YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
ለቤትዎ ለቢሮዎ እንዲሁም ለድርጅትዎ ይተለያየ ውበት ያላቸውን የፍይበር ግላስ የአበባ መትከያ ከፈለጉ እኛ አለን የድርጅትዎን እርማም መትከያው ላይ እናትምሎታለን
👋👋እንዲሁም ይሄን አዋጭ ቢዝነስ
ለመጀመር ካሰቡ ሙሉ ስልጠና እንሰጣለን ይደውሉልን
https://tttttt.me/+xvCuMwxhK19kODg0
☝️☝️☝️Join our group
Phone number:0987414243
0913676664
በአማራ ክልል የትኛውም አካባቢ ሕጋዊ ጥያቄ ያቀረበም ኾነ ፈቃድ ያገኘ ሰልፍ አለመኖሩን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫ የተጀመረውን
ህግ የማስከበር ስራ በአጭር ጊዜ እና በዝቅተኛ ጉዳት
ለማጠናቀቅ መላው የጸጥታ መዋቅሩ ከሰላም ወዳዱ ሕዝብ ጋር
ኾኖ እየሠራ እንደሚገኝ አመልክቷል።

ሕገወጥ ፈቃድ ያላገኘ ሰልፍም ኾነ የጎዳና ላይ ትዕይንት ፈጽሞ
ተቀባይነት የሌለው መኾኑን የገለጸው ቢሮው፤ በዚህ ድርጊት ላይ
በቅስቀሳ እና አመጽ ጥሪ በሚያቀርቡ አካላት ላይ እንዲሁም
በሰልፍ ሰበብ የሕግ ማስከበር ሥራውን ለማደናቀፍ በሚደረጉ
ማንኛውም ድርጊቶች ላይ አስፈላጊውን የሕግ የማስከበር እርምጃ
የሚወስድ መኾኑን አስታውቋል።

የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠው
መግለጫ ቀጥሎ ቀርቧል:-

የአማራ ክልል ጸጥታ ምክር ቤት የክልሉን የሰላምና እና ደኅንነት
ሁኔታ በጥልቀት ከገመገመ በኋላ የአሸባሪው ትህነግ ወረራ
ስጋትን ለመመከት ዝግጅት ማድረግ እና የክልሉን አንድነት
የሚሸረሽሩ ሕገወጥ ተግባራትን ማረም አስፈላጊ መኾኑን መወሰኑ
ይታወሳል።

ሕግ የማስከበር ሥራው ዋና ዓላማ ሊቃጣ የሚችልን የአሸባሪው
ትህነግ ድጋሚ ወረራ ለመቀልበስ፣ ለክልላችን ሕዝቦች ሰላም እና
ደኅንነት ዋስትና ለመስጠት እንዲሁም የሚታየውን ሕገ ወጥነት
መልክ በማስያዝ ሕዝቡ እየጠየቀ ያለውን የልማት እና መልካም
አሥተዳደር ጥያቄ ለመፍታት ዓላማ ያደረገ እንደኾነ የክልላችን
ርእሰ መሥተዳድር ለሕዝባችን መግለጻቸው ይታወሳል።


ካለፉት ቀናት ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ሕግ የማስከበር
ሥራ ተጠርጣሪዎች ያለምንም ግጭት እጃቸውን ለሕግ
እንዲሰጡ የማድረግ እንዲሁም እጃቸውን በሰላም ለሕግ
ለመስጠት ፈቃደኛ ያልኾኑ ግለሰቦች ላይ ጉዳት የመቀነስን ሥራ
በመሥራት በሰላም ወዳዱ ሕዝባችን አጋርነት ሕግ የማስከበር
ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።

ይህ ሕግ የማስከር ሥራ ለሕዝባችን ሰላም እና ደኅንነት
ለክልላችን እና ሀገራችን የስላም ዋስትናን ዓላማ በማድረግ
እየተከናወነ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከዋና ጠላቶችችን ጋር በማበር
ክልላችንን እና ሀገራችንን ለማፍረስ የሚሠሩ አንዳንድ
የማኅበራዊ ሚዲያ ባለቤቶች እና ግለሰቦች በአንዳንድ
የክልላችን አካባቢዎች ሰልፍ መጥራት እና ለሰላም ማስከብር
ሥራው እንቅፋት የኾኑ ቅስቀሳዎችን እያደረጉ ይገኛሉ።
ነገር ግን በክልላችን የትኛውም አካባቢ ሕጋዊ ጥያቄ ያቀረበም
ኾነ ፈቃድ ያገኘ ሰልፍ የለም።

ሕግ የማስከበር ሥራውን በአጭር ጊዜ እና በዝቅተኛ ጉዳት
ለማጠናቀቅ መላው የጸጥታ መዋቅራችን ከሰላም ወዳዱ
ሕዝባችን ጋር ኾኖ እየሠራ በሚገኝበት ወቅት እንዲህ አይነት
ሕገወጥ ፈቃድ ያላገኘ ሰልፍም ኾነ የጎዳና ላይ ትዕይንት ፈጽሞ
ተቀባይነት የሌለው መኾኑን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ እየገለጸ
በዚህ ድርጊት ላይ በቅስቀሳ እና አመጽ ጥሪ በሚያቀርቡ አካላት
ላይ እንዲሁም በሰልፍ ሰበብ የሕግ ማስከበር ሥራውን
ለማደናቀፍ በሚደረጉ ማንኛውም ድርጊቶች ላይ አስፈላጊውን
የሕግ የማስከበር እርምጃ የሚወስድ መኾኑን ያሳውቃል።

የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
ግንቦት 13/ 2014 ዓ.ም
ባሕር ዳር

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ ወረዳ ለኔትዎርክ ጥገና ስራ በአከባቢው ተሰማርተው የነበሩ ሶስት የኢትዮ ቴለኮም ሰራተኞች መገደላቸው ተሰማ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የድርጅቱ ሠራተኞች መገደላቸውን ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ በኢትዮ ቴሌኮም ሆለታ ዲስትሪክት የሚያገለግሉ ባለሙያ እንደገለጹት ከሆነ ሶስቱ የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች ላይ ግድያ የተፈፀመው ሐሙስ ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ነው፡፡

ሁለት የቴክኒክ ሰራተኞች እና አሽከርካሪያቸው ላይ ግድያው የተፈፀመው ከሆለታ ከተማ 76 ኪ.ሜ. ገደማ ርቀት ላይ እንደምገኝ በተገለጸው ሜታ ወልቂጤ ወረዳ እኩለ ቀን አከባቢ መሆኑን የተቋሙ ባልደረባ አረጋግጠዋል። “ሰራተኞቹ ለስራ እንደወጡ ሜታ ወልቂጤ በምትባል ወረዳ ከምናሬ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ መንገድ ላይ ነው በጥይት ተመተው ተገድለው የተገኙት...” መረጃ ሰጪው አክለውም የሟቾች ቀብር ትናንት እና ዛሬ በሆለታ ከተማ እና በነቀምት ከተማ መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡

ግድያው በተፈጸመበት አከባቢ መንግስትን የሚፋለሙ ታጣቂዎች እንደሚንቀሳቀሱ አስቀድሞ ቢታወቅም ሰራተኞቹ ለአስቸኳይ የጥገና ስራ ወደ ስፍራው ተልከው እንደነበርም ተገልጿል፡፡የኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሳይ ውብሸት ግን የግድያውን መፈጸም አረጋግጠው ለዝርዝሩ በፖሊስ ምርመራ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞን እስር እየተከታተለ መሆኑን ኬሚሽነር ዳንዔል በቀለ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ጸጥታ ኃይሎች ሰሞኑን እየፈጸሟቸው ያሉ እስሮች እንዳሳሰቡት ዳንዔል ጨምረው ገልጸዋል።የአማራ ክልል ጸጥታ ኃይሎች በባሕርዳር ከተማ "አሻራ" ለተባለ መገናኛ ብዙኀን የሚሰሩ አምስት ጋዜጠኞችን ከትናንት ወዲያ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ እና ቢሮውንም እንደዘጉ ዘግቧል።ሁለት የፋኖ አባላት በባሕርዳር እና ዘጠኝ የአብን አባላት በሁለት ከተሞች መታሰራቸውንም ዘገባው ምንጮቹ ጠቅሶ ጽፏል።የአብን የፓርላማ ተወካዮችም የፓርቲው አባላት እስራት ባስቸኳይ እንዲያቆም ጠይቀዋል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
👉 ለጤናው ቅድሚያ እንሰጣለን


መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን
በተሰጠንና ባገኘነው ልምድና ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሔወችን እንሰጣለን።፦

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም

👉 የኪንታሮት መድኀኒት በሚቀባ ታማሚው
ወደቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላሳይነካ
ሳያቆስል ስራ ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛ እንዳይተካ አድርጎ የፈውሳል።
👉 የእሪህ መድአኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉 ገብያ ለገረገረው ለገብያ
👉 ለመፍትሔ ስራይ
👉 ለአይነ ጥላ (ለገርጋሪ)
👉 ለስንፈተ ወሲቢ ለሚቸኩልበት
👉 የአስም (የሳይነስ)
👉 ለማይስማሙ (ለመስተፋቅር)
👉 ገንዘብ ለሚበተንበት
👉 ስራ አልሳካለት ላለ
👉 ለቡዳ
👉 ለሚጥል በሽታ
👉 ለማህጸን እንፌክሽን
👉 ህይወቱ ለሚመሰቃቀልበት
👉 ለአዕምሮ ጭንቀት
👉 ሌሊት ለሚሸና
👉 ለነገረ በትን
👉 ለሆድ ሀህመም
👉 ለስኳር መቀነሻ
👉 ለነርብ
👉 እራሱን ለሚያመው

እነዚህንና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን

መዳኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል

በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈጽማሉ

አድራሻ
ባህርዳር ቀበሌ 11
ዲያስፖራ በኮብሉ

ለበለጠ መረጃ
☎️ 0917040506
📞 0912718883

ይደውሉ👍

መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ
መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
የሚፈልጉትን ለማግኔት ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ
🩺
https://tttttt.me/meritibe
https://tttttt.me/meritibe👇
👇
በማህበራዊና በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥትን በመተቸት የምትታወቀው መስከረም አበራ ቅዳሜ እለት፣ ግንቦት 13 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር መዋሏን ባለቤቷ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

በአዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆነችው መስከረም በቁጥጥር ስር የዋለችው በአዲስ አበባ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲሆን ያለችበትንም ስፍራ እንደማያውቁ ባለቤቷ ተናግረዋል።ይህም በሳምንቱ የታሰሩትን የጋዜጠኞች እና የሚዲያ አካላት ቁጥር ሰባት ያደረሰው ሲሆን ሁኔታውም የተችዎን ድምጽ በማፈኑ ረገድ አዲስ እርምጃ ሊኖር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

በያዝነው ሳምንት ሐሙስ ግንቦት 11፣ 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል ተቀማጭነቱን ያደረገውና የቅርብ ዘገባቸው በፋኖ ላይ ያተኮረው አሻራ ሚዲያ አምስት ጋዜጠኞቹ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል።ጋዜጠኞቹ የአማራ ልዩ ኃይል፣ የአማራ ፖሊስና የአድማ በታኝ የደንብ ልብስ በለበሱ የጸጥታ አካላት እንደተወሰዱ "ሽንት ቤት ውስጥ ተደብቄ ነበር" ያለ የስራ ባልደረባቸው ለሮይተርስ ተናግሯል።ግለሰቡ በባህርዳር ከተማ የሚገኘው የአሻራ ጽህፈት ቤት መዘጋቱንም ተናግሯል።

በተጨማሪም በሃገሪቱ የተካሄደውን ጦርነት በመቃወምና የሰላምና ድርድር መንገዶች የተሻሉ አማራጮች እንደሆኑ በተደጋጋሚ አፅንኦት በመስጠት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬም መታሰሩ ተዘግቧል።ቢቢሲ የአዲስ አበባን ሆነ የፌደራል ፖሊስን ለማግኘት ቢሞክርም ባለመሳካቱ ምላሻቸውን ለማካተት አልተቻለም።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
መርካቶ ምን አለሽ ተራ የእሳት አደጋ ተከሰተ!

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ በተለምዶ ምን አለሽ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከባድ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከል በርካታ የአካባቢው ወጣቶች እና የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባለሙያዎች ርብርብ እያደረጉ ነው ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
መርካቶ ምን አለሽ ተራ የእሳት አደጋ ተከሰተ! በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ በተለምዶ ምን አለሽ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከባድ የእሳት አደጋ ተከስቷል። አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከል በርካታ የአካባቢው ወጣቶች እና የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባለሙያዎች ርብርብ እያደረጉ ነው ተብሏል። @YeneTube @FikerAssefa
#update

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ መሃል መርካቶ ምን አለሽ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በተከሰተው የእሳት አደጋ የንብረት ውድመት ያጋጠመ ሲሆን የእሳትና ድንገተኛ መከላከል ሰራተኞች፣ የአካባቢው በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና የፀጥታ ሃይሎች ባደረጉት ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል።

[A.A Mayor Office]
@YeneTube @FikerAssefa
ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሲሚንቶ ቸርቻሪዎችን ተክተው ሊሠሩ ነው!

የሲሚንቶ ቸርቻሪ ነጋዴዎችን ሙሉ በሙሉ ከስርዓቱ እንዲወጡ በማድረግ በየክልሉ ያሉ የሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተክተው እንዲሠሩ ለማስቻል እየተሠራ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ በአሁን ወቅት በገበያው ላይ በቂ የሲሚንቶ ምርት ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ በገበያ ላይ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በአማካይ እስከ አንድ ሺሕ አንድ መቶ ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሆነ እና መንግሥት ሲያደርግ የነበረው የቁጥጥር ሥራ መነሳቱም እየታየ ላለው ችግር አባባሽ ሆኖ እንደተገኘ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ቁምነገር እሸቱ አስታውቀዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአራት ዓመት በፊት ያቋረጠውን የመሬት ሊዝ ጨረታ እንደገና ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል።

አስተዳደሩ ለሊዝ ጨረታው በመቶዎች የሚቆጠሩ መሬቶችን እያዘጋጀ እንደሆነ የከተማዋ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለሪፖርተር ተናግሯል። የሊዝ ጨረታ የሚወጣባቸው መሬቶች ለመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ ለንግድ ሥራ እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ሲሆኑ፣ አስተዳደሩም የጨረታ ሂደቱን የሚያስፈጽምለትን ቡድን አዋቅሯል። የሊዝ ጨረታው በ2010 ዓ፣ም የጨረታ ሂደታቸው ተጀምሮ የተቋረጠባቸውን መሬቶች ጭምር ያካትታል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በጉራጌ ዞን የሚገኘው የእነሞርና ኤነር ወረዳ ስያሜ " እኖር " ተብሎ እንዲቀየር ተወሰነ!

የእነሞርና ኤነር ወረዳ ስያሜ " እኖር " ተብሎ ስያሜ ለመቀየር የተዘጋጀው የውይይት ሰነድ ለወረዳው ምክር ቤት አባላት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ እንዲቀየር ውሳኔ መተላለፉ ተነግሯል፡፡ነባሩ የእነሞርና ኤነር ወረዳ በተሰጡ የህዝቡ የአደረጃጀት ጥያቄዎች ምላሽ ምክንያት በስሩ ሲተዳደሩ ከነበሩ አካባቢዎች ራሳቸውን ችለው በወረዳና ከተማ አስተዳደር የተደራጁ በመኖራቸው ምክንያት በቀረው ወረዳ ስር ያሉ ነዋሪዎች ሊገልጽ የሚችል ስያሜ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል።

በእዚህ ሳቢያ በተሰጠው አዲስ ስም ቅያሪ ወረዳው "እኖር " ተብሎ እንዲጠራ ተወስኗል ሲሉ የእኖር ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ያዕቆብ ግርማ ሸዋ በተለይ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።የወረዳው አመሰራረትና ስያሜ በተመለከተ ከወረዳውና ከጉንችሬ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ወረዳውን ከዚህ ቀደም ሲያገለግሉ ከነበሩ አባቶች ጋር ውይይት መደረጉን ያነሱት ሃላፊው ወረዳው ከ1967 ዓ.ም በፊት << እኖር>> ተብሎ ሲጠራ እንደነበር ከተደረጉ በውይይቶች የተገኙ መረጃዎች ማመላከታቸውን አስታውቀዋል፡፡

በሂደትም በ1967 ዓ.ም በወቅቱ የነበረው አመራር ከህዝቡ ጋር ውይይት ሳይደረግ እኖር የሚለውን ስያሜ በመቀየር "እነሞርና ኤነር " በሚል እንዲጠራ ማድረጉ ከዳሰሳዊ ጥናቱ ሊገኝ መቻሉን አስተዳዳሪው አቶ ያዕቆብ ጨምረው ተናግረዋል።በአሁኑ ሰዓትም ወረዳው ከ1967 ዓ.ም በፊት ሲጠራበት ወደነበረው ስያሜ መመለስ እንደቻለ ታውቋል ።ከውሳኔው በኋላ መንግስታዊ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ወረዳው የሚመጡ አካላት "እነሞርና ኤነር " ሳይሆን "እኖር" በሚለው በአዲሱ ስያሜ ሊጠቀሙ ይገባል ተብሏል።

[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንብር የሆኑት የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ሩሲያና ዩክሬንን ሊጎበኙ ነው!

ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል የአፍሪካ ህብተረትን በመወከል በቅርቡ ወደ ሁለቱም ሀገራት እንደሚያቀኑ መግለጻቸውን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።

የጉዞዋቸው ዋነኛ አላማም አፍሪካ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት ቆሞ በሁለቱም ሀገራ መካካል በንግር ላይ የተመሰረተ ሰላ አንዲሰፍን ያላትን ቁርጠኝነት ለማሳወቅ ነው ብለዋል።

[CGTN/Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል 4 ሺህ 552 ግለሠቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ!

በአማራ ክልል በጥምር ኃይሉ እየተከናወነ በሚገኘው የህግ ማስከበር ተግባር 4 ሺህ 552 ግለሠቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ሠላም እና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።የክልሉ የሠላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሠው በወቅታዊ የክልሉ ፀጥታ ሁኔታ ላይ መግለጫ ሠጥተዋል።በመግለጫውም፣ ክልሉ ከግንቦት ወር መግቢያ ጀምሮ ስርአት አልበኝነትን ማስወገድ እና የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ በሚል የጀመረው ዘመቻ የክልሉን አንድነት በማጠናከር የውጭ ጠላትን ማስወገድን ያለመ ስለመሆኑ አስገንዝበዋል።

[AMC]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮለኔል ገመቹ አያና የታሰሩበትን ሁኔታ ቀርቦ እንዲያስረዳ ቢታዘዝም ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ቀረ!

የኦሮሚያ ፖሊስ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር የሆኑት ኮለኔል ገመቹ አያና የታሰሩበትን ሁኔታ ቀርቦ እንዲያስረዳ በጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት የታዘዘ ቢሆንም ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ቀረ።የኦሮሚያ ፖሊስ በሰበር ሰሚ ችሎቱ ቀርቦ የኮለኔል ገመቹን የእስራት ሁኔታ በጽሁፍና በአካል እንዲያብራራ ባሳለፍነው ሳምንት አርብ በነበረ የችሎት ቀጠሮ መታዘዙ ይታወሳል።

በትዕዛዙ መሰረት ዛሬ ረፋድ ላይ በነበረ በችሎቱ ቀጠሮ ጥሪ ቢደረግም ከኦሮሚያ ፖሊስ ማንም አካል ሳይቀርብ ቀርቷል።የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር የሆኑት ኮለኔል ገመቹ አያና በግንቦት 09 ቀን 2013 በስር ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ነጻ ከተባሉ በኋላ፤ በነጋታው ግንቦት 10 ቀን ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሲወጡ በኦሮሚያ ፖሊስ ተይዘው በገላን ፖሊስ ጣቢያ እና በወታደሪዊ ካንፕ እንዲሁም በአዋሽ መልካሳ በአንድ ጀነራል ዶሮ ዕርባታ ውስጥ ለ6 ወራት ታስረው እንደነበር እና ከስድስት ወር በኋላ ከህዳር 16 ጀምሮ ደግሞ በፌደራል ፖሊስ በእስራት ላይ መሆናቸውን ከዚህ በፊት ለፍርድ ቤት አስረድተው ነበር።

ኮለኔል ገመቹ አያና ነጻ በተባሉበት የሽብር ክስ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዓቃቢህግ ይግባኝ ጠይቆ የነበረ ሲሆን፤ ይግባኝ ሰሚ ችሎቱም ኮነሬል ገመቹ ታስረው በነበሩበት የእስራት ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙና አለመፈጸሙ ማረጋገጪያ ባልቀረበበት ሁኔታ ክርክር ማስቀጠል አይቻልም ሲል መዝገቡን መዝጋቱ ይታወሳል።

ይሁንና ዓቃቢህግ በድጋሚ ለሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ በጠየቀበት በዚህ መዝገብ፤ የኮነሬል ገመቹ አያና የእስር ሁኔታ ላይ ባሳለፈው አርብ ዕለት በነበረ ቀጠሮ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በኮነሬል ገመቹ አያና ላይ ምንም አይነት የተከፈተ የወንጀል ምርመራ መዝገብ እንደሌለው ምላሽ ሰጥቷል።

ሰበር ሰሚ ችሎቱም በኮነሬል ገመቹ የእስር ሁኔታ ላይ የኦሮሚያ ፖሊስ ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም በዛሬው ቀጠሮ ሳይቀርብ መቅረቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።ጉዳዩን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎቱ በይደር ቀጠሮ መያዙም ታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መስከረም አበራ የአማራ ክልልን ከፌደራል መንግስት ለመነጠል ገንዘብ ተከፍሏት እየሰራች ነው ሲል ፖሊስ ገለፀ!

መስከረም አበራ ሚድያዎችን በመጠቀም ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በማድረግ፣ የአማራ ክልልን ከፌደራል መንግስት ለመነጠል ገንዘብ ተከፍሏት በመስራት እንዲሁም በፋኖ እና በፌዴራል መንግስት መካከል እምነት እንዳይኖር አድርጋለች ሲል መርማሪ ፖሊስ ለችሎት አስረዳ።

መስከረም አበራ ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም. በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ተኛ የጊዜ ቀጠሮ በዋለው የወንጀል ችሎት ከጠበቃዎቿ ጋር ቀርባለች።መርማሪ ፖሊስ የ14 ቀን ቀጠሮ የጠየቀ ሲሆን የመስከረም አበራ ጠበቃዎች ፖሊስ ተፈጸመ ያለው ወንጀል በመገናኛ ብዙሃን መደበኛው የጊዜ ቀጠሮ ሳይሰጥ ለዐቃቤ ሕግ ተመርቶ ክስ የሚመሰረትበት እንጂ የምርመራ ጊዜ የሚጠየቅበት ስርዓት የለም በማለት ተከራክረዋል።

በተጨማሪም ለተጨማሪ ጊዜ ያቀረባቸው ተባባሪ አባሪዎችን ለመያዝ ፣ የኤሌክትሮኒስ ማስረጃቸውን ምርመራ ለማከናወን እና ምስክሮችን ለማሰባሰብ የሚሉት ምክንያቶች ተፈፀመ ስለተባለው ወንጀል ማስረጃ እንደሌለ ያሳያል ብለዋል።መስከረም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸውን ተጠቅመው ስርዓቱን በመሞገታቸው ለማሸማቀቅ የቀረበ እስር እንጂ ለእስር የሚዳርግ ተግባር አልፈፀሙም ያሉት ጠበቆቿ የ7 ወር አራስ በመሆናቸው የዋስትና መብታቸው ይከበር ብለዋል።ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ለነገ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠዋት 3፡30 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው ዕለት 1ሺህ 68 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ስራ 1ሺህ 68 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ የተቻለ ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥ አንድ ሕጻንና 1 ሺህ 67 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡እስካሁን በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ከ 26 ሺህ 868 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
#ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

በአቴና ጎዳናዎች ላይ በባዶ እግሩ እየተጓዘ ከሰዎች ጋር መጨቃጨቅ የሚወድ አንድ ሰው አለ፤ “ምነው ቤት የለህምን? ስለምንስ እኛን ትጨቃጨቃለህ?” ቢሉት “ቤትማ አለኝ ከአስቀያሚዋ እና ነዝናዛዋ ሚስቴ ሽሽት ወደዚህ መጣሁ” ነበር መልሱ፤ ይህ ሰው ታላቁ ፈላስፋ ሶቅራጥስ ነው። የአቴና ሰዎች የሶቅራጥስን ስድብ እና ጭቅጭቅ አልችል ቢሉ፣ መርዝ አጠጥተው ገደሉት።

የእኛው ሀገር የባዶ እግር ፈላስፋ የሆነው ዘርዓ ያዕቆብንም በዙሪያው ያሉ ሰዎች ጠልተው አሳደዱት። እንደ ቀበሮም ዋሻ ምሶ ለብቻው ኖረ። ዋሻውንም በእሾህ እና በድንጋይ አጠረ፤ ድንገት እንኳ ሰው ቢመጣበት ማምለጫ እንዲሆነው በአጥሩ ላይ ቀዳዳን አበጀ።

ሶቅራጥስም፣ ዘርዓ ያዕቆብም የዘመናቸው ወፈፌዎች ነበሩ። እንኳን ሊጠየቁ፣ ሊታሰቡ እንኳ የከበዱ ጥያቄዎችን አንስተው መርምረዋል።

#ሶቅራጥስን_ያስገደለ_ዘርዓ_ያዕቆብንም_ከሀገር_ያሰደደ ፍልስፍና ምንድን ነው? እውቀት ምንድን ነው? ... እውነት ምንድነው? ... ፍትህ ምንድነው? የሕይወት ትርጉምስ ምንድን ነው? … እኛ ማን ነን? ... ከየት መጣን? ... ወዴትስ እንሄዳለን?... ስለምንስ እንኖራለን?...

#ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ መጽሐፍ ጥያቄዎቻችን እየመለሰ መንገዱ በዚህ ነው ይለናልና ማሿችንን እንዳበራን ጥበብን ፍለጋ በጨለማ መሃል እንጓዝ...

#ፍልስፍና_ከዘርዓ_ያዕቆብ_እስከ_ሶቅራጥስ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡
*
ቤተሰብ ይሁኑ
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
ለቤትዎ ለቢሮዎ እንዲሁም ለድርጅትዎ ይተለያየ ውበት ያላቸውን የፍይበር ግላስ የአበባ መትከያ ከፈለጉ እኛ አለን የድርጅትዎን እርማም መትከያው ላይ እናትምሎታለን
👋👋እንዲሁም ይሄን አዋጭ ቢዝነስ
ለመጀመር ካሰቡ ሙሉ ስልጠና እንሰጣለን ይደውሉልን
https://tttttt.me/+xvCuMwxhK19kODg0
☝️☝️☝️Join our group
Phone number:0987414243
0913676664
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ማኅበር መንግሥት ለመገናኛ ብዙኀን ችግሮች መፍትሄ እንዲሰጥ ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ደብዳቤ ማስገባቱን ዋዜማ ሬዲዮ ተረድቻለሁ ብላለች።

ማኅበሩ የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ከቤታቸውና ከሥራ ገበታቸው በጸጥታ ኃይሎች መታፈናቸው እንዳሳሰበው ገልጦ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ከፍተኛ የሕግ ጥሰት ሰምተው እንዳልሰሙ መሆናቸው አሳዝኖኛል ብሏል።መንግሥት ጋዜጠኞችን በሕግ አግባብ ብቻ እንዲጠይቅ እና ጋዜጠኞችን ያፈኑ አካላትም ለሕግ እንዲቀርቡ ማኅበሩ ጠይቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት ለ200 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስኳር ግዥ ላቀረበው ዓለማቀፍ ጥሪ አራት ስኳር አቅራቢ የውጭ ኩባንያዎች እንዳለፉ ካፒታል አስነብቧል።

ሌሎች ሁለቱ ኩባንያዎች ግን የፋይናንስ እና ቴክኒክ ሰነድ ባለማሟላታቸው ከስኳር አቅራቢዎች ዝርዝር ተሰርዘዋል። ለጨረታው ያቀረቡት ሰነድ ተገምግሞ ያለፉት፣ የሲንጋፖር፣ የብሪታንያ፣ የፈረንሳይ እና የአሜሪካ ኩባንያዎች ናቸው። በዘርፉ አዲስ እንደሆነ የተነገረለት የአሜሪካው ኩባንያ ከሁሉም ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ሲሆን፣ ስኳሩን ከብራዚል እንደሚገዛ ገልጧል።

@YeneTube @FikerAssefa