YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በደቡብ ክልል ሃድያ ዞን በምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ እና ሾኔ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ላለፉት ሦስት ወራት ደሞዝ ባለመግኘታችን ተቸገርን አሉ፡፡

ሠራተኞቹ በደሞዝ አጦት የተነሳ አንዳንዶቹ የሚበሉት በማጣት የቤት እቃዎቻቸውን እየሸጡ ፤ ከፊሎቹም ቤት ኪራይ መክፈል ባለመቻላቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመጠጋት መገደዳቸውን ገልጸዋል።ክፍያው ሊፈጸም ያልቻለው የቀድሞው የወረዳው አመራሮች የመንግሥት ሠራተኞችን የደሞዝ በጀት በዋስትና በማስያዝ የወሰዱሱት የአፈር ማዳበሪያ ዕዳ ባለመከፈሉ አሁን ላይ በዋስትና የተያዘው የደሞዝ በጀት ለአበዳሪው አካል ገቢ በመደረጉ ነው መባሉን ዶቼ ቬለ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የሱዳን ፕረዚደንት አልበሽር ከእስር ቤት ማምለጣቸውን ተሰማ።

ፕረዚደንት ዑመር አል በሽር ግጭቱ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ሚያዝያ 15 ቀን በፊት ወደ ወታደራዊ ሆስፒታል እንዲዛወሩ ተደርጎ እንደነበር ታውቋል።ከሳቸው ጋራ ቢያንስ 5 የቀድሞ ባለስልጣኖቻቸው የነበሩ ሲሆን በዳርፉር ለተፈጸመው እልቂት በዓለም አቀፉ የጦር መዳኛ ፍርድ ቤት የሚፈለጉት አብደልራሂም ሞሐመድ ሐሰን ይገኙበታል ተብሏል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በሱዳን ያለውን ግጭት በመሸሽ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው!

በሱዳን ያለውን ግጭት በመሸሽ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሐንስ ከተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው።ግጭቱን ሸሽተው በኢትዮጵያ ለተጠለሉ ሰዎችም በመተማ ዮሐንስ ከተማ ተገቢው እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ እንደሚያመላክተው እስካሁን የሱዳንን ጨምሮ የ23 ሀገራት ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ሕጻናት፣ ሴቶች እና አቅመ ደካሞች እንደሚገኙበትም ነው የተገለጸው፡፡

ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉ ሰዎችም በፍላጎታቸው መሰረት ከመተማ ዮሐንስ ወደ ጎንደር እና ሌሎች አካባቢዎች እየተጓጓዙ መሆኑም ተመላክቷል፡፡የመተማ ዮሐንስ ከተማ አስተዳደር፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚመለከታቸው ጸጥታ አካላትም ሰዎቹ ያለምንም እንግልት ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እንዲደርሱ ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረጉ ነው ተብሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዘመኑን የዋጁ ዝንጥ ፣ ጥንቅቅ ብለው የተሰሩ ፈርኒቸሮችን እነሆ ከ #ላንጋኖ_ፈርኒቸር

ላንጋኖ  ፈርኒቸር
ዘመናዊነትና ውበትን የተላበሱ የሀገር ወስጥ የፈርኒቸር ምርቶቻችን፡-
✔️ ለዜርና የጨርቅ ሶፋዎች

✔️ የአዋቂ እና የህጻን ልጅ አልጋዎች በተለያዩ መጠን እና ዲዛይን

✔️  ቁ/ሳጥኖች በተለያዩ ዲዛይን

✔️ የምግብ ጠረጴዛዎች በተለያየ ዲዛይን፡-በ6ወንበር,በ8ወንበር፣በ4ወንበር

✔️ የሶፋ ጠረጴዛዎች በተለያዩ መጠንና ዲዛይን

✔️  ዘመናዊ ኪችኖች

✔️  የጫማ ሸልፍ በተለያዩ መጠንና ዲዛይን…..ወዘተ ሲሆን በእርስዎ ፍላት መሰረት የሚቀርቡ አዳዲስ ዲዛይኖችን ተቀብለን እናዘጋጃለን፡፡
       
       ልዩነታችን
♦️ ከጊዜ በኃላ ማሳደስ ቢፈልጉ እንደ አዲስ አድርገን መሳደሳችን፣

♦️ ያዘዙትን ፈርኒቸር በቁርጥ ቀጠሮ ቀን እናቀርባን፣

♦️ ከኛ የገዙትን ዕቃዎችን ከረጅም ጊዜ በኃላ በአዲስ መለወጥ ሲፈልጉ እንቀበላለን

♦️ መጓጓዣና ጫኝ እስከ ቤትዎ ድረስ ከኛው መሆኑ፣

♦️ ከደንበኞች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠታችን

♦️ በማንኛውም በዓላት ወቅት 5% የዋጋ ቅናሽ የሚናደርግ መሆናችን፣

♦️ አዲስ ደንበኛ በርሶዎ በኩል ሲመጣ ማበረታች አዘጋጅተናል
ስለሆነም ለዘላቂ ተጠቃሚነት እና እርካታ የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር ምርቶችን ከእኛ ይግዙ፡፡

🛑አድራሻችን፡-ሀዋሳ
ከሳሙኤል ገበያ አዳራሽ ተሻግሮ / ዋንዛ አደባባይ ሳይደርሱ

በሰልክ ቁጥሮቻችን ፡0916581884 /0907212223/0944221511

ይደውሉልን,ይጎበኙን!       
ላንጋኖ ፈርኒቸር
በሀዋሳ የአበራ ላንጋኖ ፈርኒቸር እህት ድርጅት
Meri Geta Tibebu
👉አስደሳች ዜና ማየት ማመን ነው

መፍትሔ ስራይ ወአይነጥላ
   መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማእከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድለኒቾች ፍቱን ህክምናወችን
እንሰጣለን ።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ባለበት ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላ ሳይነካ ሳያቆስል ስራ ሳያስቆም ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረ በትን
👉ለደም ግፊት
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለሁሉም ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ ለህዝብ መስተፋቅር
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉የሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ገብያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሔ ስራይ
👉ለአስም (ለሳይነስ)

👉 ለአይነጥላ ለሰው እጅ ለገርጋሪ👇

       እንዲሁም የተለያዩ የጤና ችግሮች መቶ ተመርምሮ የለብወትን ችግር አውቆ መታከም ይችላሉ

እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት
አገልግሎቶቻችን  ውጤት እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ።
እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
    መድሀኒቱን ባሉበት መላላክ ይቻላል

👉ለበለጠ መረጃ አድራሻ ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በኮብሉ መጨረሻ ንግድ ባንኩ ላይ።

    ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ሳሪስ አደይ አበባ

👉እኒህን እና ሌሎች አገልልግሎቶችን ለማግኔት
                   👎ይደውሉ
👉☎️0917040506
          0912718883

    ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://tttttt.me/mergatah

👉ቻናሉን በመቀላቀል ሊንኳን በመጫን ጤናወ በቤትወ የባህል ህክምና የእጽዋት የህቡ ስም የጠልሰም ጥቅሞችን ይጋሩ ይፈወሱ
ዉጪ የመማር እድልዎ ከምንግዜም በላይ ቅርብ ሆኗል ፡፡
            💯 ያለምንም ቅድመ ክፍያ !! 💯

ማራኪ የትምህርት አማካሪ በአሜሪካ እና ካናዳ በመሰናዶ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ እና  ሁለተኛ ዲግሪ ዉጪ ሃገር መማር የምትችሉበን እድል አመቻችቶ እየጠበቀ ይገኛል፡፡

እርስዎም ይሄ እድል ሳያመልጥዎ ዛሬዉኑ

  💯 ያለምንም ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ፡፡ 💯

APPLY: @marakischolarshipbot
Contact: @marakiapplication
Channel @marakiconsultancy

Phone Number:  +251960612222
+251960612224
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መልዕክት‼️

በሱዳን ለዜጎች አስፈላጊው ድጋፍ እየተሰጠ ነው!

በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚገኝበት አካባቢ የውጊያ ቀጠና በመሆኑ ፣ በአካባቢው የመብራት አገልግሎት በመቋረጡ፣የምግብ ቁሳቁስ ለማግኘትም ሆነ ከኤምባሲ ወጥቶ ለመግባት ስላልተቻለ በዚህ ሁኔታ ዜጋን መርዳት ስለሚያዳግትና የዲፕሎማቶች ህልውናም አደጋ ላይ ስለሚወደቀ በኤምባሲው የተወሰኑ ሰራተኞች እዲቀሩ ተደርጎ አምባሳደሩን ጨምሮ ቀሪዎቹ ደግሞ ከገዳሪፍ ስራቸውን እያከናውኑ ይገኛሉ።ለዜጎች ሊደረግ የሚችለው ድጋፍም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራው ቡድን መቀሌ ገባ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሁሉም ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እየተመሩ ወደ መቀሌ ይሄዳሉ ባሉት መሠረት ፤በአቶ አደም ፋራህ የተመራውና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮችና ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን መቀሌ ገብቷል።

በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርስ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳና ሌሎች የአስተዳደሩ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።

ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "የሁሉም ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በፓርቲያችን ምክትል ፕሬዝዳንት እየተመሩ ወደ መቀሌ ይሄዳሉ፤ ያነቡ አይኖችን ለማበስ የተበላሹ ቦታዎችን ለመጠገን ክልሎች እንደወንድም ህዝቦች ካላቸው ለማጋራት እና ይህን የሰላም ጅማሮ በተግባር ለማስቀጠል ይጓዛሉ" ማለታቸው ይታወሳል።

በኤርፖርቱ በተደረገው አቀባበል የሐይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ተቋርጦ የቆየውን ግንኙነት ማሻሻል የሚያስችል ውይይት እንደሚደረግም ታውቋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
ነዳጅ ለመቅዳት አስበው በሚሄዱበት ማደያ ሁሉ ነዳጅ የለም ተብለው ያውቃሉ???

እነሆ ከዚህ በኋላ መንከራተት ቀረ!
የነዳጅ መተግበሪያ በአቅራቢያዎ ያሉ ነዳጅ ማደያዎችን እንዲሁም ነዳጅ መኖሩን እና አለመኖሩን አረጋግጠው መሄድ የሚያስችሎትን አማራጭ ይዝዎሎት መቷል!

ነዳጅ መተግበሪያን በመጠቀም አላስፈላጊ የነዳጅ ፍጆታዎን ይቆጥቡ!

Download the app and Register!
For Android: https://play.google.com/store/apps/details...
For iOS: https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926
ከሃሰተኛ ሰነድ ጋር በተያያዘ  በሚመጡ ዛቻ እና ማስፈራሪያ መቸገሩን የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት አስታወቀ!

ከሃሰተኛ ሰነድ ጋር በተያያዘ  ወደ ፍርድ ቤት ደርሰው በዋስትና ከሚወጡ ሰዎች መካከል  በሚመጡ ዛቻ እና ማስፈራሪያ  መቸገሩን  የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ  የሆኑት አቶ መኑር መሃመድ  ለኢቲዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

እንደ ሀላፊው ገለጻ ከሃሰተኛ ሰነዶች ጋር በተያያዘ  ክትትል እና  ፍተሻ  ሲደረግ እንደሚገኙ ና ተጠርጣሪ  ሰዎችን ወደ ህግ ወስዶ ጉዳዩ ላይ ወሳኔ እስኪሰጠው ክትትል የማድረግ ስራ እንደሚሰሩም  አቶ መኑር ነግረውናል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ  ፍርድ ቤት በፍትህ ሂደቱ አንድ ሰው ወንጀለኛ  መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ  የሚታሰርበት  መንገድ እንደሌለ አስታውሰው ሰዎቹ በዋስትና ሲለቀቁ የማስፈራራት እና ዛቻ መሰል ጉዳዮች  እየመጡ  ተቸግረናል ስራችንንም እየረበሸው ነው ብለዋል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ ነገ ይጠናቀቃል!

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ ነገ ሚያዚያ. 20/2015 ዓም ከቀኑ 11:30 ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታዉቋል።እስካሁን ያልተመዘገቡ ተፈታኝ ተማሪዎች እስከ ነገ እንዲመዘገቡ አገልግሎቱ ማሳሰቡ ተሰምቷል። በማንኛውም ምክኒያት ያልተመዘገቡ ተፈታኞችንም አገልግሎቱ ከነገ በኋላ የማያስተናግድ መሆኑን አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
አርጀንቲና የቻይና ምርቶችን ከዶላር ይልቅ በዩዋን ልትከፍል ነው!

አርጀንቲና ከዶላር ይልቅ ከቻይና ለሚገቡ ምርቶች በዩዋን መክፈል ትጀምራለች ሲል የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።ሀገሪቱ በሚያዝያ ወር ከዶላር ይልቅ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የቻይና ምርቶች በዩዋን ለመክፈል አቅዳለች።

ከዚያም በኋላ ወደ 790 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ወርሃዊ የገቢ ንግዷን በዩዋን ትከፍላለች ሲል የመንግስት ገልጿል።ውሳኔው የዶላር ማሻቀብን ለማቃለል ያለመ ነው ሲሉ የአርጀንቲና የምጣኔ-ሀብት ሚንስትር ሰርጂዮ ማሳሳ ተናግረዋል።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
60 ተጋላጭ ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ አገራቸው ተመለሱ!

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ቢሮ ጋር በመተባባር 60 ፍልሰተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ፍልሰተኞቹ በአፍላ የወጣትነት እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ከፍልሰተኞች መካከል 14 ያህሉ በየመን በአስከፊ ችግር ውስጥ ቆይተው ወደ ጅቡቲ የገቡ መሆናቸው ተነግሯል። ቀሪዎቹ ደግሞ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመሻገር ጅቡቲ ከገቡ በኋላ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ተገንዝበው ባህር የመሻገር ሀሳባቸውን ለመቀየር የተገደዱ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በመካከኛው ምስራቅ አገራት በአጭር ጊዜ ለመክበር በሚል ምኞት ተታልለውና ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው ከአገራቸው የወጡት ፍልሰተኞቹ በመሸጋገሪያና መዳረሻ አገራት ለረሃብ፣ ለውሃ ጥም፣ ለጤና መታወክ፣ ለከፍተኛ እንግልትና ተያያዥ ችግሮች የተዳረጉ መሆናቸውን ኤምባሲው አስታውቋል፡፡

ከኢትዮጵያ-ጅቡቲ- የመን የሚደረገው ህገ-ወጥ የሰዎች ፍልሰት በሞትና ልዩ ልዩ አደጋዎች የተሞላ በመሆኑ፤ ኤምባሲው የአገራችን ወጣቶች በህገ-ወጥ ደላሎች የውሸት ስብከት በመታለል ውድ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆና ተመረጠች!

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንድትመራ ተመረጠች፡፡በዛምቢያ ሉሳካ ፍፃሜውን ባገኘው የኮንፌዴሬሽን ኦፍ አፍሪካ አትሌቲክስ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ አትሌቲክስን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንድትመራ ካውንስሉ በሙሉ ድምፅ እንደመረጣት ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአሮሚያ ክልል ለትግራይ ክልል መልሶ ግንባታ እስከ 1 ቢልየን ብር አስተዋፅዖ ያደርጋል ተባለ!

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጦርነት ሳቢያ የወደሙ የትግራይ ክልል መሰረተ ልማቶች መልሶ ለመገንባት የሚውል እስከ 1 ቢልየን ብር የሚደርስ አስተዋፅዖ እንደሚያደርግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ገለፁ።

የክልል ርዕሳነ መስተዳድራን በትግራይ ክልል ተገኝተው በጦርነቱ ሳቢያ የደረሱ ውድመቶችን በመመልከት ላይ  እንደሚገኙ የትግራይ ቴሌቭዥን ዘገባ ያመላክታል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ "የኦሮሚያ ክልል በቅርብ ጊዜ ውስጥ 30 ትራክተሮች እንዲሁም አንድ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት ገንብቶ" ለትግራይ ክልል ህዝብ እና መንግስት ያስረክባል ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa