞች ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ይፋ እንደምታደርግ አሜሪካ አስታወቀች!
አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺህ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ ወይም ዲቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ ታስገባለች።ባሳለፍነው ጥቅምት እና ህዳር ወራት ላይ በበይነ መረብ አማካኝነት የተሞላው የ2024 ድቪ ሎተሪ አሸናፊዎች መታወቃቸው ተገልጿል።የዲቪ 2024 ማመልከቻ የሞሉ ዜጎችም መመረጣቸውን እና አለመመረጣቸውን የፊታችን ቅዳሜ ማለትም ከሚያዚያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በትዊተር ገጹ ጽፏል።
ኢምባሲው አክሎም በዲቪ ሎተሪ ድረገጽ ላይ በመግባት አመልካቾች ያመለከቱበትን ልዩ ቁጥር ወይም ኮድ በማስገባት ማወቅ ይችላሉም ብሏል።ይህ በዚህ እንዳለም የዲቪ ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁም አሳስቧል።
ለዲቪ ሎተሪ ስለማሸነፋቸው እና አለመድረሱን አመልካቾች በራሳቸው እጃቸው ላይ ባለው ሚስጢራዊ ቁጥር ማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ እንደሆነም ተገልጿል።የ2023 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች እስከ ቀጣዩ መስከረም 2016 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንደሚስተናገዱም ኢምባሲው በመግለጫው ላይ ጠቁሟል።የ2022 ዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መከሰቱን ተከትሎ የአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት በመሻከሩ ተጎድተናል ማለታቸው ይታወሳል።
✍Alain

ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሌራ ወረርሽኝ እስከ ሰኞ ሚያዝያ 23 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ድረስ 84 ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ።
ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ከአምስት ሺህ አምስት መቶ በላይ ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ መጠቃታቸውም ተገለጿል።የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ(UN OCHA Ethiopia) በይፋዊ የትዊተር ገጹ እንዳወጣው ከሆነ፦ ከነሐሴ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ጀምሮ ከ5,500 በላይ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሌራ ተጠቅተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት «118 ከፍተኛ ተጠቂ አካባቢዎች» መለየቱን እንዲሁም «41 የኮሌራ ህክምና ማዕከላት» ማቋቋሙን ዓለም አቀፍ ድርጅቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
በዋናነት ችግሩ የታየባቸው አካባቢዎች፦ የሶማሌ፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች፤ የኦሮሚያ፤ የአፋር፤ የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ናቸው ብሏል።አጣዳፊ ተቅማጥ የሚያስከትለው የኮሌራ ወረሽኝ የሚሰራጨው በተሐዋሲው የተበከለ ምግብ አለያም መጠጥ በመውሰድ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ኦቻ አሳስቧል።ኢትዮጵያ ውስጥ በምኅጻሩ አተር (አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት) በተደጋጋሚ የጤና እክል ሆኖ እንደሚታይ ይዘገባል።አተት የኮሌራ ሌላው የማለሳለሺያ ስም ነው የሚሉም አሉ።

ኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን በመስጠት ከአለም ሀገራት የምትበልጪው 30ውን ብቻ ነው ተባለች፡፡
ዛሬ ይፋ በተደረገውና ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ወይንም ሪፖርተርስ ዊዝ ሀውት ቦርደር በየዓመቱ ይፋ በሚያደርገው የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት የአገራት ደረጃ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ከነበረችበት 114ኛ ወደ 130ኛ አሽቆልቁላለች፡፡አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ በይዘቱ ለመገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞች የተሻለ ነፃነትን የሚሰጥ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረጉ ግን ፈተና እየገጠመው ነው ተብሏል፡፡
የቅድመ ክስ እስርና ሌላውም በአዋጁ የተከለከለ ቢሆንም ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም ተብሏል፡፡በአሁኑ ሰዓት ቢያንስ 8 የመገናኛ ብዙሃን ሰራተኞች በተለያየ ወንጀል ተጠርጥረዋል ተብለው በእስር ላይ ስለመሆናቸውም ተነግሯል፡፡የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ አማካኝነት ሜይ 3 ወይንም ሚያዚያ 25 ቀን የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት እለቱን በማስመልከት ዛሬ በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ባሰናዳው ዝግጅት ላይ የፕሬስ ነፃነትን የተመለከቱ በርከት ያሉ ሀሳቦች ተነስቷል፡፡የዘንድሮ የፕሬስ ነፃነት ቀን በአለም ዙሪያ በጦርነትና የሕዝብ መፈናቀል ሰበብ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ስጋት ላይ በወደቀበት ጊዜ የሚከበር ነው ተብሏል፡፡በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተከሰቱ ጉልህ የሰብአዊ መብት ችግሮች በፀጥታ ሀይል እየተፈፀመ ያለ ፍርድ እስር ህገ-ወጥና የዘፈቀደ አፈናን በተመለከተ እንደ ሰብአዊ መብት ባሉ ተቋማት የሚወጡ ሪፖርቶችን መነሻ በማድረግ በዚህ ቀን በደንብ መነጋገር ይገባል ተብሏል፡፡
አዲሱ መገናኛ ብዙሃን አዋጅ በተመለከተ ሀሳብ ያነሱት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ አዲሱ አዋጅ ይዞ የመጣው ጠቀሜታ ብዙ ቢሆንም የዛን ያክል አዋጁን ተፈፃሚ ለማድረግ ችግር እየገጠመ ነው ብለዋል፡፡ሚዛናዊና እውነተኛ ዘገባ፣ የጋዜጠኛው ከስጋት ነፃ ሆኖ ስራውን መስራትና የህዝቡን እውነተኛ መረጃ የማግኘት መብትን በተመለከተ ሁሉንም አቻችሎ የመሄድ አስፈላጊነትን አንስተው በማብራሪያ አቅርበዋል፡፡
ዛሬም የሚዲያ ነፃነት ጉዳይ አደጋ ውስጥ ስለመሆኑ ማብራሪያ ያቀረቡት ደግሞ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነሩ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ናቸው፡፡መሻሻል አሳይቶ የነበረው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መልሶ አደጋ ውስጥ ገብቷል ብለዋል፡፡አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ በርከት ያሉ ሊጠቀሱ የሚችሉ በጎ ጎኖች ቢኖሩትም አሁንም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆን አልቻለም ብለዋል፡፡
አዋጁ የቅድመ ክስ እስርን የሚከለክል ቢሆንም አሁንም በቀጥታ ክስ ከማቅረብ ይልቅ የቅድመ ክስ እስር ተደጋግሞ እየታየ ነው ብለዋል፡፡በአሁኑ ሰዓትም በተለያየ ወንጀል ተጠርጥረዋል የተባሉ ቢያንስ 8 የሚዲያ ሰራተኞች በስር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ዶ/ር ዳንኤል የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን የማንሳቱን ያክል መገናኛ ብዙሃኑ ያለባቸውን ግዴታ አብሮ ማንሳት ተገቢ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡
የሚዲያ ነፃነት ገደብ የሌለው መብት አለመሆኑ ማወቅና መብትን ከግዴታ ጋር አቻችሎ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡በፕሬስ ነፃነት ቀኑ ላይ ጋዜጠኞች መረጃ ለማግኘት እየገጠማቸው ስላለው ችግርና ሌሎች ሀሳቦች ተነስቷል፡፡ፍርሃትና ምን ይገጥመኝ ይሆን በሚል ስጋት ውስጥ ሆኖ መስራት የመገናኛ ብዙሃኑ እና የጋዜጠኞቹ ፈተና ነው ተብሏል፡፡
የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት አማካኝነት ሁሌም ሚያዚያ 25 ቀን እንዲከበር የተወሰነው ከ31 ዓመት በፊት በናሚቢያ ዊንዶ ኦክ የተካሄደውን ጉባኤ ተከትሎ ነው፡፡የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት እለቱን የተመከተውን ጉባኤ ከዩኔስኮ ካርድ ከተባለ ተቋምና ከሌሎችም ጋር በመሆን ያሰናዳው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ዛሬ ይፋ በተደረገው የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት የአለም አገራት ደረጃ ኢትዮጵያ ከ180 አገራት 130ኛ ደረጃ መያዟን ይፋ ተደርጓል፡፡
[Sheger FM]

"በታንዛኒያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ውይይት የመጀመሪያ ምዕራፍ ዛሬ ተጠናቋል!" - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት በማስወገድ ሰላምን ለማምጣት ያለመው እና በታንዛኒያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ውይይት የመጀመሪያ ምዕራፍ ዛሬ ተጠናቋል።
ውይይቱ በአብዛኛው በአዎንታዊ መልኩ የተከናወነ ቢሆንም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ግን በዚህኛው የውይይት ምዕራፍ ስምምነት ላይ ለመድረስ አልተቻለም።
ግጭቱን በዘላቂነትና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማስቆም እንዲቻል ሁለቱም አካላት የሰላም ውይይቱን መቀጠል አስፈላጊ መሆኑ ላይ ተግባብተዋል።

ከአዲስ አበባ ፓስታዎችን የባንክ ዶክመንቶችን ፣ሽሮ ፣በርበሬ ፣ ምጥን ፣ ቂቤ የተለያዩ ለምግብነት የሚውሉ መልዕክቶችን በአዲስ ኤክስፕረስ በኩል ይላኩ ወደ ሀዋሳ ወደ ሻሸመኔ
0962627762
0980526262
T.me/deliveryhawassaexpress
0962627762
0980526262
T.me/deliveryhawassaexpress
"መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ የጀመረውን ጥቃት በአስቸኳይ ያቁም!"፦ እናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ
መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ የጀመረውን ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያቆም እናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።
ፓርቲዎቹ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ የአማራ ህዝብ መፈናቀል፣ ስደትና እንግልት እንዲቆም፣ የጋዜጠኞች፣ የምሁራንና ማኅበራዊ አንቂዎችን በግፍ ማሰር፣ መደብደብ፣ ማንገላታት እና አፍኖ-መሰወርን እንዲቆም እንዲሁም ማንነትን ማዕከል ባደረገ ሁኔታ የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች በላያቸው ላይ ማፍረስና ማባረር እንዲቆም አሳስበዋል።
የጋራ መግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦
መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ የጀመረውን ጥቃት በአስቸኳይ ያቁም!
በወቅታዊ ጉዳይ ከእናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ የተሰጠ የጋራ መግለጫ
ባለፉት 30 ዓመታት የተከተልነው “የጎሳ ፌደራሊዝም” የኢትዮጵያ ህዝብ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች በሰብዓዊነቱ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንዳያደርግ አግዶታል፡፡ የሠላምና የጸጥታ ዕጦት፣ መረን የለቀቀ ሙስና፣ አድሏዊ አሠራር፣ ዘውገኛነትና ጎጠኝነት ሥር ሠዶ የገነገነበት ዘመን ላይ እንድንደርስም አስገድዶናል። በዚህ ላይ ስለሀገሩ ኅላዌ፣ አንድነትና ሉዓላዊነት የሚገደው ዜጋ ደግሞ ተብከንካኝና ባይተዋር እንዲሆን ተፈርዶበታል። ኢትዮጵያውያን ዛሬ የምንገኝበትን የብሶት ደረጃ “አላውቅም” የሚል የገዥው ፓርቲም ሆነ የመንግሥት ባለሥልጣን ካለ ያለበትን የኃላፊነት ሥፍራ የዘነጋና እውነታውን የካደ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በከፍተኛ ችግር፣ ምስቅልቅልና ብሶት ዉስጥ ነው።
ማንኛውም ዜጋ በአገሩ ዉስጥ የህይወት ዋስትና ሊኖረው ሲገባ፣ ዛሬ ዘውግን ወይንም ሃይማኖትን፣ ወይንም ደግም ከገዥዎች ፍላጎት የተለየ ሃሳብ መግለጽን መሠረት ባደረጉ ፍረጃዎች የተነሳ በዜጎች ላይ ከባድ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል። በሠላም ወጥቶ መግባትም ፈታኝ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ በተለይም ማንነትን መሰረት ባደረገ የጥላቻ እሣቤ የአማራ ህዝብ ለመፈናቀል፣ ስደትና እንግልት ተዳርጓል፡፡ በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልሎች ዜጎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፣ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፡፡
ሕወሓት መራሹ ኢህአዴግ በ1983 የፖለቲካ ሥልጣን ከጨበጠበት ወቅት ጀምሮ አማሮች በጠላትነት ተፈርጀው በተደጋጋሚ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ደርሶባቸዋል፡፡ የብልጽግና መንግስትም ይህንኑ ፈለግ ተከትሎ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ጦስ የዜጎች ህይወት በሰብአዊነት መንጠፍ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጓል።
ከዚህ አኳያ የሁሉም ዜጎች ህይወት እኩል ዋጋ፣ እኩል ክብርና ዋስትና ሊያገኝ ይገባል ብለን እናምናለን። የመንግሥት ግንባር ቀደም ሃላፊነትና ሥራ የዜጎችን ህይወት መጠበቅ ሆኖ ሳለ ባለፉት አምስት አመታት የዜጎች ህይወት በእየለቱ ሲቀጠፍ መንግስት ያሳየው ዳተኝነት አሳፋሪ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጡ ሰሞን የነበረው የለውጥ ፍላጎትና ጠንካራ ትግል የተወሰነ ለውጥ መሣይ ብልጭታ በመፍጠሩ፣ ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት ለመግለጥ የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። “ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ይቻላል” የሚል ተስፋም አጭሮ ነበር። ይሁን እንጂ “ላም አለኝ በሰማይ …” በሆነ መልኩ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ተክዶ በተለመደው መልኩ በጎሳ ስሁት ትርክት ውስጥ የምትታሽ ሀገርና ሥርዓት ውስጥ እንድንኖር ተገደናል፡፡
ጋዜጠኞች፣ ምሁራንና ማኅበራዊ አንቂዎች፣ በተናገሩትና በጻፉት ህግን ጥሰው ከሆነ በፍርድ ቤት እንደሚጠየቁ እናውቃለን፡፡ ከዚህ ውጭ በሆነ መልኩ ዜጎችን በግፍ ማሰር፣ መደብደብ፣ ማንገላታት እና አፍኖ-መሰወርን ግን ምን አመጣው?
በቅርቡ ዳግም ጅምላ እስሩ መፈናቀሉ ግድያውና አፈናው የበረታው በአማራው ህዝብ ላይ መሆኑ ምሬትና ብሥጭት እንዲጨምር አድርጓል። በአገራችን ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሣይቀር ማንነትን ማዕከል ባደረገ ሁኔታ ማፈናቀልና ማሣደድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
የብልጽግና መራሹ መንግሥት የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች በላያቸው ላይ ማፍረስና ማባረር ከጀመረ ሰነባብቷል። በተለይም የዜጎችን በአገራቸው ዉስጥ በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት በሚደፈጥጥ መልኩ አማሮች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ እየተደረጉ ለከፍተኛ ችግርና እንግልት መዳረጋቸውም አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። የአማራው ህዝብ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በመሆን በደሙና በአጥንቱ በሠራት አገር ባይተዋርና አገር አልባ ተሳዳጅ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን በግልጽ ተገንዝበናል፡፡ ከዚህ በላይ የተገለጡት እውነታዎች፣ በአማራው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ብሶቶችን እንደፈጠሩ፣ የዚህ ችግር ባለቤት በመሆን የወረራ ስልትና ፈጠራውን ያቀነባበሩ ኃይሎች ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ከዚህ ቀደም ሦስቱም ፓርቲዎች (እናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ) ቀደም ሲል የተዘረዘሩትን ጉዳዮች እየገለጡ ችግሮች እንዳይባባሱ መንግስትን ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል።
በሕወሓት እና በፌደራል መንግስት መካከል የተከናወነው ከባድ የእርስበርስ ጦርነት አገርንና ህዝብን ከፍተኛ ጉዳት ላይ ጥሏል። የትግራይን፣ የአማራን፣ የአፋርን ህዝብንም የበለጠ ጎድቶታል። ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ወገኖቻችን የጦርነቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡ በመቶ ሺ የሚቆጠሩት የአካል ጉዳተኛ ተደርገዋል፡፡ ዜጎች በገዛ አገራቸው ተፈናቃይና ስደተኛ ሆነዋል። የመሠረተ-ልማት አውታሮችና ተቋማት ወድመዋል። ህዝቡ ገና ከጦርነቱ ቁስል አላገገመም። ታዲያ ገዥው መንግስት ይህንን መራር እውነት ዘንግቶ እንዴት በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት ሊከፍት ቻለ!? ይህ አይነቱ አካሄድ አገር አፍራሽ በመሆኑ ከወዲሁ ጊዜው ሳይሄድ መንግስት እጁን ሊሰበስብ ይገባል፡፡
ነገሮች እንዲህ በተወሳሰቡ ሁኔታዎች ውስጥ እያሉ የፌዴራል መንግሥት ችግሩን በሚያባብስ መልኩ ወደ አማራ ክልል ሠራዊት አዝምቶ “ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችን መቆጣጠርና ትጥቅ ማስፈታት” በሚል ሽፋን በየቦታው በከባድ መሣሪያ ጭምር በዜጎች ላይ ተኩስ ከፍቷል። የተረጋጋና አስተማማኝ ሁኔታዎች ሳይፈጠሩ፣ ተቻኩሎ፣ በሃይል ትጥቅ ለማስፈታት መሞከር ሌላ ጦርነት ከመቀስቀስ የተለየ ውጤት የለውም።
ሠላም የተነፈጉና እየተሳደዱ ያሉ ዜጎችን፣ በቅድሚያ ትጥቅ ማስወረድ ለምን አስፈለገ? ኢትዮጵያ ከተዘፈቀችበት የጎሰኝነት አረንቋ ሳትወጣ፣ በዘውግ በተደራጁ ሃይሎች በሚመራ መንግሥት የሚወሰዱ ማናቸውም እርምጃዎች ወደ ሌላ ችግር የሚያስገቡ ናቸውና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለሆነም መንግስት በአማራ ክልል ዉስጥ የጀመረውን ህገ-ወጥ ጥቃት በአስቸኳይ አቁሞ ውይይትን መሰረት ባደረጉ አካሄዶች ብቻ ችግሮችን እንዲፈታ አጥብቀን እናሳስባለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ
ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፳፻፲፭
አዲስ አበባ

ዩክሬን ፑቲንን ለመግደል ሙከራ አድርጋለች ስትል ሩሲያ ከሰሰች!
ሩሲያ ትናንት ምሽት በሞስኮ ክሬምሊን ላይ ያነጣጠሩትን ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች መታ መጣሏን አስታውቃለች።ዩክሬን የሩሲያ ፕሬዝዳንት የሆኑትን ቭላድሚር ፑቲንን ለመግደል ሙከራ አድርጋለች ስትል ሞስኮ ወንጅላለች።በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ያልተረጋገጡ ምስሎች እንዳመላከቱት ከአነስተኛ ፍንዳታ በፊት በክሬምሊን ላይ የሚበሩ ሰው አልባ አካላት ታይተዋል።
ዩክሬን የቀረበባትን ውንጀላ በማጣጣል ከሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላት ተናግራለች። የፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ቃል አቀባይ ባለፈው አመት ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ የራሷን ግዛት ነፃ ለማውጣት ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው ብለዋል። ስማቸው ያልተገለፀ የዩክሬን ባለስልጣን እንደተናገሩት ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ “ለከፍተኛ የሽብር ቅስቀሳ እየተዘጋጀች ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።
በክሬምሊን ላይ ያነጣጠሩት ሁለቱ ሰው አልባ አውሮፕላኖች የኤሌክትሮኒክ ራዳር ንብረቶች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ሩሲያ ተናግራለች። የፑቲን ቃል አቀባይ በወቅቱ ክሬምሊን ውስጥ እንዳልነበሩ ተናግረዋል.።ክረምሊን ባወጣው መግለጫ “ትላንት ምሽት የዩክሬን አገዛዝ በሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የክሬምሊን መኖሪያ ላይ ሰው አልባ በሆኑ የአየር ላይ ተሽከርካሪዎች ጥቃት ለማድረግ ሞክሯል” ብሏል።
[ዳጉ ጆርናል]

የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ ዋጋን ለማረጋጋት በሚታገልበት ወቅት ባለፉት 16 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የወለድ ምጣኔን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሳደገ።
የፌደራል ሪዘርቭ ቁልፍ የወለድ መጠኑን በ0.25 በመቶ ጨምሯል። ማዕከላዊ ባንክ ባለፈው መጋቢት ወር ከዋጋ ግሽበት ጋር መዋጋት ከጀመረ ወዲህ ይህ አሥረኛው የዋጋ ጭማሪ ነው።
ርምጃዎቹ በዓለም ትልቁ ኢኮኖሚ ያላት አሜሪካ ውስጥ የመበደር ወጪዎችን በከፍተኛ ሁኔታ አሳድገዋል፣ ይህም እንደ መኖሪያ ቤት ባሉ ዘርፎች ላይ መቀዛቀዝ እና በቅርብ ጊዜ ለሦስት የአሜሪካ ባንኮች ውድቀት ሚና ተጫውቷል። ይህ የዛሬው የወለድ ጭማሪ ለጊዜው የመጨረሻው ሊሆን እንደሚችል የአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ አስታውቋል።
ከፍ ያለ የወለድ ተመኖች ቤት መግዛትን፣ ንግድን ለማስፋፋት መበደር ወይም ሌላ ዕዳ (ክሬዲት ካርድ) ለመውሰድ የበለጠ ውድ ያደርገዋል። ባለስልጣናት ወለድን መጨመር የተበዳሪዎችን የመበደር ፍላጎት እንደሚቀንስ እና ዋጋዎች እንዲቀዛቀዙ ያደርጋሉ የሚል እምነት አላቸው።

የርዳታ እህል ሻጮችንም ገዢዎችንም ለመቆጣጠር እንደሚሠራ የትግራይ ክልል አስታወቀ!
በትግራይ ክልል ሲከናወን የቆየው የርዳታ ምግብ ሥርጭት እንዲቆም ከተወሰነ 20 ቀናት መቆጠራቸውን፣ የክልሉ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡ ለሥርጭቱ መቆም መንሥኤ ነው የተባለው የርዳታ እህል ሽያጭንም፣ ለማስቆም እየተሠራ መኾኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ፕሮግራም(WFP)፣ በክልሉ ለርዳታ በተለገሰው ምግብ ላይ የተፈጸመውን ምዝበራ ለማጣራት የያዘውን የውስጥ ምርመራ እያካሔደ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል የሚያሠራጨውን የርዳታ ምግብ ሥርጭት ማቋረጡን፣ አሶሽየትድ ፕሬስ የዜና ወኪል መዘገቡ ይታወቃል፡፡
በክልሉ፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ግብረ መልስ ዳይሬክቶሬት ዲሬክተር አቶ ገብረ እግዚአብሔር አረጋዊ፣ የክልሉ አስተዳደር ሲቆጣጠራቸው በነበሩ አካባቢዎች፣ የተዘረፈ የርዳታ እህል የለም፤ በማለት አስተባብለዋል፡፡
አሶሽየትድ ፕረስ የዜና ወኪል ባወጣው ዜና፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ፕሮግራም (WFP)፣ ለረኀብ ለተጋለጡ ሰዎች በተለገሰ የርዳታ ምግብ ላይ የተፈጸመውን ምዝበራ ለማጣራት የያዘውን የውስጥ ምርመራ እያካሔደ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ በትግራይ ክልል የሚያካሒደውን የርዳታ ምግብ ሥርጭት ማቋረጡን፣ ከአራት የረድኤት ሠራተኞች ያገኘውን መረጃ መሠረት በማድረግ ዘግቧል፡፡
በዚኹ ጉዳይ ላይ፣ በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ግብረ መልስ ዳይሬክቶሬት ዲሬክተር አቶ ገብረ እግዚአብሔር አረጋዊ፣ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራርያ፣ ወደ ክልሉ የነፍስ አድን የርዳታ እህል መግባት እንዲቆም ከተወሰነ 20 ቀናት ማለፋቸውን ገልጸዋል፡፡ በክልሉ ጦርነቱ በነበረባቸው የተለያዩ ጊዜያት፣ የርዳታ እህሎች መዘረፋቸውን ተናግረዋል፡፡
“በመጀመርያ የጦርነቱ ጊዜያት፣ የርዳታ እህል የተከማቸባቸው ብዙ መጋዘኖች ተዘርፈዋል፡፡ዛላንበሳ፣ ኩለመኸዳ፣ ዓዲግራት፣ ኢሮብ፣ ራማ፣ አኵስም፣ ዓድዋ፣ በደቡብ አቅጣጫም አላማጣ፣ ራያ አላማጣ፣ ኮረም፣ እንዲሁም ወጅራት አካባቢ ተዘርፏል ማለት ይቻላል፡፡” ያሉት አቶ ገብረ እግዚአብሔር “በመጨረሻው ጦርነት ወቅትም፣ በዓዲ ሃገራይ እና በሸራሮ፣ ከ13ሺሕ ኩንታል በላይ እህል በኤርትራ ሠራዊት ተዘርፏል፡፡” ብለዋል።
አቶ ገብረ እግዚአብሔር አያይዘው “የርዳታ እህልን ከዓላማው ውጭ ለገበያ ማዋልንና የምዝበራ ችግሮችን መፍታት፣ ለጥያቄ የማይቀርብ ጉዳይ ነው፡፡ ኾኖም፣ የትግራይ ክልል መንግሥት ያስተዳድራቸው በነበሩ የርዳታ እህል መጋዝኖች ላይ፣ አይደለም የተወረረ እና የተዘረፈ፣ በሩ እንኳን የተሰበረ መጋዘን የለም፡፡” ብለዋል።
ኤርትራ፣ ለውንጀላው ቀጥተኛ መልስ ባትሰጥም፣ ከአሁን በፊት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት ፈጽማቸዋለች በሚል የሚቀርቡባትን ክሦች ስታስተባብል ቆይታለች::
በትግራይ ክልል፣ የርዳታ ምግብ ሊደርሳቸው የሚገቡ ሰዎችን የመለየት እና የማከፋፈል ሥራ፣ ፍትሐዊነት ይጎድለዋል፡፡ ይህንም ለማስተካከል ጥረት እየተደረገ ነው፤ ሲሉ ዲሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
የነፍስ አድን የርዳታ ምግብ፣ ለምግብ ፈላጊዎች ብቻ የሚሰጥ እንጂ ለገበያ መዋል እንደማይገባው የገለጹት ዲሬክተሩ፣ በክልሉ በገበያ ላይ የርዳታ እህል እየተሸጠ መኾኑን አምነው፣ “ለገበያ የዋሉ የርዳታ ምግብ ቁጥጥር ጀምረናል፤ ለማስቆም እየሠራን ነው፤” ብለዋል፡፡
ለሰብአዊ ርዳታ የሚለገሱ ምግቦች፣ በሱቆች እና በፋብሪካዎች በብዛት በመኾኑ ትኩረት አድርገው እንዲሠሩበት ፣ በጊዜያዊ አስተዳደሩ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡ የርዳታ እህል፣ ከሌሎች ክልሎች ይልቅ በትግራይ ክልል ዋጋው ስለሚጨምር፣ ከሌሎች ክልሎችም ወደ ትግራይ ገብቶ ይሸጣል፤ ያሉት ዲሬክተሩ፣ በዚኽም የቁጥጥር ሥራ እንደሚሠራ አመልክተዋል፡፡
ይህም ሁሉ ኾኖ፣ በትግራይ ክልል የተቋረጠው የምግብ ርዳታ ሥርጭት እንዲቀጥልና ችግር ውስጥ የሚገኘው ሕዝብ ድጋፍ እንዲደረግለት፣ ክልሉ ከርዳታ ሰጪ ተቋማት ጋራ እየተወያየ መኾኑን፣ የክልሉ ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ግብረ መልስ ዳይሬክቶሬት ዲሬክተር አቶ ገብረ እግዚአብሔር አረጋዊ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በፊት፣ በትግራይ ክልል ጉብኝት ያደረጉት፣ በኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዲሬክተር ክላውድ ጂቢዳር፣ መሸጥ የማይገባቸው የርዳታ ምግቦች፥ በመቐለ እና በሽረ እንዳሥላሴ ከተሞች፣ በገበያ ላይ መታየታቸውንና የሕፃናት አልሚ ምግቦች ሳይቀሩ፣ በብዛት ለሽያጭ እየዋሉ መኾናቸውን ተናግረዋል፡፡በጉዳዩ ላይ፣ ተጨማሪ ምርመራ እንዲሚካሔድም ጠቁመዋል፡፡የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፣ ለርዳታ ፈላጊዎች የሚለገሰውን ምግብ በመሸጥ ጽዩፍ ተግባር ላይ የተሠማሩ ግለሰቦችን ለማረም፣ ርምጃ እንደሚወሰድ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
Via VoA