YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የብልፅግና ከፍተኛ አመራር የሆኑ አቶ ግርማ የሺጥላ ተገደሉ!

የብልፅግና ከፍተኛ አመራር የሆኑ አቶ ግርማ የሺጥላ መገደላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አረጋግጠዋል።

ጠ/ ሚስትሩ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ይሄን አስፍረዋል;

"ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል።

ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው።

ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው።

ነፍስህ በሰላም ትረፍ"

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
አንድ ጊዜ ብቻ ከሂሳብ አካውንትዎ ጋር በማስተሳሰር እስከወዲያኛው ቀጥታ ከአካውንትዎ የነዳጅ ግብይት የሚፈጽሙበት!

አሁኑኑ ከ play store እና app store በማውረድ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ።

For Android: https://play.google.com/store/apps/details...
For iOS: https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በተከበሩ ግርማ የሺጥላ፣ በግል ጥበቃዎቻቸው እና በቤተሰቦቻቸው ላይ የመንግሥትና የድርጅት ሥራዎችን በአካባቢው ላይ ሠርተው ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን እየመጡ በነበረበት ሰዓት መንዝ ጓሳ ላይ በታጠቁ ኢ-መደበኛ ኃይሎች ጥቃት ተፈጽሟል፡፡

በዚህም ግርማ የሺጥላን ጨምሮ እስካሁን በደረሰን መረጃ የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ በደረሰው ልብ ሰባሪ ጥቃት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰማውን መሪር ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ይገልጻል፡፡

እንዲህ አይነት አጥፊዎች እያደረሱት ያለው መረን የለቀቀ የሽብር ድርጊት ክልሉን እየመራ ያለውን መንግሥትና መላውን ሕዝብ የበለጠ ሊያጠናክር እንጂ በጥፋት ሃይሎች ሴራና ፍላጎት የሚሳካ ምንም አይነት ተልዕኮ የለም፡፡

ስለሆነም ይህንን የሽብር ሥራ እየሠሩ ያሉ እንዲህ አይነት ኃይሎች ላይ የክልሉ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል፡፡ የጥቃቱን አድራሾችም ለሕግ ያቀርባል፡፡ ማንኛውም በእንደዚህ አይነት ድርጊት የተሳተፉ ኀይሎችንንና ተባባሪዎችን ሁሉ ከያሉበት ለሕግ በማቅረብ አስፈላጊው ፍትሕ እዲረጋገጥ ይደረጋል፡፡

በመሆኑም መላው የክልላችን ሕዝብ የተፈጠረውን የሽብር ድርጊት ከማውገዝ ጀምሮ ወንጀለኞች ለሕግ ቀርበው ፍትሕ እንዲረጋገጥ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግና እንዲረጋጋ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የጥፋት ኃይሎች ከዚህ በላይ ዓላማ ያላቸው እና ክልሉን የማፍረስ ተልዕኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በኋላ የክልሉ መንግሥት እንደማይታገስ እና ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ እናረጋግጣለን፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም

ባሕር ዳር

@YeneTube @FikerAssefa
"የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል" - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በ2015 ዓም. የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሚመለከት ውይይት አካሄዷል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡ፈተናው ልክ እንደባለፈው አመት በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

ሚኒስትሩ የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡በ2016 ዓ.ም የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸዋል ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን ገልጸዋል።

[የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት]
@YeneTube @FikerAssefa
“ከሱዳን ወደ መተማ የሚገቡ የልዩ ልዩ ሀገራት ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው” አይኦኤም

ካለፈው ዐርብ እስከ ማክሰኞ በነበሩት አምስት ቀናት ብቻ፣ ከ3ሺሕ500 በላይ የ35 ሀገራት ዜጎች፣ የሱዳኑን ግጭት በመሸሽ ወደ ኢትዮጵያ የድንበር ከተማ መተማ መግባታቸውን፣ ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (አይኦኤም) አስታወቀ።

መተማ ከደረሱት ሰዎች መካከል የሚበዙቱ፣ የቱርክ ዜጎች እንደኾኑ የጠቀሱት፣ በኢትዮጵያ የአይኦ ኤም ቃል አቀባይ ኬ ቪራይ፥ የዩጋንዳ፣ የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያ፣ የሱዳንና የቻይና ዜጎች ደግሞ እንደ ቅደም ተከተላቸው ተከታዮቹን ደረጃዎች እንደሚይዙ አመልክተዋል።

