YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሩሲያው ፕሬዝዳንት የስዊድን እና የፊንላንድ ኔቶን መቀላቀል "ስጋታችን አይደለም" አሉ!

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፒቲን ስዊድን እና ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ)ን ቢቀላቀሉም ለሀገራቸው ስጋት እንደማይሆን አስታወቁ፡፡ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት ከሰሞኑ ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን ለመቀላቀል መወሰናቸውን ካሳወቁ በኋላ ነው፡፡

ከሰሞኑ የፊንላንድ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሀገራቸው ኔቶን መቀላቀል እንዳለባት ድጋፍ መስጠታቸውን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ሃሳቦች እየተሰነዘሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡እስካሁን በፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን የመቀላቀል ሂደት ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የሩሲያ እና የቱርክ ፕሬዝዳንቶች ናቸው፡፡

ቭላድሚር ፑቲን ሁለቱ ሀገራት ድርጅቱን መቀላቀላቸው ለሩሲያ ስጋት ባይሆንም ምላሽ ሊያሰጥ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡የፖለቲካ ሰዎች የስዊድን እና ፊንላንድ ኔቶን መቀላቀል አሁን በዩክሬን ያለውን ጦርነት ወደ ሌሎች ሀገራት ሊያዛምተው እንደሚችል እየተነበዩ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ ግን የሩሲያው ፕሬዝዳንት የሀገራቱን ወደ ኔቶ አባልነት የመቅረብ ሂደት በቀጥታ አልተቃወሙም፡፡

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
1
በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ ዓረቢያ የመመለስ ስራ 1 ሺህ 40 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመለሾች ውስጥም 303 ሴቶች ሲሆኑ÷ 90 የሚሆኑት ደግሞ ህጻናትና መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጁላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 23 ሺህ 640 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👉 ለጤናው ቅድሚያ እንሰጣለን


መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን
በተሰጠንና ባገኘነው ልምድና ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሔወችን እንሰጣለን።፦

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም

👉 የኪንታሮት መድኀኒት በሚቀባ ታማሚው
ወደቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላሳይነካ
ሳያቆስል ስራ ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛ እንዳይተካ አድርጎ የፈውሳል።
👉 የእሪህ መድአኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉 ገብያ ለገረገረው ለገብያ
👉 ለመፍትሔ ስራይ
👉 ለአይነ ጥላ (ለገርጋሪ)
👉 ለስንፈተ ወሲቢ ለሚቸኩልበት
👉 የአስም (የሳይነስ)
👉 ለማይስማሙ (ለመስተፋቅር)
👉 ገንዘብ ለሚበተንበት
👉 ስራ አልሳካለት ላለ
👉 ለቡዳ
👉 ለሚጥል በሽታ
👉 ለማህጸን እንፌክሽን
👉 ህይወቱ ለሚመሰቃቀልበት
👉 ለአዕምሮ ጭንቀት
👉 ሌሊት ለሚሸና
👉 ለነገረ በትን
👉 ለሆድ ሀህመም
👉 ለስኳር መቀነሻ
👉 ለነርብ
👉 እራሱን ለሚያመው

እነዚህንና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን

መዳኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል

በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈጽማሉ

አድራሻ
ባህርዳር ቀበሌ 11
ዲያስፖራ በኮብሉ

ለበለጠ መረጃ
☎️ 0917040506
📞 0912718883

ይደውሉ👍

መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ
መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
የሚፈልጉትን ለማግኔት ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ
🩺
https://tttttt.me/meritibe
https://tttttt.me/meritibe👇
👇
ለቤትዎ ለቢሮዎ እንዲሁም ለድርጅትዎ ይተለያየ ውበት ያላቸውን የፍይበር ግላስ የአበባ መትከያ ከፈለጉ እኛ አለን የድርጅትዎን እርማም መትከያው ላይ እናትምሎታለን
👋👋እንዲሁም ይሄን አዋጭ ቢዝነስ
ለመጀመር ካሰቡ ሙሉ ስልጠና እንሰጣለን ይደውሉልን
https://tttttt.me/+xvCuMwxhK19kODg0
☝️☝️☝️Join our group
Phone number:0987414243
0913676664
የአሜሪካ ወታደሮች በሶማሊያ እንዲሰማሩ ጆ ባይደን ወሰኑ!

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሳቸው በፊት በነበሩት ዶናልድ ትራምፕ የተወሰነዉን ውሳኔ በመቀልበስ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ እንዲሰማሩ ፈቅደዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ ሊመለሱ ይችላሉ ተብሏል።

ፕሬዚዳንቱ በአልሸባብ የታጣቂ ቡድን መሪዎች ላይ ዒላማ ለማድረግ ከፔንታጎን የቀረበላቸዉን ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸዉን በፊርማቸውን አኑረዋል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ የሆነችዉ አድሪያን ዋትሰን እንደተናገሩት "እንደገና ለማስጀመር የወሰነው የኃይላችንን ደህንነት እና ውጤታማነት ከፍ ለማድረግ ብሎም ለአጋሮቻችን ቀልጣፋ ድጋፍ ለመስጠት ነው" ብለዋል።

አክለዉም "በአልሸባብ ላይ የበለጠ ውጤታማ ትግል" ለማድረግ ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡አሜሪካ ይህንን ዉሳኔ ያሳለፈችዉ የሶማሊያ የፓርላማ አባላት እሁድ እለት አዲሱን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድን መምረጣቸዉን ተከትሎ ነዉ፡፡

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት በሕወሃት ኩባንያዎች በኢፈርት፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኡንጂነሪንግና ትራንስ ኢትዮጵያ ላይ የመሠረተው ክስ ዛሬ በችሎት ለተከሳሾቹ እንደተነበበ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። ክሱ ኩባንያዎቹ ሕወሃት ፌደራል መንግሥቱን ከሥልጣን አስወግዳለሁ ብሎ የተነሳለትን ዓላማ ለማስፈጸም በከባድ ተሽከርካሪዎቻቸው ለትግራይ ወታደራዊ ዕዝ የሰው ኃይል፣ ነዳጅ፣ ጦር መሳሪያ እና ስንቅ እንዳጓጓዙ ይገልጣል። ዓቃቤ ሕግ የኩባንያዎቹን የተናጥል ወንጀሎች ጭምር ዘርዝሮ አቅርቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በባቲ ወረዳ ታጣቂዎች 3 ሰዎችን ገደሉ!

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ባቲ ወረዳና በአፋር ክልል አዳአር ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች ከእንስሳት ሰርቆት፣ ከሳር ግጦሽና አልፎ አልፎ ከሚፈጠር ግድያ ጋር በተያያዘ በአዋሳኝ አካባቢዎች ረዘም ያለ የሰላም ችግር እንደነበር የሁለቱም ወረዳ አስተዳዳሪዎች ለዶይቼ ቬለ አመልክተዋል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት ተከታታይ ውይይቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን የነገሩን በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀማል ሀሰን የዚህ አካል የሆነ ውይይት በባቲ ወረዳ ልዩ ሰሟ “ጨኮርቲ” ተካሄዶ ውይይቱ ካበቃ በኋላ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የባቲ ወረዳ የሰላምና ፀጥታ ኃላፊ ተገድሏል፣ የወረዳው ሚሊሺያ ጽ/ቤት ኃላፊም ቆስሏል ብለዋል፡፡

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የባቲ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሰኢድም ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡በአፋር ክልል የአዳአር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ኑር በበኩላቸው ታጣቂዎች በሁለቱ ወረዳ ተወያዮች ላይ በፈፀሙት ጥቃት በአፋር በኩል ሁለት ሰዎች መሞታቸውን 4 መቁሰካቸውን ተናግረዋል፡፡

የድርጊቱ ፈፃማዎች ማንነት አስካሁን ባታወቅም የአፋርንና የኦሮሞን ህዝቦች አንድነትና መተሳሰብ የማይፈልጉ ኃሎች መሆናቸውን በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊው አቶ ጀማል ሐሰን አመልክተዋል፡፡

አጥፊዎችን ተከታትሎ ለህግ የማቅረብ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የባቲ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ መሐመድ ሰኢድ አረጋግጠዋል፡፡በአፋርና አማራ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች ከሳር ግጦሽና ከእንስሳት ሰርቆት ጋር በተያያዘ አልፎ አልፎ ግጭቶች ሲፈጠሩ እንደነበር ታወሳል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የኦዴሳ ጦርነት

ፕሬዝዳንት ፑቲን ከወጣትነት ዕድሜያቸው ጀምሮ የሶቪየት መፈራረስና የሩሲያ ልዕልና ማነስ ሲያንገበግባቸው ማደጋቸውን የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ፡፡ በተለይ የዩክሬይን አገር መሆን ውስጥ ውስጡን ይበላቸዋል፡፡ የፑቲንን ስነልቦና እናውቃለን የሚሉ በርካቶች የአሁኑ ጦርነት የሩሲያን ክብር ለመመለስ የሚደረግ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን ይህን ለማሳካት ዋነኛዋ ቁልፍ የጥቁር ባህር ፈርጥ የሆነችውን ኦዴሳን መቆጣጠር ግዴታ ነው፡፡ ዩክሬኖቹ ኦዴሳን አሳልፈን አንሰጥም ብለዋል፡፡ በፑቲን ህልምና በዩክሬይኖች መካከል ስለሚደረገው የኦዴሳ ጦርነት ይህን አስደናቂ ቪዲዮ ይከታተሉ!!!

https://youtu.be/sW0rM_nr8Uo
👉 ለጤናው ቅድሚያ እንሰጣለን


መሪጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን
በተሰጠንና ባገኘነው ልምድና ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሔወችን እንሰጣለን።፦

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም

👉 የኪንታሮት መድኀኒት በሚቀባ ታማሚው
ወደቤቱ ወስዶ በመቀባት ሌላ ገላሳይነካ
ሳያቆስል ስራ ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛ እንዳይተካ አድርጎ የፈውሳል።
👉 የእሪህ መድአኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉 ገብያ ለገረገረው ለገብያ
👉 ለመፍትሔ ስራይ
👉 ለአይነ ጥላ (ለገርጋሪ)
👉 ለስንፈተ ወሲቢ ለሚቸኩልበት
👉 የአስም (የሳይነስ)
👉 ለማይስማሙ (ለመስተፋቅር)
👉 ገንዘብ ለሚበተንበት
👉 ስራ አልሳካለት ላለ
👉 ለቡዳ
👉 ለሚጥል በሽታ
👉 ለማህጸን እንፌክሽን
👉 ህይወቱ ለሚመሰቃቀልበት
👉 ለአዕምሮ ጭንቀት
👉 ሌሊት ለሚሸና
👉 ለነገረ በትን
👉 ለሆድ ሀህመም
👉 ለስኳር መቀነሻ
👉 ለነርብ
👉 እራሱን ለሚያመው

እነዚህንና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን

መዳኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል

በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈጽማሉ

አድራሻ
ባህርዳር ቀበሌ 11
ዲያስፖራ በኮብሉ

ለበለጠ መረጃ
☎️ 0917040506
📞 0912718883

ይደውሉ👍

መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ
መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
የሚፈልጉትን ለማግኔት ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ
🩺
https://tttttt.me/meritibe
https://tttttt.me/meritibe👇
👇
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
ሕወሃት የትግራይ ወጣቶችን በግዳጅ ለውጊያ እንደሚመለምሉ ከሕወሃት ምርኮኞች፣ ከነዋሪዎችና ከረድዔት ድርጅቶች ሰምቻለሁ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

በተለይ በመቀሌ፣ ሽሬ፣ ውቅሮ፣ አዲግራት እና አድዋ ከተሞች በርካታ አስገዳጅ ምልመላ እንደሚካሄድ አንዳንድ ነዋሪዎች መረጃ እንዳላቸው ተናግረዋል። ባለሥልጣናቱ ለተዋጊነት የሚፈልጓቸውን ሰዎች ቤተሰቦች በማሰርና የገንዘብ መቀጮ በመጣል እንደሚያስገድዱና አንዳንዶች ለመዋጋት ፍቃደኛ እንዳልሆኑ እማኞች ተናግረዋል። የሕወሃት ቃል አቀባይ ክንደያ ገ/ሕይወት ውንጀላውን አስተባብለዋል። የመንግሥት ቃል አቀባይ ለገሠ ተሉ ግን ስለ ግዳጅ ምልመላ በርካታ ሪፖርቶች ደርሰውናል ብለዋል።

Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
ዘ ኢኮኖሚስት የቶም ጋርድነር የሥራ ፈቃድን ለመሰረዝ የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበው ምክንያት አግባብ አይደለም አለ!

