YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ወደ ሀዋሳ እና ዝዋይ / ባቱ

ለአመታዊ የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ተጓዦች በሙሉ የምስራች ከሩም ኢቲ! የሆቴል ክፍሎችን በሀዋሳ እና በዝዋይ(ባቱ) ከተሞች ቀድመው በሩም ኢቲ ይያዙ።

አሁኑኑ ይደውሉ!
📞9883

Room.et አፕን ለማውረድ👇🏾
https://bit.ly/3z94pZt
.
.
.
ለሆቴል ፍላጎትዎ Room.et
Forwarded from YeneTube
ብራቮ፣ በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የተሰራ የግል ፋይናንስ አስተዳዳሪ መተግበሪያ

በጀቶን በብቃት ለማውጣት ፣ የገንዘብ ልውውጦን በቀላሉ ለመከታተል ፣ የፋይናንስ እውቀቶንም ለመጨመር አሁኑኑ መተግበሪያውን አውርደው ይጠቀሙ።

ወቅታዊ መረጃዎችንም ቻናላችን በመቀላቀል በቀለላሉ ያገኙ
https://tttttt.me/birravo
Forwarded from YeneTube
#ማራ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

#ሙሉ_በሙሉ_እውነተኛ_ታሪክ

የሞት ፍርድ የተፈረደባት አንዲት እንስት ይቅርታ ጠይቂና የሞት ፍርዱ ይነሳልሽ ብትባል እንቢ አሻፈረኝ ትላለች፡፡

ምሕረትን እንዳትቀበል ያደረጋት፣ ሕይወቷን ያስመረረውና የሞት ጽዋውን ያሰኛት ምክንያት ምን ይሆን?

የሴተኛ አዳሪዎች ንግስት፣ የልኡላን ቅምጥ የሆነችው እንስት በሴቶች የሚደረጉ አስገራሚ አብዮቶች ምልክት ተብላ ተሞግሳለች፡፡ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ የሆነው #ማራ መጽሐፍ እነሆ በገበያ ላይ ውሏል፡፡

📗📒📕
“ከእስር ቤት የምትወጪበት አንድ ተስፋ ተገኝቷል፡፡ ለፕሬዚዳንቱ የይቅርታ መልዕክት ፅፈሽ ይቅርታ እንዲደረግልሽና ሁለተኛ ወንጀል ላለመስራት ቃል የምትገቢ ከሆነ ከእስር ቤት እንደምትወጪ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡”

“አልፈልግም። በምሕረት ብወጣም መግደሌን አላቆምም!”

“አንቺ ወንጀለኛ ነሽ!”

“አይደለሁም! እናንተ ሁላችሁም ናችሁ ወንጀለኞች፡፡ አባቶች፣ አጎቶች፣ ባሎች፣ የሴተኛ አዳሪ ደንበኞች፣ ዶክተሮች፣ ጋዜጠኞች፣ በሁሉም ሙያ ላይ ያላችሁ ሁላችሁም ወንዶች! አባቴ፣ አጎቴ፣ ባሌ… ሁላችሁም ሴተኛ አዳሪ ሆኜ እንዳድግ አስተምራችሁኝ አልፋችኋልና ወንጀለኞች ናችሁ!!!”
📚#ከመጽሐፉ_የተወሰደ

#ማራ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና መጽሐፍ ሽልማቶችን ለማግኘት ቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ።)

*
Telegram- https://tttttt.me/teklu_tilahun
ከወጪ ንግድ ከፍተኛ የኾነው 4 ነጥብ 12 ቢሊዮን ዶላር ተገኘ

በተሰሩ ሀገራዊ የለውጥ ስራዎች በ2014 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 4.12 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ በማግኝት በዘርፉ የመጀመሪያ የሆነው ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል፡፡

ሀገራችን ባለፉት የለውጥ ዓመታት የወጪ ንግድ ገቢን ለማሳደግ በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ በተለይም ባለፉት 3 የበጀት ዓመታት የሀገር በቀል ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት፣የወጨ ንግድን በመጠን፣ በአይነትና በጥራት ለማሳደግ የፖሊሲ፣ የስትራቴጂና የመዋቅራዊ ለውጥ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡

በተወሰዱት እርምጃዎችም በ2014 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 4.12 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ገልጸዋል፡፡ ገቢው የእቅዱን 90.3 በመቶ ሲሆን ከባለፉት ዓመታት ዓፈፃጸም አንፃር ለታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመዘገበ የወጪ ንግድ ገቢ መሆኑንም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል፡፡

ሀገራችን በውስጣዊና በውጫዊ ፈተና ውስጥ ሆና የተገኘው ይህ ገቢ ከባለፈው በጀት ዓመት ገቢ በ13.81 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን ከገቢም በዘለለ ለሀገራችን ብዙ ትርጉም ይሰጣል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የወጪ ንግድ ገቢ እያደገ መምጣት የሀገሪቱን ዓለምአቀፋዊ ተቀባይነት፣ የመበርና ብድርን የመመለስ አቅምን ያሻሽላልም ሲሉ አብራርተዋል፡፡

በበጀተ ዓመቱ የግብርናው ዘርፍ የእቅዱን 105 በመቶ የአጠቃላይ እቀዱን 72 በመቶ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ የእቅዱን 80 በመቶ የጠቅላላ እቅዱን 12 በመቶ ገቢ ያስገኙ ሲሆን የማእድን ዘርፍ የእቅዱን 53 በመቶ የአጠቃላይ ወጪ ንግድ እቅዱን ደግሞ 14 በመቶ ነው ገቢ ያስገኘው፡፡

የግብርናው ዘርፍ ከፍተኛውን ገቢ በማስገኘት አሁንም የኢኮኖሚው የመሪነት ደረጃውን የያዝ ሲሆን መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር ለማድረግ የተያዘውን ውጥን ለማሳካት ብዙ መስራት እንደሚጠይቅ አቶ ካሳሁን ጠቁመዋል፡፡

የጎንዮሽ ግንኙነት አለመዳበር፣ የኮንትሮባንድ ንግድ እና መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር አዝጋሚነት የወጪ ንግዱን እየፈተኑት ያሉ ችግሮች ናቸው፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
🔥1
በኢትዮጵያ የተጀመረው የሰላም ጥረት እንዲሳካ አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ ተገለጸ!

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ በአፍሪካ ቀንድ ከአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሚካኤል ሃመር ጋር መነጋገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በውይይቱም በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሚካኤል ሃመር በኢትዮጵያ የተጀመረው የሰላም ጥረት እንዲሳካ ሀገራቸው ድጋፍ እንደምታደርግ መግለጻቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የአሜሪካ ዲፕሎማት ኢትዮጵያውያን ሰላም እንዲያገኙ ሀገራቸው ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቷንም ለአምባሳደር ስለሺ ገልጸዋል።

የሕዳሴ ግድብን በሚመለከት ኢትዮጵያ የምትከተለው አቋም ሚዛናዊ መሆኑን የገለጹ ሲሆን አምባሳደር ሚካኤል ሃመር ደግሞ ሶስቱ ሀገሮች ሁሉንም ጠቃሚ የሚያደርግ መንገድ ላይ ይደርሳሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

Via Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
የራሺያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በሚቀጥለው ሳምንት አዲስ አበባ ይመጣሉ ተብሏል። ሰርጌ ላቭሮቭ ወድ ኢትዮጵያ የሚመጡት በቀጣይ ለሚካሄደው የራሺያ-አፍሪካ ሰብሰባ ዝግጅት ከባለስለጣናትና ዲፕሎማቶች ጋር ለመምከር መሆኑን ካፒታል ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ ከስልጣን መልቀቃቸውን አስታወቁ!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ለመልቀቅ ቀደም ብለው ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ሆኖ ነበር። ይሁንና አሁን የጥምር መንግስቱ እንደገና ማንሰራራት ባለመቻሉ ስልጣን መልቀቃቸው ተገልጿል።ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ፤ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ለፓርላማው ተናግረዋል ተብሏል።ከሰሞኑ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን መልቀቃቸው የተሰማ ሲሆን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትርምበተመሳሳይ ከሃላፊነት መልቀቃቸው ይታወሳል።

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የራይድ ሾፌሮች ለሳለዲን ፍትህ ጠየቁ።

የራይድ ሹፌሮች በጠራራ ጸሀይ በጩቤ ተወግቶ የተገደለው የራይድ ሹፌር ሳለዲን ሀሰን ፍትህ እንዲሰጠው ሲሉ በሰልፍ ጠየቁ ።
ቤተሰቦቹን አጽናንተዋል።

በአዲስ አበባ ማክሰኞ ሀምሌ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ገርጂ 24 ልዩ ቦታው ኤርትራ ቆንጽላ አካባቢ ከቀኑ 10 ሰዓት በስለት ተወግቶ የተገደለው ወጣት ሳለዲን ፍትህ እንዲሰጠው ጠይቀዋል ። በመዲናችን አዲስ አበባ መሰል የወንጀል ድርጊቶች መበራከታቸው ጠቅሰው ፤ ‘እየሰሩ መሞት ይብቃ' ሲሉ መንግስት ለጉዳዩ የተለየ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል ።

በአዲስ አበባ ያውም በጠራራ ጸሀይ ጋሻ መከታዬ የሚሉትን ልጃቸውን የተነጠቁት የሳለዲን እናትና አባት ፍትህ ይሰጠን ሲሉ በሲቃ ይማጸናሉ ። የልጃቸው ሞት ለማመን የከበዳቸው እናቱ ፤ ከሰመን ውስጥ በባንኑ ቁጥር መንግስት ፣የጸጥታ አካላት የልጄን ገዳይ ለህግ ያቅርብልኝ ሲሉ ተምልጽኖ ያሰማሉ ። እውነት ነው የሳለዲን ነፍስ ትጮሀለች ፤ ፍትህ ፣ፍትህ ስትል ትጣራለች።

Via:- የኢፕድ ጋዜጠኛ ዳንኤል ዘነበ
@Yenetube @Fikerassefa
1
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በመከላከያ ሰራዊት ላይ በመፃፍ ወንጀል እየሰራ ስለሆነ እርምጃ እወስዳለው ማለቱን ጠበቃው ተናገሩ
 

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለአቃቢ ህግ በላከው የመልስ መልስ ጽሁፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በተደጋጋሚ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በተደጋጋሚ እየፃፈ ወንጀል እየሰራ ስለሆነ መከላከያ ሰረዊት እርምጃ እንደሚወስድ የገለፀ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን ለመከልከል ከግምት ውስጥ ያስገባልኝ ማለቱን ጠበቃው አቶ ሄኖክ ለአዲስ ስታንዳርደ ተናገሩ፡፡

አቶ ሄኖክ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እርምጃውን የሚወስደው የጋዜጠኛው ዋስትና ከተፈቀደለት ይሁን በፃፈው ጽሁፍ አለማወቃቸውንም አክለው ገልጸዋል፡፡ 

ሐምሌ 11 ቀን 2014 አቃቢ ህግ ጋዜጠኛ ተመስገን ዋስትና ሊከለከልበት የሚችልበትን መከላከያ ለፍርድ ቤት የመልስ መልስ በፅሁፍ መቅረቡንና ፀሁፉን ትናንት በዋለው ችሎት ላይ እነደተሰጣቸው አቶ ሄኖክ አክሎ ተናግሯል፡፡

ጠበቃ ሄኖክ በዚህ ጉዳይ ላይ “ህጉ ስለማይፈቅድልን እኛ የመልስ ምት መስጠት ባለመቻላችን መከላከያ ሰራዊት እወስዳለሁ ባለው እርምጃ ላይ መልስ ለመስጠትና ጥያቄዎች ማንሳት አልቻልንም” ሲሉ  አስረድተዋል፡፡

በሰኔ 27 ቀን፣ 2014 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስት ጉዳዩች እና የፀረ ሽብር ችሎት የቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በተከሰሰበት ሶስት የወንጀል ክሶች በ100,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲወጣ የዋስትና መብት መፈቀዱ ይታወሳል። ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ያቀረበው ዐቃቤ ሕግ፣ የዋስትና መቃወሚያውን  ሰኞ ሃምሌ 11/2014  አቅርቧል፡፡ ዐቃቤ ሕግ ካቀረባቸው የዋስትና መቃወሚያዎች መካከል የሀገር መከላከያ ሠራዊት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የገለፀው ይገኝበታል ሲለ ጠበቃው ገልጸዋል፡፡

የፍትሕ መጽሔት ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዋስትና ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት መዝገብ እያየ መሆኑን ያስታወቀው የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ የወንጀል ይግባኝ ችሎት፣ መዝገቡን አይቶ እንዳልጨረሰ በመጠቆም ውሳኔ ለመስጠት ለሐምሌ 21/2014 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ  ”ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት፣ህዝቡ በመከላከያ ሰራዊት ላይ እንዲሁም በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ እና እንዲያምፅ በመቀስቀስ” ጠርጥሬዋለሁ ሲል ፖሊስ ሀሙስ ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓም ረፋድ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወቃል።

Via :- Addis Standard
@Yenetube @Fikerassefa
የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኤሌክትሪክ አቅርቦት፡-

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አርብ ሃምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ስራ ያከናውናል፡፡

በዚህም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ በሲቪል ሰርቪስ ፊት ለፊት፣ በሲ ኤሚ ሲ ልዩ ቤቶች፣ በተባበሩት፣ በሲ ኤ ሚ ሲ ሚካኤል እና አካባቢዎች፤

እንዲሁም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ በአያት 49 ማዞርያ፣ በአየር መንገድ ቤቶች፣ በአያት 2፣ 3፣ 4 ኮንደሚኒየም፣ በቦሌ አራብሳ እና አካባቢዎቻቸው ኤሌክትሪክ ይቋረጣል፡፡

በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞቹ ይህንን ተገንዝበዉ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳስቧል፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኮቪድ 19 መያዛቸዉ ተነገረ፡፡

ነጩ ቤተመንግስት በዛሬዉ እለት እንዳስታወቀዉ፣ባይደን በኮቪድ 19 መያዛቸዉ የተረጋገጠዉ በዛሬዉ እለት ነዉ፡፡

ፕሬዝዳንቱ የኮቪድ 19 ክትባትን በተሟላ መልኩ መዉሰዳቸዉና ማጠናከሪያ/ቡስተር/ ወስደዉ እንደነበርም ተነግሯል፡፡

የ79 ዓመቱ ባይደን በአሁኑ ወቅት ደረቅ ሳል፣ድካምና ሌሎች የህመም ስሜቶች እንደሚታዩባቸዉም ሲ ኤን ቢሲ ዘግቧል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ጨፌ ኦሮሚያ እያካሔደ ባለው 6ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን የቀረበለትን የኦቢኤን ዋና ስራ አስኪያጅ እና የቦርድ አባላትን ሹመት አፀደቀ

በዚሁ መሰረት፡- አቶ አዲሱ አረጋ የኦቢኤን ቦርድ ሰብሳቢ

ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ

አቶ አብዱልሀኪም ሙሉ

ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና

ዶ/ር ቶላ በሪሶ

ወ/ሮ ለሊሴ ዱጋ

ወ/ሮ ኮከቤ ዲዳ

አቶ ሀይሉ አዱኛ እና አቶ አህመድ ኢድሪስን የቦርድ አባላት

አቶ ግዛቸው ገቢሳ የኦቢኤን ዋና ስራ አስኪያጅ አድርጎ ሾሟል፡፡

ተሿሚዎችም በጨፌው ፊት ቀርበው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል፡፡

Via:- OBN
@Yenetube @Fikerassefa
በጥገና ላይ የነበረው የሩሲያ-አውሮፓ ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ዳግም ስራ ጀመረ

ሩሲያ ከ40 በመቶ በላይ የአውሮፓ ሀገራትን ነዳጅ ፍጆታን ለማሟላት ኖርድ ስትሪም በተሰኘ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር አማካኝነት ለሀገራቱ ታደርሳለች።

ይህ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ባለፉት ሳምንታት በጥገና ላይ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ጥገናውን ጨርሶ ወደ አገልግሎት መመለሱን ሮይተርስ ዘግቧል።

ይህ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ከጥገና በኋላ ሩሲያ ወደ አገልግሎት ላይመለስ እንደሚችል ጀርመን እና ሌሎች ሀገራት ስጋት ውስጥ ወድቀው ነበርም ተብሏል።

Via:- Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
ነገ በእነዚህ አካባቢዎች መብራት ይጠፋል

አርብ፣ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ በመካከለኛ የኤሌትሪክ ሃይል ተሸካሚ ላይ የማሻሻያ ሥራ ስለሚከናወን በሚከተሉት አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አቅርቦት ለሰዓታት የሚቋረጥ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ

👉🏻 በሲቪል ሰርቪስ ፊት ለፊት፣
👉🏻 በሲ ኤሚ ሲ ልዩ ቤቶች፣
👉🏻 በተባበሩት፣
👉🏻 በሲኤሚሲ ሚካኤል እና አካባቢዎች

ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ

👉🏻 በአያት 49 ማዞርያ፣
👉🏻 በአየር መንገድ ቤቶች፣
👉🏻 በአያት 2፣ 3፣ 4 ኮንደሚኒየም፣
👉🏻 በቦሌ አራብሳ እና አካባቢዎቻቸው

በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጉ ተብሏል፡፡

Via:- Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሚቀጥለው ሳምንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

በኢትዩጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ፕሬስ አታቼ ማሪያ ቸርኑኪና ለአል ዐይን እንዳሉት፤ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የፊታችን ማክሰኞ ሐምሌ 19 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ይገባሉ።

ላቭሮቭ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ኃላፊዎች እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አምባሰደሮች ጋር ይመክራሉ።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከኢትዮጵያ በተጨማሪም በግብፅ፣ በኡጋንዳ እና በኮንጎ ሪፐብሊክ ጉብኝት እንደሚያደርጉም በአዲስ አበባ የሩሲያ ኤምባሲ አክሎ አስታውቋል።

Via:- Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
በመዲናዋ ከሰንጋተራ እስከ ተክለሀይማኖት የሚዘልቅ ግዙፍ ግንባታ ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ ከሰንጋ ተራ እስከ ተክለሀይማኖት ባለው አካባቢ 39 የመንግስት ተቋማትን በአንድ ላይ ያሰባሰበ ግዙፍ የከተማ ማዕከል ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ተገልጿል።

የሜጋ ኮንስትራክሽን የፕሮጀክት ኮንትራት አስተዳዳር ዳይሬክተር ዳዊት ጥበቡ (ኢንጂነር) ለዋዜማ ራዲዮ እንደተናገሩት፤ ክፍለ ከተሞችን ሳይጨምር ሰላሳ ዘጠኝ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ከሰንጋተራ አንስቶ እስከ ተክለሀይማኖት በሚዘልቀው 14 ሔክታር መሬት ላይ በሚሰሩ የተለያዩ ዘመናዊ ሕንፃዎች ውስጥ ይገባሉ።

ተቋማት እንደሚሰጡት አገልግሎት አይነት በዘርፍ በዘርፍ ተደራጅተው በመንደሮች የሚደራጁ ይሆናሉ።
የሚሰሩት ህንፃዎች እጅግ ዘመናዊና ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ ጋር የተዋደዱ እንደሚሆኑም ኢንጂነር ዳዊት ተናግረዋል።

ይህ አይነቱ አደረጃጀት አገልግሎት ፈላጊው ህዝብ በአንድ አካባቢ ኹሉንም አይነት አገልግሎት እንዲያገኝ የሚረዳው እንደሚሆንም እምነታቸውን ገልፀዋል።

ፕሮጀክቱን ለማስጀመር የጨረታ ሂደቱ የተጀመረ ሲሆን፤ በቢሊየን ብሮች የሚያወጣው ይህ ፕሮጀክት ቁርጥ ዋጋውን የጨረታ ሂደቱ እስኪያበቃ መግለፅ እንደማይችሉ ዳይሬክተሩ ለዋዜማ ተናግረዋል።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በነባሩ የአዲስ አበባ ይዞታና በነዋሪዎች ላይ ስለሚያስከትለው ተፅዕኖ ሀላፊው አላብራሩም።

Via:- Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ታጣቂዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸሙት ጭፍጨፋ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ አምነስቲ ጠየቀ፡፡

ድርጅቱ በጥቃቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተገደሉ ከዓይን ምስክሮችና በሕይወት ከተረፉ ሰዎች ሰምቻለሁ ብሏል፡፡
የጥቃቱ ፈጻሚዎች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መሆናቸውን ከጥቃት የተረፉ ሰዎች ነግረውኛል ሲልም አምነስቲ አክሏል።

ጥቃቱ እንደተጀመረ የአካባቢው አስተዳደር መረጃው ቢደርሰውም፣ መንገዱ ተዘግቷል በማለት ጸጥታ ኃይል ሳይልክ እንደቀረ አምነስቲ ከምንጮቹ ማረጋገጡን መጥቀሱን ዋዜማ ሬድዮ ዘግባለች፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርዕስቱ ይርዳው ከኦሮሚያ ክልል ጋር በሚዋሰኑ የክልሉ አካባቢዎች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በየዕለቱ ንጹሃን ነዋሪዎችን እየገደሉብን ነው ሲሉ ለክልሉ ምክር ቤት ጉባዔ መናገራቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

ታጣቂዎቹ ወደ ኮንሶ ዞን፣ ቡርጂ እና አማሮ ልዩ ወረዳዎች ሰርገው በመግባት በርካታ ሰዎችን እንደገደሉና የልማት ሥራዎችን እንዳስተጓጎሉ ርዕስቱ ተናግረዋል። ርዕስቱ የክልሉ መንግሥት የታጣቂዎቹን ተደጋጋሚ ጥቃት ለማስቆም ከኦሮሚያ ክልል ጋር በቅንጅት እየሠራ ነው ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የዓለም ጤና ድርጅት የአጣዳፊ በሽታዎች ኮሚቴ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታን ዓለማቀፍ አጣዳፊ የጤና ቀውስ ብሎ መፈረጅ ይገባ እንደሆነ ለመወሰን ዛሬ ተሰብስቧል።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ ከምዕራብ አፍሪካ አገራት ውጭ መሰራጨት ከጀመረ ወዲህ፣ የድርጅቱ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ ሲሰበሰብ ያሁኑ ሁለተኛው ነው።

የአፍሪካ የጤና ሃላፊዎች ግን የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታን አጣዳፊ የጤና ቀውስ አድርገው እንደሚቆጥሩት ገልጸዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
**የሲራላካ ወታራዊ ሀይል የተቃውሞ ካምፖችን ወሯል ..የተቃውሞ መሪዎችንም ማሰራቸው ተሰምቷል፡፡**

➩ ተቃዋሚዎች አርብ ማለዳ ላይ ወታደሮች የዋና ከተማዋ ኮሎምቦ አከባቢዎችን ከተቁጣጠሩ በኃላ፣ በአንዳንዱች ላይ 'በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት ደርሶባቸዋል' ብለዋል።
➩ በስሪላንካ የሚገኘው ጦር በተቃዋሚዎች ላይ ጭካኔ በተሞላበት ሆኔታ ድብደባን ከፈጸመ በኋላ በዋና ከተማው የሚገኘውን የፕሬዚዳንቱን ሴክሬታሪያት ተቆጣጥሯል።
በጎታጎጋማ የተቃውሞ ቦታ ላይ በወታደሮቹ በርካታ ድንኳኖች ወድመዋል፣ከ100 በላይ የተቃውሞ ሰልፈኞች ታስረዋል፤ በርካቱችም ተከበዋል ብሏል፤ የአልጀዚራ ዘገባ፡፡
የሲሪላንካው አዲሱ ፕሬዝዳንት ራኒል ዊክርሜሲንግህ በመላው አገሪቱ የሚጸና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው ብዙዎችን ያስቆጣ ነበር።

➩ ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ተላልፈውታል። በወቅቱ ዊክርሜሲንግህ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉትን “ፋሺስቶች” ሲሉ ጠርተዋቸዋል።

➩ ፕሬዝደንቱ ጨምረውም ወታደራዊ ኃይሉ የሀገሪቱን ሰላም እና ጸጥታ እንዲያስጠብቅ መመሪያ ማሳለፋቸውን ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የተጠናከረ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ ስለመሆኑ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

Via:- Ethio Fm
@Yenetube @Fikerassefa