አይኦኤም፣ ወደ 700 የሚጠጉ የልዩ ልዩ ሀገራት ዜጎችን የመቀበል እና የማጓጓዝ ድጋፍ እንዲያደርግ፣ ከኤምባሲዎች በርካታ ጥያቄዎች እንደቀረቡለት የገለጹት ኬ ቪራይ፣ ያንንም እያከናወነ መኾኑን አስታውቀዋል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
Nita Hand craft and Home Decor"

እኛ ጋር፡

👉ለየት ያሉ የቤት ውስጥ ጌጦችን፣ ቀለል ያሉ በእጅ የተሠሩ የሶፋ ጠረጴዛዎችን ፣ በተለያየ ዲዛይን የተሠሩ የፊት መስታወቶችን ፣ ግድግዳ ላይ የሚሰቀሉና ጠረጴዛ ላይ የሚቀመጡ ጌጦችን ፣ የአበባ ማስቀመጫዎችን እና የመሳሰሉ የእጅ ሥራ ውጤቶችን ያገኛሉ!

👉 ቤት ለማስጌጥ፣ ለሚወዱት ሰው ለየት ያለ ሥጦታ ለመስጠት!

👉 የተፈጥሮ ውበት፣ ጥንካሬ (durability)ና ተመጣጣኝ ዋጋ!

👉 በሚፈልጉት ጊዜና ያሉበት ድረስ እናደርሳለን!

👉 ዐዲስ የመኖሪያና የንግድ ቤት ሲገቡ ፥ የቤት ውስጥ ዕቃዎትን ዲኮር ለዐይን በሚማርክ አቀማመጥ እናስተካክላለን!

👉  አሁኑኑ ይዘዙን!!

ስልክ — 0911386193
ቴሌግራም — @nitagidie
https://tttttt.me/nita3214

💎Discover the perfect addition to your home!

💎 We specialize in creating unique and handmade crafts that are sure to make your home stand out!

💎 Follow us today in our
telegram channel https://tttttt.me/nita3214

"WE CRAFT YOUR IMAGINATION"

"Nita Hand craft and Home Decor"
👍1
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
Meri Geta Tibebu
👉አስደሳች ዜና ማየት ማመን ነው

መፍትሔ ስራይ ወአይነጥላ
   መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማእከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሔ ስራይ
👉ለአስም (ለሳይነስ)

👉 ለአይነጥላ ለሰው እጅ ለገርጋሪ👇

       እንዲሁም የተለያዩ የጤና ችግሮች መቶ ተመርምሮ የለብወትን ችግር አውቆ መታከም ይችላሉ

እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት
አገልግሎቶቻችን  ውጤት እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ።
እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
    መድሀኒቱን ባሉበት መላላክ ይቻላል

👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

    ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
                   👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
          0912718883

    ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah

👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ
"የስርዓት አልበኝነት የመጨረሻ መዳረሻው ጥፋትና መጠፋፋት ነው"፦ ርዕሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በሃዘን መግለጫቸው፤ “ወንድማችን ግርማ የሺጥላ በሥራ ላይ እያለ በታጠቁ ኃይሎች ግድያ ተፈጽሞበታል፤ እንዲህ አይነት እብሪተኝነት ውድቀትን እንጅ ድልን አያጎናጽፍም፤ ጥፋትን እንጅ ሰላምን አይሰጥም” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አክለውም፤ "የሕዝባችን የቆየ መገለጫው ሥርዓታዊነት፣ ፍትሐዊነትና እኩልነት ነው። ከዚህ ታሪኩና ሥነ ልቦናው ጋር የሚቃረኑ ተግባሮች በሙሉ ሥርዓት አልበኝነት የወለዳቸው ናቸው።" ብለዋል።

"በሕግና ሥርዓት እንጅ በደቦ ፍርድ የግልም ሆነ የቡድን፤ እንዲሁም የሕዝብም ሆነ የሀገር ጥቅምና ፍላጎት ማሳካት አይቻልም። ምክንያቱም የስርዓት አልበኝነት የመጨረሻ መዳረሻው ጥፋትና መጠፋፋት ነው።" ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ፤ ስለሆነም የክልሉ ሕዝብ ዘላቂ ሰላሙን ለማረጋገጥ እንዲህ አይነት ሥርዓት አልበኝነትንና ሕገወጥ ተግባሮችን ከመንግሥት ጎን ቆሞ ሊያወግዝና ሊታገል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ርዕሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ በመግለጫቸው፤ በግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በክልሉ መንግስትና በራሳቸው ሥም የገለጹ ሲሆን፤ ለክልሉ ህዝብ፣ ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መጽናናትን ተመኝተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች ጋር መወያየታቸውን ገለፁ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ጦር ዋና አዛዥ ጀኔራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን እና ከሱዳን ፈጥኖ ደረሽ ሃይሎች ዋና አዛዥ ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስ ገጻቸው፣ ሁለቱ መሪዎች ልዩነቶቻቸውን በምክክር እንዲፈቱና ለሀገራቸው መረጋጋትን ማምጣት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይተናል ብለዋል።የሱዳን ሕዝብ ሰላም ያስፈልገዋል ሲሉ ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
አብን በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈጸመው ግድያ "የአገሪቱን ሰላምና መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል የዜሮ ድምር ፖለቲካዊ ሽብር ውጤት" መኾኑን ገልጧል።

አብን ቀደም ሲል በክልሉ አመራሮች ላይ የተፈጸመው የግድያ ወንጀል "ተሸፋፍኖ መቅረቱና ተጠያቂነት አለመስፈኑ"፣ አኹንም የአመራሮች ግድያ "ተባብሶ እንዲቀጥል" ምክንያት መኾኑን አምናለኹ ብሏል። አብን ግድያው ሳይጣራና የገዳዮች ማንነት ሳይታወቅ፣ ከድርጊቱ "ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት ሲባል በአደባባይ የሚደርጉ ፍረጃዎችንና መግለጫዎችን" እንደሚያወግዝም ገልጧል። የግድያው ፈጻሚዎች ማንነት እንዲጣራና ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ አብን ጨምሮ ጠይቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በጋሞ እና በጎፋ ዞኖች በተዛመተው ኮሌራ ሰዎች እየሞቱና በብዛት እየታመሙ ናቸው!

በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን በተከሠተው የኮሌራ ወረርሽኝ፣ ስምንት ሰዎች መሞታቸውን የዞኑ ጤና መምሪያ ሲያስታውቅ፣ በጋሞ እና በጎፋ ዞኖች፣ እስከ ትላንት ድረስ በጥቅሉ ከ430 በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን፣ የየዞኖቹ ባለሥልጣናትና ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት፣ እንዲሁም መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች፣ ድጋፍ እያደረጉ ቢኾንም፣ የመድኃኒት እና የሕክምና ቁሳቁሶች እጥረት መኖሩን አመልክተዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት(OCHA)፣ ሰሞኑን በአወጣው ሪፖርት፣ እ.አ.አ. ካለፈው ዓመት ነሐሴ ወር አንሥቶ፣ የደቡብ ክልልን ጨምሮ በሌሎች ክልሎችም በተከሠተው ወረርሽኝ፣ ከአራት ሺሕ በላይ ሰዎች መያዛቸውንና 71 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
አንድ ጊዜ ብቻ ከሂሳብ አካውንትዎ ጋር በማስተሳሰር እስከወዲያኛው ቀጥታ ከአካውንትዎ የነዳጅ ግብይት የሚፈጽሙበት!

አሁኑኑ ከ play store እና app store በማውረድ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ።

For Android: https://play.google.com/store/apps/details...
For iOS: https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926
በሱዳን ያሉ ኢትዮጰያዊያን እና የሌሎች ሀገር ዜጎችን ለማገዝ የሚረዳ ግብረ ኃይል መቋቋሙ ተገለጸ!

በሱዳን ያለውን ጦርነት ተከትሎ በሱዳን ያሉ ኢትዮጰያዊያን እና የሌሎች ሀገር ዜጎችን ለማገዝ የሚረዳ ግብረ ኃይል መቋቋሙ ተገለጸ፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ግብረ ኃይሉ ሚኒስቴሩን ጨምሮ የተለያዩ ክልሎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል::

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ጦር መሪ ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪ ጄነራል ሞሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ጋር በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አምባሳደር መለስ አለም አስታውቀዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሱዳን ያለው ጦርነት እንዲቆም እና ሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች ወደ ስለማዊ ውይይት እንዲመጡ ማሳሰባቸውንም አመላክተዋል::

@YeneTube @FikerAssefa
1
በናይሮቢ በታገተው ኢትዮጲያዊ ዙሪያ ለኬኒያ መንግስት ሁለት ጊዜ ደብዳቤ ፅፈናል ሲሉ አምባሳደር መለሰ ተናገሩ!

በኬኒያ ናይሮቢ ማንነታቸው ባልታወቁና የደንብ ልብስ በለበሱ አምስት ግለሰቦች የታገተው ኢትዮጲያዊ ሳምሶን ተክለሚካኤል ያለበት ሳይታወቅ አንድ ዓመት ከስድስት ወራት አስቆጥሯል። ይህንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ የኬንያ ኤምባሲ ላይ ክስ መመሥረታቸውን የታጋች ባለቤትና ጠበቃቸው ማስታወቃቸው ይታወሳል።

የአቶ ሳምሶን ባለቤት ወ/ሮ ሚለን ሐለፎም፣ አቶ ሳምሶን በኬንያ ፖሊሶች ታፍነው ከተወሰዱ አንድ ዓመት ከስድስት ወራት ቢሆናቸውም፣ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ስለጉዳዩ ምርመራ እያደረጉ መሆናቸውን ከመግለጽ ባሻገር፣ ያሉበትን ሁኔታ ለማሳወቅ እየተንቀሳቀሱ ያለበት ሁኔታ ቸልተኝነት ታይቶበታል ማለታቸው አይዘነጋም።

ይህንኑ ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለቀረበበት ቅሬታ ምን ምላሽ አለው በሚል ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦለታል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለአቀባይ አምባሰደር መለስ አለም ጉዳዩ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱንና አሁንም እያደረገ መሆኑን በማንሳት ለኬኒያ መንግስት ሁለት ጊዜ ደብዳቤ ጽፈናል ማለታቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።የኬኒያ መንግስት ለደብዳቤው ስለ ሰጠው ምላሽ ግን አምባሳደር መለሰ አለም ከመግለፅ ተቆጥበዋል።

በፌዴራል መንግሥትና በኦሮሚያ ክልል በማንኛውም ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ የሆኑት ጠበቃ ዳባ ጩፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ‹‹ደንበኛዬ በኬንያ በደረሰባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከአንድ ዓመት በላይ ያለበት አይታወቅም፤›› ብለው፣ መታሰራቸው ወይም መሞታቸው አለመነገሩ አሳሳቢ እንደሆነ መግለፃቸውን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።‹‹ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የመጣበት ምክንያት እነዚህ የተከሰሱ አካላት ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ነው፡፡ፍርድ ቤት በሕግ አግባብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማስገደድ የሚችል በመሆኑ እንደሚያስገድዳቸው እንጠብቃለን፤›› ሲሉም ጠበቃው ተናግረዋል፡፡

[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ/ኢባትሎ ሁለት የነዳጅ ጫኝ መርከቦቹን በአንድ ትልቅ የደረቅ ጭነት፣ አልትራማክስ መርከብ የመቀየር ሂደት ማጠናቀቁን ይፋ አደረገ፡፡

የኢባትሎ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ቺፍ ወንድወሰን ካሳ እንደተናገሩት አዲሷ ግዙፍ መርከብ በሻንጋይ የምትገኝ ሲሆን የኢባትሎ ሰራተኞች መርከቧን ተረክበዋል፡፡አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ እየተጠናቀቀ መሆኑን የተናገሩት ቺፍ ወንድወሰን መርከቧ በቅርቡ ወደ ስራ ትገባለች ብለዋል፡፡

ኢባትሎ ሁለቱን የነዳጅ መጫኛ መርከቦች በሌላ ለመቀየር ወይም ለመሸጥ ሲንቀሳቀስ ቆይቶ ነበር፡፡አሁን በቅያሬ የመጣችው መርከብ ኤም ቪ አባይ 2 የሚል ስያሜ የተሰጣት ሲሆን በመጫን አቅም ለኢባትሎ የመጀመሪያዋ ግዙፍ መርከብ ነች፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa