#Breaking
ዛሬ በጀኔቫ የተካሄደው የዓለም ጤና ድርጅት አባል አገራት ጉባዔ ኢትዮጵያዊው የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም በድጋሚ ድርጅቱን ለአምስት ዓመታት እንዲመሩ ዛሬ መርጧቸዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ድርጅቱን ለሁለተኛ ሥልጣን ዘመን እንዲመሩ የድርጅቱ የበላይ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ብቸኛው ዕጩ አድርጎ ያቀረባቸው ባለፈው ጥር ነበር።
ዶ/ር ቴዎድሮስ ሁለተኛውን ዙር የሥልጣን ዘመናቸውን በመጭው ነሐሴ ይጀምራሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴዎድሮስ ለሕወሃት ድጋፍ ሰጥተዋል በማለት፣ በድጋሚ እንዳይመረጡ ድጋፉን እንደነፈጋቸው ይታወሳል። ሌሎች በርካታ አገራት ግን ዶ/ር ቴዎድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም ዙሪያ ለተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ብቁ አመራር ሰጥተዋል ብለው ሲያወድሷቸው ቆይተዋል።
[ዋዜማ ራዲዮ]
@Yenetube @Fikerassefa

አሜሪካ በኢትዮጵያ የሰሞኑ የጋዜጠኞች እና ማሕብረሰብ አንቂዎች የጅምላ እስር እንዳሳሰባት ገለጸች፡፡
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳለዉ የጅምላ እስሮቹን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባቀረበው ምክረ ሃሳብ መሠረት የፌደራል እና የክልል ፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ሕጋዊ አሰራሮችን መከተል አለባቸው ብሏል።
በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች እና የማህበረሰብ አንቂዎች በጅምላ እየታሰሩ ነው ያለው ኤምባሲው የፌደራል እና የክልል የጸጥታ ሀይሎች ተገቢውን የህግ ሂደት እንዲጠብቁና የህግ የበላይነት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጉዳዩን በተመለከተ የገለጸውን ስጋት እንደሚጋራውም ነው ኤምባሲው ያስታወቀው፡
ኢሰመኮ ግንቦት 14/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ የጋዜጠኞችና ማኅበረሰብ አንቂዎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለእስር እየተዳረጉ መሆኑን ኮንኖ ነበር።
በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ያሉት ተጠርጣሪዎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከመታሰራቸው ባሻገር የተወሰኑት ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡና በቤተሰቦቻቸው ያልተጎበኙ መኖራቸውንም ኢሰመኮ ገልጿል።
"በርካታ ታሳሪዎች ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ መታሰራቸውን፣ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን፣ በቤተሰብ አለመጎብኘታቸውን" እንደተገነዘበ የሰብአዊ መብት ኮሚሽኑ መግለጹ ይታወሳል፡፡
ከሰሞኑ የፌዴራል መንግሥት እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች በተቀናጀ መንገድ "የሕግ የበላይነትን ማስከበር" በሚል መውሰድ በጀመሩት እርምጃ ጋዜጠኞች እና የማኅብረሰብ አንቂዎችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቁጥጥር መዋላቸዉ ተገልጿል፡፡
በአማራ ክልል ብቻ ከ4500 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ባሳለፍነዉ ሰኞ ማስታወቁም ይታወሳል፡፡
Via :- Ethio FM

#ሉባር መጽሐፍ
ሁለተኛው ዕትም በገበያ ላይ
ሊከድኑት የሚሳሱለት ተወዳጁ ሉባር መጽሐፍ ለሁለተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ዋለ።
ድርሰቱ ከጎንደር ፋሲለደስ እስከ ዘጌ ጊዮርጊስ፤ ከዘጌ ጊዮርጊስ እስከ ዳጋ እስጢፋኖስ፤ ከዳጋ እስጢፋኖስ እስከ ጣና ቂርቆስ፤ ከጣና ቂርቆስ እስከ ዲማ ጊዮርጊስ የተዘረጋ መሳጭ ታሪክ፡፡
ታሪክን- ከወቅታዊ ክስተት፣ ፍልስፍናን- ከነባራዊ ሁነት፣ እውቀትን - ከጥበብ፣ ስልጣኔን - ከባህልና ወግ ጋር አግባብቶና አጣጥሞ በፍቅር ቅኝት ሞሽሮና ገምዶ የያዘ መጽሐፍ፤
እንደ ስሙ ቅዱስና ከፍ ያለ የሀሳብ ልዕልናን የተጎናፀፈ መጽሐፍ ነው። ቢያነቡት በርካታ ህይወት ቀያሪ ተሞክሮዎችን ከተሟላ እርካታ ጋር ያገኙበታል።
#ሉባር
#ለትውልድና_ለሀገር
“ደራሲው በቁጭት የሀገራችንን የከፍታ ዘመን እያነሳ ወደ ኋላቀርነትና ድኅነት የተንደረደርንባቸውን ምክንያቶች እየጠቀሰ፣ ከችግሮች የምንላቀቅባቸውን መንገዶች በዝርዝር ያስረዳል፡፡ ቢያነቡት አስተማሪ ተሞክሮዎችንና በርካታ ጭብጦችን ያገኙበታል።”
ዶ/ር ሞገስ ሚካኤል
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ የዐባይ የቋንቋና የባህል ጥናት ተቋም ኃላፊ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡
*
ቤተሰብ ይሁኑ
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun

በቴክሳስ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በተፈፀመ ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ 21 ሰዎች ተገደሉ!
በደቡብ ቴክሳስ በሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ 19 ህፃናት እና ሁለት ጎልማሶች ህይወታቸው አልፏል።የ18 አመቱ ታጣቂ በኡቫልዴ ከተማ ሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በህግ አስከባሪዎች ከመገደሉ በፊት ጥቃቱን መፈፀሙን የመንግስት ባለስልጣናት ተናግረዋል።
መርማሪዎቹ እንደተናገሩት ተጠርጣሪው የእጅ ሽጉጥ እና ኤአር-15 የተሰኘ ከፊል አውቶማቲክ ጠመንጃ እና ከፍተኛ አቅም ያለው መሳሪያ ታጥቆ እንደነበር ገልፀዋል። ታዳጊው ጥቃቱን የጀመረው አያቱ ላይ በመተኮስ እንደሆነም ተገልጿል። ምናልባት በአካባቢው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሊሆን እንደሚችል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የኡቫልዴ አውራጃ የፖሊስ አዛዥ ፒት አርሬዶንዶ እንደተናገሩት ታዳጊው ተኩሱ የጀመረው በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ማክሰኞ 11፡32 ላይ ሲሆን መርማሪዎች ይህንን አሰቃቂ ጥቃ ለብቻው መፈፀሙን ያምናሉ።የቴክሳስ ገዥ ግሬግ አቦት እንደተናገሩት ሳልቫዶር ራሞስ የተባለው ጥቃት አድራሽ መኪናው በትምህርት ቤቱ በራፍ ላይ በመተው “በአሰቃቂ ሁኔታ ለመረዳት በማይቻል ሁኔታ” ተኩስ ከፍቷል ሲሉ ተናግረዋል።በሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በጅምላ የተፈፀመው የተኩስ እሩምታ በ10 ዓመታት ውስጥ በአሜሪካ ውስጥ ከታዩት ሁሉ የከፋ መሆኑን መረጃዎች አመላክተዋል።
@YeneTube @FikerAssefa

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከአብን ሥራ አስፈፃሚነታቸው መልቀቃቸውን በይፋ አሳወቁ!
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ትናንት ማምሻውን ባሰፈሩት መልዕክት አብን ባለፈው የካቲት አካሂዶት በነበረው ጊዜያዊ የአስፈፃሚ ሪፎርም ላይ ንቅናቄው በቀጣይ 3 ወር ውስጥ የሚያካሂደው ሪፎርም ተከናውኖ አዳዲስ አመራሮች እስኪመረጡ ድረስ ከ2 እስከ 3 ወር ላልበለጠ ጊዜ ወደ ሥራ አስፈፃሚ እንዲመለሱ የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ ወስኖ እንደነበር አስታውሰዋል።
አክለውም ”ወደ አመራርነት የመመለስ ፍላጎት ባይኖረኝም የድርጅቴ ውሳኔ ስለነበር ውሳኔውን ተቀብየው ቆይቻለሁ።” ብለዋል።
”ለአጭር ጊዜ ብየ የተመለስኩበት ጊዜ ስለተጠናቀቀ፣ እንዲሁም ወደፊት ጊዜው ሲደርስ በምገልፃቸው ምክንያቶች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከአብን ሥራ አስፈፃሚ አባልነቴ በፈቃዴ የለቀቅሁ ሲሆን፤ በማኮ አባልነት ግን የአብን ሪፎርም በስኬት እስኪጠናቀቅ የምቀጥል ይሆናል።“ ሲሉም ገልፀዋል።
ዶ/ር ደሳለኝ “የንቅናቄው ሪፎርም በአጭር ጊዜ ተጠናቆ አብን ተጠናክሮ ሲቆም፤ ደግሞ ልክ ከአብን ሊቀ መንበርነቴ በገዛ ፈቃዴ እንደለቀቅሁት ኹሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነቴንም በገዛ ፈቃዴ በመልቀቅ አዳዲስ መሪዎች በማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ እድል እንዲያገኙ ለማድረግ መወሰኔን እገልፃለሁ።“ ያሉ ሲሆን ከአብን ሥራ አስፈፃሚነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ "የፀጥታና ደህንነት ኦፕሬሽን" አካሄድን በተመለከተ ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡
የፀጥታና ደህንነት ኦፕሬሽን አካሄድ ግምገማ ላይ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ እንዲሁም የክልልና የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት በወሰነው መሰረት በኢትዮጵያ የህግ የበላይነትን በማስከበር የህዝብ ደህንነት ስጋትን ማስወገድ፣ ለውጭ ጠላት ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ ያለውን የውስጥ ተጋላጭነትን መቀነስ፣ እንዲሁም ሰላምን በማስፈን ልማትን ማረጋገጥን ታሳቢ ተደርጎ ወደ ሥራ መገባቱ ይታወሳል።
ምክር ቤቱ የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው የታጠቁ ሀይሎችን በመለየት መልክ ማስያዝ፣ ታጥቀውና ተደራጅተው በህገወጥ መንገድ የተሰማሩ ፅንፈኛ ቡድኖችን ወደ ህጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ ማስቻልን ታሳቢ ያደረገ አቅጣጫ ማስቀመጡ ተነግሯል።
በዚህም የፀጥታ አካላት እንዲሁም የክልል አመራሮች የፀጥታና ደህንነትን በማረጋገጡ ሂደት የተሰሩ ሥራዎች ተገምግመው ቀጣይ አቅጣጫ የሚቀመጥ ይሆናል መባሉን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ናይጄሪያ አቡጃ ገቡ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ ልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ናይጄሪያ አቡጃ ገብተዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ ልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ናይጄሪያ አቡጃ ገብተዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
አብን በስራ አስፈፃሚው ደሳለኝ ጫኔ ከአባልነት መነሳት ዙሪያ አልተወያየሁም አለ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ስራ አስፈፃሚ አባሉና የቀድሞው የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ማምሻውን በተረጋገጠ የፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት በገዛ ፍቃዳቸው ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡
ዶክተር ” ንቅናቄው ባለፈው የካቲት ወር ባካሄደው የአስፈፃሚ ተሃድሶ በቀጣይ ሦስት ወራት ተከናውኖ አዳዲስ አመራሮች እስኪመረጡ ድረስ ከ2 እስከ 3 ወር ባልበለጠ ጊዜ ወደ ስራ አስፈፃሚ እንደመለስ ፓርቲው ወስኖ ነበር” ብለዋል፡፡
ለመመለሱ ፍላጎት ባይኖረኝም የፓርቲው ውሳኔ በመሆኑ ተቀብዬው ቆይቻላሁ ያሉት ስራ አስፈፃሚ አባሉ ወደፊት በምገልጸው ባሉትና አሁን ባልዘረዘሩት ምክንያት ከስራ አስፈፃሚ አባልነቴ ራሴን አግልያለሁ ሲሉ ፅፈዋል፡፡
በንቅናቄው አባልነት እንደሚወጥሉ ግን ማረጋገጫቸውን ሰጥተዋል፡፡ አሻም ይህን በመያዝ የንቅናቄው ጽ/ቤት ሃለፊ ዶክተር ቴዎድሮስ ሀይለማርያምን ያነጋገረች ሲሆን ሃለፊው በሰጡት ምላሽ ፓርቲው በስራ አስፈፃሚ ደረጃ ውይይት አላካሄደበትም ብለዋል፡፡
ከአንድ ወር ገደማ አብን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ አባሉ ክስርስቲያን ታደለ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
እንደ ጣሂር መሀመድ፣ ዩሱፍ ኢብራሂም ያሉ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርና በአማራ ክልል የተለያዩ የስራ ሃለፊነቶች ከመንግስት እንደተሠጣቸው ይታወቃል፡፡

ተመድ በየመን የታሰሩ 6 ሺ 750 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ሊመልስ ነው!
የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ በመጪዎቹ ወራት ቢያንስ 6 ሺ 750 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በጦርነት በመታመስ ላይ ካለቸው የመን ለማስመለስ ማቀዱን አስታወቀ፡፡ድርጅቱ ስደተኞቹን ለመመለስ በሚያደርገው ጥረት 7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ጠይቋል።ባለፉት ወራት በሶስት በረራዎች ከ600 በላይ ስደተኞችንና ቤተሰብ የሌላቸው 60 ህጻናትን ወደ ኢትዮጵያ ማዘዋወሩን የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቋል።በደቡብ የመን የወደብ ከተማ ኤደን እና በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ መካከል ተጨማሪ በረራዎች ለማድረግ እቅድ እንዳለም ገልጿል ድርጅቱ፡፡
[Alain]

የህክምና ቁሳቁስ የጫኑ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ተሽከርካሪዎች መቀሌ ገቡ!
የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቀሌ መግባታቸውን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ።ለአምስተኛ ጊዜ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ የምግብ ድጋፎችን፣ የውሃ ማጣሪያ ግብዓቶችንና አስፈላጊ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን ይዘው መቀሌ መግባታቸውን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ አሰታውቋል።በተመሳሳይ በትናንትናው ዕለት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙ ሁለት መጠለያ ጣቢያዎች ለሚኖሩ 9 ሺህ ዜጎች የምግብ ድጋፍ ማድረጉን ኮሚቴው ጨምሮ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት አዳዲስ ቦይንግ 777 ካርጎ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙን ዛሬ ቦይንግ በድረገጹ አስታውቋል።
አየር መንገዱ አምስት ተጨማሪ ካርጎ አውሮፕላኖችን ማዘዙ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሄደውን የካርጎ ገበያ ለማሟላት ያግዘዋል ሲሉ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል። አየር መንገዱ ባሁኑ ወቅት 9 ቦይንግ ካርጎ አውሮፕላኖች አሉት።
@YeneTube @FikerAssefa
አየር መንገዱ አምስት ተጨማሪ ካርጎ አውሮፕላኖችን ማዘዙ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሄደውን የካርጎ ገበያ ለማሟላት ያግዘዋል ሲሉ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል። አየር መንገዱ ባሁኑ ወቅት 9 ቦይንግ ካርጎ አውሮፕላኖች አሉት።
@YeneTube @FikerAssefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው የሚገኙ ከ400 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በአስቸኳይ ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ፣ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) ጠየቀ፡፡
በክልሉ ከ2010 ዓ.ም. ጀምሮ በነበሩ ግጭቶች የተፈናቀሉ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በካምፕና በተለያዩ ቦታዎች መኖራቸውንና ክረምት ከመግባቱ በፊት ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ ፓርቲው ጠይቋል። ተፈናቃዮቹ በቂ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳልሆነና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ፣ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ብርሃኑ ለሪፖርተር ገልጸዋል።በክልሉ በተወሰደ የሰላም ማስከበር ዘመቻ አንፃራዊ ሰላም መገኘቱን ገልጸው፣ ነገር ግን ተፈናቃዮችን ወደ ቦታቸው የመመለሱ ሒደት መዘግየቱንና በአስቸኳይ የመመለስ ሥራው ሊከናወን ይገባል ብለዋል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች የሚገኙ ተፈናቃዮችን በተመለከተ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ተሲሳ፣ በክልሉ በአጠቃላይ 442 ሺሕ ተፈናቃዮች መኖራቸውንና ይህም ቁጥር ከክልሉ ሕዝብ አንድ ሦስተኛ እንደሚሆን ገልጸዋል።
በመተከል፣ በካማሺና በአሶሳ ዞኖች ተፈናቃዮች በብዛት እንደሚገኙ ገልጸው፣ እስካሁን የሰባዓዊ ዕርዳታ በበቂ ሁኔታ እየደረሰ ነው ብለዋል። ለዚህም በተለይም መንግሥት እስከ 70 በመቶ የሚሆነውን ዕርዳታ እየሸፈነ መሆኑን፣ ለእያንዳንዱ ተፈናቃዮች በወር 15 ኪሎ ምግብ ነክ ዕርዳታ እየደረሰ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ነገር ግን ዕርዳታውን በማድረስ በኩል ምዕራብ ወለጋ አካባቢ መንገድ በመዘጋቱ መቸገራቸውን ገልጸዋል። በግጭቱ በርካታ የግል ንብረቶች፣ እንዲሁም 189 የጤና ተቋማትና ከ250 በላይ ትምህርት ቤቶች መውደማቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም ተፈናቃዮችን ወደ ቦታቸው መልሶ ለማቋቋም ፈታኝ መሆኑን ጠቁመው፣ ሁሉም የበኩሉን ዕገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
በክልሉ የእርሻ ወቅት ከመድረሱ ጋር ተያይዞ ማዳበሪያና ሌሎች ግብዓቶች በሚፈለገው ደረጃ ባይሆንም መገኘቱን ገልጸው፣ ሥርጭት እየተደረገ ነው ብለዋል። ተፈናቅለው የሚገኙ ሰዎችን መጪው የክረምት ወቅት ከመግባቱ በፊት፣ ወደ ቀዬአቸው እንደሚመለሱ አቶ ታረቀኝ አክለዋል፡፡
Via Reporter

በአማራ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች የሚገኙ የፖለቲካ አመራር የገቡበትን ማወቅ እንዳልቻለ እናት ፓርቲ ገለፀ።
ፓርቲው ከሰሞኑ በአማራ ክልል ቀጥሏል ባለው መንግሥታዊ አፈና በሰቆጣ፣ በአዊ ዞን ቲሊሊ እና በሞጣ ከተሞች የሚገኙ ሁለት አመራሩ የት እንደሚገኙ ማወቅ እንዳልቻለና አንደኛው በፖሊስ መታሰሩራቸውን ማረጋገጡን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል።
በተመሳሳይ በወላይታ ዞን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑ ሴት ከሥራ ቦታቸው ተወስደው ቤተሰብም ሊጠይቃቸው እንዳልቻለ ማወቁን የእናት ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሰይፈ ሥላሴ አያሌው ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናግረዋል።
«እዚህም እዚያም በማናቃቸው ምክንያቶች ሰው በቁጥጥር ስርበሚውልበት ጊዜ በሕጉ መሠረት ከሚታሰርበት ምክንያት፣ አሳሪው የመሳሰሉ ነገሮች ግልጽ መደረግ አለባቸው። ይኼንን ባላመላከተ ወይንም ደግሞ ባላገናዘበ አይነት መልኩ እስካሁን ድረስ በምናውቀው አራት አባሎቻችን በቁጥጥር ስር ውለዋል።ይኼ በጣም እያሳሰበን ያለ ጉዳይ ነው።
የሚያሳስበን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ብቻ አይደለም። አንዳንዶቹ በአግባብም ቤተሰብ ሊያገኛቸው አለመቻሉ ትንሽ ስጋታችን የሚጨምር ነገር አለው።»ፓርቲው «እነዚህ አፈናዎች ፍጹም ፖለቲካዊና አምባገነናዊ ሥርዓትን ለማዋለድ የሚደረግ ነው ብሎ ያምናል» ብሏል በመግለጫው።
መንግሥት ግለሰቦቹን ቢጠረጥራቸው እንኳን ያሉበትን ቦታ የማሳወቅ፣ ቤተዘመድ እንዲጠይቃቸውና ከሥጋት ነጻ እንዲሆን የማድረግ፣ ሕጋዊነትንና ሥርዓትን በተከተለ መልኩ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብታቸውን ማክበር ብሎም ጠበቃ እንዲያቆሙ መፍቀድ ነበረበት ብሏል። ጉዳዩን ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ከሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና መሰል ተቋማት ጋር እንደሚከታተለው የያስታወቀው እናት ፓርቲ መንግሥት «የዜሮ ድምር ፖለቲካዊ» ያለውን አካሄዱን በአፋጣኝ እንዲያርም ጠይቋል።
[DW]

የተፈጥሮ ጋዝና የማዕድን ፈቃድ ወስደው ውጤት ላላሳዩ ኩባንያዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጠ!
በነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ እንዲሁም ወርቅ ምርት እና ፍለጋ ላይ ተሠማርተው ለረጅም ዓመታት ውጤት ላላሳዩ ኩባንያዎች ማስጠንቀቂያ መስጠቱን የማዕድን ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፤ ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባ በዚህ ሳምንት መባቻ የ2014 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሪፖርቱን ሲያቀርቡ እንደገለፁት፤ በነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ እንዲሁም ወርቅ ምርት እና ፍለጋ ላይ ተሠማርተው ለረጅም ዓመታት ውጤት ላላሳዩ ሁለት ኩባንያዎች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡
Via EPA

👍1
በባቡር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ ተገለጸ!
በባቡር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ማስተባበሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቡልቱማ ቂጣታ÷ለባቡር በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል የሃገርን ኢኮኖሚ ወደኋላ ከማስቀረቱም በተጨማሪ በከተማዋ ያለውን የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት እያስተጓጎለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ 16 ሺህ 402 ሜትር የሚረዝም የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኬብል ስርቆት መፈጸሙን ጠቁመው፥ በዚህም 26 ሚሊየን 94 ሺህ 75 ብር የሚገመት ኪሳራ በተቋሙ ላይ መድረሱን አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ በየዓመቱ 3 ሚሊዮን ህፃናት እንደሚውለዱ ተነገረ!
ዮንሴ የተሰኘው አለም አቀፉ ተቋም በኢትዮጵያ ውስጥ የተመጣጠነ ደስተኛ እና ውጤታማ የሆነ የቤተሰብ ፕሮጀክት ሁለተኛውን ክፍል ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስራ መሰራቱን ተነግሯል።ዳሰሳዊ ጥናቱ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ጨምሮ ከአማራ ፣ ኦሮሚያ ፣ ሲዳማ ፣ ሶማሌ እና ደቡብ ክልሎች በተውጣጡ የኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን አዘጋጅቶታል ተብሏል።
በእነዚህ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በተደረገው ዳሰሳዊ ጥናት በተገኘው ግኝት መሰረት በ 54 .1 የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ለቤተሰብ እቅድ ያላቸው አመለካከት ዝቅተኛ ነው ተብሏል።ከእዚህ በተጨማሪ 49 ከመቶ የሚሆኑ ሴቶች ለወሊድ መቆጣጠሪያ ያላቸው ግምት አናሳ መሆኑን በኢትዮጵያ የዮንሴ ዓለም አቀፍ ጥናት የጤና ማዕከል ዶ/ር ጆንግ ኢን ሊ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በአማካይ በየዓመቱ 3 ሚሊዮን ህፃናት እንደሚወለዱ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ ተናግረዋል።
በከተሞች ደረጃ በአንድ ቤተሰብ እስከ ሶስት ልጆች እንደሚኖሩ ያነሱት ሚኒስትር ድኤታው ይህ ቁጥር በክልሎች በእጥፍ ይጨምራል ብለዋል ፣ በሶማሊያ ክልል ደግሞ በአማካይ እስከ 7 ልጆች እንደሚወለዱ በጥናት መረጋገጡን ገልፀዋል።ይህንን ቁጥር በመቀነስ በቤተሰብ እስከ ሶስት ልጆች ለማውረድ እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።የተመጣጠነ ደስተኛ እና ውጤታማ የሆነ የቤተሰብ ፕሮጀክት ሁለተኛውን ክፍል 22.6 ሚሊዮን ኢትዮጲያውያንን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል ተብሏል።
[Bisrat FM]

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቁጥጥር ስር ዋለ!
የፍትህ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሥራ ባልደረቦቹ ለቢቢሲ አረጋገጡ።
ተመስገን ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 18/2014 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ከሥራ ቦታው በሁለት መኪና በመጡ የፀጥታ ኃይሎች ተይዞ መወሰዱን ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ባልደረቦቹ ተናግረዋል።
በቁጥጥር ስር ያዋሉት ኃይሎች መሳሪያ የታጠቁ ይሁኑ እንጂ የሲቪል ልብስ የለበሱ መሆናቸውንም አክለዋል።

በኮንጎ ኪንሻሣ በቅርቡ በኢቦላ ቫይረስ መታመማቸው የተረጋገጠ 5 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ፡፡
ሰዎቹ በኢቦላ መያዛቸው የተረጋገጠው ባለፈው ቅዳሜ እንደነበር አናዶሉ ፅፏል፡፡በሰሜናዊ ምዕራብ ኮንጎ ኪንሻሣ የኢቦላ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ ሰንብቷል፡፡እስካሁን በበሽታው ከተያዙት እና ከሞቱት ጋር ቅርርብ የነበራቸው ከ200 በላይ ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡
የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ለበሽታው ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ የሆነ ከሺህ በላይ ሰዎች የኢቦላ በሽታ መከላከያ መከተባቸው ታውቋል፡፡በኮንጎ ኪንሻሣ ከ40 ዓመታት በላይ በሆነ ጊዜ ኢቦላ ሲከሰት የአሁኑ ለ14ኛ ጊዜ እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡
[Sheger FM]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት ኢኳቶሪያል ጊኒ ርእሰ ከተማ ማላቦ ገብተዋል፡፡
በናይጄሪያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉብኝቱን አጠናቀው በአፍሪካ ሕብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ነው ከልኡካን ቡድናቸው ጋር ማላቦ የገቡት፡፡
በቆይታቸውም በሰብዓዊ እርዳታ፣ ፀረ ሽብር ጉዳዮች ላይ እና ኢ-ሕገመንግሥታዊ በሆነ መንገድ ሥልጣን ለመያዝ የሚደረጉ ጥረቶችን መከላከል ላይ በሚያተኩረው በሕብረቱ ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማላቦ ሲደርሱ በአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ኢቢሲ ዘግቧል፡

በጎንደር ከተማ ሰዎችን በማገት የተጠረጠሩ 36 ግለሰቦች በቁጥጥ ስር መዋላቸውን ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ በሕግ ማስከበር እንቅስቃሴው ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በሰጡት መግለጫ÷ በከተማዋ የእገታ፣ የመሬት ወረራ እና የጥይት ተኩስ መበራከት ለከተማዋ ነዋሪዎች ቅሬታ ፈጥሯል፡፡
የከተማዋን ነዋሪዎች ጥያቄ ለመመለስም የሕግ ማስከበር ሥራ መጀመሩን ገልጸው÷ ከፍረጃ በፀዳ ሁኔታ የሕግ ማስከበር ስራዎች መከናወናቸውን በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡በዚህም መሰረት ሰዎችን በማገት ወንጀል የተጠረጠሩ 36 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡
ከሕግ ማስከበሩ ጋር በተያያዘ 10 የመንግስት ቤቶችን በኃይል ሰብረው የገቡ ግለሰቦች ቤቱን አስረክበው እንዲወጡ መደረጉን÷ በሕገ ወጥ መንገድ የተገነቡ 103 ቤቶች መፍረሳቸውን እንዲሁም 102 በሕገ ወጥ መንገድ ታጥረው የነበሩ የመንግስት ቦታዎችን ማፍረስ መቻሉን አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም በሕገ ወጥ መንገድ የተገነቡ 106 ሸዶችና ኮንቲነሮችን ማስነሳት መቻሉን ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡የሕግ ማስከበር ሥራው ፋኖን ለመያዝ እና ትጥቅ ለማስፈታት ነው እየተባለ የሚይናፈሰው አሉባልታ ከእውነት የራቀ መሆኑን ያወሱት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው÷ ከእውነተኛ ፋኖዎች ጋር በጋራ በሕግ ማስከበር ሥራው ተስማምተን እየሠራን ነው ብለዋል፡፡
Via FBC