YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአብን ተወካዮች መንግሥት በሕግ ማስከበር ዘመቻ ስም በአማራ ክልል እና በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲመረምር አቤቱታ ማስገባታቸውን የአብን የምክር ቤት ተወካይ ክርስቲያን ታደለ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። አብን መንግሥት በተለይ በአማራ ክልል የፓርቲውን አመራሮች እና አባላትን ጨምሮ እያካሄደ ያለውን የጅምላ እስር ባስቸኳይ እንዲያቆም ከትናንት ወዲያ ባወጣው መግለጫ መጠየቁ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ እንዲቀጥል ወሰነ!

በአውሮፓውያኑ 2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ላይ የጣለው ማዕቀብ እንዲራዘም መወሰኑን አስታወቀ።ሀገሪቱ ከተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ባደረገችው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ነበር ማዕቀብ ተጥሎባት የነበረው። የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው ስብሰባ በደቡብ ሱዳን ላይ የተጣለው ማዕቀብ ባለበት እንዲቀጥል ውሳኔ ማስተላለፉን ሲጂቲኤንን ጠቅሶ አልአይን ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው ትናንት ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት 24 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው የደረሰው፡፡በደረሰው አደጋ የሁለት ሰወች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ፥ በሁለት ሰወች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ከአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ድምጻዊ አብርሀም በላይነህ ( ሻላዬ) በተጠረጠረበት የግድያ ወንጀል ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረበ።

ድምጻዊ አብርሀም በላይነህ በግድያ ወንጀል መጠርጠሩን ተከትሎ መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ውስጥ የሰራውን ስራ ሪፖርት ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

በዚህም የሟች አስከሬን ምርመራ ለማከናወን ለህክምና ተቋም ደብዳቤ መላኩን እና በሟች ላይ የደረሰ አካላዊ ጉዳት ካለ ለማጣራት የህክምና ማስረጃ እየተጠባበቀ መሆኑን ለችሎቱ አስረድቷል።

ድምጻዊ አብርሀም ከሟች ጋር ያደረገውን የስልክ ለማጣራት ለኢትዮ ቴሌኮም ደብዳቤ መላኩንና ተጨማሪ ምርመራ ለማከናወን ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ድምጻዊ አብርሀም በላይነህ በበኩሉ ከዚህ በፊት 14 ቀን የተሰጠ በመሆኑ አሁንም 14 ቀን ሊሰጥ እንደማይጠባ በመግለጽ ምርመራቸውን ለመጨረስ አጭር ቀጠሮ ይሰጣቸው ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎትም ፖሊስ የጀመረውን የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ተጨማሪ 12 ቀን በመፍቀድ ለሰኔ 1ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Via Tarik Adugna
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በምዕራብ ጎጃም ዞን ከ595 በላይ ተጠርጣሪዎች ለሕግ መቅረባቸው ተገለጸ!

በምዕራብ ጎጃም ዞን በተለያዩ ህገ-ወጥ የወንጀል ድርጊቶች የተጠረጠሩ 595 የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመ በሰጡት መግለጫ በህግ ማስከበር እንቅስቃሴው ውስጥ በማናቸውም ዓይነት ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ የሚጠረጠር ሰው ያለ ምንም ልዩነት በእኩል ወደ ህግ እንዲቀርብ የማድረግ ስራ በመሰራት ላይ ነው ብለዋል።በዚህም በዞኑ እስካሁን በድምሩ 595 የሚሆኑ ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመዋል።በህግ ማስከበር ስራው አንዳንድ ያጋጠሙ መስተጓጉሎች እንደተጠበቁ ሆነው ከሞላ ጎደል በሰላማዊ መንገድ በመፈፀም ላይ ነው ብለዋል ሀላፊው።

[AMC]
@YeneTube @FikerAssefa
በሃሰተኛ ገንዘብ ነዳጅ ቀድቶ ለማምለጥ የሞከረው አሽከርካሪ በትራፊክ አደጋ ህይወቱ አለፈ፡፡

በሃሰተኛ ገንዘብ ነዳጅ ቀድቶ ለማምለጥ የሞከረው አሽከርካሪ ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡የትራፊክ አደጋው የደረሰው ትናንት ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ/ም ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ሚካኤል አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው ፡፡


የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1- 30262 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ ከጀሞ 1 አቅጣጫ ወደ ሚካኤል አደባባይ እየተጓዘ 67 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ነዳጅ ማደያ ውስጥ ነዳጅ ሊቀዳ መግባቱን በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ አደጋ ምርመራ ቲም ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ወልዴ ገልፀዋል፡፡

አሽከርካሪው ነዳጅ ከቀዳ በኋላ አምስት ባለ 100 መቶ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ለነዳጅ ማደያው ሰራተኛ ሰጥቶ በሚሄድበት ወቅት ነዳጅ ቀጂው የብሮቹን ትክክለኛነት በመጠራጠሩ ሊያስቆመው መሞከሩን ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ጠቅሰዋል፡፡

አሽከርካሪው ግን በፍጥነት በማሽከርከር ለማምለጥ ጥረት ሲያደርግ መንገድ ዳር ቆሞ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3A- 60203 አ.አ ከሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ህይወቱ ማለፉን ተናግረዋል፡፡

በወቅቱ አብረውት ተሳፍረው የነበሩ 2 ግለሰቦች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት በመድረሱ ተጎጂዎቹ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ወልዴ አስረድተዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ጸጥታ ኃይሎች ትናንት ከቀትር በኋላ ይዘው የወሰዱት የ"ኢትዮ ፎረም" የዩትዩብ መገናኛ ብዙኀን አዘጋጅ ጋዜጠኛ ያየህሰው ሽመልስ፣ ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ፣ በፖሊስ የተጠረጠረበት ወንጀል እንደተነገረው ዋዜማ ዘግባለች።

መርማሪ ፖሊስ ያየህሰውን በብሄሮች እና ሐይማኖቶች መካከል ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት ፌደራል መንግሥቱን በሕዝብ ዘንድ አመኔታ ለማሳጣት ሙከራ አድርጓል በሚል ወንጀል እንደጠረጠረው ለችሎቱ አስረድቷል።መርማሪ ፖሊስ ይህንኑ ተጠርጣሪው የተጠረጠረበትን ወንጀል ለመመርመር 14 የምርመራ ቀናት ይሰጠኝ ሲል ችሎቱን ጠይቋል።

የተከሳሽ ጠበቃ ግን በደንበኛቸው ላይ የቀረበው የምርመራ ጊዜ ጥያቄ ግልጽነት የጎደለው፣ በዘፈቀደ የቀረበ እና ተጠርጣሪው መቼ፣ የት እና በየትኛው ብዙኀን መገናኛ ሁከትና ብጥብጥ እንዳስነሳ ያላስረዳ ነው በማለት ተቃውሞውን አቅርቧል።መርማሪ ፖሊስ የተጠርጣሪውን ግብረ አበሮች ለመያዝ ስለጠየቀ ብቻ ተጠርጣሪው በእስር ላይ መቆየት የለበትም በማለትም የተጠርጣሪ ጠበቃ አቤት ብሏል።በመቀጠልም ጠበቃ ደንበኛቸው ለችሎቱ የሚያስረዳው ጉዳይ እንዳለው ገልጾ፣ ተጠርጣሪው እንዲናገር ተፈቅዶለታል።

ተጠርጣሪው በሁለት ዓመታት ውስጥ ሲታሰር ያሁኑ ስድስተኛው እንደሆነ እና በየጊዜው በሚደርስበት ማስፈራሪያ ሳቢያ ሥራ ከሰራ ሁለት ዓመት እንደሆነው ለችሎቱ ተናግሯል።ተጠርጣሪው በየትኛው ጊዜ ነው መንግሥት ላይ ሁከት የምፈጥረው? በማለትም ጠይቋል።ካሁን ቀደም በአፋር ክልል አዋሽ አርባ ለ54 ቀናት ታስሮ እንደነበር የገለጸው ተጠርጣሪው፣ ትናንት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከመንገድ ላይ እንደታፈነ እና ችሎቱን በማመን ብቻ ችሎት እንደቀረበ አስረድቷል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ፣ በመገናኛ ብዙኀን ሁከት ለመቀስቀስ በስውር ተደራጅቶ ከሚንቀሳቀስ ቡድን ውስጥ አብሮ አለበት፤ ይህንኑ ቡድንም ይመራል የሚል እምነት አለን ሲል ለችሎቱ ተናግሯል። ተጠርጣሪው ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ መታሰሩ ይህንኑ ጥርጣሬ ያጠናክራል በማለት ሃሳቡን ያጠናከረው መርማሪ ፖሊስ፣ በ"ኢትዮ ፎረም" እና ሌሎች መገናኛ ብዙኀን እየቀረበ የተለያዩ ንግግሮችን ሲያደርግ ቆይቷል ብሏል። ሆኖም ፖሊስ ተጠርጣሪው የቀረበባቸው መገናኛ ብዙኀን መረጃ ሊያጠፉብኝ ይችላሉ በማለት ስማቸውን መጥቀስ እንደማይፈልግ ለችሎቱ አብራርቷል።

ተጠርጣሪው ግን ካሁን ቀደም አምስት ጊዜ ሲታሰር አንድም ጊዜ ዓቃቤ ሕግ አስፈርዶበት እንደማያውቅ እና በድንገት እየታፈነ ከታሰረ በኋላ እንደሚለቀቅ ለችሎቱ አስረድቷል።

ችሎቱ የሁለቱን ወገኖች ክርክር ካዳመጠ በኋላ፣ የመርማሪ ፖሊስ ምርመራ ገና መጀመሩ እንደሆነ በመግለጽ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅጃለሁ በማለት፣ መርማሪ ፖሊስ ጅምር የምርመራ መዝገቡን ለግንቦት 29 ይዞ እንዲቀርብ ለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢሰመኮ በኢትዮጵያ የታሰሩት ጋዜጠኞች ቁጥር 16 ደርሷል አለ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ዛሬ ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣው አጭር መግለጫ ግንቦት 18 የፍትሕ መፅሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝና የኢትዮ-ፎረም የዩተብ ቻናል አዘጋጅ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ መታሰር የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸው ጋዜጠኞች ቀጥር 16 መደረሱን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽነሩ ዳኒኤል በቀለ(ዶ/ር) በመግለጫው ላይ በተላለፈ መልዕክታቸው ” የሚዲያ ባለሙያዎች እስር አስደንጋጭ ነው፤ ምክንያቱም ከመገናኛ ብዙሃን ህግ ጋር የሚቃረን ነው” ሲሉ ተችተዋል፡፡

”የጋዜጠኞቹ እስር የሚያሰከትለው መዘዝ ከመገናኛ ብዙሃንና ሀሳብን ከነፃነት መግለፅም በላይ የተለጠጠ ነው::” ብለውታል፡፡”ከፍርድ ቤት በፊት ያለ የተራዘመ እስራት፣ ታስረው የት እንዳሉ አለማወቅ፣ መደበኛ ባልሆኑ ማቆያ ስፍራዎች ማሰር፣ ከሚዲያ ህግ ጋር የሚቃረንና ሁኔታውን የሚያባብስ ነው፡፡” ሲሉ አሳስበዋል፡፡አክለውም ” ሁሉም የሚዲያ ሰራተኞች በአፋጣኝ ከእስር እንዲፈቱ” ጠይቀዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሀጂ ዑመር እድሪስ "ከስልጣን እንደተነሱ ተደርጎ የተወሰነው ውሳኔ በየትኛውም ተቋም ተፈጻሚነት የለውም" ተባለ!

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ፤ ትናንት በሸራተን ሆቴል በተደረገ ስብሰባ ከሥልጣን መነሳታቸው በየትኛውም ተቋም ተፈፃሚነት እንደሌለው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

ም/ቤቱ በዛሬ መግለጫው፤ ትናንትና ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም ``የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ውሳኔዎች`` በሚል በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል የተካሄደውን ስብሰባም ህገወጥ መሆኑን ገልጿል ፡፡

ህገ ወጥ የተባለው የሸራተኑ ስብሰባ ባካሄደው ምርጫ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሒም ቱፋ የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ አብዱልከሪም ሼኽ በድረዲን የመጅሊሱ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጦ ነበር።

ከዚህ ባለፈም በስብሰባው ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እና ምክትላቸው ጄይላን ከድር (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የመጅሊሱ አመራሮችም ከቦታቸው እንዲነሱና የፈትዋ ምክር ቤት አመራር እንዲሆኑ ተወስኖ ነበር።

ውሳኔው ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጽ ዛሬ አርብ ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ/ም መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስብሰባውንም ሆነ የስብሰባውን ውሳኔ ውድቅ አድርጓል፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በፖሊሳዊ ኢንተለጀንስ ሙያ ያሠለጠናቸውን የፖሊስ አመራሮችና አባላት አስመረቀ!

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በፖሊሳዊ ኢንተለጀንስ ሙያ ያሠለጠናቸውን የፖሊስ አመራሮችና አባላት በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡ተቋሙ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ባለሙያዎች አማካኝነት ያሠለጠናቸው የፖሊስ አመራሮችና አባላት በወንጀል መከላከልና በምርመራ ሥራው ላይ መረጃ መር የሆነ ፖሊሳዊ ሥምሪት መሥጠት እንዲችሉ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ፥ ተመራቂዎች የሥራ ስምሪት በመውሰድ ክፍተቶችን እንደምትሞሉና የህዝብ ደኅንነት እንደምታረጋግጡ ብሎም ለማናቸውም ተልዕኮ ብቁ በመሆን በጥብቅ ፖሊሳዊ ስነ ምግባር እንደምትሰሩ አምናለሁ ብለዋል፡፡

የሥራ አቅማችንን ከ25 በመቶ በማሳደግ ሽፋናችንን የተሻለ እንደምታደርጉ እናምናለንም ነው ያሉት፡፡በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል የፖሊስ ኮሚሽነሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የተምች ወረርሽኝ መከሰቱን የክልሉ አርሶ አደሮች ገለጹ።

አርሶ አደሮቹ እንዳሉት በአካባቢያቸው ከባለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ የተከሰተው የተምች ወረርሽኝ በበቆሎና በሩዝ ማሳዎቻቸው ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።የተምች ወረርሽኙ በክልሉ 12 ወረዳዎች ውስጥ በ1 ሺህ 219 ሄክታር መሬት ላይ መከሰቱን ለዶቼ ቬለ የገለጹት የክልሉ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ በአሁኑ ወቅትም ወረርሽኙን በባህላዊና በዘመናዊ የመከላከያ ዘዴዎች ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች እንዳሉት የተምች ወረርሽኙ በአካባቢያቸው መታየት የጀመረው ከባለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ ነው።በተለይም በክልሉ በሰብል አምራችነቱ በሚታወቀው የቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ወረርሽኙ በስፋት መታየቱን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

በዞኑ ጉራፈርዳ ወረዳ የኩጃ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶአደር ጎቻው አይተንፍሱ እና ገበየሁ አማረ የተምች ወረርሽኙ የተከሰተው ሰሞኑን በአካባቢያቸው በካፊያ መልክ የጣለውን ዝናብ ተከትሎ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ወረርሽኙ አሁንባለው ሁኔታ በደረሱ የቦቆሎና የሩዝ ሰብሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ የጠቀሱት አርሶአደሮቹ በዚህም የምርት መቀነስ ሊያጋጥም ይችላል የሚል ሥጋት እንዳደረባቸው ተናግረዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ያጋጠመው የተምች ወረርሽኝ በቅድሚያ በክልሉ ከፋ ዞን ከተከሰተ በኋላ በቀናት ልዩነት በሌሎች አካባቢዎችም መታየቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል። የግብርና ጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ በአሁኑወቅት ወረርሽኙ በክልሉ 4 ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 12 ወረዳዎች ውስጥ በ 1 ሺህ 219 ሄክታር መሬት ላይ መታየቱን ነው ለዶቼ ቬለ የገለጹት።በአሁኑ ወቅት በክልሉ የተከሰተውን የተምች ወረርሽኝ በባህላዊና በዘመናዊ የመከላከያ ዘዴዎች ለመቆጣጠር ጥረት በመደረግ ላይ እንደሚገኝም ምክትል ኃላፊ ተናግረዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የጋዜጠኛ ሰቦንቱ አህመድና በቃሉ አላምረውን እስር ጨምሮ የታሰሩ የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች 18 ደረሱ!

አልፋ ቴሌቪዥን የተሰኘው የዩቲዩብ ገፅ መስራች ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው እና የፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ ጋዜጠኛዋ ሰቦንቱ አህመድ በፀጥታ ኃይሎች መያዛቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው የሁለቱን ባለሙያዎች እስር ተከትሎ በፀጥታ ኃይሎች የተያዙ የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ቁጥር 18 ደርሷል።

ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) እንደገለፁት በኢትዮጵያ የሚድያ ህግ፤ በመገናኛ ብዙኀን አውታሮች ተፈፅመዋል ለሚባሉ የህግ ጥሰቶች በምንም መንገድ ለፍርድ ሳይቀርቡ ማሰር ክልክል መሆኑን አስታውሰዋል።

በመሆኑም ሁሉም የታሰሩ የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች እንዲፈቱ ኮሚሽኑ ጠይቋል።በተያያዘ መረጃ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራር የሆነው ስንታየሁ ቸኮል በባህር ዳር ከተማ በፀጥታ ኃይሎች ተይዞ 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩን ፓርቲው ገልጿል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ግብፅ ውስጥ ሊደፍራት ሞክሯል የተባለውን ‘የባጃጅ’ ሹፌር የገደለችው ሶማሊያዊት ታዳጊ ከእስር ተለቀቀች።

የ15 ዓመቷ ታዳጊ ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ ብላ ለፖሊስ እጇን መስጠቷን እና ለአራት ቀናት በእስር ላይ እንደነበረች የግብፅ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።የፖሊስ እና የሕክምና ምርመራ ታዳጊዋ ራሷን ለመከላከል የወሰደችው እርምጃ ሊሆን እንደሚችል ማሳየቱን የግብፅ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ገልጿል።

ሶማሊያዊቷ ታዳጊ ትላንት አርብ ከእስር መለቀቋ የተሰማ ሲሆን ተጨማሪ ምርመራ እንደሚደረግም ተሰምቷል።

ሟቹ የባጃጅ ሹፌር ታዳጊዋን ራቅ ወዳለ ስፍራ ወስዶ ለመድፈር መሞከሩን አህራም ሆንላይን የተባለ የግብፅ ሚዲያ ዘግቧል።ሆኖም ከግለሰቡ ጋር ግብግብ የገጠመች ታዳጊዋ በቢላዋ ወግታው ከአከባቢው መሸሿ የተነገረ ሲሆን የእሷም እጅ መጎዳቱ ተዘግቧል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት የሕወሓትን ምርኮኛ መልቀቅ ሐሰት ነው ቢልም የተማረኩ አባላት ተለቀናል አሉ!

የፌዴራል መንግሥት ሕወሓት “ምርኮኞችን ለቀቅኩ የሚለው የሐሰት ትርክቱ ነው” ቢልም፣ ከተለቀቁት ሰዎች ውስጥ በሕወሓት ተማርከን ነበር የሚሉ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት መኖራቸውን አዲስ ማለዳ ከተለቀቁ የመከላከያ አባላት ቤተሰብ ሠምታለች።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው ሕወሓት ለአራት ሺሕ ምርኮኞችን ምኅረት አደረኩ ብሎ የለቀቃቸውን ሰዎች ወደ አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢ መሸኘቱ የሚታወስ ነው። ሕወሓት በሰቆጣ በኩል ወደ አማራ ክልል የሸኛቸው አራት ሺሕ ሰዎች ግንቦት አጋማሽ ሰቆጣ መግባታቸውንና ሕወሓት ከለቀቃቸው ሰዎች መካከል፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባል የነበሩና የፌዴራል መንግሥት ከትግራይ ከመውጣቱ በፊት በሕወሓት የተማረኩ የሠራዊት አባላት አሉበት።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ በፌደራል ፖሊስ አባላት መታሰሯ ተሰማ።