የዘ ኢኮኖሚስት ዘጋቢው ቶም ጋርድነር የስራ ፈቃድ ለመሰረዝ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ያቀረበው ምክንያት ተቀባይነት የለውም ሲል ድርጅቱ ገለፀ።በተጨማሪም የቶም ጋርድነር የስራ ፈቃድ መሰረዝ በኢትዮጵያ ያለውን የሚድያ ነፃነት ደረጃ የሚያመላክት ነው ሲልም ዘ ኢኮኒሚስት ግሩፕ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ግንቦት 5 ቀን 2014 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የዘ ኢኮኖሚስት ዘጋቢነት የሚሰራው ቶም ጋርድነር በሀገሪቱ የነበረውን የሥራ ፈቃድ መሰረዙን አስታውቆ ነበር።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለጋዜጠኛው በጻፈው ደብዳቤ “ጋዜጠኛው ከሙያ ሥነ መግባር ውጭ በተደጋጋሚ ሲሰራ በመገኘቱ ተደጋጋሚ የቃል እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት እንደነበርና ከጋዜጠኛው ጋር ውይይት በማድረግ ከስህተቱ እንዲታቀብ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል ብሏል።

ዘ ኢኮኖሚስት ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኛ ቶም ጋርድነር ላይ የሰነዘረው ቅሬታ ተገቢ አይደለም ብሏል። ድርጅቱ “ቶም ጋርድነር በኢትዮጵያ ባለው ቆይታ የሰሜኑን ጦርነት ጨምሮ የሰራቸው ዘገባዎች ገለልተኛ እና ሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሰ ነው” በማለት መከላከያ አቅርቧል።

በተጨማሪም ዘ ኢኮኖሚስት የኢትዮጵያ መንግስት ሀሳብን የመግለፅ ነፃነትን በተመለከተ የሚያንፀባርቃቸውን ሀሳቦች በተግባር እንዲያሳይ ሲል በአፅንኦት ጠይቋል።የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣንን ውሳኔ ተከትሎ አዲስ ዘይቤ ቶም ጋርድነር ያለውን ምላሽ ጠይቆ “የባለስልጣኑን ውሳኔ በተመለከተ የምሰጠው አስተያየት የለም” ብሏል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦዴሳ ጦርነት

ፕሬዝዳንት ፑቲን ከወጣትነት ዕድሜያቸው ጀምሮ የሶቪየት መፈራረስና የሩሲያ ልዕልና ማነስ ሲያንገበግባቸው ማደጋቸውን የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ፡፡ በተለይ የዩክሬይን አገር መሆን ውስጥ ውስጡን ይበላቸዋል፡፡ የፑቲንን ስነልቦና እናውቃለን የሚሉ በርካቶች የአሁኑ ጦርነት የሩሲያን ክብር ለመመለስ የሚደረግ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን ይህን ለማሳካት ዋነኛዋ ቁልፍ የጥቁር ባህር ፈርጥ የሆነችውን ኦዴሳን መቆጣጠር ግዴታ ነው፡፡ ዩክሬኖቹ ኦዴሳን አሳልፈን አንሰጥም ብለዋል፡፡ በፑቲን ህልምና በዩክሬይኖች መካከል ስለሚደረገው የኦዴሳ ጦርነት ይህን አስደናቂ ቪዲዮ ይከታተሉ!!!

https://youtu.be/sW0rM_nr8Uo
ከሰሞኑን በአሶሳ ከተማ ውስጥ በግለሰቦች ቤት በተደረገ ፍተሻ የተከማቸ 50 በርሜል ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የአሶሳ ከተማ ፖሊስ ለኢዜአ በሰጠው ቃል ፤ በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸው 50 በርሜል ነዳጅ (ቤንዚን እና ናፍጣ) ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር በህብረተሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድቷል።

በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በከተማው #ቤንዚን እና #ናፍጣ በጥቁር ገበያ በሊትር እስከ 200 ብር እየተሸጠ መሆኑን ፖሊስ የጠቆመ ሲሆን የዚህ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ምንጭ በህጋዊ መንገድ ከነዳጅ ማደያዎች ተቀድቶ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ጥቂት ግለሰቦች እጅ መግባት መሆኑን አስረድቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ አዲስ አበባ ውስጥ ከቤታቸው እንደወጡ አለመመለሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ለቢቢሲ ገለፁ።

ወ/ሮ መነን ስለ ባለቤታቸው ሲናገሩ ትናንት ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው 5፡15 አካባቢ የወጡት ከጓደኛቸው ጋር ቀጠሮ እንደነበራቸው ገልፀው መሆኑን ያስረዳሉ።
ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤታቸው ባለመመለሳቸው ደጋግመው ወደ ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ቢደውሉም ምላሽ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
ከኤርትራ ጋር የጋራ ጥቅሞቻችንን መሰረት በማድረግ በትብብር እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታወቁ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮች ጋር መልካም የሚባል ግንኙነት አላት።

ከኤርትራ ጋር የጋራ ጥቅምን መሰረት በማድረግ በትብብር እየተሰራ እንደሆነ ገልጸው፤ ግንኙነቱን ወደ ጠንካራ የኢኮኖሚ ትብብር ለማሸጋገር የተለያዩ ተግባራት በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

“የድንበር አካባቢ ንግድና የሰዎች ዝውውሮችን የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ የወደብ አጠቃቀም፣ የንግድ ልውውጥ፣ የጉምሩክ፣ የኢሚግሬሽንና የመሳሰሉ የሁለቱን አገሮች ህዝቦች ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ የትብብር ማዕቀፎችን ለማበጀት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን” ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ለቤትዎ ለቢሮዎ እንዲሁም ለድርጅትዎ ይተለያየ ውበት ያላቸውን የፍይበር ግላስ የአበባ መትከያ ከፈለጉ እኛ አለን የድርጅትዎን እርማም መትከያው ላይ እናትምሎታለን
👋👋እንዲሁም ይሄን አዋጭ ቢዝነስ
ለመጀመር ካሰቡ ሙሉ ስልጠና እንሰጣለን ይደውሉልን
https://tttttt.me/+xvCuMwxhK19kODg0
☝️☝️☝️Join our group
Phone number:0987414243
0913676664
ከየመን 146 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ!

ከየመን ወደ ኢትዮጵያ በተደረገ የአንድ ጊዜ በረራ 146 ዜጎችን ወደ ትውልድ አገራቸው መመለስ መቻሉ ተገለጸ።

ከኢፌዴሪ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነዉ መረጃ እንዳመለከተዉ ከተመለሡት መካከል 126 ወንዶች እንዲሁም 15 ሴቶች ሲሆኑ 5ቱ ህጻናት ናቸዉ።

@YeneTube @FikerAssefa
ኤርትራ ከህወሓት ጥቃት እራሷን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች!

የኤርትራ መንግሥት በማስታወቂያ ሚኒስቴሩ በኩል ዛሬ ግንቦት 09/2104 ዓ.ም. ባሰፈረው መልዕክት ህወሓት በኤርትራ ድንበር በኩል እና በምዕራብ ትግራይ አቅጣጫ በሁለት ግንባሮች ጦርነት ለመክፈት እየተዘጋጀ ነው ብሏል።ጨምሮም በዚህ በህወሓት ሊሰነዘር ይችላል ላለው ጥቃት የመጀመሪያው ዒላማ "ኤርትራ እና የኤርትራ ሕዝብ ናቸው" ሲል አቋሙን አንጸባርቋል።

ከወራት በፊት ከተደረገው ከባድ ውጊያ በኋላ ጋብ ብሎ የቆየው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዳግም ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት እየጨመረ በመጣበት ጊዜ ነው የኤርትራ መንግሥት ይህንን ያለው።ከቀናት በፊት የአማራ ክልል ከህወሓት በኩል ሊሰነዘር ይችላል ላለው ሌላ ዙር ወረራ የክልሉ የፀጥታ መዋቅር ዝግጁ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ኃይሎች እና በፌደራል መንግሥት ኃይሎች መካከል ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም አልፎ አልፎም ግጭቶች ሪፖርት መደረጋቸው እንዳሳሰበው ገልጾ ነበር።እያየለ ከመጣው የዳግም ጦርነት ስጋት በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ለጥቂት ሰዓታት የቆየ ጥቃት ሰንዝረው የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ እንደነበረ ቢቢሲ መዘገቡ ይታወሳል።

ዛሬ በኤርትራ መንግሥት ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሑፍ ላይ ግን ሚያዚያ 30/2014 ዓ.ም. ራማ እና ባድመ አካባቢ ከህወሓት ኃይሎች ጋር ግጭት አጋጥሞ ነበር ስለመባሉ ያለው ነገር የለም።የኤርትራ መንግሥት ባስተላለፈው መልዕክት በዓለም አቀፍ ሕግ የኤርትራ ሉዓላዊ ግዛት እንደሆነ ያረጋገጠወን አካባቢ ህወሓት ዳግም ለመውረር በዝግጅት ይገኛል ሲል ከሷል።

ከዚህ በተጨማሪም፤ ህወሓት ሊከፍት ነው ላለው አዲስ ጥቃት በምዕራብ ወልቃይት፣ ጸገዴ እና ሑመራን መልሶ በመቆጣጠር ከሱዳን ጋር የሚያዋስነውን ድንበር ለመክፈት አቅዷል ብሏል።በመጨረሻም ከህወሓት ሊሰነዘር የሚችልን ጥቃት የኤርትራ ሕዝብ እና መንግሥት እራሱን መከላከል ይችላል በማለት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።ለዚህ ከኤርትራ መንግሥት በኩል በይፋ ለቀረበው ወረራ ለመፈጸም የመዘጋጀት ክስ ከህወሓት በኩል አስካሁን የተባለ ነገር የለም ሲል ቢቢሲ ዘግቦታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ባሳለፍነው ሀምሌ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሳኔ ከአለም አቀፍ አጋሮች ጋር የቀጥታ ትስስር ላለው የመድን ዘርፍ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን ባለሞያዎች ተናገሩ፡፡

በዋልያ ስቲል ኢንሰደስትሪ እና በኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራን መካከል በነበረው የካሳ ክርክር የሰበር ሰሚ ችሎት በመጨረሻ ይግባኝ የሰጠው ውሳኔ የአገሪቱን የመድን ህግ እና በሁለቱ ወገኖች መካከል የነበረውን የኢንሹራንስ ፖሊሲ ከግምት ያላስገባ እና መሰል ጉዳዬች ስጋት ውስጥ እንዲገቡ የሚያደርግ ነው ሲል መድን ሰጪው ቅሬታውን አስታውቋል፡፡ውሳኔው ባሳለፍነው አመት መጨረሻ መሰጠቱን ተከትሎ ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራን ውሳኔው እንዲገመገም እና ሌሎች መድን ሰጪ ድርጅቶች የራሳቸውን አካሄድ እንዲያስተካክሉ በማሰብ ለትንተና ለመድን ሰጪዎች ማህበር ጠቅላላ ውሳኔውን እና ሂደቱን የሚያሳይ ሰነድ መስጠቱን ገልጿል፡፡

በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የመድን ሰጪ ኩባንያዎች የህግ መሪዎች ሰነዱን በጥልቀት መርምረው ውሳኔው እጅግ የተዛባ እና መሰረታዊ የሚባሉ የአገሪቱ ህጎችን እና የኢንሹራንስ ውሉን ያላገናዘበ ነው ሲሉ ጥልቅ ትንታኔ በመስጠት ጉዳዩ ለዘርፉ ስጋት የደቀነ እና አጋር አለም አቀፍ ተቋማት ከአገሪቱ መድን ሰጪዎች ጋር እንዴት መስራት እንደሚችሉ ጥያቄ የሚያስነሳ የሆነ ነው ሲሉ ባሎመያዎች ተናግረዋል፡፡የመድን ሰጪዎች ያቀረቡት ጥልቅ ትንታኔ ለብሄራዊ ባንክ፣ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት እንዲሁም ሌሎች የመንግስት አካላት መቅረቡ ታውቋል፡፡

በውሳኔው መሰረት ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራን ተጨማሪ ወጪዎችን ጨምሮ 115 ሚሊየን ብር እንዲከፍል የተፈረደ ሲሆን ክፍያውም በዚህ ወር ተፈጽሞ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡ቀደም ሲል የብረት ፋብሪካው ወደ 75 ሚሊየን ብር ግድም የሚያወጣ የብረት ጥሬ እቃ ከግብፅ ለማስገባት ከመድን ሰጪው የማሪን መድን ሽፋን ቢገዛም ጭነቱ በወቅቱ ወደ ኢትዮጵያ ከመግባት ይልቅ እቃውን የያዘችው መርከብ በመሰወሩዋ ፋብሪካው ለካሳ መድን ሰጪውን ይጠይቃል፡፡

ሆኖም መርከቧ በሂደት ፓኪስታን ወደብ እንደምትገኝ ጭነቱንም በዛው አገር የመርከቡ ሰራተኞች ከካፒቴናቸው ጋር በመመሳጠር ለመሸጥ ሲሞክሩ መታወቁን ተከትሎ በህግ ሂደት የፖኪስታን ፍርድ ቤት እቃው ሳይሸጥ እንዲታገድ ያደረገ ቢሆንም ዋልያ ካሳ ይከፈለኝ ሲል ጉዳዩን ለፌደራል ፍርድ ቤት አቅርቦ ተፈርዶለታል፡፡ሆኖም እቃው አልጠፋብ/አልተበላሸም፣ ውላችንም ለጠፋ እቃ ብቻ ነው ካሳ የሚያስከፍለው፣ የተጫነበት መርከብ ከውላችን ውጭ ከ 25 አመት በላይ እድሜ ያላት እና በሚታወቁ 9 አለም አቀፍ ማህበራት ውስጥ አባል ያልሆነች ነች በመሆኑም ካሳ መክፈል የለብንም ሲል መድን ሰጪው ተከራክሮ ነበር፡፡

በተጨማሪም ለረጅም ጊዜ ያገለገለው የኢትዮጵያ መድን ህግ ምንም እንኳን የብሪታንያን የማሪን መድን ህግ ከሞላ ጎደል የተቀበለ ቢሆንም ልዩነቶች አሉት ሲል ተከራክሮ ነበር፡፡ለዚህም ማጠናከሪያ ያቀረበው የመድን ህጉ አንቀፅ 303 የማሪን መድን የሚሰጣቸውን የዋስትና አይነቶች ዘርዝሮ ከብሪታንያው ህግ በተለየ መልኩ በሰዎች ጣልቃ ገብነት ሆን ብሎ ለሚፈፀም ጥፋት ዋስትና/ሽፋን እንደማይኖረው ይደነግጋል ሲል ጠቅሷል፡፡ከመጀመሪያው ፍርድ ቤት ውሳኔ በኋላም ጉዳዩን ወደ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቤት ብሎበት ለሱ ተፈርዶ ነበር፡፡
ሆኖም ከሳሽ (ዋልያ ስቲል) ጉዳዩን በድጋሚ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ ማቅረቡን ተከትሎ ሰበር ሰሚውም ለሱ ወስኖለታል፡፡

ሆኖም የመድን ሰጪ ያሰባሰባቸው የሁሉም ኢንሹራንስ ኩባንያዎች የህግ ባለሞያዎች የውሳኔ ሰነዱን ከተመለከተ በኋላ ሰበር ሰሚው የብሪታንያን ህግ መሰረት ማድረጉን ሆኖም ኢትዮጵያ አብዛኛው ህግ ከዛ ብትቀበልም ህጉ የኢትዮጵያ መሆኑን፤ በተጨማሪ በሰው ሆን ተብሎ ለጠፋ ንብረት ዋስትና እንደሚኖር ህጉ እንደማይደነግግ በተጨማሪም እቃው አለመጥፋቱን ተችቶ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa