YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አዲስ ነገር ከነዳጅ!!ስልፍ ቀረ‼️

በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች እንዲሁም በነዳጅ ማድያዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ ብዙ ሰዓታትን በሰልፍ ላይ እንደሚያጠፉ የከተማዋ አሽከርካሪዎች ገልጸዋል።

ይህንንም ተግዳሮት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዳጅ በተሰኝው መተግበሪያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች ያለውን ሰልፍ ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች በመጅመሪያ

ነዳጅ መተግበሪያን በመክፈት
STANDBY ሚለውን ይምረጡ❗️

የመዘገቡትን መኪና ይምረጡ

ሚቀዱትን መጠንና ነዳጅ አይነት ያስግቡ፦

🚀ወድያውኑ ስታንድ ባይ ኮድ ይሰጦታል❗️
አሽከርካሪው የሚደርሰውን ኮድ ለነዳጅ ቀጂው በሚሰጥበት ወቅት መተግበሪያው ላይ የሚመጣለትን  ሙሉ መረጃ በማረጋገጥ ግብይቱን በቀላሉ ማጠናቀቅ ይችላል።

ይህም የነዳጅ ቀጂው ሙሉ መረጃ አስገብቶ ግብይት እስኪፈጠር ደረስ ያለውን ጊዜ በመቆጠብ ከአላስፈላጊ ሰልፍ እና መንገላታት የነዳጅ ግብይቱን እንደሚያሳልጥ ተነግሯል።

በነዳጅ አፕ ይጠቀሙ ግዚዎትን ይቆጥቡ።

አሁኑኑ ከ PLAY STORE እና APP STORE ያውርዱ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ!

For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj


For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

#Nedaj #nedajapp
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
Meri Geta Tibebu
👉አስደሳች ዜና ማየት ማመን ነው

መፍትሔ ስራይ ወአይነጥላ
   መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማእከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሔ ስራይ
👉ለአስም (ለሳይነስ)

👉 ለአይነጥላ ለሰው እጅ ለገርጋሪ👇

       እንዲሁም የተለያዩ የጤና ችግሮች መቶ ተመርምሮ የለብወትን ችግር አውቆ መታከም ይችላሉ

እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት
አገልግሎቶቻችን  ውጤት እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ።
እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
    መድሀኒቱን ባሉበት መላላክ ይቻላል

👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

    ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
                   👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
          0912718883

    ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah

👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ
መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ያላስማማው የሽግግር መንግሥት ምሥረታ ጉዳይ መሆኑ ተነገረ!

በፌደራሉ መንግሥት እና እራሱን በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራውና በመንግስት "ኦነግ ሸኔ" ተብሎ በሚጠራው ቡድን መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሜናዊ ምሥራቅ ዛንዚባር ሙዪኒ የባሕር ዳርቻ ለዘጠኝ ቀናት ያህል በተካሄደው ውይይት፤ ኹለቱን አካላት ካላስማሙ ጉዳዮች መካከል አንዱ የጋራ የሽግግር መንግሥት ምሥረታ መሆኑን ተሳታፊዎች ተናገሩ።የሰላም ውይይቱ ትናንት ረቡዕ ሚያዝያ 25/2015 ያለ ስምምነት መጠናቀቁን ኹለቱም ወገኖች በተናጥል ባወጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ተደራዳሪዎቹን ካላስማሟቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የጋራ የሽግግር መንግሥት መቋቋም እንደሆነ ሥማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የንግግሩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።በዚህም በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱትን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን እና ብልጽግናን ጨምሮ ሌሎች ፓለቲካ ፓርቲዎችን ያካተተ የጋራ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መጠየቁን ቢቢሲ ከተሳታፊዎች ማረጋገጡን ዘግቧል።

የጋራ የሽግግር መንግሥት ምሥረታው በፌደራል መንግሥቱ ተደራዳሪዎች በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱንም እነዚህ ምንጮች በዛንዚባር ለሚገኙት የቢቢሲ ጋዜጠኞች ተናግረዋል።ተሳታፊዎቹ እንደገለጹት፤ የሽግግር መንግሥት በዋነኝነት የሚቋቋመው በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል መተማመን እንዲኖር እና አገሪቱ ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ እንድትችል የማሻገር ኃላፊነትን እንዲወጣ ለማድረግ መሆኑ ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ፤ በትናንትናው ዕለት በመጀመሪያው ዙር በነበረው ንግግር በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልተቻለ ጠቅሶ፤ ውይይቱ በአመዛኙ ገንቢ መሆኑንም አስታውቋል።የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ውይይቱ መጠናቀቁን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ፤ ቁልፍ ብሎ በጠራቸው ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መደረስ አለመቻሉን አመልክቷል።

በዚህ በመጀመሪያው ዙር ውይይት ላይ ከተነሱ ሃሳቦች ሌላኛው በመንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል ሊደረስ የሚገባው ስምምነት በዘላቂነት ጦርነት በሚያከትም መልኩ፤ እንዲሁም ኹሉንም የሠራዊቱን ፖለቲካዊ እና የጦር ክንፉን ማካተት አለበት ተብሏል።ኬንያ እና ኖርዌይ በአሸማጋይነት በተሰየሙበት በዚህ የመጀመሪያ ውይይት ላይ ከደቡብ ኦሮሚያ አካባቢ ከሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት መካከል ኹለት ተወካዮች በዚህ ውይይት እንዲሳተፉ መደረጉም ተገልጿል።

በዚህ ውይይት ላይ የተገኙት ስድስት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ተወካዮች ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ልዑካን ሲሆኑ፤ ኹለቱ የሠራዊቱ አባላት በአሸማጋዮቹ በኩል እንዲሳተፉ መደረጉን እና በአጠቃላይም ቡድኑ በስምንት ተወካዮች መወከሉም ተሰምቷል።የኢትዮጵያ መንግሥትን በመወከል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዴዎን ጤሞቴዎስ ተደራዳሪ ሆነው መቅረባቸውንም ተገልጿል።

በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በኩል ደግሞ የታሪክ ምሁሩና በጆርጂያ ስቴት ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን፣ ከኦነግ መስራቾች አንዱና ለበርካታ ዓመታት አመራር የነበሩት ጣሃ አብዲ እንዲሁም የጦሩ አዛዥ ዋና አማካሪ የሆኑት ጂሬኛ ጉደታ ይገኙበታል።በኦሮሚያ ክልል ለዓመታት የዘለቀውና ለበርካታ ሰዎች ሞት እና መፈናቀል ምክንያት የሆነውን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት በፌደራሉ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል የመጀመሪያ ዙር ውይይት የተጠናቀቀ ሲሆን ቀጣይ ዙር መቼ ሊካሄድ እንደሚችል አልተገለጸም።

በዚህ የመጀመሪያ ውይይት የተነሱ ጉዳዮች ዝርዝር ባይጠቀሱም፣ ግጭቱን በዘላቂነት እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማስቆም እንዲቻል የሰላም ውይይቱን መቀጠል አስፈላጊ ስለመሆኑ መግባባት ላይ መደረሱን ተገልጿል።በዚህም ኹለቱም አካላት ባወጡት መግለጫ በቀጣይ ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያላቸውን ቁርጠኝነት አስታውቀዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
1
አንበሳ የከተማ አዉቶብስ ተጨማሪ 1 መቶ አውቶብሶችን በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ አስገባለሁ አለ!

አንበሳ የከተማ አዉቶብስ አገልግሎት ድርጅት በቅርቡ ተጨማሪ 1 መቶ አውቶብሶችን ወደ ሀገር ዉስጥ እንደሚያስገባ የድርጅቱ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ፍሰሃ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።የአዲስአበባ ከተማ መስተዳደር በቅርቡ 1መቶ አዳዲስ አውቶብሶችን በከፍተኛ የግዢ ዋጋ ወደ ስራ ማስገባቱ ይታወሳል። በወቅቱ ሳይገቡ የቀሩ 1 መቶ ተጨማሪ ባሶች በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት እንደሚገቡ አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ በቀጣይ ይገባሉ ሲሉ የገለጿቸዉን ተሽከርካሪዎች መቼ እንደሚገቡ ቁርጥ ቀናቸዉን ባይጠቅሱም ፤ በተለይም በረጃጅም መስመሮች ላይ ያለዉን የአውቶቡስ እጥረት እንደሚቀንሱ ጠቁመዋል።በሌላ በኩል ከሰሞኑ በተለይም በከተማ አዉቶብስ ላይ እየተፈጠረ ያለዉ የትራንስፖርት እጥረት እየተወራ እንደሚገኘዉ አንበሳ የከተማ አዉቶብስ የነዳጅ እጥረት አጋጥሞት ሳይሆን በወቅቱ እየታየ ባለዉ የአየር ንብረት ለዉጥ መንገዶች በመጨናነቃቸዉ የመጣ መሆኑን የአንበሳ የከተማ አዉቶብስ ድርጅት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ፍሰሃ ጨምረው ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ ለትግራይ ክልል የምታደርገዉን የምግብ እርዳታ ልታቆም መሆኑን ገለጸች፡፡

የአሜሪካዉ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስ ኤድ ዋና ሃላፊ በጦርነት ወደተጎዳችዉ ትግራይ ክልል የምናደርገዉን የምግብ እርዳታ እናቆማለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ድርጅቱ ወደ ትግራይ የሚላኩ የምግብ እርዳታዎችን የሚያጓጉዙ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት እንዲያቆሙ እያደረግን ነዉ ያለ ሲሆን ለዚህም በእርዳታ የሚሰጠዉ ምግብ በገበያዎች ዉስጥ ሲሸጥ መገኘቱን ነዉ እንደ ምክንያት ያነሳዉ፡፡የዩኤስ ኤድ ሃላፊ ሳማንታ ፓወር ትናንት በሰጡት መግለጫ‹‹ እርዳታዉ በጦርነት ምክንያት ክፉኛ በረሃብ ለተጎዱ የትግራይ ህዝቦች ታስቦ የተሰጠ ነዉ፡፡›› ብለዋል፡፡

‹‹ወደ ፊት የሚሻሻል ጉዳይ እስኪመጣ ድረስ በዩኤስ ኤድ አማካኝነት ወደ ትግራይ የሚላከዉን ሁሉንም ምግብ ነክ እርዳታ ለማቆም ከባድ የሆነዉን ዉሳኔ ወስነናል፡፡›› ሲሉ አክለዋል፡፡የዩኤስ ኤድ ኢንስፔክተር ጀነራል ጉዳዩን መመርመሩን ገልጸዉ እርዳታዉን ማቆሙ ትክክለኛ ዉሳኔ ሆኖ በመገኘቱ ይህን ለመወሰን መገደዳቸዉን ገልጸዋል፡፡

ሳማንታ ፓወር እንዳሉት ጉዳዩን ከፌደራል መንግስት እና ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር መወያየታቸዉን ገልጸዉ ፣ የፌደራሉም የክልሉም መሪዎች በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ለይቶ በማዉጣት እና ተጠያቂ በማድረግ ረገድ ሀላፊነታቸዉን እንደሚወጡ አሳዉቀዉኛል ብለዋል፡፡ነገሮች ከተስተካከሉ እና ወደ ቀድሞ ቦታቸዉ ከተመለሱ ዩኤስ ኤድ በድጋሚ እርዳታ የሚያስፈልጋቸዉን በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመርዳት ዝግጁ ሆኖ ይጠብቃል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ወደ ትግራይ በሚላኩ የምግብ እርዳታዎች ዙሪያ የተበራከተዉን የሌብነት ጉዳይ ለመመርመር በማሰብ እርዳታዎችን ለጊዜዉ ማቆሙን ካሳወቀ ከጥቂት ቀናት በኋላ ዩኤስ ኤድ ይህን ዉሳኔ ማስተላለፉ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ወደ 20 ሚሊየን የሚጠጉ እርዳታ ጠባቂ ዜጎችን ችግር ላይ ይጥላቸዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው በክልሉ ተፈጸመ በተባለው የዕርዳታ እህል ዝርፊያ ዙሪያ አስተዳደራቸው ምርመራ መጀመሩን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ከዓለማቀፍ የረድዔት ድርጅቶች፣ ዲፕሎማቶችና ከክልሉ ማኅበረሰብ መሪዎች የዕርዳታ እህል ላልታሰበለት ዓላማ እየዋለ ስለመኾኑ ጥቆማ እንደደረሳቸውና ድርጊቱቱ እንደተፈጸመ "በርካታ መረጃ" መኖሩን የገለጡት ጌታቸው፣ ጥፋተኛው ማንም ይኹን ማን ተጠያቂ እናደርጋለን ያሉ ሲሆን ኾኖም ኹሉም ረድኤት ድርጅቶች በክልሉ የዕርዳታ አቅርቦታቸውን እንዲቀጥሉ አቶ ጌታቸው ጠይቀዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ከቀረጥና ታክስ ነጻ የሚገቡ እቃዎች

የገንዘብ ሚኒስቴር የግል መገልገያ እቃዎች ከቀረጥና ታክስ ለጻ ሆነው ወደ ሀገር የሚገቡበት እና የሚወጡበትን ሁኔታ የሚወስን መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡

መመሪያውም ለግል መገልገያ እንዲውሉ ወደ ሀገር የሚገቡ ወይም ከሀገር የሚወጡ እቃዎችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 923/2014 በመባል ይታወቃል፡፡

በዚሁ መመሪያ መሰረት ለግል መገልገያ ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ሆነው የሚገቡ እቃዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ባሳለፍነው ቅዳሜ ማለትም በቀን #21/08/2015 ከጥዋቱ 1፡50 ላይ በእንጅባራ ዩንቨርሲቲ በተምዶ ኪዳነምህረት መግቢያ በመባል በሚታወቀው በር በኩል የዩንቨርሲቲው የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት ተማሪ የሆነችው ተማሪ ኤደን ገብሩ ከቤተክርስቲያን መልስ የግቢ መታወቂያ ( ID Card ) #አለመያዟን ተከትሎ ከዩንቨርሲቲው ተረኛ የጥበቃ ሠራተኞች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በደረሰባት አካላዊ ጥቃት ምክንያት በአሁኑ ሰዓት ተማሪዋ ከባድ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በርካታ የእንጅባራ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ጥቆማ አድርሰውናል።

ይህንን ጥቆማ በመቀበል ጉዳዩን ለማረጋገጥ ጉዳት የደረሰባት ተማሪ ጋር እንዲሁም የዩንቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረትን አናግረናል።

ተማሪ ኤደን ገብሩ ጋር በደወልንበት ጊዜ ተማሪዋ በስልክ ለማውራት አቅም ስላጠራት አጠገቧ ከነበሩት ጓደኞቿ ነው መረጃውን ያገኘነው>

ጉዳት በደረሰባት ተማሪ የእጅ ስልክ ደውለን ያገኘነውን መረጃ በአጭሩ ለመግለፅ

ተማሪዋ ወደ ቤተክርስትያን ስትሄድ የግቢ መታወቂያ ትረሳለች።

ወደ ግቢ ስትመለስ የግቢ መታወቂያ እንዳልያዘች በመንገር በመመገቢያ ካርድ ያስገቧት ዘንድ የጥበቃ ሠራተኞችን ስትጠይቅ አንዱ ጥበቃ ይገፈትራታል።

አትገፍትረኝ ብላ እጁን ለማስለቀቅ ስትሞክር በጥፊ ይመታታል። ለምን በጥፊ ትመታኛለህ ስትለው  በድጋሚ ገፍትሮ ጥሎ ጭኗ አካባቢ ይረግጣታል።

ጭኗ አካባቢ የረገጣት ህመም ሲበረታባት ሌሌች ጥበቃዎች ጣልቃ ገብተው ወደ ግቢ እንድትገባ ይፈቅዱላታል። ዶርም ገብታ መታወቂያዋን ይዛ ክስ ለመመስረት ዲሲፕሊን ቢሮ ሄዳ ሰኞ ትመለስ ዘንድ ነግረዋት ከቢሮ ስትወጣ ራሷን ሳተች።

አሁን ላይ ማህፀኗ አካባቢ የተቋጠረ ደም እንዳለ እንደተነገራትና ህመሙ ምናልባትም ቀዶ ህክምና ሊያስፈልገው እንደሚችል በእጅ ስልኳ መረጃ የሰጡን ከጎኗ ያሉ ጓደኞቿ ነግረውናል። ጓደኞቿ በተጨማሪ እንደነገሩን ከሆነ ተማሪዋ ሽንት ለመሽናትና ለመንቀሳቀስ እጅጉን እየተቸገረች እንደሆነ ገልፀው ዩንቨርሲቲው ጉዳዩን አለባብሶ ለማለፍ እንዳይሞክር ድምፅ እንሆንላት ዘንድ ጠይቀዋል።


ይህን ጉዳይ በተመለከተ የእንጅባራ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዘዳንት የሰጠን ምላሽ

ዩንቨርሲቲው መረጃው የደረሰው ቢሆንም ጉዳዩ በመጣራት ሂደት ላይ እንዳለ ፕሬዝዳንቱ ነግረውናል።

አሁን ላይ ተማሪዋ የህክምና እርዳታ እያገኘች እንዳለ ገልፀው የህመሟን ምክንያት ማለትም ተማሪዋ ያቀረበችውን ምክንያት በተጨማሪም ራሷን ስታ በምትወድቅበት ጊዜ የመታት ነገር መኖር አለመኖሩን የባለሙያ ማረጋገጫ እንደሚያስፈልግና እንደ ፀጥታም መጠየቅ ያለባቸው ነገሮች በመኖራቸው ጉዳዩን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እያጣሩ እንደሚገኙና በሚናፈሱ ወሬዎች ላይ ብቻ ተመስርቶ የግል አስተያየት መስጠት እንደማይገባ ገልፀውልናል።

@Yenetube @Fikerassefa
የጀርመን መራኄ መንግሥት አዲስ አበባ ገቡ!

የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። መራኄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ ርእሠ ብሔር፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጋር በሁለትዮሽ ፣ አካባቢያዊ እና ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።DW እንደዘገበው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ እና ጀርመን ጠንካራ ግንኙነት ያላቸውና በብዙ የኢትዮጵያ ፈታኝ ወቅቶች ጀርመን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን የቆየች አገር ናት ብለዋል።

የኢትዮጵያ እና የጀርመን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተጀመረ አንድ ምዕተ ዓመት ተሻግሯል። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ሲደርሱ የንግድ ተቋማት ባለቤቶችን እና ኃላፊዎች አስከትለው ነበር።ከጀርመን ሰፊ ቁጥር ያለው ባለሃብት የገለፁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስዓለም ጀርመን የኢትዮጵያ ሰፊ የልማት አጋር መሆኗን ጠቅሰዋል። በትምህርት እና በስልጠና ከምታደርገው ሰፊ ድጋፍ ባለፈ አሁን የሰላም ስምምነት ሒደቱ በላቀ እንዲሳካ ፣ ለመልሶ ግንባታ ሥራዎችም ድጋፍ ያደርጋሉ ብለዋል።

በሌላ በኩል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያ ላይ ችግር የሚፈጥር ነው የተባለው የሱዳን ቀውስ ክስተቱ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ነው ተብሏል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም እንዳሉት እስካሁን 61 አገሮች 7726 ዜጎቻቸውን በኢትዮጵያ በኩል ከሰዳን ማስወጣታቸውንና ከነዚህም 3517ቱ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ገልፀዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የመቀሌ ወደብና ተርሚናል ወደ አገልግሎት ተመለሰ፡፡

የመቀሌ ወደብና ተርሚናል ወደ አገልግሎት የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት (ኢባትሎአድ)የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታውቋል፡፡በነበረው የፀጥታ ችግር ተቋርጦ የቆየው የመቀሌ ወደብና ተርሚናል አገልግሎት መስጠት የመጀመሩን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡መዳረሻቸው መቀሌ ወደብና ተርሚናል ለሆኑ ገቢ ጭነቶች ከዛሬ ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከመነሻ የባሕር ወደብ ለመቀሌ ኦፕሬሽን መክፈት የሚቻል መሆኑንም ነው ድርጅቱ ለደንበኞቹ ያስታወቀው፡፡

[ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8]
@YeneTube @FikerAssefa
የሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ በላይ በሚሸጡ አከፋፋዮች እና የችርቻሮ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በከተማዋ የሚታዩ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪዎችን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በዚህ መሰረት ቢሮው በሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ  በላይ በሚሸጡ የንግድ ድርጅቶች ላይ ከማሸግ ጀምሮ ሌሎች ህጋዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስታውቋል።

ህብረተሰቡ በተለይም ሸማቾች ከተተመነው ዋጋ በላይ ከፍለው መሸመት የሌለባቸው ሲሆን፣ ጉዳዩ ሲያጋጥማቸው በነፃ የስልክ መስመር 8588 በመደወል ጥቆማ አድርሱኝ ሲል ቢሮው አሳውቋል፡፡

የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋን በተመለከተ ደርባ በ1067.36 ፣ ዳንጎቴ 1106.85፣ ሀበሻ በ1305 ብር፣ ሙገር በ1016 ብር፣ ኢትዮ 1056.80 ሳንቲም የመሸጫ ዋጋው መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።

Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
በአማራ ክልል መከላከያ ሰራዊትና ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ግጭት ውስጥ ሙግባታቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

የክልል ልዩ ሀይል መልሶ ማደራጀት በሚመለከት የተቃውሞ ሰልፍን አስተባብረዋል የተባሉ ወጣቶች እየታሰሩ መሆኑንም ኢሰመኩ ገልጿል

በአማራ ክልል የሀገር መከላከያ እና በአካባቢው ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ግጭት ውስጥ ሙግባታቸውን ኢሰመኮ ገለጸ።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው “የሕግ ማስከበር ዘመቻ”ን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።
ኮሚሽኑ ይህ ድርጊት በሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን አንድምታና ተጽእኖ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑ አስታውቋል።
ኮሚሽኑ አደረኩት ባለው ክትትል በሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት አለ ብሏል።

በተለይም ሸዋ ሮቢት፣ አርማኒያ፣ አንጾኪያ፣ ገምዛ እና ማጀቴ በመከላከያ ሰራዊት እና በአካባቢው ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥና በከባድ መሣሪያ ጭምር የታገዘ ጥቃት መኖሩን ደርሼበታለሁም ብሏል።

በዚህ የተኩስ ልውውጥ ምክንያትም በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ከመድረሱ ባለፈ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ በተለያዩ ጊዜያት መዘጋቱን እንዳረጋገጠ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የተወሰኑ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የክልል ልዩ ኃይሎችን እንደገና የማዋቀር ውሳኔን በመቃወም የተካሄዱ ሰልፎችን መርተዋል የተባሉ የተወሰኑ ወጣቶች እና ከፋኖ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች እንደታሰሩ ኢሰመኮ መረዳቱንም አስታውቋል።

በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚፈጠሩ ተጨማሪ ግጭቶች ሰብአዊ መብቶች ላይ አስከፊ ወይም ከባድ ጥሰቶች የሚያስከትሉ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም የሚመለከታቸው ወገኖች ችግሩን በሰላማዊ መንገድና በውይይት እንዲፈቱ አሳስቧል።

ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶችና ንግግሮች እንዲቆጠቡ፣ ስለደረሰው ጉዳት ሁሉ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥም ኢሰመኮ ጥቋል።

እንዲሁም በማናቸውም ሁኔታ የሚፈጸሙ እስራቶች ሕግን መሠረት ያደረጉ በተለይም “የጥብቅ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት እና ከመድልዎ ነጻ መሆን” የሚሉትን የሰብአዊ መብቶች መርሆችን ያከበሩ መሆናቸውን መንግሥት እንዲያረጋግጥ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።
@Yenetube @Fikerassefa
👍1
ቀድመው ይዘጋጁ

ከመጪው ግንቦት አንድ ጀምሮ የድረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ክፍያ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ የክፍያ ሥርዓቶች እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።


ዘመናዊ የክፍያ ሥርዓቱ በቴሌ ብር፣ ሲቢኢ ብር እንዲሁም በሞባይል ባንኪንግ አማራጮች በኩል የሚተገበር ሲሆን ደንበኞች ይህንን በመገንዘብ የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያቸውን በወቅቱ እንዲያከናውኑ አገልግሎቱ አሳስቧል።

በአገልግሎቱ የደንበኞች አገልግሎት ሽያጭ እና ቅሬታ ሰሚ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሪት ስምረት በለጠ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የድህረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ወርሃዊ የክፍያ ሥርዓትን ለማዘመን ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ስትራቴጂካዊ ትግበራ መጀመሩን አስታውሰዋል።

በዚህም፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት 72 በመቶ የሚሆኑ የድረ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ወደ ዘመናዊ የክፍያ ሥርዓት መቀላቀላቸውን ጠቅሰው አሁን የቀሩት 28 በመቶ የሚሆኑ ተጠቃሚዎች ወደ ሥርዓቱ የሚካተቱ ይሆናል ብለዋል።

በመላ አዲስ አበባ 30 የድረ-ክፍያ አገልግሎት ሰጪ ማዕከላት መኖራቸውን ጠቅሰው በመጪው የግንቦት ወር 21 የሚሆኑት የድረ-ክፍያ ማዕከላት ሙሉ በሙሉ በቀጥታ ወደ ዘመናዊ ሥርዓት ይገባሉ ብለዋል።

እንደ ሥራ አስኪያጇ ማብራሪያ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የሚገኙ ዘጠኝ የድረ-ክፍያ አገልግሎት ሰጪ ማዕከላት ለግንቦት ወር ብቻ የቢል የአከፋፈል ሥርዓትን የሚሰጡ ይሆናሉ።

የክፍያ ሥርዓቱን በዘመናዊ የአከፋፈል ሥርዓቶች ማድረጉ ደንበኞች ከዚህ ቀደም በክፍያ ማዕከላት ሲያጋጥማቸው የነበሩ መጉላላቶችን ከማስቀረቱ ባሻገር ፈጣን እና ተደራሽ የሚሆን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል።

አገልግሎቱ ከዚህ ቀደም የፍጆታ ክፍያ አገልግሎትን ይሰጥ በነበረበት የጊዜ ገደብ መሰረት የዘመናዊ የክፍያ ሥርዓቱ እንደሚሰጥ አስታውቀው ደንበኞች ወር በገባ ከ26 እስከ ቀጣይ ወር 15 ባሉ ቀናቶች ፍጆታቸውን በመክፈል ከተጨማሪ የቅጣት ወጪ ራሳቸውን እንዲታደጉም ጥሪ አቅርበዋል።

የዘመናዊ የክፍያ ሥርዓቱ ለተጠቃሚዎች ምቹና ቀላል እንዲሁም በማንኛውን አይነት የስልክ ቀፎ የሚሰራና በተለይም አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞች ወደ ማዕከላቱ በሚመጡበት ሂደት ሊያጋጥማቸው የሚችለውን እንግልት የሚያስቀር መሆኑንም አብራርተዋል።

EBC
@Yenetube @Fikerassefa
በወላይታ ዞን በድጋሚ የሚደረገው ህዝበ ውሳኔ ሰኔ 12 እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

የ“ደቡብ ኢትዮጵያ” ክልልን ለመመስረት በወላይታ ዞን በድጋሚ የሚደረገው ህዝበ ውሳኔ፤ በመጪው ሰኔ 12፤ 2015 እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ለህዝበ ውሳኔው የመራጮች ምዝገባ የሚካሄደው፤ ድምጽ በሚሰጥበት ቀን እንደሆነም ቦርዱ ገልጿል።

ምርጫ ቦርድ ይህንን ያስታወቀው በወላይታ ዞን በድጋሚ የሚካሄደውን ህዝበ ውሳኔ አስመልክቶ፤ ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 26፤ 2015 በአዲስ አበባ ሳፋየር ሆቴል እያደረገ ባለው የባለድርሻ አካላት ውይይት ላይ ነው። በዚህ ምክክር ላይ የነባሩ ደቡብ ክልል እና የወላይታ ዞን አመራሮች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።

በዚህ ውይይት ላይ በድጋሚ ለሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ፤ ቦርዱ ያዘጋጀውን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል። በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ህዝበ ውሳኔው ከአንድ ወር ከ15 ቀናት በኋላ የሚካሄድ ሲሆን ውጤቱ ደግሞ በሰኔ 19 ይገለጻል።

በዚህ ህዝበ ውሳኔ 998,00 መራጮች ይሳተፋሉ የሚል ግምቱን ያስቀመጠው ቦርዱ፤ የመራጮች ምዝገባ የሚከናወነው በድምጽ መስጫው ዕለት ሰኔ 12 መሆኑን አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
አዲስ አበባ እና ሀዋሳ ከምን ጊዜውም በላይ ተቀራርበዋል።

በምን?🏃🏃

አዲስ ኤክስፕረስ

ዶክመንቶች : የጨረታ ሰነዶች : የመኪና ስፔር ፓርቶች: እንዲሁም ፈጣን መልዕክቶችን በታማኝነት ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ ቤት ለቤት ማድረስ ጀምረናል።

ስልክ
📞  0962627762
       0980526262