" ሮሃ ሚዲያ " የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነችው መዓዛ መሐመድ ዛሬ ጠዋት በፖሊስ ተይዛ መወሰዷን የስራ ባልደረባዋ እና ጓደኛዋን ዋቢ አድርጎ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ " ዘግቧል።

የጋዜጠኛዋ እስር በኢትዮጵያ ከሰሞኑ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞችን ቁጥር 19 አድርሶታል።

ጋዜጠኛ መዓዛ የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ በለበሱ 2 ፖሊሶች እና የሲቪል ልብስ ባደረጉ 3 የጸጥታ ኃይሎች የተያዘችው በአዲስ አበባ ሰሚት ኮንዶሚኒየም ከሚገኝ የእርሷ መኖሪያ ቤት እንደሆነ ጋዜጠኛ ምስራቅ ተፈራ ገልጻለች።

የጸጥታ ኃይሎቹ መዓዛን ለ " ጥያቄ እንፈልጋታለን " በሚል ምክንያት ቢይዟትም ወዴት እንደሚወስዷት ለመናገር ፈቃደኛ እንዳልነበሩ ጋዜጠኛዋ ማስረዳቷን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር አስነብቧል።ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ ከወራት በፊት ለእስር ተዳርጋ መፈታቷ ይታወሳል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል በዘጠኝ ወራት 471 ሴቶች ተጠልፈዋል ተባለ!

በአማራ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት 471 ሴቶች መጠለፋቸውን የአማራ ክልል ሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።

የአማራ ክልል ሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ የሴቶች ንቅናቄ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ስማቸው ዳኘ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ በክልሉ ያለው ጠለፋ እና ያለእድሜ ጋብቻ እንደቀጠለ ነው። በ2013 ሐምሌ ጀምሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 471 ሴቶች ካለፍላጎታቸው ተጠልፈዋል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም በተያዘው ዓመት በክልል ያለው ያለዕድሜ ጋብቻ እንደጨመረ እና ለዚህም በባለፈው ዓመት በነበረው የሰሜን ጦርነት ኢኮኖሚያቸው ላይ ተፅዕኖ ያደረባቸው ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ያለዕድሜያቸው ለመዳር እንደተገደዱ እና መንግሥትም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መወጠሩ ለችግሩ መጨመር በምክንያትነት ተጠቅሳል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ሩፋኤል አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል፡፡

አደጋዉ የተከሰተዉ በአንድ የቢሮ እቃዎች ማምረቻ መጋዘን ዉስጥ መሆኑም ታዉቋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞችና 13 ተሸከርካሪዎች በቦታዉ ላይ የደረሱ ሲሆን፣ እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ በአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረዉናል፡፡

አካበባዉ በርካታ ቤቶች በተጨናነቀ መልኩ ተሰርተዉ የሚገኙበት በመሆኑ እሳቱን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እንዳደረገዉም ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡

ከቀኑ 6፡30 አካባቢ በተከሰተዉ በዚህ የእሳት አደጋ እስካሁን ባለዉ መረጃ የተወሰኑ ሰዎች በጭስ የመታፈን አደጋ አጋጥሟቸዋል ተብሏል፡፡
አሁን ላይ የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ገና ጥረት እየተደረገ ተብሏል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ዋልያዎቹ ከሌሴቶ አቻቸው ጋር በአቻ ውጤት ተለያይተዋል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሌሴቶ አቻው ጋር ባደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይቷል፡፡ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሌሴቶ በ20ኛው ደቂቃ በማክሀ ቱሜሎ አማካኝነት የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥራለች፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደግሞ አቻ የምታደርገውን ጎል በ61ኛ ደቂቃ በይገዙ ቦጋለ አማካኝነት አስቆጥሯል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ዶ/ር ሊያ ታደሰ የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆነው ተመረጡ።

ከቀናት በፊት በተደረገው የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ምርጫ ላይ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ዳግም መመረጥ የተቃወመችው ኢትዮጵያ ከግንቦት 14 2014 ዓ.ም ጀምሮ በጄኔቭ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የአለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ዶ/ር ሊያ ታደሰን የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል አድርጋ አስመርጣለች።

ከመላው ዓለም የተውጣጡ 34 በጤና ዘርፍ ከፍተኛ እውቀት ያላቸው እና በአባል ሀገራት የተወከሉ ባለምያዎችን በሚይዘው ቦርድ ውስጥ ከአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሰባት ሀገራት ተወካዮቻቸውን ያስመረጡ ሲሆን እነኚህ ተመራጮች ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት ድርጅቱን ያገለግላሉ። የቦርዱ ዋነኛ ተግባር የጠቅላላ ጉባዔውን ውሳኔ እና ፖሊሲ ማስፈጸም እንዲሁም ምክረ-ሀሳብ ማቅረብ እና ስራዎችን ማመቻቸት ነው።

@Yenetube @Fikerassefa
ሩሲያ በታሪክ ከፍተኛውን ገቢ ከነዳጅ እንደምታገኝ ገለጸች

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የገባችበት ጦርነት የዓለም ነዳጅ ዋጋን በማናር ላይ ይገኛል
ሩሲያ በታሪክ ከፍተኛውን ገቢ ከነዳጅ እንደምታገኝ ገለጸች።

የሩሲያ ፋይናንስ ሚኒስትር እንዳሉት በተያዘው የፈረንጆቹ 2022 ዓመት ተጨማሪ 14 ቢሊዮን ዶላር ነዳጅ እንደምታገኝ ይጠበቃል።

ሚኒስትሩ አንተን ሲሉአኖቭ እንደተናገሩት ባለፈው ዓመት ሩሲያ ከነዳጅ ገበያ ያገኘችው ዓመታዊ ገቢ 9 ቢሊየን ዶላር ነበር።

በተያዘው ዓመት ተጨማሪ 14 ቢሊየን ዶላር ነዳጅ እንደምታገኝ የገለጸችው ሩሲያ፤ ገቢውን የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚዋን ለማረጋጋት እንደምታውለውም ሚኒስትሩ አክለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ከዩክሬን ጋር ለጀመረችው ጦርነት ወጪ እንደምታውለውም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ከጀመረች ሶስት ወራት አልፎታል።

ጦርነቱን ተከትሎም በአሜሪካ አስተባባሪነት ከ6 ሺህ በላይ ማዕቀቦችን የተለያዩ ሀገራት በሩሲያ ላይ ጥለዋል።

ሩሲያም ወዳጅ አይደሉም ያለቻቸውን ሀገራት ነዳጇን በሩብል እንዲከፍሉ ትዕዛዝ ማስተላለፏን ተከትሎ የአውሮፓ ኩባንያዎች ነዳጅ በሩብል መግዛት ጀምረዋል።

ጀርመን እና ጣልያን ከሩሲያ ነዳጅን በሩብል ለመግዛት ወሰኑ 40 በመቶ የአውሮፓ ሀገራትን ነዳጅ ፍላጎት የምታሟላው ሩሲያ ነዳጇን እንዳትሸጥ ማዕቀብ ቢጣልባትም ሀገራት ግን ምርጫ አጥተው አሁንም የሩሲያን ነዳጅ በመግዛት ላይ ናቸው።
በዚህ ጦርነት ምክንያት የዩክሬን ዋና ዋና የሚባሉ ከተሞችን ጨምሮ የንግድ ማሳለጫ ወደቦች እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ወድመዋል።

Via:- Al ain
@Yenetube @Fikerassefa