YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቀጣዩ አመት የኢትዮጵያ የቡና ምርት እስከ 4 እጥፍ ሊጨምር እንደሚችል ተገመተ!

ባለፉት አራት አመታት መንግስት የቡናን ምርት እና ምርታማነት ለማሻሻል በወሰዳቻው የፋፊ የንቅናቄ ስራዎች የመጪው ምርት ዘመን ለዘርፉ ተጨማሪ ውጤት ይዞ እንደሚመጣ ተገምቷል፡፡የቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶር) እንደተናገሩት ላለፉት አመታት በቡና ልማት ላይ የተሰሩ ስራዎች በመጪው የምርት ዘመን ፍሬ ማፍራት ይጀምራሉ ብለዋል፡፡ በዚህም የቀጣዩ ምርት ዘመን በመጠን ከ 3 እስከ አራት እጥፍ ሊጨምር ይችላል ሲሉ ያላቸውን ግምት ሰጥተዋል፡፡

ባለፉት አመታት ያረጁ የቡና ዛፎችን የመጎንደል እና የመተካት እንዲሁም አዳዲስ ልማት ሲደረግ መቆቱ ይታወሳል፡፡በተለይ እስከ 40 አመት እድሜ ያስቆጠሩ ቡናዎች የበዙበት የነበረው ዘርፍ በአዲሱ ኢንሼቲቭ ጉንደላ በመከናወኑ እና ያንንም ተከትሎ የተሻለ ፍሬ የመስጫ ወቅታቸው በመቃረቡ የምርቱ እድገት እንደሚኖር ተገምቷል፡፡በተጠናቀቀው በጀት አመት አገሪቱ 300 ሺ ሜትሪክ ቶን ቡና ወደ ውጭ የላከች ሲሆን ይህም ከፍተኛ መጠን ነው፡፡መንግስት ከፍተኛ ቡና በማምረት እና ወደ ውጭ በመላክ ከዘርፉ የተሻለ ገቢ ለማግኘት ፍላጎት አለው፡፡በጠቅላላው በአማካኝ በአገሪቱ 700 ሺ ቶን የሚሆን ቡና የሚመረት ሲሆን አብዛኛው ለራስ ፍላጎት ይውላል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው ሕወሃት የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራዩ ጦርነት የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባቱን ሃላፊነት በተናጥል ውሳኔ ለተመድ የፕሮጀክቶች አገልግሎት ቢሮ መስጠቱን እንደሚቃወም መናገሩን ዘ ኢስት አፍሪካን ጋዜጣ ዘግቧል። መንግሥት የትግራይን መልሶ ግንባታ የተመድ ቢሮ ሃላፊነት ወስዶ እንዲመራው ባለፈው ሳምንት ስምምነት ላይ ሲደርስ፣ ሕወሃት አንዳችም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል። ጌታቸው የትግራይ መልሶ ግንባታ ሥራ ከመጀመሩ በፊት፣ በአጠቃላይ በመልሶ ግንባታው መርሃ ግብር ላይ ሁሉም ባለድርሻዎች መግባባት ላይ መድረስ አለባቸው ብለዋል።

Via Wazema
@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
በውቢቷ ሃዋሳ ከተማ ለማረፍ ሲያስቡ በቀላሉ በሩም_ኢቲ ሆቴልዎን ቀድመው ያሲዙ።

150 ብር ጀምሮ

አሁኑኑ ይደውሉ!
📞9883

Room.et አፕን ለማውረድ👇🏾
https://bit.ly/3P5seGC
.
.
.
ለሆቴል ፍላጎትዎ Room.et
Forwarded from YeneTube
ብራቮ፣ በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የተሰራ የግል ፋይናንስ አስተዳዳሪ መተግበሪያ

በጀቶን በብቃት ለማውጣት ፣ የገንዘብ ልውውጦን በቀላሉ ለመከታተል ፣ የፋይናንስ እውቀቶንም ለመጨመር አሁኑኑ መተግበሪያውን አውርደው ይጠቀሙ።

ወቅታዊ መረጃዎችንም ቻናላችን በመቀላቀል በቀለላሉ ያገኙ
https://tttttt.me/birravo
Forwarded from YeneTube
መፍትሔ ስራይ ወአይነ ጥላ
መርጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድሀኒቶች ፍቱን ህክምናወችን እንሰጣለን።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረበትን
👉ሆዱን ለሚአመው
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለትምርት አልገባው ላለ
👉ሁሉም ቦታ ላይ ላሉ ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለአቃቤ እርእስ ለጥላት መጠበቂያ
👉ለማንኛውም አይነት ቁስል
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ በሄደበት ሁሉ ሰው እንዲወደው
👉ለአይነ ጥላ
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉የሚአስቡት ሁሉ አልሳካ ላለ
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ለእራስ ህመም
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉ፍቅረኛ ላጣ
👉የሌባ ገትር ሌባ እማያስነካ
👉ለሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ለቡዳ
👉ለመስተፋቅር
👉ገበያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሄ ስራይ
👉ለስንፈተ ወሲብ ሲገናኝ ለሚቸኩልበት
👉ለአስም (ሳይነስ)
👉ለትዳር ለማይስማሙ ለመስተዋድድ
እንዲሁም የተለያዩ
መድኀኒቶችን እንቀምማለን
👉እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።
👉እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል
👍ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883
https://tttttt.me/meritibe
👉ቻናሉን በመቀላቀል ጥንታዊ የአባቶች ጥበብ እንደወረደ ያገኙታል በየስሀቱ የምንለቃቸውን ተደብቀው የቆዪ የብራና መጽሀፍ በሚፈልጉት አይነት ይለቀቃሉ የሚፈልጉትን ለማግኔት ይቀላቀሉ ሼር ሼር ሼር ያድርጉ
Forwarded from YeneTube
#ማራ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

#ሙሉ_በሙሉ_እውነተኛ_ታሪክ

የሞት ፍርድ የተፈረደባት አንዲት እንስት ይቅርታ ጠይቂና የሞት ፍርዱ ይነሳልሽ ብትባል እንቢ አሻፈረኝ ትላለች፡፡

ምሕረትን እንዳትቀበል ያደረጋት፣ ሕይወቷን ያስመረረውና የሞት ጽዋውን ያሰኛት ምክንያት ምን ይሆን?

የሴተኛ አዳሪዎች ንግስት፣ የልኡላን ቅምጥ የሆነችው እንስት በሴቶች የሚደረጉ አስገራሚ አብዮቶች ምልክት ተብላ ተሞግሳለች፡፡ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ የሆነው #ማራ መጽሐፍ እነሆ በገበያ ላይ ውሏል፡፡

📗📒📕
“ከእስር ቤት የምትወጪበት አንድ ተስፋ ተገኝቷል፡፡ ለፕሬዚዳንቱ የይቅርታ መልዕክት ፅፈሽ ይቅርታ እንዲደረግልሽና ሁለተኛ ወንጀል ላለመስራት ቃል የምትገቢ ከሆነ ከእስር ቤት እንደምትወጪ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡”

“አልፈልግም። በምሕረት ብወጣም መግደሌን አላቆምም!”

“አንቺ ወንጀለኛ ነሽ!”

“አይደለሁም! እናንተ ሁላችሁም ናችሁ ወንጀለኞች፡፡ አባቶች፣ አጎቶች፣ ባሎች፣ የሴተኛ አዳሪ ደንበኞች፣ ዶክተሮች፣ ጋዜጠኞች፣ በሁሉም ሙያ ላይ ያላችሁ ሁላችሁም ወንዶች! አባቴ፣ አጎቴ፣ ባሌ… ሁላችሁም ሴተኛ አዳሪ ሆኜ እንዳድግ አስተምራችሁኝ አልፋችኋልና ወንጀለኞች ናችሁ!!!”
📚#ከመጽሐፉ_የተወሰደ

#ማራ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና መጽሐፍ ሽልማቶችን ለማግኘት ቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ።)

*
Telegram- https://tttttt.me/teklu_tilahun
Forwarded from YeneTube
#ላጤውባለትዳር
የፊልም እና የቴአትር ባለሞያዎች የተጣመሩበትን ይሄንን ቴአትር ማክሰኞ ምሽት በ 11:30 በብሔራዊ ቴአትር መጥተው ይመልከቱ🔥🔥
#ተዋንያን
ቸርነት ፍቃዱ 🔥
ናርዶስ አዳነ🔥
የምስራች ግርማ🔥
ምትኩ በቀለ🔥
ዳንኤል ተገኝ🔥
ሀና ጌትነት🔥
#ደራሲ ዳንኤል ሙሉነህ
#አዘጋጅ ሔኖክ ብርሀኑ
#HK Entertainment ተዘጋጅቶ የቀረበ😍
ለበለጠ መረጃ :_09 21 59 34 71
@H2n8k
እንቦጭን የሚያጠፋ የእንጉዳይ ዝርያ በምርምር መገኘቱ ተገለጸ!

እንቦጭን በመመገብ ማጥፋት የሚችል የእንጉዳይ ዝርያ በምርምር መገኘቱን የኢትዮጵያ ደን ልማት አስታወቀ።በኢትዮጵያ ደን ልማት የደን ውጤቶች እና ኢኖቬሽን ዳይሬክተር ዳንኤል ገበየሁ እንቦጭ አረምን ለማጥፋት ብዙ ጥረትና ምርምር ሲደረግ መቆየቱን ገልጸው በአሁኑ ወቅት እንቦጭን በመመገብ የሚያጠፋ እንጉዳይ ዝርያ በምርምር ተገኝቷል ብለዋል።

የምርምር ውጤቱ የእንቦጭ አረምን ለማጥፋት ይረዳሉ ተብለው ለመፍትሔነት ከቀረቡ አማራጮች መካከል አንዱ መሆኑንም ገልጸዋል።

በምርምሩ መሠረት እንቦጭ ያለበት ቦታ ላይ እንጉዳዩ እንዲዘራ ይደረጋል ያሉት ዳይሬክተሩ እንጉዳዩ ሲበቅል እንቦጭን እንደ ምግብ በመጠቀም የሚያድግ ይሆናል፤ በዚህ ሂደት እንጉዳዩ ለሰው ልጆች ምግብነት የሚውል ሲሆን እንቦጩ ደግሞ እየጠፋ ይሄዳል ብለዋል።ከዚህ ባለፈ ተቋሙ መጤ አረሞችን ወደ ጥቅም ሰጪ ነገር ለመቀየር የተለያዩ ምርምሮችን እና የቴክኖሎጂ አማራጮችን ጥቅም ላይ ለማዋል እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
ጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረሀማን ጉባኤውን በይፋ አስጀምረዋል፡፡ጉባኤው የ2014 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በማዳመጥ የሚወያይ ሲሆን በ2015 እቅድ ዙሪያ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል፤ የክልሉንም የ2015 በጀትንም ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።ጨፌው ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ኦቢኤን ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በጋምቤላ ከተማ ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ ተነሳ!

ሰሞኑን በጋምቤላ ከተማ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ከቀናት በፊት ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ መነሳቱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡

በጋምቤላ ከተማ የሰው እና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 11 ሰዓት 30 ድረስ ከሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም አንስቶ መገደቡ እና ተግባራዊ እንዲደረግ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በትላንትናው እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ስምንት ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደረሰባቸዉ፡፡

ከአዲሱ ገበያ ወደ ፒያሳ በማቅናት ላይ የነበረ አይሱዙ የጭነት መኪና መንገድ በመሳቱ ምክንያት ነው አደጋው የደረሰው፡፡በአደጋው ምክንያትም ስምንት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አቤት ጠቅላላ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

እንደዚሁም በአካባቢው የነበሩ አምስት መኪኖችም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
አደጋ ያደረሰው የጭነት መኪናው መንገድ ስቶ ስለነበረ በሁለት የንግድ ሱቆች ላይም የንብረት ጉዳት ማድረሱ ነው የተነገረው፡፡ዜናዉ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ያለዉ መረጃ ይህ ነዉ፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ኢመደአ ከ91 በላይ የሚሆኑ በሳይበር እና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን አዳዲስ ታዳጊ ወጣቶችን መቀበሉን አስታወቀ!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል በ2014 የክረምት መርሃ ግብር ከ91 በላይ የሚሆኑ በሳይበር እና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶችን ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተቀብሎ የሥልጠና ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን አስታውቋል፡፡

የማዕከሉ ሀላፊ ካሳሁን ደሳለኝ እንዳሉት፤ የክረምት ወቅት ትምህርት የሚዘጋበት ጊዜ በመሆኑ በርካታ ተማሪዎች በመስኩ ካላቸው ልዩ ተሰጥዖ አኳያ በታለንት ማዕከሉ ተቀብለን የሥልጠና ድጋፍ እያደረግን ነው ብለዋል፡፡ማዕከሉ ከ6ኛ ክፍል ጀምሮ ከ91 በላይ ተማሪዎች በ2014 የክረምት ወቅት የተቀበላቸውን ጨምሮ ለአራት ዙር ያክል 127 ወንዶች እና 14 ሴቶች በጥቅሉ 141 ባለ ልዩ ተሰጥዖ ግለሰቦች በአሁኑ ወቅት ቴክኒካል ድጋፍ እየተደረገላቸው ስለመሆኑም ካሳሁን አስታውቀዋል፡፡

የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከሉ የተቀበላቸውን ታዳጊ ወጣቶች ከክህሎት ስልጠናዎች ጀምሮ የቴክኒክ እና ለሥራቸው የሚጠቀሙባቸውን ቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር የሚሰሯቸውን የጥናትና ምርምር ሥራዎች ለመፈተሽና ለመሞከር የሚያስችላቸው ላብራቶሪም በማዕከሉ ውስጥ እንደሚያገኝ ሀላፊው አብራርተዋል፡፡በተለያየ ምክንያት ወደ ተቋሙ የታለንት ማዕከል ላልመጡ እና በመስኩ ጥሩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን በተመለከተም የቀጥታ መረብ (Online) ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።

ተማሪዎች የሚመረጡበት ወይም የሚመለመሉበት መስፈርትም ባዘጋጁት ፕሮጀከት መሰረት መሆኑን ተናግረዋል።ማዕከሉ በቀጣይም አብዛኛውን ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች የቀጥታ ድጋፉን አጠናክሮ ለመቀጠል ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም ሀላፊው አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል በሳይበር ሴኪዩሪቲ እና ተያያዥ ዘርፎች ላይ ተሰጥዖ ያላቸው ታዳጊዎች እና ወጣቶች ክህሎታቸውን ለማሳደግ እና ፕሮጀክቶቻቸውን ለመተግበር የሚያስችል የባለሙያ ድጋፍ ለማድረግ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተጠቁሟል።አሁንም ፍላጎት እና ተሰጥዖ ያላቸው ታዳጊዎች እና ወጣቶች በ cychalleng.insa.gov.et ድረ-ገጽ መመዝገብ እንደሚችሉ እንዲሁም ለበለጠ ማብራሪያ በ 0904311833 ወይም 0904311837 መደወል እንደሚችሉ ሀላፊው ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ በታሪኩ ከፍተኛ የተባለዉን ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ!

የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ 95 ከመቶ የሚሆነውን የፋይናንስ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ መደገፉን ተከትሎ በታሪክ ከፍተኛ የተባለውን ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡በኢንተርኔት ባንኪንግ መክፈል ፣ ለገቢዎች ሚኒስቴር በኢታክስ አማካይነት ቫት ፣ ዊዝሆልዲንግ እንዲሁም ግብር ማሳወቅ ፣ በዳሪስ ሲስተም የገቢ ደረሰኝ እንዲቆረጥ ማድረግ እና የተለያዩ ክፍያዎችን በኢ-ፔይመንት በባንክ በኩል መክፈል መቻሉን ተከትሎ ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን በፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ አብነት ሰለሞን ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው በ2014 በጀት አመት ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ያስቻለው አሰራሩን በቴክኖሎጂ በማስደገፉ ነው ያሉት ባለሙያው ፤ ከዚህም ሌላ የሰራተኞች ትርፍ ሰአታቸውን ጨምሮ በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ መደረጉ አስተዋጾ ነበረው ተብሏል፡፡ከእዚህ በተጨማሪ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ባንኮች ገብተው እንዲሰሩ መደረጉ እና የተሰበሰበ ገንዘብ በእለቱ ወደ ባንክ ገቢ መደረጉ ለአፈጻጸሙ መሳካት ጉልህ ሚና እንደነበረው አቶ አብነት ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ በ2014 በጀት አመት ከአገልግሎት 650 ሚሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 154.66 % ማሳካት እንደቻለ ተገልጿል፡፡በቀጣይም የገንዘብ አሰባሰቡን ስርአት ለማዘመን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እየተሰራ በመሆኑ በተያዘው ወር ውስጥ አገልግሎቱ ይጀመራል ተብሏል፡፡

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መርከብ ከ23 ዓመታት በኋላ በሞምባሳ ወደብ አገልግሎት መስጠት መጀመሯን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት (ኢባትሎአድ) አስታወቀ።

ድርጅቱ የአፍሪካ አገራትን በንግድ የማስተሳሰር ሥራን በ2010 ዓ.ም መጨረሻ የኤርትራን ጭነት ከምጽዋ ወደብ ወደ ቻይና በማጓጓዝ የጀመረውን አገልግሎት በማስቀጠል ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በሶማሌላንድ በበርበራ እና በግብጽ በሳፋጋ እና ፖርት ሳይድ ወደቦች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጿል።ባለፈው ሳምንት መጨረሻ “ጊቤ” የተሰኘችው የኢትዮጵያ መርከብ የኬኒያን ጭነት ከኦማን ሱሐር ወደብ በመጫን ሞምባሳ ወደብ ገብታ በማራገፍ ላይ እንደምትገኝ አመልክቷል።

ከዛሬ 23 ዓመታት በፊት “አድማስ” የተባለችው መርከብ ወደ ሞምባሳ ካደረገችው የመጨረሻ ጉዞ በኋላ የጊቤ መርከብ በሞምባሳ መገኘት ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ነው ድርጅቱ ያስታወቀው።የኢትዮጵያ መርከቦች የገቢ ወጪ ጭነት ከማጓጓዝ በተጨማሪ በቀጠናው ላሉ አገራት አገልግሎት በመስጠት ተደራሽነታቸውን እያሰፉና ተጨማሪ ገቢ እያስገኙ ነው ብሏል።

“ኢባትሎአድ አፍሪካን ከሌላ አህጉር በንግድ የሚያገናኝ የመጀመሪያው እና ብቸኛው አፍሪካዊ የመርከብ ኩባንያ መሆኑን ቀጥሏል” ያለው ድርጅቱ “ብሔራዊ የንግድ መርከባችን ከአፍሪካ ብቸኛው የአገርን ሰንደቅ ዓላማ በባሕር ላይ የሚያውለበልብ ሆኖ በመቀጠል የኢትዮጵያ ኩራት ሆኗል” ሲል ገልጿል።ኢትዮጵያ ዘጠኝ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡና ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች አላት፤ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡት መርከቦች በተመሳሳይ 28 ሺሕ ቶን የመጫን አቅም ያላቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከንቲባ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ለሕግ እንዲቀርቡ ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ ጠየቀ።

"የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዥው ፓርቲ የሚፈጸሙበት የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውሶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፉ በመሄድ ላይ ይገኛሉ" ሲል በመግለጫው የተናገረው ፓርቲው "የከንቲባ አዳነች አበቤ አስተዳደር ከተማዋንም ሆነ አገሪቷን ወደ ቀውስ በፍጥነት እና በጥልቀት እየገፋት ይገኛል" ብሏል።

ፓርቲው ሰሞኑን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለባለ እድለኞች ለመስጠት በወጣው የተጭበረበረ ዕጣ የከተማዋ ከንቲባ "በድርጊቱ መሪ ተዋናይ እንደነበሩ በርካታ መረጃዎች ተገኝቶባቸዋል" ብሏል በመግለጫው፡፡ "በዚህ አውድ፣ ከንቲባዋን ትቶ ሌሎች የአዲስ አበባ አስተዳዳር ባለሥልጣናት እና ሙያተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱ የፍትሕ ሥርዓቱን ባዶነት እና አድሎኝነት አጋልጧል" የሚለው ባልደራስ « የከንቲባዋ ያለመከሰስ መብት ተነስቶ ለተነሱባቸው ጥያቄዎች የከንቲባዋ ያለመከሰስ መብት ተነስቶ ለሕግ እንዲቀርቡ፣ የኦሮሚያ ክልል ሕገ መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ እንዳይሆን እና የኦሮሚያ ክልል ባንዲራና መዝሙር በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች እንዳይሰቀል እና እንዳይዘመር" ሲል ጠይቋል።

የከተማው ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶክተር ሲሳይ መንግሥቴ ሰሞኑን በተከናወነው የምክር ቤቱ ጉባኤ ላይ "ትምህርት ቤቶች ላይ የኦሮሚያ ባንዲራ ይውለብለብ አይውለብለብ በሚል ችግር ፈጥሯል፣ መዝሙሩ ይዘመር አይዘመር በሥርዓት ነው መወሰን ያለበት" በሚል ላቀረቡት ጥያቄ ከንቲባ አዳነች አቤቤ "የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለአዲስ አበባ በሚሆን መንገድ የአዲስ አበባ ተማሪዎች ኦሮሚኛን መማር የሚገባቸው በምን መልኩ ነው ለሚለው ካሪኩለም ቀርጿል። ኦሮምኛ መዘመራቸው ይቀጥላል ብለዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና De Havilland አውሮፕላን አምራች ካምፓኒ አራት Q-400 የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ወደ ካርጎ ለመቀየር የሚያስችሉ መለዋወጫዎችን ለማቅረብ የሚያስችል ቅድመ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
1
የኢትዮጵያና የሱዳን አመራሮች ስለጋላባት ድንበር መከፈት ለመነጋገር ቀጠሮ ያዙ!

የኢትዮጵያና የሱዳን አመራሮች ለአንድ ወር ገደማ ተዘግቶ የቆየውንና በመተማ በኩል ኢትዮጵያና ሱዳንን የሚያዋስነው የጋላባት ድንበር መከፈት በተመለከተ ለመነጋገር፣ ለነገ ሐሙስ ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ቀጠሮ ያዙ፡፡

የሱዳን ወታደራዊ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ነቢል አብደላህ ዓሊ እሑድ ሐምሌ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ ሱዳን ድንበሩን እንደከፈተች ቢገልጹም፣ እስካሁን ድረስ የሰውም ሆነ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አለመጀመሩን የመተማ ዮሐንስ ከተማ አስተዳደር ሚዲያ ልማትና ብዝኃነት ቡድን መሪ አቶ ልዑልሰገድ አሰፋ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በሱዳን ወታደራዊ አመራር የተሰጠውን መግለጫ ተከትሎ በሱዳን በኩል ያለው ኬላ በመከፈቱ ረዕቡ ሐምሌ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ነዳጅ የጫኑ ሁለት ተሽከርካሪዎች ወደ መተማ ዮሐንስ ከተማ መጥተው እንደነበር የገለጹት አቶ ልዑልሰገድ፣ መኪኖቹ ከእነ ጭነታቸው እንዲመለሱ መደረጉን አስረድተዋል፡፡ እንደ ቡድን መሪው ገለጻ መኪኖቹ እንዲመለሱ የተደረገው፣ ስለድንበሩ መከፈት በሁለቱ ከተሞች በኩል የጋራ ንግግርና ስምምነት ባለመኖሩ ነው፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://www.ethiopianreporter.com/108495/
@YeneTube @FikerAssefa
ከእስር እንዲለቀቁ የተበየነላቸው የኦነግ አመራሮች ዛሬም አልተፈቱም!

በቡራዩ በእስር ላይ የሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮች ከእስር እንዲፈቱ የቡራዩ ወረዳ ፍርድቤት ከትናንት በስቲያ ሰኞ ብይን ቢያሳልፍም እስካሁን ከእስር አለመለቀቃቸውን የእስረኞቹ ቤተሰቦች ገለጹ።ፍርድ ቤቱ ከእስር እንዲለቀቁ የበየነላቸው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮችን የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አብዲ ረጋሳ፣ ሚካኤል ቦረን፣ ለሚ ቤኛ እና ገዳ ገቢሳ ናቸው።

ከትናንት በስቲያ ሰኞ በዋለው ችሎት ፖሊስ እስረኞቹን ባለማቅረቡ እስረኞቹ በሌሉበት እንዲፈቱ ውሳኔውን የተላለፈ ቢሆንም የወረዳው ፍርድቤት ውሳኔ እስካሁን በጽሁፍ ተዘጋጅቶ ለፖሊስ ጣቢያ ባለመድረሱ እስረኞቹ አለመለቀቃቸውን ከእስረኞቹ ቤተሰብ አንዱ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ በእስር ላይ ከሚገኙ የኦነግ አመራር አባላት አንዱ የሆኑት የአቶ ዳዊት አብደታ ወንድም አቶ ብርሃኑ አብደታ እንዳሉት እስከ ዛሬ ድረስ ውሳኔው ተግባራዊ አልሆነም፡፡

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለጅቡቲና ሱዳን ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ95 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን እንዳሉት፦ ተቋሙ በጅምላ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ለአገር ውስጥና ለውጭ አገራት ደንበኞች ያቀርባል።በዚህም የ2014 በጀት ዓመትም ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ለከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች፣ እንዲሁም ለሱዳንና ጅቡቲ ኃይል በሽያጭ በማቅረብ ገቢ መሰብሰብ እንደቻለ ተናግረዋል።

በዚህም ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 9 ሺህ 472 ጊጋ ዋት ማቅረቡን ገልፀው፤ ለከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች የእቅዱን 90 በመቶ እንዲሁም ለኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር የእቅዱን 116 በመቶ ኃይል ማቅረብ መቻሉን አስረድተዋል።ተቋሙ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለጅቡቲ 527 ጊጋ ዋት ኃይል ለማቅረብ አቅዶ 611 ጊጋ ዋት ማቅረብ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ለሱዳን ደግሞ 1 ሺህ 93 ጊጋ ዋት በሰዓት አቅርቧል ነው ያሉት።

በአጠቃላይ ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ለአገር ውስጥና ለውጭ አገራት 12 ሺህ 30 ጊጋ ዋት ኃይል ማቅረቡንም ተናግረዋል።ተቋሙ ለጅቡቲና ሱዳን ካቀረበው የኃይል ሽያጭ 95 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘቱንም ነው የገለፁት።ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ4 ነጥብ 9 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም የ5 ነጥብ 4 በመቶ ጭማሪ እንዳለውም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ካቀረበው ኃይል 11 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ከኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ደግሞ 364 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡንም ተናግረዋል።

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
እንኳን ደስ አለን!

በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል ተጨማሪ የብር እና የነሀስ ሜዳልያ አግኝተናል።

ወርቅውሀ ጌታቸው በ8:54.61 በመግባት የሁለተኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ መቅደስ አበበ በ8:56.08 በሶስተኛነት ውድድሯን ጨርሳለች።

@YeneTube @FikerAssefa